You are on page 1of 30

የእንስሳት መድኃኒትና መኖ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን

Veterinary Drug and Animal Feed Administration and Control


Authority

በአዋጅ ቁጥር 728/2004 ላይ ያተኮረ ሥልጠና

በሕግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት


ለእንስሳት መኖ ባለሙያዎች የተዘጋጀ

1
የእንስሳት መኖ አስተዳደርና ቁጥጥርን የተመለከቱ
የሕግ ድንጋጌዎች
 የእንስሳት መድኃኒትና መኖ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር
728/2004
 የእንስሳት መድኃኒት እና መኖ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣንን
ለማÌÌM የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 272/2005
 የመኖ አምራች፣ አስመጪ፣ ጅምላ አከፋፋይና ላኪ ድርጅቶች
የምዝገባና የሥራ ፈቃድ መስጫ አሠራር መመሪያ
 ሌሎች ተዛማጅ ሕጎች

2
የገለጻው ይዘት
 ባለስልጣን መ/ቤቱ የተቋቋመበትን አላማ

 የሕግ ትርጉም የተሠጠባቸው ቃላት

 የአዋጁ የተፈጻሚነት ወሰን

 ለባለስልጣኑ በአዋጁ መሰረት የተሰጡትን ስልጣንና ተግባሮች

 ከአዋጁ ጋር ተያዥነት ስላላቸው ሌሎች ሕጎች

 የአዋጁን ደንቦችና መመሪያዎችን እንዲሁም ሌሎች ሕጎችን


ተላልፎ መገኘት ስለሚያስከትለው አስተዳደራዊ እርምጃዎች እና
3
የወንጀል ተጠያቂነት
የእንስሳት መድኃኒትና መኖ አስተዳደርና ቁጥጥር
ባለስልጣን ለምን ዓላማ ተቋቋመ?

የእንስሳት ምርትና ምርታማነት


እንዲያድግና ጤናማ የእንስሳት ምርት
ለተጠቃሚው ሕብረተሰብ እንዲቀርብ
ማስቻል ነው፡፡ (ደንብ 272 (2))

4
yxê° አላማ
1. ደህንነቱ ጥራቱ እንዲሁም ፈዋሽነቱ የተጠበቀ የእንስሳት መድሃኒትና
መኖ እንዲሁም የመኖ ተጨማሪ ንጥረ-ነገር አቅርቦትን አጠቃቀምን
እንዲሁም ቁጥጥርን በማሻሻል የእንስሳት ሃብት ልማትና ጤንነት
አጠባበቅን በማሳደግ በዘርፉ ያለንን ምርታማነትን ማሳደግ

