You are on page 1of 2

የተባለን ማለትህ አዋቂ አያደርግህም!

መድገም ለምን ይጣፍጠናል?


ወሬ መድገም፤ ቡና መድገም፤ የሰው ስራ መድገም፣ copy ማድረግ፣ መኮረጅ፤ አባባል፣ ፅሁፍ፣ መድገም፤ በእውነቱ አዲስ ነገር ማድረግ ከብዶን
ነውን?
አይደለም! ጉዳዩ የመደጋገም ልማድ ውጤት ነው።
የምናየው ሁሉ የተደጋገመ ነው፣ የሚናገረው ሳይሆን የሚያስተጋባው፣ የሚያሟሙቀው በዝቷል።
ከሚጨፍረው አስጨፋሪው ቁጥሩ ጨምሯል። የተባለን ማለታችን የእኛ ያደረገው ይመስለናል።
አዎ! ጀግናዬ..! የተባለን ማለትህ አዋቂ አያደርግህም!
የተሰራን መድገምህ ምሁር አያሰኝህም!
አዋቂ ለመሆን ወይ ልትጨምርበት ወይም አዲስ ግኚት ሊኖርህ ይገባል።
ምሁር ለመባል የእራስህ ስራ፣ የእራስህ ፈጠራ፣ የእራስህ ግኝት ያስፈልግሃል።
የሚደግም ሞልቷል።
አዎ! የተባለም አንዴ ተብሏል፤ ያንተ መደጋገም፣ መድገምን መውደድህንና የሰው ስራ ባለቤት ለመሆን የምታደርገውን ጥረት ከማሳየት ውጪ
ሌላ የሚያመለክተው ነገር የለም። "በሎሌው ጀብድ ንጉስ ተሞገሰ" እንደሚባለው እንዳይሆንብህ።
አዎ! ጀግናዬ..! በእራስህ መንገድ ተፅኖ ፍጠር፣ የራስህን Brand መለያ ገንባ፣ በፈጠራህ፣ በግኝትህ፣ በስራህ እመን ከልብህ ተማመን፤ በሰው ሰራ
መኩራትህን ትተህ ወደ እራስህ ተመለስ።
መንገስ ካለብህ አንተው በሰራሀው ንገስ፤
መሞገስ፣ መመስገን ካለብህ በእራስህ ስራ፤
የሌላን Credit ለመውሰድ ሳይሆን የእራስህን ለማስፋት ተሯሯጥ።
በመደጋገም፣ የተባለውን በማለትህ ልታጣ የምትችለው አንተነትህን ነው፣ በማንነትህ ማድረግ የምትችለውን፣ መናገር የምትችለውን፣ የፈጠራ
ክህሎትህን፣ እምቅ ሃይልህን ነው።
በሌላ ሰው Photo ከጀርባው ግን በእራስህ Profile አትንቀሳቀስ። ገፅታህ ሌላ ውስጥህ ሌላ አይሁን።
በጊዜው የሚደግም ሞልቷል፤ የሚያብጠለጥል ሞልቷል፤
የሚያጣጥል የትየለሌ ነው፤ በእራሱ የቆመ ጠፍቷል፤ በአንድ ማንነት በተመሳሳይ ገፅ የሚንቀሳቀስ የለም፤
አዎ! አንተ ግን እራስህን አውጣ፤ እራስህን ነጥል፣ እራስህን ለይ፤ ገፅህን አድምቅ፤ ፎቶህን ለጥፍ፤ Profileህን አጠናክር፣ በአንተው ማንነት
በሃሳብህ ቁጪትን አታትርፍ!
እውቁ ቢልዬነር ስቲቭ ጆብስ ምን ይላል "ተግባር የሌለው ሃሳብ፣ ሃሳብ አይደለም እርሱ ቁጪት ነው።"
የዚህን አባባል እውነታነት ለማረጋገጥ የትም አትሒድ፣ ከዚህ በፊት ስታስባቸው፣ ስታሰላስላቸው የነበሩትን አስገራሚ፣ ድንቅና ማራኪ ሃሳቦች
