You are on page 1of 18

በደ/ብ/ብ/ክ/መንግስት/ ቴ/ሙ ት/ሥ/ በሮ

በሆልና ቱሪዚም በደረቅ ምግቦች ዝግጅት ለእነጄራ ጋጋራ


አጫጭር ሥልጠና ለመስጠት የተዘጋጄ የሥለጠና
ሞጁል/መንዋል፡፡

1
አጫጫር ሥልጠናዉ የሚካተትበት የብቃት አሀዶች ዝርዝር

የሙያ ዓይነት-- ሆቴል ክቺን ኦፔረሽ /በምግብ ዝገጅት እንጄራ ጋገራ /

የብቃት አሀድ ስም የብቃት አሀድ ኮድ ተሰጠዉ ሰዓት ምርመራ


2 እንጄራ ጋገራ
1- Use Basic Methods of Cookery CST HKO1 M01 0412 20
2- Prepare Basic Ethiopian Cultural Dishes CST HKO1 M03 0412 25
3 Clean and Maintain Kitchen Premises CST HKO1 M07 0412 15
4- Follow Health, Safety and Security Procedures CST HKO1 M012 0412 10
5-Follow Workplace Hygiene Procedure CST HKO1 M013 0412 10
6- Apply 5’s Procedure CST HKO1 M020 0412 6
7-Prepare intermediate Ethiopian Cultural Dishes CST HKO2 M02 0413 25
111

ይዘት፤ ገጽ

2
1. አጫጫር ሥልጠናዉ የሚካተትበት የብቃት አሀዶች ዝርዝር---------------------------- 1
2. ምግብና የምግብ ሳይንስ----------------------------------------------------------------2
3. የምግብ ደህንነት አጠባበቅ-------------------------------------------------------------2
4. የምግብ አበሳሰል ዘዴዎችና የተዘጋጁ ምግቦች አስተሻሸግ-----------------------3
5. የአምስቱ ማዎች አተገባበር------------------------------------------------------------10
6. የእንጄራ አዘገጃጀት------------------------------------------------------------------------------10
5.1. የጤፍ እንጀራ--------------------------------------------------------------------12
5.2. የቦቆሎና የጤፍ እንጀራ-------------------------------------------------------13
5.3. የቦቆሎና የገብስ እነጄራ---------------------------------------------------------15
5.4.የጠፍና የሩዝ እንጀራ-------------------------------------------------------------16
5.5. የጤፍና የማሽላ እንጀራ--------------------------------------------------------17
5.6. የጠፍና የስካርድንች ወይም የቦይና እንጀራ--------------------------------- 17
5.7. እንጀራ ከብክነት መከላከል-----------------------------------------------------18

መግቢያ

ምገብ ዝግጅት በሁለት ታላላቅ ክፍሎች ይከፈላል

ይሄዉም፤-

1. ምግብ ማቀነቀበር ቅድሜ ምግብ ዝግጅት /የባልቲና ዉጤቶች አዘገጃጀት/

3
2. ባሕላዊና ዘመናዊ የምግብ ዝግጅት ሲሁን የዝህ ማንዋል ዝግጅት የእነጀራን አዘገጃጀት በዝርዘር የያዘ
ነዉ

ዝርዝር ዓላማ

 ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ የምግብ አዘገጃጀት ፤ምግብን ለረዥም ጊዜ የማቆያ ዜዴዎችንና የአስተሸሸግ
ጭዉቀት ማጠናከር

አጠቃላይ ዓላማ

በፓኬጅ ለታቀፉ የሥራ መስኮች ለሚሳተፉ አንቀሳቃሾች በቴክኒኪና ሙያ መስክ ያለባችዉን የክህሎት
ክፍተት መሙላትምግብን ከብክለት መከላከልና በምግብ መበከል ምክንያት የሚመጡ በሽታዎችንና ኪሳራን
መከላከል

