Professional Documents
Culture Documents
HMIS Guideline
HMIS Guideline
መጀመሪያ ከዋናው ማውጫ ላይ profile የሚለውን ይጫኑ በመቀጠል Customize drug list የሚለውን ይጫኑ
በቀጠል ከላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ ካታጎሪ (categories) ከሚለው ውስጥ ወደ መድሃኒቱ የሚገኝበትን ወይም የመድሃኒቱ
መገለጫ ይምረጡ ከፋርማሲዩቲካል፣ ሰፕላይ፣ ኬሚካል ወይም ኢኩፕመንት የሚለውን በመምረጥ ቀጥሎ Filter by
Item Name የሚለው ባዶ ቦታ ላይ በመጫን የመድሃኒቱን የመጀመሪያዎችን ፊደሎች በመፃፍ የሚፈልጉትን መድሃኒት
በቀላሉ እንዲያገኙ ይረዳዎታል የሚፈልጉትን መድሃኒት እንዳገኙ መድሃኒቱ ላይ በተደጋጋሚ በመጫን Double click
በማድረግ ቀጥሎ በሚመጣው ዊንዶው ላይ Use at this facility የሚለው ሳጥን ላይ የራይት ምልክት በማድረግ
ሴቭ ያድርጉት ይህንንም በማድረግ ከተዘረዘሩት መድሃኒቶች ውስይ እርሶ ወይም ተቋሙ የሚፈልጋቸውን
መድሃኒቶች ብቻ በመምረጥ እናስገባለን ማለት ነው ይህንን በማድረግ ተቋሙ የሚጠቀምባቸውን መድሃኒቶች
ብዛት እና የትኞቹ መድሃኒቶች መሆናቸውን በቀላሉ ለማወቅ ይረዳል ማለት ነው፡፡
አንድ ጊዜ የመረጥነውን መድሃኒት የማንፈልገው ከሆነ ወይም ከድራግ ሊስታችን ማውጣት ከተፈለገ
የመጀመሪያውን አካሄድ በመሄድ Use at this facility የሚለው ሳጥን ላይ የራይት ምልክቱ ላይ ደግመው በመጫን
የራይት ምልክቱ ካጠፉ በኋላ ሴቭ Save የሚለውን በተን ይጫኑ
መጀመሪያ ከዋናው ማውጫ ላይ profile የሚለውን ይጫኑ በመቀጠል Facility Details የሚለውን ይጫኑ ይህንን
ሲጫኑ ከጎን (በቀኝ) በኩል በሚመታየው ዊንዶው ላይ Suppliers, Store, Bin Location & Issue locations የሚሉ
ይገኛሉ እነዚህም መድሃኒት አቅራቢዎቻችን መድሃኒት ወሳጆቻችን እና መድሃኒቱ የሚቀመጥበትን የስቶር መረጃ
እናስገባለን ማለት ነው፡፡
1. መድሃኒት አቅራቢ ለማስገባት Suppliers የመለውን ከተጫንን በኋላ በመቀጠል በቀኝ በኩል ካለው ላይ
Add New Supplier በተን እንጫናለን ከዚህም በመቀጠል መረጃዎቸን እናስገባለን
- Company Name (የመድሃኒት አቅራቢውን ስም) ከታች የሚገኙትን መረጃዎች ሁሉ አድራሳች
እንሞላለን ሆኖም ግን አድራሻዎቹ ግዴታ ስላልሆኑ ማለፍም ይቻላል
- Company Info የሚለውን በመጫን የመድሃኒት አቅራቢውን መረጃ ከተዘረዘሩት ውስጥ አንድኑ
መበመምረጥ እናስገባለን Government, NGO, Privet or Others ይህን እንደጨረስን Save
የሚለውን በተን እንጫናለን፡፡
2
አንድ ጊዜ መረጃዎቸን ካስገባን በኋላ በተደጋጋሚ ማስገባት አይጠበቅብንም አንድ ጊዜ የገባን መረጃ ሁሌም
