Professional Documents
Culture Documents
የሂሳብ መዝገብ አያያዝ
የሂሳብ መዝገብ አያያዝ
2) Methods of accounting :
1. Scientific system
ምሳሌ
የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች 5000
ጥሬ ገንዘብ (ሳጥን/ባንክ ዩኒ) 5000
2. ጥሬ ገንዘብን መሰረት ያላደረገ /accrual base/
•ጥሬ ገንዘብ ስራ ላይ ባይውልም ( ክፍያ ባይፈፀም እና ገቢ ባይሰበሰብም) ስራዎች
ምሳሌ
አቶ አወል ከX ድርጅት የ10000 ብር የቢሮ
መገልገያ ዕቃዎች ገዙና 5000 ብር ከፍለው ቀሪውን
በ2 ወር ውስጥ ሊከፍሉ ተስማሙ ፡፡የአቶ አወል
መ/ቤት ሂሳባቸውን የሚይዙት ጥሬ ገንዘብን
መሰረት ያላደረገ ሲሆን ምዝገባቸውን አስቀምጡ?
Conti……
•ጥሬ ገንዘብን መሠረት ያደረገ የተሻሻለ የሂሣብ አያያዝ በአብዛኛው በጥሬ ገንዘብ ላይ የተመሠረተ
ሲሆን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ጥሬ ገንዘብ ነክ ያልሆኑ የተወሰኑ የሂሣብ እቅስቃሴዎችን ዕውቅና
መስጠትን ያካትታል፣
LIABILITIE
ASSETS & S,
REVENUE
EXPENSES S&
capital
• የሰራተኛ ብድር/አበበ/................2000.00
ባንክ ያለ ገንዘብ ………….......................2000.00
• የሰራተኛ ብድር/ትዕግስት/.................2000.00
ባንክ ያለ ገንዘብ……...............................2000.00
• የሰራተኛ ብድር/አለሙ/.................2000.00
ባንክ ያለ ገንዘብ………...........................2000.00
• ታህሳስ 12 አ/አ ለስራ የሄዱት ሰራተኞች ስራቸውን አጠናቀው ሲመለሱ አበላቸው
ሲወራረድ አቶ አበበ ከወሰደው አበል ተጨማሪ ብር 200.00፣ አቶ አለሙ ከወሰደው
ተመላሽ ብር 120.00 እና ወ/ሮ ትዕግስት ቀደው ብሰዱት ልክ አወራረዱ በዚሁ
መሰረት የሂሳብ ምዝገባው በሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ፣በጥሬ ገንዘብ መክፈያ እና ገንዘብ
መቀበያ ደረሰኝ እንደሚከተለው የሚመዘገብ ይሆናል፡-JV-
107,108,&109,PCPV-0003 &CRV-1002
• አቶ አበበ
የጥቃቅን ወጭ ማስመስከሪያ
–ውሎ አበል ወጭ/…...........2200.00
ሰራተኛ ብድር/አበበ)……...................2000.00
ጥቃቅን ክፍያዋች ገንዘብ……..…...............200.00
አቶ አለሙ
በሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ
ውሎ አበል ወጭ ………......................1880.00
ካዘና ያለ ገንንዘብ/አበልተመላሽ/...............120
ሰራተኛ ብድር/አለሙ/.................................2000.00
ወ/ሮ ትግስት
ሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ
ውሎ አበል ወጭ..........2000.00
ሰራተኛ ብድር/ትዕግስት/.................2000.00
• ታህስስ13 የXY ከተማ ውሃ አገ/ጽቤት የህዳር ወር 2015 ዓ.ም የውሃ ማምረቻ
