Professional Documents
Culture Documents
የሴቶቸች ሚና በቤተክርስቲያን
የሴቶቸች ሚና በቤተክርስቲያን
በ
ቤተክርስቲያን
መግቢያ
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ
የክርስቲያኖችን አንድነት በሦስት “ፆታ ምዕመናን” ይከፍላቸዋል።
እነርሱም ወንዶች፣ ሴቶችና ካህናት ናቸው።
እግዚአብሔር በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተናገረን በመንፈሳዊ
ህይወት የሁሉም ፆታ ምዕመናን ዓላማ መስዋዕትነትና ከራስ በላይ
ለሌሎች መኖር ነው።
ወንዶች የቤተሰብ ራስ (ተጠሪ) መባላቸው እንደ ክርስቶስ
ራሳቸውን ስለቤተሰባቸው ቤዛ እስከማድረግ የሚገለጥ ነው።
ሴቶች የሕይወት ምንጭ (እናት) በመሆናቸው በብዙ መከራ
እየተፈተኑ የቤተክርስቲያንን ሕይወት ያስቀጥላሉ።
ካህናትም ክህነታቸው “እናንተም እንዲሁ አድርጉ” ብሎ አብነት
እንደሆናቸው ጌታ ዝቅ ብለው ምዕመናንን እንዲያገለግሉ ነው።
የሴትነት (የእናትነት) አገልግሎት
ክብር
“ ቅድስት ሥላሴ ” ብለን በእናት አንቀፅ
መጥራታችን
“ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ” ሰው ሁሉ
እናታችን ጽዮን ይላል (መዝ 86:5)” ተብሎ በትንቢት
የተነገረላት፣ “እነኋት እናትህ (ዮሐ 19:38)” ብሎ
በአካል የሰጠን እናታችን ናት።
“ እናት ቤተክርስቲያን ”
የሴቶች አገልግሎት በብሉይ ኪዳን
እናታችን ሔዋን (ዘፍ 3:20)
እናታችን ሣራ ደግሞ የእስራኤል ዘሥጋ እናት (ዘፍ 17:16)
ያዕቆብ በረከትን እንዲያገኝ ያደረገችው ርብቃ
የዮሴፍ እናት ራሄል
ሙሴን በፈርኦን ቤት በጥበብ ያሳደገችው የሙሴ እናት (ዮካቤድ) (ዘፀ 1:28
ሕዝበ እስራኤል ባህረ ኤርትራን ከተሻገሩ በኋላ ከበሮን ይዛ ምስጋናውን ስትመራ የነበረችው
የሙሴ እኅት ማርያምም ሴቶች በዝማሬ እና በምስጋና ዘርፍ ለሚያበረክቱት ድርሻ አብነት ሆናለች
(ዘጸ 15:20)
የእስራኤልን ሰላዮች ተቀብላ ያተረፈቻቸው በኢያሪኮ ትኖር የነበረችውና በኋላም በዳዊትና
በክርስቶስ የዘር ሀረግ ለመቆጠር የበቃችው ረዓብ ሌላዋ ታላቅ ሴት ነበረች።
እግዚአብሔር በገለጠላት ጥበብ የጠላትን መሪ ድል ያደረገችው ዮዲት (መጽሐፈ ዮዲት 1)፣
በድንቅ እምነቷ እግዚአብሔር ከሐሰት ፍርድ ያዳናት ሶስና (መጽሐፈ ሶስና 1)
የቀጠለ…
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ ስለ ተአምራት ሲያስተምር “
ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ
ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፥ እነሆም፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ (ማቴ 12:42)”
