You are on page 1of 26

በዕድገት ድርና ማግ የስፌት ክር አክስዮን ማህበር

እና
በዕድገት ድርና ማግ የስፌት ክር አክስዮን ማህበር መሠረታዊ
ሠራተኛ ማኅበር

መካከል
ለ 15 ኛ ጊዜ የተደረገ የሕብረት ስምምነት

አዲስ አበባ 
ግንቦት 200 ዓ.ም 

ክፍል አንድ
የህብረት ስምምነቱ ዓላማና አስፈላጊነት፣ የቃላት አተረጓጎም፣ እውቅና እና 
የህብረት ስምምነት ተፈፃሚነት ወሰን
አንቀጽ 1
የህብረት ስምምነት ዓላማና አስፈላጊነት
የህብረት ስምምነት ዓላማና አስፈላጊነት የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 እና የዚህ አዋጅ ማሻሻያ
494/98 እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪ አዋጁ ለህብረት ስምምነት የተዋቸውን መብቶችና ሌሎችንም
በዚህ ህ/ስምምነት ውስጥ ስምምነት የተደረሰባቸውን ጉዳዮች በድርጅቱ ውስጥ በአሰሪና ሰራተኛ መካከል
ያለው የሥራ ግንኙነት ጤናማ እንዲሆን እና አሠሪና ሠራተኛውም መብትና ግዴታውን አውቀው
በአንድነት ለጋራ ጥቅም ለድርጅቱ ህልውና እና ለሠራተኛ መብት መጠበቅና ለኢንዱስትሪ ሰላም መስፈን
ተጣጥመው እንዲሰሩ ለማድረግ ነው፡፡ 
አንቀጽ 2
የመሪ ቃሎች ትርጉም
በዚህ ህብረት ስምምነት የመሪ ቃሎች ትርጉም ከዚህ በታች የተሰጠው ትርጉም ይኖረዋል፡፡ 
2.1. እርሻ፡- ማለት ዕድገት ድርና ማግ የስፌት ክር አክስዮን ማህበር ማለት ነው፡፡ 
2.2. የሠራተኛ ማህበር፡- ማለት የዕድገት ድርና ማግ የስፌት ክር አክስዮን ማህበር መሠረታዊ ሠራተኛ
ማህበር ማለት ነው፡፡  
2.3. የደረጃ ዕድገት፡- ማለት በድርጅቱ መዋቅርና በአስተዳደር የሥራ መመሪያ መሠረት ከዝቅተኛ የሥራ
መደብ ወደ ቀጣዩ ወይም ወደ ከፍተኛ የሥራ መደብ የሚደረግ የሥራ ምደባ ነው፡፡ 
2.4. ሠራተኛ፡- ማለት በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ 377/96 አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የተሰጠው
ትርጉም ይኖረዋል፡፡ 
2.5. አሰሪ፡- ማለት በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት የተሰጠው
ትርጉም ይኖረዋል፡፡ 
2.6. የሥራ መሪ፡- ማለት በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 እና ተሻሽሎ በወጣው አዋጅ ቁጥር
494/98 የተሠጠው ትርጉም ይኖረዋል፡፡ 
2.7. ውክልና፡- ማለት አንድ የስራ መሪ ከአለው የሥራ ኃላፊነት ላይ በተጨማሪ የተጓደለ የኃላፊነት ሥራ
ቦታን ደርቦ እንዲሠራ ወደ ላይ የሚሰጥ ኃላፊነት ነው፡፡ 
2.8. የውጤት ክፍያ፡- ማለት አንድ ሠራተኛ በውጤት በሚከፈል የማምረቻ መሣሪያ ላይ ሲሰራ ብቻ
በእርሻዉየውጤት ክፍያ መመሪያ መሠረት የሚከፈል ክፍያ ማለት ነው፡፡ 
2.9. የማትጊያ ክፍያ፡- ማለት ሠራተኛው የተመደበለትን የምርት ዕቅድ በነጠላም ሆነ በወል ከታቀደው
በላይ ማምረት ሊችል ወይም ሠራተኛው ባለው ዕውቀት በነጠላም ሆነ በወል እርሻውን ከወጪ ሊያድን
በነጠላም ሆነ በወል የሚሰጥ ልዩ ክፍያ ነው፡፡ 
2.10. ቦነስ (ጉርሻ)፡- ማለት አሠሪው በበጀት ዓመቱ ውስጥ ከታክስ በኋላ ከሚያገኘው ትርፍ ላይ እርሻው
ፈቅዶ ለሠራተኛው የሚሰጠው ገንዘብ ነው፡፡ 
2.11. ቶፕ አፕ ()፡- ማለት የማነቃቂያ ክፍያ አይነት ሲሆን አንድ ኦፕሬተር መደበኛ ማሽን መያዝ
ከሚገባው በላይ ተጨማሪ እንዲይዝ/እንድትይዝ በእርሻዉበጽሁፍ ተፈቅዶ ሲይዝ/ስትይዝ እንዲሁም
ከመደበኛ ሥራው በተጨማሪ ሌላ የሥራ መደብን ሸፍኖ ወይም ሸፍና እንድትሠሪ በፋብካው በጽሁፍ
ተፈቅዶ የሚከፈል ማለት ነው፡፡ ክፍያውም በተሠራባቸው ቀናቶች ብቻ ታስቦ ይሆናል፡፡ 
2.12. አዲስ የሥራ መደብ፡- ማለት ለእርሻው መስፋፋትና ዕድገት አስፈላጊነቱ በአሰሪው ሲታመንበተ
ጽድቆ በሥራ ላይ እንዲውል የሚደረግ የፀደቀ አዲስ የሥራ መደብ ነው፡፡ 
2.13. ፈቃድ፡- ማለት በዚህ ህብረት ስምምነት መሠረት ሠራተኛ በሥራ ቀን በሥራ ሰዓት ፈቃድ
ከደመወዝ ጋር ወይም ያለደመወዝ ተፈቅዶለት በሥራ ገበታው ላይ የማይገኝበት ነው፡፡ 
2.14. ቅጣት፡- ማለት ሠራተኛው በዚህ የህብረት ስምምነት ወይም በመንግስት አዋጆችና ሌሎች ህጎችና
ደንቦች ውስጥ ከተመለከተው የጥፋት ዓይነት አንዱን ፈጽሞ በመገኘቱ ለወደፊቱ እንዳይደገም የሚወሰድ
የሥነሥርዓት እርምጃ ነው፡፡ 
