You are on page 1of 4

ኤል ሆም ኦፍ ኪድስ አካዳሚ

KG- Campus 0112760985/ Darmar Campus {Grade 1-4} 0112781006/ Torhailoch Campus{Grade 5-
8}/0118685567email- elhomeofkids2005@gmail.com

የአካባቢሳይንስትምህርትናመልመጃ ለ 2 ኛ ክፍል 2012 ዓ.ም


ተክሎችን ማብቀል

-ለተክሎች ዕድገት አስፈላጊ ነገሮች


 አየር
 ውሀ
 የፀሐይ ብርሀን
 አፈር ናቸው
-ከእነዚህ አስፈላጊ ነገሮች አንዱ እንኳን ቢጎድል ተክሎች ማደግ አይችሉም፡፡
 አየር ፡- ተክሎች ምግባቸውን ለማዘጋጀት አየር ያስፈልጋቸዋል፡፡ ተክሎች ጉልበትን ከምግብ
ለማመንጨት አየር ይጠቅማሉ፡፡
 አፈር፡- ተክሎች ምግባቸውን ለማዘጋጀትና ለማደግ የሚረዳቸውን ውሀ እንዲሁም አልሚ ምግብ
የሚገኙት ከአፈር ነው፡፡
- አፈር ተክሎችን ስሮች አቅፎ በመያዝ ቀጥ ብለው እንዲያድኑ ያደርጋል፡፡
- ብርሀን ፡- ተክሎች ምግባቸውን ለማዘጋጀት የጉልበት ምንጭ ያስፈልጋቸው ፡፡ይህም የጉልበት
ምንጭ የፀሐይ ብርሀን ነው፡፡
- ውሀ ፡- በቅጠል ውስጥ ምግብ እንዲዘጋጅ ይረዳል፡፡
- ምግብ በተክል ውስጥ እንዲዘዋወር ያደርጋል
- ለተክል ዕድገት አስፈላጊ የሆኑትን አልሚ ምግቦችን ያሟሟል፡፡
ተክሎችን ለማብቀል የሚረዱ ቁሳቁሶች
ተክልን ለማብቀል የሚረዱ ዋና ዋና መሳሪያዎች
 መቆፈሪያ
 አካፋ
 መኮትኮቻ
 ውሀ ማጠጫ
 መስመር ማውጫ
 ማንገዋለያና መቧጠጫ
 ጋሪ ናቸው
ዶማ፡- ዶማ ዘር ከመዘራቱ ወይም ችግኝ ከመተከሉ በፊት መሬትን ቆፍሮ ለማለስለስ የሚረዳ
መሳሪያ ነው፡፡
አካፋ ፡- አፈር ለመዘቅና ለማንሳት የሚጠቅም መሳሪያ ነው፡፡
ውሀ ማጠጫ፡-ከፕላስቲክ ወይ ከቆርቆሮ የተሰራ ወንፊት ያለው አትክልቶችን ውሀ ለማጠጣት
የሚጠቅም መሳሪያ ነው፡፡
ጋሪ፡- ፍግና (ማደበሪያ)ችግኞችን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለማጓጓዝ የሚረዳ መሳሪያ ነው፡፡