በማለት የተናገረላት ንግሥተ ዓዜብ
ለእስራኤል ድኅነት ምክንያት የሆነች ታላቅ ሴት አስቴር (አስቴር 4:14)።
አቢጊያ ከባልዋ ከናባል ይልቅ ባለታላቅ አእምሮ ስለነበረች ከዳዊት ጦር የታዘዘውን የሞት ቅጣት
በጥበብ መመለስ ችላለች (1ኛ ሳሙ 25:3)።
ጌታችንን በመቅደስ ያመሰገነችው (በሉቃ 2:36-38) ነቢይት ሐና ሴቶች ነቢያት ሆነው (በፆም
በጸሎት ተወስነው መጻዕያትን እየተናገሩ፣ የእግዚአብሔርን ድንቅ ስራ እየመሰከሩ) ሲያገለግሉ
እንደነበር ጥሩ ማሳያ ናት።
በእስራኤል የፍርድ ወንበር ተቀምጣ ትፈርድ የነበረችው ዲቦራም (መሳፍ 4:4-5) ሴቶች በኃላፊነት
ደረጃ ተቀምጠው ለሕዝብና ለቤተክርስቲያን የሚጠቅም ሥራን መሥራት እንደሚችሉ ጥሩ ምሳሌ
ናት።
የእምነቷ ጽናት በልዩ ሁኔታ የተመሰከረላትና ከክርስቶስ የትውልድ ሀረግ የተቆጠረችው ሞአባዊቷ
ሩት እንዲሁ ልዩ ምሳሌያችን ሆና ትኖራለች።
የሴቶች አገልግሎት በዘመነ ሥጋዌ
ቅድስት ድንግል ማርያም ከሴቶች ሁሉ የተለየች ናት (ሉቃ 1:26-30)
ቅድስት ኤልሳቤጥም (ሉቃ 1:39-44)
ሰሎሜ
ሳምራዊቷ ሴት (ቅድስት ፎቲና) (ዮሐ 4:4-26)።
36 ቅዱሳት አንስት (ዮሐ 10:38):።
ያላትን አንዲት ዲናር ሰጥታ ጌታችን እምነቷን ያደነቀላት ሴት፣
የልብሱን ጫፍ ብነካ እድናላሁ ብላ በማመን ልብሱን ነክታ የዳነችው ደም
ይፈሳት የነበረችው ሴት (ዮስቃና)
ማርያም እንተ ዕፍረት
ጌታችን መስቀል ተሸክሞ በጎልጎታ መከራን ሲቀበል አይሁድን ሳትፈራ ላቡን
እንዲጠርግበት መጎናጸፊያዋን የሰጠችው ቅድስት ቬሮኒካ
ማርያም መግደላዊት (ማቴ 28:1)
የሴቶች አገልግሎት በዘመነ
ሐዋርያት
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ (
ሮሜ 16:1-7) የጻፈላቸው ፌቤንና፣
ጵርስቅላና አቂላ ሌሎችም ቅዱሳት ሴቶች
ወንጌላዊው ዮሐንስም (2ኛ ዮሐ 1:1) “በእኛ ስለሚኖርና ከእኛ ጋር
ለዘላለም ስለሚሆን እውነት፥ እኔ ሽማግሌው በእውነት
ለምወዳቸውና እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ደግሞ
ለሚወዱአቸው ለተመረጠች እመቤት ና ለልጆችዋ፤ ከእግዚአብሔር
አብና ከአብ ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም
በእውነትና በፍቅር ከእኛ ጋር ይሆናሉ።” በማለት ያገለግሉ ከነበሩ
ቅዱሳት ሴቶች መካከል ለነበረችው ሮምና ን “እመቤቴ”
የሴቶች አገልግሎት በዘመነ
ሰማዕታት
ሰማዕታት ታሪካቸውን በደም የጻፉ ቅዱሳት አንስት
ቅድስት አርሴማ (ስንክሳር መስከረም 29)
ከ50 ቅዱሳት አንስት ጋር በንጉሥ ዑልያኖስ ሰማዕትነትን የተቀበለችው
ቅድስት ሶፊያ
በንጉሥ ዴሲየስ ዘመን ሰማዕትነትን የተቀበለችው ቅድስት አንስጣስያ፣
ገድላቸው ሲዘከር የሚኖረው ቅድስት ባርባራ ፣ ቅድስት ዮልያና እና
