You are on page 1of 56

የሽመና የስልጠና ማንወል

ሒፋም ፒፒ ከረጢት ፋብሪካ

በጀማል ኢብራሂም
ግንቦት 2012
ምዕራፍ አንድ፡- አጠቃላይ ግንዛቤ

መግቢያ
 ስለ ስልጠና ያለን ግንዛቤና በስራ ላይ የሚገኙ ሰራተኞች/ተከታዮች ስልጠናን
የሚተገብሩባቸው ዘዴዎች ሲነፃፀሩ ትልቅ የግንዛቤ ችግር እንዳለ ይታያል፡፡
በየጊዜው እያደገና እየተለወጠ በመሔድ ላይ ባለው ዓለማችን ውስጥ በአንድ ወቅት
በነበረን ዕውቅትና ግንዛቤ አብረን እንጓዝ ብንል የማይቻለን ይሆናል፡፡
በተለዋዋጭ ሁኔታ ውስጥ የምንገኝ በመሆኑ ዕውቀታችንና ችሎታችንም በየጊዜው
እየዳበረ ተለዋዋጩን ሁኔታ ለማስተናገድ በሚያስችል ደረጃ ላይ እንዲገኝ የግድ
ይላል፡፡
መግቢያ
• በዘመናችን ያለውን የስራ ሁኔታ ለመተግበር ከስሜትና ከፍላጐት ባሻገር
በሥራ ልምድ፣ በትምህርትና ሥልጠና ራሳችንን ማሻሻል አማራጭ የሌለው
ሆኖ ተገኝቷል፡፡ የዚህ ስልጠና ዓላማ በተለያዩ የስራ ደረጃዎች ላይ የሚገኙ
ሰራተኞች የአሰራር ክህሎታቸውን በማዳበር፣ ተግባርና ሓላፊነታቸውን
በብቃት ለመወጣትና አስቸጋሪ ሁኔታዎችን በመጋፈጥ እንደየክስተቶቹ
ባሕርይ የቅደም ተከተል አሠራር በመዘርጋት ውጤታማ የሚሆኑበትንና
ሀላፊነታቸውን የሚወጡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የሚያስችል ግንዛቤን
መፍጠር ነው::
አላማዎች

 ሠልጣኞች የአሰራር መሠረቶችን እና የስራ ቁልፍ ተግባሮችን ይረዳሉ፡፡

 ሠልጣኞች የተከታይነት ጽንሰ ዐሳቦችን፣ የተከታይነት ማዕቀፎችን እና

ስለ ተኪነት በቂ ግንዛቤ ያገኛሉ፡፡

 ሠልጣኞች በእውቀት ላይ በተመሰረተ የአሰራር ስርአት በፍጥነት

ራሳቸውንና የሚሰሩበትን ድርጅት ውጤታማ ለማድረግ ነው፡፡


ሀላፊዎችን ለምን እንከተላለን?

 ሃላፊዎችን የምንከተለው ስለሚያግባቡንና ስለሚያሳምኑን፣ ዐሳባቸውንና


አመራራቸውን በፈቃደኝነት ስለምንቀበል ነው፡፡
 ሀላፊዎችን የምንከተለው በድርጅቱ ላይ ባላቸው የሥልጠን ውክልና መሠረት
የመታዘዝ ግዴታ ስላለብን ነው፡፡
 በሰራተኞች መካከል የጋራ የሆነ እምነት እንዲዳብርና የድርጅትን ራዕይ እውን
ለማድረግ የተግባቦት ስርአት እንድፈጠር ከፍተኛ ሚና ስለሚሰጣቸው ነው፡፡
 አጠቃላይ ከስልጠና በኃላ የምናሳየውን የስራ እንቅስቃሴ በተገቢው ሁኔታ
ስለሚከታተሉን ነው፡፡
የተከታዮች/የሰልጣኞች/ ዝግጁነትና ፈቃደኝነት መሠረት ያደረገ ስልጠና

 በዚህ ጽንሰ ዐሳብ መሠረት ተከታዮች/ስልጣኞች/ እንደ ሥራና


እንደ ሥነ ልቦና የብስለት ደረጃቸው በአራት ዐይነት የዝግጁነት
ደረጃ ስልጠና ወስደው ወደ ስራ ይመደባሉ፡፡ ይህም
ያስፈለገበት ምክንያት ማንኛውም ሰራተኛ ስራ ከመጀመሩ በፊት
ለሚሰራውን ስራ ተጨማሪ እውቀትና የስነ ልቦና ግንባታ
ይሰጣል፣ እንዲሁም ሰራተኞች ያላቸውን የስራ ፍላጎት፣ችሎታ
እና ፍቃደኝነት ለመለየት ይጠቅማል፡፡
የቀጠለ………
ከፍተኛ መካከለኛ ዝቅተኛ

ችሎታም ያለው ችሎታ ያለው ችሎታ የሌለው ችሎታም


ፈቃደኛም ግን ፈቃደኛ ግን ፈቃደኛ ፍቃደኝነትም
የሆነ ያልሆነ የሆነ የሌለው
በሰንጠረዡ መሠረት እንደ ተከታዮቹ /ሰልጣኞች/ ዝግጁነት የሚሰጡት
የአሰራር ዘይቤዎች የሚከተሉት ናቸው ፣

 የተከታዮች /ሰልጣኞች/ የሥራ ዕውቀትና ችሎታም ሆነ ለሥራው ያላቸው

ፈቃደኝነት ዝቅተኛ ሲሆን የአመራር ዘይቤው በማዘዝ፣ በመንገርና በቅርብ

በመከታተል ላይ ያዘነበለ ይሆናል፡፡

 የተከታዮች /ሰልጣኞች/ የሥራ ዕውቀትና ችሎታ ዝቅተኛ ቢሆንም ለሥራው

ያላቸው ፈቃደኛነት ከፍተኛ ሲሆን የአመራር ዘይቤው በማሳወቅና በማሳየት ላይ

ያተኮረ ይሆናል፡፡
የቀጠለ………..

