You are on page 1of 8

የተሸሻለ የሥራ ተያዥ ማቅረብ ለሚያስፈልጋቸው የመንግሥት ሠራተኞች የወጣ አፈጻጸም ረቂቅ መመሪያ

የሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማትቢሮ


ሚያዝያ 2011 ዓ/ም
ባህር ዳር

መግቢያ

 የመንግሥት ሃብትና ንብረት በአግባቡ እንዲያዝ ማድረግ በማስፈለጉ፣


 በመንግሥት መ/ቤቶችና በሠራተኞች መካከል መብታቸውንና ግዴታቸውን ማስቀመጥና ግልጽኝነትንና
ተጠያቂነት ማስፈን በማስፈለጉ፣
 ከመመሪያና ደንብ ውጭ ያለአግባብ የሚባክነውን የመንግሥት ሐብትና ንብረት በህግ አግባብ ለመጠበቅ ወይም
ለማስመለስ እንዲቻል የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ይህን መመሪያ
አዘጋጅቷል፡፡

ጠቅላላ

1.1 አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ የስራ ተያዥ ማቅረብ ለሚያስፈልጋቸው የመንግሥት ሠራተኞች የወጣ አፈጻጸም መመሪያ ተብሎ

ሊጠቀስ ይችላል፡፡

1.2 ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፡-

1.2.1 “የመንግሥት መ/ቤት” ማለት በየትኛውም የአስተዳደር እርከን ራሱን ችሎ በአዋጅ ወይም በደንብ
የተቋቋመ እና ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ከመንግስት በሚመደብለት በጀት የሚተዳደር መ/ቤት ነው፡፡
1.2.2 “የመንግስት ሠራተኛ” ማለት በክልሉ በየደረጃው በሚገኙ የመንግሥት መ/ቤቶች ውስጥ የሚሰራና
የመንግሥትን ገንዘብና ንብረት በኃላፊነት ተረክቦ የሚያንቀሣቅስ ሰው ነው፡፡
1.2.3 “ውል ሰጭ” ማለት የዋስትና ግዴታ የሚሰጥ በየደረጃው የሚገኝ መሥሪያ ቤት ነው፡፡
1.2.4 “ውል ተቀባይ” ማለት በውል ሰጭው መሥሪያ ቤት በዋስትና ግዴታ መቀበያ ሰነድ መሰረት ስምምነት
የሚወስድ ማለት ነው፡፡
1.2.5 “ዋስ/ተያዥ” ማለት ውል ተቀባይ ሠራተኛ በውል ውስጥ በገባው ግዴታ መሠረት ሳይፈጽም ቢቀር ወይም
አፍርሶ ቢገኝ እርሱን ተክቶ እንደውለታው ግዴታውን ለመፈፀም የሚገደድ ግለሰብ ወይም አካል ነው፡፡
1.2.6 “የዋስትና መቀበያ ሰነድ” ማለት በውል ሰጭ መ/ቤት እና ውል ተቀባይ ሠራተኛ መካከል የሚደረገው ውል
አንድ አካል ሆኖ ውል ተቀባይ ሠራተኛ በገባው ውል መሠረት ግዴታውን በአግባቡ ሳይፈጽም ቢቀር ዋሶች
በተናጠል ወይም በጋራ ዋስ የሆኑበትን የገንዘብ መጠን ለውል ሰጭ መ/ቤት ገቢ ለማድረግ ተስማምተው
የሚፈርሙበት ቅጽ ነው፡፡
1.2.7 “የጋራ ዋስ” ማለት አንድ ሠራተኛ ለሚረከበው ንብረት ወይም ለሚያንቀሳቅሰው ንብረት እንደ መያዣ
የሚያገለግሉና ለሚጠፋውም ጥፋት በጋራ የሚጠየቁ የግለሰቦች ስብስብ ማለት ነው፡፡
1.2.8 “የተናጠል ዋስ” ማለት አንድ ሠራተኛ ከገንዘብና ንብረት ጋር ተያያዥነት ባላቸው የስራ መደቦች ላይ
ለሚረከበው ንብረት ወይም ለሚያንቀሳቅሰው ገንዘብ እንደመያዣ የሚያቀርበውና በሠራተኛው የስራ አጋጣሚ
ለሚፈጠር የገንዘብና የንብረት መጥፋት ራሱን ችሎ የሚጠየቅ ማለት ነው፡፡
1.3 መመሪያው ተፈፃሚ የሚሆንባቸው አካላት

1.3.1 ይህ መመሪያ ተፈፃሚ የሚሆነው በክልሉ የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ በሚተዳደሩ መስሪያ ቤቶች ውስጥ

በገንዘብ ያዥ፣ ረዳት ገንዘብ ያዥ፣ በዕለት ገንዘብ ተቀባይ፣ በንብረት ኦፊሰር፣ በአሽከርካሪ/መኪናና ሞተር/፣ በእቃ

ግዥ ኦፊሰር፣ በጥበቃ ሰራተኛ፣ በቅየሳ ሰራተኝነት፣ በቤተመጽሃፍት ሰራተኝነት፣ በፋርማሲስትነት፣ በላቦራቶሪ

ቴክኒሽያንነት እና በወርክሾፕ ቴክኒሻንነት፣ በቋሚ ንብረት አሥተዳደርና ምዝገባ ኦፊሰር፣የኢ.ኮ.ቴ.(የአይ ሲቲ)