2. የመኖ አስተዳደርና ቁጥጥርን በማጠናከር የመኖ ልማቱን እንደስትሪና


የእንስሳት እርባታውን በማሻሻል የህዝብን ጤንነት መጠበቅ

3. የእንስሳት መድሃኒት መኖ እንዲሁም የመኖ ተጨማሪ ንጥረ ነገሮች


ህገ-ወጥ ምርት ስርጭትና አጠቃቀምን መከላከልና መቆጣጠር

4. ከላይ የተጠቀሱትን አላማዎች ለማሳካት የቁጥጥር ስርአት በመዘርጋት


በሃገሪቱ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን የእንስሳት ጤና አጠባበቅ መርሃ ግብር
በተሻለ ሁኔታ ውጤታማ በማድረግ በእንስሳትና በእንስሳት ውጤቶች
አለም አቀፍ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ ሆኖ መገኘት ነው፡፡ 5
ትር¹ሜ
በአዋጁ የተጠቀሱና ትርጉም የተሰጣቸው ቃላት በጥቂቱ፡-
"እንስሳ": ማለት ለማዳና የዱር እንስሳት አእዋፍን የውሃ ውስጥ እንስሳትን ንብንና የሃር
ትልን ያጠቃልላል፡፡ አንቀጽ 2(1)
"መኖ" ማለት ለንግድ አላማ የተዘጋጀ ወይም የተመረተ የእንስሳት ምግብ ማለት ነው፡፡ (አንቀጽ
2(10)
"የመኖ ንግድ" ማለት ደግሞ መኖን ለንግድ ማሸግ ፤ ከውጪ ማስመጣት ወደ ውጪ መላክ
፤በጅምላ ወይም በችርቻሮ መሸጥን እንዲሁም የመኖ ጥራት ምርመራ ላቦራቶሪ
አገልግሎትን መስጠት እና በንግድ ወኪል ሆኖ መስራትን ይጨምራል፡፡ አንቀጽ 2(12)
"የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት" ማለት ደግሞ ባለስልጣኑ ያወጣውን መስፈርት
በማሟላት በእንስሳት መኖ ንግድ ለመሰማራት ብቁ መሆንን የሚያረጋግጥ
በባለስልጣኑ ወይም ሥልጣን በተሰጠው የክልል መንግስት የሚሰጥ ምስክር ወረቀት
ነው፡፡ አንቀጽ 2(13)
“የእንስሳት መኖ ባለሙያ”: ማለት ከታወቀ ዩኒቨርሲቲ ወይም ተቋም በእንስሳት ሳይንስ ወይም
6
በእንስሳት መኖና ግጦሽ በዲፕሎማ ወይም በመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ከዚያ በላይ የተመረቀና
በተጨማሪ የመኖና የእንስሳት ስነምግብ ስልጠና የወሰደ ነው (አንቀጽ2(26) ፤
"የሙያ ፍቃድ’’ ማለት የእንስሳት መኖ

ባለሙያ በሙያው መስራት እንዲችል

በባለስልጣኑ ወይም ስልጣን በተሰጠው

የክልል መንግስት የሚሰጥ የምስክር

ወረቀት ነው፡፡ አንቀጽ 2(23)


7
የተፈጻሚነት ወሠን
በአንቀጽ 3 በንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት አዋጁ በሀገሪቱ በሚደረግ የእንስሳት መኖ የቁጥጥር

ስራዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ (በመኖውም ሆነ በባለሙያው ላይ በሚደረጉ የቁጥጥር

ስራዎች)
በአንቀጽ 3 በንኡስ አንቀጽ 2 መሰረት በፌደራል ደረጃ የአዋጁ ተፈጻሚነት የሚከተሉትን

በሚመለከት ነው፡-

1. የእንስሳት መኖና ባለሙያዎችን ደረጃ ማውጣት፣

2. ክልል ተሻጋሪ የእንስሳት መኖ ማምረትን፤ ማከፋፈልን ፤ ማከማቸትን ፤

ማስተዋወቅንንና የጥራት ቁጥጥር ላቦራቶሪ አገልግሎት መስጠትን ፤ መኖ መላክንና

ከውጪ ማስገባትን መቆጣጠር


በአንቀጽ 3 በንኡስ አንቀጽ 3 መሰረት በአዋጁ በአንቀጽ 20 ለባለስልጣኑ ከተሰጡት ስልጣንና

ተግባራት ውጪ ያሉት የቁጥጥር ተግባራት በክልል መንግስታት ተቆጣጣሪ አካላት የሚፈጸሙ8

ይሆናሉ፡፡
ክፍል ሶስት
የእንስሳት መኖ አስተዳደርና ቁጥጥር
አንቀጽ ርዕስ
4-13……………………………………… (ክፍል ሁለት) የመድኃኒት
አስተዳደርና ቁጥጥር
14 ………………………………………………..የመኖ ጥራት ደረጃዎች
15 ………………………………………………..የመኖ ደህንነት ቁጥጥር
16 ………………………………………………..የመኖ ማሸጊያና ገላጭ ጽሑፍ
17 ………………………………………………..ስለ መረጃ አያያዛ
18 ………………………………………………..መኖ ወደ ሃገር ውስጥ ስለማስገባትና ወደ
ውጪ ሃገር ስለመላክ
19 ………………………………………………..የመኖ ንግድ
አንቀጽ 14፡- የመኖ ጥራት ደረጃዎች

ማንኛውም መኖ ወይም የመኖ


ተጨማሪ ነጥረ ነገር ሥልጣን
የተሰጠው አካል ያወጣውን
ወይም የተቀበለውን የጥራት
ደረጃዎችን የሚያሟላ መሆኑ
አግባብ ባለው አካል
ካልተረጋገጠ በስተቀር 10
አንቀጽ 15፡- የመኖ ደህንነት ቁጥጥር