 የተከታዮች/ሰልጣኞች/ የሥራ ዕውቀትና ችሎታ ከፍተኛ ሆኖ ለሥራው

ያላቸው ፈቃደኛነት ዝቅተኛ ሲሆን የአመራር ዘይቤው በማግባባት፣

ተሳትፎን በማበረታታትና ሁኔታዎችን በማመቻቸት ላይ ያተኮረ ይሆናል፡፡

 የተከታዮች/ሰልጣኞች/ የሥራ ዕውቀትና ችሎታ እንዲሁም ለሥራው

ያላቸው ፈቃደኛነት ከፍተኛ ሲሆን የአመራር ዘይቤው በሙሉ አቅም

እንዲሠሩ ሓላፊነቱን በመስጠትና በመወከል ላይ ያተኮረ ይሆናል፡፡


የሠልጣኞች/የተከታዩች ባህሪያት

 ጥሩ ተከታዮች/ሰራተኞች/፡- ራሳቸውን ከድርጅቱ /ከተቋሙ/ ዓላማ


አንፃር በማየት የሚያስቡና በመሪያቸው በሚሰጣቸው አጠቃላይ
አመራር መሠረት በራስ ተነሳሽነት ጭምር ተገቢውን እንቅስቃሴ
የሚያደርጉ ናቸው፡፡
 መጥፎ ተከታዮች፡- ሁልጊዜ ይህን አድርጉ ያንን አታድርጉ እስኪባሉ
ድረስ የሚጠብቁ የቅርብ ክትትልና ቁጥጥር የሚያስፈልጋቸው ናቸው፡፡
የቀጠለ……
 ተከታዮች እንደየባሕሪያቸው የተለያዩ ዐይነት የአሰራር ዘይቤ
ያስፈልጋቸዋል፡፡ ለምሳሌ አዲስ ተቀጣሪ /ሰልጣኝ/ ከነባሩና
ልምድ ካለው ሠራተኛ የበለጠ ክትትልና ድጋፍ ያስፈልጋዋል፡፡
ተነሳሽነት የጐደለው ሠራተኛ ከፍተኛ ተነሳሽነት ካለው ሠራተኛ
የተለየ የአሰራር ዘይቤ ያስፈልገዋል፡፡ አንድ የቅርብ ሀላፊ
የተከታዮቹን/የሰራተኞቹን/ ተፈጥሮአዊ ስብእናና የስራ
ፍላጐታቸውን የሚያነሳሳቸውንና የማያነሳሳቸውን ሁኔታ፣ ...
ወዘተ ለይቶ ማወቅ ይጠበቅበታል፡፡
የቀጠለ…….

 ተከታዮች/ሰልጣኞች/ ለሃላፊዎቻቸው ታማኝና ደፋር እንዲሆኑ

ይጠበቃል፡፡ ከተከታዮች የሚጠበቅ ድፍረት የሚከተለውን ያጠቃልላል፡፡

1. ከሀላፊው የሚሰጥ አሰራርን ከሓላፊነትና ከተጠያቂነት ጋር የመቀበል

ድፍረት፣

2. ተገቢውን ተግባር በመፈጸም ሀላፊን የመደገፍ

ድፍረት፣
የቀጠለ……

3.አግባብ ያልሆኑና ድርጅቱን የሚጐዱ የአሰራር ተግባራትንና

ሁኔታዎችን የመጋፈጥ ድፍረት፣

4.በለውጥ ሂደት በንቃት የመሳተፍና ለውጡን የመደገፍ ድፍረት፣

5.የተሻለ ዕድገት የሚያመጣ ለውጥን የማያራምድና የማይደግፍ

አሰራርን የመጋፈጥና አስፈላጊ ሲሆንም ትቶ የመውጣት ድፍረት

የመሳሰሉት ናቸው፡፡
ምዕራፍ ሁለት፡- ፒፒ ከረጢት (PP BAG)
በአሁኑ ሰአት ይህን ማቴሪያል በመጠቀም አለማችን የተለያዩ የቅንጦት እቃዎች
በማምረት ላይ ትገኛለች፤ በዋናነት ደግሞ ለእሸጋ የሚያገለግሉ ምርቶች
ይጠቀሳሉ ፡፡ ለምሳሌ ፒፒ ከረጢት በአገራችን በርካታ ፋብሪካዎች ቢኖሩም
ድርጅታችን በጥራት፣ በዋጋ እና በአመራረት ሂደትና ፍጥነት ቀዳሚ ሆኖ
ይገኛል፡፡
.ፒፒ ከረጢት ለማምረት ሦስት ዋና ዋና ኦፕሬሽናል ሂደቶች
ይሳተፋሉ/ያስፈልጋሉ/ ፡- 1.የክር ስራ 2.የሽመና ስራ 3.የከረጢት ስራ
ናቸው፡፡ ነገር ግን በዚህ የስልጠና ፕሮግራም ላይ ሽመና እንዴት እንደሚሰራ
በዝርዝር የምንመለከት ይሆናል፡፡
1. የክር ስራ(YARN MAKING)
ምስል 1
3. ሽመና (WEAVING)

ከላይ ከተጠቀሱት ሂደቶች ሰፊና በፋብሪካችን ውስጥ በፍጥነት


ትኩረት ተሰቶት ሲሰራበት የነበረውና ወደ ፊትም ምርትና
ምርታማነትን ለማሳደግ ከሚያግዙ የስራ ክፍሎች ቀዳሚ
በመሆኑ አጠቃላይ በስራ ክፍሉ የሚመደቡ ሰራተኞች ስለስራው
ያላቸው ግንዛቤ እጅግ ያማረና በእውቀት ላይ የተመሰረተ
የአመራረት ዘይቤ እንዲኖር በማሰብ የተዘጋጀ ማንዋል ነው፡፡
 ፒፒ ከረጢት እንዴት ይሸመናል?
2. የከረጢት ስራ (BAG MAKING)
ምስል 2
የቀጠለ…….

