You are on page 1of 20

የሥራ መደቡ መጠሪያ ፡ ጁኒየር የኮንቴነር ኦፕሬሽን ኦፊሰር

የሚገኝበት ቅ/
ቅ/ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ

ክፍሉ ፡ ኦፕሬሽን

ቀጥታ ተጠሪነቱ ፡ ለኦፕሬሽን አስተባባሪ

ዝርዝር ተግባራት

1. ከበር ቁጥጥር ሠራተኛ በሹፌር አማካኝነት የቀረቡለትን ሰነዶች በመቀበል የመኪና ሰሌዳ፣ የኮንቴነር ቁጥር፣
የሹፌር ስምና የመንገድ ወረቀት (way bill) በማመሳከር ኮንቴነሩ ቀድሞ በተዘጋጀለት ሥፍራ (Location)
እንዲራገፍ ለማሽን ኦፕሬተር የሥራ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ ስለመራገፉ “way
“way bill” ላይ ማህተምና ፊርማውን
በማኖር ማረጋገጫ ይሰጣል፡፡ በመጨረሻም በአገልግሎት መከታተያ ቅፅ ላይ ሥራው የተጠናቀቀበትን ሠዓት
በመሙላት ሹፌሩን ያሰናብታል፡፡

2. በተርሚናል የተቀመጠ ኮንቴነር የተራገፈበትን ትክክለኛ ቦታ የሚጠቁም መረጃ በ”EIR” ላይ ሞልቶ


ወዲያውኑ የተርሚናል ሎኬሽን መረጃ ቅርንጫፍ ጽ/
ጽ/ቤቱ አሁን ባለበት የመረጃ አያያዝ መዝግቦ ይይዛል፡፡

3. በየጊዜው የተርሚናል አጠቃቀም መረጃ ይይዛል፡፡ክፍት ቦታዎች እና ኮንቴይነር ያረፈባቸውን በቦታዎች


በመለየት መረጃ ይያዛል፡፡የተርሚናል አጠቃቀም በ Occupancy Rate መሰረት ያከናውናል፡፡

4. ባዶ ኮንቴነሮችን ከበር ቁጥጥር ሠራተኛ በሹፌር አማካኝነት የቀረቡትን ሠነዶች በማረጋገጥ ቀድሞ
በተዘጋጀላቸው ቦታ ተረክቦ ያስቀምጣል፣ የባዶ ኮንቴነር መረጃ ለሚመለከተው የሥራ ክፍል ያሰራጫል፡፡

5. አደገኛ የሆኑ (Hazardous) ኮንቴነሮች ምንነት ቀደም ብሎ በመለየት ለብቻ በተዘጋጀላቸው ቦታ እንዲራገፉ
ያደርጋል፡፡

6. የኮንቴነር ቦታ ለውጥ (Shifting)


Shifting) በሚኖርበት ወቅት ይህንኑ የኮንቴነር እንቅስቃሴ መረጃ በተቀመጠው
ሥታንዳርድ መሰረት መረጃ መያዝ፡፡ ከስምንት ቀን በላይ ወይንም አዲሱ ታሪፍ በሚያፀድቀው የነፃ የመጋዘን
አገልግሎት ታሪፍ በላይ በቆዩ ኮንቴይነሮች ላይ ሽፍቲንግ የሚሰራ ከሆነ ስራውን ለሁሳብ ክፍል ማሳወቅ፡፡

7. ኮንቴነር እንዲጫን በተላለፈለት የሥራ ትዕዛዝ መሰረት ተገቢውን የማሽንና የሰው ኃይል ዝግጅት በማድረግ
ጭነቱን የሚጭነው ተሽከርካሪ እንደደረሰ የሰሌዳ ቁጥር፣ የሚጫነው ኮንቴነር ቁጥርና መጠን በማመሳከር
አስጭኖ ተሽከርካሪው ወደበር እንዲሄድ ያደርጋል(
ያደርጋል(ይልካል)
ይልካል)፡፡

8. ለጉምሩክ ፍተሻና ለአስንስታፊንግ ጥያቄ የሚቀርብባቸው ኮንቴነሮች በተላለፈበት የሥራ ትዕዛዝ መሰረት
ወደ ተፈለገው ቦታ እንዲዛወሩ ያደርጋል፡፡(
ያደርጋል፡፡(የወደፊት የስራ አካል ነው)
ነው)

9. ባለማቀዝቀዣ ኮንቴነር ጭነቶች መረጃ ቀድሞ በመያዝ ቀድሞ በተለየለት ቦታ እንዲቀመጥ ያደርጋል፡፡
(የወደፍት የስራ አካ ነው)
ነው)

10. ስለሥራ አፈፃፀሙ ወቅታዊ ሪፖርት ያቀርባል፡፡


11. ከቅርብ ኃላፊው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡

የሥራ መደቡ መጠሪያ ፡ ታሊ ክለርክ

የሚገኝበት ቅ/
ቅ/ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ

ክፍሉ ፡ ኦፕሬሽን

ቀጥታ ተጠሪነቱ ፡ ለኦፕሬሽን አስተባባሪ

ዝርዘር የሥራ ተግባራት


1. ከኮንቴነር ለፍተሻ ወደ መጋዘን ሲገባ የጉምሩክ እንስፔክተር ሲሉን ሲቆርጥ ቆጥሮ መዝግቦ ይይዛል
የተቆጠረው እቃ ከቢል ኦፍ ሎዲንግ (Bill of lading) ጋር አመሳክሮ እኩል መሆኑን ያረጋግጣል፡፡

2. በቆጠራ የተገኘ ዕቃ ከ ‘bill of lading’


lading’ ጋር ካለው ቁጥር ልዩነት ካለው CFS Aea ከሆነ ለእስታፊንግ/
ለእስታፊንግ/
አንስታፊንግ ኦፊሰር ያሳውቃል፡፡ ወደ መጋዘን ከሆነ ደግሞ ለመጋዘን ኃላፊ ያሳውቃል፡፡

3. ከኮንቴነር የሚወጣ ዕቃ በማሽን ወይም በሰው ኃይል ለማውጣት አስቸጋሪ ሆኖ ካገኘ ወዲያው
ለቅርብ ኃላፊው ያሳውቃል፡፡

4. ታሊ ሸት (Tally sheet) ያዘጋጃል፡፡

5. ዕቃው ወጥቶ የተጠናቀቀ ኮንቴነር በ‘stacking form’


form’ መሠረት ለባዶ ኮንቴነር ኦፕሬሽን ሠራተኛ
ያስተላልፋል፡፡

6. ባዶ ኮንቴነር ከ CFS ወይም ከመጋዘን ስፍራ ወደ ባዶ ኮንቴነር ተርሚናል እንዲጓጓዝ ያደርጋል፡፡

7. ስለ ሥራ አፈፃፀም ወቅታዊ ሪፖርት አዘጋጅቶ ያቀርባል፡፡

8. ከኃላፊው የሚሰጡትን ሌሎች ተጨማሪ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

የሥራ መደቡ መጠሪያ ፡ የፎርክሊፍት ኦፕሬተር (2.5-6 ቶን)