ባለሙያዎች፣እንስሳት ሐኪም ፣ በአገልግሎት መረጃ ኦዲዮቪዡዋልና የህትመት ሠራተኛ፣በሙዝየም

ኃላፊ/ባለሙያ/፣ የስራ መደቦች እና ከእነዚህ በተጨማሪ በመ/ቤቶች ውሣኔ ተያዥ እንዲያቀርቡ የተለዩ ሥራ

መደቦች ላይ ተመድበው እየሰሩ ባሉና ወደፊትም በእነዚህ የስራ መደቦች ላይ በሚመደቡ ሰራተኞች ላይ ነው፡፡

1.3.2 በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1.3.1 ላይ ከተገለጹት የስራ መደቦች ውጭ ሆነው ከንብረትና ከገንዘብ ጋር

ተያያዥ የሆኑ ሌሎች የስራ መደቦች ሲያጋጥሙ በመሥሪያ ቤቱ የማኔጅመንት አካል ውሳኔ ዋስትና እንዲገቡ

ማድረግ ይቻላል፡፡ የሚገቡት የዋስትና መጠንም በማኔጅመንቱ ውሳኔ ከላይ ለተዘረዘሩት የስራ መደቦች ከተገለጸው

የአንዱን መውሰድ ይቻላል፡፡ሆኖም ግን የማኔጅሜንት አካል ከወሰነው ውጭ በሌሎች የሥራ መደቦች ላይ ዋስትና

ማስያዝ አስፈላጊ አይደለም፡፡

ክፍል ሁለት

ሠራተኞች ዋስትና ስለሚያቀርቡበት ሁኔታ

2.1 የንብረት ኦፊሰሮች ፣ ፋርማሲስቶች ፣ ላቦራቶሪ ቴክኒሽያኖች እና ወርክሾፕ ቴክኒሽያኖች፣ የእንስሳት ህክምና

ባለሙያ በክልሉ በየደረጃው በሚገኙ የመንግሥት መ/ቤቶች ውስጥ በንብረት ኦፊሰርነት፣ በፋርማሲስትነት፣

በላቦራቶሪ ቴክኒሽያንነት እና በወርክሾፕ ቴክኒሽያንነት፣ የቋሚ ንብረት አሥተዳደርና ምዝገባ ኦፊሰር፣የእንስሳት

ህክምና ባለሙያ የስራ መደብ ላይ ተቀጥሮ ወይም ተመድቦ የሚሰራ ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ

ለሚረከበው ንብረት ለብር 100‚000 (የአንድ መቶ ሺ ብር) የጋራ ዋስ የሚሆኑ የእያንዳንዳቸው የወር ደመወዝ ብር

2748.00 /ሁለት ሺ ሰባት መቶ አር ስምንት ብር/ እና በላይ የሆኑ 2 ቋሚ ሠራተኞች ወይም የወር ደመወዙ ብር

3579.00 /ሦስት ሺ አምስት መቶ ሰባ ዘጠኝ ብር/ እና በላይ የሆነ 1 ቋሚ ሠራተኛ ወይም ግምቱ ብር 100000

(አንድ መቶ ሺ ብር) የሆነ ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት በዋስነት ማቅረብ/ማስያዝ/ አለበት፡፡ ወይም ግምቱ

ብር 100‚000 (አንድ መቶ ሺ ብር) የሆነ ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት የሚያቀርብ ግለሰብ በዋስነት

ማቅረብ/ማስያዝ/ አለበት፡፡

2.2 ዋና ገንዘብ ያዥ፣ ገንዘብ ያዥ፣ ረዳት ገንዘብ ያዥ እና የዕለት ገንዘብ ሰብሳቢ/ተቀባዮች/፣ እቃ ግዢ፣

አሽከርካሪዎች(ለመኪና ብቻ) በክልሉ በየደረጃው በሚገኙ የመንግሥት መ/ቤቶች ውስጥ በገንዘብ ያዥነት፣ በዕለት

ገንዘብ ተቀባይነትና ረዳት ገንዘብ ያዦች የስራ መደብ ላይ የሚቀጠሩ፣ የሚዛወሩ እና ደረጃ እድገት የሚያድጉ
ባለሙያ ወይም ሠራተኞች የሚሠራ ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ለሚረከበው ገንዘብ ለብር 8 ዐ‚ዐዐዐ

(ሰማንያ ሺ ብር ) የጋራ ዋስ የሚሆኑ የእያንዳንዳቸው የወር ደመወዝ ብር 2404 /ሁለት ሺ አራት መቶ አራት ብር/

እና በላይ የሆኑ 2 ቋሚ ሠራተኞች ወይም የወር ደመወዙ ብር 3137 /ሦስት ሺ አንድ መቶ ሰላሣ ሰባት ብር/ እና

በላይ የሆነ 1 ቋሚ ሠራተኛ ወይም ግምቱ ብር 80‚000 (ሰማንያ ሽ ብር ) የሆነ ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት

በዋስትና ማቅረብ/ማስያዝ/ አለበት፡፡ ፡

2.3 የእቃ ግዥ ኦፊሰሮች


በክልሉ በየደረጃው በሚገኙ የመንግሥት መ/ቤቶች ውስጥ በእቃ ግዥ ኦፊሰርነት ተቀጥሮ ወይም ተመድቦ የሚሠራ

ሠራተኛ ለብር 8 ዐ‚ዐዐዐ (ሰማንያ ሺ ብር ) የጋራ ዋስ የሚሆኑ የእያንዳንዳቸው የወር ደመወዝ ብር 2404 /ሁለት

ሺ አራት መቶ አራት ብር/ እና በላይ የሆኑ 2 ቋሚ ሠራተኞች ወይም የወር ደመወዙ ብር 3137 /ሦስት ሺ አንድ

መቶ ሰላሣ ሰባት ብር/ እና በላይ የሆነ 1 ቋሚ ሠራተኛ ወይም ግምቱ ብር 80‚000 (ሰማንያ ሽ ብር ) የሆነ ቋሚ

ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት በዋስትና ማቅረብ/ማስያዝ/ አለበት፡፡

2.4 አሽከርካሪዎች (ለመኪና ብቻ)


በክልሉ በየደረጃው በሚገኙ የመንግሥት መ/ቤቶች ውስጥ በአሽከርካሪነት የስራ መደብ ላይ ተቀጥሮ ወይም

ተመድቦ የሚሠራ ማንኛውም አሽከርካሪ በስሙ ለተረከበው ተሽከርካሪ ለብር 8 ዐ‚ዐዐዐ (ሰማንያ ሺ ብር ) የጋራ

ዋስ የሚሆኑ የእያንዳንዳቸው የወር ደመወዝ ብር 2404 /ሁለት ሺ አራት መቶ አራት ብር/ እና በላይ የሆኑ 2 ቋሚ

ሠራተኞች ወይም የወር ደመወዙ ብር 3137 /ሦስት ሺ አንድ መቶ ሰላሣ ሰባት ብር/ እና በላይ የሆነ 1 ቋሚ

ሠራተኛ ወይም ግምቱ ብር 80‚000 (ሰማንያ ሽ ብር ) የሆነ ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት የሚያቀርብ ግለሰብ

በዋስትና ማቅረብ/ማስያዝ/ አለበት፡፡

2.3 የጥበቃ ሠራተኞች እና ሞተረኞች


በክልሉ በየደረጃው በሚገኙ የመንግሥት መ/ቤቶች ውስጥ በጥበቃ ሠራተኝነት እና በሞተረኝነት ተሰማርቶ

የሚሠራ ሠራተኛ ለብር 30‚000 ( ሰላሣ ሺ ብር ) የጋራ ዋስ የሚሆኑ የእያንዳንዳቸው የወር ደመወዝ ብር

2100 /ሁለት ሺ አንድ መቶ ብር/ እና በላይ የሆኑ 2 ቋሚ ሠራተኞች ወይም የወር ደመወዙ ብር 2404 /ሁለት ሺ

አራት መቶ አራት ብር/ እና በላይ የሆነ 1 ቋሚ ሠራተኛ ወይም ግምቱ ብር 30‚000 ( ሰላሣ ሺ ብር ) በላይ የሆነ

ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት በዋስትና ማቅረብ /ማስያዝ/ አለበት፡፡

2.4. የቤተመፃህፍት ሠራተኞች፣


በክልሉ በየደረጃው በሚገኙ የመንግሥት መ/ቤቶች ውስጥ በቤተ መፃህፍት ሠራተኝነት የስራ መደብ ላይ ተቀጥሮ

ወይም ተመድቦ የሚሠራ ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ለሚረከበው ንብረት ለብር 1 ዐ,ዐዐዐ (አስር ሽህ) የጋራ

ዋስ የሚሆኑ የእያንዳንዳቸው የወር ደመወዝ ብር 1828 /አንድ ሺ ስምንት መቶ ሃያ ስምንት ብር/ እና በላይ የሆኑ
2 ቋሚ ሠራተኞችን ይህ ካልሆነ የወር ደመወዙ 2100 /ሁለት ሺ አንድ መቶ ብር/ የሆነ 1 ቋሚ ሠራተኛ ወይም

ግምቱ ብር 1 ዐ,ዐዐዐ (አስር ሽህ) የሆነ የቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት በዋስትና ማቅረብ/ማስያዝ አለበት፡፡

