You are on page 1of 92

ይሄነው ማስተዋል የአሽከርካሪዎች ማሠልጠኛ ተቋም

ኃ/የተ/የግ/ማህበር

የተሸከርካሪ ልዩ ልዩ ክፍሎች

1
የተሸከርካሪ ልዩ ልዩ ክፍሎች የሚባሉት
 የተሸከርካሪ እንቅስቃሴ መቆጣጠሪ ያ ክፍሎች
 የተሸከርካሪ መገናኛ መሳሪያዎች
 የተሸከርካሪ ትዕይንት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች
 የዳሽቦርድ ጠቀሚ ጌጆች
 የዳሽቦርድ ጠቀሚ መብራቶች
 የደህንነት መጠበቂያ መሳሪያዎች
 የምቾት መጠበቂያ መሳሪያዎች
 የስርቆት መከላከያ መሳሪያዎች

2
የተሸከርካሪ እንቅስቃሴ መቆጣጠሪያ መሳሪያ

ተሸከርካሪን በማሽከርከር ላይ በቀላሉ ተቆጣጥሮ


ማሽከርከር የሚያገለግሉ ክፍሎች ናቸው
እነርሱም፡-
 የሞተር ማስነሻ ቁልፍ
 የነዳጅ መስ ፔዳል
 የፍሪሲዮን ፔዳል ከ ማርሸ ዘንግ ጋር
 መሪ
 ፍሬን

3
የተሸከርካሪ መቆጣጠሪያ መሳሪያ

የሞተር ማስነሻ ቁልፍ የኤሌትሪክ ኃይልከባትሪ ወደ


ተለያዩ ክፍሎች እንዲተላለፉ ያደረጋል፡፡
የነዳጅ መስጫ ፔዳል የተሽከርካሪን ፍጥነት ለመጨመር
እና ለመቀነስያገለግላል፡፡
የፍሪሲዮን ፔዳል ከማረሽ ዘንግ ጋር አገልግሎቱ ማርሽ
ለመጨመር እና ለመቀነስ ያገለግላል፡፡
መሪ የተሸከርካሪ አቅጣጫ ለመቆጣጠር ያገለግላል
 ፍሬን ተሸከርካሪን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ያገለግላል

4
የመገናኛ መሣሪያዎች
አሽከርካሪዎች ሊያደርጉ የፈለጉትን አስቀድመው
የሚያሳውቁባቸው እና ከሌሎች ጋር መረጃ
የሚለዋወጡባቸው ናቸው
 የግንባር መብራት(head lamp)
 የፍሬን መብራት(stop light)
 የኋላ ማርሽ መብራት(backup light)
 የታርጋ መብራት (license plate light)
 የማቆሚያ መብራት(parking light)
 የአደጋ ጊዜ መብራት(hazard light)
 የጎን መብራት (side light)
 ፍሬቻ መብራት(signal light)
 ጡሩንባ(ክላክስ)/horn/

5
የመገናኛ መሣሪያዎች
 የግንባር መብራት አሽከርካሪ ለሌላኝው
አሽከርካሪ መልዕክትን ለማስተላለፍ
የሚጠቀምበት ሲሆን
ይህን ለማድረግ አጭር ረጅም አበራሩን እንዲቀያየር
በማድረግ ሲሆን መልዕክቶቹ
 ከፊት የሚመጣው ተሸከርካሪ

መስመሩን እንዲያስተካክል ለማሳወቅ


 ከፊት የሚመጣው ተሸከርካሪ የመብራቱን

አበራር እንዲያስተካክል ለመጠየቅ


 ከፊት ያለን ተሽከርካሪ ቅድሚያ

እንዲሰጠን ለመጠየቅ የሚገልጽ ነው

6
 የማቆሚያ መብራት ከኃላ ደብዘዝ ባሉ ቀይ እንዲሁም ከፊት
ደብዘዝ ባሉ ነጭ መብራቶች የሚገለፁ ናቸው
 ተሸከርካሪ በምሽት ወቅት መኪናን ስናቆም መኪናን
እንደቆመ ለሌሌች አሽከርካሪዎች መልእክት ለማስታለፍ
ያገለግላል
 የኋላ ማርሽ መብራት ከኃላ በኩል በነጭ ቀለም
የሚበራ መብራት የሚበራው የኃላ ማርሽ ሲገባ
የሚበራ ሲሆን ተሸከርካሪው ወደ ኃላ እየተጋዘ
መሆኑን ያመለክታል
 የፍሬን መብራት ከተሸከርካሪው የኃለኛው ክፍል ላይ በቀይ
አሽከርካሪው የተሽከርካሪውን የሚበራ ሲሆን ከኃላ ለሚከተሉ
ተሸከርካሪዎች ፍጥነት እየቀነሰ መሆኑን ያመለክታል
 የሰሌዳ መብራት ከኃላ በኩል ያለው ስሌዳ ላይ
በመብራት የተሸከርካሪውን የአገልግሎት ዓይነት እና
መለያ ቁጥሩን ለማሳወቅ ያገለግላል

7
የመገናኛ መሳሪያዎች
 የማስጠንቀቂያ መብራት በአራቱም አቅጣጫ ከፊት ከጉን ከኃላ
በኩል ያሉ
ቢጫ መብራቶች እኩል ብርት ጥፍት እያሉ ሲታዩ ሲሆን
የምንጠቀመው
 መኪና በብልሽት በሚቆምበት ወቅት ለሌሌች
አሽከርካሪዎች ለማሳወቅ ያገለግላል
 ተቀጣጣይ ጭነቶችን የጫነ ተሸከርካሪ ስናሽከረክር
 ሰሌዳ የሌላቸውን ተሸከርካሪዎች ከወደብ ወደ ጉምሩክ ሲንቀሳቀሱ
 የአደጋ አገልግሎት ተሸከርካሪ ለአገልግሎት ሲንቀሳቀሱ
 ጭጋጋማ በሆነ የአየር ሁኔታዎች ውስጥ ስናሽከረክር እንጠቀማለን
 የጎን መብራት በረጃጅም ተሸከርካሪዎች ላይ በቢጫ ቀለም
የሚበራ ሲሆን አገልግሎቱ በመስቀለኛ መንገድ ላይ
የተሸከርካሪውን ርዝመት ለሌሎች አሽከርካሪዎች የሚያሳሰሰ
ነው

8
ፍሬቻ

 የግራ ፍሬቻ  የቀኝ ፍሬቻ


 ከቆምንበት ለመነሳት  ለመቆም
 ወደ ግራ ለመታጠፍ  ወደ ቀኝ ለመታጠፍ
 ረድፍ ከቀኝ ወደ ግራ  ረድፍ ግራ ወደ ቀኝ
ለመቀየር ለመቀየር
 ከፊት ያለን ተሸከርካሪ  ከኅላ ያለን ተሸከርካራ
ለመቅደም ለማስቀደም

9
መገናኛ መሳሪዎች
 ጡርንባ(ክላክስ) ድምፅ አማካኝነት መልዕክት
የሚያሰተላልፍ መሳሪያ ነው
 የምንጠቀመው ተሸከርካሪ በፍሬን መቆም የማይችልበት
ሁኔታ ሲፈጠር
 እግረኞች በተሸከርካሪ መንቀሳቀሻውስጥ ገብተው ሲገዙ
 ለእይታ ግልፅባልሆኑ መንገዶች ላይ ስናሽከረክር ከተቃራኒ
አቅጣጫ የሚመጣውን ለማስጠንቀቅ ናቸው
 ሁለት ዓይነት አሰራሮች ሲኖረት እነርሱም
1.በኤሌክትሪክ
2.በታመቀ አየር የሚሰሩ ናቸው

