You are on page 1of 4

የ 2014 ዓ.

ም የፋሲካ ትንሳኤ በዓል እና የዮፕ ታለንት ሾው የመጨረሻ ውድድር ልዩ የመዝናኛ ፕሮግራምን በጋራ
ለማዘጋጀት የቀረበ እቅድ

ማህሌት ሰለሞን ፊልም ፕሮዳክሽን

ለኢትዮጵያ ቴሌቭዥን

መጋቢ
ቀን: 10/07/14 ዓ.ም
ቁጥር: ማሰፊፕ/ /2014

ለኢትዮጵያ ቴሌቭዥን

የስፖንስርሽፕ ድጋፍ ስለ መጠየቅ

”ዮጵ የትወና ታለንት ሾው“ የተሰኘው ይህ የቴሌቪዥን የትወና፣ የክህሎት ውድድር በ”ማኅሌት ሰለሞን የፊልም ፕሮዳክሽን“
እና ”በ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን’’ (ETV) የጋር ትብብር እየተዘጋጅ ዘወትር ቅዳሜ 11፡30 ላይ የ 60 ደቂቃ የስርጭት ቆይታን
ተጠቅሞ የሚቀርብ አዝናኝና ቁም ነገር አዘል እና አስቂኝ እንዲሁም ከፍተኛ የደረጃ ጥራቱን የጠበቀ እጂግ ተወዳጅ

ማህሌት ሰለሞን ፊልም ፕሮዳክሽን


ሳምንታዊ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ነው፡፡

ይህ ”ዮጵ የትወና ታለንት ሾው“ የተሰኘው የቴሌቪዥን የትወና፣ የክህሎት ውድድር የፕሮግራም ይዘት ጥራቱንና እጂግ
ተወዳጅነቱን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጨመረ ስርጭቱን ለተመልካች ማድረስ ከጀመረ እነሆ ከግማሽ አመት በላይ ያስቆጠርን
ሲሆን የዝግጂታችን አንደኛ ምእራፍ (ሲዝን) አሸናፊዎችን አውዳድረን በእለት ትንሳኤ በታላቅ ድምቀትና ክብር ለመሸለም
ቅድመ ዝግጂታችንን አጠናቀን ከወዲሁ እንገኛለን፡፡

በተጨማሪም የእናንተው ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ይህ ”ዮጵ የትወና ታለንት ሾው“ መዝጊያንና የእለተ ትንሳእኤ በአል ልዩ
የአንድ ሰአት የመዝናኛ ዝግጂታችንን የአየር ስርጭት ድጋፍ በማድረግ ለዝግጂታችን ድምቀት የበኩላችሁን አስተዋጾ
እንዲያበረክቱልን በአክብሮት እየጠየቅን ስለ ፕሮግራሙ አጠቃላይ ይዘት እና የስፖንሰርሽፕ ድጋፍ እንዲሁም ተያያዢ
ጥቅማጥቅሞቹ ከዚህ ደብዳቤ ጋር ሰፋ ያለ ማብራሪያን አባሪ በማድረግ በላክነው ፕሮፖዛል ውስጥ ማግኘት የሚችሉ
መሆኑን እያሳወቅን ድርጅታችሁ ለሚያደርግልን ድጋፍና አዎንታዊ ምላሽ በማህሌት ፊልም ፕሮዳክሽን፣ እና በሰፊው
የፕሮግራሙ ታዳሚዎች ስም አስቀድመን ከልብ የምናመሰግን መሆኑን በትህትና እንገልጻለን፡

ከሰላምታ ጋር

ማህሌት ሰለሞን
ዋና ስራ አስኪያጅ

1
ማህሌት ሰለሞን ፊልም ፕሮዳክሽን : +251 911 242 242 : mishuyid@gmail.com
1。 መግቢያ

ይህ ፕሮፖዛል የተዘጋጀበት ዓላማ ”ዮጵ የትወና ታለንት ሾው“ አንደኛ ምእራፍ (ሲዝን) አሸናፊዎችን አውዳድረን
ለመሸለም በ 2014 ዓም በመላው ኢትዮጵያ በክርስትና ሀይማኖት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረውን የትንሳኤ ልዩ
የበዓል የቴሌቭዥን የመዝናኛ ፕሮግራም ለማዘጋጀት የስፖንሰርሽፕ ድጋፍ በማድረግ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እና
በዝግጅቱ ላይ ከኢትዮጵያ ቴሌቭዢንና ከማህሌት ሰለሞን ፊልም ፕሮዳክሽን እንዲሁም ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር
በጋራ እንዲሰሩ እድልን የሚፈጥር ነው።