 በመሰኩ የተሰማሩትን የሕብረተሰብ ክፍሎች በምግብ አየያዝ አዘገጃጀትና አስተሸሸግ በኩል ያለዉን
የክህሎት ክፍተት በመሙላት ጥራቱን የጠበቀ የምግብ ሸቀጣ ሸቀጥ አቅራቢ በገበያ ላይ ብቁ
ተወዳዳሪ ማድረግ፡፡

1. ምግብና የምግብ ሳይንስ

ትርጉም

የምግብ ሳይንስ ማለት ስለ ምግብ ምንጮች፣ ስለንጥረ ምግቦችና ጥቅማቸው፣ ስለ ምግብ ደህነነት
አጠባበበቅ፣ የምግብ መበከል ከምን እንደሚመጣና መከላከያውን፣ ምግብ ሳይበላሽ ለረዥም ጊዜ የማቆያ
ዘዴዎችን፣ የአካባቢና የግል ንፅህና አጠባበቅን ስለምግቦችን አዘገጃጀት አያያዝና አስተሻሸግ የምናጠናበት
ሳይንስ ነው፡፡

4
a. ንጥረ ምግቦችና ጥቅማቸው

ንጥረ ምግቦች ማለት በምግብ ውስጥ የሚገኙና ለሰውነታቸን የተለያየ ጥቅሞች የሚሠጡ የምግብ ክፍሎች
ናቸው፡፡ እነሱም፡- ፕሮቲን፣ ካርቦሃይድሬት፣ ቫይታሚን፣ ማዕድንናት፣ ቅባትና ውሃ ናቸው፡፡

1. ፕሮቲን

ፕሮቲን እጅግ ጠቃሚ የሆነ አልሚ ምግብ ነው፡፡ ለዕድገት ጡንቻዎችን ለማዳበር፣ አጥንቶችንና ጥርሶችን
ለማጠንከር ሰውነታችን በየዕለቱ ከፍተኛ መጠን ያለው ፕሮቲን 1

ያስፈልገዋል፡፡

ፕሮቲን የሚገኝባቸው የምግብ አይነቶች ሥጋ፣ ዓሣ፣ ወተትና የወተት ውጤቶች ከቂቤ በስተቀር፣ አተር፣
ሽንብራ፣ እንቁላል፣ ባቄላና ምስር እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

2. ቅባትና ካርቦሃይድሬት

ለሰው ልጅ ሰውነት ኃይልን ይሰጣል፡፡ የሚገኘውም ከድንች፣ ከስኳር፣ ከማር፣ ከቂቤ፣ ከዘይት፣ ከጤፍ፣ ከበቆሎ፣
ከማሽላ፣ ከዳጉሳ፣ ከአጃና ከመሳሰሉት ነው፡፡

3. ማዕድናት

እንደ ብረት፣ ካልሺየም፣ እና የመሳሰሉት በምግብ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ብረት ለቀይ ደም ሴሎች
የሚያገለግል ከፍተኛ ንጥረ ምግብ ነው፡፡ ካልሺየም አጥንትንና ጥርስን ለማጠንከር የሚጠቅም ነው፡፡
የካልሺየም ምንጭ የሆኑ የምግብ ዓይነቶች ወተትና የወተት ውጤቶች ጤፍ፣ ቦለቄ፣ ዳጉሳ፣ እንሰት፣ ሽንብራ
ወዘተ ናቸው፡፡

4. ቫይታሚን

የቫይታሚን ይዘት ያላቸው የምግብ አይነቶች

5
 ሰውነትን ከበሽታ የመከላከል
 የሰውነትን ቆዳ ጤንነት ለመጠበቅና
 የሰውነት ክፍል በትክክል ሥራውን እንዲያከናውን ለማድረግ ይረዱናል

የቫይታሚን ምንጭ የሆኑ የምግብ አይነቶች ወተት፣ ቂቤ፣ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ እንቁላል እና የመሳሰሉትን
ይይዛል፡፡