2.15. የህብረት ስምምነት፡- ማለት በዕድገት ድርና ማግ የስፌት ክር አክስዮን ማህበርና
በእርሻዉመሠረታዊ ሰራተኛ ማህበር መካከል የተደረገ ስምምነት ነው፡፡ 
2.16. ደመወዝ፡- ማለት አንድ ሠራተኛ በሥራ ውሉ መሠረት ለሚያከናውነው ሥራ የሚከፈለው መደበኛ
ክፍያ ነው፡፡ 
አንቀጽ 3
እውቅናን በተመለከተ
3.1. እርሻው በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 እና የዚሁ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 494/98 እና በዚህ
ህብረት ስምምነት መሰረት የሰራተኛውን ህልውና እና የእርሻውን ዕድገት ለማስጠበቅ በባለቤትነት
ለመምራት አሰሪው መብት ያለው መሆኑን የሠራተኛ ማህበሩ አውቆለታል፡፡  
3.2. በዚህ ህብረት ስምምነት መሠረት፡- ስለተመለከቱት አንቀጾች ስለሠራተኛው ጉዳዮች ከግል ክርክር
በስተቀር ከእርሻው ጋር የህብረት ስምምነት ድርድር ለማድረግና ስለአጠቃላይ ሰራተኛ ጉዳይ ቀርቦ
ማነጋገር የሚችለው የዕድገት ድርና ማግ የስፌት ክር አክሲዮን ማህበር መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ብቻ
መሆኑን አውቆ እርሻው ተቀብሎታል፡፡ 
አንቀጽ 4
በዚህ ህብረት ስምምነት ያልተጠቀሱ ጉዳዮችን በተመለከተ
4.1. በዚህ ህብረት ስምምነት ያልተወሰነ ማህበሩንና እርሻውን የሚመለከት ነጥብ ወይም ጉዳይ
ቢያጋጥም እርሻውና ማህበሩ ህግ በሚፈቅደው መሠረት በመነጋገር በሁለቱም ወገን ተቀባይነት ሲያገኝ
እንዲጨመርና የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲያውቀው ወይም እንዲመዘገብ ያደርጋሉ፡፡ 
አንቀጽ 5
የዚህ ህብት ስምምነት ተፈፃሚነት ወሰን
5.1. ይህ የህብረት ስምምነት በዕድገት ድርና ማግ የስፊት ክር አክሲዮን ማህበር ውስጥ በአሰሪና ሠራተኛ
መካከል በሚደረግ የዋና ክፍል የሥራ መደብንና ከዚያ በታች ባሉ የሥራ መደቦች ቅጥር ላይ በተመሠረተ
የሥራ ግንኙነት ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 
5.2. የሥራ መሪዎች ማለትም በህግ ወይም በአሠሪው በተሰጠው ስልጣን መሠረት የእርሻውን ዋና ዋና
ተግባሮች በቀጥታ የሚያከናውኑ የመምሪያ ኃላፊዎችንና፣ ከዚህ በላይ የሆኑ የሥራ መሪዎችን
(ኃላፊዎችን) እንዲሁም እነዚህን የሥራ አመራር ጉዳዮች አስመልክቶ የአሰሪውን ጥቅም ለመጠበቅ
አሰሪው መውሰድ ስለሚገባው እርምጃ በራሱ የውሣኔ ኃሳብ የሚያቀርብ የህግ አገልግሎት ኃላፊውንም
ጭምር የዚህ ህብረት ስምምነት ተፈፃሚነት ወሰን እነዚህን አካሎች አያካትትም፡፡ 
አንቀጽ 6
የእርሻውና የሠራተኛ ማህበሩ ግንኙነት
6.1. በእርሻዉማኔጅመንትና ሠራተኛ ማህበር መካከል ያለው ግንኙነት እርሻው የተቋቋመበትን ዓላማ
ለማስፈፀም ተመካክረው በመስራት እርሻውንና ሠራተኛውን ውጤታማ በማድረግ ላይ የተመሠረተ
ይሆናል፡፡ 
ክፍል ሁለት
የተዋዋይ ወገኖ ግዴታዎች
አንቀጽ 7
የአሰሪ ግዴታ
7.1. ማንኛውም አሠሪ በሥራ ውሉ ከተመለከተው ልዩ ግዴታዎችና በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 12
ከተዘረዘሩት በተጨማሪ የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩታል፡፡ 
7.2. ሠራተኞች በየወሩ ለማህበራቸው የሚያዋጡትን የአባልነት መዋጮ እርሻው ከደመወዛቸው እየቀነሱ
በ 30 ቀን ውስጥ ለማህበሩ ገንዘብ ያዥ ወይም ማህበሩ በጽሁፍ ለሚወክለው በህጋዊ ደረሰኝ ግቢ
ያደርጋል፡፡ 
7.3. የሠራተኛው የግል ማህደር በጥንቃቄ እንዲያዝ አስፈላጊውን ክትትል ያደርጋል፡፡ ተገቢውን
እርምጃም ይወስዳል፡፡ 
7.4. ከአንድ የሥራ ቦታ ወደ ሌላ ሥራ ቦታ የሚዛወሩትን ሠራተኞች የቦታውን መስፈርት የሚያሟሉ
ከሆነ በቦታው ሲያገኙ የሚችሉትን ማንኛውም ጥቅም መጠበቅ፡፡ 
7.5. የማስታወቂያ መለጠፊያ ቦታዎች ሠራተኛው ሊያይ በሚችልበት አካባቢ እርሻው ያዘጋጃል፡፡ 
7.6. አሠሪ በሠራተኛ ጉዳይ በዕድገት፣ በዝውውር በሥነ ሥርዓት ርምጅ እና በሌሎ የሠራተኛ ጉዳዮች ላይ
የሚወሰደውን ውሳኔ በኮፒ ለማህበሩ ያሳውቃል፡፡ 
አንቀጽ 8
የሠራተኛ ግዴታዎች
8.1. በዚህ ህብረት ስምምነት ስለ ስራ ውል የተጠቀሱትን በእርሻዉ ውስጥ በሥራ ላይ የሚውሉ ደንቦችን
የድርጅቱ የሥራ መመሪያዎችን እና በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 በአንቀጽ 13 የተዘረዘሩትን