10
የአምፓል ዓይነቶች 11
የትዕይንት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች
የተሸከርካሪ ከፊት ከኃላ እንዲሁም ከጎን ያለውን እንቅስቃሴ
ለመቆጣጠር የሚያገለግሉ መሳሪያ ነው፡፡
እነርሱም
 የግንባር መብራት
 አጭር የግንባር መብራት
 ረጅም የግንባር መብራት
 የግንባር መስታወት
 የዝናብ መጥረጊያ
 የጎን ማያ መስታወት(ስፖኪዮ)
 የጋቢና ውስጥ መብራት
 የፀሃይ ጨረር መከላከያ
 የኋላ መስታወት
 ጭጋግ መስለቀቂያ

12
የትዕይንት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች
 የግንባር መብራት በምሽት ወቅት አሽከርካሪዎች ዕይታን
ለመቆጣጠር ይረዳል
 የግንባር መስታወት አሽከርካሪው በተለያየየ የአየር ሁኔታዎች
እይታውን እንዳይጋርደው ያደርጋል
 የዝናብ መጥረጊያ የግንባር መስታወት በዝናብ እንዲሁም
በጭቃ በሚሸፈንበት ወቅት ለመፅዳት ተሰገለግላል
 የጎን መመልከቻ መስታወት በተሸከርካሪውን በጎን በኩል
ያለውን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ያገለግላል
 የፀሃይ ጨረር መከላከያ ተሸከርካሪውን ወደ ፀሀይ አቅጣጫ
ሲያሽከረክከር ጨረርን ለመከካለል ይረዳል

13
የትዕይንት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች
 የጭጋግ ማቅለጫ ፡- በኃለኛው መስታወት ላይ
በመገጠም የኤሌክትሪክ ኃይልን ወደ ሙቀት ኃይል
በመቀየር መስታወቱን ከጉም የሚያስለቅቅ ነው
 የጋቢና ውስጥ መብራት :- አሽከርካሪው
የተሽከርካሪው ውስጥ በመሆን የተለያዩ ሥራዎችን
ማከናወን ሲፈልግ የሚጠቀመው መብራት ነው

14
11 November 2017
15
የዳሽ ቦርድ ጠቀሚ ጊጆች
 ኦዶ ሜትር
 ስፒዶ ሜትር
 ትሪፕ ኦዶ ሜትር
 ታኮ ሜትር
 የሞተር ሙቀት ጠቋሚ ጌጅ
 የነዳጅ ጠቋሚ ጌጅ
 የባትሪ ቻርጂንግ ጠቋሚ ጌጅ
 የዘይት ግፊት ጠቋሚ ጌጅ
 የዘይት ፍሬን ጠቋሚ ጌጅ

16
የዳሽ ቦርድ ላይ ያሉ ጠሚ ጌጆች
የዳሽ ቦርድ ጠቀሚ ጌጆች

ስፒዶ ሜትር ተሸከርካሪው


በሰዓት እየተገዘበት ያለውን
ፍጥነት ለአሽከርካሪው
እየመዘገበ የሚያሳይ ነው

ኦዶ ሜትርተሸከርካሪው
መነዳት ከጀመረበት ጊዜ
ጀምሮ የሄደውን ኬ.ሜ
የሚመዘግብ ነው

ትሪፕ ካውንተር ኦዶ ሜትር


ተሸከርካሪው በአንድ ጉዞ
ምን ያህል ኪ.ሜ እንደተገዘ
የሚያሳይ ነው

18 18
የዳሽ ቦርድ ጠቀሚ ጌጆች

ታኮ ሜትር ሞተሩ በደቂቃ ምን ያህል


እየዞረ እንደሆነ ለአሽከርካሪው በቀለም እና
በቁጥር የሚያሳይ ነው

 የነዳጅ መጠን ጠቀሚ ጌጅ በነዳጅ


መያዘ ጋን ውሰጥ ያለውን የነዳጅ
መጠን ያመለክታል

19
የዳሽ ቦርድ ጠቋሚ ጌጆች

 የፍሬን ንፍስ መጠን ጠቀሚ ጌጅ


በንፋስ በሚሰራ የእግር ፍሬን
ባለቸው ተሸከርካሪዋች ላይ የሚገኝ
ሲሆን አገልግሎቱም በአየር
ማጠራቀሚያ ውስጥ ያለውን የንፋስ
መጠን ለአሽርካሪው የሚያሳይ ነው

 የሞተር ሙቀት ጠቀሚ ጌጅ


የሞተር ሙቀት መጠን ለአሽከርከሪው
ያሳያል

20
የዳሽ ቦርድ ጠቀሚ ጌጆች
 የባትሪ ቻርጂንግ ጠቀሚ ጌጅ
የባትሪ ቻርቺንግ ሁኔታን
ለአሽከርካሪው የሚያሣይ ነው

 የሞተር ዘይት ግሪት ጠቀሚ


የሞተር ዘይት ስርጭትን
ግፊትን አሽከርካሪው
የሚያሳይ ነው

21
ዳሽ ቦርድ ላይ ያሉ ጠቋሚ መብራቶች

22
ዳሽ ቦርድ ላይ ያሉ ጠቀሚ መብራቶች
 የዳሽ ቦርድ ላይ ያሉ ጠቀሚ መብራት በሦስት
ዓይነት መብራት ይበራሉ
 የሚበሩበትም ቀለሞች
 በቀይ

 በቢጫ (በብርቱካን)

 በአረንጎዴ

 በሰማያዊ(ወይን ጠጅ)

 እነዚህ መብራት አገልግሎታቸው በሁሉም


ተሸከርካሪዎች ላይ ተመሳሳይ እንዲሆን
ተደርጎል

23
ዳሽ ቦርድ ላይ ያሉ ጠቀሚ መብራቶች
 በቀይ የሚበሩ መብራቶች መልእክታቸው
 በተሸከርካሪው የቴክኒክ ክፍል ላይ ከባድ
ችግርን ለመጠቆም
 በተሸከርካሪው ላይ የደህንነት ሁኔታን
ለማስታወስ ወይም ለመጠቆም ያገለግላል
 በቢጫ ወይም በብርቱካን ቀለም የሚበሩ
መልዕክታቸው
 በተሸከርካሪው ላይ መጠገን ወይም
መስተካከል ያለባቸውን ክፍሎች ለመጠቆም
 ከማሽከርከር በፊት መደረገግ ያለትን
ለመጠቆም ያገለግላሉ
 አረንገዲ እና በሰማያዊ የሚበሩ መልዕክታቸው
 የተለያዩ የቴክኒክ ክፍሎች እየሰሩ
መሆናቸውን ይጠቁማሉ

24
በቀይ የሚበሩ
 የሞተር ዘይት ግፊት ጠቋሚ መብራት

- የባትሪ ቻርጂንግ ጠቋሚ

 እግር ፍሬን ዘይት ጠቋሚ መብራት


 የፍሬን ንፋስ መጠን ጠቋሚ መብራት

 የብሬክ ሎክ ማስጠንቀቂቀያ

 የእጅ ፍሬን ጠቋሚ መብራት

25
በቢጫ የሚበሩ የዳሽ ቦርድ ጠቀሚ መበራት
 ቺክ ኢንጅን መብራት

 ግሎ ፕለግ ጠቋሚ

 የጭጋግ ጠቋሚ መብራት

በዘይት የሚሰራ መሪ ጠቋሚ መብራት

26
በአረንገዲ የሚበሩ የዳሽቦርድ መብራቶች

ረጅም መብራት መብራት

የፍሬቻና የማስጠንቀቂያ መብራት ጠቋሚ


መብራት

27
የደህንነት መጠበቂያ መሣሪያዎች

28
የደህንነት መጠበቂያ መሣሪያዎች

 የደህንነት ቀበቶ(seat belt)