የሚገኝበት ቅ/
ቅ/ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ

ክፍሉ ፡ ኦፕሬሽን

ቀጥታ ተጠሪነቱ ፡ ለኦፕሬሽን አስተባባሪ

ዝርዝር የሥራ ተግባራት

1. የተሰጡትን የደህንነት መመሪያዎች ማክበርና መጠበቅ፣ የኦፕሬሽንና ጥገና ማኑዋል በጥንቃቄ


ማንበብና የሚያንቀሳቅሰውን ማሽን ብቃቱን ማረጋገጥ፡፡
2. የፎርክሊፍት ኦፕሬተር ክብደት የማንሳት አቅም የሚያሳየውን መሳሪያ በመጠቀም አደጋ
የሚያስከትልና ከአቅም በላይ አለመሆኑን በመረዳት ጥንቃቄ ማድረግ፡፡
3. የስራ ቦታው በቂ መንቀሳቀሻ ያለው መሆኑንና ከሰዎች ወይም ህይወት ካላቸው እንስሳት
የፀዳ እንዲሁም አደናቃፊ ነገሮች አለመኖራቸውን ማረጋገጥ አለበት፡፡
4. የፎርክሊፍት ኦፕሬተሩ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ለእይታ የሚጋርዱ ሁኔታዎች ወይም
የሠው እንቅስቃሴ በሚበዛበት አካባቢ በሚሠራበት ጊዜ ምልክት የሚሠጡትን ረዳቶች
መጠቀም እና በረዳቱ የሚሰጡትን ምልክቶች በሚገባ መገንዘብና መግባባቱን እርግጠኛ መሆን
አለበት፡፡
5. በድርጅቱ የሚወጡ የደህንነት ህጎችንና ሌሎች ደንቦችን ማክበር፡፡
6. በየዕለቱ የማሽኑን ሴፍቲና ደህንነት ማረጋገጥ አለበት፣ ለዚሁ ሥራ የተዘጋጀውን ቼክሊስት
መሙላት አለበት፡፡
7. የፎርክሊፍት ኦፕሬተር ከሚመለከተው ክፍል በሚሰጠው የሥራ ትዕዛዝ ብቻ መሥራት
ይኖርበታል፡፡
8. ማሽኑን በየጊዜውና አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ ማፅዳት፣ንፅህናውን መጠበቅ አለበት፡፡
9. የፎርክሊፍት ኦፕሬተሩ የሚጠቀምበትን ፎርክሊፍት ወይም ሌላ መሣሪያ ስራውን ሲያጠናቅቅ
ወይም በማንኛውም ጊዜ ሁሉ ሲያቆም ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እና በጥንቃቄ ማቆም
ይጠበቅበታል፡፡
10. ለሥራ አፈፃፀም ወቅታዊ ሪፖርት ያቀርባል፡፡
11. ከኃላፊ የሚሰጡት ተጨማሪ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

የስራ መደቡ መጠሪያ ፡ የሪች ስታከር ኦፕሬተር

የሚገኝበት ቅ/
ቅ/ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ

ክፍሉ ፡ ኦፕሬሽን

ቀጥታ ተጠሪነት ፡ ለኦፕሬሽን አስተባባሪ

ዝርዝር ተግባርና ኃላፊነት

1. የተሠጠውን ሪች ስታከር በአግባቡና በጥንቃቄ ከንብረት ውድመትና የህይወት አደጋ በመጠበቅ


በአግባቡ ይይዛል፡፡

2. የማሽኑን የጥገናና የቅድመ ጥንቃቄ ማንዋል በተገቢው ሁኔታ በማንበብ ማሽኑን መጠቀም
ይኖርበታል፡፡

3. ማንኛውንም ካርጎ ከመጫንና ከማውረድ በፊት የክብደት ማንዋል (Loading chart) በተገቢው
ሁኔት ማወቅና በሚያዘው መሠረት እንደ ስራው አይነት ይሠራል፡፡
4. ኦኘሬተሩ በስራ አካባቢ ማሽኑን በሚጠቀምበት ወቅት ሠዎች፣ ማሽኖችንና ሌሎች ለአደጋ
የሚዳርጉ ነገሮች አለመኖሩን ማረጋገጥና ጥንቃቄ በመውሰድ ይሠራል፡፡

5. ኦኘሬተሩ በወደቡ ውስጥ በስራ ላይ በቀላሉ ለእይታ የሚያሰቸግሩ ቦታዎች ላይ በሚሠራበት ወቅት
ሌላ ከሥራው ጋር ግንኙነት ያለው ሰው በሚያመላክተው መሠረት ማሽኑን እና ማንኛውንም
ንብረት ከአደጋ በመጠበቅ ይሠራል፡፡

6. ሁሉንም የትራክ ደህንነት ምልክቶችና ህጐችን ጠንቅቆ ማወቅና መተግበር አለበት፡፡

7. በሚጭንበት ወይም በሚያራግፍበት ጊዜ የዕቃውን (ኮንቴነር)


ኮንቴነር) እና ጭነት የሚጭን ተሽከርካሪ
ደህንነት መጠበቅ ይኖርበታል፡፡

8. ኮንቴነሮች በአግባቡ (standard) በጠበቀ መልኩ መደርደር እና በማሽኑ እንዳይጋጩ ጥንቀቄ ማድረግ
አለበት፡፡

9. ኦፕሬተሩ በተርሚናል ውስጥ በተገቢው ፍጥነት እና በጥንቃቄ ብቻ ማሽከርከር አለበት፡፡

10. ኦኘሬተሩ ወደ ስራ ከመግባቱ በፊት የቅድመ ጥንቃቄ እይታ (Inspection) እና ስራውን ካጠናቀቀ
በኋላ በቼክ ሊስት ላይ ያለውን ሁኔታ በማስፈር ሪፖርት ያደርጋል፡፡

11. የተሠጠውን ሪች ስታከር በጽዳት መያዝ አለበት፡፡

12. ማሽኑን በማንኛውም ጊዜ ለአደጋ በማያጋልጠው ቦታ ላይ ማቆም አለበት፡፡

13. ኦፕሬተሩ ከሚመለከተው ክፍል በሚሰጠው የሥራ ትዕዛዝ ብቻ ይሰራል፡፡

14. የሥራ አፈፃፀም ወቅታዊ ሪፖርት ያቀርባል፡፡

15. ከኃላፊው የሚሰጡ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡


የስራ መደቡ መጠሪያ ፡ የፎርክሊፍት ኦኘሬተር (7-10 ቶን)