በሙሉ ያከብራል ይፈጽማል፡፡ 
8.2. የእርሻው የምርት ውጤት በጥራትና በብዛት እንዲመረት የምርት ዕቅዱ ግቡን እንዲመታ መላ
ችሎታውነን እንዲሁም መደበኛ የሥራ ሰዓቱን በአግባቡ ሥራ ላይ ያውላል፡፡ 
8.3. ሁልግዜም የራሱንና የድርጅቱን ሥምና ዝና ይጠብቃል፡፡ እንዲሁም የፋብካውን ምስጢር
ለማይመለከታቸው ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች እንዲያውቁ አያደርግም፡፡ 
8.4. ማህበሩና እርሻው በህብረት ስምምነት የተስማሙባቸውን የሥነ ሥርዓት ደንቦች ያከብራል፡፡ 
8.5. ሠራተኛው እርሻው ባዘጋጀው የሰዓት መቆጣጠሪያ መዝገብ ወይም ፓንች ላይ ወደ ሥራ ሲገባ
ይመዘገባል ወይም ፓንች ያደርጋል፡፡ የእርሻውን የስራ ሰዓትም አክብሮ በሥራ ላይ ይገኛል፡፡ 
8.6. ከህግና ከህብረት ስምምነቱ ውጪ እስካልሆነ ድረስ እርሻው ባዘዘው ማንኛውም ቦታ ይሠራል፡፡ 
8.7. በእርሻውና በሠራተኛ ማህበር (ተወካይ) መካከል አለመግባባት የሚፈጥር የሐሰት ወሬ ከማውራት
ይቆጠባል፡፡ 
8.8. ከእርሻው ደንበኞች ወይም ከማንኛውም ሰው መደለያ ወይም ጉቦ መቀበል የለበትም፡፡ 
8.9. ወደ እርሻው ሲገባና ሲወጣ ለፍተሻ ይተባበራል፡፡ መታወቂያ ሲጠየቅ ያሳያል፡፡ 
8.10. የእርሻውን ንብረት ወይም ኃብት ለግሉ ወይም ለሌላ ሰው አገልግሎት አያውልም፡፡ 
8.11. በእርሻዉ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሥራ ሰዓት ወይም በሰርቪስ አገልግሎት ላይ በማንኛውም ምክንየት
መደባደብ፣ መዛትና መሣደብ እንዲሁም ማንኛውም አፀያፊ ድርጊት ከማድረግ ይቆጠባል፡፡ 
8.12. እርሻው ካልፈቀደ በስተቀር በሥራ ቦታና ጊዜ ሰብሰባ መሰብሰብ ልዩ ልዩ እትሞችንና ጽሁፎችን
ማስፈረሚያ ሊስቶችን ማደል መለጠፍ ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑን አውቆ ማክበር አለበት፡፡ 
8.13. ህግ ሊያስገድድ ወይም እርሻው በበቂ ምክንያት ሲጠይቅ ለጤና ምርመራ ፈቃደኛ ሆኖ መገኘት
(ከኤች.አይ.ቪ) ምርመራ በስተቀር 
8.14. በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ 377/96 መሠረት ትርፍ ሰዓት ሥራ እንዲሰራ ሲጠየቅ የመስራት 
8.15. ሠራተኛ ሥራውን ለማከናወን የተሰጠውን የመገልገያ መሣሪያዎች የአደጋ መከላከያ ቁሳቁሶች
በአግባቡ ይጠብቃል፡፡ የስራ ልብሱን ለብሶ ይሰራል፡፡ 
8.16. ሲጋራ ከተፈቀደው ቦታ ውጪ ማጤስ የለበትም፡፡ 
8.17. ያለፈቃድና ያለበቂ ምክንያት ከሥራ መቅረት ከሥራ ቦታ ላይ ተነስቶ መሄድ የማይመለከተውን
የግል ሥራ በስራ ሰዓት መሥራት የለበትም፡፡ 
8.18. ራሱንም ሆነ የሥራ ጓደኞቹን አደጋ ላይ የሚጥል የድርጅቱን ጥቅም የሚነካ ሁኔታ ሲያጋጥመው
ወዲያውኑ ለአሰሪው የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡ 
አንቀጽ 9
የሠራተኛ ማህበሩ ግዴታዎች
9.1. ይህን የህብረት ስምምነት ወይም አዳዲስ የሥራ ሁኔታዎችን ለማሻሻል በሚመለከት አሰሪው
ለውይይት ሲጠየቅ ይቀርባል፡፡ 
9.2. ሠራተኛ የእርሻውን ምርትና ምርታማነት እዲጎለብት የስራ መመሪያዎችንና ደንቦችን የህብረት
ስምምነቱን እንዲያከብር አስፈላጊውን ድጋፍ ትምህርትና ቅስቀሳ ያደርጋል፡፡ 
9.3. እርሻው የምርት ዕቅዱን እንዲመታ የተሻለ የአሰራር ዘዴን ለመጠቀም በየጊዜው የሚያወጣቸውን
ደንቦች የሚጥስ የሚቃረን ወይም ሊገድብ የሚችል ማንኛውም ተግባር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ
ከመፈፀም ይቆጠባል፡፡ 
9.4. ማህበሩ የሰራተኛ ጉዳዮችን አስመልክቶ በማስታወቂያ ለሠራተኛ ሲያሳውቅ ወይም ሲለጥፍ
ለእርሻው በቅድሚያ ያሳውቃል፡፡ ከእርሻው ፍቃድ ካላገኘ ከመለጠፍ ይቆጠባል፡፡ ድርጅቱም በ 10 ቀናት
ውስጥ በጽሁፍ መፍቀድና አለመፍቀዱን ያሳውቃል፡፡ 
9.5. በህግ ወይም በዚህ የህብረት ስምምሰነት አሰሪው ያገኘውን ህጋዊ መብት የሚጥስ ወይም ሊገድብ
የሚችል ማንኛውም ተግባር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ከመፈፀም ይቆጠባል፡፡ በአሰሪው ላይ
ህገወጥ ተግባርም አይፈጽምም፡፡ 
9.6. ማህበሩ የእርሻው ዕቅድ አወጣጥና ተግባራዊነት ተገቢውን ድጋፍና ተሣትፎ ያደርጋል፡፡ 
