You are on page 1of 3

LEMLEM TESFA SCHOOL

የ2012 ዓ.ም የ2ኛ ወሰነ ትምህርት አማርኛ መልመጃ ለኬጂ3


ስም ክፍል ቀን

ተመሳሳይ ቃላት

ተመሳሳይ ቃላት ማለት አንድ አይነት ትርጉም ያላቸው ማለት ነው


ለምሳሌ በላ - ተመገበ
ሰማ - አዳመጠ
ጥሩ - መልካም

ተመሳሳይ ቃላቶችን አንብቡ፡፡


ገፅ 54
ገፅ 55 ላይ ያለውን መልመጃ ስሩ

ለተሰመረባቸው ቃላቶች ተመሳሳያቸውን ፃፉ

ሀ. ልጁ ገመዱን ጎተተ፡፡
ለ. ውሻው ስጋ በላ ፡፡
ሐ. አልማዝ ቆንጆ ናት ፡፡
መ. አባቴ ዜና አዳመጠ ፡፡
ሠ. አስቴር መልካም ፀባይ ያላት ልጅ ናት ፡፡
ረ. ትዕግስት ጥቂት መንገድ ተጓዘች፡፡
ሰ. ብሩክ ከእንቅልፉ ተነሳ፡፡
LEMLEM TESFA SCHOOL

ገፅ 56 ላይ ያለውን መልመጃ ስሩ

ድርብ ድምፅ ያላቸውን ፊደላት

ሏ ሟ ሯ ሷ ሿ
ቋ ቧ ቷ ቿ ኋ
ኗ ኟ ዟ ዧ ዷ
ጇ ጧ ጯ ጿ ፏ

በድርብ ድምፅ የተመሠረቱ ቃላትን አንብቡ

ቋንቋ ጧፍ
ቧንቧ ፏፏቴ
ሏሟ ቋንጣ
ቋጥኝ ሯጭ

ፊደሎቹን ከቃላቾቹ ጋር አዛምዱ


–––– ጓ ሀ. ቋጥኝ
–– ሟ ለ. ፏፏቴ
–– ቋ
ሐ. ቧንቧ
–– ቧ
–– ፏ መ. ጓጓ
ሠ. ሟሟ
በተሠጡት ፊደላት ቃላት መስርቱ
ፏ = –––––
ቋ = –––––
ቧ = –––––
ሏ = –––––
ሟ = –––––

በድርብ ድምፅ የተመሰረቱትን ቃላቶች አስምሩ

ሀ. የአባይ ፏፏቴ ያምራል ፡፡


ለ. እናቴ ቋንጣ ትወዳለች ፡፡
ሐ. ቋንቋ መግባቢያ ነው፡፡
መ. አቡሽ ኳስ ተጫወተ ፡፡
ሠ. ጫልቱ ጧፍ አበራች ፡፡
ረ. አስማረ ብስኩት ለመብላት ጓጓ ፡፡

ድርብ ድምፅ ያላቸውን ፊደላት በመምረጥ አክብቡ

You might also like