አስታውስ።
በሃሳብህ፣ የእራሴ የምትለው ጥሩ ስራ ነበረህ፤
በሃሳብህ፣ ይሔ ነው የማይባል ትርፍ የምታገኝበት ንድፍ ነበረህ፤
በምናብህ፣ ከእራስህም አልፎ ሰዎችን ሊጠቅም የሚችል ፈጠራ ነበረህ፤
ፍላጎትህ፣ የሚያሳርፉህና እውቀትህን በብዙ የሚያሳድጉልህ፣ የሚቀይሩህ ሃሳቦችን እንድታመነጭ አድርጎህ ነበር፤
አዎ! ጀግናዬ..! ሃሳቡ ስለነበረህ ባለመተግበርህ ዛሬ ቁጪትን አትርፈሃል፣ ዛሬ ያ ያለፈ ጊዜ እንዲመለስ ትመኛለህ፤ ዛሬ ነገ እያልክ ለዛሬ ደርሰሃል፣
ሲመቸኝ አደርገዋለሁ ስትል ነበር ነገር ግን ሳይሆን ቀረ።
አዎ! በኑሮ ሂደት ነገ የሚባለው ቀን ከዛሬ የተሻለ ፋታ የምናገኝበት ቢመስለንም እርሱ ግን የይባስ የተጨናነቀና ፋታ የማይሰጥ ሆኖ እናገኘዋለን።
ምክንያቱም ብዙ ጫና አለብን፣ ሃላፊነታችን እየጨመረ ይሔዳል፣ ተራ ነገሮችን እናቆማለን፤ ህይወታችን በሙሉ በቁብ ነገር መሞላት
ይጀምራል፤ ማስተዋል እንጀምራለን፤ በአንድም ሆነ በሌላ እውቀታችን ይጨምራል፣ ኑሮን ለማሸነፍም ብዙ ነገር እንሰራለን፤ ያኔ አስገራሚው
ሃሳብ ሾልኮ ያመልጠናል፤ ሲመቸን ብንልም ሳይመቸን ይቀራል፤ ነገ ነገ ብንልም ያሰብናትን ነገ ሳናገኝ እንቀራለን።
"ወይኔ ትናንት ባደርገው ኖሮ" የሚለው ቁጪት እንዲመጣ መንገዱን እንከፍታለን።
አዎ! ጀግናዬ..! በሃሳብህ ቁጪትን አታትርፍ!
በምክንያት ተጨንቀህ፣ ተጠበህ ያመጣሀውን ድንቅ ሃሳብ እንደላስፈላጊ ነገር አትጣለው፤
አንተ ብቻ ያለምከውን ትልቅ ህልም እንደ መንደር ወሬ አውርተህ አትለፈው፤ ኑረው!
አዎ! ብዙ ምክንያት ይኖርሃል፤ ቁጪት ግን ምክንያትን አይሰማም፤ በስተመጨረሻ "የማትኖረው፣ የማትሰራው ከሆነ ይህን ሃሳብ ስለምን
አመጣሀው? " ሊልህ ይችላል።
የዛኔ ምላሽህ ምንድነው? ዝምታና ሌላ ጥያቄ እንዳይጠይቅ እርሱን ማስታመም።
አዎ! ጀግናዬ..! እርሱ አያዋጣህም! አለማሰብ፣ አለማለም፣ አለማቀድ አትችልም ሁሌም በውስጥህ የተሻሉ ሃሳቦች ይመጣሉ፤ ሃሳቦችህ ግን
ብቻቸውን አይመጡም ተግባርን ፈልገው፣ ቁጪትንና ወቀሳን በጉያቸው አንግበው ይመጣሉ።
ስለዚህ ሁለት አማራጭ አለህ። አንድም ሃሳብህን፣ ህልምህን መተግበር፣ መኖር፤
ሌላም አይንህ እያየ፣ እያወከው ወደ ቁጪት፣ ወደ ጭንቀት፣ ወደ ብስጪት እንዲቀየር መፍቀድና ወደነርሱ ሰተት ብለህ መግባት።

You might also like