የሚገኝበት ቅ/
ቅ/ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ

ክፍሉ ፡ ኦፕሬሽን

ቀጥታ ተጠሪነት ፡ ለኦፕሬሽን አስተባባሪ

ዝርዝር ተግባራት

1.የተሰጡትን የደህንነት መመሪያዎች ማክበርና መጠበቅ፣ የኦፕሬሽንና ጥገና ማኑዋል በጥንቃቄ


ማንበብና የሚያንቀሳቅሰውን ማሽን ብቃቱን ማረጋገጥ፡፡

1. የፎርክሊፍት ኦፕሬተር ክብደት የማንሳት አቅም የሚያሳየውን መሳሪያ በመጠቀም አደጋ


የሚያስከትልና ከአቅም በላይ አለመሆኑን በመረዳት ጥንቃቄ ማድረግ፡፡
2. የስራ ቦታው በቂ መንቀሳቀሻ ያለው መሆኑንና ከሰዎች ወይም ህይወት ካላቸው እንስሳት የፀዳ
እንዲሁም አደናቃፊ ነገሮች አለመኖራቸውን ማረጋገጥ አለበት፡፡
3. የፎርክሊፍት ኦፕሬተሩ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ለእይታ የሚጋርዱ ሁኔታዎች ወይም
የሠው እንቅስቃሴ በሚበዛበት አካባቢ በሚሠራበት ጊዜ ምልክት የሚሠጡትን ረዳቶች
መጠቀም እና በረዳቱ የሚሰጡትን ምልክቶች በሚገባ መገንዘብና መግባባቱን እርግጠኛ መሆን
አለበት፡፡
4. በድርጅቱ የሚወጡ የደህንነት ህጎችንና ሌሎች ደንቦችን ማክበር፡፡
5. በየዕለቱ የማሽኑን ሴፍቲና ደህንነት ማረጋገጥ አለበት፣ ለዚሁ ሥራ የተዘጋጀውን ቼክሊስት
መሙላት አለበት፡፡
6. የፎርክሊፍት ኦፕሬተር ከሚመለከተው ክፍል በሚሰጠው የሥራ ትዕዛዝ ብቻ መሥራት
ይኖርበታል፡፡
7. ማሽኑን በየጊዜውና አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ ማፅዳት፣ ንፅህናውን መጠበቅ አለበት፡፡
8. የፎርክሊፍት ኦፕሬተሩ የሚጠቀምበትን ፎርክሊፍት ወይም ሌላ መሣሪያ ስራውን ሲያጠናቅቅ
ወይም በማንኛውም ጊዜ ሁሉ ሲያቆም ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እና በጥንቃቄ ማቆም
ይጠበቅበታል፡፡
9. ለሥራ አፈፃፀም ወቅታዊ ሪፖርት ያቀርባል፡፡
10. ከኃላፊ የሚሰጡት ተጨማሪ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

የስራ መደቡ መጠሪያ ፡ አሰስመንትና ክሊራንስ ኦፊሰር

የሚገኝበት ቅ/
ቅ/ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት

ክፍሉ ፡ ኬዝ ቲም

ቀጥታ ተጠሪነት ፡ ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ

ዝርዝር ተግባርና ኃላፊነት

1. በደንበኞች የሚቀርቡ ሰነዶች ትክክለኛና የተሟሉ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡


2. የጉምሩክ ዲክላሬሲዮን በ Asycuda++ ሲስተም በመጠቀም መረጃዎችን ይሞላል፡፡
3. የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ከዋጋና ከታሪፍ አንጻር ሰነዶችን በመመርመር ማስላትና ደንበኛ ክፍያ
እንዲፈጽም ያደርጋል፡፡
4. የወደብ አገልግሎት ክፍያ መተመንና ደንበኞች ክፍያውን እንዲፈጽሙ ያሳውቃል፡፡
5. ደንበኛው የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ እንዲሁም የወደብ አገልግሎት ክፍያ እንደፈጸመ ሰነዶችን
ወደ ጉምሩክ ጣቢያ እንዲላክ ያደርጋል፡፡
6. ሰነዱን ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ ገቢ በማድረግ የትራንዚት ፈቃድ ያገኛል፡፡
7. የትራንዚት ፈቃዱን ኮፒ ለጅቡቲ ቅ/
ቅ/ጽ/ቤት በፋክስ ወይም ኢሜል መላክና መድረሱን
ይከታተላል፡፡ለሚዘጋጀው ኦፕሬሽን ከዋናው መስሪያ ቤት የኦፕሬሽን ቁጥር ይቀበላል፣በሰነዱ
ይሞላል፡፡ለጅቡቲ የተላውን ሰነድ ከፐፒ ለዋናወ 3 መስሪያ ቤት ይልካል፡፡
8. የተቆጣጣሪ ባለስልጣናት ፍቃድ ከተገኘ በኃላ የወጪ ዲክላሬሲዮን በማዘጋጀት በመተመን
ሰነዱን ለጉምሩክ ኢንስፔክተር በመስጠት እንዲፈተሽ እና ዕቃው እንዲታሸግ ያደርጋል፡፡
9. ወጪ ዕቃ የጫነው መኪና ወደ ወደብ እንዲጓዝ የዕቃ መልቀቂያ ፍቃድ ከጉምሩክ በመቀበል
ለአጓጓዥ ይሰጣል፡፡
10. የዲስፓች ሪፖርት በማዘጋጀት ለጅቡቲ ጽ/
ጽ/ቤት ይልካል፡፡ኮፒ ለዋናው መስሪያ ቤት ይልካል፡፤
11. ከዋናው መ/
መ/ቤት የተላኩ ሰነዶች ጅቡቲ ቅ/
ቅ/ጽ/ቤት መድረሳቸውን የጉምሩክና የወደብ ፎርማሊቲ
መጠናቀቁን መከታተል ችግር ካጋጠመ ከሚመለከታቸዉ ጋር በመነጋገር መፍትሄ እንዲያገኝ
ያደርጋል፡፡
12. የደንበኞች ጭነት ከወደብ መነሳቱን መከታተልና ለደንበኞች ያሳውቃል፡፡
13. የገቢም ሆነ የወጪ ዕቃዎች ሰነዶች ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ያለውን የክሊራንስ ሂደት
በመፈፀም ኦፕሬሽኑ እንዲዘጋ ያደርጋል፡፡
14. ከጉምሩክ ተጓዳኝ መ/
መ/ቤቶች ለሚጠየቁ መጠይቆች ምላሽ ይሰጣል፡፡
15. ከወደብ የመጣው ገቢ ዕቃ መቅረጫ ጣቢያ እንደደረሰ ኦርጅናል ሰነድ ጉምሩክ ገቢ በማድረግ
እንዲፈተሽ አድርጐ የዕቃ መልቀቂያ ይቀበላል፡፡
16. የመጋዘን ክፍያ በማስላት ደንበኛው እንደከፈለ ዕቃው ከጉምሩክ ክልል እንዲወጣ ያደርጋል፡፡
17. ዕለታዊ፣ ሣምንታዊ፣ወርሃዊና ዓመታዊ ሪፖርት ያቀርባል፡፡
18. ከቅርብ ኃላፊው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡

የስራ መደቡ መጠሪያ ፡ ከስተምስ ቦንድ ሪኮንስሌሽንና የኮንቴይነር ክትትል ኦፊሰር

የሚገኝበት ቅ/
ቅ/ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት

ክፍሉ ፡ ኦፕሬሽን

ቀጥታ ተጠሪነቱ ፡ ለኦፕሬሽን አስተባባሪ


ዝርዝር ተግባርና ኃላፊነት

1. በየእለቱ ሎዲንግ ሪፖርት በመከታተል ለወደቡ ከጅቡቲ የተጫኑ ኮንቴይነሮችን መረጃ ይቀበላል፡፡
ለመመለከታቸው አካላት ለስራ ዝግጁነት እንዲያገለግል መረጃ ያስተላልፋል
2. ከዋናው መ/
መ/ቤት ለደረቅ ወደብ የሚላኩትን ኢንተርቼንጅ /ባዶ ኮንቴነሮች ወደ ጅቡቲ ወደብ የተመለሱበት
ሰነድ/
ሰነድ/ እና ጋላፊ የሚገኘው የጉምሩክ ማስተባበሪያ ጽ/
ጽ/ቤት ኮንቴነሮች ከአገር የወጡ ለመሆናቸው
የሰጠውን ማረጋገጫ መሠረት በማድረግ የኮንቴነሮቹን ዝርዝር መረጃዎች መዝግቦ ይይዛል፡፡
3. በጅቡቲ ወደብ ላይ መዘግየት ያጋጠማቸውን ደንበኞች ወይንም ልዩ እገዛ የሚፈልጉ በማንፋክቸሪንግ ዘረፍ
የተሰማሩ ባለሀብቶችን እቃቸው እንዲጫንላቸው ልዩ ክትትል ያደርጋል፣ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ካለ
ለሀላፊው ያቀርባል፡፡
4. አደጋ የደረሰባቸው ኮንቴይነሮችን በተመለከተ የካሳ ክፍያ እና መሰል ጉዳዮች እንዲጠናቀ ከዋናው መስሪያ
ቤት ጋር በመነጋገር ያስፈፅማል፡፡
5. ደንበኛው ወስዶ ያልመለሳቸውን ባዶ ኮንቴይነሮች በመከታተል እንዲመለሱ ያደርጋል፡፡ መልስ ከደንበኛው
የማያገኝ ከሆነ ለህግ ክፍል ደብዳቤ በመፃፍ ጉዳዩን ይከታተላል፡፡
6. ለኮምቦልቻ እና አካባቢው የሚገኙ ላኪዎች የባዶ ኮንቴይነር ጥያቄ ሲቀርቡ አስፈላጊው ሰነድ መሟላቱን
በማረጋገጥ ይሰጣል፡፡አስፈላጊውን መረጃ ይይዛል፡፡
7. የውጪ ፍተሻ ለተፈቀደላቸው ደንበኞች ጉምሩክ በግልባጭ በሚያሳውቁን መሠረት ከደንበኛው አስፈላጊ
ሠነዶች በመቀበል እቃው ወደ መጋዘኑ ቀጥታ እንዲሄድ ለዋናው መስሪያ ቤት ባዶ ኮንቴይነር ከወደቡ
ከወጣ በኃላ ጅቡቲ መድረሱን ይከታተላል ያልደረሱ ካሉ ወዲያውኑ ለቅርብ ኃላፊው ሪፖርት ያደርጋል፡፡
8. ከጉምሩክ በኩል ለሚቀርቡ ከተመላሽ ኮንቴይነሮች ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ተቀብሎ ያስተናግዳል'
ያስተናግዳል'
ከአቅም በላይ የሆኑ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ለቅርብ አለቃው ያሳውቃል፡፡
9. ስለሥራው አፈፃፀም ወቅታዊ ሪፖርት ያቀርባል፡፡
10. ከኃላፊ የሚሰጠውን ተጨማሪ ሥራዎች ያናውናል፡፡

የስራ መደቡ መጠሪያ ፡ ጁኒየርዴሊቨሪ ኦርደር ኦፊሰር

የሚገኝበት ቅ/
ቅ/ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት

ክፍሉ ፡ ኦፕሬሽን

ቀጥታ ተጠሪነቱ ፡ ለኦፕሬሽን አስተባባሪ

ዝርዝር ተግባርና ኃላፊነት


1. የዕቃ መልቀቂያ የሚጠይቁ አስመጭዎች/
አስመጭዎች/ወኪሎች የሚያቀርባቸውን ሰነዶች የተሟሉና ሕጋዊ
መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡
2. ሰነዶች መሟላታቸውን በማረጋገጥ የዕቃ መልቀቂያ (Delivery order) አዘጋጅቶና
የሚመለከተው ኃላፊ እንዲፈርም በማድረግ ለሚመለከታቸው አስመጪዎች/
አስመጪዎች/ወኪሎች ይሰጣል፡፡
3. Dangerous Cargo ሰነድ ላይ በሚቀርበው መሰረት ለሂሳብ ክፍል በስሌቱ መሰረት እንዲከናወን
መረጃ ይሰጣል፡፡
4. Dangerous Cargo በሚፈተሸበት ጊዜ ለቀን ሰራተኞች አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ
ኮንቴይነሩ ከመከፈቱ በፈት ለታሊ ማን በቅድሚያ መረጃ ይሰጣል፡፡
5. ዕቃቸውን ከደረቅ ወደቡ በኮንቴነር መውሰድ የሚፈልጉ ደንበኞች ሲጠይቁ የተሟሉ ሰነዶች
መቅረባቸውን በማጣራትና የሚፈለግባቸውን የኮንቴነር ዲፖዚት እንዲያስይዙ በማድረግ ወይም
ያለክፍያ እንዲወሰዱ ከሚመለከታቸዉ ኃላፊዎች ደብዳቤ ከተፃፈ ተቀብሎ የኮንቴነር መልቀቂያ
(Container release) ይሰጣል፡፡
6. ዕቃቸውን (Unstuff) በማድረግ ያለኮንቴነር ለመውሰድ ለሚፈልጉ ደንበኞች የዕቃ መልቀቂያ
D/O ከመስጠቱ በፊት ከክፍያ ነፃ የሆነው ጊዜ (grace period) ያበቃ (ያለፈ)
ያለፈ) መሆኑን አለማለቁን
አረጋግጦ ለደንበኞች በማሳወቅ ዲመሬጅ እንዲከፍሉ ያደርጋል፡፡
7. ለፋይል ቀሪ የሚደረጉ የዕቃ መልቀቂያ D/O ሰነዶች አመች በሆነ ቦታ በጥንቃቄ እንዲቀመጡ
ያደርጋል፡፡ በሚመለከታቸው ኃላፊዎች ሰነድ ሲጠየቅ ያቀርባል፡፡
8. ስለ ሥራ አፈፃፀሙ ወቅታዊ ሪፖርቶችን አዘጋጅቶ ለቅርብ አለቃውና ለሚመለከታቸው ሁሉ
ያቀርባል፡፡
9. ስለ ሥራ አፈጻጸሙ ወቅታዊ ሪፖርት ያቀርባል፡፡
10. ከቅርብ ኃላፊው የሚሠጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡
የስራ መደቡ መጠሪያ ፡ የበር ቁጥጥር ኦፊሰር