ፓምፖች የመብራት ፍጆታ ብር 7000.00 እንዲከፍል ቢጠየቅ ጥሬ ገንዘቡ ከባንክ
ሲወጣ አመዘጋገቡ በቸክ መክፈያ ሰነድ እንደሚከተለው ይመዘገባል፡-CPV-55
• ቅድሚያ ክፍያ/ ...............7000.00
ባንክ ያለ ገንዘብ……..................7000.00
• ታህሳስ 14-ክፍያው ተከናውኖ ክፍያ የተፈጸመበት ሰነድ ሲቀርብ በሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ
በሚከተለው መልኩ ይመዘገባል፡-JV-110
• የመብራት ወጪ..............7000.00
ቅድሚያ ክፍያ....................7000.00
የጥቃቅን ክፍያዋች የመጀመሪያ ምስረታ ምዝገባ
/establishment of petty cash fund/
• የመብራት ወጭ..................1500.00
የግዥ ጥቃቅን ክፍያ ገንዘብ……….........1500.00
• የስልክ ወጭ …..................1500.00
• የፖስታ ወጭ …………...........200.00
የግዥ ጥቃቅን ክፍያ ገንዘብ..................1700.00
• ታህሳስ 17-ለመ/ቤቱ የሚያገለግሉ የተለያዩ መገጣጠሚያዋች እንዲገዙ ለግዥ
ሰራተኛው ብር 60000.00 ወጪ ተደርጎ ሲሰጠው የሂሳብ ምዝገባው በባንክ ወጪ
ማስመስከሪያ የሚከናወን ይሆናል ፡-CPV-57
• የግዥ ቅድሚያ ክፍያ ...........60000.00
ባንክ ያለ ገንዘብ …...................60000.00
• ታህሳስ 18-ከላይ እንዲገዛ ከታዘዛቸው መገጣጠሚያወች ውስጥ የ 50000.00
ገዝቶ ገቢ ቢያደርግ እና የተረፈውን ሲመልስ የሂሳብ ምዝገባው በሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ
እንደሚከተለው ይመዘገባል ፡-JV-111
• መገጣጠሚያ ............50000.00
• ባንክ…………............10000.00
ግዥ ቅድሚያ ክፍያ ..............60000.00
• አቶ አወል የዱቤ ውሃ መስመር ሲያዘረጉ ከእቃ ሽያጪ 850.00 ከቴ/አገልግሎት
780.00 ከእ/አገልግሎት 255.00 ከተቀማጪ 200.00 ውል ካርድ
20.00 ግምት እና ፈቃድ 40.00 ማስቆፈሪያ 240.00 በዱቤ ለመክፈል ግዴታ
ሲገቡ የሂሳብ ምዝገባ በሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ ይመዘገባል ፡-JV-112
• ዱቤ ተሰብሳቢ/አወል/........2385.0
• ግምትና ፈቃድ……………..……..........40.00
• እቃ ሽያጪ....................................850.00
• ከቴ/አገልግሎት...............................780.00
• ከእ/አገልግሎት................................255.0
• ተቀማጭ……...................................200.00
• ውል ካርድ. ………………….……….......20.00
• ማስቆፈሪያ.......................................240.00
• ዱቤ የወሰዱት አቶ አወል 500.00 ብር ገቢ ሲያደርጉ የሂሳብ ምዝገባው
በጥሬ ገንዘብ መቀበያ ይመዘገባል ፡-CRV-1003
• ካዘና ................500.00
• ዱቤ ተሰብሳቢ……..............500.00
