Professional Documents
Culture Documents
2015
2015
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን በተመለከተ ኮሙኒኬሽን
ጽ/ቤት የህዝብ አስተያየት ለመሰብሰብ የተዘጋጀ መጠይቅ ዳሰሳ ጥናት
1
መሬት ይዞታ አገልግሎት ለማግኘት 53 ሰዎች፤
ለግንባታ ፍቃድ ለማስፈቀድ 39 ሰዎች ፤
ስም ዝውውር አገልግሎት ለማግኘት 3 ሰዎች ሰዎች፤
የሊዝ ቦታ አገልግሎት ለማግኘትለመጠቅ 25 ሰዎች፤
የፕላን ተቃርኖ ችግር አገልግሎት ለማግኘትለማሰራት 35 ሰዎች ፤
ካርታ አገልግሎት ለማግኘት 31 ሰዎች ፤
የቤተሰብ የቤት ውርስ ባለቤትነት ለማረጋገጥ እና ማህበር ቤት የጀርባ ማህተም ለማስመታት አገልግሎት
ለማግኘት 12 ሰዎች ፤
መታወቂያ እድሳት አገልግሎት ለማግኘት 18 ሰዎች ፤
አዲስ መታወቂያ የማውጠት አገልግሎት ለማግኘት 55 ሰዎች ፤
የልደት ሰርተፊኬት ለማውጣት አገልግሎት ለማግኘት 29 ሰዎች፤
ያላገባ ሰርተፊኬት አገልግሎት ለማግኘት 13 ሰዎች፤
የገበሬ ልጅነትን መረጃ ለማግኘት አገልግሎት ለማግኘት 13 ሰዎች ፤
የአርሶ አደር አገልግሎት ለማግኘት 16 ሰዎች፤
ንግድ ፍቃድ ለማውጣት አገልግሎት ለማግኘት 40 ሰዎች ፤
ንግድ ፍቃድ ለማሳደስ አገልግሎት ለማግኘት 17 ሰዎች ፤
የስራ አጥ መታወቂያ አገልግሎት ለማግኘት 23 ሰዎች ፤
በጥቃቅንና አነስተኛ የመደራጀት አገልግሎት ለማግኘና ስራ ለከመስራት 18 ሰዎች፤
የተለያዩ አስተዳደራዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት 13 ሰዎች ፤
ግብር ክፍያ ስህተት ለማስተካከል አገልግሎት ለማግኘት 5 ሰዎች ፤
3. አመራሮች እና ሰራተኞች የስራ ሰአታቸውን ጠብቀው አገልግሎት ይሰጣሉ?
2
አመራሮች በቀጠና በተለያዩ ስብሰባ ምክንያት በማድረግ ቢሮ ተገኝተው ለባለጉዳይ በሰዓቱ አለማስተናገድ
ባለጉዳዩን በተለያዩ በታኪሲ በተለያዩ ነገሮች በመፍጠር በሰዓቱ ቢሮ አይገኙም 9 ሰዎች ምላሻቸውን
ሰጥተዋል፤
4. አመራሮች እና ባለሙያዎች ራሳቸውን የሚገልጽ ባጅ ያደርጋሉ?
አዎ ያደርጋሉ 76 ሰዎች ሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤
አንዳንዶች/የተወሰኑ ብቻ ያደርጋሉ 56 ሰዎች የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤
አያደርጉም 55 ሰዎች የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤
ባለሙያዎች ይሁኑ አመራር ወይም ባለጉዳይ በትክክል አይታወቅም አስር ሰዎች መልሰዋል፤
አንዳንዶቹ ያደርጋሉ አመራሮቱ ግን አድርገው አይቼ አላውቅም 7 ሰዎች የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤
አገልግሎት ለማግኘት እንጂ በስታንዳርድ አላቅም 38 ሰዎች በስታንዳርዱ መሰረት ለመገልገል ተጠይቀው
ምላሽ ሰጥተዋል፤
አንዳንድ ጽ/ቤቶች እስታዳርድ የላቸውም 3 ሰዎች ምላሽ ሰጥተዋል፤
በግልጽ ቦታ ስታዳርድቸውን አይለጥፉም ስለጽ/ቤት ለማወቅ ከባድ ነው 7 ሰዎች የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤
በጭራሽ አላውቅም 47 ሰዎች የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤
6. አገልግሎት ፈልገው ሲመጡ የእጅ መንሻ ይጠየቃሉ?