የሚገኝበት ቅ/
ቅ/ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት

ክፍሉ ፡ ኦፕሬሽን

ቀጥታ ተጠሪነቱ ፡ ለኦፕሬሽን አስተባባሪ

ዝርዝር የሥራ ተግባር

1. የወደብ በር ቁጥጥር ሠራተኛ የመድረሻ ወደብ ጉምሩክ ትራንዚት ኦፊሰር በመንገድ ወረቀቱ (Way bill)
bill) ላይ
የትራንዚት ማብቂያ መግለጫ ፊርማና ማህተም ማኖሩን አረጋግጦና ተቀብሎ በተጨማሪም ሌሎች ተዛማች
ሠነዶችን ከሹፌሩ በመቀበል ቀድሞ ከደረሰው የገቢ ዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ ጋር በማገናዘብና በማመሣከር፣
የኮንቴይነር ውጫዊ አካል በመፈተሽ የመግቢያ ፍቃድ (Gate pass)
pass) እና የኮንቴይነር መረካከቢያ ቅፅ (EIR)
EIR)
በማዘጋጀትና ወደ ወደብ ተርሚናል እንዲገባ ያደርጋል፡፡
2. የበር ቁጥጥር ሰራተኛው ያዘጋጀውን ‘Gate pass’ እና ‘EIR’ ፓድ ላይ ከቀረው በሥተቀር ያሉትን ከአባሪ ሰነዶች
ጋር በማያያዝ ለኦፕሬሽን ዶክመንቴሽን ኦፊሰርና ለጭነትና ሰነድ ክትል ኦፊሰር እንዲደርስ ያደርጋል፡፡

3. ገቢ ጭነቶችን ጭኖ የገባው አሽከርካሪ ጭነቱን አራግፎ ሲመለስ የመግቢያ ፍቃዱንና የአገልግሎት መከታተያ ቅፁን
በመቀበል ሠዓቱን በመሙላት በተቀመጠለት ጊዜ ለማስተናገዱ በማረጋገጥ እንዲወጣ ያደርጋል፡፡

4. ጭነት ለመጫን ወደ ወደብ የሚገቡትን ተሽከርካሪዎች የበር ቁጥጥር ሠራኛው ከተርሚናል ኦፕሽን ክፍል በተላከለት
ትዕዛዝ መሠረት ተሽከርካሪዎቹ ባዶና ለጭነት የተዘጋጁ መሆናቸውን በማረጋገጥ እንደቅድመ ተከተላቸው ‘Gate
pass’ በማዘጋጀትና የሚጭኑበትን ቦታ በሠነድ ላይ በመጥቀስ ወደ ወደብ ተርሚናል እንዲገቡ ያደርጋል፡፡

5. ጭነት ከወደቡ ጭነው ለመውጣት የሚመጡ ተሽከርካሪዎች የበር ቁጥጥር ሠራተኛው የወደብ አገልግሎት ክፍያ
የተፈፀመባቸው ለመሆኑ የክፍያ ደረሰኝ ወይም ማረጋገጫ ሲደርሠው በማገናዘብ፣ በማመሣከርና የኮንቴይነሩን
ውጫዊ አካል በመፈተሽ ‘FULL EIR OUT’ በማዘጋጀት ከሹፌሩ ጋር በመተማመንና በመፈራረም፣ የጉምሩክ
ኢንስፔክተር መኖሩን በማረጋገጥ በጋራ ጭነቱ እንዲወጣ በማድረግ ያዘጋጀውን ‘FULL EIR OUT’
ለሚመለከተው ሰራተኛ ያስተላልፋል፡፡

6. ገቢ ባዶ ኮንቴይነር ወደ ወደብ ሲመጣ የበር ቁጥጥር ሰራተኛው አሽከርካሪው በመጣበት ቅድመ ተከተል መሰረት ቀድሞ
በወደቡ የተስተናገደ ከሆነ ሙሉ ኮንቴይነሩን ጭኖ ሲወጣ የተሰጠው ‘FULL EIR OUT’ ያለው መሆኑን
ያረጋግጣል፣ ቀድሞ በወደቡ ያልተስተናገደ ከሆነ ከመርከብ ወኪል ጥያቄ የቀረበና በወደቡ እንዲስተናገድ የተፈቀደ
መሆኑን በማረጋገጥ የባዶ ኮንቴይነሩን ውስጣዊና ውጫዊ አካል በመፈተሽ ‘GATE PASS’ እና ‘EMPTY IN
EIR’ በማዘጋጀትና ከአሽከርካሪው ጋር በመተማመንና በመፈራረም ኮንቴይነሩን የሚያራግፍበትን ቦታ በሰነድ
ላይ በመጥቀስ ወደ ወደብ ተርሚናል እንዲገባ ያደርጋል፡፡

7. በፓዱ ላይ ቀሪ ከሚሆነው በስተቀር ያሉ ‘GATE PASS’ እና ‘EIR’ ¢ú c’Ê‹ KT>SKŸ}¨< W^}— ¾}LŸuƒ”
W¯ƒ uSS<Lƒ Áe}LMóM::

8. ከወደቡ ለሚወጡ ወጪ ባዶ ኮንቴይነሮች ተገቢውን ሰነድ ማሟላታቸውን በማረጋገጥ እና የኮንቴይነሩን ውስጣዊና


ውጫዊ አካል በመፈተሽ ‘EMPTY OUT EIR’
EIR’ በማዘጋጀት እንዲወጡ ያደርጋል፡፡

9. የክፍያ ሰነድ ሥህተት ሲኖር ወደ ፋይናንስ ክፍል በመመለስ እንዲስተካከል ያደርጋል፡፡

10. ጭነቶች በተሣሣተ መንገድ ከወደቡ እንዳይወጡ ጥብቅ ቁጥጥርና ፍተሻ ያደርጋል፡፡

11. በተለያየ ምክንያት ጭነት ከጫኑ በኋላ ወደቡ ግቢ ውስጥ የሚያድሩ ጭነቶች ተጨማሪ ክፍያ እንዲከፍሉ ያደርጋል፣
ሣይከፍሉ እንዳይወጡ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡፡

12. የገቢና ወጪ ጭነቶች መረጃ መዝግቦ ይይዛል፡፡

13. ዕለታዊ፣ ሣምንታዊ፣ ወርሃዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመትና ዓመታዊ ሪፖርት ያቀርባል፡፡

14. ከቅርብ ኃላፊው የሚሰጡትን ሌሎችት ተግባራትን ያከናውናል፡፡


የሥራ መደቡ መጠሪያ ፡ ጁኒየር የኦፕሬሽን ዶክመንቴሽን ኦፊሰር

የሚገኝበት ቅ/
ቅ/ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት

ክፍሉ ፡ ኦፕሬሽን

ቀጥታ ተጠሪነቱ ፡ ለኦፕሬሽን አስተባባሪ

ዝርዝር ተግባራት

1. ወደ ኦፕሬሽን ዋና ክፍል የሚመጡለትን የኦፕሬሽን ሠነዶች ተገቢውን የመረካከቢያ ሠነድ በመሙላት


ይረከባል፡፡

2. የተረከባቸውን ሠነዶች ይመዘግባል፣ ያደራጃል፡፡

3. ወደ ግልፅና ዝግ መጋዘን የገቡ ጭነቶች መረካከቢያ ሰነድ (GOODS RECEIPT DOCUMENT) ከመጋዘን
ሠራተኛው ሲደርሰው መዝግቦ ይረከባል፡፡