ቅድስት ዮስቲና፣
በጽኑ ተጋድሎ ክብርን ያገኘች ቅድስት ዕንባ መሪና (ስንክሳር ነሐሴ 25)፣
ገዳማዊ ሕይወትን ለእናቶች ያስተማረች ሰማዕቷ ዴምያና፣
ከልጇ ጋር ሰማዕትነትን የተቀበለችው ቅድስት እየሉጣ ና (ስንከሳር
ሐምሌ 19) ሌሎችም
…የቀጠለ
ለ25 ዓመታት በገዳም የተጋደለችው ቅድስት ማርታ ተሐራሚት (ስንክሳር ሰኔ 3)፣
በዘመነ ሰማዕታት ልጇን በደም ያጠመቀችው ቅድስት ሣራ ፣
የጌታችን ቅዱስ መስቀል ከ300 ዓመታት በላይ ከተቀበረበት እንዲወጣ ያደረገችው
ንግሥት ኢሌኒ የክርስትና ታሪክ ፈርጦች ናቸው።
የቤተክርስቲያን ወርቃማ ዘመን በሚባለው
በ4ኛው መቶ ከፍለ ዘመን የነበሩት የቅዱስ አውግስቲን እናት ቅድስት ሞኒካ፣
የቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ እኅት ቅድስት ማክሪና
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ረዳት የነበረችው ቅድስት ኦሊምፒያ
ከዚህም ባሻገር ታላላቅ ቅዱሳንን ያስገኙልን እንደ
ቅድስት እግዚእ ኃረያ
ቅድስት አቅሌስያ
የቀጠለ….
ጻድቋ ክርስቶስ ሠምራ (ስንክሳር ነሐሴ24)፣
ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት በመዐርግ የተስተካከለችውና ከላሊበላ ውቅር አብያተ
ክርስቲያናት አንዱን ያነፀችው ቅድስት መስቀል ክብራ (ስንክሳር ሐምሌ 28)፣
በቅድስናና በንጽሕና ኖራ ሰማዕትነትን የተቀበለችው ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ
(እመ ምዑዝ) (ስንክሳር የካቲት 29)፣
ካቶሊካውያን ቅኝ ገዥዎች በሀገራችን ኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳውያንን አስገድደው
እምነት በማስለወጥ ላይ በነበሩበት ዘመን በቅድስናና በጥብዓት ሰማዕትነትን
የተቀበለችው ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ (ስንክሳር ህዳር 17)
ጸዋሬ ክርስቶስ የሆነችው ኢትዮጵያዊቷ ቅድስት ፀበለ ማርያም
የሴቶች አገልግሎት በዘመነ
ሊቃውንት
በቅኔው ዘርፍም ድንቅ ታሪክን ያስመዘገበችው እማሆይ ሃይመት፣
ሴቶች በመንፈሳዊው ዕውቀትና በማስተማሩም ሥራ ታላቅ ድርሻ ማበርከት እንደሚችሉ
አርአያዎች በዘመናችንም ያሉት
መምህርት ጥዕምተ ዜማ፣
መምህርት ሶስና በላይ ፣
መምህርት ሕይወት ፀሐይ ናቸው።
ያሳዩት አርአያነት ሴቶች ከባድ በሚባለው የቅኔ ዘርፍ ሳይቀር በማስተማር ጉልህ ድርሻ
ሊኖራቸው እንደሚችል ማረጋገጫዎቻችን
እማሆይ ገላነሽ ፣
ቀጥሎም የመጡት ሴት የቅኔ መምህራን
እማሆይ ኅሪትና
እማሆይ ወለተ ሕይወት ናቸው።
ብዙ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለቤተክርስቲያን ያበረከቱት እቴጌ እሌኒ