የእነዚህ ንጥረ ምግቦች በሰውነታችን ውስጥ በበቂ ሁኔታ ተሟልቶ አለመገኘት ሰውነታችንን ለተለያዩ
በሽታዎች ሊያጋልጥ ይችላል፡፡

2. . የምግብ ደህንነት አጠባበቅ

የምግብ ደህንት አጠባበቅ ማለት ምግብ በተለያዩ መንገዶች ሳይበላሹ የማቆየት ዘዴ ነው፡፡ ምግብ ለብዙ ጊዜ
ሲቆይ ለብልሽት የሚዳረግባቸው መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፡፡ 2

ሀ/ በተፈጥሮ ባሉት ንጥረነገሮች ላይ በሚመጣ ለውጥ


ለ/ በልዩ ልዩ ተባዮች፡- (አይጥ፣ ዝንብ፣ ነቀዝ፣ ወዘተ…)
ሐ/ በልዩ ልዩ ጥቃቅን ሕዋሳት፡- ባክቴሪያ እንደ ሻጋታ፣ እርሾ፣ ወዘተ ….

ምግብን ሳይበላሽ ለረጅም ጊዜ ማቆያ ዘዴዎች

ምግብን የሚያበላሹ ልዩ ልዩ ሕዋሳቶችን ለመራባት እርጥበት ያስፈልጋቸዋል፡፡

ሀ/ ስለዚህ ምግብ ውስጥ ያለውን እርጥበት ወይም ውሃ በማስወገድ፣

ለ/ ምግብን አብስሎ በውስጡ የሚገኙትን ሕዋሳት በማጥፋ ማቆየት ይቻላል፡፡

ሐ/ ምግብን አቀዝቅዞ ያሉትን ሕዋሳትን እንዳይበዙ በማድረግ

መ/ በምግብ ውስጥ ቅመማ ቅመም በመጨመር

ለምሳሌ፡- ጨው፣ ስኳር፣ ኮምጣጤ እና የተለያዩ ቅመማ ቅመሞች

6
 የአካባቢና የግል ንፅህና አጠባበቅ

ምግብ ከምርት አንስቶ ለሰው ልጅ ፍጆታ እስከሚውል ድረስ ልዩ እንክብካቤ መደረግ ይኖርበታል፡፡ ምግብ
በሚዘጋጅበት ቦታና ለማዘጋጀት የሚውሉ ዕቃዎችን ንፅህና መጠበቅ አለበት፡፡ እንደዚሁም ከምግብ ጋራ ንክኪ
ያለው ሰው የግል ንፅህናውና ጤንነቱን ጭምር በደንብ መጠበቅ ይኖርበታል፡፡

ንጽህና የጎደለው አካባቢ የዝንብና የተላላፊ በሽታ መንስኤ ሲሆኑ የሚችሉ ጥቃቅን ሕዋሳት መራቢያ
ይሆናል፡፡ የግል ንጽህና በተለይም የእጅና የሌሎች የአካል ክፍሎች ንጽህና ጉድለት፣ በሚዘጋጀው ምግብ ዙሪያ
ማስነጠስና ማሳል የመሳሰሉት፣ የምግብ ማዘጋጃ ዕቃዎች አጠቃቀምና ንፅህና ጉድለት፣ ተገቢውን ዕቃ
በተገቢው አገልግሎት ላይ አለማዋል የምግብን መበከል ያስከትላል፡፡

የምግብ መበከል ተመጋቢውን መመረዝና በሽታ ላይ መጣል ብሎም ሞትን ሊያስከትል ሲችል በአቅርቦትም
በኩል ሲታይ የጥራትን ማነስና፣ ተፈላጊነትን ማጣት እና ባጠቃላይ ኪሣራን በግልና በሀገር ደረጃ ያስከትላል፡፡
አንድ ምግብን የሚያዘጋጅ ሰው የግል ንጽህናውን መጠበቅ አለበት፡፡ ይኸውም፡
3