 በግጭት ወቅት ከተሸከርካሪው
የተለያየየ ክፍሎች ጋር
በመጋጨት ሊደርስ
የሚችልን ጉዳት
ለመከላከል ያገለግላል

29
የአየር ከረጢት(SRS Air
bag)
በግጭት ወቅት
አሽከርካሪውን
ከተሸከርካሪው ክፍሎች
ጋር እንዳይጋጭ
ይከላከላል

30
የአንገት ማስደገፊያ(Head rest)
በግጭት ወቅት የአሽከርካሪውን
አንገት ከመቀጨት እና
ጭንቅላቱ ከመጎዳት ይከላከላል

ቻይልድ ሎክ (child restrain)


በሩ ከውስጥ እንዳይከፈት ለማድረግ
ያገለግላል

31
የደህንነት መጠበቂያ መሣሪያዎች

 ፓራውልት(bamper)
 የግጭት ኃይልን ለማብረድ ከፍተኛ
አስተዋፅኦ እንዲኖረው ተደርጎ የተዘጋጀ
ነው

32
የምቾት መጠበቂያ መሳሪያዎች
 የምቾት መጠበቂያ መሳሪያዎች አሽከርካሪውና ሌሎች
ተሸከርካሪ ውስጥ ያሉት የመንገድገደኞች በሚጋዙበት
ወቅት ምቾታቸው እንዲጠበቅ ለማድረግ ያገለግላል
 የምቾት መጠበቂያ መሳሪያዎች የሚባሉት
 ወንበር
 የአየር መቆጣጠሪያ
 ቴፕ (ሬድዩ)
 የጎን መስታወት

33
ምቾት መጠበቂያ መሳሪያ

ወንበር አሽከርካሪው
ተሽከርካሪው እንደሚፈለገው
ሁኔታ ማስተካከል እንዲችል
ተደርጎ የተሰራ ነው

34
1 2 3
አሽከረካሪው ወስጥ ያለውን
የአየር መቆጣጠሪያ
አየር ለመቆጣጠር የሚያስችለው ሲሆን
ሦስት መቆጣሪያ መሳሪያዎች አሉት
1.የመጀመሪያው የሚገባውን አየር ሙቅ ወይም ቀዝቃዞ
ለማድረግ የሚመመስችል ነው
2. የአየሩን የሚገባበት ፍጥነት የሚያስተካክልበት ነው
3.አየሩ እንዲያርፍ የተፈለገበትን ቦታ ለማስተካከል ይረዳል 35
ምቾት መጠበቂያ መሳሪያ

 ቴፕ (ሬድዩ) አሽከርካሪው ተሸከርካሪውን


በሚያሽከረክርበት ወቅት ራሱን ለማዝናናት
ያግዘዋል

36
የስርቆት መከላከያ መሳሪያዎች

 የሞተር ማስነሻ ቁልፍ(ignition switch)


 የማንቂያ ደውል (alarm)

37
የማንዋል ዓይነት እና አገልግሉት

 አንድን መሳሪያ አጠቃቀሙን በተመለከተ እንዲሁም


ብልሽቶች ሲከሰቱ ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች
ብልሽቶችን በተመለከተ ለማስተካከል የምንጠቀምባቸው
መመሪያዎችን በተመለከተ መረጃ የሚሰጥ ነው
 በተሸከርካሪዎች ዙሪያ የሚዘጋጁ ማንዎሎች ዓይነት
አምስት ሲሆኑ እነርሱም
 1.ስፔስፊኬሽን ማንዋል
 2. ኦነር(ኦፕሬቲንግ) ማንዎል
 3. ሰርቪስ ማንዋል
 4.ሜንቴናንስ ማንዋል
 5.ስፔርፓርት ማንዋል ናቸው

38
የማንዋል ዓይነት እና አገልግሎት

 ማንወል ማለት አንድን መሳሪያ በተመለከተ


እንዴት መጠቀም እንደሚቻል
ሊደረጉለት ስለሚገቡ ጥንቃቄዎች
ብልሽቶችን በተመለከተ ሊደረጉ ስለሚገባቸው
ክንዋኔዎች መረጃ የሚሰጥ መመሪያ ነው
 በተሸከርካሪ ላይ ማንዋሎች በአምስት ዓይነት ይዘጋጃሉ

 እነርሱም

1. ስፔስፊኬሽን ማንዋል
2. ኦነር(ኦፕሬቲን) ማንዋል
3. ሰርቪስ ማንዋል
4. ሜንቴናንስ ማንዋል
5. ስፔርፓርት ማንዋል

39
የማንዋል ዓይነት

 ስፔስፊኬሽን ማንዋል፡- የተሽከርካሪውን


አጠቃላይ ይዘት(ሁኔታ) መረጃ የሚሰጥ ነው
ለምሳሌ የተሸከርካሪውን ከፍታ ስፋት ርዝመት
 ኦፕሬቲንግ ማንዋል፡-በተሸከርካሪው ላይ ያሉ
አጠቃላይ መሳሪያዎችን አጠቃቀም ለማወቅ ይረዳል
ለምሳሌ የዳሽቦርድ መብራቶች ጌጆች ወንበር
የማስተካከል የመሳሰሉት ናቸው
4

40
የማንዋል ዓይነት
 ሰርቪስ ማንዋል፡-ተሽከርካሪው በአግባቡ አንዲሰራ
ለማድረግ የእንክብካቤ ስራ የምናከናውንበትን ሁኔታ
ይገልል
ለምሳሌ የሞተር ዘይት መቀየሪያን ጊዜ
 ሜንተናንስ ማንዋል፡-የተሸከርካሪውን የተጎዱ ክፍሎች

ወደ ነበረበት ለመመለስ ይጠቅማል


ለምሳሌ የቫልቨ ክፍተቶችን የሲሊንደር ሰፋትልኬት
 የመለዋመጫ ማንዋል የሚያገለግለው ተሸከርካሪ ጥገና
በሚደረግት ወቅት የሚያስፈልጉ ዕቃዎች በተሰጠው
መለያ በሞዴላቸው በሞተር ቁጥር እና በቻንሲ ቁጥር
አማካኝነትፖርት ቁጥሩን ለማወቅ እንድንችል ለማድረግ
4
ያገለግላል

41
የማሽከርከር ስልት
 የማሽከርከር ስልት አንድ
 አሽከርካሪ ራሱን ለጉዞ ዝግጁ ማድረግ
 ተሸከርካሪን ለጉዞ ዝግጁ ስለማድረግ
o የማሽከርከር ስልት ሁለት