እንዳስገባነው ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
Transaction (የዚህ
ዋና ሜኑ አገልግሎት መድሃኒቶቸን ገቢ፣ ወጪ፣ ሎስ እና አጀስትመንት እንዲሁም
በአመቱ መጨሻ ላይ የቆጠራ መረጃዎቸን ማስገባትን ያካትታል እነዚህም ስራዎች ሁልጊዜም በስቶራችን
የሚሰሩ ስለሆነ እነዚህን በመስራት የተለያዩ መረጃዎቸን ማግኘት ይቻላል)
በአጋጣሚ አንድ መድሃኒት ኖሮ ሁለት አይነት Batch Number ያለው ቢገጥመን በመድሃኒቱ
አቅጣጫ የሚገኘውን (+) ምልክት ይጫኑ በመቀጠል (Pack Qty, Qty/Pack, Price/Pack, Batch
Number, Expire Date) መረጃዎቸን ያስገቡ ከመረጡት መድሃኒት ውስጥ መቀነስ የሚፈልጉት
ካለ (-) ይጫኑ፡፡
- ሲጨርሱ Save የሚለውን በተን እንጫናለን፡፡
Step 3 (Pick list) (በዚህ ስቴፕ ላይ ሲስተሙ እያንዳንዱ መድሃኒት ከየትኛው ባች መውጣት
እንዳለበት የሚጠቁም ስለሆነ ሲስተሙ የሰጠንን መረጃ በመጠቀም እያንዳንዱን መድሃኒት ወጪ
እናደርጋለን ይህም ለማድረግ Save and Print የሚለውን ይጫኑ በመቀጠል ከሚመጣው ዊንድዎ
ላይ ፐሪንተ ምልክቱን በመጫን Pick list ፕሪንት ያድርጉ በዚህም መሰረት መድሃኒት ወጪ
በሚያደርጉ ቁጥር ይህን ፕሪንት እያደረጉ ሲስተሙ የሚጠቁመውን በቅድሚያ ኤክስፓየር
የሚያደርገውን መድሃኒት ወጪ በማድረግ ኤክዝፓየር የሚያደርግብንን መድሃኒት መጠን
እንቀንሳለን፡፡
መጀመሪያ ከዋናው ማውጫ ላይ Transaction የሚለውን ይጫኑ በመቀጠል ከላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ
Losses and Adjustment የሚለውን ይጫኑ በመቀጠል በመቀጠል ሎስ አጀስተመንቱን መስራት የሚፈልጉት
መድሃኒት የሚገኘበትን Store እና ከ category (ከፋርማሲዩቲካል፣ ሰፕላይ፣ ኬሚካል ወይም ኢኩፕመንት) ከሚለው
ላይ እርሶ የሚፈልጉትን ይምረጡ
በመቀጠል Expired ያደረጉትን መድሃኒቶች ብቻ የሚፈልጉ ከሆነ Show Expire Only በማድረግ መለየት ይቻላል
በመቀጠል መድሃኒቶቹን በመምረጥ ከታች Pick የሚለውን ይጫኑ በመቀጠል
Expired ካደረጉት መድሃኒቶች ውጪ ሁሉንም መድሃኒት ለማግኘት ከፈለጉ ሳጥኑ ላይ በመጫን ሳጥኑን ባዶ ያድርጉት
Ref. No ላይ መድሃኒቱ ሎስ የሚሰራ Losses አጀስትመንት የሚሰራ ከሆነ Adjustment በማለት እንፅፋለን
በመቀጠል ሎሰስ የምንሰራ ከሆነ ሎሰስ በሚለው አቅጣቻ መቀነስ የምንፈልገውን መድሃኒት በታብሌት ብዛት
እናስገባለን ይህንን ስናደርግ BU Qty (Remaining) ላይ ከተገፀው መጠን በላይ መቀነስ አይቻልም በመቀጠል
Reason ከሚለው ላይ መድሃኒቱን ሎስ የሰራንበት ምክንያት እንመርጣለን በመጨረሻም Save የሚለውን በተን
እንጫናለን፡፡