8. በተቋሙ ከዚህ በፊት ተገልግለው የሚያውቁ ከሆነ አሁን ላይ ምን የተለየ ነገር አለ?
እንግልቱ፤ ግልምጫው፤ሌብነቱለ 100% እጥፍ ጨምሯል ፤
የተሻለ መስተንግዶ እና አገልግሎት አለ የሚል ምላሽ 46 ሰዎች ሰጥተዋል፤
ምንም የተለየ ነገር የለም የሚል ምላሽ 23 ሰዎች ሰጥተዋል፤
ምንም የተለየ ነገር አላየሁም እንደውም በየምክንያቱ ባለጉዳይን ማገላታታቸውን ቀጥለዋል በተግባር
ያለው እና የሚወራው ይለያያል፤
ጠንካራ አመራርና ባለሙያ እንዲሁም በስራ ሰዓት ስራ ቦታ ላይ ይገኛሉ 3 ሰዎች ሠጥተዋል፤
በተለይ ወሳኝ ኩሁነት ስራዎች በሲስተም ነው የሚሰሩት እየተባለ የሲስተም ወቆራረጥ ብዙውን ግዜ
ችግር አለ የሚል 15 ሰዎች ሠጥተዋል፤
የተለየ ነገር ምንም ነገር አላየሁም የሚል 17 ሰዎች ሠጥተዋል፤
የሰራተኛው ቀና አመለካከት እና በትግስት በማስረዳት፤ እንዲሁም በአግባቡ ለማስተንግዶ በተወሰነ
ተሻሽሏል የሚል 7 ሰዎች ሠጥተዋል፤
ሰራተኛው ለተገልጋይ የሚሰጠውን ትኩረት በጣም ጥሩ ነው የሚል 11 ሰዎች ሠጥተዋል፤
3
በአንድ ማዕከል መገልገል ችለናል ለፀጥታ ሲባል ከበር ጀምሮ ራሳችንን የሚገጽ መታወቂያ ተጠይቀን ባጅ
ለብሰን ነው የምንገባው ይህ ጥሩ ነው ይቀጥል የሚል 3 ሰዎች ሠጥተዋል፤
ለአገልግሎት ውሳኔ የመወሰን ችግሮች አለ በጣም እጅግ የመዘግየት ነገር አለ የሚል 3 ሰዎች ሠጥተዋል፤
ከቀድሞው የተለየ ነገር የአሰራር ሁኔታ አለ ጥሩ ነው በአግባቡ ነው አመራሩን በአንድ ቦታ ባለጉዳዩ ማግኘት
ያስቻለ ነው በዚሁ ይቀጥል 19 የሚል 5 ሰዎች ሠጥተዋል፤
በመጀመሪያ ነበር ሲገባ መታወቂያ አስይዘን ባጅ የምንፈልግበት ተቋም ጠይቀን ይሰጠናል ውስጥም
ለተገልጋይ ምቹ ነበር ግን አሁን ቀረ የሚል 3 ሰዎች ሠጥተዋል፤
ምንም የተለየ ነገር የለም ባለሙያው በመጣበት ሰዓት እንደበፊትም እየተስተናገድን ነው የሚል 5 ሰዎች
ሠጥተዋል፤
9. በቅርቡ ስለተጀመረው የአንድ ማእከል አገልግሎት መረጃ አሎት? ካለው ምን ለውጥ አምጥቷል ብለው
ያምናሉ?