ይህ የትንሳኤ በዓል ልዩ የቴሌቭዥን የመዝናኛ ፕሮግራም በማህሌት ፊልም ፕሮዳክሽን ከኢትዮጵያ ቴሌቭዢን ጋር
በመተባበር የተዘጋጅ ሲሆን የፕሮግራም ተቀዳሚ ዓላማ በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሃገር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን
የበዓሉ አክባሪዎችን በእለቱ በማዝናናት ቁም ነገር ማስጨበጥ ሲሆን ለአጋርና ስፖንሰር አድራጊ ድርጅቶች ምርትና
አገልግሎታቸውን በስፋት በማስተዋወቅ የገበያ እድልን የሚፈጥር ታላቅ የመዝናኛ ዝግጅት ነው።

የዝግጅቱን ዓላማ ከግብ ለማድረስም በፕሮግራሙ ይዘት ውስጥ የተካተቱ ከበዓሉ ጋር ተያያዥ የሆኑ አዝናኝና ቁም
ነገር አዘል ዝግጂቶች፣ አጫጫር የመድረክ ድራማዎች፣ የባህላዊና የዘመናዊ የሙዚቃ ዳንስና ውዝዋዜ፣ ትዕይንቶች፣

ማህሌት ሰለሞን ፊልም ፕሮዳክሽን


አስቂኝ የኮሜዲ ቀልዶች በበሳል እና ተወዳጅ የመድረክ ባለሙያዎች እየተመራ ለፕሮግራሙ ታዳሚዎችና ለመላው
የኢትዮጵያ ህዝብ በቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት ይቀርባል።

በዚህ በይዘቱ ልዩና አዝናኝ የበዓል ዝግጅት ለህዝብ እንዲደርስና የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የአዳራሽ ስፖንሰር
እንዲያደርግ እየጠየቅን በእለቱ የቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት ላይና በሌሎች የኢትዮጵያ ቴሌቭዢን ፕሮግራሞች ላይ
ምርትና አገልግሎታቸሁን በስፋት የምናስተዋውቅ ይሆናል።

2。 የዝግጅቱ ይዘት
የ 2014 ዓ.ም የትንሳኤ በዓል ልዩ የመዝናኛ ዝግጅት በዋናነት በዓሉን ለሚያኩብሩ ኢትዮጵያዊያን በማዝናናት
ቁም ነገር ማስጨበጥ ሲሆን በተጨማሪም በታላቅ ጉጉት እየተጠበቀ ያለውን የዮጵ የቴሌቭዢን ታለንት ሾው
አንደኛ ምእራፍ (ሲዝን) አሸናፊዎችን አውዳድረን በእለት ትንሳኤ በታላቅ ድምቀትና ክብር ለመሸለም ነው።

ከዚህ በተጨማሪም ይህ ዝግጅት በይዘቱ ይበልጥ አዝናኝ እንዲሆን ከትንሳኤ በዓል አከባበር ጋር ተያያዥ የሆኑ
የመዝናኛ ፕሮግራሞችን ከልዩ ልዩ የድራማ፣ የሙዚቃ፣ የዘመናዊ ዳንስና ባህላዊ ውዝዋዜ ዝግጅቶች በተጨማሪ ጥሪ
ተደርጎላቸው ከሚታደሙ የጥበቡ አለም ሙህራኖች እና ታዋቂ ሰዎች፡ ስለ ኢትዮጵያ የጥበብ ኢንዱስትሪ ቃለ
መጠይቅ ጋር የህይወት ልምድና ተሞክሮ ማጋራት ይቀርባል።

