You are on page 1of 30

በየደረጃዉ ያሉ ትምህርት ተቋማት ኮቪድ -19 ወረሽኝን

ከመከላከል አንጻር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ምን ደረጃ


ላይ እንዳሉ ለማወቅ የተደረገ የዳሰሳ ጥናት ሪፖርት

ህዳር፣ 2013
ባህር ዳር፣ኢትዪጲያ
1. የቡድኑ አባላት ስም ዝርዝር

ተ.ቁ ስም የሚሰሩበት ተቋም ምርመራ

1 ህብስት አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

2 ስማቸዉ አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ቴክኒክና ሙያ ቢሮ

3 ተከተል ጡሜቦ ከአፍሪካ ህብረት ሲዲሲ(through FMOH/EPHI) AU-CDC


የቡድን አባላት ፎቶ
የቡድን አባላት ፎቶ
የቡድን አባላት ፎቶ
2. በዳሰሳ ጥናቱ የተካተቱ ተቋማት
 የተመረጡ 13 የትምህር ተቋማት ከአዊ ብሔረሰብ
ዞን፤ምዕራብ ጎጃም እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች በዚህ ዳሰሳ
ጥናት ተካቱዋል፡፡
12 የትምህርት ተቋማትን ለመስራት አቅደን 13 ማሳካት
ችለናል፡፡ በዚሁ መሰረት ሁለት መምህራን ማሰልጠኛ
ኮሌጅ፤2 ቴክኒክና ሙያ ማስልጠኛ ኮሌጅ ፤5 አንደኛ ደረጃ
እና ሙሉ ሣይክል ት/ቤት(1-8) እና 4 አጠቃላይ ከፍተኛ
2ተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ት/ቤቶቸ በአጠቃላይ 13 ተቋማት
በዳሰሳ ጥናቱ ተካቱዋል፡፡
አዴት ቴ/ሙ ኮሌጅ የተጎበኘ ብሆንም በወቅቱ ማግኘት ግን
አልተቻለም
በዳሰሳ ጥናት የተካተቱ ተቋማት ስም ዝርዝር
ተ. ስም ዞን ወረዳ

1 ዱርቤቴ መሰናዶ ት/ቤት ምዕራብ ጎጃም ደ/አቸፈር

2 አሁሪ አንደኛ ደረጃ እና ሙሉ ሣይክል ት/ቤት(1-8) ምዕራብ ጎጃም ደ/አቸፈር

3 ጋፋት አንደኛ ደረጃ እና ሙሉ ሣይክል ት/ቤት(1-8) ምዕራብ ጎጃም ይልማና ዴንሳ

4 አዴት አጠቃላይ ከፍተኛ 2ተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ት/ቤት ምዕራብ ጎጃም ይልማና ዴንሳ

5 አፍራ አንደኛ ደረጃ እና ሙሉ ሣይክል ት/ቤት(1-8) አዊ አዲስ ቅዳም


የቀጠለ………
ተ. ስም ዞን ወረዳ

6 አዲስ ቅደም ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አዊ አዲስ ቅዳም

7 እንጅባራ አጠቃላይ ከፍተኛ 2ተኛ አዊ እንጅባራ ከተማ


ደረጃ እና መሰናዶ ት/ቤት

8 እንጅባራ መምህራን ማሰልጠኛ አዊ እንጅባራ ከተማ


ተቋም

9 አማኑኤል ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ምስራቅ ጎጃም ማቻከል

10 አማኑኤል አጠቃላይ ከፍተኛ 2ተኛ ምስራቅ ጎጃም ማቻከል


ደረጃ እና መሰናዶ ት/ቤት
የቀጠለ ……………
ተ.ቁ ስም ዞን ወረዳ

11 ቀራር አንደኛ ደረጃ እና ሙሉ ምስራቅ ጎጃም ማቻከል


ሣይክል ት/ቤት(1-8)

12 ንጉስ ተክሌ ኃይማኖት አንደኛ ምስራቅ ጎጃም ደ/ማረቆስ ከተማ


ደረጃ እና ሙሉ ሣይክል
ት/ቤት(1-8)