በአንድ በተቀመጠ የክብ ቅርፅ ባለው ሉም ማሽን ላይ ክሪሎችን


እንደ ዋርፕ በመጠቀም ክሮችን ድሮይንግ ማውጣትና
ስድስት/6/ ወይም አራት/4/ ሻትሎችን ከሉሙ ውስጥ
በማስገባት ማሽኑን በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ማንቀሳቀስ
ሽመና ይባላል፡፡(the yarn is draw out from the creel
stand is set on the loom in circular shape &
used as a warp, then set on six or four shuttle
which are inside the loom and to move in the
given direction is called weaving).
ምስል3



ክ ል






እንዴት ድሮይንግ ይደረጋል?
1.ባለ 61ሴ.ሜ ስፋት ያለው ትዕዛዝ

 ሙሉ በሙሉ የሚፈለገዉን ቦቢን ብዛት(የዋርፕ ክሮችን ) በሉሙ በሁለቱም


በኩል(both side) ሲሆን ማምረት በፈለግነዉ fabric size(የፋብሪክ
መጠን ወይም ወርድ) ይለያያል፡፡
ለምሳሌ፣ የከረጢቱ ፋብሪክ ወርድ/ስፋት 61cm የሆነ ትዕዛዝ ለማምረት፡-
ጠቅላላ ዋርፕ ብዛት ለማግኘት 61cm*2=122cm
ዋርፕ ዴንሲቲ= 4 ክሮች በአንድ ሴ.ሜ (40tapes በ10cm =4tapes
በ1cm ) ማለት ሲሆን ፣ 122*4 =488 ክሮች ይሆናል ስለዚህ ጠቅላላ
ስፓይድል 10በ9 ቢሆን
ከ720- 488=232 ስፓይድሎችን ለዚህ ትዕዛዝ አንጠቀምባቸዉም ማለት ነው፡፡
488/2=244 በሁለቱም በኩል ይደረጋል ፣በዚህ መሰረት ምሳሌ ማየት
ይቻላል….
ባለ 61 ሴ.ሜ ስፋት ከረጢት ሲደረደር
61 61

122 122
61 ሉም
ማሽን ባለ 61
244 244
61 ሳይዝ

61
61
122
122
61
61
የቀጠለ………
 በመሆኑም አንድ ሉም ላይ 36 ቤልቶች ይገኛሉ፡፡ስለዚህ ከላይ
የተቀመጡትን የዋርፕ ክሮች ለ36 ቤልቶች እኩል እኩል
እናካፍላለን፤
488/36=13.555 ይህም ማለት በአንድ ቤልት ላይ 20
ዋየሮች ስላሉን፤ ከመጀመሪያዉ በመጀመር 13ቱን በተከታታይ
ሁለት ቤልት ዉስጥ በማራራቅ ካስገባን በኋላ ቀጣይ ዴግሞ
14ቱን አሁንም በተከታታይ ቤልቶች በማስገባት ክሮች በሉሙ
ዙሪያ ገብተዉ እስከሚያልቁ ድረስ ማስገባት ይኖርብናል፡፡
የቀጠለ………
 ሲተነተን፡- 13*18=234 and 14*18=252 ይህም ማለት
234+252=486ክሮች በሪዱ ሪንግ ዉስጥ ገብተዉ የሚተርፉት 2 ክሮችን ዳርና ዳር
ላይ ማስገባት ይኖርብናል፡፡
ጥቅሞች፡-1. ወጥነት ያለዉ ፋብሪክ ለማምረት (fabric uniformity)
2. የፋብሪኩን ወርድ ለመጨመር ወይም ለመቀነስ ብንፈልግ ያለምንም
ድሮዊንግ- በቀላሉ ለመቀየር ያስችለናል፡፡
Remember (ትኩረት)፡-ትርፍ ክር አስገብተን ከሆነ ለምሳሌ ሁለት ዋርፕ ክር
ጨምረን ቢሆን፣ በተከታታይ ያሉትን ክሮች እንጅ አልፎ አልፎ መቁረጥ አይቻልም፡፡
ምክንያቱም ሸድንጉን(ዌፍት ክር ለማስገባት የዋርፕ ክር ወደላይና ወዴታች የማለት
ሂደትን) ስለሚያዛባዉ፡፡
 ማስታወሻ፡- ከላይ የተጠቀሱትን 61ሴ.ሜ ወርድ ብቻ ላለዉ ትዕዛዝ

ነው፡፡
የቀጠለ……..
Total number of warp ends(ጠቅላላ ዋርፕ ብዛት)፡-
40tapes/10cm (በአንድ ሴ.ሜ አራት ክሮች) መኖር አለባቸዉ
ለምሳሌ፡- የፋብሪክ ወርድ 61ሴ.ሜ ቢሆን
በሁለቱም በኩል ሲታይ 61*2=122 ሴ.ሜ. ይሆናል ማለት ነዉ፡፡
ማስታዎሻ ፡-የአንድ ክር ስፋት 2.5ሚ.ሜ(0.25ሴ.ሜ) ነው፡፡
ስለዚህ በአንድ ሴ.ሜ =4 ክሮች ካሉ፣
በ 122ሴ.ሜ ……………?
4*122=488 ክሮች ይሆናል ማለት ነዉ፡፡
2.ባለ 55ሴ.ሜ ስፋት ድሮይንግ ለማድረግ
 ከላይ 61ሴ.ሜ የጎን ስፋት ያለውን የምርት ትእዛዝ በዝርዝር
የተመለከትን መሆኑ በማስታዎስ ከዚህ ውጭ ያሉ ምርቶች ስለሚመረቱ
የተወሰኑትን ማየት ግድ ስለሚሆን ፡-
 ባለ 55 ሴ.ሜ ድሮይንግ ለማድረግ ሁሉም ክሪሎች በስድስት
በስድስት ይደረደራሉ፣ ከዘጠኙ የመጀመሪያዎቹ ብቻ ሰባት ሰባት
ይደረጋሉ፡፡ ይህ ማለት፡-
9*6=54 ሲሆን ፣ቀሪ አንድ ክር ስለለ 54+1=55
ከስምንቱ በአንድኛው በኩል ብቻ ያለው ብዛት ሲሆን
(54*8)+(1*8)=440 ክሮች ሙሉ በሙሉ የሚያስፈልገውና
በሪዱ ሪንግ ውስጥ የሚያልፉት ናቸው፡፡
የቀጠለ……
ማስታዎሻ ፡-የአንድ ክር ስፋት 2.5ሚ.ሜ(0.25ሴ.ሜ) ነው፡፡
ስለዚህ በአንድ ሴ.ሜ =4 ክሮች ካሉ፣
በ 55ሴ.ሜ = ?
4*55ሴ.ሜ =220 ክሮች
220*2 ( በሁለቱም በኩል)=440 ክሮች ይሆናል ማለት ነዉ፡፡