በመጀመሪያ Activity Log ይጫኑ በመቀጠል ከላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ Received Log ይጫኑ በመቀጠል
መድሃኒቱን የተቀበሉበት Store ይመረጡ በመቀጠል መድሃኒቱን ገቢያደረጉበትን የሞዴል ቁጠር በግራ
ከተዘረዘሩት Ref. No በታች ካለው ዝርዝር ላይ ይጫኑ ይህንን በሚያደርጉበት ወቅት በቀኝ ካለው ዊንዶው ላይ
በተጫኑት ሞዴል ቁጥር ገቢ ያደረጉዋቸው መድሃኒቶች በግልፅ ይታያሉ በዚህን ጊዜ ከተዘረዘሩት መድሃኒቶች
ውስጥ ማስተካከል የሚፈልጉትን መድሃኒት ላይ በማውሱ በቀኝ በኩል ይጫኑ(Right Click) በዚህን ጊዜ ሁለት
Edit /Delete የሚሉ ዝርዝሮች ይመጣሉ መድሃኒቱን ማጥፋት ከፈለጉ Delete የሚለውን ይጫኑ ሆኖም ግን
መድሃኒቱን ገቢ ሲያደርጉ የሞዴል ቁጥር/ ባች ቁጥር/ ኤክስፓየር ዴት/ መድሃኒቱ ገቢ የሆነበት ስቶር/ የመድሃኒቱ
ብዛት/ ዋጋ ተሳስተው ከሆነ Edit የሚለውን ይጫኑ ይህንን በሚያደርጉበት ወቅት ገቢ ያደረጉት መድሃኒት ሙሉ
መረጃ የያዘ ሌላ ዊንዶው ይከፈታል በመሆኑም ከተከፈተው ዊንዶው ላይ ማስተካከል የመፈልጉትን
6
አስተካክለው እንደጨረሱ ከታች Update የሚለውን ይጫኑ ይህንን በማድረግ አንድን መድሃኒት ገቢ ሲያደርጉ
የተሳሳቱንን ነገር ማስተካከል ይቻላል፡፡
መድሃቱን ገቢ ሲያደርጉ የሞዴል ቁጥሩንና ገቢ ያደረጉበትን ቀን ከተሳሳቱ በቀላሉ በግራ ከተዘረዘረው የሞዴል
ቁጥር ላይ በማውሱ በቀኝ በኩል ይጫኑ(Right Click) በዚህን ጊዜ ሁለት Edit /Delete ይመጣል ማስተካከል
የሚፈልጉ ከሆነ Edit የሚለውን ይጫኑ፡፡
በመጀመሪያ Activity Log ይጫኑ በመቀጠል ከላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ Issue Log ይጫኑ በመቀጠል
መድሃኒቱን ወጪ ያደረጉበትን Store ይመረጡ በመቀጠል መድሃኒቱን ወጪ ያደረጉበትን የሞዴል ቁጠር በግራ
ከተዘረዘሩት Ref. No በታች ካለው ዝርዝር ላይ ይጫኑ ይህንን በሚያደርጉበት ወቅት በቀኝ ካለው ዊንዶው ላይ
በተጫኑት ሞዴል ቁጥር ወጪ ያደረጉዋቸው መድሃኒቶች በግልፅ ይታያሉ በዚህን ጊዜ ከተዘረዘሩት መድሃኒቶች
ውስጥ ዝርዝር መረጃ (Detail) ማየት ከፈለጉ ወይም የሚፈልጉትን መድሃኒት ማጥፋት ከፈለጉ በማውሱ
በቀኝ በኩል ይጫኑ(Right Click) በዚህን ጊዜ ሁለት Detail /Delete የሚሉ ዝርዝሮች ይመጣሉ መድሃኒቱን
ማጥፋት ከፈለጉ Delete የሚለውን ይጫኑ ወይም የመድሃኒቱን መረጃ ከፈለጉ ወይም ኤሌክትሮኒክ ቢን ካርድ
(e-Bin Card)ማየት ከፈለጉ Detail የሚለውን ይጫኑ ይህንን በሚያደርጉበት ወጪ ያደረጉትን የአንድን መድሃኒት
ሙሉ መረጃት ይቻላል፡፡
Losses/Adjustment Log ፡ (በዚህ ሎግ) ሎስ/ አጀስትምንት የሰራናቸውን ያደረደግናቸውን መድሃኒቶች በየሞዴል
ቁሮቻቸው የምናገኝበትና መድሃኒቱን ወጪ ስናደር የተሳትነውን የምናጠፋበት ነው)