2.7 ቀያሾች፣ የኢ.ኮ.ቴ.(የአይ ሲቲ) ባለሙያዎች፣ የአገልግሎት መረጃ ኦዲዮ-ቪዡዋል፣ ካሜራ ማኖች፣ የህትመት

ሠራተኛ፣ የሙዝየም ኃላፊ/ባለሙያ/

በክልሉ በየደረጃው በሚገኙ የመንግሥት መ/ቤት ውስጥ በቀያሽነት፣ የኢ.ኮ.ቴ.(የአይ ሲቲ) ባለሙያዎች/ሰርቨር

ወይም የአዳራሽ ቁልፍ ከያዙ ብቻ/፣ የአገልግሎት መረጃ ኦዲዮቪዡዋል፣ ካሜራማኖች፣ የህትመት ሠራተኛ፣

የሙዝየም ኃላፊ/ባለሙያ/ ተሰማርቶ የሚሠራ ሠራተኛ ለብር 50,000 ( ሃምሣ ሽህ) የጋራ ዋስ የሚሆኑ

የእያንዳንዳቸው የወር ደመወዝ ብር 2404/ሁለት ሺ አራት መቶ አራት ብር/ እና በላይ የሆኑ 2 ቋሚ ሠራተኞች

ወይም የወር ደመወዙ ብር 3137/ሦስት ሺ አንድ መቶ ሰላሣ ሰባት ብር/ እና በላይ የሆነ 1 ቋሚ ሠራተኛ ወይም

ግምቱ ብር 50,000 ( ሃምሣ ሽህ) የሆነ ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት በዋስትና ማቅረብ/ማስያዝ/ አለበት፡:

ክፍል ሦስት
የውል ሰጭ መስሪያ ቤት እና የዋሶች ግዴታ
3.1 የውል ሰጭ መ/ቤት ግዴታ
3.1.1 በዋስትና መቀበያ ሠነድ /ቅጽ/ ላይ የቀረቡት ዋሶች ውል ሰጭና ተቀባይ ባሉበት በውዴታ እንዲፈርሙ
ማድረግ አለበት፡፡
3.1.2 የዋስትና መቀበያ ሰነዱ ከመፈረሙ በፊት ዋሶች ማሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላታቸውን
ማረጋገጥ አለበት፡፡
3.1.3 ሠራተኛው በስሙ የተረከበውን ገንዘብ ወይም ንብረት ያጠፋ ወይም ይዞ የተሰወረ እንደሆነ ቀጣሪው
መ/ቤት ሁኔታውን እንዳወቀ ወዲያውኑ ለዋሶች የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡
3.1.4 ዋሶች ሠራተኛው ያጠፋውን ሀብትና ንብረት በጋራ ወይም በተናጠል በስምምነታቸው መሠረት
ለመንግሥት ገቢ እንዲያደርጉ ጠይቆ ይህንን ለማድረግ ፈቃደኛ ካልሆኑ መረጃዎችን በማጠናቀር ለፍትህ አካል
ያቀርባል፡፡
3.1.5 ዋስትና በሚጠይቅ መደብ ላይ የነበረ ሠራተኛ መደቡን ሲቀይር ለተያዡ /ለዋሱ በመ/ቤቱ በኩል
እንዲያውቀው ማድረግ አለበት፡፡
3.2 የዋሶች ግዴታ
3.2.1 ዋስ ለመሆን ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች በውል ሰጭ/በቀጣሪ መ/ቤት/ በኩል የተዘጋጀውን የዋስትና መቀበያ ሰነድ
/ቅጽ/ ውል ተቀባይና ውል ሰጭ ባሉበት በሙሉ ፍቃደኝነት የመፈረም ግዴታ አለባቸው፡፡
3.2.2 ውል ተቀባይ በስራው አጋጣሚ በእጁ የሚገባውን ንብረትም ሆነ ገንዘብ ሆን ብሎም ይሁን በሥራው
አጋጣሚ ቢጠፋበት ወይም ይዞ ቢሰወር ዋሶች ዋስ የሆኑበትን የገንዘብ መጠን በጋራ ወይም በተናጠል ገቢ የማድረግ
ግዴታ አለባቸው፡፡
3.2.3 ዋሶች ዋስ ስለሆኑት ሠራተኛ በየጊዜው እየተከታተሉና የተለየ ሁኔታ በሚኖርበት ወቅትም ለቀጣሪው /ውል
ሰጭ/ መ/ቤት የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው፡፡
3.2.4 ማንኛውም ዋስ መሆን የሚችል ሰው በህግ እገዳ ያልተጣለበት፣ የአእምሮ ችግር የሌለበትና በራሱ አመዛዝኖ
መወሰን የሚችል መሆን አለበት፣
3.2.5 ዋስ የሚሆነው ሰው የመንግስት ሠራተኛ ከሆነ ቋሚ የሆነና ጡረታ ለመውጣት ቢያንስ 5 ዓመት የቀረው
መሆን አለበት፡፡
3.2.6 ዋስ የሚሆነው ሰው የመንግስት ሠራተኛ ከሆነ ደመወዙ በማንኛውም የዋስትና እዳ ያልተያዘ መሆኑን
ከሚሰራበት መ/ቤት የጽሁፍ ማረጋገጫ ማቅረብ አለበት፡፡
3.2.7 ለዋስትና የሚቀርበው ቋሚም ሆነ ተንቀሳቃሽ ንብረት ከማንኛውም እዳ ነፃ መሆኑን በህግ ስልጣን
በተሰጠው አካል በጽሁፍ ማረጋገጫ ማቅረብ አለበት፡፡
3.2.8 ማንኛውም ግለሰብ የመንግሥት ሠራተኛ ለትዳር ጓደኛው/ዋ ዋስ ሆኖ መቅረብ አይችልም፡፡
3.2.9 ለውል ተቀባይ አካል ዋስ ሆነው የሚቀርቡ ግለሰቦች ባለትዳር ከሆኑ ባለቤቶቻቸው አብረው እንዲፈርሙ
ይደረጋል፡፡
3.2.10 ተያዥ ለሚያስፈልጋቸው የስራ መደቦች ዋስ ወይም ተያዥ የሚሆነው ሠራተኛ ወይም ግለሰብ ከውል
ሰነዱ ጋር ጉርድ ፎቶ ግራፍ ማያያዝ አለበት፡፡
3.3 የሥራ ተያዥ ውል ማስፈፀሚያ ቅጽ ከመመሪያው ጋር በአባሪነት የተያያዘ ሲሆን ከዚህ ቅጽ በስተቀር በሌላ
ቅጽ መጠቀም አይቻልም፡፡
ክፍል አራት
ሌሎች ልዩ ልዩ ጉዳዮች

