You are on page 1of 72

የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጅ

 የሰነዱ ዋና ዋና ይዘቶች

 የስትራቴጅው መነሻ መርሆዎች

 ለኢንዱስትሪ ልማትና ለልማታዊ ባለሃብት የተመቻቸ ሁኔታን መፍጠር

 ለልማታዊ ባለሀብቱ ቀጥተኛ ድጋፍና አመራር መስጠት

1 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
መግቢያ

 በዚህ ሰነድ ላይ የምናደርገው ውይይት የጋራ ግንዛቤና እምነት


ለመያዝ ያግዛል ተብሎ ይገመታል፣

 የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጅ ስንል በዋናነት የማንፋክቸሪንግ


ዘርፉን ማለትም በተለያዩ የማምረቻ ተቋሞችና ፋብሪካዎች
የሚመረተውን ማለታችን ነው፡፡

 የግል ባለሃብቶችን ዕድገት ለማቀላጠፍና ሚናቸውን እንዲጫወቱ


መደረግ ስለሚገባው ጉዳይም እንመለከታለን

2 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ
ክፍል አንድ
የስትራቴጅው መነሻ መርሆዎች
1.1 የግል ባለሀብቱ የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ ሞተር ነው

 በአገራችን እየተገነባ ያለው የኢኮኖሚ ስርዓት የነጻ ገበያ


የኢኮኖሚ ስርዓት ነው
 በሂደት የኢኮኖሚ መዋቅር ሽግግር መደረጉ
አይቀርም፤(ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ)(ከአርሶ አደር ወደ
ባለሃብት)

3 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT BUREAU


…የቀጠለ
 ዓለም በንግድና ኢንዱስትሪ በጥብቅ የተሳሳረችበት ወቅት
ላይ ነን፣
 በትስስሩ የሚኖረንን ድርሻ ለማሻሻልና በይበልጥ
ተጠቃሚ ለመሆን በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ መሆን ይገባናል
 ኢንዱስትሪን ለማልማት የሚደረገው እንቅስቃሴ ከዚህ
መነሳት አለበት

4 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT BUREAU


…የቀጠለ
 የግሉ ባለሀብት ሚናውን እንዲጫወት ማስቻልና ማብቃት
ያስፈልጋል፣
 ከዓለም የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ተጠቃሚ መሆን
አለብን፣ ይህንን ለማድረግ በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ (በዋጋ፣
በጥራትና በጊዜ) መሆን አለብን፣
 የግሉ ባለሀብት ሞተር የሚሆንበት የኢንዱስትሪ ልማታችን
በዓለም ገበያ በመወዳደር ብቃት ላይ መመሥረት አለበት፣
 እንደኛ ባሉ ሃገራት ያሉ ባለሃብቶች ተወዳድረው
እንዳያሸንፉ የሚያደርጉ ችግሮች አሉ፣

5 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ
 ውድድሩ የተጠናከረ የቴክኖሎጂ፣ የካፒታልና የማኔጅመንት
አቅም ካላቸው ጋር መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፤ እነዚህ
ደግሞ የተጠናከረ መሠረተ-ልማት፣ ሠፊ የንግድ መረብ በዘረጉ፣
የሠለጠነና ታታሪ የሠው ኃይል ካላቸው ቀልጣፋ የመንግሥት
አስተዳደር ካላቸው ጋር መሆኑን ልናስታውስ ይገባናል፣

6 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ
 ከዚህ ውድድር አንፃር የሀገራችን ባለሀብት አቅም በጣም ደካማ
ነው በመሆኑም ውድድሩን ይፈራዋል ወይም ወደ ውድድሩ
መግባት አይፈልግም፡፡
 የልማት ሞተር የሆነ ባለሀብት መሆንን አይመርጥም፣
 ከዚህ ይልቅ አቋራጭ ጎዳናን ለመከተል ይፈልጋል፡፡

7 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT BUREAU


…የቀጠለ
 አማራጮቹ፡-
 ከመንግስት ባለስልጣኖች ጋር በመተባበር የሙስና ተግባር ላይ
መሰማራት
 የገበያ እጥረቶችን መሰረት በማድረግና በማባባስ በሸቀጦች
ዝውውር ከፍተኛ ትርፍ ማግኘት ነው
 ምርት አምርቶ በጥራቱ ከመወዳደር ይልቅ በተለያዩ
የመንግስት ድጎማዎች ላይ ተንጠልጥሎ ለመኖር መሻት
ናቸው፡፡
 የሀገራችን ነባራዊ ሁኔታም ከልማታዊ ባለሀብት ይልቅ ለጥገኛው
እጅግ የተመቸ ነው፣

8 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ
 በሃገራችን ጥገኝነት የሚጠናከረው የልማት ፍላጎትና ምኞት የሌላቸው
ሃይሎች ስለተበራከቱ አይደለም፡፡ዋነኛው ነባራዊ ሁኔታው
ከልማታዊው ባለሃብት ይልቅ ለኪ/ሰብሳቢው የተመቸ መሆኑ ነው፡፡
 በግል ባለሃብቱ ውስጥ ጥገኛው የበላይ የሚሆንበት ሁኔታ ስላለ ነው፡፡
 ይህንን ያልተመቸ ሁኔታ ለመቀየር፡-
ሀ/ ለጥገኝነት የማያመች ነባራዊ ሁኔታን መፍጠር፣
ለ/ የተሟላ ድጋፍ መስጠትና የልማታዊ ባለሀብቱን አቅም ማጎልበት
ያስፈልጋል፡፡
 በአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ይህንኑ ሚና ሊጫወት የሚችለው
ልማታዊ ባለሃብቱ መሆኑን የተገነዘበ የአገራችን ሁኔታ
ከልማታዊው ባለሃብት ይልቅ ለጥገኛው እጅግ የተመቸ መሆኑን
ያስተዋለ የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጅ ሊኖረን ይገባል፡፡