 ፀጉርን በንጽህና መያዝና ፀጉርን መሸፈን

 እጆችን መታጠብ
 ጥፍር መቁረጥ
 ገላ መታጠብ
 ንፁህ ልብስና ሽርጥ መልበስ
 ጥርስ መፋቅ
 በምግብና በምግብ ዙሪያ አለመሳልና አለማስነጠስ
 በተላላፊ በሽታ የተያዘን ሰው እስኪድን ድረስ በምግብ ሥራ እንዳይሳተፍ ማድረግ
 የምግብ ሠራተኛ ወደ ምግብ ሥራ ከመግባቱ በፊት መታከም እንዲሁም በሥራ ላይ ያለ ሠራተኛ
በየጊዜው የሕክምና ምርመራ ማድረግ አለበት
 እርጥብና ደረቅ ምግቦችን ለይቶ ማስቀመጥ
 እርጥብ ምግቦችን በፀሀይ በምናሰጣበት ጊዜ የፀሐይ ብርሃን ማስተላለፍ በሚችል ስስ ጨርቅ መሸፈን
 የሚታሸጉ ምግቦችን በወቅቱ ማሸግ
3. የምግብ አበሳሰል ዘዴዎች

7
መሠረታዊ የምግብ አበሳሰል ዘዴዎች በሁለት ይከፈላሉ
1. በፈሳሽ የማብሰል
ሀ. መቀቀል
ለ. ማገንፈል
ሐ. ወጥ መሥራት
መ. ፖች በማደረግ ፤በምንተከተክ ዉሀ ላይ ማብሰል
ሰ. በሬይዝ በማደረግ ጣዕሙን በዋጠ ማብሰል
2. በደረቁ ማብሰል
ሀ. መጥበስ 1 ኛ፡ በትንሽ ዘይት ማብሰል 2 ኛ. በብዙ ዘይት ማብሰል
ለ. አሮስቶ
ሐ. ማይክሮ ዌቭ

3.የተዘጋጁ ምግቦች አስተሻሸግ

ምግቦችን በምናሽግበት ጊዜ እንደየ ምግቡ አይነት የተለያዩ አይነት ዕቃዎችን መጠቀም የምንችል ሲሆን
በጠቅላላው ምግቦችን ለረዥም ጊዜ እንዲቆዩ በምናሽግበት ጊዜ የምንጠቀምባቸው ዕቃዎች፡-

 ለደረቅ ምግብ ጠንካራ ፕላስቲኮችን መጠቀም


 ለእርጥብ ምግቦች የሚገጥም ክዳን ያላቸውን ብርጭቆ ነክ ማሸጊያዎችን መጠቀም

ምግብን በምናሽግበት ጊዜ በማሸጊያው ላይ ስያሜ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ፡- የምርቱ አይነት፣


የተመረተበት ቀን፣ ለምርቱ የተጠቀምንባቸው ግብዓቶች፣ የድርጅቱ ስም (ምርቱን የሚያመርተው)፣ ቢቻል
የምረቱ አጠቃቀምና የመሳሰሉትን በማካተት ስያሜ ከሰጠን በኋላ ለገበያ ማቅረብ ይቻላል፡፡
ምገብ ማቀናበር
ምገብ ማቀናበር ማለት ቅሜማ ቅሜሞችን ማዘጋለትና ጥረእቃዎችን በማቀናጀት
ቅድሜዝግጅት ማድረግና ምግብ ለመመገብ አስከሚመች ድረስ የማዘጋጀት ሂደት ነዉ

የቅሜማ ቅሜሞች አዘገጃጀትና አሰተሸሻጋችዉ


የቅሜማ ቅሜሞች ጥቅም ምግብን ማጣፈጥ ምግብ ሳይበላሽ ለረዥም ጊዜ ማቆየት
ለብቻና በጥምረት ተዘጋጅተዉ የታሸጉ ቅሜማ ቅሜሞች ገበያ ላይ ሲቀርቡ የገቢ መስገኛና አንዳንድ
ቅሜማ ቅሜሞች ለጤንነት አስፈላጊ ናቸዉ ለምሳሌ ነጭ ሽንኩርት ዝንጅብል አብሽ ጥቁር
አዝሙድ ወ ዘተ
በርበሬ በተለያየ መልክ ሊዘጋጅ ይችላል ለምሳሌ ዛላዉ በርበሬ ተቀመምሞ የተፈጨ፤
አፍርንጅ፤አዋዜ ፤ዳታና ሚጥሚጣ ለመሳሰሉት ስሆን የምግብነት ጥቅሙም ለወጥ መልክ መስጠትና
፤ማባያነት የምግብነትና የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡

የአምስቱ ማዎች አሠራር ሥርዕት መከተል


1. ማጣራት

8
2. ማስቀመጥ
3. ማጽዳት
4. ማላመድ
5. መዝለቅ
 ማጣራት /መለየት/፡- የሚሠራና የማይሠራ ፤የሚወገድ፤የሚጠግን፤ንጹህና የቆሸሸ መለየት
 ማስቀመጥ መሆን የሚገባዉን ቦታ መስጠት /መሰየም
 ማጽዳት ፡- መታጠብ የሚገባዉን ማጠብ መጠረግ የሚገባዉን መጥረግ መጠገን የሚገባዉን
መጠገን መወገድ የሚገባዉን ማስወገድ
 ማላመድ፡- ስሙን ጽፎ መለያ በመሥራት ማነኛዉንም ነገር ከተጠቀሙ በኃላ
ወደ ተለመደዉ ቦታ በመመለስ እነደለመድ ማድረግ
ደረጃዉን የጠበቀ አሰራር እነድሆን ማድረግ
መዝለቅ፡- ይህን ደረጃዉን የጠበቀ አሰራር ቀጣይነት ያለዉ ማድረግ

7. የእንጄራ አዘገጃጀት

እንጄራ ከተለያ የእህል ዘሮች ሊዘጋጅ የሚችል የምግብ አይነት ነዉ ለምሳሌ ከጤፍ፤ ከገብስ፤
ቦቆሎ፤ ማሽላ፤ ከቦቆሎ፤ ቦይና ወዘተ..ሊዘጋጅ ይችላል ፡፡ እንድሁም እንዳስፈላጊነቱ ከተለያዩ
የእህል ዘሮችና ከለሎእ የዕጽዋይት ዉጤቶች ጋር በመቀየጥ እንጀራ ሊዘጋጅ የችላል፡፡

የተጠቀለለ እንጀራ

5.1. የጤፍ እንጀራ


 25 እንጀራ ለመጋገር 5 ኪሎ ነጭ ወይም ቀይ ጤፍ የሚያስፈልግ ሲሆን ጥራቱን የጥበቀ
እነጀራ ለመጋገር
ሀ/ የፍሬዉ ዓይነት ትናንሽ
ለ/ ከአሸዋ ነጻ የሆነ
ሐ/ ዝናብ ያልመጣዉ/ዝናብ የመታዉ ጤፍ እምክ እምክ የምል ሽታ ይኖረዋል

የጤፍ እንጀራ ጥቅሙ

 ቴፍ በአብዘኛዉ ብረት/ አይረን/ የተባለዉን ማዕድን ለሰዉነታችን ይሰጣል፡፡

9
አዘገጃጀቱ

1. 25 እንጀራ ለመጋገር 5 ኪሎ ነጭ ወይም ቀይ ጤፍ


2. ጤፉን በወንፍት ነፍቶ ማበጠርና አብሽና ትንሽ ድንብላል ጨምሮ ማስፈጨት
3. የተፈጨዉን ዱቀት በወንፈት መንፋት
4. ዱቀቱን በዉሀ ማቡካት
5. እነዳካባቢዉ አየር ሁኔታ ኩፍ ስል/ሲቦካ/ ሻጋታዉን ለመከላከል ዉሀ በማድረግ ከላ\ ቀራራዉን
ማፍሰስና ለአብስት የሚበቃ ሊጥ መዉሰድ
6. ዉሀ አፍልቶ ሊጡን እየጨመሩ በማወፈር አብስቱን ማበሰል
7. አብስቱን ሊጡ ዉስጥ ጨምሮ ኩፍ አስከሚል መጠበቅ
8. ምጣዱን ጥዶ ካጋሉ በኃላ በቅባት እህል ማሰስ አድስ ሚጣድ ከሆነ ማማሸት
9. ምጣዱ ሲግል ከሊጡ በማዞሪያ እየቀዱ መጋገር
10. አከንባሎዉን ከድኖ እስክበስል መጠበቅ ስበስል ዳርዳሩ መነሳት ይጀምራል
11. በመጨረሻ በሰፈድ እያወጡ ሌማት ዉስጥ ማስቀመጥ