4.1 ለአንድ ሰው የሥራ ተያዥ/ዋስ የሆነ ግለሰብ ዋስትናውን እስካላነሳ ድረስ ለሌላ ሰው ዋስ መሆን አይችልም፡፡
ሆኖም ለሌሎች ጉዳዮች ዋስ/ ተያዥ መሆን ይችላል፡፡ ለምሣሌ፡- ለብድር፣ ለሥልጠና እና ተመሣሣይ ጉዳዮች ዋስ
መሆን ይቻላል፡፡
4.2 የልማት ድርጅት ቋሚ ተቀጣሪ ሠራተኞችን፣ የፋይናንሽያል ተቋማት/ ኢንሹራንስ/ባንኮች ወዘተ… ቋሚ
ተቀጣሪ ሠራተኞችን፣ ህጋዊነት ያላቸው የግል ተቋማት ቋሚ ተቀጣሪ ሠራተኞችን ለዋስትና እንደ መንግሥት
ሠራተኞች ማቅረብ የሚቻል ሲሆን የሚያቀርቧቸው ማስረጃዎችም በዚህ መመሪያ የተገለጹትን ያጠቃልላል፡፡
4.3 በአንቀጽ 4.2 የተገለጸው ቢኖርም ዋስ የሚሆኑት ሠራተኞች ከተቀጠሩበት ተቋም በማንኛውም ምክንያት
በሚለቁበት ጊዜ ውል ተቀባዮች ተከታትለው ማሳወቅ እና ተለዋጭ ዋስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4.4 ዋሶች በክልሉ የሚኖሩ ወይም የሚገኙ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም የቅርንጫፍ መ/ቤቱ በክልላችን የሚገኝ
ሆኖ ተጠሪነታቸው ለፌደራል መ/ቤት የሆኑ መ/ቤቶች የሚሰሩ ሠራተኞች ዋስ መሆን ይችላሉ፡፡
4.5 ለውል ተቀባይ በዋስትና የሚቀርቡ ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ለዋስትና በሚቀርቡበት ጊዜ
ከሚመለከታቸው አካላት ግምታቸው ተገምቶ ከእዳና እገዳ ነፃ መሆኑ ተገልፆ መቅረብ አለበት፡፡ እንዲሁም
በዋስትና የሚያዘው ቋሚና ተንቀሣቃሽ ንብረት ለሌላ ሦስተኛ ወገን እንዳይተላለፍ/እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ ውል
ሰጭው አካል ለሚመለከተው አካል መግለጽ ይኖርበታል፡፡
4.6 ዋስትና በሚጠይቁ የሥራ መደቦች ላይ ተመድበው የሚሰሩ ሠራተኞች ሌሎች ዋስትና በሚጠይቁ የሥራ
መደቦች ላይ ተመድበው ለሚሰሩ ሠራተኞች ዋስ መሆን አይችሉም፡፡
4.7 ውል ተቀባይ ተያዥ ያቀረበበትን የስራ መደብ ለቆ ተያዥ ወደሚጠይቅ ሌላ የስራ መደብ ከተዛወረ ውሉን
እንደገና ማደስ ይጠበቅበታል፡፡ይህን ካላደረገ ግን የመጀመሪያው ተያዥ በአዲሱ የስራ መደብ ላይ ለሚደርስ
ማናቸውም ጥፋት ሀላፊነት አይወስድም፡፡
4.8 ዋስትና በሚጠይቁ የሥራ መደቦች ላይ ተመድበው ለሚሰሩ ዋስ/ተያዥ የሚሆነው ሰው ዋስትናውን ማንሳት
ከፈለገ ዋስትናዉን ላስሞላዉ መስ/ቤት ወይም ለሰዉ ኃብት ስራ አመራር ቡድን አስቀድሞ ከ 5 የስራ ቀናት በፊት
ዋስትናው እንዲነሳለት በቅድሚያ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ የሚሰራበት መ/ቤትም ዋስ ለሆነበት መ/ቤት በደብዳቤ
በማሣወቅ ዋስትናው እንዲነሳለት ይጠይቃል፡፡ መ/ቤቱም ዋስትና ላስያዘው ሠራተኛ በ 5 የስራ ቀናት ውስጥ
ተለዋጭ ዋስ ማቅረብ እንዳለበት ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ ሠራተኛውም በ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ተተኪ ዋስ ማቅረብ
ግዴታ አለበት፡፡ ሆኖም በነዚህ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ካልቻለ ለ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከሥራው ታግዶ
ይቆያል፡፡ ሆኖም በነዚህ ቀናት በተባለው የጊዜ ማቅረብ ከቻለ የታገደባቸዉ ቀናት ደመወዝ እንዲከፈል የሚደረግ
ሲሆን ይህም ሁኖ በተባለዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ማቅረብ ካልቻለ ከሥራው እንዲሰናበት ይደረጋል፡፡
4.9 ዋስትና በሚጠይቁ የሥራ መደቦች ላይ ተመድበው የሚሰሩ ሠራተኞችም ሆነ ወደፊት የሚመደቡ ሠራተኞች