 የተሽከርካሪን ሞተር ስለማስነሳት


 ተሸከርካሪን ጉዞ ስለማስጀመር
 ርቀትን ጠብቆ ስለማሽከርከር
 ተሸከርካሪን መቅደምና ማስቀደም
 አቅጣጫን ስለመለወጥ
 ፍጥነትን ጠብቆ ስለማስከርከር
 ወደ ኋላ ስለማሽከርከር
 ባላንስ ስለመስራት
 ተሽከርካሪን ስለማቆም
42
 የተሸከርካሪን ሞተር ስለማጥፋት
የማሽከርከር ስልት
 የማሽከርከር ስልት
አንድ
 አሽከርካሪ ራሱን ለጉዞ ዝግጁ ማድረግ
 ከአልኮል መጠጥ ራስን ማፅዳት
 ከድበርት ከአላስፈላጊ ባህሪያት ራስን ማፅዳት
 የአየር ሁኔታን መረጃን መሰብሰብ
 የጎንና የኃላ መስታወቶችን ማስተካከል
 የአለባበስ ሁኔታን ማስተካከል
 ወንበር ማስተካከል የደህንት ቀበቶን ማስር
 ተሸከርካሪን ለጉዞ ዝግጁ ስለማድረግ
 በተሸከርካሪ ላይ የምናደርገው ፍተሻ በተለያዩ ዘዴዎች ሊከፈል ይችላል
 ውስጣዊና ውጫዊ በመባል
 የተሸከርክሪ ሞተር ከመነሳቱና ከተነሳ በሓላ
 ከጉዞ በፊት በጉዞ ላይ እና ከጉዞ በሓላ በመባል ነው

43
በተሽከርካሪ ላይ የሚደረግ ዝግጅት ዓይነቶች
1.ሞተርን ከማስነሳት በፊትና በሃላ
1.1 ሞተር ከማስነሳት በፊት
 ማለት ሞተር ከመነሳት በፊት የሚደረግ ሲሆን ዘይቶችን ጎማዎችን ማየት
1.2 ሞተር ከተነሳ በኋላ
 ሞተሩ እየሰራ የተለያዩ ድምፆችን በማዳመጥ የሚደረግ የፍተሻ ዓይነት ነው
2.ቅድመ ጉዞ በጉዞ ላይ እና ከጉዞ በኋላ የሚደረጉ ፍተሻዎች
2.1 ቅድመ ጉዞ ፍተሻ
 ተሸከርካሪው ጉዞ ከመጀመሩ በፊት የሚደረግ ነው

2.2 በጉዞ ላይ የሚደረግ


 ተሽከርካሪ በጉዞ ላይ እያለ አሽከርካሪ የስሜት ህዋሳትን በመጠቀም የሚደረግ ነው

2.3 ከጉዞ በኋላ ለሚደረግ


 ተሸከርካሪ ከቆመ በኃላ በጉዞ ላይ የተሰሙ ችግሮችን ላይ የሚደረግ ፍተሻ ነው

3. ውስጣዊና ውጫዊ ፍተሻ


3.1 ውጫዊ ፍተሻ
 ማለት የተሸከርካሪን ውጫዊ ክፍሎች ላይ የሚደረግ ነው

3.2 ውስጣዊ ፍተሻ


 ማለት የተሸከርካሪን ውስጣዊ ክፍሎች ላይ የሚደረግ ነው

44
ዉጫዊ ፍተሻ
 የተሸከርካሪው ውጫዊ አካል ላይ የሚደረግ ፍተሻ ሲሆን
 የሚያፈሱ ክፍሎችን ማየት
 የጎማ ንፋስን ማየት የላሉ የጎማ ብሎኖችን ማየት
 የሞተር ዘይትን መጠን እና ጥራትን ማየት
 የፍሬን የመሪ ዓይቶችን ማየት
 የባትሪ ውኃ መጠንን ማየት
 የባትሪ ተርሚናሎችን ማየት
 የራዲያተር ውሃ ክዳኑ ላይ ቫልቮችን ማየት

 የመብራት ክፍሎችን ማየት

 ተቀያሪ ጎማን ለመለወጥ የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችን ማየት

 የዝናብ መጥሪጊያን ማየትየጎማ ንፋስ መጠንን ማየት


 ጎማ በስለትና ሹል በሆኑ ነገሮች 45

አለመወጋቱን ማረጋገጥ
 የጎማ ማሰሪያ ብሎኖች(ነቶች)
መፈታትና መላላታቸውን ማየት
 የጎማ ጥርስ ማለቅ አለማለቁን ማየት

ውስጣዊ ፍተሻ
የሞተር ዘይት ማየትና መሙላት
 ተሸከርካሪው ቀጥ ያለ ቦታ ላይ መቆሙን ማረጋገጥ
 ከሞተር አካባቢ የሚያፈሱ ክፍሎች መኖራቸውን ማየትና ማረጋገጥ
 ንፁህ ጨርቅ ማዘጋጀት
 የሞተር ኮፈን መክፈት
 ዲፕ ስቲኩን በማውጣት በንፁህ ጨርቅ በመጥረግ መልሶ መክተት
 በድጋሚ በማውጣት የዘይት መጠኑን ላዩ ላይ ባለው
መግለጫ መሰረት ማየት
 የዘይት ውፍረቱን ቅጥነቱን መቆሸሽ አለመቆሸሹን ማየት
 ዘይቱ ከወፈረና ከቆሸሸ መጠኑ ካነሰ መቀየር ያስፈልጋል
46
የሞተር ዘይት መጠንና ጥራት ማያ ዘንግ(ሊቤሎ)

47
የራዲያተር ውሃን መሙላትና ክዳኑን መፈተሸ
 የራዲያተር ክዳንን በመክፈት
 በራዲያተር ውስጥ ፈሳሽ መኖሩን መቆሸሽ
አለመቆሸሹን ማየት
 የራዲያተር ከዳን ቫልቮችና ስፕሪንጎችን
ትክክል መስራቱን ማየት
 ውሃ ወደውጭ መፍሰሱን ማየት
 በሪዘርቨር ውስጥ ውሃ በመተኑ ልክ መኖሩን ማረጋገጥ
 ራዲያተር ውስጥ ውሃ ከሌለው ሞተር
ሳይነሳ መሙላት

48
የራዲያተር ክዳን ራዲያተር

49
ባትሪን ማየት
 የባትሪ ውሃን መጠንን ማየት
 የባትሪ ተርሚናሎችን ማየትና ከላሉ ማጥበቅ
 ባትሪ ሁለት ዓይነት ሲሆኑ እነርሱም
 ሜንቴናንስ ባትሪ እና ሜንቴናንስ ፍሪ ባትሪ ናቸው
 ሜንቲናንስ ፍሪ ባትሪ ከሆነ
 ቀለማቶቹን ማየት
 አረንገዴ - ሰማያዊ
 ነጭ - ነጭ
 ጥቁር - ቀይ

50
51
ውስጣዊ ፍተሻ
 ማለት የተሸከርካሪውን ውስጣዊ አካለት የምንፈትሽበት ሲሆን
 የተሸከርካሪን መቆጣጠሪያ መሳሪያዎችን
 የነዳጅ መስጫ ፔዳልን
 የፍሬን ፔዳልን
 የፍሬሲዩን ፔዳልን
 የትዕይንት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎችን
 የኋላ ማያ መስታወትን
 የጎን ማያ (መስታወት)ስፓኪዮ

52
ውስጣዊ ፍተሻ
በዳሽቦርድ ላይ ያሉ ክፍሎችን ማየት
 ጠቀሚ ጌጆች መስራታቸን ማየት

 ጠቀሚ መብራቶች መስራታቸውን ማየት

 ጡሩንባ መስራቱን ማየት


 መሪው በእንቅስቃሴ ውስጥ መስራቱን ማየት

53
የማሽከርከር ስልት ሁለት
 የተሽከርካሪን ሞተር ስለማስነሳት
 ተሸከርካሪን ጉዞ ስለማስጀመር
 ርቀትን ጠብቆ ስለማሽከርከር
 ተሸከርካሪን መቅደምና ማስቀደም
 አቅጣጫን ስለመለወጥ
 ፍጥነትን ጠብቆ ስለማሽከርከር
 ወደ ኋላ ስለማሽከርከር
 ባላንስ ስለመስራት
 ተሽከርካሪን ስለማቆም
 የተሸከርካሪን ሞተር ስለማጥፋት