4. ከኮንቴነር ለሚወጡና ወደ ኮንቴነር ለሚገቡ ጭነቶች የሚዘጋጀውን ታሊ ሽት ቅጂ ከታሊማን ሠራተኛው


ሲደርሰው ለቢሊንግ ግብዓት እንዲሆን ቀድሞ ከያዘው ሰነዶች ጋር በማቀናጀት እንዲያያዝ ያደርጋል፡፡

5. ከደንበኞች የሚቀርቡ የዕቃ መልቀቂያ ጥያቄና ክሊራንስ ሠነዶች ሲቀርብለት የተሟላ መሆኑን በማረጋገጥ
ሠዓት መዝግቦ በመረከብ ቀድሞ ከያዛቸው ሠነዶች ጋር በማያያዝ ለቢሊንግ ዝግጅት ያስተላልፋል፡፡

6. ከደንበኞች የሚቀርቡ ልዩ ልዩ ኦፕሬሽናል አገልግሎቶች ጥያቄ በመቀበል የጉምሩክ መልቀቂያ እና


ኮንቴይነርና እቃ መልቀቂያ መሟላቱን በማረጋገጥ ተገቢውን GRR (GOODS RECEIVING
REQUEST) እንዲሞላ ያደርጋል፡፡

7. አገልግሎት የተጠየቀበትን SSR አገልግሎት ማግኘቱን በማረጋገጥ አንድ ኮፒ ከ GRR ሠነድ ጋር


እንዲያያዝ ያደርጋል፡፡

8. በየእለቱ ለቢሊንግ የተላለፉ ሰነዶችን መዝግቦ ይይዛል፡፡


9. እለታዊና ሣምንታዊ ክንውን ሪፖርቶችን ያዘጋጃል፡፡

10. በክፍሉ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ አሠራሮችን በመቀየስና በመተግበር ሂደት ጉልህ
ተሳትፎ ያደርጋል፡፡

11. ከቅርብ ኃላፊው የሚሰጡ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡

የስራ መደቡ መጠሪያ ፡ ጁኒየር ኦፕሬሽን ኦፊሰር

የሚገኝበት መምሪያ ፡ ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት

ክፍሉ ፡ ኦፕሬሽን

ቀጥታ ተጠሪነቱ ፡ ለኦፕሬሽን አስተባባሪ

ዝርዝር ተግባርና ኃላፊነት

1. የተርሚናል ኦፕሬሽን ቦታ አጠቃቀም ዕቅድ ያዘጋጃል(


ያዘጋጃል(የጭነት ማቀነባበሪያ ስፍራ(CFS)፤የማሽን
ስፍራ(CFS)፤የማሽን
ማንቀሳቀሻና መተላለፊያ፤ ለሙሉ፤ ለባዶ ፤ለአደገኛ እቃዎች ማስቀመጫ ቦታ በመለየት ያዘጋጃል)
ያዘጋጃል) ፡፡
2. ወደ ወደቡ የሚመጡ ኮንቴነሮችን መረጃ ቀድሞ በማደረጀት በወደቡ ውስጥ ለኮንቴራይዝድ
ካርጎዎችን የማከማቻ ቦታ (Bay Plan) ያዘጋጃል፡፡
3. የኮነቴነር እንቅስቃሴን ለመቀነስ በሚያስችል መልኩ ኮንቴነሮች በማስጫኛ ሰነዳቸው እና በአስመጪ
ተለይተው እንዲቀመጡና እንዲደረደሩ ያደርጋል
4. ወደ ወደቡ የሚገቡ ኮንቴነሮችን በቀጥታ በተዘጋጀላቸው ቦታ ተገቢው የማስቀመጫ ቦታ መለያ
ተሰጥቷቸው እንዲቀመጡ ያደርጋል መረጃውንም ይይዛል፡፡
5. ኮነቴነሮች የተቀመጡበትን መለያ ቦታ(
ቦታ(ሎኬሽን)
ሎኬሽን) መረጃ ለውጥ ሲኖር ከኮነቴነር ኦፕሬሽን ኦፊሰሩ
በመቀበል መረጃውን ወቅታዊ ያደርጋል
6. ማናቸውም የወደቡን ፎረማሊቴ አጠናቀው ከወደብ የሚወጡ ኮነቴነሮች የተቀመጡበትን መለያ
ቦታ(
ቦታ(ሎኬሽን)
ሎኬሽን) በማስጫኛ ትእዛዝ ላይ በመሙላት ያስተላልፋል
7. በመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ስርዓት ወደ ወደቡ የመጡ ማናቸውም የገቢ ዕቃዎች እና ከሀገር
የሚወጡ ዕቃዎችና ባዶ ኮንቴይነሮች መረጃ በአግባቡ ይይዛል፡፡
8. ወቅቱን የጠበቀ የስራ ሪፖርት ለቅርብ ሀላፊው ያቀርባል
9. በየእለቱ በቡድን ስራን ይገመግማል፡፡
10. የክፍሉን መረጃዎችን ያደራጃል::
ያደራጃል::
11. ከቅርብ ኃላፊው የሚሰጡ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
የሥራ መደቡ መጠሪያ ፡ የመጋዘን ሰራተኛ

የሚገኝበት ቅ/
ቅ/ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት

ክፍሉ ፡ ኦፕሬሽን

ቀጥታ ተጠሪነቱ ፡ ለኦፕሬሽን አስተባባሪ

ዝርዝር ተግባራት

1. ከመጋዘን ኃላፊው በሚሰጠው ትዕዛዝ መሰረት እቃዎች በተገቢውና ተለይቶ በተቀመጠላቸው ቦታ


እንዲቀመጡ ያደርጋል፡፡

2. በገቢ ዕቃ መረካከቢያ (Goods Receiving Document) ሰነድ ያዘጋጃል፡፡ በዚህም መሰረት የዕቃ ቆጠራ
ያደርጋል፣ ጉድለት ካለበት ለመጋዘን ኃላፊ ሪፖርት ያደርጋል፡፡

3. የገቢ እቃ መረካከቢያ ሰነድ (Goods Receiving Document) ኦሪጅናሉን ለአጓጓዥ አንድ ኮፒ ለጉምሩክ እና
አንድ ኮፒ ለኦፕሬሽን መረጃ ክፍል ያሰራጫል፡፡

4. ከበር ቁጥጥር ተሞልቶ ወደ ሥራ ክፍሉ የተላለፉትን የአገልግሎት መከታተያ ቅፅ ላይ አገልግሎት መስጠት


የተጀመረበትን አገልግሎት ተሰጥቶ ያለቀበትን ሰዓት በመሙላት ደንበኛውን ያሰናብታል፡፡

5. ርክክቡ የተፈፀመባቸው ዕቃዎች ‘Tag’


Tag’ እና ‘Location’
Location’ እንዲሰጣቸው ያደርጋል፡፡

6. በጭነት መለያ ፓድ ውስጥ ተገቢው መረጃ ማለትም የአስመጪው ስም፣ የዕቃው ብዛት፣ ዲክላራሲዮን እና
ክብደት ያሰፍራል፡፡

7. ርክክብ የተፈፀመባቸው ሰነዶች በአግባቡ ያስቀምጣል፣ መዝግቦ ይይዛል፡፡

8. በጉምሩክ ጥያቄ ለፍተሻ የተፈለጉ እቃዎችን አስፈላጊ የሆኑ የሰው ኃይልና መሳሪያ በመያዝ ይከፍታል፡፡
ፍተሻው ከተጠናቀቀ በኋላም ዕቃው በነበረበት ሁኔታ እንዲታሸጉ ያደርጋል፡፡