• የተጠራቀመ እርጅና.........................5999.25
• እቃውን በማስወገድ የመጣ ኪሳራ .........2000.75
ጠረጴዛ ……...........................................8000.00
• ዋጋው 8000.00 የሆነ ጠረጴዛ እርጅና ተቀናንሶለት ብር 2000.75 ቀሪ ዋጋ ቢኖረው እና
1500.75 በመሸጥ እንዲወገድ ቢደረግ አመዘጋገቡ እንደሚከተለው ይሆናለ ፡-JV-117
• የተጠራቀመ እርጅና/.......................5999.25
• እቃውን በማስወገድ የመጣ ኪሳራ ........500.00
ባንክ ……………………………..……1500.75
ጠረጴዛ ……………….........................................8000.00
• ዋጋው 8000.00 የሆነ ጠረጴዛ እርጅና ተቀናንሶለት ብር 2000.75 ቀሪ ዋጋ ቢኖረው እና
2500.75 በመሸጥ እንዲወገድ ቢደረግ አመዘጋገቡ እንደሚከተለው ይሆናለ ፡-JV-118
• የተጠራቀመ እርጅና.........................5999.25
• ጥሬ ገንዘብ /bank.........................2500.75
እቃውን በማስወገድ የመጣ ትርፍ........................500.00
ጠረጴዛ ……...............................................8000.00
• የተጠራቀመ እርጅና...........................5999.25
• ጥሬ ገንዘብ /bank.........................2000.75
ጠረጴዛ ..................................................8000.00
23 ታህሳስ መ/ቤቱ ቢሮ ለማስገንባት ሻትን ጨምሮ 115000.00 ዉል ቢዋዋልና ቅድሚያ ክፍያ
30 ፐርሰንት ተከፍሎት ግንባታ ሲጀምር ምዝገባዉ እንደሚከተለዉ በባንክ ወጪ ማስመስከሪያ
ይመዘገባል ፡-
ቅድመ ግንባታ ክፍያ / ………………. 345000.00
ባንክ / …………………..……………………. 345000.00
ታህሳስ በባለሙያ ሥራዉ ተረጋግጦ የመጀመሪያ ዙር 40 ፐርሰንት ክፍያ ሲፈጸም በባንክ ወጪ
ማስመስከሪያ ምዝገባዉ ይከናወናል ፡-
ኮንስትራክሸን ኢን ፕሮግረስ.…………….. 460000.00
40ፐርሰንት ቅድመ ግንባታ ክፍያ ……………..… 138000.00
5ፕርሰንት ሪቴንሽን …………………………..….. 23000.00
2ፐርሰንት ቅድመ ግብር …………………………. 8000.00
ባንክ ………………………………………………. 291000.00
ታህሳስ በባለሙያ ሥራዉ ተረጋግጦ የሁተኛ ዙር 40 ፐርሰንት ክፍያ ሲፈጸም በባንክ ወጪ ማስመስከሪያ ምዝገባዉ
ይከናወናል ፡-
ኮንስትራክሸን ኢን ፕሮግረስ /…………….. 460000.00
40ፐርሰንት ቅድመ ግንባታ ክፍያ ……………..… 138000.00
5ፕርሰንት ሪቴንሽን/ …………………………..….. 23000.00
2ፐርሰንት ቅድመ ግብር/ …………………………. 8000.00
ባንክ ………………………………………………. 291000.00
ታህሳስ በባለሙያ ሥራዉ ተረጋግጦ ሦስተኛው ዙር 20 ፐርሰንት ክፍያ ሲፈጸም በባንክ ወጪ
ማስመስከሪያ ምዝገባዉ ይከናወናል ፡-
ኮንስትራክሸን ኢን ፕሮግረስ …………….. 230000.00
20ፐርሰንት ቅድመ ግንባታ ክፍያ ……….……………… 69000.00