9 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT BUREAU


1.2. ግብርና መር የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ አቅጣጫ መከተል፡-
 ግባችን የበለፀገ ኢንዱስትሪ ያላትን ሀገር መገንባት ሆኖ
ይህንኑ በተቻለ ፍጥነት ለማሣካት የሚቻለው ግብርናና
ገጠርን ማዕከል ያደረገ ግብርና መር የኢኮኖሚና የኢንዱስትሪ
ልማት ስትራቴጂ ስንከተል ነው፣
 ከፍተኛ የካፒታል ውስንነት ያለብን ሆኖ መሬትና የሠው
ጉልበት አለን፤
 ስለዚህ ካፒታልን ለመቆጠብና የሠው ጉልበትን በሠፊው
ከመጠቀም አንፃር ከግብርና ጋር የሚወዳደር ዘርፍ የለም፣

10 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ
 ስለዚህ ግብርና አጠቃላይ የኢኮኖሚያችን ዕድገትና የዕድገቱንም
ፍጥነት የሚወስን፤ ኢንዱስትሪም የዚሁ ጉዞ አካል ሆኖ መታየት
አለበት፣

 ኢንዱስትሪ በፍጥነት ማደግ የሚችለው በግብርና ምርቶች ላይ


ዕሴት ጨምሮ ለገበያ በማቅረብ አቅጣጫ ሲራመድ፣ ለግብርና
የሚሆን የኢንዱስትሪ ግብዓቶችንና የፍጆታ ዕቃዎችን
በማምረት አቅጣጫ ሲራመድ ነው፣

11 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
……የቀጠለ

 በዚህ ዓይነት ትስስር ስንጓዝ የካፒታል ክምችታችን በከፍተኛ


ፍጥነት ያድጋል፤ ኢንዱስትሪም በኢኮኖሚው ውስጥ ያለው
ድርሻ ያድጋል፣ የኢኮኖሚ አመራሩንም በሂደት ይረከባል፤

 የሃገራችን የኑሮ ደረጃ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚደርሰው አገራችን


በኢንዱስትሪ የበለጸገች ስትሆን ነው፡፡

12 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
1.3. ኤክስፖርት-መር የኢንዱስትሪ ልማት አቅጣጫን መከተል
 ግብርና በሚያስቀምጠው አጠቃላይ አመራር ሥር ሆኖ
የኢንዱስትሪ ልማቱን አቅጣጫና ፍጥነት የሚወሰነው
የኤክስፖርት ኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፍ መሆን አለበት፡-

 የግብርና ምርቶች ጥራታቸው ተጠብቆ ለኤክስፖርት


ሊቀርቡ ይገባል፤ በዓለም ገበያ መመራት አለባቸው፣
 ኢንዱስትሪም የግብርና ምርቶች ላይ ዕሴት ጨምሮ
ኤክስፖርት ማድረግ አለበት፣
 ማምረት የምንችለውን አምርተን ኤክስፖርት በማድረግ
የውጪ ምንዛሪ አግኝተን ለልማት የሚያስፈልገንን መግዛት
መቻል አለብን፣

13 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ
 ምርታማነቱን ለማሻሻል ሌት ተቀን የሚጥር ኢንዱስትሪ
ዘርፍ በኤክስፖርት ላይ የተመሠረተ ነው፣
 በኤክስፖርት መሠማራት ያለማቋረጥ ተወዳዳሪነትን
የማጠናከር ፍላጎት ከመፍጠሩም በተጨማሪ የመወዳደር
አቅሙም እንዲጎለብት አመቺ ሁኔታ ይፈጥራል፣
 ከኤክስፖርት አድራጊ ዘርፍ የሚገኘው ልምድ፣ ክህሎትና
አሠራር ወደ ሌሎች ዘርፎችም በመሰራጨት አጠቃላይ
ዕድገቱን ያግዛል፡፡

14 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
1.4. ጉልበትን በሠፊው በሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች ላይ ያተኮረ አቅጣጫ
መከተል

 ፈጣን ልማትና ቀልጣፋ የሀብት ድልድልን ለማረጋገጥ


ካፒታልን የሚቆጥብና የሠው ጉልበትን በሠፊው
የሚጠቀም የልማት አቅጣጫ መከተል የግድ ነው፡፡

 አንፃራዊ የመወዳደሪያ ብቃታችን ተመጣጣኝ ክፍያና


ታታሪ ሠራተኛ በስፋት መጠቀም ነው፡፡

  

15 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ

 ይህ አቅጣጫ ባለን አቅም /ሀብት/ በበቂ ፍጥነት ለማደግ

የምንችልበትን ዕድል ይከፍትልናል፣

 በመሆኑም ካፒታልን ቆጥበን ጉልበትን በሠፊው በሚጠቀሙ

(የጨርቃጨርቅና ልብስ ስፌት) የአግሮ ፕሮሰሲንግ

ኢንዱስትሪዎች ላይ ማተኮር አለብን፣

16 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ
 የእያንዳንዱ ሠራተኛ የማምረት ችሎታና ታታሪነት የላቀ
ደረጃ ለማድረስ መሠራት አለበት፤
 የኢንዱስትሪ ልማታችን ፍጥነት የሚወሰነው ያለንን ካፒታል
ቆጥበን ብዙ ተቋሞች ማቋቋም ስንችልና ይህንንም
ለመፍጠር የሚያስፈልገንን የካፒታል ክምችት፣ የሠለጠነ
የሰው ኃይልና ማኔጅመንት ማሰባሰብ ስንችል ነው፣
 በዚህ ማዕቀፍ ውስጥም ሆነን ካፒታልን በስፋት የሚጠቀሙ
ኢንዱስትሪዎችን አቅም በፈቀደ ፍጥነት ለማሣደግ
መሥራት ይኖርብናል፡፡

17 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
1.5. የሀገር ውስጥና የውጪ ባለሀብትን አቀናጅቶ የመጠቀም
አቅጣጫ መከተል፡-

ሀ. የውጪው ባለሀብት፡-
 ሠፊ የካፒታል ክምችት፤
 ጠንካራ የገበያ መረብ፤  ጠንካራ ጐኖች
 ዘመናዊ ቴክኖሎጂና የአመራር ሥርዓት፤

 ትርፉን ወደ ውጪ ይወስዳል፤
 የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሊኮበልል ይችላል፤ • ደካማ ጐኖች
 ቀጣይነቱ አስተማማኝ አይደለም፤

