You are on page 1of 6

ኤል ስውዲ ኬብል ማምረቻ

የካፍቴሪያ አገልግሎት የሥራ ውል ስምምነት


ይህ የካፍቴሪያ አገልግሎት ውል ከዚህ በኋላ ውል ሰጪ ተብሎ በሚጠራው ኤል ስውዲ ኬብል ማምረቻ
አድራሻ ብሾፍቱ አስተዳደር ከተማ ------------ ክ/ከተማ ኦዳ ነቤ ወረዳ የቤት ቁጥር --------- ስልክ ቁጥር፡-
011-3-87-00-88/011-3-87-03-11 ከዚህ በኋላ አሰሪ እየተባለ በሚጠራው፤

እና

ከዚህ በኋላ ውል ተቀባይ ተብሎ በሚጠራው ወ/ሮ ሳዲያ አንበሴ ሰይድ አድራሻ ሸገር ከተማ ገላን ጉዳ ክ/ከተማ
ዳለቲ ወረዳ የቤት ቁጥር-አዲስ፤ ስልክ ቁጥር 09-11-31-62-53 መካከል ዛሬ ጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓ/ም
መካከል የተደረገ የዉል ስምምነት ነዉ፡፡

አንቀፅ አንድ
1. የውሉ ዓላማ
የዚህ ውል ዓላማ ውል ተቀባይ በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው ካፍቴሪያ ለውል ሰጪ ሠራተኞች
ጥራቱንና መጠኑን የጠበቀ የተለያዩ የምግብ አይነቶችን፤ ዉሃ እና ትኩስ ነገሮችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ
ማድረግ ነው፡፡

አንቀፅ ሁለት
2. ውል ተቀባይ አገልግሎት የሚሰጥበት ጊዜ፡

2.1 ውል ተቀባይ ለውል ሰጪ ሠራተኞች ጥራቱን የጠበቀ ምሳ ያቀርባል፡፡ እንዲሁም አምሺ እና በሌሊት
ፈረቃ ለሚመደቡ ሠራተኞች በቀን አንድ ጊዜ እራት ያቀርባል፡፡
2.2 ውል ተቀባይ ለውል ሰጪ ሠራተኞች

Ordinal-number 1. የጠዋት 1:00 - ከሰዓት 9፡00 ሰዓት

Ordinal-number 2. ለቀን ፈረቃዎች ምርት ሠራተኞች ከቀኑ 12፡00 እስከ ምሽት 1፡00 ሰዓት የምሳ
መመገቢያ ሲሆን
Ordinal-number 3. ሌሎች ከለሊቱ 11፡00 እስከ ጥዋቱ 1፡00 ሰዓት የምሳ መመገቢያ ሰዓት፣ የከሰዓት
9፡00-ምሽት 3፡00 ሰዓት ለአምሽ ፈረቃዎች ከምሽት 12፡00 እስከ ምሽት 1፡00 የእራት መመገቢያ
ሰዓት፣ የምሽት 3፡00 - ጠዋት 1፡00 ሰዓት ለአዳር ፈረቃዎች ከምሽቱ 4፡00 እስከ ምሽት 5፡00 ሰዓት

እራት መመገቢያ ሰዓት፤የመደበኛ ሰዓት ሰራተኞች ከቀትር 6፡00 ሰዓት እስከ ቀትር 7፡00 የምሳ መመገቢያ
ሰዓት ሲሆን ሁሌም ለአርብ ቀን ለመደበኛ ሰራተኛ ብቻ ከቀትር 6፡00 እስከ ቀትር 8፡00 ሰዓት የምሳ
መመገቢያ ሰዓት ሲሆን ከላይ ከተጠቀሰዉ ሰዓት ዉጪ ምግብ ቤቱ ዝግ ሆኖ የምግብ ማብስያ እና የፅዳት
ሰዓት ይሆናል፡፡
አንቀጽ ሦስት
3. ውል ተቀባይ የሚሰጠው አገልግሎት ዓይነትና ዋጋ
3.1 ውል ተቀባይ ለውል ሰጪ ሠራተኞች የሚቀርበው የምግብ ዓይነት እና የዋጋ ዝርዝር እንደሚከተለው
ይሆናል፡፡