3. ባለ 50 ሴ.ሜ ድሮይንግ ለማድረግ


በሁሉም ክሪሎች ላይ ክሮች ከመደርደራችን በፊት የሳይዙን ሁኔታ ማሰብ ያስፈልጋል
፣ከላይ ወደታች ካሉት ዘጠኝ ክሪሎች ውስጥ አምስቱ በስድስት ይደረደራሉ፣ የሚቀሩት
አራቱ ደግሞ በአምሰት ይደረጋሉ፡፡ ይህም ማለት፡-
5*6=30 ሲሆን እና 4*5=20 ፣ ጠቅላላ ብዛት 30+20 =50 ክሮች ከስምንቱ
በአንድኛው ብቻ ያለው ብዛት ሲሆን
50*8=400 ክሮች ሙሉ በሙሉ የሚያስፈልገውና በሪዱ ሪንግ ውስጥ የሚያልፉት
ናቸው፡፡
የቀጠለ…….
 ስለዚህ የአንድ ክር ስፋት 2.5ሚ.ሜ(0.25ሴ.ሜ) ነው፡፡
ስለዚህ በአንድ ሴ.ሜ =4 ክሮች ካሉ፣
በ 50ሴ.ሜ = ?
4*50*2=400 ክሮች ይሆናል ማለት ነዉ፡፡
4. ባለ 45ሴ.ሜ የሆነ ከረጢት ትዕዛዝ ድሮይንግ ለማድረግ
በዚህ የስራ ክፍል ውስጥ ከሁሉም የምርት አይነቶች በብዛትም ሆነ በአደራደር ቀላል ሲሆን ይህም ማለት ፡-
ሁሉም(ዘጠኙም) ከላይ ወደ ታች በአምስት መደርደር ሲሆን
9*5=45 ክሮች ከስምንቱ በአንደኛው ብቻ የሚቀመጡ ሲሆኑ
8*45=360 ክሮች በሪዱ ሪንግ ውስጥ ሲገቡ ቀጥታ ወደ ስራ መግባት ይቻላል ማለት ነው፡፡
ስለዚህ የአንድ ክር ስፋት 2.5ሚ.ሜ(0.25ሴ.ሜ) ነው፡፡
ስለዚህ በአንድ ሴ.ሜ =4 ክሮች ካሉ፣
በ 50ሴ.ሜ = ?
4*45*2=360 ክሮች ይሆናል ማለት ነዉ፡፡
ምስል4