በእጃቸው ለገባው የመንግሥት ሀብትና ንብረት ተያዥ ማቅረብ ካልቻሉ እንዲሰናበቱ ይደረጋል፡፡ ስንብቱም
በየደረጃው በሚገኘው የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አማካይነት ይፈጸማል፡፡ ሆኖም በቅጥር፣ በደረጃ
እድገት፣ በውጭ ዝውውርና በወጣ ማስታወቂያ ተወዳዳሪዎች በፍላጐታቸው ተመዝግበው ካልተመደቡ በስተቀር
በመ/ቤቱ አስገዳጅነት ዋስትና በሚጠይቁ የሥራ መደቦች ላይ የሚመደቡ ሠራተኞች ለሥራ መደቡ የተፈቀደው
ደረጃ ተሰጥቷቸው ከሆነ ከያዙት የስራ ደረጃና ደመወዝ ጋር አቻ ከሆነ መደብ እንዲመደቡ ይደረጋል፣ አቻ ደረጃና
ደመወዝ ካልተገኘ የያዙትን ደመወዝ እንደያዙ በአንድ ደረጃ ዝቅ የሚለዉን የስራ ደረጃ እንዲመደብ ይደረጋል፣
ይህም ካልተገኘ የያዙትን ደመወዝ እንደያዙ በሁለት ደረጃ ዝቅ ብለዉ እንዲመደቡ ከማድረግ በስተቀር
እንዲሰናበቱ አይደረግም፡፡
4.10 ዋስትና በሚጠይቁ የሥራ መደቦች ላይ በቅጥርም፣ በዝውውር፣ በደረጃ እድገትም ሆነ በምደባ ወቅት
ሠራተኞችን አወዳድሮ መመደብ ሲያስፈልግ የሚገቡት የዋስትና ግዴታ በሚወጣው ማስታወቂያ ላይ መገለጽ
ይኖርበታል፡፡ ተያዥ ሳይቀርብ ማንኛውንም ሥምሪት መፈጸም አግባብ ባለው ህግ ፈጻሚውን ያስጠይቃል፡፡
4.11 ይህ መመሪያ ዋስትናን በሚጠይቁ የስራ መደቦች ላይ የተቀጠሩ ጊዜያዊ ወይም የኮንትራት ቅጥር
ሠራተኞችን ይመለከታል፡፡
4.12 በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 253/2010 አንቀጽ 96 ን/አንቀጽ
2 መሠረት ይህን መመሪያ የመለወጥ፣ የማሻሻል ወይም በሥራ ላይ በሚውልበት ጊዜ ማብራሪያ ወይም ትርጉም
የመስጠት ኃላፊነት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ነው፡፡
4.13 ይህ መመሪያ ተፈፃሚነት የሚኖረው በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ማሻሻያ አዋጅ
ቁጥር 253/2010 በሚተዳደሩ መ/ቤቶችና ሠራተኞች ላይ ብቻ ነው፡፡
4.14 በሐምሌ ወር 2002 ዓ/ም ወጥቶ በሥራ ላይ የነበረው የሥራ ተያዥ ማቅረብ ለሚያስፈልጋቸው የመንግሥት
ሠራተኞች የወጣ መመሪያና ይህን አስመልክቶ የተላለፉ ሰርኩላሮች በዚህ መመሪያ ተተክተዋል፡፡
4.15 ይህን መመሪያ በተዛባ መልኩ ወይም አላግባብ የሚያስፈፅም ማነኛዉም አካል ወይም የስራ ኃላፊ አግባብ
ባለዉ ህግ ተጠያቂ ይሆናል፡፡
4.16 በዚህ መመሪያ አፈፃፀም ላይ የሚኖር ቅሬታ በስራ ላይ ባለዉ የቅሬታ አቀራረብስርዓት መሰረት ተፈፃሚ
ይሆናል፡፡
4.17 ይህ መመሪያ ከሰኔ/2011 ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡
የሥራ ተያዥ ውል ማስፈፀሚያ ቅጽ
ይህ የውል ሰነድ ከዚህ በኃላ ውል ሰጭ እየተባለ የሚጠራው የ-------------------------------------
ቢሮ/ጽ/ቤት/ኮሚሽን/ኤጀንሲ/ኢንስቲትዩት/ባለሥልጣን አድራሻ--------------------------እና ውል ተቀባይ እየተባለ
የሚጠራው አቶ/ወ/ሮ/ወ/ሪት----------------------------እንዲሁም ዋስ/ተያዥ እየተባለ የሚጠራው
በአቶ/ወ/ሮ/ወ/ሪት--------------------------------መካከል የተደረገ የውል ስምምነት ሆኖ ውል
ሰጪ፣ውል ተቀባይና ዋስ/ተያዥ/ ተዋዋይ ወገኖች ወደውና ፈቅደው በዛሬው ዕለት ማለትም በ-------------
ቀን-------ወር--------ዓ/ም ከዚህ እንደሚከተለው ተስማምተው ተዋውለዋል፡፡
1. አቶ/ወ/ሮ/ወ/ሪት------------------------------የተባሉት ሰራተኛ ከ---------------------ጀምሮ በውል ሰጪ
መ/ቤት በ--------------------------------------የሥራ መደብ እንዲሰሩ አስፈላጊውን የአሠራር ሥርዓት ፈጽመው