9.7. ሠራተኛው የህብረት ስምምነቱን ትርጉምና አፈፃፀም በሚገባ እንዲረዳ ከድርጅቱ ጋር በመተባበር
አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል፡፡ 
9.8. በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 እና የዚህ ማሻሻያ 494/98 የተደነገጉትን ያከብራል፡፡ 
አንቀጽ 10
የእርሻው (የአሰሪው) መብቶች
10.1. በህግ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅና በዚህ የህብረት ስምምነት የተሰጠውን መብት እስካልተቃረነ ድረስ
አሰሪው ከሥራ ውሉ የተነሳ የሰራተኛውን የሥራ እንቅስቃሴ ክንውን የመከታተልና የመቆጣጠር፣ ሥራን
የመምራት፣ የሥራ ዕቅድ የማውጣት፣ ሠራተኛን አዛውሮ የማሠራት፣ ሠራተኛን የማሰናበት ወይም
የመቅጠር፣ የሥነ ሥርዓት (ዲስፕሊን) ማስከበሪያ እርምጃዎችን የመውሰድ፡፡ 
10.2. ለሥራና ለድርጅቱ እድገት ወይም ውጤታማነት የሚረዱ መመሪያዎችን የሥራ ዕቅድ የማውጣት
ተግባራዊነቱንም የመቆጣጠርና የማስፈፀም፡፡ 
10.3. ድርጅቱ ለሥራ ይጠቅመኛል ያለውን ሠራተኛ የመቅጠር፣ የማሳደግ፣ የሠራተኛውን ጥቅም
በማይነካ ሁኔታ ከቦታ ቦታ አዛውሮ የማሠራት፡፡ 
10.4. በዚህ ህብረት ስምምነትና በአዋጅ ቁጥር 377/96 እና በማሻሻያው አዋጅ ቁጥር 494/98
የተደነገጉትን የሥራ ሥርዓት እርምጃዎችን እራሱ አጣርቶ እርምጃ መውሰድ፡፡ 
10.5. በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 እና በማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 494/98 መሠረት የስራ ውልን
የማቋረጥ፣ የሠራተኛ ቅነሣና እገዳ የማድረግ መብት አለው፡፡  
አንቀጽ 11
የሠራተኛ ማህበሩ መብቶች
11.1. በዚህ ህብረት ስምምነትና በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 እና የማሻሻያ አዋጅ ቁጥር
494/98 ስለተመለከቱትም ሆኑ ሌሎች ከስምምነቱ ውጭ ሲያጋጥሙ ስለሚችሉ ማንኛውም የሥራ
ሁኔታ ሠራተኛውን ወክሎ ከአሰሪው ጋር የመነጋገር መብት አለው፡፡ 
11.2. በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 115 የተመለከቱትን ተግባራት የማከናወን፡፡  
11.3. ድርጅቱ በዕድገት አወዳድሮ ለሚመድባቸው ሠራተኞች ማህበሩ ሠራተኛን ወክሎ ያገኛል፡፡ ሆኖም
ድርጅቱ ከሠራተኛው መሃል የተሻለ ይሠራልኛል ብሎ ያመነበትን ያለ ውድድር ሊመድብ ይችላል፡፡  
11.4. ጠቅላላ ሠራተኛውን የሚመለከቱ ከህብረት ስምምነቱና ከአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ 377/96 ውጪ
በድርጅቱ በኩል የሚወጡ መመሪያዎች ተግባራዊ ከመሆናቸው በፊት በቅድሚያ ማህበሩ እንዲያውቅ
ይደረጋል፡፡ ማህበሩም ሊያምንበት ለተግባራዊነቱ ይተባበራል፡፡ 
11.5. በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ 377/96 መሠረት የሠራተኛ ቅነሣ በሚደረግበት ጊዜ ማህበሩ
በአፈፃፀሙ የመሣተፍ መብት አለው፡፡ 
ክፍል ሦስት
የሥራ ውል ለማሻሻልና ከሥራ ውል የሚመነጩ መብትና ግዴታዎችን 
ለጊዜው ስለማገድ
አንቀጽ 12 
የሥራ ውል የሚሻሻልበት ሁኔታ 
12.1. የሥራ ውል የሚሻሻልበት ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሠረት ይሆናል፡፡ 
አንቀጽ 13 
ከስራ ውል የሚመነጩ መብትና ግዴታዎችን ለጊዜው ስለማገድ 
13.1. የሥራ ውል ለጊዜው ለማገድ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 18 መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 
አንቀጽ 14
ቅጥር፣ ዕድገት፣ ዝውውር፣ ውክልናና ተጠባባቂነት
አንቀጽ 14
የሠራተኛ ቅጥር
14.1. ለተወሰነም ሆነ ላልተወሰነ ጊዜ የሚቀጠር ሠራተኛ የሥራው ዓይነት የሥራው ቦታ ለሥራው
የሚከፈለው ደመወዝ መጠን የአከፋፈሉ ሁኔታና ጊዜ እና ውሉ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ የሚዘረዝር ውል
መያዝ ይኖርበታል፡፡ 
14.2. ማንኛውም አዲስ ተቀጣሪ ሠራተኛ የሙከራ ጊዜ 45 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡ 