13 ደብረ ማርቆስ መምህራን ምስራቅ ጎጃም ደ/ማረቆስ ከተማ


ማሰልጠኛ ተቋም
3. የዳሰሳ ጥናቱ ዋና አላማ
 የዳሰሳ ጥናቱ ዋና አላማ በተመረጡ የትምህርት
ተቋማት ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል
የተቀመጡትን ፕሮቶኮሎች በማሟላት የመማር
ማስተማሩ እየተከናወነ መሆኑን ማረጋገጥ እና
በየደረጃው ያለው ባለድርሻ አካላት የቅንጅት ስራ
ምን እንደሚመስል የዳሰሳ ጥናት በማድረግ
በተገኘው ግኝት መሰረት ለግብረ ሃይሉ ቀጣይ
መወሰድ ያለባቸውን የመፍትሄ አቅጣጫዎች
ለማስቀመጥ የሚያስችል ግብዓት ለአማራ ብሔራዊ
ክልላዊ መንግስት ኮቪድ-19 መከላከል ግበረ-ኃይል
ለማቅረብ ነው::
4. የዳሰሳ ጥናቱ ዉጤት(Results)
ዳሰሳ ጥናቱ ዉጤት(Findings) ቀጥሎ ባለዉ ክፍል
ቀርቡዋል፡፡
A.አደረጃጀትን በተመለከተ የተገኘ ዉጤት
አደረጃጀትን በተመለከተ ከታዩት 13 ተቀማት ዉስጥ፡-
 ከ13 ተቋማት ከአንድ ተቋም ባስተቀር(አማኑኤል ቴክኒክና ሙያ
ኮሌጅ) 12ቶቹ(92.3%) ግብረ-ኃይል አቀቀሙዋል፡፡ በሁሉም
ተቋማት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ላይ ዉስንነት አለባቸዉ፡፡
 በሁሉም 13(100%) ተቋማት ኮቪድ-19 በተመለከተ የተዘጋጀ
እቅድ (ከድርጊት መርሐ-ግብር ጋር) የለም፡፡
 ከተጎበኙት ተቋማት 9ኙ ተቋም(69.2%) ፎካል ሰዉ በተቋም ደረጃ
መድባዋል፡፡ አረት ተቋማት(30.8%) ማለትም አፍራ አንደኛ ደረጃ
እና ሙሉ ሣይክል ት/ቤት(1-8) ፣ አዲስ ቅደም ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ
፣ ቀራር አንደኛ ደረጃ እና ሙሉ ሣይክል ት/ቤት(1-8) ፤ ንጉስ ተክሌ
ኃይማኖት አንደኛ ደረጃ እና ሙሉ ሣይክል ት/ቤት(1-8) ፎካል ሰዉ
አልመደቡም፡፡ በሁሉም ተቋማት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ
ላይ ዉስንነት አለ፡፡
 በሁሉም 13 ተቋማት (100%) ከጤና ሴክቴር ኮቪድ-19 ፎካል ሰዉ
አልተመደበም፡፡
B.የግብዓት አቅርቦትና ንጽህና አጠባበቅ
በተመለከተ የተገኘ ዉጤት
የግብዓት አቅርቦትና ንጽህና አጠባበቅ በተመለከተ
የተገኘ ዉጤት፤ ከታዩት 13 ተቋማት ዉስጥ፡-
 በተጎበኙበት ወቅት 7(53.8%) ተቋማት የዉሃ
እጥረት እንደገጠማቸዉ ሲነግሩን በሌላ በኩል
6(46%) ተቋማት የዉሃ እጥረት እንዳልገጠማቸዉ
ተናግሩዋል፡፡ ነገር ግን በሁሉም 13(100%) ተቋማት
የዉሃ አቅርቦት ዉስንነት አለ ማለት ይቻላል፡፡
የግብዓት አቅርቦትና ንጽህና አጠባበቅ በተመለከተ
የተገኘ ዉጤት፤ ከታዩት 13 ተቋማት ዉስጥ፡-
 በሁሉም 13(100%) ተቋማት የፊት
ጭምብል/አፍና አፍንጫ መሸፈኛ በአግባቡ
የመጠቀም ቸግር አለባቸዉ
 ሁሉም 13 (100%) ተቋማት በአግባቡ እጅ
የመታጠብ ችግር አለባቸዉ፡፡
 ሁሉም 13 (100%) ተቋማትአካላዊ ሪቀትን
የመጠበቅ ችግር(ክፍል ዉስጥ እና ከክፍል ዉጭ)
ታይቶባቸዋል፡፡
የግብዓት አቅርቦትና ንጽህና አጠባበቅ በተመለከተ
የተገኘ ዉጤት፤ ከታዩት 13 ተቋማት ዉስጥ፡-