18 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
ለ. የሀገር ውስጥ ባለሃብት፡-
 የካፒታል ዕጥረት፤
 የገበያ መረብ አልዘረጋም
• ደካማጐ
 ዘመናዊ የአመራር ችሎታውና ዕውቀት ውስን ነው፤ ኖች
 ምርታማነቱና ቴክኖሎጂው ዝቅተኛ ነው፡፡

 ካፒታሉና ትርፉ ሀገር ውስጥ የሚቀር ነው፤ • ጠንካራ


ጐኖች
 የካፒታል ክምችትን ለማጠናከርና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ
ወሣኝ ነው፡፡
 

19 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ
 በመሆኑም ስትራቴጂያችን በዋናነነት በአገር ውስጥ ባለሀብቱ ላይ
የተመሠረተ ሆኖ የዉጪ ባለሀብቱን ልማታችንን በሚያግዝ ሁኔታ
በሠፊው የመሣብ አቅጣጫ መከተል አለብን፣

 የሀገር ውስጥ ባለሀብቱን አቅም የማጎልበት ሥራ መሥራት


አለብን፣ የተጠናከረ ዕገዛ ልንሰጠው ይገባል፣

20 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT BUREAU


…የቀጠለ
 ለውጪው ባለሀብት ሠርቶ የሚያተርፍበትንና ለንብረቱ ጥበቃ
የሚደረግበትን ሁኔታ መፍጠር አለብን፣

 ካፒታል ይዘው የሚገቡ፣ የገበያ መረብ የሚዘረጉ፣ የአመራር


ዕውቀት ማሸጋገር የሚችሉ፣ ወዘተ የውጪ ባለሀብቶችን መሳብ
አለብን፡፡

 በመሆኑም የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ዋነኛ ኃይል ሆኖ የውጪው


ባለሀብትም በሠፊው ተሣታፊ የሚሆንበት ሁኔታ በመፍጠር
የሁለቱንም አቅም ለመጠቀም መሥራት አለብን፤

21 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
1.6 መንግሥት ጠንካራ የአመራር ሚና የሚጫወትበትን አቅጣጫ
መከተል፡-

 በሀገራችን ፈጣን የኢንዱስትሪ ልማት ማረጋገጥ የሚቻለው


መንግሥት ብቃት ያለው አመራር ከሰጠ ብቻ ነው፡፡
 ይህ የሚሆንባቸው ምክንያቶች፡-
 በገበያውና በግል ባለሀብት በአጥጋቢ ሁኔታ ሊሰሩ
የማይችሉ ክፍተቶች በመኖራቸውና እነዚህ መቀረፍ
ስላለባቸው፤

22 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ
• የገበያ ኢኮኖሚው በተሟላ ሁኔታ እንዲሰራ የሚያስችሉት
ጠንካራና ቀልጣፋ መሠረተ ልማቶች ስለሚያስፈልጉ፤
• የገበያ ጉድለቱን ለመሙላት የሚደረግ ጣልቃ ገብነት
በጥንቃቄ ተመርጦ የሚፈፀም መሆን ስላለበት፤
• የመንግሥት የጣልቃ ገብነት ባህሪይ የገበያ ጉድለቶችን
በጊዜያዊነት ከመቅረፍ ጎን ለጎን በተቻለ ፍጥነት ጉደለቶቹ
በገበያውና በግሉ ባለሀብት በዘላቂነት የሚወገዱበትን ሁኔታ
የሚያመቻች መሆን አለበት፤

23 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ
• የገበያ ጉድለትን ለመቅረፍ የሚቀረፅ ፖሊሲ እና ስልት
ከመንግሥት የማስፈፀምና የገንዘብ አቅም ጋር የሚጣጣም
መሆን አለበት፤

• መንግሥት ቀልጣፋና ከሙስና የፀዳ የመንግሥት አስተዳዳርን


መፍጠር፤ በመላ ሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋትን ማስፈን፣ ልማትን
የሚያቀላጥፉ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን መንደፍ አለበት፡፡

24 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
1.7 መላው ሕብረተሰብ ለኢንዱስትሪ ልማት በጋራ የሚሰለፍበትን አቅጣጫ
መከተል፡-
   በጋራ ለልማቱ የሚሰሩበትና
መንግሥት፣ የግል ባለሀብቱ፣ ሕዝቡ
የማይተካ ሚና ይዘው የሚጫወቱበት ሁኔታን ማመቻቸትና
የአመለካከት አንድነት መፍጠር ያስፈልጋል፤

 የኢንዱስትሪ ልማት የሁሉም ዜጋ የጋራ ዓላማ ተደርጎ መታየት


አለበት፤ ሁሉም በየደረጃው የሚሳተፍበትና ባስገኘው ውጤትም
የሚጠቀምበትን ሁኔታ ማስፈን የግድ ነው፤

25 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ
 በልማት ሥራው ላይ የሚሳተፈው ተዋናይ የሥራ ድርሻና ሚና
ግልፅ መሆን አለበት፤ ሚናውን በአጥጋቢ ደረጃ ለመወጣት
የሚያስችል ብቃት እንዲኖረው መደረግ አለበት፤
 የሁሉንም ተዋናይ አካላት አቅም አቀናጅቶና አሟጦ ለልማቱ
መጠቀም የግድ ነው፤

መላውን ሕብረተሰብ የሚያሳትፍ ቅንጅት በዋናነነት የሚከተሉትን


ተዋንያን ያካተተ ይሆናል፡፡

26 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
ሀ. የመንግሥትና የግል ባለሀብት ቅንጅት

 መንግሥት ከግል ባለሀብቶች ነፃ መሆን አለበት፡፡


 ለፈጣን ልማትና የግል ባለሀብት የኢንዱስትሪ ልማት ሞተር ሆኖ
ለሚያንቀሳቅሰው ፈጣን ልማት በፅናት መቆም መቻል አለበት፤
 የጥገኝነት አረንቋን ለማድረቅና ለልማታዊ ባለሀብት የተመቸ ሁኔታ
መፍጠር አለበት፤
 የገበያ ጉድለትን በተመረጠና በተጠና ሁኔታ መድፈን አለበት፤

