You are on page 1of 1

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር

ባለስልጣን
በትራንስፖርት ቢሮ የቀጣይ 10 አመት ዕቅድ ላይ ሊካተቱ የሚገባቸው 6 ዋና ዋና ግቦች

ግብ 1. ከአሽከርካሪና ተሽከርካሪ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ያሉ ችግሮችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመደገፍ


አገልግሎቱን በማዘመን ብልሹ አሰራርን በማስቀረት የተገልጋዩን እርካታ ማሳደግ የሚችለውን
SIDVMIS(SUPPLY AND IMPLEMENT OF DRIVER AND VEHICLE MANAGEMENT INFORMATION
SYSTEM) ፕሮጀክት በማጠናቀቅ ወደ ተግባር ማስገባት

ግብ 2. በከተማችን ላሉ አዲስ የመንጃ ፈቃድ ማውጣት ለሚፈልጉ ተገልጋዮች አገልግሎት እየሰጠ ያለውን
የቃሊቲ አዲስ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጥ ማህከልን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማደራጀት አጠቃላይ አገልግሎት
የንድፈ ሀሳብና የተግባር ፈተና አሰጣጡን ከሰው ንክክ ነፃ በማድረግ የማዘመን ስራ መስራት

ግብ 3. የተገልጋይ ፍላጎትትን ማህከል በማድረግና ከተማችንን ሊመጥን የሚችሉ አመናዊ የአሽከርካሪ ብቃት
ማረጋገጫ ምዘና የሚካሄድባቸው ሁለት የትራፊክ ኮምፕሌክት በመገንባት አገልግሎቱን በማዘመን በፍላጎትና
በአቅርቦት መሀከል ያለውን ልዩንት በማጥበብ ተገልጋዩን ማርካት

ግብ 4. ከተማችንን ሊመጥን የሚችል የተሸክርካሪ ሰሌዳ አለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የዲዛይን
ስራ በመስራት አሁን ያለውን የሰሌዳ አይነት በዘመናዊ መልኩ እንዲቀየር ማድረግ

ግብ 5. በከተማችን አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁና በዘመናዊ ቴክሎኖጂ የታገዙ የአሽከርካሪ ብቃት
ማረጋገጫ(የመንጃ ፈቃድ) ማስተማሪያ ተቋማት እንዲኖሩ የሚያስችል ስታንዳርድ በማዘጋጀት አዲስ
የሚከፈቱትም ሆነ በስራ ላይ ያሉት ወደ ስታንዳርዱ እንዲመጡ በማድረግ የስልጠና አሰጣጡን ማዘመን

ግብ 6. የተሸከርካሪ የቴክኒክ ምርመራ የሚያደርጉ የምርመራ ተቋማት የቴክኒክ ምርመራ ስራቸውን


በአመናዊ ቴክኖሎጂ በማስደገፍ እንዲሰጡና የቴክኒክ ችግር ያለባቸውን ተሸከርካሪዎች በአግባቡ ሊለይ
የሚችል በቴክኖሎጂ የተደገፈ የቴክኒክ ምርመራ እንዲያከናወኑና ይህንኑ ተቆጣጣሪው አካል በአግባቡ
መከታተል እንዲችል የሚያደርግ አሰራር በመዘርጋት የቴክኒክ ምርመራ ስራውን ዘመናዊና ደረጃውን የጠበቀ
ማድረግ

You might also like