ተ.ቁ የምግቡ እና የመጠጥ ዓይነት መለኪያ ብዛት የአንዱ ዋጋ ቲኦቲ


ጨምሮ
1 ዋና ዋና ምግቦች
1.1 የፆም በየአይነት በነጠላ 1 50.00
1.2 ተጋቢኖ በነጠላ 1 50.00
1.3 ፓስታ በስጎ/በአትክልት በነጠላ 1 50.00
1.4 ማኮሮኒ በስጎ/በአትክልት በነጠላ 1 50.00
1.5 ሽሮ ፈሰስ በነጠላ 1 50.00
1.6 የጾም እንጀራ ፍርፍርበአልጫ/በቀይ በነጠላ 1 50.00
1.7 ቲማቲም ለብለብ በነጠላ 1 50.00
2 ተጨማሪ ምግቦች
2.1 እንቁላል ፍርፍር በነጠላ 1 60.00
2.2 እንቁላል ሳንድዊች በነጠላ 1 60.00
2.3 እንቁላል ስልስ በነጠላ 1 60.00
2.4 ኖርማል ፈጢራ በነጠላ 1 65.00
2.5 ሩዝ በስጎ/በአትክልት በነጠላ 1 60.00
2.6 ስፔሻል ፈጢራ በነጠላ 1 80.00
2.7 ቂንጬ በነጠላ 1 60.00
2.8 አንባሻ በቁጥር 1 10.00
2.9 ዳቦ በቁጥር 1 10.00
2.10 ቲማቲም ቁርጥ በነጠላ 1 55.00
2.11 ሰላጣ በነጠላ 1 55.00
2.12 ፉል ኖርማል በነጠላ 1 55.00
ፉል እፔሻል በነጠላ
2.13 1 60.00
3 ትኩስ ነገር
3.1 ሻይ በብርጭቆ 1 7.00
3.2 የጀበና ቡና በሲኒ 1 10.00
3.4 ግማሽ ሊትር ዉሃ (600 ሚ.ሊ) በቁጥር 1 10.00
3.5 ለስላሳ በጠርሙዝ 1 25.00

አንቀፅ አራት
4. የምግብ እና የግብዓት ስታንዳርድ
ውል ተቀባይ ለውል ሰጪ ሠራተኞች ጥራት ያለውን ምግብ ማቅረብ እንደተጠበቀ ሆኖ መጠኑ ከዚህ በታች
በዝርዝር በቀረበው መሰረት መሆን አለበት

4.1 እንጀራ -------------------------250 ግራም


4.2 ዳቦ/አንባሻ ----------------------100 ግራም
4.3 ፖስታ/መኮሮኒ/ሩዝ------------------180 ግራም ከነተከታዩ
4.4 ሻይ--------------------------------የሻይ ብርጭቆ
4.5 ቡና-------------------------------የቡና ሲኒ
4.6 በየአይነት ----------------------የመሀሉን ጨምሮ ሶስት የወጥ ዐይነት እና ከዚያ በላይ
አንቅፅ አምስት
5. የውል ተቀባይ ግዴታዎች

