You are on page 1of 5

ስራ ዕድል ፈጠራ ማለት

ስራ ዕድል ፈጠራ ማለት አስፈላጊውን ጊዜና ጥረት በመጠቀም ሊመጡ የሚችሉ ፈተናዎችን በመቋቋም የራስን ስራ
በመፍጠር የስራውን ውጤት ማጣጣም ማለት ነው፡፡
ስራ ፈጣሪ ማለት ምቹ ሁኔታዎችን በመጠቀም ሀብት ስራ ላይ አውሎ ተጨማሪ ሀብት የማፍራት ችሎታ ሲሆን
ባፈራው ተጨማሪ ሀብት የአኗኗር ለውጥ የሚያመጣ ሰው ማለት ነው፡፡
አንድ ኢንተርፐርነር ማንኛውንም ስራ ከመጀመሩ በፊት በሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ተመስረቶ የራሱን ድከመትና
ጥንካሬ መገምገምና መፈተሸ ይኖርበታል፡፡ እነሱም
የስራ ተነሳሽነት (motivation for work)
በራስ መተማመን (self-confidence)
ወደፊት ማቀድ (plan ahead)
በጥለቀት በመረዳት ላይ ማተኮር (focus on understanding)
በተመረጡ ተግባሮች ላይ ብቻ ማተኮር (be selective)
አከባቢን በጥልቀት መቃኘት (ability to analyze the environment)
የጊዜ አጠቃቀም (time management practice)
ስህተትን መቀበል (admitting mistake)

የስኬታማ ስራ ዕድል ፈጣሪ ባህሪያት


በራስ የመተማመንና እና ጥሩ ነገርን መጠበቅ (self-confidence)
የታሰቡ/የተገመቱ ስጋቶችን መቀበል መቻል (risk taking)
ችግሮችንና መሰናክሎችን በፀጋ መቀበል (risk taking)
ግትር ያልሆነ ከሁኔታዎች ጋር መጣጣም የሚችል (flexable)
የገበያ ዕውቀት ያለው (understanding the market)
ከሌሎች ጋር አብሮ የመስራት ችሎታ ያለው (cooprativness)
በራሱ አመለካከትና አስተሳሰብ የሚመራ
በርካታ ሀሳቦችን ማፍለቅ የሚያሰችል ዕውቀት ያለው (creativity)
በሙሉ ሀይል ፡በጥናቃቄና በስሜት የሚሰራ (usefull potential)
አዲስ ነገርን መፍጠር አዲስ ግኝቶችን የሚፈልግ (inovative)

አብዱልአዚዝ መሀመድአሚን
2011
ስኬታማ ስራ ፈጣሪዎች የምንላቸው

ወደ ውስጥ የሚያይ (Internal locus of control)

የተግባር ሰው (action oriented)

ምቹ ሁኔታዎችን የሚፈልግ (opportunity seeker)

ሀይሉን አሟጦ የሚጠቀም (energetic & forceful)

ከፍተኛ የስኬት ጉጉት ያለው

የአመራር ጥበብ (dynamic leadership)

የአስተዳደር ችሎታ (administrative ability)

የገንዘብ አያያዝ (financial management)

የጊዜ አጠቃቀም (time management)

አስፈላጊ ሰንሰለት (networking)

ጥገኝነትን አለመፈለግ (independent)

የግል ስራ እንዴት መፍጠር ይቻላል

ስራ ፈጣሪዎች ትክክለኛ የግብ አቅጣጫ በመምረጥ ስራ ከመጀመራቸው በፊት ቀጥሎ ለተዘረዘሩት ጥያቄዎች
መልስ ያገኛሉ

ተፈላጊ የመስሪያ ካፒታል ከየት ይገኛል

ምን መስራት ይቻላል

የሙያ ስልጠና ከየት ይገኛል

ምቹ የመስሪያ ቦታ እንዴት ይገኛል

የስራውን ውጤት ተጠቃሚው ማነው

ደንበኞችን እንዴት ማግኘት ይቻላል

ግብር ተከፍሎ እንዴት ትርፋማ መሆን ይቻላል

ስራ ፈጣሪ ለመሆን ራሶዎን ይፈትኑ

የራስዎን ስራ ለመጀመር ከመወሰንዎ በፊት ግላዊ ባህሪዎን፡ሙያዎንን የአከባቢዎን ሁኔታዎች ይፈትሹ፡፡

ድርጅትዎን ለመምራትና ትክክለኛ የስራ ሰው መሆንዎን ለማረጋገጥ ባህሪዎን፡ ሙያዎንና አከባቢዎን


በሚገባ ይገምግሙ፡፡

አብዱልአዚዝ መሀመድአሚን
2011
እያንዳነዱ ሁኔታዎች በድርጅትዎ ላይ በጥንካሬ ይሁን በድክመት የሚያስከተለውን ተፅእኖ ይለዩ፡፡

ድርጅት ለመምራት የሚያስችል እውቀት ካልዎ ጥንካሬ ነው ነገር ግን ውሳኔዎችን ለመወሰን የሌላ ሰው
ድጋፍ የሚያስፈልግዎ ከሆነ ድክመትዎ ነው፡፡