54
የተሸከርካሪን ሞተር ስለማስነሳት
 ሞተርን ለማስነሳት
 የእጅ ፍሬን በአግባብ መያዝ
 ማርሽ ዜሮ ማድረግ
 የሞተር ማስነሻ ቁልፍ በአግባብ መሰካትና
የተቆለፈውን መሪ መክፈት
 የሞተር ማስነሻ ቁልፍን ከሎክ ወደ ስታርት
ማዞርና ማስነሳት
 ተሸከርካሪው ለተወሰነ ደቂቃ በራሱ እንዲሰራ ማድረግ
 ለተወሰነ ደቂቃ በአይድል እንዲሰራ ማድረግ

55
ተሽከርካሪው ከቆመበት ጉዞ አጀማመር
 ማየት
 በኋላና በጎን መስታወት(ስፖኪዩ)የአካባቢውንና የትራፊክ ሁኔታን ማየት
 ማርሽ አጠቃቀም
 አነስተኛ ተሽከርካሪዎችን ለማንቀሳቀስ አንደኛ ማርሽ መጠቀም
 ከባድ ተሽከርካሪን ለማንቀሳቀስ ዳገትና ጭነት ሲጭን አንደኛ
ማርሽ መጠቀም ካልጫነ ሁለተኛ ማርሽ መጠቀም
 ፍሬቻ አጠቃቀም
 የፍሬቻ መብራት ማሳየት በተጨማሪም የእጅ ምልክት መጠቀም
 ጉዞ አጀማመር
 ፍሬሲዩን ግማሽ በመልቀቅ ነዳጅ ደገፍ ማድረግ
 የእጅ ፍሬን ማውረድ
 መሪን በማስተካከል ተሸከርካሪው እንቅስቃሴ ሲጀምር ፍሪሲዩን ሙሉ
ለሙሉ
መልቀቅ
56
ርቀት ጠብቆ ማሽከርከር
አንድ አሽከርካሪ ከፊት ካለው ተሸከርካሪ
ርቀቱን ጠብቆ ለማሽከርከር ማስተዋል
የሚገባው
 የተሽከርካሪውን ፍጥነት
 የመንገዱን አጠቃላይ ሁኔታ
 የአካባቢውን አየር በርቀት ማሳየት ሁኔታ
 የተሽከርካሪውን ቴክኒክ ሁኔታ
 የራሳቸውን ጤንነት ሁኔታና ቅልጥፍና ማገናዘብ አለበት
ስለዚህ ማንኛውም አሽከርካሪ የሚከተለውን የማሽከርከር ሥነ-
ስርዓት
 ከሚከተሉት መኪና ቢያንስ 6 ሜትር ወይም የአንድ አውቶብስ
ርዝመት ያክል በመራቅ ማሽከርከር

57
የፍጥነት ሁኔታና የተሸከርካሪ ርዝማኔ
ፍጥነት በኪሎ ሜትር ና በሰዓት ርቀት በሜትር (በመኪኖች ርዝመት)

40-50 ኪ. ሜትር 20 ሜትር የ3 መኪና ርዝማኔ

50-60 ኪ.ሜትር 25 ሜትር የ4 መኪና ርዝማኔ

70-80 ኪ.ሜትር 30 ሜትር የ5 መኪና ርዝማኔ

90-100 ኪ.ሜትር 36 ሜትር የ6 መኪና ርዝማኔ

100-110 ኪ.ሜትር 43 ሜትር የ7መኪና ርዝማኔ


58
የሰከንዶች ህግ
 የሦስት ሰከንዶች ህግ ርቀትን ጠብቆ ለማሽከርከር ዋነኛ መፍትሄ
ነው
 የሦስት ሰከንዶች ህግ ማለት ተሸከርካሪው በሦስት ሰከንድ የሚሄደው
ርቀት ማለት ነው
 ይህ ህግ የተሸከርካሪን ዙሪያለማየት
 በፍጥነት መስመር ለመቀየር

 በድንገት ተሸከርካሪ ቢያቆም ተሸርካሪን ለማቆም ይረዳል

 ከፈት የሚከልል ነገር ካለ ግን ከ3 ወደ 4 ሰከንድ ማሳደግ


 መንገዱ አንሸራታች ከሆነ ወደ 6 ሰከንድ ማሳደግ አለብን

59
ከሦስት ሰከንድ በላይ ርቀት
የሚያስፈልጋቸው ሁኔታዎች
 በአንሸራታች መንገድ ላይ
 ለማየት አመቺ ባልሆነ መንገድ ላይ
 ሞተር ሳይክል ስንከተል
 ተሸከርካሪን በምናስቀድምበት ወቅት
 ተሳቢ ሲኖር ወይም ከባድ ጭነት ስንጭን
 ለማየት የሚያስቸግር ከባድ ተሸከርካሪ ከፈት ለፊት ሲኖር
 በከፍተኛ ፍጥነት ማሽከርከር የሚቻልባቸው መንገዶች ላይ
 የጠጡ ወይም የተምታቱ አሽከርካሪዎች ሲያጋጥሙን

60
ረድፍ አያያዝና ተከታትሎ ማሽከርከር
 በስፖኪዩ አካባቢውን በሚገባ መቆጣጠር

 የያዝነውን ረድፍ ጠብቆ ማሽከርከር

 ፍጥነትን እንደ ትራፊክ ሁኔታ በአግባብ


ማሽከርከር
 ተገቢውን ርቀት በመጠቀም ማሽከርከር
 የፋክክር አነዳድን ማስወገድ

 በመንገዱ ላይ የተቀመጠውን ፍጥነት ወሰን


ገደብን ማክበር

61
ተሸከርካሪን መቅደምና መስቀደም
 ተሽከርካሪን ለመቅደም መደረግ ያለበት ክንዋኔ
 ሁሌም በግራ በኩል ብቻ መቅደም
 ለመቅደም የተከለከለ ቦታ እንዳልሆነ ማየት
 በጎን ማያ ስፖኪዩ ከኋላና ከጎን አለመኖሩን ማየት
 ከፊት በተቃራኒ አቅጣጫ ሌላ ተሸከርካሪ
አለመኖሩን ማየት
 የግራ ፍሬቻ ማሳየት
 ለምንቀድመው ተሸከርካሪ ተገቢውን ምልክት ማሳየት
 ከቀደምን በኋላ ወደረድፍ ለመመለስ የቀኝ ስፖኪዩ ማየት
 የቀኝ ፍሬቻ በማሳየት ወደ ረድፍ መመለስ

62
ተሸከርካሪን መቅደምና ማስቀደም
 ተሽከርካሪን ለማስቀደም መደረግ ያለበት ክንዋኔ
 ለቀድመን የፈለገውን ተሽከርካሪ ፍጥነት
ሁኔታ በስፖኪዩ መመልከት
 ለመስቀደም መፍቀዳችንን ለመግለፅ የቀኝ
ፍሬቻ ማሳየት
 የቀኝ ስፖኪዩን በመጠቀም በቀኝ ረድፍ
ያለውን እንቅስቃሴ በማየት የቀኝ ረድፍን
መያዝ
 የቀደመን ተሸከርካሪ ትክክለኛ ረድፍ
እስኪይዝ ፍጥነትን መቀነስ