 6(46%) ተቋማት 1 ለ 30 የተማሪ ክፍል ጥምርታ
ማድረግ ላይ ዉስንነት ያለባቸዉ ሲሆን 7ቶቹ ጥሩ
የሚባል ደረጃ ላይ ናቸዉ፡፡
የግብዓት አቅርቦትና ንጽህና አጠባበቅ በተመለከተ
የተገኘ ዉጤት፤ ከታዩት 13 ተቀማት ዉስጥ፡-
 9(69.2%) ተቋማት በአግባቡ አንድ ወንበር ለአንድ
ተማሪ አድርጎደ ስጠቀሙ 4 ተቀማት ግን አንድ
ወንበር ለአንድ ተማሪ አድርጎ የመጠቀም ቸግር
ያለባቸዉ ናቸዉ፡፡
 ሁሉም 13 (100%) ተቋማት የደረቅ እና ፈሳሽ ቆሻሻ
ማስወገጃ አዘጋጅቶ በአግባቡ የመጠቀም ችግር
አለባቸዉ፡፡ሁሉም ት/ቤቶች ጉድጓድ አላቸዉ፡፡
ሁሉም ላይ ቅርጨት ክፍል ዉስጥ የለም፡፡ ለፅዳት
ትኩረት አልተሰጠም ከኮቪድ አንጻር፡፡
የግብዓት አቅርቦትና ንጽህና አጠባበቅ በተመለከተ
የተገኘ ዉጤት፤ ከታዩት 13 ተቀማት ዉስጥ፡-
 5(38.5%) ተቋማት የሙቀት መለኪያ ያላቸዉ ሲሆን
ነግረ ግን ተማሪዎች ሁል ጊዜ እየተለኩ ወደ ግቢ
መግባት ላይ ዉስንነት አለ፡፡
 5(38.5%) ተቋማት ጊዜያዊ ለይቶ ማቆያ ክፍል
አዘጋጅቱዋል፡፡
C. ስልጠናን በተመለከተ
ኮቪድ-19 ስልጠና በተመለከተ የተገኘ ዉጤት፤በዳሰሳ
ጥናቱ ከታካተቱት 13 ተቋማት ዉስጥ፡-
 ሁለት ተቋማት(15.4%) ብቻ በጤና ባለሙያ
ለግቢዉ ማህበረሰብ/ተማሪዎች ኦሬንቴሺን
ተሰጥቱዋል፡፡ እነሱም እንጅባራ መምህራን
ማሰልጠኛ ተቋም እና አዴት አጠቃላይ ከፍተኛ
2ተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ት/ቤት ናቸዉ፡፡
 በሁሉም 13(100%)ተቋማት ኮቪድ-19 ላይ አግባብ
ያለዉ ስልጠና አልተሰጠም፡፡
D.ተግባቦት እና ቅስቀሳን በተመለከተ የተገኘ
ዉጤት
ተግባቦትና ቅስቀሳን በተመለከተ የተገኘ ዉጤት፤ ከታዩት 13
ተቋማት ዉስጥ፡-
 2 ተቋማት (15.4%) ብቻ (እንድ ተቋም ባኔር ግቢ መግቢያ
ላይ እና አንድ ሌላ ተቋምደግሞ ብሩሼር በማዘጋጀት መጠቀም
ችሉዋል)፡፡
 አንድ ተቋም ብቻ ከሚዲያ በዉሰድ (ከአሸም ቲቪ) የትምህርት
ቤቱን የሚኒሚዲያ ክበብ በመጠቀም የግንዛቤ ፈጠራ ስራ
ይሰራል፡፡(እንጅባራ መሰናዶ ት/ቤት)
 12ቹ ተቋማት(92.3%) ምንም የሚኒሚዲያ ክበብ በመጠቀም
የሚሰጥ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ አልሰሩም፡፡
 13ቱም ተቋማት ላይ መማር ማስተማር ከመጀመሩ በፊት
በመምህራን በየክፍሉ ስለ ኮቪድ-19 የጥንቃቄ መልክት
አያስተላልፉም፡፡(ሁሉም ጋር የለም ከዉይይት ባስተቀር)
E. ከቢሮ የወረዱ የተለያዩ ሰነዶችን
በተመለከተ፣
ከቢሮ ወደ ተቋማት የወረዱ የተለያዩ ሰነዶችን በተመለከተ
የተገኘ ዉጤት፤ ከታዩት 13 ተቋማት ዉስጥ፡-
 ሁሉም 13(100%) ተቋማት ከቢሮ የወረደ የአሰራር
መመሪያ/የኮቪድ-መከላከል ጋይድላይን አላቸዉ፡፡ ነግር
ግን መመሪያዉን ወደ ተግባር መቀየር ላይ ከፍተኛ
ዉስንነት አለባቸዉ፡፡
 2(15.4%) ተቋማት ብቻ የውስጥ ደንብ በማዘጋጀት
መፈራራም ችሉዋል፡፡(አንድ ተቀም ከመምህራን ጋር
ብቻ እና አንዱ ደግሞ ከተማሪዎች፤ከመምህራን እና
ከተማሪ ወላጆች ጋር ተፈራርሙዋል)