የንግድ ዕቅድ/ቢዘነስ ፕላን ምንድነው

ቢዝነስ ፕላን ማለት ለተወሰነ/ለታሰበ/ ንግድ ስራ ሃሳብን አሰባስቦ በወረቀት ላይ በማስቀመጥ ስራው
እንዴት እንደሚጀመር፡ እንደሚንቀሳቀስ የሚያሳይ በአሀዝ በተገቢው መረጃ የተደገፈ የጽሁፍ ዶክመንት
ከመሆኑ ባሻገር በፕሮጀክቱ አዋጭነት እና አስተማማኝነት ለማወቅ የሚያሰችል መሳሪያ ነው፡፡

ቢዝነስ ፕላን በአጠቃላይ አራት ክፍሎች አሉት እነዚህም

የግብይት ዕቅድ

ምርትና የምርት ሂደት ዕቅድ

የአደረጃጀትና የስራ አመራር እቅድ

የገንዘብ ዕቅድ

ቢዝነስ ፕላን መች ለማንና ለምን ይዘጋጃል

አዲስ ነገር ሲጀመር

በስራ ላይ ለሚገኙ ድርጀቶች

ቢዝነሽ ላን ለሶስት መሰረታዊ ጥያቄዎች መልስ መስጠት አለበት

ድርጅቱ አሁን ያለበት ሁኔታ

ድርጅቱ የት መድረስ እንዳቀደ ወይንም ምን ለመስራት እንዳቀደ

ከታቀደው ግብ ለመድረስ የሚረዱ ዘዴዎችን መዘርዘር አለበት

የጠደምአ ትንተና (SWOT ANALYSIS)

ጠንካራ ጎን

በሙያው ላይ ያለው በቂ ዕውቀት

ከደንበኞች ጋር ያለው ግንኙነት

ስራዎችን የመምራት ልምድ

አብዱልአዚዝ መሀመድአሚን
2011
የማሰራጨት ሂደቱ ምቹ መሆን

በተነፃፃሪ ርካሽ ዋጋ መጠቀም

ምርቱን በየጊዜው ማሻሻል

የምርቱን ጥራት መጠበቅ

የቴክኖሎጂ አጠቃቀም

የምርቱ ጠቀሜታና ጥንካሬ መኖር

ደካማ ጎን

ጥሬ ዕቃ በአግባቡ አለመጠቀም

የምርቱ ዕድሜ ውሰንነት

የምርቱ ዲዛይን አለመሳብ

ደካማ የሽያጭ ጥራት

በተነፃፃሪ የምርቱ ዋጋ ውድ መሆን

የስራው በቂ የሆነ እውቀትና ክህሎት ያለመኖር

የማስተዋወቅ ልምድ ማነስ

ጊዜው ያለፈበት ቴክኖሎጂ መጠቀም

ስራውን በተገቢው ለመምራት ልምድ ያለመኖር

የስራ ማስኬጃ በቂ ገንዘብ ያለመኖር

ከፍተኛ ሽያጭ በሚኖርበት ጊዜ አነስተኛ ክምችት መኖር

ምቹ ሁኔታዋች

ደካማና በቁጥራቸው አናሳ ተወዳዳሪዎች መኖር

የደንበኞች የገቢ መጠን ማደግ

ሙያውን ሊያግዙ የሚችሉ ሙያተኞች መኖር

ርካሽ የጥሬ ዕቃ በቅርበት መገኘት

ተመሳሳይ ምርቶች በገበያው ውስጥ በብዛት ያለመኖር

አብዱልአዚዝ መሀመድአሚን
2011
የምርቱ ዕጥረት በአከባቢው መኖር

ምቹ የመንግስት ፖሊሲ

ዝቅተኛ የወለድ መጠን መኖር

በቂ የሆነ የስልጠና ዕድል ማግኘት

አብዱልአዚዝ መሀመድአሚን
2011

You might also like