ማንኛውም መኖ፣ የመኖ ጥሬ ዕቃ ወይም የመኖ


ተጨማሪ ንጥረ ነገር ብክለትንና ብልሽትን
በሚከላከል አሰራር መመረት፣ መከማቸትና
መጓጓዝ አለበት፡፡

11
አንቀጽ 16፡- የመኖ ማሸጊያና ገላጭ ጽሑፍ

1/ ማንኛውም የመኖ አምራች፣ አስመጪ፣ አከፋፋይ


ወይም የእንስሳት መኖ መሸጫ መኖው በአግባቡ
ካልታሸገና ገላጭ ጽሑፍ ካልተደረገበት በስተቀር ለገበያ
ሊያቀርበው ወይም በማንኛውም አኳኋን ሊያሰራጨው
አይችልም፡፡

2/ የማንኛውም መኖ ገላጭ ጽሑፍ በአማርኛ ወይም


በእንግሊዝኛ ቋንቋ በጉልህ የተጻፈ ሊሆን ይገባል፡፡ 12
አንቀጽ 17፡- ስለ መረጃ አያያዝ

1/ የመኖ ግብዓቶችን፣ የማምረት ሂደትና ስር ጭትን


የሚያሳዩ መረጃዎች ተመዝግበውና በቀላሉ ተደራሽ
እንዲሆኑ ተደርገው መያዝ አለባቸው፡፡

2/ መረጃዎቹ የምርቱ ጐጂ ጐን ሲከሰት የጥሬ ግብዓቶቹን


አቅራቢም ሆነ ያለቀለትን ምርት ተጠቃሚ መለየት
የሚያስችሉ ሆነው መደራጀት አለባቸው፡፡
13
አንቀጽ 18፡- ስለ መኖ ወደ ሃገር ውስጥ
ስለማስገባትና ወደ ውጪ ሃገር ስለመላክ

1/ ማንኛውም ወደ አገር ውስጥ የሚገባ የመኖ ምርት


በላኪው አገር የሚመለከተው አካል የተረጋገጠ የጥራት
ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያለው መሆን አለበት፡፡

2/ ማንኛውም ወደ ውጭ አገር የሚላክ መኖ በባለሥልጣኑ


የተሰጠ የጥራት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያለው
መሆን አለበት፡፡
14
አንቀጽ 19፡- የመኖ ንግድ

ማንኛውም ሰው አግባብ ባለው አካል የተሰጠ የብቃት


ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሳይኖረው በመኖ ንግድ
ሊሰማራ አይችልም፡፡

15
አንቀጽ 20 የባለስልጣኑ ስልጣንና ተግባራት
1. የእንስሳት መኖ ጥራትና ደህንነትን በተመለከተ ደረጃ አውጥቶ ስልጣን ለተሰጠው አካል
ያቀርባል (ስልጣን የተሰጠው አካል በአዋጁ አንቀጽ 2(31) መሰረት የደረጃዎች ኤጀንሲ
ነው) ፤

2. በእንስሳት መኖ ንግድ ለሚሰማሩ ሰዎች የብቃት መመዘኛ ያዘጋጃል ፤

3. ለክልል ተሻጋሪ የእንስሳት መኖ አምራቾች ፤ ላኪዎች አስመጪዎች ፤ አከፋፋዮች


፤ አስተዋዋቂዎችና የጥራት ቁጥጥር ላቦራቶሪ አገልግሎት ሰጪዎች የብቃት
ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ይሰጣል ያግዳል ይሰርዛል፤

4. የእንስሳት መኖ ዘርፉን ለማስፋፋት በሃገር ውስጥና ውጪ በሚደረጉ ሳይንሳዊ


ግኝቶችን በመከታተል በሃገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር እንዲጣጣሙ ያደርጋል፡፡ የእንስሳት
መኖን በተመለከተ የፖሊሲ ሃሳቦችን ያመነጫል ረቂቅ ህጎችን ያዘጋጃል ሲጸድቁም
16
ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል፡፡
የቀጠለ
5. አስፈላጊ የሆኑ የጥራት ምርመራ ላቦራቶሪዎችን ያደራጃል፡፡

6. ስለ እንስሳት መኖ የመረጃ ምንጭ ሆኖ ያገለግላለል፡፡

7. በእንስሳት መኖ አያያዝና አጠቃቀምን አስመልክቶ

ለሚመለከታቸው አካላት ስልጠና ይሰጣል፡፡

8. ሀገር ውስጥ የሚመረቱም ሆነ ከውጪ ሀገር የሚመጡ

የእንስሳት መኖ ተጨማሪ ንጥረ ነገሮችን ገምግሞ


17
ይመዘግባል፣ ምዝገባውን ያድሳል፣ ያግዳል፣ ይሰርዛል፡፡
በሌሎች አንቀጾች ላይ የተዘረዘሩ የባለስልጣኑ ስልጣንና
ተግባራት፡
1. አስተዳደራዊ እርምጃ የመውሰድ ፡- (አንቀጽ 24)