5.1 ውል ተቀባይ አሸናፊ በሆኑበት ዝርዝር የምግብ ዐይነቶችን በጥራት እና መጠኑን እንዲሁም ዋጋውን
ጠብቆ ለሰራተኞች መቅረብ አለበት፡፡
5.2 ውል ተቀባይ ለካፍቴርያው አገልግሎት ከውል ሰጪ የተረከባቸውን ማንኛውንም ንብረቶች በጥንቃቄ
ይይዛል፡፡ ሲበላሹም በራሱ ወጪ ይጠግናል፡፡
5.3 ውል ሰጪ የውል ተቀባይ ሠራተኞች የጤና ምርመራ እንዲያደርጉ ሲጠየቅ ለምርመራው ወደ ጤና
ተቋም መላክ አለበት፤
5.4 የካፍቴሪያ የውስጡንና የውጪውን ዕቃ ንፅህና መጠበቅ አለበት፤
5.5 ውል ተቀባይ ከተዋዋይ ወገኖች ፈቃድ ውጪ በውሉ ላይ ተማምነው ካስቀመጡት ውጪ የዋጋ፣
የአይነትና የመጠን ለውጥ ያለማድረግ
5.6 ውል ተቀባይ ለሌላ ወገን ውሉን ማስተላለፍ አይችልም፤ አሳልፎ ቢገኝ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ውሉን
ያቋርጣል፡፡
5.7 ውል ተቀባይ በምንም አይነት ሁኔታ የአልኮል መጠጦችን በካፍቴርያው ውስጥ ማስገባትም ሆነ መሸጥ
ክልክል ነው፡፡
5.8 ውል ተቀባይ የሚቀጥራቸው ሰራተኞች በስነምግባር የታነፁና ንፅህናቸውን የጠበቁ እንዲሁም ዩኒፎርም
እና የፀጉር መሸፈኛ እንዲለብሱ እና ጤንነታቸው የተሟላ የማድረግ ግዴታ አለበት፤
5.9 ውል ተቀባይ የውል ሰጪን ሠራተኞች ሰብዓዊ ክብር የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት፤
5.10 ውል ተቀባይ ለሚሰጠው የካፊቴሪያ አገልግሎት ክፍያ ሲቀበል የምግብ አገልገሎቱን የተጠቀሙ
ስራተኞች ስም ዝርዘር ማቅረብ አለበት፤
5.11 ውል ተቀባይ የምግብ ዓይነት ዋጋና የተመገቡበት ቀን የሠራተኛው መለያ ቁጥርና ደረሰኝ ቁጥር
በመመዝገብና በማስፈረም ክፍያ በሚጠይቅበት ጊዜ አብሮ ማቅረብ አለበት፡፡ ወር በገባ እስከ ቀን ሁለት
ላይ ከዋጋ መጠየቂያ ጋር በሚያያዝ ክፍያው እንዲፈፀምለት ለውል ሰጪ ማቅረብ አለበት፤
5.12 ውል ተቀባይ ለምግብ ዝግጅቱ የሚጠቀምብትን ግብዓቶች በራሱ ወጪና በራሱ ትራንስፖርት የማቅረብ
ግዴታ አለበት፤
5.13 ውል ተቀባይ ለምግብ አቅርቦት የተሰጠውን ቁሳቁስ በጥንቃቄና ከጉደለት በፀዳ መልኩ መያዝ
ይኖርበታል፡፡
5.14 ለካፍቴሪያው አገልግሎት የሚያስፈልገው የሰው ኃይል በራሱ ወጪ ቀጥሮ ማሰራት አለበት፤
5.15 ውል ተቀባይ የአገልግሎት ውሉን ለማቋረጥ ሲፈልግ የአንድ ወር ቅድመ ማስጠንቀቂያ ለውል ሰጪ
መስጠት አለበት፤
5.16 በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ከካፍቴሪያ ሥራ ጋር በተያያዘ የሚከፈል የመንግስት የውዝሆልድ ግብር ግዴታ
ኃላፊነቱ የዉል ተቀባይ ነው፡፡
5.17 ውል በማንኛውም ወገን ቢቋረጥ ውል ተቀባይ የተረከበው ዕቃ በተረከበው ሁኔታ መልሶ የማስረከብ
ወይም ውል ሰጪ በሚያቀርበው ዋጋ መሠረት የጎደለውን ወይም የተበላሸውን ዕቃ መክፈል አለበት፤
5.18 ውል ተቀባይ ከውል ሰጪ የተረከበውን ቁሳቁሶች /ከዚህ ውል ጋር አባሪ በሆነ የርክክብ ዝርዝር ሰነድ/ላይ
የተጠቀሱትን በጥንቃቄ መያዝ ይኖርበታል፡፡
5.19 ከውል ሰጪ ሠራተኞች ወይም እንግዶች ውጪ ለሌሎች የውጭ ሰዎች በካፍቴሪያው ውስጥ አገልግሎት
መስጠት አይቻልም፡፡
5.20 ዉል ሰጪ ያዘጋጀዉ የቀን ምግብ ሜኑ መሰረት ምግብ ማቅረብ ግዴታ አለበት፤
5.21 ዉል ተቀባይ የድርጅቱ ሰራተኞች ከመመገቢያ ሰዓት ዉጪ ምግብ ቤት እንዳይቀመጡ ይቆጣጣራል፡፡
5.22 ለምግብ አገልግሎት የሚጠቀሙት ምግብ ነክ ነገሮች በሙሉ ንፁህ፤ የመጠቀሚያ ጊዚያቸዉ ያላለፈና
ለሰዉ ጤንነት ጎጂ ያልሆነ መሆናቸዉን የማረጋገጥ ግዴታ አለባጨዉ፡፡
5.23 የምግብ ዘይትን በተመለከተ የማይረጋ ፈሳሽ የሆነና ለምግብ መስሪያ አገልግሎት የተመረጠና የመጠቀሚ
ጊዜዉ ያላለፈ መሆኑን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸዉ፡፡
አንቅፅ ስድስት
6. የውል ተቀባይ መብት
6.1 ለተሰጠው ምግብ የአገልግሎት ክፍያ አገልግሎት ከተሰጠበት ወር ቀጥሎ ባሉት አምስት የሥራ ቀናት
ውስጥ ክፍያ የማግኝት መብት፡፡
6.2 ውል ሰጪ ለካፍቴሪያው አገልግሎት የሚያስፈልገውን የካፍቴሪያውን መመገቢያ ጠረጴዛ እና ወንበር
የኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ውኃና የካፍቴሪያ ቤት መጠቀመ እንዲችሉ ይቀርባል፡፡
6.3 ውል ተቀባይ በካፍቴሪያ አገልገሎት አስጣጡ ላይ በውል ሰጪ ስህተት ለሚያጋጥሙ ችግሮች ውል ሰጪ
ጠይቆ የመረዳት መብት አለው፡፡
6.4 ውል ሰጪ ባዘጋጃችው ኮፖኖች ዋጋ መሰራት ክፍያ የመፈጸም ግዴታ አለበት ከኩፖኑ ዋጋ በላይ
ለሚያወጡ ምግቦች ልዩነቱን ውል ተቀባይ ከሰራተኞች በቅጥታ መቀበል አለበት፡፡
6.5 ዉል ሰጪ ዉል ተቀባይ ያቀረበዉ ምግብ የቀን ምግብ ሜኑ መሰረት የቀረበ መሆኑን ይቆጣጣራል፤
አንቀፅ ሰባት
7. የውል ሰጪ ግዴታ
7.1 ለካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውለውን የኤሌክትሪክና የውኃ እንዲሁም የጥበቃ አገልግሎት ያለክፍያ
ማቅረብ፡፡
7.2 የተመጋቢ ሠራተኞች ስም ዝርዝርና የመመገቢያ ኩፖን ውል ሰጪ ለውል ተቀባይ ሠራተኞች በሚገቡበት
ጊዜ እንዲያቀርቡ አዘጋጅቶ ሥራ ላይ ማዋል አለባቸው፡፡
7.3 የካፍቴሪያውን አገልገሎት እንዲከታተሉ የተመደቡ ሥራ ኃላፊዎች በካፍቴሪያው ውስጥ ህግና ደንብ
እንዲከበር የመከታተል ኃላፊነት አለባቸው፡፡
7.4 ውል ሰጪ ውሉን ለማቋረጥ ሲፈልግ የአንድ ወር ቅድመ ማስጠንቀቂያ ለውል ተቀባይ መስጠት ግዴታ
አለበት፡፡
አንቀፅ ስምንት
8. የውል ሰጪ መብት
8.1 በካፍቴሪያው ውስጥ ለውል ሰጪ ሠራተኞች የሚያቀርበው ምግብ ጥራት፣ መጠን፣ዓይነትና ዋጋ
የመቆጣጣርና የማስተካከያ እርምጃ የመውሰድ መብት አለበት፡፡
8.2 የካፍቴሪያውን ንፅህና የመቆጣጠርና የካፍቴሪያው ሠራተኞች በየጊዜው የጤና ምርመራ ማድረጋቸውን
መከታተል፡፡
8.3 የውል ተቀባይ አገልግሎት አሰጣጥ ጥሩ ካልሆነ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ውሉን የማቋረጥ ኃላፊነት አለው፡፡
8.4 ውል ሲቋረጥ ያስረከበውን ዕቃ በነበርበት ሁኔታ መልሶ የመረከብ፣ ተበላሽቶ የጠፋ የተሰበረ ወዘተ ዕቃ ካለበ
ዓይነት ውይም ዋጋቸውን የማስከፈል መብት አለው፡፡
8.5 ውል ሰጪ በየጊዜው በድርጅቱ ባለሞያዎች ለሠራተኞች የሚያቀርበው የምግብ ጥራት መጠን ክትትል
የማድረግ መብት አለው፡፡
አንቀፅ ዘጠኝ
9. ውሉ ስለማሻሻል
9.1 ይህ ውል በሁለቱ ወገኖች ስምምነት ውይም አንደኛው ወገን ውሉ እንዲሻሻል ጠይቆ ሁለተኛው ወገን
ሲስማማ ሊሻሻል ይችላል፡፡

