You are on page 1of 4

የስራ መደቡ መጠሪያ ፡ የወደብ ትራፊክ

የሚገኝበት መምሪያ/
መምሪያ/ቅ/ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት

ዋና ክፍል ፡ ተርሚናል ኦፕሬሽን ዋና ክፍል

ቀጥታ ተጠሪነት ፡ ለኦፕሬሽን አስተባባሪ

ዝርዝር ተግባርና ኃላፊነት

1. እቃ ለመጫን ከውጭ ወደ ወደብ ውስጥ የሚገቡ ተሽከርካሪዎችን ወደ ጭነቱ ያለበት ቦታ


ማመላከት/
ማመላከት/ እንዲሄድ ማድረግ፡፡
2. ተርሚናል ውስጥ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይኖር ኮንቴነር ኦፕሬሽን ኦፊሰሮች ጋር በመነጋገር
መጥኖ ማስገባት፡፡
3. ከባህር ወደብ ሙሉ ጭነት ይዘው ወደ ወደቡ የሚገቡ ተሽከርካሪዎች በተቀላጠፈ ሁኔታ
እንዲያራግፉ ከተርሚናል ኮንቴይነር ኦፕሬሽን ጋር በመሆን በመነጋገር መጥኖ እንዲገቡ ማድረግ፡፡
4. ማንኛውም ወደብ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች በወደቡ በተወሰነው ፍጥነት እንዲንቀሳቀሱ
ማድረግ፡፡
5. ከወደብ ጭነት ጭነው ወደ ውጭ የሚወጡ መኪኖችን ሌሎችን ወደ ወደቡ የሚገቡ መኪኖች
መንገድ እንዳይዘጉ ክትትል በማድረግ የተሳለጠ አገልግሎት እንዲኖር ማድረግ፡፡
6. በግቢው ውስጥ የሚስተናገድ ተሽከርካሪ በተፈቀደለት ቦታ መቆሙን ያረጋግጣል፡፡
7. ተፈትሾ የተለቀቀ ኮንቴነር ለመጫን የሚገቡ መኪኖች በ CFS የፍተሻ ቦታ ላይ መንገድ ይዘው
እንዳይቆሙ መከልከል፡፡
8. በተመደበበት የሥራ አካባቢ ላይ ያሉትን የትራፊክ እንቅስቃሴዎች የመመልከትና ተገቢውን
ማስተካከያ ማድረግ፡፡
9. ማንኛውም ጭነት ለመጫን ጌት ፓስ የሌለው መኪና በግቢ ውስጥ እንዳይቆም ማድረግ፡፡
10. በተርሚናል ውስጥ ትራክተሮች ኮንቴነር ጭነው ሲንቀሳቀሱ ሌሎች መኪኖች መንገድ
እንዳይዘጉባቸው ማድረግ፡፡
11. በድርጅቱ የወደብ አስተዳደር መመሪያ መሰረት ማንኛውም ተሽከርካሪ የስራ እንቅስቃሴ አደናቅፎ
ሲገኝ በመመሪያው መሠረት እርምጃ እንዲወሠድ ማድረግ፡፡
12. በግቢ ውስጥ አግባብነት ያላቸው የትራፊክ ምልክቶች መሰረት ተሽከርካሪዎች እየተንቀሳቀሱ
መሆኑን መከታተል፡፡
13. ወቅታዊ ሪፖርት ማቅረብ፡፡
14. ከቅርብ ኃላፊው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡

የሥራ መደቡ መጠሪያ ፡ የዝግ መጋዘን ሰራተኛ

የሚገኝበት መምሪያ ቅርንጫፍ ፡ ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት

ዋና ክፍል ፡ ተርሚናል ኦፕሬሽን ዋና ክፍል

ቀጥታ ተጠሪነት ፡ ለኦፕሬሽን አስተባባሪ


ዝርዝር ተግባራት

1. ቀድሞ በደረሰ መረጃ መሰረት የጭነት ዝርዝር መግለጫዎች (Cargo Manifest) መሠረት ጭነቱን
ለማሥተናገድ የሚያስችል የሰው ኃይል፣ የቦታ እና የመሳሪያ ዝግጅት ያደርጋል፡፡

2. በፕሎም ታሽገው ከባህር ወደብ ተጭነው የደረሱ ብትን ዕቃዎችን በታሸጉበት ሁኔታ መድረሳቸውን
ከጉምሩክ ኢንስፔክተሮች ጋር በመሆን ያረጋግጣል፡፡

