You are on page 1of 4

1.

መግቢያ (Introduction)

ድርጅታችን ከሚያከናውናቸው አበይት ተግባራት መካከል አንዱ የሰው ኃይል አቅርቦት እና አስተዳደር ስራዎችን
ለሶስተኛ ወገን ማቅረብ ዋነኛዉ ነው፡፡ በመሆኑም አገልግሎት የምንሠጣቸውን ደንበኞች የእርካታ ደረጃ ከፍ
ለማድረግና ጠንካራ የሥራ ግንኙነት ለመፍጠር በመምሪያው በኩል የ 2012 የገና በዓል ምክንያት በማድረግ የእንኳን
አደረሣችሁ የአበባ ስጦታ ለ 32 ዋና መ/ቤቶች እና ቅርንጫፍ ባንኮች ለማበርከት የታሰበ ሲሆን ይህም ሊሆን
የቻለበት ዋነኛ ምክንያት ከስጦታው ጎን ለጎን የድርጅታችንን ስምና አገልግሎት በማስተዋወቅ ረገድ እንዲሁም በገጽታ
ግንባታ ዙሪያ የሚያበረክተውን አወንታዊ አስተዋፆኦን ከግምት ውስጥ በማስገባት ሥራውን መስራት ተገቢ እንደሆነ
በአውትሶርስድ አገልግሎት አስተዳደር መምሪያ በኩል የታመነበት በመሆኑ ሥራውን ለመሥራት የሚያስፈልጉ የበጀት
መጠን እና የሚከናወኑ ተግባራትን የያዘ ፕሮፖዛል እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

2. ዓላማ

 የደንበኞችን የእርካታ ደረጃ ከፍ ማድረግ እና የድርጅቱን የገፅታ ግንባታ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ፡፡


 በድርጅታችንና በደንበኞቻችን መካከል ጠንካራ የስራ ግንኙነት በመፍጠር ደንበኞቻችን የሥራችን መስካሪ
/አስተዋዋቂ/ እንዲሆኑ በማድረግ የደንበኞችን ቁጥር ለማሳደግ፡፡
 ድርጅታችንን ለሌሎች ደንበኛ ላልሆኑ ባንኮች እና ድርጅቶች ለማስተዋወቅ፡፡

3. የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

3.1 ስራውን ሊያከናውን የሚችል የሰው ኃይል/ሱፐርቫይዘር/ በየዲስትሪክቱ መመደብ፣


3.2 ከሁሉም ደንበኞች ባንኮች ስጦታው ሊሰጣቸው የሚገባ ደንበኛ ባንኮችን መለየት፣
3.3 በጋራ የሚሠሩ ተግባራትን ሊያከናውን የሚችል ኮሚቴ ማቋቋም፣
3.4 ለስጦታው ድምቀት ሊሰጡ የሚችሉ ማቴሪያሎችን መለየት የገበያ ጥናት ማድረግና ግዥ መፈፀም፣
3.5 ስጦታውን ለማጓጓዝ የተሸከርካሪ ጥያቄ ለሰው ሃይል እና ሎጀስቲክ አስተዳደር መምሪያ በማቅረብ
ማስፈቀድ
3.6 ለስራው የሚያስፈልገውን ወጪ/የገንዘብ መጠን/ በመስራት በመምሪያው በኩል ጥያቄው ለዋና ስራ
አስኪያጅ ቀርቦ እንዲፈቀድ ማድረግ እና የተፈቀደውን በጀት ለፋይናንስና አካውንትስ መምሪያ ማሣወቅ፣
3.7 አስፈላጊውን ግዥ መፈፀም፣
3.8 እንኳን ለ 2012 ዓ.ም የገና በዓል አደረሳችሁ የሚል እና የ CN አርማ ያለበት ፅሁፍ ማዘጋጀት፣
3.9 የስርጭት ሥራውን መሰራት (ስጦታውን ለደንበኞች ማቅረብ)፡፡

1
4. ሥራውን በኮሚቴነት ደረጃ የሚያስተባብሩት ፈፃሚዎች እና ስራው የሚከናወንበት የጊዜ መርሀ ግብር

የኮሜቴ አባላት

1) ሰሎሞን አበራ----- --------------------ሰብሣቢ


2) ዳንኤል ታምሩ ----------------------- አባል
3) አበባ ጃቢሳ -----------------------------አባል
4) ፀጋዬ ሰይፉ ----------------------------አባል
5) ሽፈራዉ ሰይፉ------------------------- አባል
6) ደረጀ ክፍሌ----------------------------አባል
7) የሊሾ ጌርጌ -----------------------------አባል
ስራው የሚከናወንበት የጊዜ መርሀ ግብር

ተ.ቁ የሚከናወኑ ተግባራት ተግባሩን የሚፈፀምበት ቀን

1 ፕሮፖዛል ማዘጋጀት 23/04/2012


2 የእንኳን አደረሳችሁ የሚል ፅሁፍ ህትመት ትዕዛዝ መስጠት 20/04/2012
3 የቄጤማ እና የአበባ ግዥ መፈፀም 26/04/2012
4 የተዘጋጁ ስጦታዎችን ለቅርንጫፎች መስጠት /ማሰራጨት / 27/04/2012