14.3. በሙከራ ጊዜ ያለ ሠራተኛ የሙከራ ጊዜውን የጨረሰ ሠራተኛ መብትና ግዴታ ይኖረዋል፡፡   
14.4. ጊዜ የተቀጠረ ሠራተኛ ለሥራው ብቁ ካልሆነ አሠሪው ያለማስጠንቀቂያና ያለ ሥራ ስንብት ክፍያና
ካሣ ክፍያ የሥራ ውሉን ሊያቋርጥ ይችላል፡፡ 
14.5. በአዲስ የሚቀጠር ሠራተኛ ለሥራ ብቁ ለመሆኑ የጤና የምርመራ ውጤት እንዲያመጣ ይደረጋል፡፡
ወጪውም በድርጅቱ ይሸፈናል፡፡ 
14.6. የሥራ ውል አመሠራረትና ይዘት በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሠረት ይሆናል፡፡ 
14.7. የውጭ ሃገር ዜጎች ስለሚቀጠሩበት ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሠረት ይሆናል፡፡ 
14.8. በሙከራ ጊዜ ያለ ሠራተኛ እንደ ሥራ ቦታው አስፈላጊነት የአደጋ መከላከያ ቁሳቁስ አስፈላጊ ሆኖ
ሲገኝ ሊሰጠው ይችላል፡፡ 
14.9. የአዲስ ሠራተኛ ቅጥር የሚፈፀመው ቅጥሩ እንዲፈጸም ለሥራ አስኪያጅ ቀርቦ ሲታመንበትና በዋና
ሥራ አስኪያጅ ሲጸድቅ ነው፡፡
አንቀጽ 15
ዕድገት
15.1. አሠሪው በሥራ አፈፃፀሙ የተሻሸለውን ወይም ለድርጅቱ ውጤት ያመጣል ብሎ ያመነበትን
ሠራተኛ ያለውድድር በዕድገት ሊመድብ ይችላል፡፡ 
15.2. የደረጃ ዕድገት የሚሰጠው አንድ የሥራ መደብ በልዩ ልዩ ምክንያት ክፍት ሲሆንና ቦታው በውድድር
እንዲሟላ ለሥራ አስኪያጅ ቀርቦ ሲፈቀድና ይህም በዋና ስራ አስኪያጅ ሲፀድቅ ነው፡፡ 
15.3. ክፍት የሆነውን ቦታ ለማሟላት መጀመሪያ በእርሻዉ ውስጥ ማስታወቂያ ይወጣል፡፡ ብቁ የሆነ ሰው
ከእርሻው ከሌለ እርሻው ከውጭ ሊቀጥር ይችላል፡፡ 
15.4. አንድ ሠራተኛ ከደረጃው በታች ላለ የሥራ መደብ ሊወዳደር አይችልም፡፡ 
15.5. እርሻው ክፍት የሆነውን የሥራ መደብ በውድድር የሚያሟላ ሲሆን ለዚህም የዕድገት ኮሚቴ
ይኖረዋል፡፡ 
አንቀጽ 16
የዕድገት ኮሚቴ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል
 የአስተዳደር መምሪያ ሥራ አስኪያጅ ሰብሳቢ  ሰብሳቢ 
 ዕድገት የሚሰጥበት መምሪያ ኃላፊ  አባል 
 ዕድገት የሚሰጥበት ዋና ክፍል ኃላፊ  አባል 
 የሠራተኛ ማህበር ተወካይ  አባል 
 የሠራተኛ ማህበር ተወካይ  አባል 
 የሠራተኛ አስተዳደር ዋና ክፍል  ፀሐፊ (ድምጽ የሌለው)
አንቀጽ 17
ውድድር የማይደረግባቸው የሥራ መደቦች
17.1. ደረጃ አሥር የሥራ መደብና ከዚያ በላይ ያሉ የሥራ መደቦች ያለውድድር በእርሻዉ በቀጥታ
የሚመደቡ ይሆናሉ፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ከዚህ የሥራ መደብና ደረጃ በታች ያሉ የሥራ መደቦችም እርሻው
ካመነበት በውድድር ወይም ያለውድድር በዕድገት መመደብ ይቻላል፡፡ 
አንቀጽ 18
የደረጃ ዕድገት አወሳሰን በተመለከተ
18.1. የሥራ መደቡን መመዘኛ የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች እንደ ሥራ መደቡ ባህሪ የጽሁፍ፣ የተግባር፣
የቃል እንዲሁም ከሶስቱ በሁለቱ ወይም በሶስቱም በመፈተን በዕድገት ኮሚቴው ተመዝና እድገቱ
በአሸናፊው ይሰጣል፡፡ 
18.2. የሁለቱ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ዕጩዎች ውጤት እኩል ሲሆን በአገልግሎትና በሥራ አፈፃፀም
ብልጫ ላለው ይሰጣል፡፡ 
18.3. ለደረጃ ዕድገት የሚያበቃ ነጥብ በሥራ አፈፃፀሙ የአንድ ዓመት የሥራ አፈጻጸም የግምገማ ውጤት
2.5 እና ከዚያ በላይ የሆነ ሠራተኛን ይመለከታል፡፡ 
18.4. አንድ ሠራተኛ ከያዘው ደረጃ በውድድር በዕድገት ሲያልፍ ለሠራተኛው የሚሰጠው የደረጃ ዕድገት 

ሀ/ እድገት ያገኘበትን ደረጃ መነሻ ደመወዝ ይሆናል፡፡ 


ለ/ እድገት ያገኘበት መነሻ ደመወዝ በፊት ከያዘው ደመወዝ ያነሰ ወይም እኩል የሆነ እንደሆነ እድገት
ያገኘበት ደረጃ ደመወዝ ወደ ጎን ካሉት ዕርከኖች በፊ ከሚያገኘው ደመወዝ ብልጫ ያለውን ዕርከን
ያገኛል፡፡   

18.5. እርሻው የሚያከናውናቸው ቅጥርና ዕድገት በእርሻዉየደመወዝ እስኬል መሠረት ሲሆን እርሻው
በቀላሉ ተገቢውን ባለሙያ ሊያገኝ ለማይችለው የሥራ መደብ በድርድር ሊቀጥር ይችላል፡፡ 
18.6. የሠራተኛ ቅጥር፣ የደረጃ ዕድገትና ዝውውር ዝርዝር አሠራር በድርጅቱ መዋቅርና በአስተዳደር
የሥራ መመሪያ መስፈርት መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 
