You are on page 1of 2

አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

በ2015 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ውጤት


ላመጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ!

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ተማሪዎችን በመደበኛ መርሀ ግብር
ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዩኒቨርሲቲያችን መማር ለምትፈልጉ
ዩኒቨርሲቲያችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ የሰለጠነ የሰው ሀይል ፍላጎት ለማሟላት በመንግስት
ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ከፍተኛ የለውጥ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል ፡፡ ይህንንም እውን
ለማድረግ ልዩ ተልዕኮ ከተሰጣቸው ሁለት ሳይንስና ቴክኖሎጅ ውስጥ የአዳማ ሳይንስና
ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለፈጠራ ተግተን እንሰራለን (We are dedicated to innovative
knowledge) በሚል መርህ ቃል በዘርፉ ብቃት ያላቸውን ሙያተኞችን እያፈራ ይገኛል፡፡

በመሆኑም በ2016 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርሲተያችን ገብተው በአፕላድ ተፈጥሮ ሳይንስ እና


በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ በ2015 ዓ.ም
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ከ50% አና ከዚያ በላይ
ውጤት ያመጡትን ተማሪዎች ተቀብሎ ማተማር ይፈልጋል ፡፡

ዩኒቨርሲቲያችን ልዩ ከሚያደርጉት ነገሮች ውስጥ

• ተማሪዎች የራሳቸው ካሪኩለም (Curriculum) መቅረጽ መቻላቸውን


• አቅም ያላቸው ተማሪዎችን በአንድ ጊዜ በሁለት ሜጀር (Dual Major /minor)
መመረቅ መቻላቸው
• አቅም ያላቸውን ተማሪዎች በተፋጠነ ጊዜ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ የማግኘት
ዕድል (Fast track) ማግኘት
• ያሉን ፕሮግራሞች በሙሉ አለማአቀፍ እውቅና ያላቸው እንድሆኑ እየተሰራ
መሆኑን እየገለፅን ፡-

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች በትምህርት


ሚኒስቴር ወብሳይት ውስጥ ገብታችሁ ዩኒቨርሲቲያችንን መምረጥ የምትችሉ መሆኑን
እያሳወቅን በመጀመሪያ ድግሪ የሚሰጡ ፕሮግራሞች የሚከተሉት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

በኢንጂነሪንግ አፕላይድ ሳይንስ

አርክቴክቸር አፕላይድ ባዮሎጂ

ሲቪል ኢንጂነሪንግ አፕላይድ ኬሚስትሪ

ወተር ሪሶርስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ

ኬሚካል ኢንጂነሪንግ ፋርማሲ

ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ አፕላይድ ፊዚክስ

ማቴሪያል ሳይንስና ኢንጂነሪንግ አፕላይድ ጂኦሎጂ

ኤሌክትሪካል ፓወር እና ኮንትሮል አፕላይድ ማቲማቲክስ


ኢንጂነሪንግ

ኤሌክትሮኒክስ እና ኮሚኒኬሽን ኢንጂነሪንግ

ኮምፒዩተር ሳይንስና ኢንጂነሪንግ

ሶፍት ዌሪ ኢንጅነሪግ

ማንኛውንም ዩኒቨርሲቲውን የተመለከቱ መረጃዎችን ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያሉ መገናኛ


መንገዶች አባል በመሆኑ ይከተሉ፣ይውደዱ እንዲሁም ያጋሩ፡፡

1) የዩኒቨርሲቲው ዌብሳይት አድራሻ፡ http://www.astu.edu.et/

2) የዩኒቨርሲቲው ኦፊሲያል ፌስቡክ አድራሻ፡ https://www.facebook.com/astu.offical

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

You might also like