You are on page 1of 1

 ቅዳሴ የሚጀመረው ሁልጊዜ ከጠዋቱ 12 ሰኣት (ጾም ያልሆነ ቀን) እና ከቀኑ 6 ሰኣት ነው፣ ሁልጊዜም ቀደም

ተብሎ መመጣት አለበት ቢያንስ ከ 1 ሰኣት በፊት ኪዳን ኣድርሶ ተረጋግቶ ለማስቀደስ።

 ቅዳሴ ማለት ካህናት አና ምእመናን በህብረት አየተቀባበሉ የሚያደርሱት የጸሎትና የምስጋና ስረት ነው፣ በዚህ
ስረት ውስጥ ቀዳሾችሁ ካህናት እና አስቀዳሾቹ እመናን የሚወክሉትና የሚያደርጉት የራሳቸው ድርሻ አለ፤
ለምሳሌ የሚቀድሱት ካህናት 5 መሆናቸው ቤተ ክርስትያኗ ለምዕመናኖቿ የምታስተምራቸውን 5ቱን
ሚስጥራት (5ቱ ምስጢራተ ቤ/ክ) ይወክላሉ በተጨማሪም አምስቱም ካህናት የራሳቸው ስራ ድርሻ አላቸው
ጧፍ(መብራት) የሚይዝ አለ፣ ፍም የሚያመጣ አለ፣ ዣንጥላ የሚይዝ አለ ወዘተ. . . ። በዚህ መሰረት ቅዳሴ
ላይ ሁሉም ቀዳሽ ካህናትና ኣስቀዳሽ ምዕመናን የራሳቸው የስራ ድርሻና የሚወክሉት (symbolize የሚያረጉት)
ነገር አላቸው ማለት ነወ። ለምሳሌ
 ዲያቆኑ ለጸሎት ተነሱ ሲል ህዝቡ ኣቤቱ ይቅር በለን(እግዚኦ ተሳሃለነ) ይላል ይህም ዲያቆኑ የኣዳም ምሳሌ
ነው፣ ኣዳም ሲኦል ውስጥ እያለ ሁሉንም ለጸሎት ተነሱ ይላቸው ነበር እነሱም አቤቱ ይቅር በለን ይሉ ነበር

 ዋናው ቀዳሽ ካህን ሰላም ለሁላችሁ ይሁን ሲል ህዝቡ ከመንፈስህ ጋር ይላል ( እዚህ ላይ ምሳሌው ካህኑ የ
ኢየሱስ ክርስቶስ ነው, ክርስቶስ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞቶ በነፍሱ ሲኦል ገባና ከ አዳም ጀምሮ አስከ
መጨረሻው ሟች ድረስ 5500 ዘመን ሙሉ ሲኦል ጨለማ ውስጥ ታስረው ለነበሩት ሰላም ለሁላችሁ
ይሁን ያላቸውን ይወክላል)፣ ህዝቡ ከመንፈስህ ጋራ ይላል (ከመንፈስህ ጋራ፣ አንደቃልህ ይሁንልን
ይደረግልን ማለት ነው)

ለምን ሁሉም በምሳሌ ይደረጋል ቢባል ደግሞ ክርስቲያኖች ሃገራችን በሰማይ ነው፣ ዘላለማዊ ኑሮን የምንኖረው
ከሞት ከተነሳን በሁዋላ በመንግስተ ሰማያት ነው ብለን ስለምናምን፣ መንግስተ ሰማያት ላይ ደግሞ ያሉትን
ስርአቶች እግዚአብሔር ለሚወዳቸው ስለገለጸላቸው ለነሱ የተገለጸውን እያሰብን አንደምንኖረው አንደምንወርሰው
ተስፋችንን ለማጠንከር እንዲሁም ከዚህ በፊት የተደረጉልንን ነገሮች ሁሉ አንድናስብ ተብሎ ነው።

ሙሉ ቅዳሴው ውስጥ የሚባሉት በጠቅላላ ትርጉምና ምሳሌ አላቸው፣ በተጨማሪም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ 14
ኣይነት ቅዳሴወች አሉ ሁሉም የተለያዩና በተለያዩ ጊዜወች የሚቀደሱ ናቸው፣ ቅዳሴ ለማስቀደስ ምን እየተባለ
አንደሆነ ማወቅ ያስፈልጋል ምን ማለት አንዳለብንም እንደዚሁ ለዚህ ደሞ በርካታ የቅዳሴ መማርያ መጽሃፎች ኣሉ
ዜማቸውንም ጭምር ። ለጊዜው ግን ቤተ ክርስቲያን ለማስቀደስ ስንሄድ ትንሽዬ መጽሃፍ አለች የቅዳሴ ተሰጥኦ
የምትል እሱዋን ገዝቶ መከታተል ይቻላል።

3. ማህሌት የሚኖረው ንግስ ካለ ብቻ ነው (ነገር ግን በ ጽጌ ጾም ጊዜ ሁሌ ቅዳሜ ማታ ከ 2 ሰኣት ጀምሮ እስከ 11


ሰኣት ይቆማል ንግስ ኖረም አልኖረም)፥ ለምሳሌ ነገ የ እመቤታችን ንግስ ካለ ዛሬ ከቀኑ 7 ሰኣት ጀምሮ አስከ 10
ሰኣት ድረስ ዋዜማ ይቆማል፣ ምግብ ተበልቶ መግባት ይቻላል፣ ከዛ ማታ 2 ሰኣት ጀምሮ ደግሞ ማህሌት ይቆማል
እዚህም ላይ ምግብ ተበልቶ መግባት ይቻላል፣ ለምን ቢባል ተበልቶ የማይገባው ቅዳሴ ከመቀደሱ በፊት ነው።

You might also like