You are on page 1of 4

❤#ሰባቱ #ዘመነ-#መግቦቶች

(#Ages , #Dispensations )❤

📌2 ጢሞቴዎስ 2 (2 Timothy)

15፤ የእውነትን ቃል በቅንነት(በትክክል)የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር


ልታቀርብ ትጋ።

ልዑል እግዚአብሔር ከፍጥረት መጀመሪያ እስከ አለም መጨረሻ ድረስ ከሰው ልጆች ጋር ብዙ ውሎችን፣የተለያዩ
ዘመናትን ገብቷል፤ የገባቸውን ውሎችንም ፈጽሟል፤ እየፈጸመም ነው፥ እርሱ ታማኝ አምላክ ስለሆነ። አብዛኛው
ውሎቹ(ዘመናት) ግን በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። እግዚአብሔር "እናንተ፡ እንዲህ ብታደርጉ እና እንዲያ
ባታደርጉ "

፥ እኔ ደግሞ "እንዲህና እንዲያ አደርግላችኋለሁ" በማለት ውል ሲገባ ነበር። ሰውም የተገባውን ውል ሲያፈርስና
በውሉም መሠረት እግዚአብሔር ሲፈረድባቸው፤ ከእንደገና ሌላ ውል ሲያደርግ እንመለከታለን።

✍️##የዘመን #መጨረሻ እና #የአለም #መጨረሻ #የተለያዩ #መሆናቸውን #መረዳት #አለብን:: ከዚህ በፊት 5 የተለያዩ
ዘመናት አልፈዋል አሁን የምንገኝው 6 ኛው የፀጋ ዘመን ላይ ነው ከዚህ ቀጥሎ ደግሞ 7 ኛው የሺው አመት መንግስት
ይቀጥላል።

ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ (ገላ 4:4) የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች
የተወለደውን ልጁን ላከ ይላል።

(ሮሜ 10:4) የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነው። Christ is the end of the law

በማለት የሕግ ዘመን ፍጻሜ እንዳገኝ እና የሚያምኑ ሁሉ የሚጸድቁበት የጸጋ ዘመን አንደጀመረ ያበስራል።

በኤፌሶን መልዕክቱ ደግሞ ኤፌሶን 1 (Ephesians)

9፤ በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤

10፤ #በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።

NB) ግን በዚህ ሁሉ ውል ውስጥ በሰው ብቃትና ችሎታ፤ የሰው እጅ ሳይገባበት የተመሰረተ አንድ ውል አለ። የፀጋ ዘመነ
መግቦት ነው።

✍️እግዚአብሔር ከሰው ልጆች ጋር ያደረጋቸው ዘመነ መግቦቶች ምን ምን ናቸው ከዚህ በታች አብረን እናጥና
📌1). (Dispensation of Innocency) ክፉውን እና ደጉን ያለማወቅ ዘመን ከአዳም ጋር የተደረገ ውል ነው።

🍭የውሉ ቅድመ ሁኔታ፦ መልካሙንና ክፉን የሚያስታውቀውን ዛፍ አለመብላት ነበር [ ዘፍ 2:15-17]። ግን ኋላ ላይ አዳም
ውሉን አፍርሶ [ ዘፍ 3:6፤7] ፤ በመንፈስ ሞቶ ከሚስቱ ከሔዋን ጋር ከኤደን ገነትም ተባሮ እናያለን [ ዘፍ 3:17-19፤ 3:22-
24]።

ይህ ውል እስከሚያበቃበት ጊዜ ድረስ አዳም "Innocent" ነበር። ማለትም ክፉንና ደጉን ለይቶ አያውቁም ነበር ማለት
ነው። 👇

📌2). Dispensation of Conscious/knowledge በእግዚአብሔርና በአዳም መካከል የተደረገ ነበር። 1656 ዓመታት