3. አጓጓዥ ዕቃውን ለማስረከብ መሟላት ያለበትን መስፈርት ማለትም Gate pass እና way መሟላቱን
ካረጋገጠ በኋላ

 አስፈላጊ የሆኑ የሰው ኃይልና መሳሪያ ያሰማራል፣


 ጭነቱን ጉምሩክ እና አጓጓዥ ባሉበት በጥንቃቄ እንዲወርድ ያደርጋል፡፡
 ጭነቱ ቀድሞ በተዘጋጀለት ቦታ በእቃው ባህሪ፣ በዕቃው ይዘትና ዓይነት መሰረት እንዲቀመጥ
ያዛል መቀመጡን ይቆጣጠራል፡፡
 የዕቃ መረከቢያ ሰነድ (Good Receiving Document) እንዲዘጋጅ በማድረግ ተቆጥሮ በተገኘ
መረጃ መሠረት ርክክብ ያደርጋል፣ ጉድለት ካለም አስተያየት (Remark) እንዲፃፍ ያደርጋል፡፡
 አጓጓዡን የዕቃ መረከቢያ ሰነድ ላይ በማስፈረም ኦሪጅናሉን ለአጓጓዡ ኦሪጅናል ዌይቢል (way
bill) ላይ በመፈራረም ማህተም በማድረግ ለአጓጓዥ ይሰጣል፡፡
4. ከበር ቁጥጥር ተሞልቶ የተላለፈለትን የአገልግሎት መከታተያ ቅፅን አገልግሎት መስጠት የተጀመረበትን
አገልግሎቱ ተሰጥቶ ያለቀበትን ሰዓት በመሙላት አጓጓዡን ያሰናብታል

5. ወደመጋዘን ለሚገቡ ጭነቶች ታግ (Tag) እና ሎኬሽን (Location) ይሰጣል

6. በደንበኛው ወይም በጉምሩክ ባለሙያ ጥያቄ ከኮንቴነር ወጥተው ወደ መጋዘን እንዲገቡ የተጠየቁ ገቢ
ዕቃዎችን በቀረበ ልዩ ጥያቄ(Special Service Request) መሠረት አስፈላጊ ሰነዶችን መሟላታቸውን
በማረጋገጥ ፡-

 አስፈላጊ የሆኑ የሰው ኃይልና መሳሪያ ያሰማራል፣


 ከኮንቴነር የወጣው ጭነት ወደ ዝግ መጋዘን
መጋዘን በሚገባበት ወቅት በዕቃ መረከቢያ ሰነድ እና ታሊ
ሽት እንዲዘጋጅ በማድረግ ርክክብ ይፈጽማል
 እቃዎች ወደ መጋዘን ሲገቡና ሲቀመጡ በጥንቃቄና በአግባቡ መሆኑን ይከታተላል፣
ይቆጣጠራል፡፡
 ርክክብ የተፈፀመባቸው ኦሪጅናል የዕቃ መረካከቢያ ሰነድ በመያዝ አንድ ኮፒ ለኦፕሬሽን ሰነድ
ዝግጅት አንድ ኮፒ ለጉምሩክ መሰራጨቱን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡፡
7. ከኮንቴነር ወጥተው (unstuffed) ወይም በብትን መጥተው መጋዘን የገቡ እቃዎቸ ጉምሩክ ለፍተሻ
ሲፈልጋቸው፡-

 አስፈላጊ የሆነ የሰው ኃይል እንዲመደብ ያደርጋል፣


 ፍተሻውን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣
 በፍተሻ ወቅት የተከፈቱ ጭነቶችን ከፍተሻ በኋላ በነበሩበት ሁኔታ እንደታሸጉ ያደርጋል
ይከታተላል፡፡
 ደንበኛው ለተሰጠው አገልግሎት ተገቢውን ክፍያ እንዲፈፅም በዕቃ መረካከቢያ ሰነድ ላይ
የተፈተሸውን ጭነት፣ ብዛት እና ክብደት ያሰፍራል
8. ደንበኛው በመጋዘን ያለውን ዕቃ መረከብ ሲፈለግ የአስመጪው ውክልና፣ የጉምሩክ መልቀቂያ፣የተወካይ
ኮፒ መታወቂያ እና የወደቡን የአገልግሎት ክፍያ የተፈፀመበትን ደረሰኝ ማቅረቡን በማረጋገጥ፡-

 ጭነቱን ወደተፈለገው መጓጓዢያ ለመጫን አስፈላጊ የሆኑ የሰው ኃይል እና መሳሪያ ያዘጋጃል፣
 የእቃ መልቀቂያ ሰነድ(Good Delivery Document) ያዘጋጃል
 የደንበኛው ጭነት በአግባቡና በጥንቃቄ ወደቀረበለት ተሽከርካሪ ወይም ኮንቴነር እየተጫነ
ወይም እየገባ(Stuffing) መሆኑን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡፡
 አስመጪው/ ተወካዩ/ በዕቃ መልቀቂያ ሰነድ ላይ ፈርመው ዕቃ መረከባቸው ያረጋግጣል፡፡
 የርክክቡ ሰነድ በአግባቡ ተመዝግቦ ፋይል ያደርጋል
9. በመጋዘን የተቀመጠ ዕቃ በደህና ሁኔታ ስለመሆኑ በየእለቱ ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል፡፡

10. ከቅርብ ኃላፊው የሚሰጡ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡

You might also like