5ፕርሰንት ሪቴንሽን …………………………..……….. 11500.00
2ፐርሰንት ቅድመ ግብር ……………….…………………. 4000.00
ባንክ ………………………………………..…………… 145500.00
ታህሳስ የግንባታ ርክክብ ተፈጽሞ ምንም ችግር እንደሌለበት በባለሙያ ሲረጋገጥ እና 2.5ፕርሰንት እንዲለቀቅለት
ጠይቆ ሲፈቀድ እን ክፎያ ሲፈጸም በባንክ ወጪ ማስመስከሪያ ምዝገባዉ እንደሚከተለዉ ይመዘገባል ፡-
ታህሳስ ዉሃ አግልግሎቱ ከከተማ አስተዳደር ለማስፋፊያ የሚሆን ገንዘብ 1500000.00 በርዳታ ሲሰጠዉ የሂሳብ ምዝገባ
ማዘዣዉ እንደሚከተለዉ ይከናወናል
ባንክ ……………….. 1500000.00
እርዳታ በጥሬ ገንዘብ ………………………. 1500000.00
• እዳ ፡- ማለት በሁለት ቦታ ተከፍሎ ሊታይ ይችላል ፡፡ ይህም ወቅታዊ
/የአጭር ጊዜ እዳና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ እዳ ተብሎ በጊዜ ማዕቀፍ ሊከፈል
ይችላል ።
• ካፒታል ፡- ማለት የአመቱ ካፒታል/capital/ መጠን እና ከተጣራ
ወደ ካፒታል የዞረ የተጣራ ትርፍ/retained earinings/
ድምር ነው ።
• ገቢ ፡- ገቢን ስለመመዝገብ ፡- የከተማ መጠጥ ውሃና ፍሣሽ አገልግሎት
ገቢን እንደገቢ ለመመዝገብ ሁለት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት አለባቸው፡፡
– ሀ) አገልግሎት ለደንበኛ የተሰጠ መሆን ይኖርበታል::
– ለ) በተሰጠው የአገልግሎት መጠን ገንዘብ ገቢ መደረግ ይኖርበታሌ፡፡
– የከተማ መጠጥ ውሃና ፍሣሽ አገልግልት አክሩዋል የሂሣብ አያያዝ
ሥርአትን የሚከተሉ በመሆኑ ገቢ የሚመዘገበው ገቢው እንደተገኘ ወይም
ገንዘቡ ገቢ ባይደረግም አገልግሎቱ እንደተሰጠ ይሆናል ፡፡
በአክሩዋሌ አሠራር ወጪን ስለመመዝገብ
•በአክሩዋል የሂሣብ አያያዝ ሥርአት መሠረት ወጭ የሚመዘገበው ወጪ እንደተደረገ
እንጂ የግድ ወጪው በጥሬ ገንዘብ ሲወጣ ብቻ መሆን የለበትም ፡፡ በመሠረታዊ የሂሳብ
አያያዝ መርሆዎች መሠረት ገቢና ወጪን የማዛመድ መርህ ለመጠበቅ እንዲቻል አክሩ
ያደረገው ወጪ ምዝገባ በተመሳሳይ ወቅት አክሩ ካደረገው ገቢ ምዝገባ ጋር በተዘመደ መልኩ
ይሆናል፡፡ ይህም ማለት የማዛመድ መርሁ የሚገለጸው ከተመዘገበው ወጪ ጋር ተያይዞ
በተመሳሳይ ወቅት የተገኘውን ገቢ መመዝገብ ማለት ነው ።
የበጀት ሥርአት ፡-
•በጀት የፋይናንስን ሥራ ለማከናወን የሚያስችል ለተወሰነ ጊዜ የሚሠራ
አጠቃላይ የማኔጅመንት ዕቅድ ሲሆን የወጪ ግምትና የፋይናንስ ወጪ
አደራረግ ሥራዓትን ያካትታል፡፡ ይህ ማንዋል የከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ
አገሌግልት በጀትን በአመት አንድ ጊዜ እንደሚዘጋጅ ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
ሆኖም የከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገሌግልት አስፈሊጊ ሆኖ ሲያገኝ
አመታዊ በጀቱን በሩብ አመት እና በወርሀዊ ዕቅድ ሊተነተን ይችላል፡፡
ወቅታዊ ሪፖርት ሲቀርብ ወርሀዊ ወይም የሩብ አመት ዕቅድ ከተመሳሳይ
ወቅት አፈፃፀም ጋር በማነፃፀር ልዩነቱ በተገቢው አምድ ይቀመጣል፡፡ በጀቱ
በከተማ ውሃ ቦርድና ማኔጅመንት ከታመነበት በማንኛውም ጊዜ ሊከለስ
ይችላል፡፡
