Professional Documents
Culture Documents
2016 Tor
2016 Tor
የ 2016 ዘመን መለወጫ በዓል ፤የመስቀል በዓል እና የኢሬቻ በዓላትን የሚደርሱ አደጋዎችን
ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የኮልፌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የስራ ማስመሰል ልምምድ የተዘጋጀ
ቢጋር (TOR)
1. መግቢያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን የኮልፌ ቅርንጫፍ
ጽ/ቤት በከተማው ውስጥ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን አስቀድሞ
በመከላከል፣አደጋ ሲከሰትም ፈጥኖ በመድረስና በመቆጣጠር በህብረተሰቡ ህይወትና ንብረት
ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት በመቀነስ ፣በድንገተኛ አደጋዎች ለሚጎዱ የህብረተሰብ
ክፍሎች የቅድመ ሆስፒታል ህክምናና አምቡላንስ አገልግሎት መስጠት እንዲሁም አስቾኳይ
የአደጋ ጊዜ እርዳታ ሰጭ የሥራ ክፍል በመያዝ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
በዚህም መሰረት ቅ/ጽ/ቤቱ የተሰጠውን ኃላፊነትና ተግባር በአግባቡ ለመወጣትና ተልዕኮውን
ለማሳካት ያስችለው ዘንድ በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ህብረተሰቡንና ባለድርሻ
አካላትን በማሳተፍ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ፡፡ በመሆኑም ስራችንን በተቀላጠፈ ሁኔታ
ለመስራት የ 2016 የመስቀል በዓል እና የኢሬቻ በዓላትን የሚደርሱ አደጋዎችን ለመከላከል እና
ለመቆጣጠር የአደጋ ማስመሰለል ልምምድ(ሲሙላሽን) በማስመልከት ስልጠና ለመስጠት
ከአደጋ በፊት አስቀድሞ የቅርንጫፍ ሰራተኞችና ባለድረሻ አካላትን ዝግጁ ለማረግ አስፈላጊ
ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡
2. የስልጠናዉ አስፈላጊነት
በዓላቱ እንደሌሎች ባዕላት ሰዎች በቤታቸዉ የሚያከብሩት ሳይሀን ወደ አደባባይ
በመዉጣጥ የሚከበር በዓል በመሆኑ የተለየ ስልጠና ስለሚጠይቅ
በተቋሙ ወይም በቅ/ጽ/ቤቱ ውስጥ የሚገኙ ሰራተኞች እንዲሁም ባለድርሻ
አካላት ከአደጋ ክስተት በፊት ዝግጁ ማድረግ፡፡
አደጋ ከተከሰተ በኋላ ሁሉም ሰራተኛና ባለድርሻ የስራ ድርሻቸውን አውቀው
ውጤታማ ስራ እንዲሰሩ ነው፡፡
1
የሰራተኞችንና የባለድርሻ አካላትን በአደጋ ላይ ያለውን ግንዛቤ ለማስፋት ፡፡
3. ስልጠናው የሚሰጠው፡-
ሰነድ በማዘጋጀት
የአደጋ አይነቶችን በመለየት
ቦታዎችን በመለየት
የመከላከያ መሳሪዎችንንና አልባሳትን በመለየት፡፡
የመሳሪያ አጠቃቀምና የአልባሳት አጠቃቀምን ግንዛቤ በማስፋት
የሴፍቲ ሁኔታዎችን ግንዛቤ በማስፋት
በእያንድንዱ ነጥብ ላይ በቂ ጊዜ ወስዶ የተግባር ልምምድ በመስራት
ባለድርሻ አካለካትን የድርሻ ተግባራቸውን እንዲያውቁና ኃላፊነታቸውን
እንዲወጡ ለማድረግ፡፡
2
ሁሉም ተሳታፊ ከልምምድ በኋል ልምምዱን መገምገም አለበት
ሪፖርት ማዘጋጀትና ለሚመለከተው መላክ ወይም ማቅረብ ፡፡
5. የጊዜ ሰሌዳ
3
4