9. ደንበኛው ለተሰጠው አገልግሎት ተገቢው ክፍያ እንዲፈጽሙ በእቃ መረከቢያ ሰነድ ላይ የተፈተሸውን ጭነት
ብዛት እና ክብደት ይሞላል፡፡

10. ከቅርብ ኃላፊው የሚሰጡ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡

የሥራ መደቡ መጠሪያ ፡ ጁኒየር አይቲ ሰፖርት ኦፊሰር


የሚገኝበት ቅ/
ቅ/ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት

ክፍሉ ፡ ኦፕሬሽን

ቀጥታ ተጠሪነቱ ፡ ለቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ

1. የቅ/ጽ/ቤቱ ሠራተኞች የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሁም በቂ የሆነ የመረጃ ልውውጥ


እንዲኖራቸው ማድረግ፣

2. በቅ/ጽ/ቤቱ ውስጥ ያሉትን ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ ስካነር በኔትወርክ በማገናኘት ሥራ


ላይ እንዲውሉ ማድረግ፣

3. በቅ/ጽ/ቤቱ የመረጃ ስረአት የማደራጀት የመረጃ ደህነነትን በመጠበቅና በመያዝ የመረጃ


ስህተት እንዳይኖር ማድረግ፡፡

4. ስራዎችን በፕሮሲጀር ማንዋል ሴፍቲው በተጠበቀ መልኩ ማከናወን፡፡

5. ፈጣን የኔትወርክ አገልግሎት እንዲኖር ከቴሌ ባለሙያዎች ጋር በመነጋገር የኮኔክሽን ሥራውን


ማመቻቸት፣

6. የ 'CTTS' ካርጎ ማኒፌስት ከ FTP (File Transfer Protocol) ወደ ኮምፒውተር መገልበጥና


የጅቡቲ የጭነት ሪፖርት (Loading Report) ከኢሜይል ወደ ኮምፒውተር መገልበጥ፡፡

7. የ 'CTTS' ካርጎ ማኒፌስት ዝርዝር የጭነት መግለጫ በማጣመር ወደ 'DPOIS' ሲስተም


በማስገባት ለመግቢያ (Gate Pass) ዝግጁ ማድረግና መረጃውን ለሚመለከታቸው ክፍሎች
ማሠራጨት፡፡

8. አዳዲስ ኮምፒውተሮችና ሌሎች የቢሮ ማሽኖች ሲኖሩ ከሲስተም ጋር በማገናኘት በተገቢው


ሁኔታ ሥራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ፡፡

9. የሥራ መጀመሪያ ሠዓቶች እንዳይባክኑ በየዕለቱ ግብዓቶችንና መረጃዎችን አስቀድሞ


በመያዝ ለስራ ዝግጁ መሆን፡፡

10. በ 'DPOIS' የኦፕሬሽን የሥራ ሂደት ውስጥ የሚፈፀሙ የመረጃ ስህተቶችን 'Amendment'
መስራት፡፡

11. ኮምፒውተሮች ችግር ሲገጥማቸው የ 'Maintenance' አገልግሎት መስጠት፣

12. የ 'DPOIS' ሲስተም 'stack' ሲያደርግ ወዲያውኑ መፍትሄ በመስጠት የኦፕሬሽን ሥራ


እንዳይስተጓጎል ማድረግ፡፡

13. የ 'DPOIS' ሲስተም ጉድለቶችን በመከታተል ለማስተካከያ የሚረዱ ግብአቶችን(ሃሳቦችን)


ማቅረብ

14. በቅ/ጽቤቱ የሚሰሩ ስራዎች በሲስተም የተደገፉ እንዲሆኑ እንዲሁም በ IT የተደገፈ የተጠናከረ

የመረጃ ስርአት እንዲኖር የበኩሉን ያደርጋል


15. IT ክፍል የሚሠሩ ሥራዎችንና መረጃዎችን በየዕለቱ፣ በየሣምንቱና በየወሩ ወቅታዊ በማድረግ
ለቅ/ጽ/ቤቱ ሪፖርት ማድረግ፡፡

16. ከቅርብ ኃላፊው የሚሰጡ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡

የሥራ መደቡ መጠሪያ ፡ የወደብ ሴፍቲና ሴኩሪቲ ሃላፊ

የሚገኝበት ቅ/
ቅ/ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት
ክፍሉ ፡ ኦፕሬሽን

ቀጥታ ተጠሪነቱ ፡ ለቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ

 የስራ ክፍሉን አመታዊ ወርሃዊና ሳመንታዊ እቅድ/አፈጻጸም ያዘጋጃል

 በስሩ ያሉ ሰራተኞችን "ቢኤስሲ" እቅድ ያዘጋጃል፤ ያስተባብራል፤ ይመራል


አፈጻጸማቸውንም ይገመግማል

 በወደቡ ውስጥ ሥራዎች በወደብ አስተዳደር መመሪያ፤ በሴፍቲና ሴኩሪቲ ማኑዋል


መሠረት መሰራታቸውን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ ያረጋግጣል

 በወደብ የሴፍቲና ሴኩሪቲ አልባሳትና ግብአቶችን ይለያል በወቅቱ እንዲሟላ ተገቢውን


ድጋፍና ክትትል ያደርጋል

 የድርጅቱና የደንበኞች አጠቃላይ ንብረት ከስርቆት፤ ከጉደለትና ከጉዳት በተጠበቀ መልኩ


አድንዲሆን ተገቢውን የደህንነት ክትትልና ቁጥጥር ስርአት ያደራጃል፤ ይመራል፤ ያስተባበራል
ይቆጣጠራል

 ከሴፍቲና ሴኩሪቲ ጋር የተያያዙ ግንዛቤ ማሰጨበጫ ስልጠናዎችን ይለያል፤ ስልጠናዎች


እንዲሰጡ ድጋፍና ክትትል በማደረግ ያስተባብራል

 በዜጎች ቻርተር መሰረት አገልግሎት እንዲሰጥ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል


ያደርጋል

 የሴፍቲ ምለክቶችና ማስጠነቃቂያዎች በተገቢው ስፍራቸው እንዲኖሩ ክትትል ያደረጋል


ያስተባበራል

 የወደቡ ደህንነት የተጠበቀ እንዲሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ይሰራል

 ወቅታዊ የሴፍቴና ሴኩሪቴ የስጋት ዳሰሳ ጥናት በማድረግ የተሻለ አሰራር እንዲሰፍን የበኩሉን
ያደርጋል

 ወቅታዊ የሴፍቲና ሴኩሪቲ ሪፖርቶችን ለሚመለከታቸው በወቅቱ ያስተላልፋል

 ከቅርብ ኃላፊው የሚሰጡ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፤

የሥራ መደቡ መጠሪያ ፡ የጥበቃ ሽፍት መሪ

የሚገኝበት ቅ/
ቅ/ጽ/ቤት ፡ ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት

ክፍሉ ፡ የወደብ ሴፍቲና ሴኩሪቲ


ቀጥታ ተጠሪነቱ ፡ ለወደብ ሴፍቲና ሴኩሪቲ ኃላፊ

ዝርዘር የሥራ ተግባራት

1. በተመደበበት ሽፍት የወደቡን የጥበቃ ሥራ በበላይነት ይመራል፣ ያስተባብራል፣ ይቆጣጠራል፡፡


2. ከቅርብ ኃላፊው ጋር በመተባበር በተመደበበት ሽፍት ተረኛ የጥበቃና ደህንነት ሠራተኞች በሙሉ
ተሟልተው መገኘታቸውን ያረጋግጣል፣ የተጓደለ ካለ በምትኩ እንደመደብ ያደርጋል፡፡
3. ለጥበቃ ሥራው አስፈላጊ የሆኑ ዕቃዎችና መሣሪያዎች በበቂ ሁኔታ መሟላታቸውን ያረጋግጣል፡፡
4. እርሱ በሚመራው ሽፍት የተመደቡት የጥበቃ ሠራተኞች ከአቅም በላይ ችግር ካልሆነ በስተቀር
የጥበቃ ዩኒፎርማቸውን አሟልተው በመልበስ በስራ ላይ መገኘታቸውን ያረጋግጣል፣ ይህ ሳይፈፀም
ከተገኘ ለቅርብ ኃላፊው በማሳወቅ ተገቢው እርምጃ እንዲወስድ ያደርጋል፡፡
5. ለጥበቃና ለወደብ ደህንነት አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ለቅርብ
ኃላፊው በማሳወቅ ተገቢው የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ ያደርጋል፡፡
6. ወደ ወደቡ የሚገቡም ሆነ ከወደቡ የሚወጡ ግለሰቦችም ሆነ ተሽከርካሪዎች በሚገባ ተፈትሸውና
ህጋዊነታቸው ተረጋግጦ መሆኑን ያረጋግጣል፣ ይቆጣጣራል፡፡
7. የዕለት ሁኔታ መዝግቦ ይረከባል፣ ያስረክባል፡፡
8. ወቅታዊ ሪፖርት ያቀርባል፡፡
9. ከቅርብ ኃላፊው የሚሰጡ ሌሎች ሥራዎችን ይሰራል፡፡

የስራ መደቡ መጠሪያ ፡ ጁኒየር አሰስመንትና ክሊራንስ ኦፊሰር

የሚገኝበት መምሪያ/
መምሪያ/ቅ/ጽ/ቤት ፡ ሞጆ/ገላን/ሠመራ ቅ/ጽ/ቤት

ዋና ክፍል ፡ በመልቲ ሞዳልና ክሊሪንግና ኦፕሬሽን ዋና ክፍል

ቀጥታ ተጠሪነት ፡ ሲኒየር አሠሥመንትና ክሊራንስ ኦፊሰር

ዝርዝር ተግባርና ኃላፊነት

1. በአሰስመንትና ክሊራንስ ኦፊሰር የተዘጋጀውን የጉምሩክ ዲክላራሲዮንና ሌሎች ሰነዶችን ከጉምሩክ


ቀረጥና ታክስ ጋር በመቀበል የተሟሉና ትክክል መሆኑን በማመሳከር ለጉምሩክ ገቢ ያደርጋል፡፡
2. የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ክፍያ መፈጸምና ደረሰኝ ይቀበላል፡፡
3. የትራንዚት ፈቃድ እንዲያገኝ ክትትል ማድረግና እንደተገኘ ለጅቡቲ እንዲተላለፍ ለሚመለከተው ክፍል
ይልካል፡፡
4. ለወጭ ዕቃዎች የተቆጣጣሪ ባለስልጣን ፍቃድ መገኘቱን ያረጋግጣል፡፡
5. ዲክላራሲዮን እንዲዘጋጅ ለሚመለከተው ያሳውቃል፡፡
6. የወጪ ዕቃ ሰነድና ዲክላራሲዮን እንደተቀበለ በማመሳከር ለጉምሩክ ኢንስፔክተር በመስጠት ዕቃው
እንዲፈተሽና እንዲታሸግ ያደርጋል፡፡
7. የዕቃ መልቀቂያ ፈቃድ ከጉምሩክ አሴሰር በመቀበል ለአጓጓዡ በመስጠት ከጉምሩክ ክልል እንዲወጣ
ይደረጋል፡፡
8. ገቢ ዕቃ መቅረጫ ጣቢያ እንደደረሰ ሰነዱን ጉምሩክ ገቢ በማድረግ ፈታሽ ያስመድባል፡፡
9. ከጉምሩክ ኢንስፔክተር ጋር በመሆን ዕቃውን ያስፈትሻል፡፡
10. የዕቃ መልቀቂያ ከጉምሩክ በመቀበል እንዲሁም የዴሊቨሪ ኦርደር ከሚመለከተው በመውሰድ የመጋዘንና
ሌሎች ወጪዎችን በሚመለከታቸው በማስተመን ደንበኛው /ወኪሉ/
ወኪሉ/ እንዲከፍል ያሳውቃል፡፡
እንደአስፈላጊነቱ ከደንበኛው ክፍያውን በመቀበል የመጋዘን ክፍያ ይፈጽማል፡፡
11. ዕቃውን ለመጫን የተመደበውን አጓጓዥ ድርጅት ስምና የማጓጓዣ ታሪፍ ከቅርብ ኃላፊው ይጠይቃል፡፡
12. በዕቃ አጓጓዡ /ትራንስፖርተሩ/
ትራንስፖርተሩ/ የሚቀርቡት ተሽከርካሪዎች የመጫን አቅምና ብቃት ካረጋገጠ በኋላ
ዕቃው እንዲጫን ያደርጋል፡፡
13. ጭነቱን የሚጭነው ተሽከርካሪ ከባለንብረቱ /አጓጓዥ ድርጅቶች/
ድርጅቶች/ የጭነት ማዘዥያ ሰነድ የተዘጋጀለት
መሆኑን በማረጋገጥ በኢባትሎአድ የመንገድ ወረቀት (Waybill) ላይ የሚገኙትን ዝርዝር መረጃዎች
በሙሉና በጥንቃቄ በመሙላት አዘጋጅቶ ለሚመለከተው ሹፌር አስፈርሞ ይሰጣል፡፡ ቀሪ ሰነዶችን
ለቅርብ አለቃው ያስረክባል፡፡ ዕቃው ለደንበኛው መድረሱን ተከታትሎ ያረጋግጣል፡፡
14. የዕቃ መልቀቂያ ተገኝቶላቸው በተለያዩ ምክንያቶች በዕለቱ የማይጫኑ ዕቃዎች ዝርዝር ሪፖርት ለቅርብ
ኃላፊው ያቀርባል በቀጣዩ ቀን እንዲጫኑ ያደርጋል፡፡
15. ዕለታዊ ሳምንታዊና ወርሐዊ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርቶች አዘጋጅቶ ለሚመለከተው ያቀርባል፡፡
16. ከዋና ክፍሉ ሥራ አስኪያጅና ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች የሚሰጡትን ተጨማሪ ሥራዎች ያከናውናል፡፡

You might also like