63
አቅጣጫን ስለመለወጥ
 አቅጣጫ በሚቀየርበት ወቅት ሊደረግ የሚገባ ክንወኔ
 የአካባቢውን የትራፊክ እንቅስቃሴ
በስፖኪዩ መመልከት
 ፍሬቻ ማሳየት

 ሌሎችን ለአደጋ በማያጋልጥ ሁኔታ


ፍጥነት መቀነስ
 በድጋሚ ስፖኪዩ መመልከትና መንገዱ ነፃ
መሆኑን ማረጋገጥ ተገቢውን ረድፍ መያዝ
 የተሽከርካሪው ፍጥነት በመቀነስ የመሪው
ወደምንፈልግበት አቅጣጫ ማዞር

64
ፍጥነትን ጠብቆ ማሽከርከር
 ፍጥነት ለመጨመር ሆነ ለመቀነስ ትኩረት
የሚሹ ነገሮች
 የመንገዱ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ

 የመንገዱ አሰራር

 የተሸከርካሪው የጭነት ልክ

 የአካባቢው የአየር ሁኔታ

 የትራፊክ ሁኔታ ትኩረት የሚሹ ጉዳዩች ናቸው

65
ወደኋላ ስለማሽከርከር
 ወደ ኋላ ማሽከርከር የሚኖርባቸው ሁኔታዎች
 ወደፊት ለማሽከርከር የማይቻልባቸው
ሁኔታዎች ሲፈጠሩ
 ጠባብ ቦታዎችን ለመውጣት ስንፈልግ

 ተሸከርካሪን አስተካክሎ ለማቆም መሆን አለበት

 ወደ ኋላ ስናሽከረክር

 በጎን ማያ መስታወት ወይም ሰውነትን


በማዞር ማሽከርከረክ
 የኋላ ማርሽማስገባት

 ፍጥነትን በጣም ዘግ አድርጎ ማስከርከር

66
ባላንስ ስለመስራት
 ባላንስ ማለት ተሸከርካሪን በዳገትና ቁልቁለት ላይ
ነዳጅንና ፍሪሲዩን አመጣጥኖ ተሽከርከሪን
ለተወሰነ ሰከንዶች ሳይንሸራተት ማቆም ነው
 የፊትና የኃላ
 ባላንስ አስራሮች
 የፊት ባላንስ ለመስራት
 አንደኛ ማርሽ በመጠቀም ፍሪሲዩንና ነዳጅ
በመጠቀም ወደ ኃላ እንዳይንሸራተት ማድረግ
ነው
 የኋላ ባላንስ ለመስራት
 የኃላ ማርሽ በመጠቀም ፍሪሲዩንና ነዳጅ
በመጠቀም ወደ ኃላ እንዳይንሸራተት ማድረግ ነው
67
በአደገኛ ሁኔታ ስለማሽከርከር
 1 በተለያዩ አካባቢና ወቅት ስለማሽከርከር
 ሀ.በምሽት ጊዜ ስለማሽከርከር
 ለ.በዝናባማና ጭጋጋማ የአየር
ሁኔታ ሰለማሽከርከር
 ሐ.በፀሃያማና ሞቃታማ አካባቢ ስለማሽከርከር
 መ.በተራራማ አካባቢ ስለማሽከርከር
 ሠ.በአባራማ መንገድ ላይ ስለማሽከርከር
 ረ.የጎማ መንሽራተትን ስለመቆጣጠር

68
ሀ.በምሽት ጊዜ ስለማሽከርከር
 በምሽት ማሽከርከር ከቀን የበለጠ ለከፍተኛ
አደጋ የሚያጋልጥ ነው
 ስለሆነም በምሽት ማሽከርከር ላይ ተፅዕኖ
የሚያሳድሩ ነገሮች አሉ
 የሌሎች አሽከርካሪዎች ሁኔታ
 የመንገድ ሁኔታ
 የተሸከርካሪ ሁኔታ ናቸው

69
 የሌሎች አሽከርካሪ ሁኔታ
 ለዚህ ምክንያት የሚሆነው
 በምሽት የማየት ኃይል መቀነስ

 ከብርሃን ወደ ጨለማ ሲገባ ዓይን የማየት


ኃይሉን ለማስተካከል ጊዜ ስለሚወስድ
 ከፊት የሚመጣ ተሸከርካሪ መብራት የማየት
አቅምን ላይ ችግር ስለሚፈጥር
 በምሽት በድካም ምክንያት ንቃት መቀነስ

 የመንገድ ሁኔታ
 በመንገዱ ላይ የመንገድ መብራት አለመኖር
 የተሸከርካሪ ሁኔታ
 የተሽከርካሪ የግንባር መብራት መቆሸሽ
 የግንባር መብራት አበራር አለመስተካከል
70
 በማሽት ስናሽከረክር ልንከተላቸው የሚገቡ
ቅደም ተከተሎች
 መንገድ ከመጀመር በፊት
 የእንቅልቀፍ ስሜት ካለ አለማሽከርከር

 በቂ ረፍት መወሰድ እና ንቁ መሆን

 የተሸከርካሪን መብራቶች መስታዎቶችን ማፅዳት

 የፀሃይ መነፅር አለመጠቀም

 ጉዞ ከጀመርን በኀላ
 ፍጥነትን ቀንሶ ማሽከርከር

 የግንባር መብራት የሌሌችን ዕይታ


እንዳይጋርድ ማድረግ
 ከፊት የሚመጣን ተሽከርካሪ መብራት

አለመመልከት 71
በዝናባማና ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ
 በጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ተሸከርካሪን
ያለማሽከርከር ይመረጣል
 ማሽከርከር ካለብን ግን
 አጭሩን የግንባር መብራት መጠቀም እና
በተጨማሪም የጭጋግ መብራት መጠቀም
 ፍጥነትን መቀነስ
 ከባድ ተሸከርካሪ ሲሆን የጎን መብራት ማብራት
 አደጋን ለመከላከል በጥሩ ንቃት ውስጥ ሆኖ ማሽከርከር
 የግንባር መስታወትን ውጨኛውንና ውስጣዊ
ክፍሎቹን የዝናብ መጥረጊያና የጭጋግ ማስለቀቂያ
በመጠቀም ማፅዳት ያስፈልጋል

72
 በዝናባማ የአየር ሁኔታ ከማሽከርከር በፊት
 ራዲያተር በቂ የማቀዝቀዞ ፈሳሽ ያለው መሆኑን ማየት

 የዝናብ መጥረጊያ እንደሚሰራና የማፅጃ ፈሳሽ


መኖሩን ማረጋገጥ
 ጎማዎች በቂ ጥርስ ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ

 መብራቶች አንፀባራቂ ምልክቶች ንፁህ


መሆናቸውን ማረጋገጥ
 የመስታወቶችን ማፅዳትተስፈልጋለል

 በዝናባማ የአየር ሁኔታ ስናሽከረክር

 ከቆምንበት ስንነሳ በዝግታ ተሸከርካሪን ማንቀሳቀስ

 በሚያንሸራትት መንገድ ላይ በዝግታ ማሽከርከር

 ኩርባ መንገድ ላይ በጥንቃቄ ማሽከርከር

 ጎማ እንዳይንሸራተት ፍሬን በኃይል አለመጠቀም

73
 በሚያንሽራትት መንገድ ላይ ለመቅደም አለመሞከር
 ተሽከርክሪ በጭቃ ከተያዘ የሪዶታ ማርሽን መጠቀም
 በቆመ ወይም እየፈሰሰ ባለ ውሃ ውስጥ አለማሽከርከር
ሐ.በፀሃያማና ሞቃታማ አየር ሁኔታ
ስለማሽከርከር
 በዚህ የአየር ሁኔታ ውስጥ ተፅዕኖ ውስጥ
የሚገቡ ተሽከርካሪ የቴክኒክ ክፍሎች አሉ
 የተሽከርካሪ ጎማ ፣ የሞተር ዘይት፣ እና የራዲያተር
ውሃ ናቸው
 ሰለሆነም ከማሽከርከር በፊት በቂ ውሃ እና ዘይት
መኖሩን ማረጋገጥ
 በማሽከርከር ላይ በየሁለት ሰዓት ወይም በ150 ከ.ሜ
ልዩነት የተሸከርክሪ ግምን ማየት

