You are on page 1of 4

በአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ

በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለሚሰሩ ስራዎች ለክልል፣ለዞንና ወረዳ የተዘጋጀ የአሰራር ማንዋል

ባህር ዳር 2011 ዓ.ም


በወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ደረጃ የሚሰሩ ስራዎችን

1. የኢኮኖሚ ሽግግር የሚያመጡ አምራች ኢንዱስትሪዎችን አፈጻጸም ማሳደግ


በተመለከተ መከናወን ያለባቸው
1.1 ሁለንተናዊ ችግሮቻቸ የተለየላቸውን አምራች ኢንዱስትሪዎች ከሚመለከታቸው ተቋማት
ጋር ትስስር በመፍጠር የኢንዱስትሪ ኤክስቴሽን (የቴክኒካል አቅም ግንባታ ፣
የኢንተርፕረነርሽፕ አቅም ግንባታ፣ ጥራትና ምርታማ ነት አቅም ግንባታ እና የቴክኖሎጂ
አቅም ግንባታ ) በመስጠትና ችግራቸውን በመፍታ የማምረት አቅማቸውን የማሳደግ ስራ
መስራት፡፡
1.1.1 ከዚህ በፊት የኢንዱሰትሪ-ዩኒቨርስቲ ትስስር ከተፈጠረባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ጋር መካከለኛ
እና ከፍተኛ አምራች ኢንዱሰትሪዎችን ማስተሳሰር፣

1
 ያሉንን መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪወችን ቆጥረን በመያዝ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ጥርት ያለ
መረጃ ማዘጋጀት፣
 መረጃውን መሰረት በማድረግ ቆጥረን የያዝናቸውን መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪወች በቅርበት
ካለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር እንዴት እንደምንደግፋቸው የጋራ እቅድ ማቀድ፣
 ከዚያም አንድ የዘርፉ አሰልጣኝ መምህርና የሚመለከተው የሴክተሩ የዘርፍ ባለሙያ ምን ያህልና
የተኞቹን መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪወች ቆጥረው እንደሚደግፉ ማረጋገጥና መረጃ መያዝ፣
 የዘርፍ ባለሙያ ከአሰልጣኝ መምህሩ ጋር በመሆን ወደ ኢንዱስትሪወች በመሄድ የሁኔታወች ትንተና
መስራት፣
 በተዘጋጀው የሁኔታወች ትንተና መሰረት መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪወች ያለባቸውን
የአመለካካከት፣ የእውቀትና የክህሎት፣ የቴክኖሎጅ፣ የጥራትና ምርታማነት፣ የጥሬ እቃ አቅርቦትና
አጠቃቀም፣ እንዲሁም የሂሳባ አያያዝ ክፍተቶችን በተገቢው መንገድ መለየት፣
 ከላይ የተጠቀሱትን ክፍተቶች ሊሞላ የሚችሉበትን የድርጊት መርሀ-ግብር ከኢንዱስትሪው ጋር
በጋራ ማዘጋጀት፣
 በተዘጋጀው የድርጊት መርሀግብር መሰረት የኢንዱስትሪወችን ክፍተት ሊሞላ የሚችል ድጋፍ
መስጠትና ክትትል በማድረግ ክፍተቶቹ እየተሞሉ፣ የኢንዱስትሪወች የውስጥ ችገሮች እየተፈቱ
ስለመሆኑና የመጣውንም ለውጥ እየገመገሙ በቋሚ መዝገብ በመያዝ መረጃውን ለሚመለከተው
አካል ማድረስ፡፡
1.1.2 ከዚህ በፊት የኢንዱሰትሪ-ቴ/ሙያ ኮሌጆች ትስስር ከተፈጠረባቸው ቴ/ሙያ ኮሌጆች ጋር
አነስተኛ አምራች ኢንዱሰትሪዎችን ማስተሳሰር፡፡
 ያሉንን አነስተኛ ኢንዱስትሪወችን ቆጥረን በመያዝ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ጥርት ያለ መረጃ
ማዘጋጀት፣
 መረጃውን መሰረት በማድረግ ቆጥረን የያዝናቸውን አነስተኛ ኢንዱስትሪወች በቅርበት ካለው
ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ጋር እንዴት እንደምንደግፋቸው የጋራ እቅድ ማቀድ፣
 ከዚያም አንድ የዘርፉ አሰልጣኝ መምህርና የሚመለከተው የሴክተሩ የዘርፍ ባለሙያ ምን ያህልና
የትኞቹን አነስተኛ ኢንዱስትሪወች ቆጥረው እንደሚደግፉ ማረጋገጥና መረጃ መያዝ፣
 የዘርፍ ባለሙያ ከአሰልጣኝ መምህሩ ጋር በመሆን ወደ ኢንዱስትሪወች በመሄድ የሁኔታወች ትንተና
መስራት፣
 በተዘጋጀው የሁኔታወች ትንተና መሰረት አነስተኛ ኢንዱስትሪወች ያለባቸውን የአመለካካከት፣
የእውቀትና የክህሎት፣ የቴክኖሎጅ፣ የጥራትና ምርታማነት፣ የጥሬ እቃ አጠቃቀም፣ እንዲሁም
የሂሳባ አያያዝ ክፍተቶችን በተገቢው መንገድ መለየት፣
 ከላይ የተጠቀሱትን ክፍተቶች ሊሞላ የሚችሉበትን የድርጊት መርሀግብር ከኢንዱስትሪው ጋር
በጋራ ማዘጋጀት፣