12*
3=3
6 ቤል ባለ
ቶች ስድ
ስት
ትል ሻ
ሉም

የ ሚረዱ
ለማድረግ
፣ከፍ ናዝቅ

ስነ ሻ ፣ማቆሚ

የማሽኑ ክፍሎችና ጠቀሜታቸው
 Bobbin (ቦቢን):- ክርን አጠንጥኖ የያዘዉ ሲሆን ባዶ (ጥቁሩ ፓይፕ) እስከሚታይ
መሰራት አለበት
 ቦቢን ሆልደር (bobbin holder):- ሻትሉ ውስጥ የምናሰገባውን ቦቢን በሁለቱም በኩል
እቅፎ ለመያዝ ይረዳል፡፡
 ስፒንድልስ(spindles) ቦቢኑን ክሪል ላይ እንዳይወድቅ አድርጎ የሚይዝልን
 ቦቢን አዳፕተር(bobbin adapter):- ስፒንድሎች በቀላሉ እየተሸከረከሩ
በምንፈልገዉ ርዝመትና ዉጥረት(tension) ወደ ሉም እንድዴርሱ ያደርጋል
 Creel eyelets (ክሪል አይሌትስ): ለስላሳና በቀላሉ ክር ማሳለፍ የሚችሉ
ሲሆኑ ክር ወዴ ሉም ያለምንም መሻከር እንድዴር ያረጋል፡፡
 Special drop wires (ዋየርስ)፡- የእያንዳንዱን ክር ዉጥረት(tension)
በእኩል መጠን እንድሆን በማድረግ አንዱ ክር ከሌላዉ ክር ያነሰ ወይም የበዛ ዉጥረት
ካለበት በሴንሰር(sensor) አማካኝነት ሉሙ እንድቆም ያደርጋሉ፡፡
ምስል5
የቀጠለ…….
 Warp feeding system (ክር ወደ ሉም የማስገባት ዘዴ) ፡
አይሌት ወይም ሮለር አማካኝነት ተመሳሳይ በሆነ ዉጥረትና
ርዝመት ይደርሳሉ፡፡
 Warp break detecting system (ዋርፕ ብሬክ
ዲቴክቲንግ ሲስተም)፡- ይህ ዘዴ ደግሞ ዋርፕ ክር መበጠሱን
ወይም ክሮች የተለያዬ ዉጥረት(tension) ዉስጥ
መሆናቸዉንና የተበጠሰዉ ክር የት ቦታ እንደሆነም ጭምር ቀይ
በማብራት(pilot lump) በማሳየት ሉሙን ወድያዉኑ
እንድቆም የማድረግ ዘዴ ነዉ፡፡
የቀጠለ……
 Weft break detecting system(ዌፍት ብሬክ ድቴክቲንግ ሲስተም)፡-
ሉም ላይ በተገጠሙ(magnetic sensors) ያለማቋረጥ
ዌፍት ክር በአግባቡ እየገባ መሆኑንና ባጋጣሚ አልቆ ወይም ተበጥሶ
ዝምብሎ ሉሙ እንዳይሰራ በማስቆምና ቀይ መብራት
በሁሉም አቅጣጫ ባሉ ሴንሰሮች ላይ በማብራት የት ቦታ ችግር
እንዳለ የሚያሳን ሲሆን ይህም ፋብሪኩ ላይ የጎዴለ ዌፍት
እንዳይኖር ይረዳል፡፡
 Five manual control units(አምስቱ በሉም በራሷ በኦፕሬተሯ የሚከናወኑ
የመቆጣጠሪያ ዩኒትስ)
.Inch buttons(up & down)
.Stop buttons (ማቆሚያ)
.Start button (ማስነሻ)
የቀጠለ……
 Fabric winder (fabric roller):- የተመረተዉ ፋብሪክ
ለመቁረጥ ሲተረተር አመች በሆነ
መልኩ ለመጠቅለል የሚረዳ ነው፡፡
 Bobbin storage tray(የተዘጋጁ ቦቢን ማስቀመጫ
ቦታ)፡-ከክር መግቢያዉ ከማሽኑ
ከላይ ቦቢኖችን ሲያልቁ መተኪያ አርገን እናዘጋጃለን፡፡
 Unfolding device፡-ክብ ሆኖ የተመረተዉን ፋብሪክ ወደ
ፍላት ያለማቋረጥ ፋብሪኩን ያሳልፋል፡፡
የቀጠለ…….
 Distribution of warp ends (ዋርፕ በሪድ የማሳለፍ ዘዴ)
ወዴ ሉም የምናስገባዉ ዋርፕ ክር
በሚመረተዉ ፋብሪክ (size) መጠን
ወይም ወርድ ይገለጻል፡፡ከክሪል የሚመጣዉ ክር በኢንሌት
አልፎ ሪንጉ በሚገባበት ጊዜ ትይዩ መሆን አለበት፡፡
ጥቅም፡-
1.የጎዴለ ክር ካለ በቀላሉ ለማየት ያስችላል፣
2.የተቆረጠ ዋርፕ ካለ ለመፈለግና በቀላሉ ለማየትና ለመቀጠል ያስችላል፡፡
የቀጠለ……
 Heddle belt-shedding unit ፡- ሸድንግ ዩኒት ማለት
ዌፍት ለማሳለፍ በዋየሮች የተያዙት ዋርፕ
ክሮች ወዴ ላይና ወዴታች መከፈት ስላለበት
በካም አማካኝነት ቤልት ክሮችን ይዞ ወደ
ላይና ወደታች ይንቀሳቀሳል፡፡
ምዕራፍ ሦስት፡- ከሰራተኛው ምን ይጠበቃል?