27 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
……የቀጠለ
 ጠንካራ አመራር መስጠት አለበት፤
 ከግል ባለሀብቱ ጋር የሚመካከርበት፣ ለጋራ ዓላማ በጋራ የሚሰራበት
ሥርዓት መዘርጋት አለበት፤
 የግሉን ባለሀብት የሚደግፍበት በግልፅነት ላይ የተመሰረተ የድጋፍና
የትብብር ሥርዓት መፍጠር አለበት፤

28 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
ከመንግሥት ጋር የሚመካከርበት፣ ከልምዱ ጠቃሚ ሃሳቦችን
የሚያቀርብበት የተደራጀ አሠራር ሊኖረው ይገባል፤ የጋራ አቋም
በተያዘባቸው ጉዳዩች ላይ ከመንግሥት ጋር በመተባበር ተግባራዊ
ማድረግ አለባቸው

    ነፃነታቸውን ጠብቀው መሳተፍ አለባቸው፤

ለ  ራሱን ለመርዳት ሲል በውድድር አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት ሌት


  ተቀን መጣር አለበት፤
ሀ  የመንግሥትን ዕገዛ ተጠቅመው የመወዳደር አቅማቸውን
 
ለማጎልበት ዝግጁ መሆን አለባቸው፤

   ገበያ የሚሰጠውን ብይን ለመቀበል ዝግጁ መሆን አለበት


29
  AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT
BUREAU
ለ. የኢንዱስትሪ ባለሀብቱና የአርሶአደሩ ቅንጅት

 አርሶአደሩ ለኢንዱስትሪ ልማቱ ካልተረባረበ ዓላማችን


አይሳካም፤
 አርሶአደሩ ርብርብ ሲያደርግ የራሱንና የባለሀብቱን ጥቅም
በማሳካት ዙሪያ ሊሆን ይገባል፤
 የግል ባለሀብቱም ለራሱ ዘላቂ ጥቅም ሲል ከአርሶአደሩ ጋር
ኢኮኖሚያዊ ትስስር መፍጠር አለበት፤
 ስለሆነም የባለሃብተ/ኢንዱስትረና አርሶ አደር ቅንጅት
በእጅጉ ጠቃሚ ነው፡፡

30 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ

 ሁለቱም ተዋናይ አካላት በዓለም ገበያ በዋጋና ጥራት ተወዳዳሪ


መሆን አለባቸው፤ በገበያ የውድድር ሥርዓት መገዛት
አለባቸው፤(አርሶ አደሩ ለባለኃብቱና ባለኃብቱ ለአርሶ አደሩ)
 ሁለቱም ምርታማነትን ለማሳደግ አልመው መሥራት አለባቸው፤

31 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
ሐ. የአሠሪውና የሠራተኛው ቅንጅት፡-

 ፈጣን የኢንዱስትሪ ልማት የሥራ ዋስትናን


ያረጋግጣል፤(አማራጭ ኢንዳስትሪዎች ይኖራሉና)
 የሠራተኛው የሙያ ችሎታና የኑሮ ደረጃም እየተሻሻለ
ይሄዳል፤
 አሰሪም ከኢንዱስትሪ ልማቱ ተጨማሪ ሀብትና ትርፍ ያገኛል፤
 ስለዚህ ከሂደቱ ሁለቱም ይጠቀማሉ/ ስለዚህም ተባብረው መሥራት
አለባቸው፡፡

32 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ

 የሁለቱን ወገኖች የጥቅም ግጭት ማርገብ ያስፈልጋል (Win-Win


Scenario)፤ የጥቅም ግጭቶች ሕጋዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ብቻ
ሊፈቱ ይገባል፤

 ምርታማነትን ማሳደግ የሁለቱም ወገኖች የጋራ ዓላማ እና


የዕድገታቸው ምንጭ ተደርጎ መታየት አለበት፤

 ሠራተኛው በአስተሳሰብም ሆነ በአደረጃጀት መንግሥት ዋነኛው አሰሪ


መሆኑ ለሚቀርበት ሁኔታ መዘጋጀት አለበት፤

33 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
ክፍል ሁለት
ለኢንዱስትሪ ልማትና ለልማታዊ ባለሃብት የተመቻቸ ሁኔታን መፍጠር

2.1 የጥገኝነት አረንቋን ማድረቅና ለልማታዊ ባለሀብት የተመቸ


ሁኔታ መፍጠር፣

2.2 የተረጋጋና ለልማት የሚያመች የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታን


መፍጠር፣
 ዋነኛ መስፈርቶች፡-
 የዋጋ ግሽበት፣
 የወለድ ምጣኔ፣
 የውጪ ምንዛሪ ተመን፣

34 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ
የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ለምን?
 የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ በልማት ለተሠማሩ ባለሀብቶች
በዕቅድ ለመሥራትና ለመመራት ምቹ ሁኔታ
ይፈጥርላቸዋል፣
 የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ለጥገኛውና ኪራይ ሰብሳቢው
የተመቸ አይሆንም፣
 የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚን ለማስፈን ትክክለኛ ፖሊሲዎችን
ነድፎ መተግበር ያስፈልጋል፣

35 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
2.3 ዘመናዊና ለልማት የተመቻቸ የፋይናንስ ሥርጭት መፍጠር

ምን ያካትታል?
 ለኢንቨስትመንት የሚሆን ፋይናንስ
ማሰባሰብ/ቁጠባ…
 የተሰባሰበውን ፋይናንስ ልማትን ለማምጣት
ብቃቱና ፍላጐቱ ላላቸው ክፍሎች ማዳረስ፣
 የክፍያ ስርዓቱን ማቀላጠፍ፣

36 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
የፋይናንስ ምንጮች ምንድናቸው?