74
 የሞተር ዘይት ግፊት መለኪያንና የሙቀት
ጠቀሚን በጉዞ ላይ መከታተል
 ተሸከርካሪን በማሽከርከር ላይ ሞተር ከሞቀ
በራዲያተር ላይ ውሃ ለመጨመር
 ሞተር ማጥፋት
 ሞተር እንዲቀዘቅዝ ማድረግ
 የእጅ ገንት ወይም ወፍራም ጨርቅ መጠቀም
 የራዲያተር ክዳንን በመጠኑ ማላላት
ግፊቱን ማስተንፈስ
 ሞተር ማስነሳት
 ውሃ መጨመር

75
መ.በተራራማ ላይ ስለማሽከርከር
 በተራራማ አካባቢ ስናሽከረክር የመሬት
ስበት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል
 ይህንን ለመከላከል
 ከባድ ማርሽ መጠቀም

 በቁልቁለት ላይ እና በዳግት ላይ ጉዞ ከተጀመረ


በኀላ ማርሽ ለመቀየር ስለሚያስቸግር ከባድ
ማርሽ ተጠቅሞ ጉዞ መጀመር
ሠ.በአባራማ መንገድ ላይ ስለማሽከርከር
o ዕይታ በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚቀንስ
o ከፊት ያለን ተሸከርካሪን ለመቅደም አለመሞከር
o የተሸከርካሪ ጎማ መሬት ላይቆነጥጥ
ስለሚችል ፍጥነት መቀነስ
76
ረ.የጎማ መንሸራተትን ሰለመቀነስ
 ይህ ችግር የሚፈጠረው ጎማ መሬትን
መቆንጠጥ ሳይችል ሲቀር ነው
 ለዚህ ችግር አራት ምክንያቶች ሲሆኑ እነርሱም
1. ፍሬንን በኃይል መያዝና ጎማ እንዲቆልፍ ማድረግ
2.የተሸከርካሪ መሪ መዞር ከሚችለው በላይ ማዞር
3.ከሚገባው በላይ ነዳጅ መስጠት
4.ከሚገባው ፍጥነት በላይ ማሽከርከር ናቸው

77
2. በማሽከርከር ላይ ተፅዕኖ የሚያደርጉየተፈጥሮ ህጎች

የመሬት ስበት (Gravity)


ኢነርሻ (Inertia)
ሞመንተም (Momentum)
ኬኒቲክ ሀይል(Kinetic energy)
ፓተንሻል ሀይል(Potential enegy)
ሰበቃ(Friction)
ሴንትሪፊውጋል ሀይል (centerifugal force)
በግጭት ጊዜ የሚኖር ሀይል 8
0

78
የመሬት ሰበት(GRAVITY)
ማለት ሁሉንም ነገሮች ወደ መሬት የሚስብ
ኃይል ነው
ዳገት ስንወጣ ፣ ቁልቁለት ስንወርድ ፣ በፍጥነት
ላይ እያለን ተፅዕኖ ያመጣል
የመሬት ስበት ጎማውን ከመሬት ቆንጥጦ
እንዲይዝ ያደርጋል
ዳገት ሲሆን ፍጥነትን ይቀንሳል
ቁልቁለት ሲወርድ ፍጥነት ይጨምራል

79
 ኢነርሻ(Inertia)
ማለት የሚንቀሳቀሱም ሆነ የቆሙ ነገሮች ሌላ
ተጨማሪ ኃይል
እስካልመጣ ባሉበት ሁኔታ መቀጠል
ይፈልጋሉ
 ሞመንተም(Momentum)
ሁለት የተነጣጠሉ ኃይሎች በአንድ ነገር ላይ በተቃራኒ
አቅጣጫ
ግፊታቸውን ሲያሳርፍ የሚንቀሳቀስበት ነገር የያዘው ኃይል
ነው
 ለዚህ ኃይል መጠን እንደ ተንቀሳቃሽ ነገሩ ክብደት
ፍጥነት
ይወሰናል
 ፍጥነት ሲጨምር ሞመንተም ይጨምራል

 ሞመንተም ሲጨምር የማቆሚያ ርቀት ይጨምራል

 ተሽከርካሪን ስናቆም ሞመንተም የሚቀንሰው


 የፍሬን ሰበቃ

 በጎማና በመንገዱ መካከል ያለው ሰበቃ 80

 የሞተር አቅም ኃይል


 በግጭት ወቅት ሞመንተም ወደ
 ወደ ሙቀት ይቀየራል
 ተሽከርካሪን ወደ ማውደም ይለወጣል
 መንገደኞችን ወደ መጉዳት ይለወጣል
 ኢነርሻን መቆጣጠር ያስቸግራል
 የኪኒቲክ ኃይል(Kinetic energy)
 ማለት በእንቅስቃሴ ላይ ያለ ነገር የሚኖረው ኃይል ነው
 ፍጥነት ሲጨምር ኪኒቲክ ኢነርጂ ይጨምራል
 ክብደት ሲጨምር ኪኒቲክ ኢነርጂ ይጨምራል
 ፍሬን ሲያዝ በሰበቃ ምክንያት ወደ ሙቀት ይቀየራል
 ፖተንሻል ኢነርጂ(Potential Energy)
 ነገሮች ባሉበት ሁኔታ ወይም ቅርፅ የሚኖራቸው የተጠራቀመ
ኃይል ማለት ነው
 ሰበቃ (Friction)
 አንድ ነገር ከሌላ ነገር ጋር ሲነካካ የሚኖረው ኃይል ማለት ነው
81

83
 ሰበቃ
 የተሸከርካሪው ክብደት ሲጨምር ይጨምራል
 ጎማ ሊሾ ሲሆን እና በጣም ሲነፋ ይቀንሳል
 የተሽከርካሪ ጎማ ንፋስ መጠን ሲቀንስ ይጨምራል
 መንገዱ የተሰራበት ነገር ሰበቃን ይጨማራል ወይም ይቀንሳል
 በመንገዱ ሁኔታ ይወሰናል
 ሰበቃ የሚከሰተው
 በመንገድ እና በጎማው መሀከል
 በፍሬን ውስጥ
 በሞተር ውስጥ
 በኃይል አስታላፊ ውስጥ ነው
 ፍሬሲዩን ውስጥ የሚፈጠር ሰበቃ
 ፍሬሲዩን በትክክል ካልተለቀቀ የጎማን መንሽራተት ይፈጥራል
 የፍሬ እና የፍሬሲዪን ክፍሎቻችን እንዳይበሉ
 ፍሬን ይዞ አለማሽከረርከር
 ፍሬሲዩን ይዞ አለማሽከርከር ያስፈልጋል