በመጀመሪያ ሁላችንም ከላይ በስራ ክፍሉ የተሰጡ አሰራሮችን


ሙሉ በሙሉ በመቀበል በዚህ ምዕራፍ የሚነሱ ተግባሮች ለስራ
ክፍሉ በጣም አስፈላጊና ምርትናምርታማነትን ለመጨመር
ከሚረዱ ወሳኝ ከሆኑት የአንድ ድርጅት መንገዶች ውስጥ ዋናው
ማንኛውም ሰራተኛ የስራ ክፍሉን ህግና ደንብ ማወቅ እና
መተግበር ነው፡፡ስለዚህ በሉም የስራ ክፍል ሰልጣኝ ሰራተኞች
ይህ መመሪያ ተቀብለው ወደ ስራ ቢገቡ ውጤታማ ይሆናሉ
ተብሎ የታመነባቸውን የአሰራር ቅድመ ሁኔታዎች በዝርዝር
የምንመለከት ይሆናል፡፡
1.መውጫና መግቢያ ሰአት ማክበር
 የስራ ሰአት ማክበር ከማንኛውም ሰራተኛ የሚጠበቅ የድርጅቱ ህግና ደንብ
ቢሆንም በአድስ በስልጠና ላይ ባለሰራተኛ ግን የተለየ ትኩረት ተሰቶት ይታያል
፡፡ ምክንያቱም አድስ ሰራተኛ ከውጭ ይዞት የመጣውን የስራ ባህልና ዘይቤ
በፍጥነት ከድርጅቱ የአሰራር ደንብና ስርአት ጋር ማዛመድ ስለሚስፈልግ
ነው፡፡
 የሰራተኛው የማምረትና የምርታማነት መገለጫ ተደርጎ መጀመሪያው
የሚገመገምበት ነጥብ የስራ ሰአት አከባበር፡፡
 የተመደበበትን ማሽን በትክክል መስራትና አለመስራቱን የሚያረጋግጥበት
በሰአቱና ቀድሞ በመግባት ነው፡፡
 ለሚሰሩት ስራ ቅድሚያ ትኩረት በመስጠት ማሽናቸውን ለተቃራኒ ፈረቃ
ማስረከብና መረከብ ይጠበቃል፡፡
የቀጠለ……
 ምሳ ሰአት ላይ ለቡድናቸው አመቻችተው በመስጠት የተፈቀደላቸውን
ሰአት በፍጥነት ተጠቅመው በመመለስ የጓደኛቸውን ማሽን መሸፈን
በስራ ክፍሉ ከጁኒየር እስከ ሲኒየር የስራ መደብ የሚጠበቅ ተግባር
ነው፡፡
 በአጠቃላይ ሰአትን በማንኛውም ቦታና ጊዜ በአግባቡ መጠቀም
ለምናሳየውን የስራ አፈፃፀም ለማሻሻል ፣ ወደሌላ የስራ ደረጃ ለማደግ
ከሚለኩበት የመመዘኛ ነጥቦች መሆኑን በመረዳት ሁላችሁንም
በተመደብንበት የስራ ክፍል ለሌሎችም ጥሩ አርአያ በመሆን
ድርጅታችንንና ራሳችንን አሁን ካለንበት የአስተሳሰብ ደረጃ ከፍ
እንድናደርግ ይጠበቃል፡፡
2.የስራ ላይ እውቀት
 ሁሉም ሰራተኛ በተመደበበት የስራ ክፍል በሚያከናውናቸው ተግባሮች ላይ በቂ
የሆነ እውቀት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ይህ ማለት ሰራተኛው በተቀጠረበት ድርጅት
ቀጣይነት ያለው ምርት ጥራቱን ጠብቆ እንዲመረትና የስራ ክፍሉን ከሌሎች
የተሻለ የስራ ሂደት እንዲኖር ያደርጋል፡፡
 በሚያመርትበት ጊዜ የማሽን ብልሽት ሲያጋጥመው ችግሩ የት ቦታ እንደሆነ
መፍትሄ ለመስጠትም ሆነ ሪፖርት ለማድረግ በሚሰራው ስራ ላይ በቂ እውቀት
ሊኖረው ይገባል፡፡
 በአጭር ጊዜ ውስጥ ራሱን ወደሚቀጥለው የስራ ደረጃ ከፍ እንዲል ያደርገዋል፡፡
የቀጠለ……..
 በስልጠናም ሆነ ከቅርብ ሀላፊዎች የተገኘን እውቀት በተግባር
ላይ በማዋል አሁን ከሚገኙበት የእውቀት ደረጃ የበለጠ
በማሻሻል የሚሰሩትን ስራ ማሳመርም ሆነ ውጤታማ ማድረግ
ይቻላል፡፡
 በአጠቃላይ የማያውቁትን ለማወቅ በመጣር እና የሚያውቁትን
ደግሞ ለሌሎች በማጋራት የሚሰሩትን ስራና ራስዎን ወደ ጥሩ
ቦታ ማሻገር ይጠበቅባቸዋል/ይቻላል፡፡
3. ብክነት መቀነስ
ማንኛውም ሰራተኛ የሚጠቀምበትን ማቴሪያል በአግባቡ ሊጠቀምበት ይገባል፡፡ ለምሳሌ
ዘይት፣ክር፣ምላጭ………..ወ.ዘ.ተ
 ዘይትን በተመለከተ፡- እንደሚታወቀው ዘይት ለምርት ጥራትም ሆነ ለማሽን ጤንነት
በጣም አስፈላጊ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡ በመሆኑም በተገቢው ሁኔታና መጠን
በመጠቀም ከፍተኛ ብክነትና ኪሳራ በድርጅት ላይ እንዳይከሰት የተሰጠንን በጥንቃቄ
በመያዝ ሙሉ ሰአታችንን የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖር በዘይት አጠቃቀም ዙሪያ
አስፈላጊውን ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡
 በሚፈለገው ማሽን ላይ ብቻ በመጠቀም የአካባቢን ጽዳትና ንጽህና በመጠበቅ የስራ
ቦታችንን ፅዱ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡
 በማምረት ሂደት ክሮች በጥሩ ሁኔታ ያለምንም መበጣጠስ እንዲሳቡና በተሰጠው ሰአት
የተሻለ የምርት አፈፃፀም እንዲኖር ለማስቻል ዘይት ከፍተኛ ጠቀሜታ ስላለው
በአግባቡ መጠቀም ይኖርብናል፡፡
የቀጠለ…….
 ክርን በተመለከተ፡- የተለያዩ የክር ብክነቶች በሰራተኞች ችልተኝነትም
ሆነ ባለማወቅ በዚህ የስራ ክፍል ሲስተዋሉ ይታያሉ፡፡ለምሳሌ፡-
.የሚሰራ ክር መሰንጠቅ/መቁረጥ/
.ፓይፕ እስከሚታይ ድረስ አለመስራት
.የተደረቡ ክሮችን በቦታቸው አለማጣራት
.አድስ ሰራተኞች ላይ በቂ ግንዛቤ አለመስጠት
.የሚያልቁ የክሪል ቦቢኖችን አለመከታተል
.ከዋይንደር ሲመጡ የጥራታቸውን ሁኔታ አለማየት
የቀጠለ……