የበጀት ዝግጅት በዋናነት የዕቅድና ቁጥጥር መሣሪያ ነው፡፡ በጥንቃቄ
የተዘጋጀ በጀት የውሀ ማምረትን፣ የውሀ ሥርጭትን፣ ሽያጭንና ሌሎች
አስተዳደራዊ ሥራዎችን አቀናጅቶ ለመምራት ያገለግላል፡፡ የበጀት ዋና
ዋና አላማዎች፡-
በከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ለታቀደለት ሥራዎች
ተገቢውን ገንዘብ ለማቅረብ፣
የከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የሚሠራቸውን ሥራዎች
በማቀናጀት ውጤታማ የሀብት አጠቃቀም እንዲኖር ለማስቻል፣
ከዕቅድ ውጪ እንዳይሆን መቆጣጠር የሚስችል ኃላፊነትን
የሚወስንና የእርምት እርምጃ እንዱወሰድ ለማኔጅመንት ተገቢውን
መረጃ ለመሥጠት፡፡
የበጀት አይነቶች
•የከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ሁለት የበጀት አይነቶች ሲኖሩት እነርሱም፡-
1. መደበኛ በጀት (The Recurrent Budget)
•ይህ አይነቱ በጀት በአብዛኛው ለአንድ አመት ጊዜ የከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት መደበኛ
ሥራዎችን ለማከናወን እንዲያስችል የሚዘጋጅ ነው፡፡ ይህ በጀት ለደመወዝ፣ለቢሮ ውስጥ መገልገያ
ዕቃዎች ፣ ለውሀ ማጣሪያ ኬሚካሎች፣ ለውሀ ቆጣሪ መግዣ፣ ለቧንቧ እና መገጣጠሚያዎች ግዥ፣ ለጥገና
እና እድሳት ሥራዎች፣ ወዘተ ወጪ መሸፈኛ የሚያገለግል ነው፡፡
2.ካፒታል በጀት
•የከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ለረጅም ጊዜ የታቀደ የካፒታል ማሳደጊያ መርሀ ግብርን ተከትሎ
የሚዘጋጅ በጀት ሲሆን የገንዘብ ምንጩንም መሠረት የሚያደርገው ለረጅም ጊዜ የካፒታል ፍላጎት
ለማሟላት ለኦፕሬሽን ገቢ፣ እርዳታ እና ሌሎች የካፒታል ማሻሻያ ፈንዶች ነው፡፡ በሌላ አገላለፅ ይህ
በጀት ለካፒታል እቃዎች ግዥ የሚውል ሲሆን የሚገዙት የካፒታል ዕቃዎችም ለከተማ መጠጥ ውሃና
ፍሳሽ አገልግሎት ለበርካታ አመታት የሚያገለግሉ መሆናቸውን በማመነን ነው፡፡ የካፒታል በጀት ለቢሮ
ግንባታ፣ ለተሽከርካሪዎችና ሞተር ሳይክልች ግዢ፣ ጀነሬተሮች፣ የውሀ ሥርጭት ሥርአት ማሻሻያዎችና
መስፋፊያዎች፣ ለመሣሪዎች ማሻሻያ ወይም ግዢ፣' ለቢሮ መገልገያ መሣሪያዎች ወዘተ ግዢ የሚውል
ነው፡፡
ታህሳስ የሰራተኞች ደመወዝ ለመክፈል ፔሮል በሚዘጋጅበት ወቅት ክፍያው እና
ክፍያው በባንክ ሲከፈል ምዝገባው በሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ እንደሚከተለው
ይመዘገባል ;-JV-120
•ቋሚ ሰራተኛ ደመወዝ ……........73817.00
•ኩንትራት ሰራተኛ ደመወዝ …..…...500.00
•ትርፍ ሰዐት ክፍያ …………........3580.88
•የወንበር አበል ………….............420.00
•የካዘና መጠባበቂያ ………........... 80.00
•11% ጡረታ …………… ........8119.87
የተጠራቀመ ደመወዝ …………............55731.83
ስራ ግብር/....................................13218.93
18% ጡረታ…………………..............13287.06
አልማ ...........................................90.00
