You are on page 1of 2

የንብረት መብት ከ ጋብቻ ግንኙነት አንፃር

የፌደራሌ ጠቅሊይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የወሰናቸው አስገዳጅ የህግ ትርጉሞች

1. የኮንዶሚኒየም ቤት ሇማግኘት የተደረገ ምዝገባ ከጋብቻ በፊት ቢሆንም ፡ ቤቱን እንዲገዙ እጣ የወጣው
ጋብቻው ፀንቶ ባሇበት ጊዜ ከሆነ ፡ ምዝገባው ከጋብቻ በፊት ስሇሆነ ብቻ የኮንዶሚኒየም ቤቱ ሇተመዘገበው ተጋቢ
የግሌ ንብረት እንደማይሆን ከ ፌዴራለ የቡተሰብ ህግ ቁጥር 62(1) እንረዳሇን ፡፡በመሆኑም ቤቱ የጋራ ሆኖ
ጋብቻው ከፈረሰ በኋሊ ተጋቢዎች መብትና ግዴታውን እኩሌ መካፈሌ አሇባቸው ፡፡ የሰበር መዝገብ ቁጥር 46606
ቅፅ 11

2. አንድ ተጋቢ ከጋብቻ በፊት የነበረውን የግሌ ቤት በጋብቻ ሊይ እያሇ በመሸጥ በሽያጩ ብር ላሊ ቤት ሲገዛ
በቡተሰብ ህጉ ቁጥር 58(2) መሰረት በግብይት የተገኘው ቤት የግሌ ሆኖ ይቀጥሌ ዘንድ በፍርድ ቤት ቀርቦ የግሌ
መሆኑን ማፀደቁ እስካሌተረጋገጠ ድረስ ፡ የአንደኛው ተጋቢ የግሌ የነበረው ቤት ተሸጦ በሚገኘው ገንዘብ በጋብቻ
ወቅት የተገዛው ቤት የጋራ ሀብት ይሆናሌ ፡፡ የሰበር መዝገብ ቁጥር 37275 ቅፅ 8

3. ባሌና ሚስት በጋራ ሀብታቸው ሊይ እኩሌ የሆነ መብት አሊቸው ፡ የአንደኛው ከላሊኛው አያንስም ወይም
አይበሌጥም ፡፡ የጋራ ንብረት ክፍፍሌ ስርአትም ይህን መሰረት በማድረግ መከናወን አሇበት ፡፡ ባሌና ሚስት በፍች
ወቅት የጋራ ንብረታቸውን ሇመከፋፈሌ ስምምነት ሊይ ያሌደረሱ ከሆነና ንብረቱ ፡ በዏይነት ሉካፈሌ የማችሌ
እንደሆነ ንብረቱ ተሸጦ የተገኘውን ዋጋ እኩሌ እንዲካፈለ መደረግ አሇበት እንጅ ፡ ተጋቢዎች ባሌተስማሙበት
ሁኔታ በእጣ እንዲካፈለ መወሰን የሀግ አግባብ የላሇውና የእኩሌነት መርህን የሚጥስ ነው ፡፡ የሰበር መዝገብ ቁጥር
61788 ቅፅ 11

ሳሙኤሌ ግርማ
የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ
+251 911 190 299

You might also like