You are on page 1of 2

ህዳር 23/2000 ዓ.

የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ውል ስምምነት


ውል ሠጪዎች፡-
1. ወ/ሮ አየለች በቀለ /ዜግነት ኢትዮጵያዊት/
2. አቶ ገረመው ዘለቀ /ዜግነት ኢትዮጵያዊ/
አድራሻ፡- ቃቄ
ውል ተቀባይ /ገዥ/፡-
1. አቶ ጌትነት ፋንታሁን /ዜግነት ኢትዮጵያዊት/

አድራሻ ፡- የካ ወረዳ 12 ቤት ቁ. 402

እኛ ውል ሰጪዎች ስማችን እና አድራሻችን ከላይ እንደ ተጠቀሰው በዚህ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.


1679/1680/2273/2266/1731/2005 መሠረት የተደረገ የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ውል ስምምነት ፈጽሜናል፡፡

እኛ ውል ሰጪ በስማችን ተመዝግቦ የሚገኘውን ቤት በየካ ሰዴን ቀበሌ ገበረ ማህበር ልዩ ስም


ቃቄ ውስጥ የሚገኘውን የቦታ ስፋቱ 150 ካሬ ሜትር ላይ የሰፈረውን 25 ቆርቆሮ 2 ክፍል የመኖሪያ
ቤታችንን አዋሳኞች በምስራቅ አቶ መስፍን መሀመድ ይዞታ በምእራብ የወ/ሮ የሺ አሰፋ በደቡብ
መንገድ በሰሜን መንገድ የሚያዋስኑትን ቤትና ይዞታ በዛሬው እለት ለገዥው በ በብር 41,000.00
ብር አርባ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሀምሳ ብር) የሸጥን ሲሆን የገንዘቡንም አከፋፈል በተመለከተ በዚህ
ውል ደረሰኝነት በዛሬው እለት ሙሉ በብር 41,250.00 ብር አርባ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሀምሳ ብር)
ብር ከፍሎ ቤቱን እና ይዞታውን ቤቱን ከሚመለከቱ ማስረጃዎች ጋር አስረክበናል፡፡
እኔም ገዥ በሻጮች ስም ተመዝግቦ በየካ ሰዴን ቀ/ገ/ማህበር ልዩ ስም ቃቄ ውስጥ የሚገኘውን
የቦታ ስፋት 150 ካሬ ሜትር ላይ የሰፈረውን 25 ቆርቆሮ 2 ክፍል የመኖሪያ ቤታቸውን አዋሳኞች
በምስራቅ አቶ መስፍን መሀመድ ይዞታ በምእራብ የወ/ሮ የሺ አሰፋ በደቡብ መንገድ በሰሜን
መንገድ የሚያዋስኑትን ቤትና ይዞታ በዛሬው እለት ከሻጮች ላይ በብር 41,250.00 ብር አርባ አንድ
ሺህ ሁለት መቶ ሀምሳ ብር) ብር የገዛሁ ሲሆን የገንዘቡንም አከፋፈል በተመለከተ በዚህ ውል
ደረሰኝነት በዛሬው እለት 15.250.00 (አስራ አምስት ሺህ ሁለት መቶ አምሳ ብር) የተከፈለ ሲሆን ቀሪ
26.000 ብር ቀሪውን በአንድ አመት ውስጥ ብከፍል ተስማምተናል፡፡ ሙሉ በብር 41,250.00 ብር አርባ
አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሀምሳ ብር) ከፍዬ በመግዛት ቤቱን እና ይዞታወን የሚመለከቱ ማስረጃዎችን
የተረከብኩ መሆኔን በፊርማዬ አረጋግጣለሁ፡፡
ከላይ እንደተጠቀሰው በተሸጠው ቤትና ይዞታ ላይ ማንኛውም 3 ኛ ወገን ያገባኛል ባይ ወይም
ተከራካሪ ወገን ቢኖር እኛ ውል ሰጪዎች በራሳችን ኪሳራ ማንኛውንም ነገር ተከራክረን ለውል
ተቀባይ የምናስመልስ መሆናችን በፊርማችን እናረጋግጣለን፡፡
ይህንን ውል በውሉ መሰረት ከሁለቱ ወገን የማይፈጽም ቢኖር ውሉን ላከበረ ወገን ብር
10.000.00 አስር ሺ ብር/ ከፍሎ ለመንግስት 5000. (አምስት ሺህ ብር ) ከፍሎ ውሉና ገደቡ
በፍ/ሕ/ቁጥር 1889/1890 መሰረት ኪሳራ ሲከፍሉ ውሉም በፍ/ሕ/ቁ 1731 2005 /2266 መሰረት በህግ
ፊት የፀና ይሆናል እንጂ አይፈርስም፡፡
ይህንን መኖሪያ ቤት ሽያጭ ውል ስንዋዋል የነበሩ ምስክሮች

በሻጭ በኩል የነበሩ ምስክሮች


1. አቶ አፀደ ታደሰ አድራሻ፡- አዲስ አበባ የከ ክ/ከተማ ወረዳ 12
2. ወ/ሮ ሲሳይ መኮንን አድራሻ፡- አዲስ አበባ የከ ክ/ከተማ ወረዳ 12

በገዥ በኩል የነበሩት ምስክሮች


1. ቴድሮስ አገዘ አድራሻ፡- የከ ክ/ከተማ ወረዳ 12
2. ጌታባለው አሰፋ አድራሻ፡- የከ ክ/ከተማ ወረዳ 12

እኛም ምስክሮች ሁለቱ ወገኖች ከላይ በተገለፀው መሠረት ቤቱን እና ይዞታውን ሲሻሻጡ እና
የሽያጩን ገንዘብ ሲቀባበሉ ቤቱን ሲረካከቡ ማየታችንን በየፊርማችን እናረጋግጣለን፡፡
የሻጮች ስምና ፊርማ የገዥ ስምና ፊርማ
1. ወ/ሮ አየለች በቀለ ______ 1. አቶ ጌትነት ፋንታሁን
2. አቶ ገረመው ዘለቀ _______
3. ደረጄ ገረመው _________
4. ፀሐይ ገረመው _________
5. ሰለሞን ገረመው _________
6. አልማዝ ገረመው _________
የገዥ ስምና ፊርማ
1……………………………………
የሻጮች ስምና ፊርማ
1.
2.
3.
4.
5.
6.

በሻጭ በኩል የነበሩ ምስክሮች ስምና ፊርማ


1.
2.
በገዥ በኩል የነበሩ ምስክሮች ስምና ፊርማ
1.
2.

You might also like