 አዋጁን ደንቡን ወይም መመሪያዎችን የጣሰ ሰው የሙያ ፍቃድ ወይም


የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀትን ማገድን መሰረዝን የሚያካትት
እርምጃ ነው (ከተሰጣቸው ፍቃድ ውጪ የሚሰሩትን፣ ፍቃድ
የማያሣድሱትን እና የመሳሰሉት ላይ የሚወሰድ እርምጃ ነው፡፡
 ለአገልግሎት ብቁ ያልሆኑ መኖንና የመኖ ተጨማሪ ንጥረ ነገሮችን በባለቤቱ
ወጪ እንዲወገድ የማድረግ
 የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ሳይኖረው በመኖ ንግድ የተሰማራን
18

ሰው የንግድ ተቋም በማሸግ አስፈላጊውን እርምጃ የመውሰድ


3. መመሪያዎችን የማውጣት (አንቀጽ 28(2))
በአዋጁ መሰረት አዋጁንና ደንቦችን ለማስፈጸም የሚውሉ
መመሪያዎችን የማውጣት
 በደንብ ቁጥር 272/2005 መሠረት ከተሰጡት ስልጣንና ተግባራት መካከል
 አንቀጽ 6 ንኡስ አንቀጽ 1(ለ) በመንግስት በሚወሰን ተመን መሠረት
የአገልግሎት ክፍያ ይሰበስባል
 አንቀጽ 6 ንኡስ አንቀጽ 1(መ) ዓላማውን ለማስፈጸም የሚረዳ ሌሎች
ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፡፡
አንቀጽ 6 ንኡስ አንቀጽ 2 አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ከተግባራቱ በከፊል
ለክልል አካላት ውክልና ሊሰጥ ይችላል፡፡ 19
ስለተቆጣጣሪዎች ፡- (አንቀጽ 21)
1/ ባለስልጣኑ ወይም የእንስሳት መድኃኒትና መኖ አስተዳደርና ቁጥጥር ተግባራትን

የማከናወን ሥልጣን የተሰጠው የክልል መንግስት አካል ይህን አዋጅና አዋጁን

ለማስፈጸም የሚወጡ ደንቦችና መመሪያዎች መከበራቸውን ለማረጋገጥ

የእንስሳት መኖ ተቆጣጣሪዎችን ይመድባሉ፡፡

2/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ መሠረት የተመደበ ተቆጣጣሪ የሚከተለው

ሥልጣንና ተግባር ይኖረዋል፡-

ሀ/ የእንስሳት መኖ ንግድ ሥራ ወደሚካሄድበት ወይም የእንስሳት መኖ ወደ

ተከማቸበት ግቢ በሥራ ሰዓት በመግባት ወይም የእንስሳት መኖ የጫነን

ማጓጓዣ በማስቆም የቁጥጥር ተግባር የማከናወን፣


20
ለ/ ከእንስሳት መኖ ሥራ ጋር የተዛመደ ማንኛውንም መዛግብት፣ ሰነድ፣ማዘዣና

ኮምፒውተር መመልከትና አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ኮፒ ተደርጎ እንዲሰጠው የማድረግ፤

ሐ/ ባለሥልጣኑ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ከእንስሳት መኖዎች ወይም የመኖ

ተጨማሪ ንጥረ ነገሮች ላይ ናሙናዎችን የመውሰድ፤

መ/ የተከለሱ፣ የተበላሹ፣ በማስመሰል የቀረቡ፣ የተበከሉ ወይም በማናቸውም ሌላ

ምክንያት በተጠቃሚዎች ላይ ጉዳት ያደርሳሉ ተብለው በተጠረጠሩ መኖዎች

ወይም የመኖ ተጨማሪ ንጥረ ነገሮች ላይ የጥራት ምርመራ እንዲካሄድ ለማድረግና

ውጤቱ እስኪታወቅ ድረስ ተለይተው እንዲቆዩ የማዘዝ፤

ሠ/ የእንስሳት መኖዎች ወይም የመኖ ተጨማሪ ንጥረ ነገሮች የአገልግሎት ዘመናቸው


21
ሲያበቃ ወይም በዚህ አዋጅ መሠረት ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ሲወሰን በተገቢው መንገድ