ሀ. ባንኮች
 ዋና የኢንቨስትመንት ፋይናንስ ምንጭ ናቸው፤
 እነዚህ ባንኮች ጤናማ ሆነው የኢንቨስትመንት ፋይናንስ
ማቅረብ አለባቸው፤
 ብሔራዊ ባንክ ባንኮችን ይመራል፣ ይቆጣጠራል
 የገንዘብ ፖሊሲ ያወጣል፣ የወለድ ምጣኔን ይወስናል፣
 ብሔራዊ ባንክ ማብቃትና ማጠናከር ያስፈልጋል፣

37 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
ባንኮች ኢንቨስትመንትን ለማገዝ፣

 የንግዱን ማህበረሰብ ማወቅ አለባቸው፣(የሃብት መረጃ ባለመኖሩ ወይ


ያለአግባብ ያበድራል/ገንዘብ ያከማቻል )
 ጠንካራ የማስፈፀም አቅም ሊኖራቸው ይገባል፣
 የቴክኖሎጂ አቅማቸውን ማሳደግ አለባቸው፣
 የልማት ባንክና የንግድ ባንኮች በቅንጅት የሚሠሩበት ሁኔታ
መፈጠር አለበት፣

38 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
ለ. የጡረታና የኢንሹራንስ ተቋማት

 ለጡረታናኢንሹራንስ የሚዋጣው ገንዘብ ለረጅም ጊዜ


የሚቀመጥ ኮንትራታዊ ቁጠባ ነው፣
 ይህንን ኮንትራቲዊ ቁጠባ አሰባሰቦ ለረጅም ጊዜ
ኢንቨስትመንት ማዋል ይቻላል፣

39 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
ሐ. ባንክ ያልሆኑ የፋይናንስ ተቋማት
 በባንኮች መካከል ገንዘብ የመበዳደር ሥርዓት መዳበር
አለበት፣
 የመንግሥት የግምጃ ቤት ሰነዶችን መሸጥ (የረጅምና
የአጭር ጊዜ)፣
 የኩባንያ ቦንዶች ሽያጭ ማደግ አለበት፣
 የአክስዮን ገበያ ጤናማ ዕድገት ሊያሳይ ይገባል፣
መ. የገጠር የፋይናንስ ተቋማት
 የገጠር ባንኮች ማስፋፋት፣

40 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
2.4 አስተማማኝ የመሠረተ ልማት አገልግሎት ማቅረብ፣

ይህ ምን ያካትታል?
 ደረጃቸውን የጠበቁ መንገዶች መስራት፣ መጠገንና መንከባከብ፣
 ለመንገድ ግንባታ የሚያስፈልግ ፈንድ mobilize ማድረግ፣
 በሀገር ውስጥ ዋነኛ የትራንስፖርት ኮሪደሮችን እንደዚሁም
ልንጠቀምባቸው ከምንችላቸው ወደቦች ጋር የሚያገናኙ የባቡር
መስመሮችን መዘርጋት ያስፈልጋል፣

41 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ

 የአየር ትራንስፖርት ማስፋትና ማጠናከር፣


 የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎትን ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ
ማድረግ፣
 አስተማማኝና በዋጋም ተወዳዳሪ የሆነ የኤሌክትሪክ ኃይል
አገልግሎት ሊኖር ይገባል፣
 የውሃና የመሬት አቅርቦትን ማሻሻል፣

42 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
2.5 የሰው ኃይል ሥልጠናን በብቃት መፈፀም፣

ይህ ምን ያካትታል?
 ሥራውን በብቃት ለመፈፀም የሚያስችለው የተሟላ
ዕውቀትና ክህሎት ያለው ታታሪና በሥነምግባር የታነፀ
ሠራተኛ ያስፈልጋል፣
 በሙያውና ሥነምግባሩ በሚፈለገው ደረጃ የደረሰ የሥራ
አመራር አገልግሎት የሚሰጥ የሰው ኃይል ያስፈልጋል፣
 በራሱ ተነሳሽነት ሥራን ለመፍጠር ፍላጎቱና ብቃቱ ያለው
የሰው ኃይል ያስፈልጋል፣(የሞያና ቴክኒክ ስልጠናችን ስራ
ፈጣሪ ሰዉ ለመፍጠር)

43 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ

 ስለዚህ የሰው ኃይል ልማትና ሥልጠና ሥራችን እነዚህን


እንዲያሳካ ማድረግ አለበት፣
 የሙያና የቴክኒክ ሥልጠናን ማስፋትና ጥራቱን ማሻሻል
ያስፈልጋል፣
 የመንግሥትና የባለሀብት፣ የመምህራንና አሠልጣኞች፣
የተማሪዎች… ወዘተ የተቀናጀ ጥረትን ይጠይቃል፣
 በየተቋሞቻችን ያለውን የሥራ አመራር ሥርዓት ለማሻሻል
መጣር አለብን፣

44 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
2.6 መንግሥት ጠንካራ የአመራር ሚና የሚጫወትበትን አቅጣጫ
መከተል፡-

 ምንድነው? ለምን ዓላማ ያስፈልጋል? ምን ይደረጋል?


(ብቃት ባለዉ አመራር የገበያ ጉድለትን መሙላትና ልማት መፋጠን፣ ክርክር
ቢኖርም ጣልቃገብነት የሌለበት ገበያ አለመኖሩ)

45 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
2.6.1 ግልፅነት፣ ተጠያቂነትና ቅልጥፍና ያለውን አሠራር ማስፈን
ያስፈልጋል፣

 የሠራተኛ እምነትና አመለካከት ከመመሪያዎችና አሠራሮች


ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ማድረግ ይገባል፣ ለልማት ቆርጦ
የተነሳ የሲቪል ሰርቪስ መገንባት ያስፈልጋል፣
 በቂ ሙያ ያለው ሲቪል ሰርቪስ መገንባት አለብን፣
 ታታሪና በሥነ ምግባር የታነፀ ሲቪል ሰርቪስ መገንባት አለብን፣
 ሕዝብን አገልጋይ የሆነ ለሕግና ፖሊስዎች ተገዥ የሆነ ሲቪል
ሰርቪስ ሊኖረን ይገባል፣

46 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
2.6.2 ጠንካራ የገበያ ውድድርን የሚያሰፍን አሠራር ማንገስ፣
 ለልማታዊ ባለሀብቶች የሚሰጠው ድጋፍ የገበያ ውድድርን
የሚያጠናክር መሆን አለበት፣
 ከመንግሥት ለባለሀብቶች የሚሰጡ ድጋፎች የባለሀብቱን
ተወዳዳሪነት የሚደግፉ መሆን አለባቸው፣
 የመንግሥት ድጋፍ መሰጠት ያለበት በገበያ ውድድር አሸንፎ
ለመወጣት ፍላጐቱና ዝግጁነት ላለው መሆን ይኖርበታል፣