መረጃ የለኝም 27 ሰዎች የአንድ ማእከል አገልግሎት መረጃ እንደሌላቸው ምላሽ ሰጥተዋል፤
የአንድ ማእከል አገልግሎት ምንም ለውጥ አላመጣም በአንድ ቦታ ተሰብስቦ ወሬ ነው 25 ሰዎች የሚል
ምላሽ ሠጥተዋል፤
የአንድ ማእከል አገልግሎት በጣም ጥሩ ነው እግልትን ይቀንሳል በአንድ ቦታ በርካታ ጉዳይን ለማግኘት
ያግዛል 33 ሰዎች የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤
ጥሩ ነው ሁሉም ባለጉዳይ በአንድ ማዕከል አገልግሎት ፈልገው ሲመጡ በአግባቡ ይስተናገዳሉ 13 ሰው
የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤
የሙስናን በር እንዲዘጋ አድርጓል ጥሩ ነው የሚል ምላሥ 3 ሰው አስተያየጥ ሰጥተዋል፤
በአንድ ማዕከል ስንገለገል ለሚመለከተው ሀላፊ ተጠርቶ ችግሩ ወዲያው ይቀረፋል 10 ሰው ምላሽ
ሰጥተዋል፤
አዎ እናምናለን ለውጡ ሳይመጣ በፊት አመራሩን በመስኮት ነበር የምናገኘው አሁን ግን ፊት ለፊት
ስለምነገኘው የተሸለ ለውጥ መጥቷል 5 ሰው ይህንን አስተያየት ሰጥተዋል፤
10. በተቋሙ ቀልጣፋ አገልግሎት ለማግኘት ከህብረተሰቡ ምን ይጠበቃል
መብትን ማስጠበቅና ግዴታን መወጣት አለበት የሚል ምላሽ 19 ሰዎች አስተያየታቸውን መልሰዋል፤
አስፈላጊውን መረጃ ይዞ መገኘት እንዲሁም ተራ ጠብቆ መስተናገድ እና እጅ መንሻ አለመስጠት
የሚል ምላሽ 13 ሰዎች መልሰዋል፤
መብት እና ግዴታውን አውቆ ለሚጠየቀውን ጥያቄ ማሟላት ያለበትን ቅድመ ሁኔታ አሟልቶ
መገኘት አለበት የሚል ምላሽ 6 ሰው አስተያየቱ ሰጥቷል፤
የነቃ ተሳትፎ ማድረግ የሚል ምላሽ 3 ሰዎች አስተያየታቸውን መልሰዋል፤
ንቁ ተሳትፎ እና ብልሹ አስራሮች የሚታገል መሆን አለበት የሚል ምላሽ 5 ሰዎች መልሰዋል፤
ህብረተሰቡ አገልግሎት ለማግኘት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ ማሟላት አለበት የሚል ምላሽ 15 ሰዎች
አስተያየታቸውን መልሰዋል፤
ባለጉዳዮች ለአገልግሎት ሲመጡ የሚፈልጉትን ማሟላት እንጂ እጅ መንሻ አለመስጠት በየደረጃው
መብትን ማስጠበቅ የሚል ምላሽ 25 ሰዎች አስተያየታቸውን መልሰዋል፤
ህብረተሰቡ መተጋገል አመራሩም ማዳመጥ አስተዳደሩ መከታተል ቅሬታዎች መፈታት አለበት የሚል
ምላሽ 3 ሰዎች መልሰዋል፤
መመሪያዎችን ማውቅ ፤አገልግሎት ማግኘት መብት መሆኑን ማወቅ፤ አገልግሎትን በገንዘብ ለማግኘት
አለሞከር የሚል ምላሽ 13 ሰዎች መልሰዋል፤
4
ከህብረተሰቡ ማድረግ ያለበት በስራ ሰዓት ጊዜውንና ሰዓቱን ጠብቆ እንዲሁም መሟላት ያለበትን ነገሮች
አሟልቶ ወደ ተቋሙ መቅረብ አለበት የሚል ምላሽ 5 ሰዎች አስተያየታቸውን መልሰዋል፤
o መንግስትስ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ምን ማድረግ ይጠበቅበታል?