. በባግ ወይም በሳጥን የሚቀመጥ ምርት በሚመቺ መልኩ


ማስቀመጥ
.ከሚሰሩበት ማሽን ወደ ሌላ ቦታ መንቀሳቀስ ማሽን
ሲበትንም ሆነ ሲበጥስ በፍጥነት አለማቆም
.የሚፈለፈል እና የማይፈለፈል ክር ለይቶ አለማወቅ
በክፍሉ ውስጥ ከፍተኛ ሆነ የክር ዎስት/ብክነት/
እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል፡፡
የቀጠለ……
 ምላጭን በተመለከተ፡- ምላጭ በዚህ የስራ ክፍል ብዙ ነገሮችን
ለመስራት እንጠቀምበታለን፡፡በመሆኑም በአግባቡ በመያዝ
በሚፈለገው ቦታ እና በተሰጠን የአገልገሎት ጊዜ ስራ ላይ ማዋል
ይጠበቅብናል፡፡ምላጫችንን በእጃችን በመያዝ በስራ ክፍሉ ውስጥ
የሚከተሉትን ተግባሮች ማከናወን ይኖርብናል፡፡
 ቅሪት ምርቶችን ለመቁረጥ/ለማጣራት/
 ማሽን ላይ የሚጠመጠሙ ክሮችን ለመቁረጥ
 የማዳበሪያውን ገፅታ እንዳያበላሹ ተበጥሰው/አልቀው/የሚቀጠሉ ክሮችን
በአግባቡ ለማስተካከል ይረዳል፡፡
 በድሮይንግ ጊዜ ማዳበረያዎችን እና ክሮችን ለመቁረጥ
4.ተግባቦት
ለማንኛውም ሰራተኛ በስልጠናም ላይ ሆነ በየትኛውም የስራ መደብ ቢሆን ተግባብቶና
ተስማምቶ በጋራ የተሰጠውን ስራ ሲያከናውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ እንደሚሆን
ብዙ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
 በተመደበበት የቡድን ስራ የተሻለ ተግባቦት በመፍጠር ከሌሎች የበለጠ የምርት አፈፃፀም
እንዲኖር ያስችላል፣
 በምሳ እና በእራት ሰአት በጓደኞቹ አማካኝነት የሚሰራበት ማሽን እንዲሸፈን ይሆናል፤የተሻለ
የምርት አፈፃፀምም ይኖረዋል እንዲሁም በሚሰጡ ማበረታቻዎች እኩል ተጠቃሚ
ያደርጋቸዋል፡፡
 ለሚቀጥለው የእድገት ደረጃ ከቅርብ ሀላፊው በኩል ጥሩ የሆነ ግምት ይኖረዋል ወይም
በተቀመጠው የወዳደሪያ ነጥብ ላይ የተሻለ ውጤት/አስተያየት ሊያገኝ ይችላል፡፡
5.የክር ዲኒየር/DENIER/ላይ ጥንቃቄ ማድረግ
 ዲኔየር ማለት በጣም ረቂቅ የሆኑ ክሮች መለኪያ መስፈርት ሲሆን
ከ9000 ሜትር ክብደት በግራም ከሚመዝኑ ክሮች ጋር እኩል የሆነ
ማለት ነው፡፡
 ከመጀመሪያ ጀምሮ ማንኛውም የምርት ትዕዛዝ ሲመጣ እና የዋጋ
ስምምነት ሲደረግ የማዳበሪያውን ግራም በክር ውፍረትና ቲክነስ
መሰረት በማድረግ ነው፡፡ በመሆኑም በቴፕ ፕላንት የስራ ክፍል
የተመረተው የክር መጠን ለታዘዘው የምርት አይነት ተለይቶ ለብቻው
ስለሚቀመጥ ወደ ሽመና ክፍል ሲገባ ከምድቡ መሆኑን በጥንቃቄ
ማሰብና ማጤን ያስፈልጋል፡፡ይህ ካልሆነ ግን በድርጅቱ ላይ ከፍተኛ
ኪሳራ ወይም በደንበኞች ላይ ደግሞ ቅሬታን ያመጣል፡፡
የቀጠለ…..
 በማምረት ሂደቶች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ስለሚያስከትል ከመጀመሪያ
ጀምሮ ለተመደቡበት ማሽን ተመርቶ የተቀመጠው ክር የቱ ነው የሚል
ጥሩ የሆነ ልምድ ሊዳብር ይገባል፡፡
 የሁሉም ክሮች የዲኔየር መጠን ከመለካት ውጭ በማየት፣ በመዳሰስ እና
በመገመት ማወቅ ስለማይቻል ብዙ ጊዜ ስለሚወስዱ እንዳይቀላቀሉና
ተሳስተው ወደ ምርት እንዳይገቡ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡
 ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች በአንዳኛው ፈረቃ ብቻ የተሻለ አፈፃፀም
ስለማያስገኝ በተቃራኒ ሽፍት ከሚመደቡ ኦፕሬተሮች ጋር በየቀኑ ርክክብ
በሪፖርት መልክ ለቅርብ ሀላፊ/ፎርማን/ ማድረግ ተገቢ ይሆናል፡፡
የቀጠለ…………..
 አንድ 61*100ሴ.ሜ ,90 ግራም የሆነ ማዳበሪያ ቢታዘዝና የዲኒየር መጠኑ 700
ቢሆን እና ሌላ 61*100ሴ.ሜ 120 ግራምና 800 የዲኒየር መጠን ያላቸው
ትዕዛዞች ቢኖሩ ከላይ እንደጠቀስናቸው የክር ቅልቅል ችግር ቢያጋጥም በድርጅቱ
ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት በዝርዝር ማየት ይቻላል፡፡
ለምሳሌ 800 የዲኒየር መጠን ያለው ክር 700 ከሚመረተው የምርት ትዕዛዝ ጋር
ሲቀላቀል ክብደቱ ወደ 110 ግራም ከፍ ሲል፣ልዩነቱ 20ግራም ቢሆንና ጠቅላላ
የተመረተው የምርት ብዛት በቀን 1000(አንድ ሺ) ማዳበሪያ ከሆነ 20ኪ.ግ ኪሳራ
ያሳያል ፡፡ ይህም (ሌሎች ወጭዎችን ሳይጨምር) በገንዘብ ሲቀየር 20*80ብር =
1600birr ይሆናል ማለት ነው፡፡ እንደዚሁ በተቃራኒ 700 ወደ 800 ገብቶ ግራሙ
ቢቀንስ በደንበኞች ዘንድ ቅሬታን በመፍጠር እስከ ውል ማፍረስ ደረጃ ሊደረስ
ይችላል፡፡ ስለዚህ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ መገንዘብ ይኖርብናል፡፡
6. ድሮይንግ/CROSSING/ መጠበቅ
 በሽመና የስራ ክፍል ውስጥ የመጀመሪያው የስራ ሂደት እና በጣም ጥንቃቄ
ሊደረግበት የሚገባ ፣ክሮችን በተገቢው ቦታቸው ማሳለፍና ከታዘዘው
የምርት አይነት ጋር በማዛመድ በዋየር/wire አማካኝነት ወደ ተዘጋጀው ሪድ
ሪንግ ውስጥ ማስገባት ድሮይንግ ሲባል ይህም እስከአሁን በዚህ የስራ ክፍል
ለወሰድናቸው ክንውኖች ሁሉ እንደመነሻ የሚያገለግልና በዋናነት የሚጠቀስ
የስራ መዘርዝር ነው፡፡ስለዚህ የተለያዩ የድሮይንግ አደራደር አይነቶች ሲኖሩ
ነገር ግን እንደማሽኖቹ አይነትና ዲዛይን ስለሚለያዩ የማሽኖቹን ማንዋል
መከተል በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ ያደርጋል፡፡ ለዚህም፡-
 መጀመሪያ ሀላፊዎች የሚሰጡትን የግንዛቤ ማስጨበጫ በሚገባ መከታተል፣
የቀጠለ………
 ተጨማሪ እውቀት ለማዳበር ይረዳን ዘንድ የአሰራሩን ሁኔታ
የሚያግዙ ሂደቶችን በማስታዎሻ መያዝ
 የሚታዘዙ የምርት አይነቶችን ከድሮይንግ አደራረግ ሂደት ጋር
በማዛመድ የክሮችን አደራደር በጥሞና ማጤን
 እያንዳንዱ ክር ከመጀመሪያ ጀምሮ እንዴትና በየት እንዳለፈ
መስመሩን ጠንቅቆ ማወቅ
 ከተቃራኒ ፈረቃ ጋር ሁልጊዜ በመረካከብ ያጋጠሙ ችግሮችን
ለፎርማኖች ሪፖርት ማድረግ
የቀጠለ……….
የማሽኖችን ድሮይንግ መጠበቅ የሚያስገኘው ጥቅም
1. በምናመርትበት ጊዜ አላግባብ የሆነ ድካምን ይቀንሳል፣
2. የምርት ጥራት እስከመጨረሻው ተጠብቆ እንዲመረት ያስችላል፣
3. በማሽኑ ላይ ከእቅድ ውጭ የሚባክኑ ሰአቶች እንዳይፈጠሩ ያደርጋል፣
4. በአጭር ጊዜ የተሻለ የምርት አፈፃፀም እንዲመዘገብ ይረዳል፣
5. የማሽኖችን ጤንነት ይጠብቃል፣
6. ከፍተኛ የሆነ የግብአትና የመለዋወጫ ፍጆታን ይቀንሳል፣
7. የሰራተኞችን በስራ ላይ የመቆየት ፍላጎትንና የስራ ተነሳሽነትን ይጨምራል፣
8. በድርጅቱ ውስጥ የብክነት መጠን እንዲቀንስ ያግዛል
ማጠቃለያ