47 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ

 የመንግሥትን ዕገዛ አግኝቶ የመወዳደር ብቃቱን ለመገንባት


ባለመቻሉ ከውድድር የሚወጣውን ለማዳን መንግሥት ምንም
ሙከራ ማድረግ የለበትም፣
 ጠንካራ ውድድርን የሚገድቡ ጉዳዮችን አጥንቶ ሥር ነቀል
በሆነ አኳኋን ለመፍታት የሚያስችል የህግ፣ የኢኮኖሚና
የአስተዳደር እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፣

48 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
2.6.3 ልማትን የሚደግፍ የመረጃና የግብር ሥርዓት መዘርጋት፣

 ዘላቂና ጠንካራ የልማት ሥራ ለመሥራት መንግሥት ግብር


መሰብሰብ መቻል አለበት፣ ግብር መክፈል ያለበት ሁሉ
እንዲከፍል መደረግ አለበት፣
 ጥገኛው ግብር ሳይከፍል የሚያመልጥበት ሁኔታ መቆም
አለበት፣
 ልማታዊ ባለሀብቱ የመወዳደር አቅሙን ለማጐልበት
የሚያስችለው ጊዜ እንዲያገኝ ለተወሰነ ጊዜ የታሪፍ ከለላ
የሚያገኝበት ሁኔታ መመቻቸት አለበት፣

49 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ

 የመንግሥት ወጪ አሸፋፈን ከገቢው ጋር የተጣጣመና የዋጋ


ግሽበትን የማያስከትል መሆን አለበት፣

 ዋነኛው መንገድ የመንግሥት ገቢ በተከታታይና ፋይዳ ባለው


ደረጃ ማደግ አለበት፣

 የሰዎችና ኩባንያዎችን ገቢ በትክክል ለማወቅ የሚረዳ


ወቅታዊ የመረጃ ሥርዓት ሊኖር ይገባል፣

50 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
2.7 ቀልጣፋ የፍትህ አስተዳደር ሥርዓት መፍጠር
ምን ማለት ነው? ለምን ያስፈልጋል?
 የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ በመሠረቱ የኮንትራት ኢኮኖሚ ነው፣ ይህ
ኮንትራት የሚከበረው በፍትህ ሥርዓቱ ነው፣
 በሀገራችን ጠንካራ የኮንትራት አስተዳደር ሥርዓትና ባህል
ሊዘረጋ ይገባል፣ ሥርዓቱም ቀልጣፋና በቀጣይ የማይንከባለል
መሆን አለበት፣
 የቀለጠፈና ፍትሃዊ አስተዳደር መስፈን ለኢንዱስትሪ ልማቱ
እንደመሠረተ ልማት የሚያስፈልግ ነው፣

51 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
ክፍል ሶስት
ለልማታዊ ባለሀብቱ ቀጥተኛ ድጋፍና አመራር መስጠት
 ለተመረጡ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ግልፅ አሰራር በመዘርጋት
ቀጥተኛ ድጋፍ መስጠት ያስፈልጋል፣
 ይህም ሁኔታ ትኩረት የሚሰጣቸውን:-

• ዘርፎች በቀጥታ ለመርዳት፣

• ባለሀብቶችን ለመፍጠርና ለማጠናከር


 ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ትኩረት የሚሰጣቸው ዘርፎች፡-

52 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
3.1 የጨርቃጨርቅና የልብስ ስፌት ኢንዱስትሪ፡-

የብዙ ሀገሮች የዕድገት መነሻ ተደርጐ የተወሰደ ዘርፍ ነው፣


 ብዙ ሰራተኛ ግን ተመጣጣኝ ክፍያ ያለውና ምርታማነቱ የላቀ
ሠራተኛ ወሳኝ ነው፣
 ከግብርናው ጋር ተመጋግቦ ማደግ ይችላል/ አለበት፣
 ከውጪ ገበያ ለመወዳደር ዕድል የሚሰጥ ዘርፍ ነው፣
 ስለዚህ የጥጥ ምርትን፣ የስፌት ፋብሪካዎችን፣ የጨርቃ
ጨርቅ ፋብሪካዎችን በየደረጃውና በተመጋገበ ሁኔታ ማሳደግ
አለብን፣
 የእነዚህን ዕድገት ሊወስኑ የሚችሉ አካላትን አስተዋፅኦ
በጣምራ መጠቀም መቻል አለበት፡፡

53 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT
BUREAU
ዕድገቱን ሊወስኑ የሚችሉ አካላት፡-
• ባለሀብት፣
• አ/አደር/ማህበራት፣
• የሥልጠና ተቋማት፣
• የምርምር ተቋማት፣
• የጋራ ምክክር መድረክ፤
የሴክተሩ ወሳኝ ችግሮች
• የምርታማነት ማነስ ነው፤
• የሥራ አመራር ጉድለትና፤
• የሠራተኛው የሥራ ችሎታ ደካማ መሆን፤
 ስለዚህ እነዚህን ችግሮች በተቀናጀና የተለያዩ አማራጮችን (የሀገር
ውስጥና የውጪ የልማት ኃይሎችንም በመጠቀም) ማቃለል ያስፈልጋል፡፡

54 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
……የቀጠለ
 በዘርፉ የውጪና ኢትዮጵያዊያን ባለሀብቶች ኢንቨስት
እንዲያደርጉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ያስፈልጋል፣
 ምን በማድረግ?
• የፋይናንስ አቅርቦት በማሻሻልና ቀልጣፋ በማድረግ፤
• ባለሀብቶችን በዕቅድ ላይ ተመሥርቶ ወደዘርፉ እንዲገቡ
መገፋፋትና ማሳመን፤
• የመሬት አቅርቦት ማሻሻልና ቀልጣፋ በማድረግ፤
• የመሠረተ ልማት አቅርቦትን በማቀላጠፍና ፍትሐዊ
በማድረግ