5. ስራውን ለመስራት የሚያስፈልገው በጀት


የሚያስፈልገው የዋጋ መግለጫ
ተ.ቁ የዕቃው ዓይነት መለኪያ
መጠን የአንዱ ዋጋ ጠቅላላ ዋጋ
1 የተፈጥሮ አበባ በሳጠራ የተዘጋጀ ቁጥር 46 600 27,600
2 ቄጤማ ሸክም 12 900 10,800
ጠቅላ ድምር 38,400

2
6. ስጦታው የሚካሄድባቸው ደንበኛ ባንኮች
የሚያስፈልገው የተፈጥሮ
ተ.ቁ የባንኩ ቅርንጫፍ ስም የአንዱ አበባ ዋጋ ጠቅላላ ዋጋ ስርጭቱን የሚያደርገው ባለሙያ
አበባ ብዛት

1 ፊንፊኔ ዋናው መ/ቤት (ኢ.ን.ባ) 3 600 1800 ዳንኤል

2 አዲስ አበባ ቅርንጫፍ (ኢ.ን.ባ) 1 600 600 ዳንኤል

3 ደብረ ወርቅ ህንፃ (ኢ.ን.ባ) 2 600 1200 ዳንኤል

4 ቫቲካን (ኢ.ን.ባ) 1 600 600 ዳንኤል

5 ልማት ባንክ ዋ/ቤት 1 600 600 ዳንኤል

6 ህዳሴ ህንፃ 2 600 1200 ዳንኤል

7 ፀጋዬና ቤተሰቡ ህንፃ 1 600 600 ዳንኤል

8 ገዳ ህንፃ 1 600 600 ዳንኤል

9 ጳዉሎስ ቅርንጫፍ 1 600 600 ዳንኤል

10 አን ህንፃ 1 600 600 ዳንኤል

11 ወልደማርያም ህንፃ 1 600 600 ዳንኤል


የኢትዮጵያ ባህር ትራንዚት አገልግሎት
12 1 600 600 ዳንኤል
ድርጅት
13 ዌስተርን ዩኒየን 1 600 600 ዳንኤል

14 HRD ቢሮ ሳሪስ 2 600 1200 ሽፈራዉ ሰይፉ

15 ጠመንጃ ያዥ (ኢ.ን.ባ) 1 600 600 ሽፈራዉ ሰይፉ

16 ደቡብ ዲስትሪክት (ኢ.ን.ባ) 1 600 600 ሽፈራዉ ሰይፉ

17 ኢትዮ-ጂቡቲ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን 1 600 600 ሽፈራዉ ሰይፉ

18 ምናሴ ለማ 1 600 600 ሽፈራዉ ሰይፉ

19 የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን 1 600 600 ሽፈራዉ ሰይፉ

20 ጎፋ ትራንስፖርት (ኢ.ን.ባ) 1 600 600 ፀጋዬ

21 ዛግዌ ህንፃ 2 600 1200 ፀጋዬ

22 አባኮራን (ኢ.ን.ባ) 1 600 600 አበባ

23 4 ኪሎ (ኢ.ን.ባ) ቅ/ፍ እና ዲስትሪክት 2 600 1200 አበባ


ሥላሴ (ኢ.ን.ባ) እና ቢዝነስ
24 2 600 1200 አበባ
ዴቨሎፕመንት ባንክ
25 ምዕራብ ዲስትሪክት ተክለሃይማኖት 1 600 600 አበባ

26 ተክለሃይማኖት ቅርንጫፍ (ኢ.ን.ባ) 1 600 600 አበባ

27 አዲስ ከተማ (ኢ.ን.ባ) 1 600 600 አበባ

28 መሀል ገበያ (ኢ.ን.ባ) 1 600 600 አበባ

29 CN ዋናው መ/ቤት 3 600 1800 አበባ

30 ጎላጎል ምስራቅ ዲስትሪክት (ኢ.ን.ባ) 1 600 600 ደረጀ

31 ኤዩዳኢን አክሽን ኢትዮጵያ 1 600 600 ደረጀ


አዲስ አበባ የሚገኙ የኮሜርሻል
32 5 600 3000 ፀጋዬ፣ አበባ፣ ደረጀ፣ ሽፈራው
ኖሚኒስ ቅርንጫፎች

ድምር 46 600 27600

3
7. ማጠቃለያ

 ደረሰኝ ማቅረብ በሚቻልባቸው ግዥዎች ደረሰኝ በማቅረብ ሂሳቡ የሚወራረድ ሲሆን ደረሰኝ የሌላቸውን
በባህላዊ የግዢ ዘዴ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
 ድርጅታችን የፅዳት አገልግሎት እና የሰው ኃይል አቅርቦት ስራ ሲሰራ ከማናቸውም ተግባር በበለጠ ለደንበኞቻችን
እርካታ ቅድሚያ ይሠጣል፡፡ ይህም በመሆኑ በመምሪያው ለደንበኞች ይህንን ስጦታ እንዲቀርብ ሲወስን በዝቅተኛ
ዋጋ ቀላል ግምት የማይሰጠው ተቋማዊ የገፅታ ግንባታ ሥራ ጎን ለጎን ይሰራል ብሎ በማመን ስለሆነ
የሚመለከተውም አካል ይህንን ተገንዝቦ አስፈላጊውን ድጋፍና ገንዘብ ያደርጋል ብሎ በማመን ነው፡፡

You might also like