የጤፍ እንጀራ

የእንጀራ ጥራት መለኪያዎች

ጥራት ያለዉ እንጀራ

 የልኮመጠጠ
 አይን ከዳር እስከዳር ያለዉ
 ነጭ ወይም ቀይ ጤፍ እንጀራ በፈለጉት መልክ ሲገኝ

10
 ያልተቆራረሰ
 ሰበከቱ ያማረ
 በእርጥብና ቆሸሸእጅ ያልተነካካ

 ከመስሪያ ዕቃዎች ጉድለት የተነሳ ቶሎ የማይሻግት


 ለምለም ወይም ለስላሳ እንጀራ
5.2. የቦቆሎና የጤፍ እንጀራ አዘገጃጀት
 6 ኪሎ የቦቆሎና 2 ኪሎ የጤፍ ዱቄትደባልቆ እርሾጨምሮ ማቡካት
 ሊጡን አንድ ቀን ማሳደር
 አበስቱን ማዘጋጀት
 የተዘጋጀዉን አብስት ከሊጡ ጋር ማዋሄድ
 ሊጡ ኩፍ ስል መጋገር

75%ቦቆሎና 25%የጤፍ እንጀራ

11
5.3. የቦቆሎና የገብስ እነጄራ
 6 ኪሎ የቦቆሎና 3 ኪሎ የገብስ ዱቄት ለክቶ ዱቄቱን ማደባለቅ
 የተዘጋጀዉን ዱቀት እርሾ ጨምሮ ማቡካት
 ሊጡ እንድቦካ አንድ ቀን ማሳደር
 ማቅጠንናአበስቱን ማዘጋጀት
 የተዘጋጀዉን አብስት ከሊጡ ጋር ማዋሄድና ኩፍ ስል መጋገር

67%ቦቆሎና 33%የገብስ እንጀራ

12
5.4.የጠፍና የሩዝ እንጀራ
 7 ኪሎ የቦቆሎና 3 ኪሎ የሩዝ ዱቄት ለክቶ ዱቄቱን ማደባለቅ
 የተዘጋጀዉን ዱቀት እርሾ ጨምሮ ማቡካት
 ሊጡ እንድቦካ አንድ ቀን ማሳደር
 ማቅጠንናአበስቱን ማዘጋጀት
 የተዘጋጀዉን አብስት ከሊጡ ጋር ማዋሄድና ኩፍ ስል መጋገር

70%ቦቆሎና 30%ሩዝ እንጀራ

13
5.4. የጤፍና የማሽላ እንጀራ
 8 ኪሎ የቦቆሎና 2 ኪሎ የማሽላ ዱቄት ለክቶ ዱቄቱን ማደባለቅ
 የተዘጋጀዉን ዱቀት እርሾ ጨምሮ ማቡካት
 ሊጡ እንድቦካ አንድ ቀን ማሳደር
 ማቅጠንናአበስቱን ማዘጋጀት
 የተዘጋጀዉን አብስት ከሊጡ ጋር ማዋሄድና ኩፍ ስል መጋገር