መልዕክትለወላጆች
 ሁሉምመልመጃዎችና ኖቶች በመማሪያ ደብተር ላይ መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡
 ወላጆች ልጆቻችሁን በማዘጋጀት እንድትረዷቸው እንጠይቃለን፡፡
 ወላጆች ቀጣይ ኖቶችንና መልመጃዎችን በዚሁ የቴሌግራምቻናላችን ላይ ስለምንልክ በየጊዜው
ይከታተሉን፡፡
[ዳርማር ካምፓስ |
መስመር ማውጫ፡- ብዙ ጣቶች ያሉት ክብሪት ወይም ከእንጨት የተሰራ ሆኖ ማብቀያ መደብ
ላይ ቀጥ ያሉ መስመሮችን ለማውጣት የሚጠቅም ነው፡፡
ሀ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ፃፉ፡፡
1. አራቱን የተክሎች ክፍል ዘርዝሩ፡፡
2. ተክሎችን ለማብቀል ከምንጠቀምባቸው መሳሪያዎች ውስጥ ሶስት ጥቀስ?
3. ዘርና ፍሬ የሚፈጠሩባቸው የተክል ክፍል ነው፡፡
4. ተክሎች ጉልበት ከምግብ ለማመንጨት ይጠቀማሉ፡፡
5. ለተክሎች ዕድገት አስፈላጊ ነገሮች ከሆኑት ውስጥ ሁለት ጥቅሱ?
6. የተክሎች ንስሮች አቅፎ በመያዝ ቀጥ ብለው እድያድጉ ያደርጋል፡፡
7. አፈር ለመዘቅና ለማንሳ የሚጠቅመን መሳሪያ ነው፡፡
በዙሪያችን የሚገኙ እንስሳት
ሀ. እንስሳትን መመደብ
-እንስሳን መመደብ
 በአረባባቸው
 በእንቅስቃሴያቸው
 በአመጋገባቸው
 በመኖሪያ ስፍራቸው
 በሰውነት ሽፋናቸው መሰረት ሊመደቡ ይችላሉ፡፡
እንስሳትን በአረባባቸው መሰረት መመደብ
- እንስሳ በአረባባቸው መሰረት በሁለት ይመደባሉ፡፡ እነርሱም ልጅ የሚወልዱ እንስሳትና
እንቁላል የሚጥሉ ናቸው፡፡
- ልጅ የሚወልዱ እንስሳት፡- እነዚህ አምሳያቸውን በመውለድ የሚተኩ የእንስሳት ዓይነት
ናቸው፡፡ አምሳያቸውን የሚወልዱ እንስሳት እስኪወልዱ ድረስ ልጃቸውን በማህፀናቸው
በመያዝ እንዲያድጉ ያደርጋሉ፡፡ ከወለዱም በኋላ ራሳቸውን እስከሚችሉ ድረስ ጡት እያጠቡ
ያሳድጋቸዋል፡፡
- ምሳሌ ላም'አንበሳ 'ድመት የመሳሰሉት
እንቁላል የሚጥሉ እንስሳት ፡-የእነዚህ እንስሳት ልጆች ተፈልፍለው እስከሚወጡ ድረስ
የሚፈጥሩትና የሚያድጉት በእንስሳት እንቁላሎች ውስጥ ነው፡፡
ምሳሌ፡- ዶሮ ' ወፍ ' እባብ 'እንቁራሪትና የመሳሰሉት
እንስሳት በእንቅስቃሴያቸው መስራ መመደብ
እንስሳት በተለያ ዓይነት እንቅስቃሴ ከቦታ ወደ ቦታ ይዘዋወራሉ፡፡ አንዳንዶቹ በሰማይ ላይ በመብረር
አንዳንዶቹ በመሬት ላይ በመሳብ 'ገሚሶቹ በእግራቸው በመራመድ እንዲሁም ሌሎች ደግሞ
በውሀ ውስጥ በመዋኘት ይንቀሳቀሳሉ፡፡
እንስሳት በአመጋገባቸው መሰረት መመደብ
እንስሳት በአመጋገባቸው መሰረት በሶስት ይመደባሉ፡፡
 ስጋ በል እንስሳት ለምሳሌ አንበሳ 'ውሻ 'ነብርና የመሳሰሉት ፡፡
 እፅዋት በል እንስሳት ፡-ሳርን በመንጨትና ቅጠላ ቅጠልን በመቀንጠስ በጥርሳቸው
አኝከው ይመገባሉ ፡፡ለምሳሌ ላም 'ፋይል ግመል
 ስጋና እፅዋት በል እንስሳት ፡- ሁለቱም ዓይነት የሚመገቡ ናቸው፡፡ ምሳሌ፡- ሰው
'አይጥ 'ዝንጀሮ

ሀ. በ#ሀ; ስር የተዘረዘሩትን ቃላት በ “ለ”ስር ካሉት አማራጮች ጋር አዛምዱ፡፡


ሀ ለ
ኤል ሆም ኦፍ ኪድስ አካዳሚ
KG- Campus 0112760985/ Darmar Campus {Grade 1-4} 0112781006/ Torhailoch Campus{Grade 5-
8}/0118685567email- elhomeofkids2005@gmail.com

1. ስጋ በል እንስሳ ሀ. ሰው
2. በሰማይ ላይ የሚበሩ ለ. ዓሳ
3. ስጋና እፅዋት በል እንስሳት ሐ. ፍየል
4. በመሬት ላይ የሚሳቡ መ. አንበሳ
5. በውሀ ውስጥ የሚኖሩ ሠ. እባብ

መልዕክትለወላጆች
 ሁሉምመልመጃዎችና ኖቶች በመማሪያ ደብተር ላይ መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡
 ወላጆች ልጆቻችሁን በማዘጋጀት እንድትረዷቸው እንጠይቃለን፡፡
 ወላጆች ቀጣይ ኖቶችንና መልመጃዎችን በዚሁ የቴሌግራምቻናላችን ላይ ስለምንልክ በየጊዜው
ይከታተሉን፡፡
[ዳርማር ካምፓስ |

You might also like