You are on page 1of 5

1.

አስተባባሪው መተማመን
●የወረዳው ሸክም እኛ ላይ መሆኑን ማመን
●ስኬትም ካለ ድክመትም ካለ የሁላችን መሆኑን ማመን
●ትንሽም ነገር ትሁን በሆዳችን ሳንይዝ መነጋገር
●በፋፁም እርስ በርስ አለመተማማት
●ስለ አንዳችን ወሬ ሲነሳ ጥንካሬውን አጉልተን እንጅ አወ እሱማ አለማለት
●ከምንም በላይ መደማመጥ መከባበር አለብን እኛ አስተባባሪወቹ ስንከባበር
ሌላው አመራር ያከብረናል
●ስራን አለመገፋፋት አለመጠባበቅ
●ሀሳብን ተከፋፋሎ መምራት ማጠቃለል
●አስተባባሪው ትኩረት የሚያደርጋቸውን ስራወች መለየት ከህዝብ መሰረታዊ
ጥቅም አኳያ( መሰረተ ልማት,መ/አስተዳደር,የልማት ሴክተሮች,ኑሮ
ውድነት,ሰላም,አጠቃላይ ፖለቲካ
●ስንሰራ ችግርና አጣብቂኝ ነገር መፈጠሩ ግድ ነው
በዚህ ሰአት መረጋጋት ከችግሩ በላይ ፈጥኖ መፋትሄው ላይ መረባረብ ለዚህ
መደማመጥ
●ስራወች በተቀመጠላቸው ጊዜ እንድጨረሱ መከታተል የያዝነውን እየሰራን
አድስ ተልዕኮን መቀበል
●ግብረ ሀይል መከፋፈል
●የፖርቲ አመራር ሀሳብ ማፋለቅ(እኔ ለሸትየ ምን እንደነበርኩ ሁሉም ያቃል
ቀድሜ ተጋፋጬ ነገሮችን አመቻችቼ ከፖርቲ ሰው የሚጠበቀው እሱ ነው
በተለይ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ደፋሮ መታገል!!
●የፖለቲካ አዝማሚያ መገምገም ይሄ ቢሰራ ብሎ አቅጣጫ ማቅረብ
ለአስተባባሪው መነሻና ግብአት ይዞ መቅረብ
●የአመራሩን አፈፃፅም መከታተል በተግባር መመዘን
●የሚሰራና የማይሰራውን በመረጃ በደረጃ መለየት
●የመነሻ ሰነድና የግምገማ ሀሳብ ማቅረብ
●የፖርቲ መዋቅር መትከል ከመ/ድ_ህዋስ
●መድረክ ማቀድ መፈፅሙን መከታተል
●ቁልፍ የመንግስት ተግባሮችን እንደፖርቲ መደገፋ
●ሁሉንም ስራ አውቀን መምራት ማስተባበር
●ወረዳዊ እይታ መያዝ የተሾምነው ለሁሉም ስለሆነ
●ፖለቲካ ሀይል ማሰባሰብ ስለሆነ አቃፊ መሆን የሚጠላንንም አክብረን ማገልገል
●ከተናጠል ሩጫ በአደረጃጀት ተግባርን ለመምራት መሞከር
●ራስን ለትችትና አስተያየት ተቀብሎ ለመሻሻል መዘጋጀት ሌሎች በተለይ
የምንመራው ህዝብና የተቋም
ሰራተኛው እኔን እንደት ያየኛል ብሎ ራስን አይቶ ማስተካከል
●የሰራነውን ስራ ለህዝብ የመሸጥ ስራ መስራት
●ህዝብንና ጥቂት የግለሰቦች ስብስብን መለየት
ጥቂት ግለሰቦች ከራሳቸው ጥቅም አኳያ ሲያመሰግኑን ህዝቡን ያስደሰትን
እንዳይመስለን ግለሰብ ከራሱ ጥቅም አኳያ ተከፋቶ ቢጮህና ስም ቢያጠፋ ህዝብ
እንዳልሆነ መረዳት(በህግ ከሆነ ለግለሰቡም መጨነቅ)
●ቅሬታና አቤቱታ አሰራሩን ተከትለው እንድሄዱ ማድረግ ከሚመለከተው ቀበሌ
ሴክተር የተነሱ መሆናቸውን መከታተል: በተለይ አስተባባሪው የግለሰብ ጉዳይ
በማዳመጥ ጊዜ ፈጅተን የመላ ህዝቡን ጥያቄ ሳንመልስ ከቀረን አደጋ ነው
●ሚስጥር መጠበቅ(የአመራር መከበሪያ ነው)
●ከሂደት በዘለለ የተግባር ሰው መሆን መድከምን እንደ ስኬት አለመቁጠር
●ለቀረበልን ጥያቄ በህግና አሰራር ፈጣን ምላሽ መስጠት(መወሰን አንዱ
የአመራር ብቃት ስለሆነ)
●በፈጠራ የታገዘ አመራር መስጠት የተለመደ አሰራር ሁሌ አይሰራም
የአመራሩ ፈተናወች ሊገጥሙን የሚችሉት
1.የሰላም ስጋት
2.የሀይማኖት ፋጥጫ
● የበአል አከባበር
3.የከተማ ቦታ አዋጁ ሲነሳ
4.አሉባልታ
5.የልማት ጥያቄወች
6.ሌብነት በብዙ መልኩ(ወረዳ,ቀበሌ)

መከተል ያለብን የመፋትሄ አቅጣጫወች


1●በየትኛውም መንገድ ህዝብን ሳንሰለች ማወያየት(ከወረዳ_ቀበሌ)
●ሀይል ማሰባሰብ
●የህዝብ አደረጃጀት መጠቀም(ሀ/አባት,ተፅኖፈጣሪ
እድር)
2.አሁን የማለዘብ አቅጣጫ ከኛ ቆጠብ ብለን
●ለጉዳዩ አጋዥ የመፋትሄ ሰው ተው የሚል ማፋራት

3.የልማት ጥያቄወቹን
●ልዩ ክትትል በየቀኑ አፈፃፅሙን
ለምሳሌ መንገድ
ኮብል
ማደያና ሌሎች የቀን እድገታቸውን መከታተል
●የልማት ተቋሞችን ለይቶ መደገፋ በተለይ ለህዝቡ የሚጠቅሙትንና በዞን
የምንለካበት ለይቶ ማጠናከር
4.ለአሉባልታ እኛ ቀድመን መረጃ መስጠት መነጠል
5.ሌብነትን በአሰራር መያዝ
●ጎላ ያለ ካለ መጠየቅ
●ተቋማትን ለይቶ መከታተል(መዘጋጃ,ፕሮጀክት ተጠቃሚ ተቋማት)
●ቀበሌ ያለ ሌብነት መረጃ መሰብሰብ በአግባቡ

You might also like