 የሉም የስራ ክፍል እንደተፈለገው የሚገባበት የሥራ ዘርፍ ሳይሆን በከፍተኛ ዝግጅትና

ጥንቃቄ የሚከናወን ተግባር ነው፡፡ ጥሩና ጠንካራ ሰራተኛ በመሆን የድርጅትን ተልእኮ

ለማሳካትና ጠቀሚ የሆነ ተግባር ለመፈጸም የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት

ይጠይቃል፡፡

 ራስን ማወቅና በየጊዜው ለማሻሻል መጣር፣

 የስልጠና ጽንሰ ዐሳብና ዕውቀት ብቁ ሆኖ መገኘት፣

 ሓላፊነትና ተጠያቂነትን ዐውቆና ተቀብሎ መሥራት


የቀጠለ……

 ተገቢውን ስልጠና በወቅቱ መውሰድ፣

 ሁል ጊዜ የመልካመ አርአያ/ሰራተኛ/ ምሳሌ መሆን፣

 የሚተላለፉ መልዕክቶችን ተገቢውን ቦታ መስጠት፣

 ለቡድን ስራ ተገቢውን ድጋፍና ትብብር ማድረግ፣

 ለሀላፊዎች ተገቢና ወቅታዊ መረጃ ካለ መስጠት፣

 አርቆ ማሰብና በአጭር ጊዜ የማደግና የመጠቀም ችሎታን ማዳበር ፣


የቀጠለ……..

 ደከማኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ጥብቅና ቁርጠኛ መሆን፣


 ሰራተኛ ማለት ሌሎችንና እራስን መርዳት ማለት መሆኑን መገንዘብ፣
 ለተተኪነት መዘጋጀት ማለት ለበለጠ እና ቀጣይነት ለሚኖረው ጥቅም ራስ

ማብቃት ማለት መሆኑን ጠንቅቆ ማወቅ፡፡


 በመጨረሻም ይህን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተግባራዊ በማድረግ እራሳችንን

እና ድርጅታችንን ወደ ተሻለ የእድገት ደረጃ ከፍ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡


የውይይት እና የተግባር ጥያቄዎች
1.ማሽኔ በ1 ደቂቃ 2.16ሜትር ቢያመርት በ480ደቂቃ(በ8 ሰዓት) ስንት ያመርታል ከዚህስ ምን ተረዱ?
2, ዲሮዊንግ ቢበላሽ ምን ችግር ያስከትላል?
3.ተግባብቶ የማይሰራ ሰራተኛ ምን ችግር ይገጥመዋል?
4.የብክነት አይነቶችን ጥቀሱ፡፡አስከፊነታቸዉስ ምንድን ነዉ?
5. ዲኔር ቢቀላቀል ምን ችግር ያስከትላል?
6.አለቃየን ባልታዘዝ ምን ችግር አለዉ?
7. እድገት ለማግኘት ከእኔ ምን ይጠበቃል?
8. ሰራተኞችን ከፍተኛ፣መካከለኛና ዝቅተኛ ብለን የከፈልንበት ምክናየት ምንድን ነዉ ?
9, በአንድ ማሽን ላይ ስንት ቤልትና ዋየር አሉ ?
10, 55ሴ.ሜ ወርድ ያለዉ ምርት ለመሸመን ብፈልግ ስንት ቦቢኖችን ክሪል ላይ መደርደር አለብኝ እንደት?
ከሚፈለገዉ ቢያንስ ወይም ቢጨምር በፋብሪኩ ላይ ምን ችግር ያስከትላል ?
11, የምታመረቱት ማዳበሪያ በምን በምን ነገሮችሊለያይ ይችላል?
12. አጠቃላይ ስለስልጠናዉ አስተያየት ካለዎት ባጭሩ ይገለፅ …
እናመሰግናለን

You might also like