በመጀመሪያ Activity Log ይጫኑ በመቀጠል ከላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ Losses/Adjustment ይጫኑ በመቀጠል
መድሃኒቱን ሎስ/ አጀስትምንት ያደረጉበትን Store ይመረጡ በመቀጠል መድሃኒቱን ሎስ/ አጀስትምንት
ያደረጉበትን የሞዴል ቁጠር በግራ ከተዘረዘሩት Ref. No በታች ካለው ዝርዝር ላይ ይጫኑ ይህንን በሚያደርጉበት
ወቅት በቀኝ ካለው ዊንዶው ላይ በተጫኑት ሞዴል ቁጥር ሎስ/ አጀስትምንት ያደረጉዋቸው መድሃኒቶች በግልፅ
7
ይታያሉ በዚህን ጊዜ ከተዘረዘሩት መድሃኒቶች ውስጥ ማጥፋ ወይም ማስተካከል ከፈለጉ በማውሱ በቀኝ በኩል
ይጫኑ(Right Click) በዚህን ጊዜ ሁለት Edit /Delete የሚሉ ዝርዝሮች ይመጣሉ መድሃቱን ሎስ/ አጀስትምንት
ሲያደርጉ የሞዴል ቁጥሩንና ሎስ/ አጀስትምንት ያደረጉበትን ቀን ከተሳሳቱ በቀላሉ በግራ ከተዘረዘረው የሞዴል
ቁጥር ላይ በማውሱ በቀኝ በኩል ይጫኑ(Right Click) በዚህን ጊዜ ሁለት Edit /Delete ይመጣል ማስተካከል
የሚፈልጉ ከሆነ Edit የሚለውን ይጫኑ ማጥፋት ከፈለጉ Delete የሚለውን ይጫኑ ፡፡
VII. Reports (በዚህ ዋና ሜኑ ውስጥ የተለያዪ ሆኖም ግን ለኛ ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን የምናገኝበት
ሲሆን በዚህ ሜኑ ላይ የምንሰራው ስራ አይኖርም ሆኖ ለውሳኔ የሚረዱንን መረጃዎች በቀላሉ
የምናገኝበት ነው እነዚህም ጥራት ያላቸውን ሪፖርቶች ለማግኘት ከላይ ትራንዛክሽን የመለው ሜኑ
ውስጥ መድሃኒቶችን ገቢ/ወጪ/ሎስ እና አጀስትመንት ስንሰራ በተገቢው ወቅትና ተገቢውን መረጃ
በትክክል ካስገባን ከዚህ በታች የምናገኛቸው መረጃዎች ትክክለኝነት የሚያጠራጥር አይደለም)
ሪፖርቶችን ለማግኘት በመጀመሪያ ከዋናው ሜኑ ላይ Reports የሚለውን ይጫኑ በመቀጠል ከላይ የተዘረዘሩትን አንድ
በአንድ በመጫን የምንፈልገውን ሪፖርት ማግኘት እንችላለን፡፡
1. Stock Status፡ በዚህ ሪፖርት ላይ በሁለቱም ስቶራችን ውስጥ ማለትም በበጀት እና በፕሮግራም ስቶራችን
ውስጥ ያሉትን መድሃኒቶች በእጃችን ላይ ያለንን ብዛት መጠን በቀላሉ የምናውቅበት ነው እንዲሁም
መድሃኒቱ በአሁን ሰኣት እጃችን ላይ እያለ መድሃኒቱ ያለበትን ሁኔታ በተለያየ ቀለማት በመለየት እንድናውቅ
ይረዳናል ይህም
- Excess Stock (Over Stock)
- Near EOP (Near to Emergency)
- Below EOP (Below Emergency)
- Stock Out
- Expired
እንዲሁም ከመድሃኒቶቹ በላይ ያለው ሮው ላይ የተዘረዘሩት መድሃኒቱ ያለንን መጠን አሁን ባለን
አጠቃቀም ለወፊቱ ለምን ያህል ጊዜ መድሃኒቱን መጠቀም እንደምንችል ያሳየናል፡፡
9. Consumption Trend
10. Consumption By Unit
11. AMC Report