ደመወዝ ብድር …………...................4189.93
• የስራ ግብር ብር 25368.93 ፣18% ጡረታ ብር 26847.06 እና
ለአልማ ብር 90 ለሚመለከታቸው አካላት ክፍያ ቢፈጸም እና ክፍው ከባንክ
በዝውውር የተፈጸመ ቢሆን ምዝገባው በሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ ይመዘገባል :-
JV-121
ስራ ግብር.............25368.93
18% ጡረታ ........26847.06
አልማ/......................90.00
ባንክ....................52305.99
የሂሳብ ማስተካከያ ማድረግ (Adjustments)
•የከተማ ውሃ አቅርቦት አገልግሎት የሂሳብ ሠራተኞች የውስጥ
ትራንዛክሽኖችን ለመመዝገብ ሪፖርት ማድረጊያ የመጨረሻዎቹ
ወቅቶች ላይ የሂሳብ ማስተካከያዎች ዘዴዎችን መጠቀም
አለባቸው፡፡ ማስተካከያ የሚደረግባቸው የሂሳብ መደቦች
አገልግሎት ሰጥተው ወደ ወጭ ያልተቀየሩ ዋጋዋችን
(unexpired cost)ገንዘብ ቢሰበሰብም አገልግሎት
ባለመሰጠቱ እንደ እዳ ተመዝግበው ያሉ (Unearned
Income) ሂሳቦች እና የተጠራቀሙ ሂሳቦች
(Accruals) ናቸው፡፡
ቅድሚያ የተሰበሰበ ገቢ
•ያልተመዘገበ ገቢ ወይም ወደፊት የተሸጋገረ ገቢ
(unearned or Differed Revenue) ማለት
አገልግሎቱ ሳይሰጥ ገንዘብን መቀበል ማለት ነው፡፡ በሌላ አባባል
አገልግሎት ወይም የዕቃ አቅርቦት ለወደፊት
ለማቅረብ/ለመስጠት ግዴታ ውስጥ በመግባት የተቀመጠውን
ክፍያ አስቀድሞ መቀበል ማለት ነው፡፡
• ታህሳስ 30,በጥቅም ላይ የዋለ ኬሎሪን ብር 5000.00፣ አላቂ
እቃዋች ብር 8000.000 እና ህትመት ደግሞ 1000.00
ማስተካከያ ሲደረግ የሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ እንደሚከተለው
ይመዘገባል ፡-JV-122
• ክሎሪን ወጭ .......................5000.00
• አላቂ እቃ ..........................8000.00
• ህትመት ............................1000.00
• ክሎሪን ወጭ ……….........5000.00
• አላቂ እቃ......................8000.00
• ህትመት ……......................1000.00
• ታህሳስ ቅድሚያ ከተከፈሉ ክፍያዋች ውስጥ ለመኪና ኢንሹራንስ ብር
450.00 ለሞተር ኢንሹራንስ ብር 183.33 እና ለቢሮ ኪራይ
ብር 2000.00 አገልግሎት ስለሰጡ የማስተካከያ ሂሳብ ምዝገባ
እንደሚከተለው ይሆናል ፡-JV-123
• ለኢንሹራንስ ወጭ .......633.33
• ኪራይ ................2000.00
– የመኪና ኢንሹራንስ ቅድሚያ ክፍያ............450.00
– የሞተር ኢንሹራንስ ቅድሚያ ክፍያ ...........183.33
– ለቢሮ ኪራይ ………..............................2000.00
• ታህሳስ 30-ለቢል ሽያጭ ሰራተኛ ከመኖሪያ ቤት 40000.00 መኖሪያ ቤት ካልሆኑ
35000.00 ቆጣሪ ኪራይ 10000.00 የያዘ ቢል ለሽያጭ ሲተላለፍ የሂሳብ ምዝገባው
እንደሚከተለው ይሆናል ፡-JV-124
• ቢል ተሰብሳቢ ..........85000.00
– መኖሪያቤት.............................40000.00