82
 ሴንትሪፊውጋል ኃይል
 አንድ ነገር በሌላ ዙሪያ ሲሽከረከር ወደ ውጪ የሚጎትተው
ሀይል ማለት ነው
 ይህ ኃይል ከመንገድ ውጭ እየጎተተ አደጋ እንዳይፈጠር
 ማዞሪያው ከመድረሳችን በፊት ፍጥነት መቀነስ
 ፍሬን በስሱ መያዝ
 ከባድ ማርሽ መጠቀም
 ሰፋ አድርጎ ኩርባውን መዞር
 በግጭት ጊዜ የሚኖር ኃይል
 የኪኒቲክ ኃይል ይቀንሳል
 በድንገት ተሸከርካሪው ሲቆም ኬኒቲክ ኃይል ይጨምራል
 አደጋን ለማስወገድ ቁልፍ የሆነው ነገር
 ማድረግ የፈለግነውን ለሌሎች አሽከርካሪዎች ማሳወቅ
 አደገኛ ሁኔታን ማሳወቅ
 ሁልጊዜ አደጋን ተከላክሎ ማሽከርከር

83
ከአደጋ የማምለጥ ስልቶች
 በአደገኛ ሁኔታዎች ላይ አደጋ እንዳይከሰት የሚያደርጉ
ሶስት ስልቶች አሉ
 እነርሱም
 ሀ. መሪ ማዞር
 ለ. በፍጥነት መጨመር
 ሐ. በፍሬን ማቆም
 ከላይ የተጠቀሱትን ስልቶች አሽከርካሪዎች
የሚጠቀሙት እንዳሉበት ሁኔታ እና ሊገጥሟቸው
እንደሚችሉት የአደጋ አይነቶች ነው፡፡

84
ከአደጋ የማምለጥ ስልቶች

 ሀ. መሪ መጠቀም በፍሬን ለማቆም በተሽከርካሪዎች መካከል


በቂ ርቀት ከሌለ መሪን ወደ ቀኝ ወደግራ በማዞር መጠቀም
ያስፈልጋል፡፡
 ለ. ፍጥነት መጨመር በመገናኛው መንገዶች ላይ
እዲሁም ከኋላ አደጋ ሊያስከትል የሚችል ሁኔታ
ሲያጋጥም
አሽከርካሪዎች መጠቀም ያለባቸው ስልት ነው፡፡
 ሐ. በፍሬን ማቆም ይህ ስልት ለመጠቀም በአብዛኛው
አሽከርካሪዎች ከሚከተሉት ተሽከርካሪ ርቀት ሲኖር
ነው፡፡ ምክንያቱም ተሽከርካሪዎች ፍጥነት ጭነት የጎማ
ሁኔታ የተሽከርካሪውን እንሽርት ሊጨምር ስለሚችል
ነው፡፡

85
የተሽከርካሪ አቀም እና ሞተር ስለማጥፈት
 ተሸከርካሪን ለማቆም መደረግ ያለበት ክንዋኔ
 በቀኝ ስፖኪዩ ከኋላ ተሸከርካሪ አለመኖሩን በማረጋገጥ የቀኝ ፍሬቻ
ማሳየት
 የእግር ፍሬን ፔዳል በትንሹ መርገጥ
 በድጋሚ በመሀልና በቀኝ ስፖኪዩ በማየት መሪ ወደቀኝ ረድፍ ማዞር
 በቀኝ እግር ፍሬን ፔዳልን በመርገጥ ፍጥነትን መቀነስ
 የተሸከርካሪው ፍጥነት እየቀነሰ ሲመጣ ሞተር እንዳይጠፋ ፍሬሲዩን
ፔዳል መርገጥ
 መሪ ወደ ቀኝ በማዞር ከመንገዱ ጠርዝ 40 ሳ.ሜ ጠብቆ ማቆም
 ማርሹን ዜሮ ላይ ማድረግ የእጅ ፍሬን መያዝ
 በቅድሚያ የፍረሲዩን ፔዳል ቀጥሎ የእግር ፍሬንና ፔዳል መልቀቅ
 ለትንሽ ደቂቃ በአይደል (በሚኒሞ) ማሰራት

86
ሞተር ስለማጥፈት
 ሞተር ለማጥፈት መደረግ የሚገባው ጥንቃቂ
 የሞተር ማስነሻ ቁልፍ ከኦን ወደ ሎክ

ማዞር
 ተሸከርካሪው ዳገት ላይ ከሆነ የቆመው
አንደኛ ማርሽ ማስገባ
 ተሸከርካሪው ቅልቁለት ላይ ከሆነ የቆመው
የኃላ ማርሽ ማስገባት ያስፈላጋል

87
90

የእሳት ፈጣጠር

88
የእሳት አፈጣጠር
 የእሳት አፈጣጠር ስልጠና ዋና ዓላማ
 አሽከርካሪዎች የእሳት አፈጣጠርን እንዲያውቅ ማድረግ
 የተቀጣጣይ ነገሮች ዓይነትን ለማሳወቅ
 እሳት ለማጥፊያነት የሚያገለግሉ የማጥፊያ ዘዴዎችን
ለይተው እንዲያውቁ ማድረግ
 የእሳት ምድቦችንና ለይተው እንዲያውቁ ማድረግ
 ለእያንዳንዱ እሳት ምድቦች ማጥፊያነት
የሚያገለግሉየመጥፊያ መሳሪያዎች እንዲያውቁ ማድረግ
 እሳት እንዳይፈጠር ሊያደርጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄ ማሳወቅ
ናቸው

89
የእሳት አፈጣጠር
 እሳት ለመፈጠር ሦስት ነገሮች ያስፈልጋሉ
 እነርሱም ፡-
 ተቀጣጣይ ነገሮች(ነዳጅ) ፡-
 ጠጣር፡- እንጨት፡ወረቀት
 ፈሳሽ፡- ቢንዚን፤ናፍታ
 ጋዝ፡- ቡቴን፤ሜቴን
ሙቀት፡- በሰበቃ ሀይል የሚፈጠር

 አየር (ኦክስጅን)፡-የከባቢ አየር

እሳት የማጥፊያ ዘዴዎች


 ማስራብ፤-ተቀጣጣይ የሆኑ ነገሮችን የማሸሽ ዘዴ ነው
 ማፈን፡- በሚነደው እሳት ላይ ተጨማሪ አየር እንዳይገባ
በማድረግ
 ማቀዝቀዝ፡-ተጨማሪ ሙቀት እንዳያገኝ ማድረግ

90
ተቀጣጣይ ነገሮች(እሳት) ምድብ

o ደረጃ 1(የ”ሀ”) ጠጣር፡- እንጨት፡ወረቀት


 የማጥፌያ መሳሪያው ግፊት ያለው ውሀ

o ደረጃ 2 (የ”ለ”) ፈሳሽ፡- ቢንዚን፤ናፍታ


 የማጥፊያ መሳሪያው ድራይ ፓውደር
ካርቦን ዳይኦክሳይድ ፎም
o ደረጃ 3 (የ”ሐ”) በኤሌከትሪክ አማካኝነት
 የማጥፌያ መሳሪያው ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ
ድራይ ፓውደር
o ደረጃ 4 (የ”መ”) ብረታብረት ንጥረ ነገሮች፡- ለምሳሌ
ማግኒዝየም
 የማጥፌያ መሳሪያው ድራይ ፓውደር ደቃቅ አሸዋ

91
ይሄነው ማሰተዋል
አመሰግናለሁ

0913600365

92

You might also like