55 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ

 የሰው ኃይል ልማት በማጎልበት


 አጭር የመለማመጃ ጊዜ መስጠት (የታሪፍ ከለላ)፣
 ትኩረት በውጪ ንግድ (ኤክስፖርት) ላይ እንዲሆን ማድረግ፣
 የገበያ አውታር እንዲሰፋ ማገዝ (የውጪ ገበያን ሰብሮ
ለመግባት)፣
 ገበያ ሰብሮ ከተገባ በኋላም በቀጣይ ስምን መጠበቅ፣
 በኤክስፖርት ንግድ ፋይናንስ መደገፍ (ሥራ ማስኬጃ)፣

56 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ
 የምርቶች ጥራት የሚረጋገጥበትን አሠራር ማጠናከር አለብን፣
 ቀልጣፋ የግብይት ሥርዓት መዘርጋት፣
 ምን ያካትታል?
• የዋጋ መረጃ
• የጉምሩክ አሠራር
• ቦንድድ ዌር ሀውስ አገልግሎት
 ለዘርፉ ድጋፍ የሚሰጡ አቅርቦቶችንና ኢንቨስትመንቶችን ማበረታታት፣
• ፓኬጂንግ
• ኬሚካል
• መለዋወጫና አክሰሰሪዎች

57 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
3.2 የሥጋ፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪን በሚመለከት፡-
ምንድነው? ምን አቅም አለው? ምን ይደረግ?
 ሰፊ የእንሰሳት ሀብት አለን፣
 ከዚህ ሀብት ሥጋ፣ ቆዳና ሌጦ በብዛት ማግኘት እንችላለን፣
 የኤክስፖርት መር አቅጣጫ ተከትለን በምርቶቹ ላይ በሀገር
ውስጥ ዕሴት ጨምረን ወደ ውጪ መላክ አለብን፣
 በዘርፉ የሚሳተፉ ባለሀብቶችን፣ አርሶ አደሮች/አርብቶ
አደሮችን፣ ቄራዎችን፣ የቆዳ ፋብሪካዎችን፣ የጫማና አልባሳት
ፋብሪካዎችን፣ ሌሎች ድጋፍ ሰጪ ተቋማትን በማስተባበርና
በሚታወቅ ዕቅድ በመምራት መሥራት አለብን፣

58 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ
 የእንሰሳት ሀብት ልማትና የቆዳ ውጤቶች ንዑስ ዘርፍ
ቅድሚያ አግኝተው ሊያድጉ ይገባል፣
 የቆዳ ማምረቻ ፋብሪካዎቻችን ከፍተኛ ዕሴት ወዳለው
ምርት እንዲሸጋገሩ ማድረግ አለብን፣
 በእንሰሳት ሀብት ልማት ረገድ ያለብንን የጥራት ችግር
መፍታት አለብን፣
 የመኖ
 የጤና
 የአያያዝ
 የዕርድ
 ወዘተ
59 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT
BUREAU
…የቀጠለ

 ለጨርቃጨርቅና አልባሳት ዘርፍ የሚሰጡ ድጋፎች ለዚህም


ዘርፍ መሰጠት አለባቸው፣
 ያሉን ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱና
ጥረታቸውን እንዲያሻሽሉ ማድረግ አለብን፣
 የቆዳና ሌጦ ግብይት ሥርዓት አጭርና ቀልጣፋ እንዲሆን
መደረግ አለበት፣

60 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
3.3 አግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪን በሚመለከት፡-

 ሰፊ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ነው፤


 በተለይ ለትናንሽና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ማደግ ከፍተኛ
ዕድል የሚፈጥር ነው፤
 የፖሊሲው ትኩረት ለውጪ ገበያ በሚቀርቡ ምርቶች ላይ ነው፣
 ከግብርና ጋር ተመጋግቦ ማደግ የሚችል ነው፤
 ምርቱ በዋጋና ጥራት በዓለም ተወዳዳሪ መሆን አለበት፤
 የውጪ ገዥዎችንና ኢንቨስተሮችን በመስኩ መሳብ አለብን፤
• የምግብ ኢንዱስትሪ፣ስኳር፣ቡና፣ቲማቲም፣ወተትና
የወተት ተዋፅኦ፣ማርና ሰም፣ወዘተ..

61 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
3.4 የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪን በሚመለከት፡-

 በልማት እንቅስቃሴያችን ልዩ ሚና ያለው ነው፣


 ሰፊ የሰው ኃይል ይጠቀማል፣
 በወጪ ንግድም በቀጥታ መሳተፍ የሚችል ነው፣
 የግንባታ ግብዓቶች አቅራቢ ኢንዱስትሪን ዕድገት የሚደግፍ
ነው፣
 ጥቃቃንና አነስተኛ ተቋማት በስፋት ሊሠማሩበት የሚችል
ነው፣

62 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ
 በቁጠባ የቤት ባለቤት መሆን የሚቻልበትን ዕድል የሚፈጥር ሊሆን
ይችላል (በመደራጀት ጭምር)
 በዘርፉ ተዋናይ የሆኑትን ክፍሎች ያሳተፈ በአግባቡ የተደራጁ የጋራ
መድረክ መፍጠርና በዕቅድ መመራት ያስፈልጋል፣
 የካፒታል እጥረት የሚታይበት ዘርፍ ስለሆነ ይህንን ለማቃለል
የሚረዱ አማራጮችን መጠቀም ይገባል፣
 ባንኮችና ኢንሹራንሶች፤
 መሣሪያ የማከራየት አገልግሎት፤
 ሠልጥነው የሚወጡ ወጣቶች ራሳቸውን በአነስተኛ ኩባንያ መልክ
እንዲያደራጁና በተለያዩ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ውስጥ
እንዲሰማሩ ማድረግ ይገባል፣

63 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ
 የሞርጌጅ ኩባንያዎችን ቁጠባን ለማስፋትና የመኖሪያ ቤት
እጥረትን ለማቃለል መጠቀም ይቻላል/ይገባል፣
 የሴክተሩን የሰው ኃይል ዕጥረት ለማቃለል የከፍተኛ ትምህርት
ተቋማት፣ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማትን ማጠናከርና
ማስፋት ያስፈልጋል፣
 አጫጭር የሥራ ላይ ሥልጠናዎችንም በየጊዜው በመስጠት
ክህሎትን መገንባት ይገባል፣