18.7. አንድ ሠራተኛ በዕድገት፣ በቅጥር ከተመደበ ጀምሮ በቦታው ለአንድ አመት ያህል ጊዜ ካልሠራ
ወደሚቀጥለው ከፍ ያለ የስራ መደብ በዕድገት ሊወዳደር አይችልም፡፡ ሆኖም ከአንድ ዓመት በላይ
አገልግሎት ያላቸው የተጠየቀውን መሥፈርት የሚያሟሉ ካልተገኙ የውስጥ ማስታወቂያውን በድጋሚ
በማውጣት አንድ ዓመት ያልሞላቸው አዲስ ተቀጣሪዎችና ዕድገት ያገኙ ሠራተኞች ሊወዳደሩ ይችላሉ፡፡
ይህም የሚሆነው ድርጅቱ የቀረቡትን ተወዳዳሪዎች ቢመደቡ ለድርጅቱ ይጠቅማሉ ብሎ ካመነ ብቻ
ነው፡፡ 
አንቀጽ 19
ዝውውር
19.1. እርሻው ሲያምንበት ሠራተኛን ከአንድ ክፍል ወደ ሌላ ክፍል በተመሣሣይ ደረጃ አዛውሮ ሊያሰራ
ይችላል፡፡ ሆኖም ለቦታው የሚገባውን የአደጋ መከላከያና ልብስ ይሰጠዋል፡፡ ነገር ግን ድርጅቱ በተመሣሣይ
ደረጃ የሚያሰራው ስራ ከሌለው ከደረጃው ዝቅ አድርጎ ሥራ ያለበት ቦታ በመመደብ ሊያሰራው ይችላል፡፡ 
19.2. ማንኛውም ዝውውር ሲፈፀም ከወር በላይ የሚቆይ ከሆነ ቋሚ ወይም ጊዜአዊ መሆኑ ለሠራተኛው
በጽሁፍ መግለጽ ይኖርበታል፡፡ 
19.3. ሠራተኛው ከተዛወረበት ቦታ ለመሥራት ፈቃደኛ ካልሆነ ድርጅቱ ጥቅሙን ጠብቆ ሊያሰናብተው
ይችላል፡፡ ለማህበሩም በግልባጭ ያሳውቃል፡፡ 
አንቀጽ 20
ውክልና
20.1. ውክልና፡ ማለት አንድ የሥራ ኃላፊ በሥራ ጉዳይና በዓመት ዕረፍት በህመምና በሌሎች በተለያዩ
ምክንያቶች በሥራ ገበታው ላይ ሳይገኝ ሲቀር የሥራ መደቡን ከያዘው የሥራ መደብ ጋር ደርቦ እንዲሠራ
የሚደረግበት አሰራር ነው፡፡ የአወካከል ሥርዓቱም ከሚወከልበት የሥራ መደብ በታች ያለ ሠራተኛ
በመምሪያው ኃላፊ ሲወከልና ይህም በሥራ አስኪያጅ ሊፀድቅ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡  
20.2. በውክልና ተመድቦ የሚሠራ ሠራተኛ ከተመደበበት ዕለት ጀምሮ ለ 26 ቀንና ከዚያ በላይ ከሠራ
የተኪውን የደሞዙን 25% አበል ያገኛል፡፡ ሆኖም ክፍያው በምንም መልኩ ከብር 300 (ሶስት መቶ)
አይበልጥም፡፡ 
20.3. በዚህ ህብረት ስምምነት መሠረት የውክልና አበል የሚሰጠው ለደረጃ አስርና ከዚያ በላይ ላሉ የስራ
መደቦች ይሆናል፡፡ ተወካዩ በስራ መደቡ ላይ በሚያደርሰው ድክመት ተጠያቂ ይሆናል፡፡ ሆኖም ውክልናው
ከ 6 ወር በላይ መብለጥ የለበትም፡፡ 
20.4. ከደረጃ አስር በታች ላሉ የሥራ መደቦች ክፍት በሚሆኑበት ጊዜ የሰራተኛው የክፍል ኃላፊ ሲያዘው
ያለ ደብዳቤ ከሥራ መደቡ ጋር ደርቦ ይሰራል፡፡ ሆኖም ከአንድ ወር በላይ ቦታውን ደርቦ እንዲሰራ ከተደረገ
በጽሑፍ መታዘዝ አለበት በጽሁፍ የተሰጠው ውክልና ከ 6 ወር መብለጥ የለበትም፡፡ 
20.5. የውክልና ወይም የተጠባባቂነት ደብዳቤ በሥራ አስኪያጅ ፊርማ ለመምሪያና ለአገልግሎት ሰቺዎች
ለተወካዩ እንዲደርስ ይደረጋል፡፡ 
አንቀጽ 21
ተጠባባቂ ስለመመደብ
21.1. አንድ የሥራ መደብ በሞት በዕድገት ወይም ሠራተኛው ለቆ በመሄዱ ምክንያት ክፍት ሲሆን
ከእርሻው ውስጥ የስራ መደቡን መመዘኛ የሚያሟላ ሠራተኛን ድርጅቱ በተጠባባቂነት መድቦ ሲያሠራ
ይችላል፡፡ 
21.2. በተጠባባቂነት ተመድቦ ለሚሠራ ሠራተኛ በቦታው ቢያንስ በወር 26 ተከታታይ የሥራ ቀን ከሠራ
የተጠባባቂነት አበል ለሥራ መደቡ የሚከፈለውን ደሞዝ 25% ያገኛል፡፡ ሆኖም ክፍያው በምንም መልኩ
ከብር 300 (ሶስት መቶ) አይበልጥም፡፡ 
21.3. በዚህ ህብረት ስምምነት መሠረት የተጠባባቂ አበል የሚሰጠው ለደረጃ አሥርና ከዚያ በላይ ላሉ
የስራ መደቦች ይሆናል፡፡ 
21.4. በተጠባባቂነት የሚሠራውን ሠራተኛ ከ 6 ወር በላይ ማሠራት አይቻልም፡፡ የተመደበው ሰው
ለቦታው ብቁ ከሆነ በቀጥታ ቦታው ይሰጠዋል ብቁ ካልሆነ በ 6 ወር ጊዜ ውስጥ ቦታው በውድድር ወይም
በምደባ መሟላት ይኖርበታል፡፡ 
አንቀጽ 22
የሥራ አፈጻጸም ምዘና
22.1. የሥራ አፈጻጸም ምዘና ሠራተኛው የተመደበበትን የሥራ መደብ እንዲያከናውን በተሰጠው የሥራ
ዝርዝር መሠረት የአእምሮና የአካል ብቃቱን በመጠቀም የተሰጠውን ሥራ በአጥጋቢ ሁኔታ ማከናወኑን
ለማወቅ የሚደረግ ግምገማ ነው፡፡ 
22.2. የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ውጤት ከዚህ ለሚከተሉት ዓላማዎች ይረዳል፡- 
ሀ. አጥጋቢ የሥራ አፈጻጸም ያገኘን ሠራተኛ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ደረጃ ለማሳደግ፣ 