አንቀፅ አስር
10. አለመግባባት ስለመፍታት፡
10.1 በዚሁ ውል አፈፃፀም ሂደት በሁለቱ ወገኖች መካከል አለመግባባት ሲፈጠር ሁለቱ ወገኖች
ተቀራርበው አለመግባባት በውይይት ለመፍታት ይፈጥራሉ፡፡ ሆኖም በውይይት ለመፍታት ካልቻለ
በኢትዮጵያ ህግ መሠረት ለፍትህ አካል ማቅረብ ይችላል፡፡
አንቀፅ አስራ አንድ
11. ውሉ የሚፀናበት ጊዜ
11.1 ይህ ውል በሁለቱም ወገኖች መካከል ከተፈረመበት ከጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ለአንድ ዓመት
የፀና ይሆናል፡፡

ውል ሰጪ ውል ተቀባይ

ስም፡-------------------------------- ስም፡-----------------------------------
ፊርማ፡------------------------------ ፊርማ---------------------------------

ቀን፡--------------------------------- ቀን፡---------------------------------

ውሉ ሲፈረም የነበሩ ምስክሮች

1. ስም------------------------------------ ፊርማ-------------------------------

2. ስም፡--------------------------------- ፊርማ ------------------------------

3. ስም---------------------------------- ፊርማ-------------------------------

You might also like