እንዲወገዱ መደረጋቸውን የመቆጣጠር፡፡


ክፍል አምስት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
አንቀጽ ርዕስ
22 ………………………………………………..ስለ እንስሳት መኖ አወጋገድና የንግድ ስራ ስለማቆም
23 ………………………………………………..ስለ መኖ ንግድ ማስታወቂያና መረጃ ስለመስጠት
24 ………………………………………………..አስተዳደራዊ እርምጃዎች
25 ………………………………………………..ስለ ቅሬታ አቀራረብ
 በአዋጁ የተከለከሉ ድርጊቶችና የሚያስከትሉት ሃላፊነት
(አንቀጽ 26)
 በወንጀል ህጉ የበለጠ ካላስቀጣ በስተቀር
1 - በአንቀጽ 21 መሰረት የቁጥጥር ስራን እንዲያከናውን የተመደበ ሰራተኛ
ላይ ሁከት መፍጠር --
(ከ6ወር በማያንስ ቀላል እስራት እና እስከ 10 ሽህ ብር)

2 - ብቃት ማረጋገጫን የሰጠውን አካል ሳያስፈቅዱ የብቃት ማረጋገጫውን


ለሌላ ሰው አሳልፎ መስጠት

(ከ1አመት እስከ 3 አመት ቀላል እስራት እና ከ5-20 ሺህ ብር ቅጣት)

3 - መኖ አምራች፤ አከፋፋይ ወይም አስመጪ ሆኖ ፍቃድ ለሌለው ሰው


ማከፋፈል
23
(ከ2-5 አመት እስራት እና ከ 10ሺህ - 20 ሺህ ብር ቅጣት)
4 -የጅምላ /ችርቻሮ ንግድ ላይ ተሰማርቶ የብቃት ማረጋገጫ ከሌለው ሰው ላይ መኖ መግዛት --

(ከ2-5 አመት ጽኑ እስራት እና ከ10 ሺህ -20 ሺህ የገንዘብ ቅጣት)


5 -መኖን አስመስሎ ማቅረብ /መከለሰ/ደረጃውንያ ልጠበቀ/ የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበትን ለገበያ ማቅረብ

(ከ10-20 አመት ጽኑ እስራት እና ከ20ሺህ-50 ሺህ የገንዘብ ቅጣት)

(ማስመሰል በአንቀጽ 2(16) መሰረት የእውነተኛ ምርት ማሸጊያ የንግድ ስምና የመሳሰሉትን በመጠቀም እውነተኛ

ምርት እንደሆነ አስመስሎ ማቅረብ በሚል ትርጉም የተሰጠው ሲሆን መከለስ ደግሞ በአንቀጽ 2(17) መሰረት

ከተሰራበት ንጥረ ነገር ውጪ መደባለቅ የሚል ትርጉም ተሰጥቶታል፡፡

6 -ከራሳቸው ፍጃታ የተረፈውን መኖ ከሚሸጡ አነስተኛ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች በስተቀር የብቃት

ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ሳይኖር በመኖ ንግድ መሰማራት

(ከአምስት ዓመት እስከ ሰባት ዓመት ጽኑ እስራት እና ከ20ሺህ-50 ሺህ የገንዘብ ቅጣት ( አንቀጽ

19)

7 - የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ሳይኖር በመኖ ንግድ መሰማራት (አንቀጽ12)

(ከ5 አመት--7 አመት ጽኑ እስራት እና ከ20 ሺህ - 50 ሺህ የገንዘብ መቀጮ)


24
8 - ሌሎች በአዋጁ የተመለከቱትን ድንጋጊዎች መጣስ እሰከ 2 አመት ቀላል እስራትና እሰከ ብር 10ሺህ ቅጣት

ይጠብቀዋል፡፡ ( አንቀጽ 26(6))