80%ቦቆሎና 20%ሩዝ እንጀራ

14
5.5. የጠፍና የስካርድንች ወይም የቦይና እንጀራ

 8 ኪሎ የቦቆሎና 2 ኪሎ የስካር ድንች ወይም የቦይና ዱቄት ለክቶ ዱቄቱን ማደባለቅ


 የተዘጋጀዉን ዱቀት እርሾ ጨምሮ ማቡካት
 ሊጡ እንድቦካ አንድ ቀን ማሳደር
 ማቅጠንናአበስቱን ማዘጋጀት
 የተዘጋጀዉን አብስት ከሊጡ ጋር ማዋሄድና ኩፍ ስል መጋገር

80%ቦቆሎና 20%ሩዝ እንጀራ

15
5.6. እንጀራ ከብክነት መከላከል
1. ስጋገር እንዳይሰባበር ጥንቃቄ ማድረግ
2. በቀላሉ እንዳይሻግት ማቡክያዉንና መጋገሪያ ዕቃዎእን በየጊዜዉ በማጠብ ንጽሕናዉን
መጠበቅ
3. የበሰለ እንጀራ ከምጣድ ለመዉጣት እጅን ንጹህና ደረቅ ማድረገ
4. እነጀራ የመወጣበትን ሰፌድና የሚቀመጥበትን መሶብ በማጠብና በማናፈስንጽህናዉን
መጠበቅ
5. ሲቀዘቅዝ የሚቀመጥበትን ማቆያ ላስቲክ ማጠብና መድረቅ
6. ድርቆሽ በማድረግ ለረዥም ጊዜ ሳይበላሽ አንድቆይና ለማጋጋዝ አመቺ አንድሆን ማድረግ
7. በድርቆሽ መልክ በገበያ ላይ እንድለመድ ማድረግ

እንጀራ በድርቆሽ መልክ

 እርጥቡን እንጀራ በአራት ማዕዘን በመቁረጥ በያዘዉ ቅርጽ ለማሸግ እንድመች አድርጎ
ስስዐርቅ በመሸፈን ማድረቅ የደረቀዉን እነጀራ የነበረዉን ቅርጽ ሳይለዉጥ አሽጎ በላዩ ላይ
ስሙን ቀኑንና አዘገጃጀት ሂደቱን ጽፎ በመለጠፍ ለገበያ ማቀረግ፡፡
 ሌላዉ እንጀራዉን ሳይቆራርጥ ሙለዉን በጸሐይ ላይ ማድረቅ ከደረቀም በኃላ ለፈርፈር
አንደምሆን ሰባብሮ በማሸግ ስሙን ቀኑንና አዘገጃጀት ሂደቱን ጽፎ በመለጠፍ ለገበያ
ማቀረግ፡፡

ጥቅሙ

 ራቅ ወዳሉ ሀገሮች በቀላሉ ሳይበላሽ ለማጋጋዝ


 በተፈለገ ሰዓት በየመሸጫ ቦታዎች እንዳስፈላግነቱ እንድገኝ ለማድረግ
 ብክነትን ለመከላከል

የእንጀራ መሸጊያና አስተሸሸጉ


 እርጥብ እንጀራን ሳሳ ባለ ላስቲክ መሸፈን
 ለሽያጭ በሚፈልገዉ መጠን አያንዳንዱን ጠቅልሎ ተጠቃሚ ቆርጦ ለመጠቀም
እንደሚያመቸዉ በማድረግ በማሸጊያ ላስቲክ በመሸግ ለገበያ ማቅረብ

16
የእንጀራ ማሸጊያ ላስቲክ

ምስጋና

ይህ በወቅቱ ወጥ በሆነ መልኩ ስልጠና ለመስጠት ተፈልጊ የሆነዉን የዘርፉም እቅድ የነበረዉን
በተገባር ላየ በማዋል የሠልጠና መርጃ መሣሪያ ለማዘጋጀት ቅድ ሁነታዎችን በማመቻቼት
ዉጠት ተኮር ሥራ እንድሰራ የረዳንን የደቡብ ቴ/ሙ/ት/ሥ/ብሮና አቶ ሽመልስ በኔና በሙያ
አጋሮቼ ስም አመሰግናለሁ፡፡

17
አዘጋጅ ተዋበች ጴጥሮስ

18

You might also like