2.1 የዝግጅቱ ዝርዝር ይዘት


 ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ቦታ ቦታቸውን ይይዛሉ
 የፕሮግራሙ ተወዳዳሪዎችና ዳኞች በደማቅ ሁኔታ ይገባሉ
 የትንሳኤ የበዓል ሙዚቃ በድራማ መልክ ይቀርባል 2
 ዮጵ የቴሌቭዢን ታለንት ሾው አንደኛ ምእራፍ (ሲዝን) የመጨረሻ ዙር ተወዳዳሪዎች ስራቸውን ያቀርባሉ
 ለአሸናፊዎች ሽልማት ይበረከትላቸዋል
3。የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች

በ 2014 የትንሳኤ ልዩ የበዓል የመዝናኛ ዝግጅት እና ዮጵ የቴሌቭዢን ታለንት ሾው አንደኛ ምእራፍ (ሲዝን)
የመጨረሻ ውድድር በደማቅና በልዩ ሁኔታ ለመካፈል ጥሪ ተደርጎላቸው ከሚቀርቡት የፕሮግራሙ የክብር እንግዶች
ውስጥ

1. ከአዲስ አበባ ዩኒቭርስቲ


 የአዲስ አበባ ዩኒቭርስቲ ትያትር ጥበባት የትምህርት ክፍል መምህራን
 የአዲስ አበባ ዩኒቭርስቲ የትያትር ጥበባት የትምህርት ክፍል የ 2014 ተመራቂ ተማሪዎች
2. ከትያትርና ክፊልሙ ኢንዱስትሪ ውስጥ
 የፊልም ባለሙያ፣ መምህርት፣ ደራሲ፣ ዳይሬክተር፣ ተዋናይት እናም በማለዳ ኮከቦች የትወና
ውድድር የአይዶል ዳኛ ማህሌት ሰለሞን ፣
 ክቡር የፊልምና የትያትርና ባለሙያ፣ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የትወና ትምህርት ሌክቸረር
ፕሮፌሰር ሙልጌታ ጃዋሬ

ማህሌት ሰለሞን ፊልም ፕሮዳክሽን


 የፊልም ባለሙያ፣ ዳይሬክተር እና በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የትወና ትምህርት ሌክቸረር እና
እጩ ዶክተር አንተነህ ሰይፉ፣
በተጨማሪ ከሙዚቃው ከትያትር አለም የተወጣጡ ታዋቂ ባለሙያዎች እና ክማህበረሰቡ የሚታደሙ
ሙህራኖች፣ ከሀይማኖት ተቋማት በመወከል የሚመጡ የሀይማኖት መሪዎች፣ የዮፕ ታለንት ሾው
ወዳጆች እና ሌሎችም ግለሰቦች ተሳታፊዎች ይሆናሉ።
4。 ከኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የምንጠይቀው የስፖንሰርሺፕ ድጋፍ አይነቶች

የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ለዚህ ልዩ የትንሳኤ በዓል የመዝናኛ ፕሮግራም እና ለዮፕ የቴሌቭዢን ታለንት ሾው የመጨረሻ
የቴሌቭዥን ውድድር ዝግጅት የአንድ ሰአት የስርጭት ጊዜን በስፖንሰርሺፕ ድጋፍ እንዲያደርግልን ነው።

5。ቅድመ ምስጋና
የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ለዚህ ልዩ የትንሳኤ በዓል የመዝናኛ ፕሮግራም እና ለዮፕ የቴሌቭዢን ታለንት ሾው
የመጨረሻ ዙር የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ዝግጅት የአንድ ሰአት አየር ላይ ስርጭት ሽፋን ስፖንሰርሺፕ ድጋፍ
በማድረጉ የማህሌት ሰለሞን ፊልም ፕሮዳክሽን (ሚሽካ ስቱዲዮ) በድርጅቱ ሰራተኞች፣ በዮጵ ተወዳድሪዎች፣
እንዲሁም በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ስም በቅድሚያ ከልብ እናመሰኛለን።

ማህሌት ሰለሞን የፊልም ፕሮዳክሽን


መጋቢት 2014 ዓ.ም

You might also like