2
 በተዘጋጀው የድርጊት መርሀግብር መሰረት የአነስተኛ ኢንዱስትሪወችን ክፍተት ሊሞላ የሚችል
ድጋፍ መስጠትና ክትትል በማድረግ ክፍተቶቹ እየተሞሉ፣ የኢንዱስትሪወች የውስጥ ችግሮች
እየተፈቱ ስለመሆኑና የመጣውንም ለውጥ እየገመገሙ በቋሚ መዝገብ በመያዝ መረጃውን
ለሚመለከተው አካል ማድረስ፡፡
1.1.3 በተደረገላቸው የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ መሰረት የደረጃ ለውጥ ያመጡ
ኢንዱሰትሪዎችን በትክክለኛው መስፈርት ተመዝነው የሚያልፉ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው
ደረጃ የማሸጋገር ስራ መስራት፡፡
2. የዘርፉን ፕሮጀክት ክትትልና ድጋፍ ውጤታማነት ማሻሻል በተመለከተ መከናወን ያለባቸው

 አዲስ ፕሮጀክት በመቅረጽ ወይም ነባሩን ኢንዱስትሪ ለማስፋፋት ተጨማሪ ማሽነሪ


አስፈልጓቸው የማሽነሪ ዝርዝር መግለጫ ለሚጠይቁ ባለሀብቶች ድጋፍ ማድረግ፣
 በቀረበው ፕሮጀት ውስጥ የተዘረዘሩት ማሽኖች እና ሌሎች መሳሪያዎች ዝርዝር መግለጫ
ያለቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
 በፕሮጀቱ ውስጥ የተዘረዘሩት ማሽኖች እና ሌሎች መሳሪያዎች ለምርት ሂደቱ የተሟሉ፣
አስፈላጊና የሚመጥኑ መሆናቸውን መለየት፣
 የተጓደሉ እንዲካተቱ እና አላስፈላጊ የሆኑትን ደግሞ ከዝርዝሩ እንዲወጡ በማድረግ ባለሃብቱ
አስተካክሎ እንዲያመጣ ማስቻል፣
 በቀረቡት ማሽኖች እና ሌሎች መሳሪያዎች ዝርዝር መግለጫ መሰረት ማሽንና ፕላንት ለይ አውት
መቅረቡን በማረጋገጥና በመገምገም የሚያስፈልገውን የቦታ መጠን መወሰን፣
 በተወሰነለት ማሽንና ፕላንት ለይ አውት መነሻ መሰረት ያሸነፈበትን ፕሮፎርማ ባለሀብቱ ይዞ
እንዲያቀርብ በማድረግ ትክክለኛነታቸውን የማረጋገጥ፣
 በባለሀብቱ ተገዝተው የቀረቡ ማሽኖች በፕሮፎርማው መሰረት መሆናቸውን በአካል በማየት
የማመሳከር ስራ መስራት፡፡
3. የኢንዱስትሪዎችን ምርጥ ተሞክሮ መቀመርና ማስፋትን በተመለከተ መከናወን ያለባቸው
3.1 ምርጥ ተሞክሮዎችን ስለመቀመር

 ምርጥ ተሞክሮ የሚቀመርላቸው ኢንዱስትሪወችን እና ድጋፍ የሚያደርጉ አካላትን መለየት፣


 የሞዴል ኢንዱስትሪዎችን መመዘኛ መስፈርት ማዘጋጅት፣

 ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመቀመር የሚያስችል ቼክሊስት ማዘጋጀት፣

 በቼክሊስት መሰረት መረጃ መሰብሰብ፣


1) የመስክ ጉብኝት እና ምልከታ በማድረግ፣

3
2) ሰነዶችን በመፈተሽ፣
3) ውይይት በማድረግ፣
4) ቃለ መጠይቅ በማካሄድ፣
5) የመረጃ ማሰባሰቢያ መንገዶችን በመጠቀም፣
o በጽሁፍ፣በድምፅ፣በምስል መያዝ፡፡
 በቼክ ሊስቱ መሠረት የተሰበሰቡትን መረጃዎች ከመስፈርቶቹ አንፃር ማደራጀት፣
 መረጃዎቹን መተንተን፣
 ተሞክሮውን በሚያመች ዘዴ መቀመር (በምስል በድምፅና በጽሁፍ)
 ሪፖርት በወረዳ ወይም በከተማ ደረጃ በማዘጋጀት በዞን ደረጃ ለሚገኘው መዋቅር ማስተላለፍ፤
3.2 ምርጥ ተሞክሮዎችን ስለማስፋት

 የጠራ ራዕይ መያዝ፣

 ሁኔታዎችን ማወቅ፣

 ዕቅድ ማዘጋጀት፣

 የጋራ አመለካከት መፍጠር፣

 ደጋፊ የህግና የድጋፍ ማዕቀፎችን ማወቅ፣

 ፈፃሚ እና ባላድርሻ አካላትን መለየትና በአግባቡ ማሰማራት፣

 አስፈላጊ ግብዓቶች መሟላታቸውን ማረጋገጥ፣

 ውጤታማ የግምገማና የክትትል ስርዓት መዘርጋት፣

You might also like