በየወሩ ብር-------------------/----------------------------------------/ ደመወዝ እየተከፈላቸው እንዲሰሩ
ሠራተኛውና ውል ሰጪ የሆነው መ/ቤት በተስማሙት መሠረት ሠራተኛው ዋስ/ተያዥ አቅርቧል፡፡
2. በዋስ/በተያዥ/ የሚሞላ
2.1 በዋስ/ተያዥነት/ በፍቃደኝነት የቀረቡ አቶ/ወ/ሮ/ወ/ሪት--------------------------------------
በ------------------------መ/ቤት እየሰሩ በወር ብር------------------/------------------------------/ ደመወዝ የሚገኙ
ሲሆን ዋስ የሆኑበት ሠራተኛ በሥራው አጋጣሚ በእጁ የገባውን የመንግሥት ንብረትም ሆነ ገንዘብ ቢያጠፋ ወይም
ሌላ ጥፋት ቢሰራ ዋስ የሆኑበት የገንዘብ መጠን ማለትም ብር------------/---------------------------/ በጋራ ወይም
በተናጥል ሊከፍሉ ግዴታ ገብተዋል፡፡
2.2 በዋስ/ተያዥነት/ በፍቃደኝነት የቀረቡ አቶ/ወ/ሮ/ወ/ሪት----------------------------------------------
በ-----------------------መ/ቤት እየሰሩ በወር ብር------------------/------------------------------/ ደመወዝ የሚገኙ
ሲሆን ዋስ የሆኑበት ሠራተኛ በሥራው አጋጣሚ በእጁ የገባውን የመንግሥት ንብረትም ሆነ ገንዘብ ቢያጠፋ ወይም
ሌላ ጥፋት ቢሰራ ዋስ የሆኑበት የገንዘብ መጠን ማለትም ብር------------/---------------------------/ በጋራ ወይም
በተናጥል ሊከፍሉ ግዴታ ገብተዋል፡፡
3. ሠራተኛው ወይም ተያዡ ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት ሲያስይዝ የሚሞላ፣
3.1 እኔ አቶ/ወሮ/ወ/ሪት-----------------------------------------------የተባልኩ በ-----------------------የሥራ መደብ
በሥራው አጋጣሚ በእጄ የሚገቡትን ንብረቶችም ሆነ ገንዘብ ባጎድል ወይም ሌላ ጥፋት ብፈጽም ግምቱ
--------------- የሆነ ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረቴን በማስያዣነት አቅርቤአለሁ፡፡
3.2 እኔ አቶ/ወ/ሮ/ወ/ሪት-------------------------የተባልሁ አቶ/ወ/ሮ/ወ/ሪት---------------------------
የ-------------------------------- ቢሮ ጽ/ቤት/ኮሚሽን/ኤጀንሲ/ኢንስቲትዩት/ባለሥልጣን ሠራተኛ
በተመደቡበት የስራ መደብ ላይ በሥራ አጋጣሚ በእጃቸው የገባውን የመንግሥት ንብረት ወይም ገንዘብ ቢያጠፋ
ወይም ሌላ ጥፋት ቢሰሩ ለብር------------/-----------------------------------/ ለመክፈል ግዴታ ገብቻለሁ ፡፡ ለዚህም
ዋስትና የግል ንብረቴ የሆነውን ------- ተሸከርካሪ/የተሸከርካሪው ዝርዝር መረጃ ይገለጻል/ወይም መኖሪያ ቤት
አድራሻ በ-------------ከተማ ቀበሌ-------የቤት ቁጥር ---------የሆነው ንብረት በዋስትና እንዲመዘገብ ከባለቤቴ ጋር
ሆነን ተስማምተናል፡፡ ዋስትና የተሰጠበት የዚህ ውል ኮፒ አግባብ ላለው የመንግሥት መ/ቤት ወይም አካል
እንዲደርሰው ይደረጋል፡፡ /ከመኪናና ከቤት ውጭ የሆነ ንብረት በማስያዣነት ሊቀርብ ይችላል፡፡
4. በፍቃደኝነት ዋስ የሆኑ ግለሰብ ዋስ ለሆኑበት ሠራተኛ በየጊዜው እየተከታተሉና የተለየ ሁኔታ በሚኖርበት ወቅት
ለቀጣሪው መ/ቤት/ውል ሰጪ/ የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው፡፡
5. ዋስ የሆኑት ግለሰብ የመንግሥት ሠራተኛ፣ የልማት ድርጅት ተቀጣሪዎች፣ ህጋዊነት ያላቸው የግል ተቋማት
ተቀጣሪዎች ከሆኑ ቋሚ መሆናቸውን ጡረታ ለመውጣት 5 ዓመትና ከዚያ በላይ የቀራቸው መሆኑን ፈርመዋል፡፡