ከላይ ያሉ አካላት ወረድ ብሎው ደረጃ በደጃ ያለውን መዋቅር መፈተሸ አለበት፤
ሰራተኛውን ብቁ ማድረግና ቁጥጥር ማድረግ፤
በየጊዜው ምደባ ከመስራት ይልቅ ባለሙያው ተረዳድቶ እንዲሰራ በማድረግ ተጠያቂነትን ማስፈን፤
ተጠያቂነትን ማረጋገጥ አለበት ጥፋት የጠፋ አካላትን ለህግ እና ህጋዊ እርምጃ መውሰድ፤
ለባለሙያው ስልጠና መስጠት እና ማብቃት፤
እታች ወርዶ የተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ መመልከት ጠንካራን ድክመት ታችኛውን በሚገባ
መከታተል፤
አገልግሎት ፈልጎ የሚመጣውን ህብረተሰብ በአግባቡ ማስተናገድ የሚፈልገውን በተገቢው መንገድ
እንዲያገኙ ማድረግ፤
አስፈላጊውን ሰው በቦታው መመደብ እና ጥብቅ ክትትል ማድረግ እንዲሁም በዘር በዘመድ አዝማድ ስራ
ማስቆም ህጋዊ እርምጃ መውሰድ፤
በቂ የሰው ሀይል መመደብና አነቃቂ ደሞዝ መክፈል፤
የተሻለ ስነ- ምግባርና በትምህርት የተነፁ ሰዎችን ወደ ስራ ማምጣት፤
የቢሮ ግብዓት ማሟላት፤ እንዲሁም ተጠያቂነት ያለበት አሰራርን ማስፈን አለበት፤
ለህብረተሰቡ መብቱንና ግዴታውን የማሳወቅ ስራ መስራት አለበት፤
በባለጉዳይ ቀን አመራሮችን ከቀጠና ስራ ውጪ አድርጎ በቢሮ ለህብረተሰቡ አገለልግሎት እንዲሰጡ
ማድረግ አለበት፤
የዘመነ ቀልጣፋ መንገድ አሰራሩን ማዘመን ቦታውን የሚመጥን ባለሙያና ብሎም አመራሩ በቦታው
እንዲገኝ ክትትል ማድረግ፤
መንግሰት ለተገልጋይ በቂ የአገልግሎት ቦታ መመቻቸት አለበት፤ ሰራተኛውንም በደንብ ሊከታተል ይገባል፤
o የቀረ ሃሳብ ካለ ይግለጹ
አቅም ያለው አመራርና ፈፃሚዎችን በቦታው መመደብ፤
በአግባቡ የሚጠበቀውን አገልግሎት ለህብረተሰብ እየተሰጠ ስላልሆነ የተጠያቂነት አግባብ መዘርጋት፤
አገልግሎትን ከእጅ መንሻ ውጪ ማግኘት እንደሚቻል ለህብረተሰቡ ማስገንዘብ እንዲሁም
አገልግሎትን ማግኘት የህብረተሰቡ መብት ስለመሆኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መስራት፤
በመሬት እና በይዞታ አካባቢ ያለውን እንግልት የሚቀንስ አሰራር ማስፈን፤
ሰዎች የነዋሪነት መታወቂያ ያለገንዘብ የማግኘት ችግር መፍታት ከብዶታል መንግስት ይህንን ችግር
ከመሰረቱ መፍታት አለበት፤
የቀሩ ክፍተቶችን ለመሸፈን ከባድርሻ አካላት ጋር ለለውጥ መስራት፤
የተጀመረው የአንድ ማዕከል አከልግሎት አሰጣኝ ወደ ወረዳ ማስፍት የጠቀላጠፈ አገልግሎት አሰጣጥን
ማሳደግ፤
የአመራር መዋቅር ማስተካከል በዘመድ አዝማድ ሳይሆን በትክክለኛ የሚመጥን አመራር ይመድብ፤
በቀልጣፋና በተሸለ ህዝቡን እንዲያገለግል አመራሩ ላይ በደንብ መሰራት አለበት፤
የሰው ልጅ ሰላም ማግኘት አለበት ሰላም ላይ ብዙ ስራ መሰራት አለበት ስራ የሌላቸውን ስራ መፍጥር፤
የኑሮ ውድነት በጣም ችግር ውስጥ ነው ያለው ይህንን ችግር በአፋጣኝ መፍታት አለበት፤
5
ኑሮ እንዲረጋጋ ንግድ ኢንዱስትሪ ስራ አልሰራም ፈጻሚዎች በተለየ በንግድ ቁጥጥር ባለሙያዎች በትክክል
ለደሃው የማያስብ ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድባቸው እጅግ በጣም ቁጥጥር ማደረግ
አለበት፤
ግልጽ መመሪያ ማዘጋጀት በየጊዜው ለሚታዩ ችግሮች መፍትሄ የሚሰጥ መመሪያ ማዘጋጀት ወደ ሃላፊነት
የሚመጣ ሰው በችሎታ ቢሆን ኔትወርክ በዘር ባይሆን፤