እነዚህም

8.1 (አንቀጽ 15 (1) የመኖ አቀማመጥ ፤ አያያዝ ፤ አከመቻቸት መኖውን

ለብክለት የሚያጋልጥ መሆን የለበትም፡፡

8.2 (አንቀጽ 9 እና 16) የእንስሳት መኖ በትክክል ሳይታሸግና ተገቢው

ገላጭ ጽሁፍ ሳይደረግበት ለገበያ መቅረብ የለበትም፡፡

8.3 (አንቀጽ 14) ማንኛውም መኖ ወይም የመኖ ተጨማሪ ነጥረ ነገር

ሥልጣን የተሰጠው አካል ያወጣውን ወይም የተቀበለውን የጥራት

ደረጃዎችን የሚያሟላ መሆኑ አግባብ ባለው አካል ካልተረጋገጠ

በስተቀር ለአገልግሎት ሊውል አይችልም፡፡


25
የቀጠለ
8.4 (አንቀጽ18) ማንኛውም ወደ ውጭ አገር የሚላክ መኖ

በባለሥልጣኑ የተሰጠ የጥራት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያለው

መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም ማንኛውም ወደ አገር ውስጥ

የሚገባ የመኖ ምርት በላኪው አገር የሚመለከተው አካል የተረጋገጠ

የጥራት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያለው መሆን አለበት፡፡

 እነዚህን ከላይ ያሉትን ድንጋጌዎች የጣሰ ቀደም ብለን

የጠቀስነው ሀላፊነት ይጠብቀዋል፡፡


26
የእንስሳት መድኃኒትና መኖ አስተዳደርና ቁጥጥር ስራ
እንዲያከናውን ኃላፊነት የተሰጠው ሰራተኛ በወንጀል ተጠያቂ
ስለሚሆንባቸው ሁኔታዎች (አንቀጽ 26(7) )
- አዋጁ ወይም መመሪያዎች ካስቀመጡት በሚቃረን መልኩ ማባበያ
በመቀበልም ሆነ በማናቸውም መንገድ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት
ወይም የሙያ ስራ ፈቃድ መስጠት ማደስ ወይም እንዲታደስ ማድረግ
እንዲሁም
- መድሃኒት መኖ፣ የመኖ ተጨማሪ ንጥረ- ነገር የጥራት ደረጃ ሳያሟላ
አገልግሎት ላይ እንዲውል መፍቀድ /እንዲፈቀድ ማድረግ ከ10አመት -15 አመት
ፅኑ እስራትና በብር 30ሺህ-50ሺህ ያስቀጣል፡፡ ይህም ቅጣት ማባበያውን
በሰጠው ሰው ላይም ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

- ከዚህ በላይ የገለጸውን ጥፋት በመፈጸም ተግባር ላይ የተሳተፈ


 ጉዳዩ ወደ ፍ/ቤት ከመቅረቡ በፊት ስለተፈጸመው ጥፋትና ስለ ተባባሪዎች በቂ መረጃ27ከሰጠ

የፍትህ ሚ/ር ወይም ፀረ ሙስና ኮሚሽን ክስ እንዳይመሰረትበት ሊያደርግ ይችላል ፡፡


ተያያዥነት ያላቸው ሕግጋት
 - በ1996 ዓ.ም የተሸሻለው የኢ.ፌ.Ä!.ሪ የወንጀል ሕግ ግጦሽ መበከልን
ሌሎችንም ከእስሳት ጤና ጉዳት ጋር የተያያዙ ድርጊቶችን በአንቀጽ 518
መሰረት ወንጀል አድርጓል፡፡

አንቀጽ 518
ግጦሽን መበከል
 የእንስሳት ሕይወትን ወይም ጤና አደጋ ላይ ለመጣል
 መርዛማ ነገሮችን በግጦሽ ቦታ ያሰራጨ ፣
 በጎጂ በሆኑ ነገሮች ግጦሽና መስኩን የበከለ

- በመቀጮ ወይም በቀላል በእስራት ይቀጣል፡፡ ነገሩ ከበድ ያለ ከሆነ ከ 7


ዓመት በማይበልጥ እስራት ይቀጣል፡፡
28
- ወንጀሉየተፈጸመው በቸልተኝነት እንደሆነ ቅጣቱ ከስድስት ወር
በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም መቀጮ ይሆናል፡፡
ሌሎች ተዛማጅ ሕግጋት
- የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 ፣ ይህም
…… ችርቻሮ፣ ጅምላ ንግድ፣ ማምረት እና ሌሎች በኛ አዋጅ
ትርጉም ያልተጣቸውን ከንግድ ጋር የተያያዙ ቃላትን ትርጓሜን
ለማጣቀስ ይረዳናል፡፡

- የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006

29
ጥያቄ

You might also like