64 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ

 የሙያ ማረጋገጫ ሥርዓት መዘርጋትና መጠናከር አለበት፣


 የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ከተመጋቢ ሌሎች ዘርፎች ጋር
ተደጋግፎና ተመጋግቦ ማደጉን ማረጋገጥ ይገባል፣
 በሀገር ውስጥ በሚመረት ምርት ሊተካ የሚችል ግብዓትን
በተቻለ መጠን መተካትና ለዚህም በሂደት ፋብሪካዎች
እንዲቋቋሙ ማድረግ ያስፈልጋል፣

65 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
3.5 አነስተኛና ጥቃቅን ኩባንያዎችን ማጠናከር በሚመለከት፡-
ለምን ያስፈልጋል? እንዴት ይጠናከራሉ?
 የሰው ኃይልን በሰፊው ይጠቀማሉ፣
 በአነስተኛ ካፒታል ሊሠሩ ይችላሉ፣
 በበርካታ ዘርፎች የሚሰማሩ ናቸው፣
 በሀገራችን ሰፊ ልማታዊ ባለሀብት ለመፍጠር የሚያስችሉ ዓይነተኛ
መሣሪያዎች ናቸው፣
 በየክልሉና በየማዘጋጃ ቤቱ እነዚህን ተቋማት ለመደገፍ የሚቋቋሙ
ተቋማት ሊኖሩ ይገባል፣
 በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና በተጨማሪ የኢንተርፕርነርሺፕ (ሥራ
የመፍጠርና ሥራ አመራር) የሥልጠና ድጋፍ ሊያገኙ ይገባል፣

66 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ
 የምርት ጥራትንና ምርታማነታቸውን ለማሻሻል
አመራራቸውን ለማጠናከር የሥልጠና ፕሮግራም ሊቀረፁ
ይገባል፣
 የመነሻና ማስፋፊያ ካፒታል ዕጥረታቸውን የተለያዩ
አማራጮችን በመጠቀም (ባህላዊ ቁጠባን ጭምር በመቀጠም)
መፍታት ይገባል፣ ከመንግሥት የልማት ዕቅዶች ጋር በቀጥታ
በማያያዝ መፍታትም ይቻላል፣
 ከመካከለኛና ትላልቅ ኩባንያዎች ጋር በሰብ-ኮንትራት እንዲሠሩ
ማድረግ ይገባል፣
 ማዘጋጃ ቤቶች መሬት በመስጠት እነዚህ ኩባንያዎች
ሊስፋፉባቸው የሚችሉባቸውን መንደሮች በመገንባት ሊደግፉ
67ይችላሉ፣ AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT
BUREAU
3.6. የኢንዱስትሪ ልማት ቀጣይነትን የሚያረጋግጡ ቅድመ
ዝግጅቶች ማድረግ

ምን ማለት ነው? የትኩረት መስኮቹ ምንድናቸው?

 የኢንዱስትሪ ዕድገት ከአንድ ምዕራፍ ወደሌላ ምዕራፍ ሳያቋርጥ


መሸጋገር መቻል አለበት፣
 የኢንዱስትሪ ዕድገቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ እጅግ ተፈላጊ
ከሚሆኑት መካከል መሠረተ ልማትና ፋይናንስ በቅድሚያ
ይጠቀሳሉ፣
 በስትራቴጂው መነሻ የተቀመጡ ውጥኖች ሲሳኩ ተጨማሪ
አቅምና ጥረት መፍጠራቸው እንዳለ ሆኖ ሌሎች ፍላጐቶችንም
ይዘው ይመጣሉ፣

68 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ
 እነዚህንና ሌሎች ፍላጐቶች ለማሟላት የሚረዱና ከውጪ
የሚገቡ ግብዓቶችን የሚተኩ ኢንዱስትሪዎችን ለመገንባት
ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል፣
 በመሆኑም ከመጀመሪያው ምዕራፍ ወደሚቀጥለው ምዕራፍ
ለመሸጋገር የሚያስችለን ዕቅድና ዝግጅት ሊኖረን ይገባል፣
 በቀጣይ ምዕራፍ ካፒታሉ ቢኖርም የቴክኖሎጂ አቅም
ካልተገነባ ዕድገቱን ቀጣይ ማድረግ አይቻልም፣ ይህ ደግሞ
የረጅም ጊዜ ዕይታና ጥረት የሚጠይቅ ነው፣

69 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ
 በተለዋዋጭ የግልም ኢኮኖሚ ሁኔታ አንፃር የመወዳደር
ብልጫ የሚሰጥን መስክ በመለየት መጠቀም መቻል አለብን፣
 በዚህ ረገድ ሊጠቀሱና ከወዲሁ ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው
የሚገባ የመረጃ፣ መገናኛ ቴክኖሎጂና የባዮ ቴክኖሎጂ ናቸው፣
 እነዚህን ቴክኖሎጂዎች መጠቀምና ማሳደግ የሚችል የሰው
ኃይል ማፍራት አንዱ የትኩረት አቅጣጫ መሆን አለበት፣
 ሀገራችን በዕፅዋትም ሆነ በእንሰሳት ከፍተኛ ሀብት አላት፣
በመሆኑም ባዩ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ይህንን ሀብት በላቀ
ደረጃ መጠቀም ይቻላል፣

70 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU
…የቀጠለ
 ጥራታቸው የተጠበቀ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትንና
የምርምር ማዕከላትን ማቋቋምና ማጠናከር ያስፈልጋል፣
 የጀነቲክ ሀብታችንን መጠበቅና ተጠቃሚም የምንሆንበትን
ሥርዓት መዘርጋትና ማጠናከር ይገባናል፣
 የቴክኖሎጂ ዕድገታችን ከልማቱ ፍላጐትና ዕድገት ጋር ተጣጥሞ
የሚፈፀምበት ጥብቅ ትስስር መፍጠር ያስፈልጋል፡፡

71 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT BUREAU


አመሰግናለሁ!!

72 AMHAR INDUSTRY & INVESTMENT


BUREAU

You might also like