ከመጀመሪያው ውል የሚለየው፥ በዚህ ውል አዳም ክፉንና ደጉን ለይቶ ያውቃል።

🍭የውሉ ቅደመ ሁኔታ፦ እግዚአብሔርን ማመንና ማክበር ነው[ ዘፍ 4:4-7 ዕብ 11:4] ። ሰው ግን እግዚአብሔር በማመንና
በማክበር ፋንታ በክፋት በሩቱ [ ዘፍ 6:5-7] ፤ ውሉንም ስላላከበሩት እግዚአብሔር በጥፋት ውኃ ቀጥቷቸው
እንመለከታለን [ ዘፍ 7:11-12፤23]። ይህም ውል እንደመጀመሪያው ሁሉ ፈርሶ እናያለን። በዚህ ውል አዳም ክፉንና ደግ
ምን እንደሆነ ያውቅ ነበር። ...👇

📌3). ከኖኅ ጋር ተደረገ ውል(Dispensation of the Human government) ለ 1205 ዓመታት

🍭የውሉ ቅድመ ሁኔታ፦ እግዚአብሔር ከጥፋት የተረፉቱን ስምንት ሰዎችን ወደ አለም ሁሉ እንደበተኑና እንዲበዙ
አዟቸው ነበር [ ዘፍ 9:1-6]። ነገር ግን ሰዎቹ እምቢ በማለት ታላቅ መንግስት ለመመስረት ብለው የባቢሎን ግምብ
ለመስራት በአንድነት ተነሱ [9:20-23፤ 11-1-4]። እግዚአብሔር ውሉን ስላላከበሩት ቋንቋቸውን በማደበላለቅ
እንዲበተኑ አድርጓቸዋል [ዘፍ 11:5-9]። ይህ ውል እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በሰዎች እንቢተኝነት ፈርሷል። 👇

📌4). ከአብርሃም ጋር የተደረገ ውል (Dispensation of the Promise) በዋናነት ለ 430 ዓመታት

🍭 የተስፋው ቃል(ክርስቶስ )እስኪገለጥ እግዚአብሔር ለአብርሃም እና ለ#ዘሩ (ለክርስቶስ) የሰጠው የተስፋ ቃል ነው።
[ዘፍ 15:6 ገላ 3:6-18,

ሮሜ 4:3]።

❤❤በዚህ ውል እግዚአብሔር አብርሃምን፥ "በአንተ ምክንያት አሕዛብ ይባረካሉ" በማለት ወንጌል ሰብኮ ነበር[ገላ 3:8]።
ነገር ግን ይህ ተስፋ ሳይፈጸም በመሃል የሕግ ዘመን ጣልቃ ገባ። ገላ 3:16
ቢሆንም ግን ተስፋው በስድስተኛው ውል ላይ ልፈጽም ችሏል፤ ወደ በኋላ እናያለን።

📌5). (Dispensation of the law/Mosaic law) ለ 1520 ዓመታት ከእስራኤል ሕዝብ ጋር

የውል ቅደመ ሁኔታ፦ እግዚአብሔርም በሙሴ ሆኖ፥ በመላእክት በኩል ሕግን ሰጣቸው። እነርሱ እግዚአብሔር
የሰጣቸውን ትዕዛዛት መጠበቅ ነበረባቸው፥[ ዘዳ 7:11-15፤ 8:11-20 ,ዘዳ 28 ኢሳ 1:19-20.........። ነገር ግን ሕጉን
የተቀበሉት እስራኤላውያን ሕጉን በተከታታይ ሲያፈርሱ እንጂ ሲፈጸሙና ሲታዘዙ አናይም [ዘጻ 32:1-8 መሳ 21:25
መዝ 106:16-48]። በዚህም ምክንያት ውሉ ሊፈርስ በቅቷል፤

ለጥፋታቸውም በአሶርና /ባቢሎን

በፈፋርስ እና ሜዶ

በግሪክ፣ ለሮም መንግሥት እንዲማረኩ ምንክንያት ሆኗቸዋል። በመጨረሻም በ 70 ዓም ከሀገራቸው


የተበተኑ በ 1948 ወደ ሀገራቸው የተመለሱት።

ከመጀመሪያው ውል አንስቶ እስከ አምስተኛው ውል ድረስ ያለውን ውል እንደ አንድ ኪዳን ልናየው እንችላለን፤ ማለትም
እንደ #ብሉይ_ኪዳን። ምክንያቱም እነዚህን ክስተቶች ሁሉ በብሉይ ኪዳን ተከስቶ እንመለከታቸዋለን።