 13ቱም ተቋማት ማህበረሰብ ስለ ኮቪድ-19 የተሳሳተ
ግንዛቤ አለ ተብሎ በት/ቤቱ አመራር ተገልጹዋል፡፡
5.ያጋጠሙ ችግሮች
 ለተወሰኑ ተማሪዎች ብቻ ማስክ መቅረቡ ለምሳሌ 8ተኛ
እና 12 ክፍል ተማሪዎች መቅረቡ በሌሎች ተማሪዎች እና
አስተማሪዎች ቅሬታ መፍጠሩ
 የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን ለተመግበር
መምህራን ለተማሪዎች ሞዴል ሆኖ ያለመገኘት
 በአንዳንድ/በአብዛኛዉ ተቋማት የዉሃ እጥረት መኖር
 1 ለ 30 ተማሪ ክፍል እና 1 ወንበር ለ 1 ተማሪ
ጥመርታ ለመተግበር መቸገር እና መምህራን ላይ ጫና
መፍጠሩ መማር ማስተማሩ የተረጋጋ እነዳይሆን
አድረጉዋል
 የአካባቡ የጤና ሴክቴር ት/ቤቶች በአግባቡ ያለማገዝ
የቀጠለ………….
 ከትምህርት ተቋማት ዉጭ ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎች መዘናጋት
ይህንንም ተማሪዎች/ኢስታፍ ሞዴል ማድረግ እና አፈጻጻም ላይ
ችግር መፍጠር
 በሦስት ፈረቃ እና በቀን ፈረቃ የሚሰጠዉ ትመህረት በትምህርት
ጠራት ላይ ጫና እያሳደረ መሆኑ፡፡
 አብዛኛቹ መምህራን ለጡረታ የተቃረቡ በመሆናቸዉ በሙሉ አቅም
በረካታ ክፍለ ጊዜያት ለማስያያ መቸገር(ንጉስ ተ/ሓይማኖት ት/ቤት)
 የጦዋት ፈረቃ 1፡30 ተኩል ስለሚጀምር ከገጠር የሚመጡ
ተማሪዎች በተደጋጋሚ መዘገየት እና ከሰዓት በኃላ 3ተኛ ፈረቃ ሲሆን
ወደ ቤታቸዉ ስመለሱ ለሴት ተማሪዎች ስጋት መሆን፡፡
 የበጀት ችግር መኖር
 ለኮቪድ-19 መስፋፋት ምክንያት የሆኑ ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ
ተስፋ መቁረጥ( ለምሳሌ ከፍተኛ የተማሪ ቁጥር ያለቸዉ ት/ቤቶች እና
ኮሌጆች ሙቀት መለካት እና እጅ መታጠብ መቋረጥ)
6.ከትምህርት ተቋማት የተሰጡ አስተያየቶች
 የፊት ጭምብል ወጥ በሆነ መልኩ ለሁሉም ተቋማት
ብሰራጭ
 የትመህርት ቤት አከፋፋት መመሪያ ወጥ በሆነ
መልኩ ብተገበር
7.ከቡድኑ የተሰጡ አስተያየቶች
(Recommendations)
 በተደረገዉ ዳሳሳ ጥናት መሰረት ትምህርት ቤቶች
ኮቪድ-19ን ለመከላከል የወጡ መመሪያዎች
በትክክል እየተገበሩ ስላልሆነ የሚመለከተዉ ክፍል
ትኩረት ብሰጥበት
 በመረጃ የተደገፈ ግበርኃይል ያለማቋቋም፡፡ ይህ ችግር
በሰፊዉ ታይቱዋል(ከ ሁለተ ት/ቤት ዉጭ)
 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከንጽህና አኳያ የከፋ ችግር አለ፡፡
በተለመደዉ ንጽህና አጠባበቅ መንገድ ኮቪድ-19
የመከላከል ስራ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡
8.በዳሰሳ ጥናቱ መሰረት የተደረሰ ድምዳሜ
(Conclusion)

 በተደረገዉ ዳሳሳ ጥናት መሰረት ትምህርት ቤቶች


ኮቪድ-19ን ለመከላከል የወጡ መመሪያዎች በትክክል
እየተገበሩ አይደሉም ማለት ይቻላል፡፡ስለዚህ
ማንኛዉም የሚመለከተዉ ዉሳኔ ሰጭ አካል የኮቪ-19
መመሪያ/ጋይድ-ላይን በት/ት ተቃማት ተግበራዊ
እንድደረግ የበኩሉን ሚና መወጣት አለበት፡፡

You might also like