6. ዋስ የሆኑት ግለሰብ ዋስትናቸውን እስካላነሱ ድረስ ለሌላ ሰው ዋስ መሆን እንደማይችሉ አምነው በፊርማቸው
አረጋግጠዋል፡፡
7. የዋስትና ውል በሚፈጸምበት ጊዜ የፍታብሄር ህግ በሚያዘው መሠረት ዋስ/ተያዥ/ ባለቤታቸውን በመያዝ ይህን
ውል አንብበው/ሲነበብ ሰምተው / በመስማማት በተለመደው ፊርማቸው አረጋግጠዋል፡፡
8. ለዋስትና የሚቀርበው ቋሚም ሆነ ተንቀሳቃሽ ንብረት ከማንኛውም እዳ ነጻ መሆኑን አግባብ ካለው አካል
በጽሁፍ ማረጋገጫ ያቀረቡ ሲሆን ንብረታቸውን ከመሸጣቸው ወይንም በማንኛውም አካል ወደ ሶስተኛ ወገን
ከማስተላለፋቸው በፊት ዋስትናቸውን ለማውረድ መወሰናቸውን ለውል ሰጪ መ/ቤት አሳውቀው ውል ሰጪው
መስማማቱን በማረጋገጥ እንደሚፈጽሙ በፊርማቸው ግዴታ ገብተዋል፡፡
9. ይህ የውል ሰነድ ሠራተኛው በውል ሰጪ መ/ቤት ሥራ ከጀመሩበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡
እኛ ስማችን ከላይ የተገለጸው ውል ሰጪ መ/ቤት ተያዥ አቅራቢ፣ዋስ/ተያዥ/ እንዲሁም የተያዥ /ዋስ/ ባለቤት
ከላ የተገለፁትን ሁኔታዎች አንብበን፣ተረድተንና ወደን የተስማማን መሆናችንን በፊርማችን እናረጋግጣለን፡፡
የተያዥ አቅራቢ ሠራተኛ
ሥም--------------------------------
ፊርማ------------------------------
ቀን---------------------------------
የተያዥ/ዋስ/ አንድ የተያዥ /ዋስ/አንድ ባለቤት
ሥም-------------------------------- ሥም--------------------------------
ፊርማ------------------------------ ፊርማ------------------------------
ቀን--------------------------------- ቀን---------------------------------
የተያዥ/ዋስ/ ሁለት የተያዥ /ዋስ/ሁለት ባለቤት
ሥም-------------------------------- ሥም--------------------------------
ፊርማ------------------------------ ፊርማ------------------------------
ቀን--------------------------------- ቀን---------------------------------
የውል ሰጪ መ/ቤት ኃላፊ/ባለሙያ
ሥም-------------------------------- ሥም--------------------------------
ፊርማ------------------------------ ፊርማ------------------------------
ቀን--------------------------------- ቀን---------------------------------
ይህ ውል ሲፈረም የነበሩ እማኞች
1. ሥም--------------------------------
ፊርማ------------------------------
ቀን---------------------------------
አድራሻ----------------------------- ስ.ቁ-----------------------------
2. ሥም--------------------------------
ፊርማ------------------------------
ቀን---------------------------------
አድራሻ----------------------------- ስ.ቁ-----------------------------
3. ሥም--------------------------------
ፊርማ------------------------------
ቀን---------------------------------
አድራሻ----------------------------- ስ.ቁ-----------------------------

You might also like