📌6). አዲስ ኪዳን (የቤተክርስቲያን/የጸጋ ዘመን/ Dispensation of Grace/Church age) ለ 2000 ዓመታት ቆይቷል

ይህኛውን ውል እግዚአብሔር አምላክ በሰው ብቃትና ችሎታ እንዲሆን አላደረገውም። ለኪዳኑም ተፈጻሚነት እንደ
ብሉይ ኪዳን የኮርማዎችና የፍየሎች ደም አልፈሰሰም። በብሉይ ኪዳን ሰዎቹ ለመዳን የተሰጣቸውን ሕግ በሙሉ
መፈጸም ነበረባቸው፤ ብዙ መስራት ብዙ መጣር የሁልጊዜ ጭንቀታቸው ነው። በዚህ በአዲሱ ኪዳን ውስጥ ሥጋን ለብሶ
የተገለጠው እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሚሆነውን የመዳን ሥራ ሰርቷል። ዮሐ 1:14-17,ሐሥ 13:36-

በእርግጥ በዚህም ውል ሰው የሚድነው በሥራ ነው፤ ሥራውም ደግሞ በጣም ቀላል ነች፤ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ
የሰራውን ሥራ የእኔ ብሎ #ማመን ነው (ዮሐ 6:27-29)፤ እንጂ ተራራ መውጣት፣ መጸለይ፣ መጾም ወዘተ...አይደለም።

የኢየሱስ መከራ የመስቀል ላይ ሞት ወደ መቃብር መውረድ በክብር ከሙታንም በኩር ሆኖ መነሳት ማረግም ለእኔ ነው
ብሎ የሚያምን ሁሉ ከራሱ ከእግዚአብሔር ጋር ለዘለዓለም የመኖር መብቱ የተጠበቀ ነው። ሮሜ 10:8 -13

በዚህ ውል እግዚአብሔር ገና ከመጀመሪያው ለአብርሃም በአንተ አሕዛብ ይባረካሉ ብሎ ያለው የተሰፋ ቃል ፈጽሟል።

📌7) Dispensation of Millennium /


The Kingdom]

አንድ የቀረ ውል አለ፤ እርሱም እግዚአብሔር ለዳዊት ከአንተ ጉልበት ንጉሥ ይወጣል ብሎ ከዘመናት በፊት የተናገረው
ቃል ነው። አሁን ይህ ተስፋ አልተፈጸመም፤ ምክንያቱ ለኢየሱስ አሁን ሁሉ ተገዝቶለት አናይም [ ዕብ 2:8]። ይህን ተስፋ
በሺህ ዓመት[The Kingdom/ Dispensation of Millennium] መንግሥት ለመፈጸም ቀን ቀጥሯል። በዚህ ውል ውስጥ
ቤተክርስቲያን ከኢየሱስ ጋር ለአንድ ሺህ ዓመት ትነግሳለች። ኢየሱስም ጠላቶቹ ሁሉ የእግሩ መረገጫ እስኪሆን ድረስ
ይችን አለም ለአንድ ሺህ ዓመት ይገዛታል። በሰማይ(ቤተክ) እና በምድር(የሺ ዓመት ነዋሪዎች) ያሉትንም በክርስቶስ
ይጠቀልላል ።

ዳን 7:14,ዕብ 2:8,ኤፌ 1:9-10 ,ዘፍ 22:17.

ሮሜ 11 (Romans)

33፤ የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥
ለመንገዱም ፍለጋ የለውም።

36፤ ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።

ፀጋ እና ሰላም ይብዛላችሁ። አሜን

የወንጌል እውነት አገልግሎት ጅማ

Gospel Truth Ministry Jimma

You might also like