You are on page 1of 1

ቀን 08/07/2015 ዓ.

ቤት ሽያጭ ውል ስምምነት

ውል ሰጭ፡- ወ/ሮ የሻረግ አድማሱ መንግስቴ አድራሻ፡- አማኑኤል ከተማ 01 ቀበሌ

ውል ተቀባይ፡- አቶ ጌታሰው ዋሌ ጋሻው አድራሻ፡- ግራቅዳምን ታዳጊ ከተማ

እኛ ግራ ቀኝ ተዋዋዮች ይህንን የሽያጭ ውል በማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ የህግ ድንጋጌዎች ማለትም የፍ/ህ/ቁ. 1679፣ 1723፣ 1731፣
2878 ና 1166 በሚፈቅደው መሰረት ያለማንም አስገዳጅነት በፈቃዳችን ስናቋቁም በውሉ አግባብ እንዲፈፀም የሚከተሉትን ግዴታዎች
ለመወጣት ተስማምተናል፡፡ ስለሆነም፡-

1. በውል ሰጭ ወ/ሮ የሻረግ አድማሱ ስም የሚገኝ የመኖሪያ ቤት በግራቅዳምን ታዳጊ ከተማ በአዋሳኝ በምስራቅ ገብያው ቦታ ፣
በምዕራብ አማኑ ስማቸው፣ በሰሜን ታየ ጌታሁን እንዲሁም በደቡብ ጌቴ ቢሻው በሚያዋስኑት ቦታ ላይ የካርታ ቁጥር ………
መካከል በ 100 ካ.ሜ. ቦታ ላይ የሰፈረ 25 ዚንጎ ቆርቆሮ ዋና ቤት የሆነውን የግል ቤቴን ለውል ተቀባይ በብር 240,000 / ሁለት
መቶ አርባ ሽህ/ ብር ሸጨለታለሁ፡፡
2. እኔ ውል ተቀባይም ከላይ የተጠቀሰውን ቤት ባለበት ሁኔታ አይቸ ወድጀ በተጠቀሰው ገንዘብ 240,000 / ሁለት መቶ አርባ ሽህ/
ብር ገዝቸዋለሁ፡፡
3. የገንዘቡን አከፋፈል በተመለከተ ውል ተቀባይ ለውል ሰጭ /ሻጭ/ በዛሬው እለት ቀብድ ከሽያጭ ብሩን 40,000 / አርባ ሽህ/ ብር
ከፍሏል፡፡ ቀሪውል ደግሞ 200,000 / ሁለት መቶ ሽህ / ብር ስመ- ንብረት ሲዞር ሊከፈል ተስማምተናል ፡፡
4. ከዛሬ ውሉ ከተያዘበት ቀን በፊት በቤቱ ላይ የአፈር ግብር እዳ ወይም የ 3 ተኛ ወገኖች ማንኛውም በቤቱ ላይ የሚመጣ ጥያቄና
የዋስትና ሀላፊነት ከመጣ ውል ሰጭዎች ሀላፊነቱን መወጣትና ቤቱን ነፃ በማድረግ ለገዥ የማስረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡
5. የስም ማዛወሪያ በተመለከተ በጋራ ልሸፍን ነው፡፡
6. ከላይ በተስማማንው መሰረት ውል ሰጭ ስመ-ንብረት ለማዛወር እና ለመሳሰሉት ግዴታዎች ለመወጣት ነገ ዛሬ ካለ ወይም
በፀፀትም ይሁን በማናቸውም በሌላ ምክንያት ወይም ውሉን ለማፍረስ ቢሞክር እንዲሁም ውል ተቀባይ እንደ ውሉ ባይፈጽም
በፍ/ህ/ቁ. 1889 እና ተከታዮቹ ህጎች መሰረት ለወጭ እና ኪሳራ ወይም ለጋራንት መቀጫ ብር 100,000 / አንድ መቶ ሽህ/ ብር
በመክፈል ውሉ ተፈፃሚ ይሆንና ውሉም በህግ የፀና ይሆናል፡፡
7. ስለሆነም ግራ ቀኝ ይህንን ውል ሲዋዋሉና ገንዘቡን ገዥ ሲከፍል ተቀምጠን ተነቦልን ያዋዋልን ሽማግሌዎች
1 ኛ. አቶ የሱቃል ታደሰ 3 ኛ. አቶ መልኬ ሙሉ
2 ኛ. አቶ መልሰው ፍቅሬ 4 ኛ. አቶ ማለደ ወርቁ ናቸው፡፡
8. የተዋዋዮች ፊርማ
የሻጭ፡- ስም፡- ……………………………………..………
ፊርማ፡- ……………………………………..……
የገዥ፡- ስም ……………………………………….………
ፊርማ ……………………………………….....….
9. የሽማግሌዎች /የእማኞች/ ስምና ፊርማ
1. …………………………… ………….
2. …………………………… ……….….
3. …………………………… ………….
4. …………………………… ………….

ማሳሰቢያ፡- የዚህ ዉል አንድ አንድ ኮፒ ለሻጭ እና ገዥ ደርሷል፡፡ ሌላ አንድ ኮፒ ለሽማግሌዎች ተወካይ በአቶ መልሰው ፍቅሬ እጅ
እንዲቀመጥ ተመርቷል፡፡

You might also like