– መኖሪያ ቤት ያልሆኑ...................35000.00
– ቆጣሪ ኪራይ…….......................10000.00
• ታህሳስ መ/ቤቱ አብቁተ ከተቀመጠ የቁጠባ ሂሳብ 2587.93 ወለድ ገቢ ሲያገኝ
የሂሳብ ምዝገባው እንደሚከተለው ይሆናል ፡-
ባንክ……………2587.93
ወለድ…..………………..2587.93
• የቁጥጥር ስርዐት
– የጥሬ ገንዘብ ቁጥጥር
– አዘጋጁን ፣ ተቀባዩን/ከፋይን/ እና ሂሳቡን የሚመዘግበውን
የተለያዩ ማድረግ
– ጥሬ ገንዘብ ቆጠራ ማካሄድ
– ባነከ ማስታረቂያ/bank reconcilation/ መስራት
• የንብረት ቁጥጥር
– በተጠቃሚዋች ያለ ቋሚ ንብረት መቆጣጠሪያ ካርደ ላይ
መመዝገብ ፣ኢንቨተሪዋችን በቢን ካርድ እና በስቶክ ካርድ
በማቀናነስ የንብረት ቆጠራ ማካሄድ ፡
የባንክ ሂሳብ ማስታረቂያ ዝጅት እና መነሻ ሰነዶች
• የባንክ ሂሳብ ማስታረቂያ ለማዘጋጀት መነሻ ሠነዶች
የሚሆኑት ከዚህ በታች የተመለከቱት ናቸው፡፡
ከባንክ የተቀበልነው የባንክ ሂሳብ መግለጫ፣
የሂሳብ እንቅስቃሴ መዝገብ/አጠቃላይ የሂሳብ ሌጀር
ካርድ፣
ከባንክ ሂሳብ መግለጫ ጋር አባሪ ተደርገው በሚደርሱት
ሠነዶች በጉርድ ቼክ ውስጥ ያለው ዝርዝር መረጃ፣
የባንክ ሂሰብ ማስታረቂያ በሚዘጋጅበት ወቅት የሚከናወኑ ቅደም ተከተሎች
- የባንክ ሂሳብ መግለጫ/Bank statement ከባንክ በምናገኝበት ወቅት
በባለፈው ወር ማስታረቂያ ወቅት ያልተመዘገቡ ሂሳቦች መመዝገባቸውን
ማጣራት፣
– የባንክ ሂሳብ መግለጫ ላይ የተመዘገበው መለያ ቁጥር በሂሳብ እንቅስቃሴ
መዝገብ ከተመዘገበው ጋር በመናበብ ስህተቶችና ከባንክ ገንዘብ ወጪ
ያልተደረገባቸው ቼኮች ካሉ መለየት፣
– የባንክ ሂሳብ መግለጫ ላይ ገቢ የተደረጉ ሂሳቦች በሂሳብ እንቅስቃሴ መዝገብ
ከተመዘገበው ጋር ልዩነት አለመኖሩን ማጣራት፣
– በባንክ የሂሳብ መግለጫም ሆነ በሂሳብ መዝገብ /ሌጀር ላይ ተመዝግበው
በሌላኛው ያልተመዘገቡ ሂሳቦችን መለየት፣
– የባንክ ማስታረቂያ ማዘጋጀት፣
የባንክ ሂሳብ ማስታረቂያ ቅፅ የሚከተለውን ይመስላል ፡-
የXY ከተማ ውሃ አገ/ጽቤት
Bank Recouncilation
For the month of ……/2015
የባንክ ከወጪ ቀሪ በባንክ መግለጫ መሰረት ………………………………………xxxx
ሲደመር ፡-ባንክ ገቢ ሁኖ በባንክ መግለጫ ያልታ………….xxxx
- ባንክ ስህተት…………………….……………xxxx
የባነከ ስህተት …………………………………………....... xxxx
ድምር………………………………………………………..xxxx
ሲቀነስ ፡-ባንክ ያልደረሱ ቸኮች
-ቸክ ቁጥር ……………………….xxxx
-ቸክ ቁጥር ………………………xxxxx
- ባንክ ስህተት…………………….……………xxxx
ድምር………………………………………………………..xxxx
የተስተካከለ የባንክ ሚዛን…………………………………………………..xxxxxx
ድምር………………………..…………...…………...…..714,560.08
ሲቀነስ ፡-የባንክ አገልግሎት…………………..0
-ተመላሽ ቸክ…………………………0
Adjusted/የተስተካከለ የመዝገብ ሚዛን………………………………………………714,560.08
የማስተካከያ ምዝገባ
ባንክ..........................5000.00
ቦኖ ማደያ ገቢ……………………………5000.00
Thank You
Mohamed
Yimer