ለ. በሥራ አፈጻጸም ግምገማ መሠረት የደመወዝ ጭማሪ፣ የማበረታቻ ክፍያዎችን፣ የቦነስ ሥጦታን
ለመወሰንና ለመደልደል እንዲያመች፣ 
ሐ. የሥራ ድክመት ያለባቸውን ሠራተኞች ለይቶ በማወቅ ችግራቸውን ተረድቶ የሥራ አፈፃጸማቸውን
እንዲያሻሸሉ ለማድረግ፣ 
መ. በሥራ ላይ ድክመት ያለበትን ሠራተኛ በሥልጠና ድክመቱን እንዲያሻሽል ለማድረግ፣  

22.3. እያንዳንዱ ሠራተኛ የሥራ አፈጻጸሙን እንዲያየውና እንዲፈርም ይደረጋል፣ የስራ አፈጻጸም


ምዘናው በዓመት አንድ ጊዜ ይደረጋል፡፡ 
22.4. በሥራ አፈጻጸሙ ከአምስት ነጥብ 2.5 በታች ያመጣ ሠራተኛ ለዕድገትና ለተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች
ተካፋይ አይሆንም፡፡ 
ክፍል አምስት
ትምህርት ስልጠና
አንቀጽ 23
ትምህርት
23.1. ሠራተኛው ለድርጅቱ የተሻለ ሥራና እድገት እራሱን ለማዘጋጀት በትርፍ ጊዜው ለመማር ሲጠይቅ
አሠሪው የሙያ ምክር ይሰጣል፡፡ ለሚማርበት ትምህርት ቤትም የትብብር ደብዳቤ ይጽፍለታል፡፡ 
23.2. ድርጅቱ ለሥራው አስፈላጊ ነው ብሎ ካመነ ከፍሎ ሊያስተምር ይችላል፡፡ 
23.3. አንድ ሠራተኛ በእርሻዉወጪ ከተማረ ትምህርት እንዳጠናቀቀ በቀጣይ ሁለት ዓመት እርሻውን
የማገልገል ግዴታ አለበት፡፡ 
23.4. አንድ ሠራተኛ ሁለት ዓመት ሳያገለግል ቢወጣ ከተማረ በኋላ ያገለገለበት ጊዜ
በንጽጽር (Proportion) ተሰለልቶ የተማረበትን ሂሳብ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ ይህም ከሚያገኘው
ማንኛውም ክፍያ ይቀነሳል፡፡ ሆኖ ሲገኝ ሠራተኛው ከራሱ ቀሪውን ክፍያ ይከፍላል፡፡ ይህ
ካልሆነም ሠራተኛ ውል የገባበትን ጊዜ የማገልገል ግዴታ አለበት፡፡ 
23.5. ለቋሚ ሠራተኞች ለብሔራዊ ፈታናዎች በግል ተምረው ለሚፈተኑ ሠራተኞች በሚያቀርቡት
ማስረጃ ለአንድ ጊዜ የ 3 ቀን ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡ 

አንቀጽ 24
ስልጠና
24.1. ድርጅቱ ለሥራው ይጠቅመኛል ብሎ ካመነ ለሠራተኛው ወጪውን ሸፍኖ የስልጠና ዕድል ሊሰጥ
ይችላል፡፡ 
24.2. የድርጅቱ ሠራተኛ በማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ወይም በሠራተኛ ማህበር ፌዴሬሽንና
ኮንፌዴሬሽን በሚያዘጋጀው የሙያ ትምህርት ፕሮግራሞችና ስብሰባዎች ላይ ተካፋይ እንዲሆን
በሚጠየቅበት ጊዜ ሥራን በማይበድል ሁኔታ ድርጅቱ ከክፍያ ጋር ፍቃድ በመስጠት ይተባበራል፡፡ 
24.3. ድርጅቱ አንድን ሠራተኛ ለሥልጠና ወደ ውጭ ሀገር ሲልክ የመጀመሪያ 6 ወር ሙሉ ደመወዙን
ለተወካዩ ይከፍላል ወይም በባንክ ያስቀምጣለታል፡፡
ክፍል ስድስት
የሥነ ሥርዓት እርምጃ አወሳሰድና የቅሬታ አቀራረብ ሥነ ሥርዓት 
አንቀጽ 25
የሥነ ሥርዓት እርምጃ አወሳሰድ
25.1. በሠራተኛው ላይ የሚወሰድ የሥነ ሥርዓት እርምጃ ሆን ተብሎ ሠራተኛን ለመጉት የታለመ መሆን
የለበትም፡፡ 
25.2. በዚህ ህብረት ስምምነት መሠረት አንድ ሠራተኛ በጥፋቱ ሲቀጣ የቅጣቱ ወረቀት ለሠራተኛው
መድረስ አለበት፡፡ 
25.3. የቅጣቱና የማስጠንቀቂያ ዕድሜ ለአንድ ዓመት ይሆናል፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ቅጣቱም ሆነ
ማስጠንቀቂያው በግል ማህደር የሚቀመጥ ሆኖ በበጀት ዓመቱ በሚያጠፋው ጥፋት እንደገና በአዲስ
ይጀመራል፡፡ ሆኖም የሠራተኛው የቀድሞ ጥፋቶች በዕድገት ውድድር እንደ አንድ መመዘኛ ነጥብ ሊወሰድ
ይችላል፡፡ /የሁለት ተከታታይ ዓመት ቅጣት በውድድር ወቅት በመመዘኛነት ይወሰዳል/፡፡ 
25.4. ማንኛውም ሠራተኛ መከለሉን ሳያውቅ ወይም ሳይሰማ የሥነ ሥርዓት እርምጃ (ቅጣት)
ሊወሰድበት አይችልም፡፡ 
25.5. ኃላፊው የሥነ ሥርዓት እርምጃ ከመውለዱ በፊት ሠራተኛው በትክክል ማጥፋቱን ማረጋገጥ
ይኖርበታል፡፡ 
25.6. ማንኛውም ሠራተኛ ከመምሪያው ሥራ ጋር በተያያዘ ጥፋት መፈፀሙን የቅርብ አለቃው የጥፋቱን
ዝርዝር በመግለጽ ፈርሞ ለአስተዳደር ይልካል፡፡ የአስተዳደር ሠራተኛውም በዚህ ህብረት ስምምነትና
በአዋጅ 377/96 የተመለከቱትን የሥነ ስርዓት እርምጃዎች ይወስዳል፡፡ 
25.7. በእርሻዉቅጥር ግቢ ለሚፈፀሙ አጠቃላይ ጥፋቶችና የሥነ ሥርዓት ጉድለቶች ለአስተዳደር
መምሪያ ሪፖርት ሲደርስ ወይም በመምሪያው ሲደርስበት የአስተዳደር መምሪያው አጣርቶ የሥነ ሥርዓት
ርምጃ ሊወሰድ ይችላል፡፡ 
አንቀጽ 26
ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ስለማቋረጥ
26.1. በእርሻዉሰነዶች፣ በግል ማህደሮች፣ በሰዓት መቆጣጠሪያ ሰነድ ላይ፣ አስቀድመው የተፃፉትን
እውነተኛ ነገሮች ሆንብሎ ለማጭበርበር እውነተኛውን ትቶ ሌላ ነገር የጨመረ የደለዘ፣ ያጠፋ፣ የሰረዘ፣
የቀየረ ወይም የእርሻውን ህልውና ለማሣጣት ሚስጥር ያባከነ፣ የሃሰት ማስረጃ ያቀረበ በውጤት ክፍያና
ሰነዶች ላይ ሆን ብሎ ለመጥቀም ሀሰት የመዘገበ፡፡ 
26.2. እርሻውን የሚጎዳ ፈንጂ ወይም ድምጽ የሌላው መሣሪያ ይዞ በእርሻዉቅጥር ግቢ የተገኘ፣ 
26.3. በኃላፊነት በተረከባቸው የእርሻው ንብረቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ፣ 
26.4. በእርሻዉቅጥር ግቢ ውስጥ ቁማር የሚጫወት፣ 
26.5. በእርሻዉቅጥር ግቢ ውስጥ ባልተፈቀደ ቦታ ሲጋራ ሲያጤስ የተገኘ፣ 
26.6. በእርሻዉዓርማና ማህተም አላግባብ የተጠቀመ ሠራተኛ፣ 
26.7. በኃላፊነት የተሰጠውን የእርሻንብረት ሆን ብሎ ያጎደለ፣ 
26.8. የእርሻውን ንብረት ደብቆ ሊያወጣ ሲል የተገኘ፣ 
26.9. ማንነቱን ለመደበቅ የሐሰት የምስክር ወረቀት ያቀረበና በግል ማህደር ያስቀመጠ ወይም
እንዲቀመጥ ያደርገ፣
26.10. በእርሻዉየውጭ መስመር መኪኖች ያልተፈቀደለትን ጭነነት ጭኖ የተገኘ፣ 
26.11. በሚያሽከረክረው መኪና የደረሰውን ግጭት በወቅቱ ለሚመለከተው ኃላፊ ያላሳወቀ ወይም
የደበቀ ሾፌር፣ 
26.12 በማንኛውም ሁኔታ ውላቸው በተቋረጠ ሠራተኞች ስም መብትና ጥቅም ለራሱ ጥቅም ያዋለ
ወይም አሣልፎ የሰጠ፣ 
26.13. በሠራተኛ ሰርቪስ ውስጥና መሣፈሪያ ስፍራ ፀብና አንባጓሮ በማስነሣት አገልግሎት እንዲታወክ
ያደርገ፣ 
26.14. ከእርሻው ዕውቅና ውጪ ልዩ ልዩ እትሞችንና የማስፈረሚያ ሊስቶችን ማዞርና ማስፈረም
የማስታወቂያ መለጠፊያ ላይ መለጠፍ ያለፈቃድ ስብሰባ መጥራት፣     
26.15. በእርሻዉቅጥር ግቢ ደብደባ የፈፀመ በማስረጃ ሲረጋገጥ፣ 
26.16. በወንጀል ተፈርዶበት ከ 30 ቀን በላይ የታሰረ 
26.17. በእርሻውና በሰራተኛው ላይ የሐሰት ወሬ የነዛ ሕገወጥ አድማና አመጽ ያነሣሣ፣ 
26.18. የሥራ ቦታውን ትቶ የሄደ የጥበቃና የህክምና ሠራተኛ፣ 
26.19. በስራ ቦታ ወይም በእርሻዉውስጥ በስራ ሰዓት ተኝቶ የተገኘ ሠራተኛ፣ 
26.20. ሆን ብሎ የኤሌክትሪክና የቴሌፎን መገናኛ መስመር እንዳይሰራ አድርጎ የተገኘ፣ 
26.21. ከባለ ጉዳይ ወይም ከሠራተኛው ላይ ጉቦ የተቀበለ ወይም የሰጠ፣ 
26.22. ሠራተኛው በሥራ ዝርዝሩ የተመለከተውን ሥራ ለመሥራት ችሎታ እያለው የማምረቻ
መሣሪያና ጥሬ ዕቃ ተሟልተውለት ከተወሰነው የምርት ጥራት ዓይነትና መጠን በታች በተደጋጋሚ
ያመረተ ወይም የሰራ፣ 
26.23. በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 ያለማስጠንቀቂያ ከሥራ የሚያሰናበቱትን የፈፀመና በዚህ
ህብረት ስምምነት እንዲሠራ የታዘዘውን ሥራ ለመሥራት ፈቃደኛ ያልሆነ ሠራተኛ፡፡ 
አንቀጽ 27
በማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ስለማቋረጥ
27.1. በአሠሪው አነሣሽነት በማስጠንቀቂያ የሚደረግ የስራ ውል መቋረጥ በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር
377/96 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 
27.2. በሠራተኛው አነሣሽነት በማስጠንቀቂያ የሚቋረጥ የሥራ ውል በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር
377/96 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 
27.3. በሌላ ሁኔታ በአሠሪውም ሆነ በሠራተኛው አነሳሽነት የሚደረግ የሥራ ውል መቋረጥ በአዋጅ ቁጥር
377/96 እና በማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 494/98 መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡  
አንቀጽ 28 
ደረጃ በደረጃ የሥነ ሥርዓት እርምጃ የሚሰሰጥባቸው ጥፋቶችና የቅጣት ዓይነቶች 
28.1. ከዚህ በታች በደረጃ የሚወሰደው የሥነ ሥርዓት እርምጃ አንዱ ለአንዱ ተወራራሽ አይሆንም፡፡ 
የቅጣቱ መጠንና ጥፋት
ተ.ቁ የጥፋቱ ዓይነት 6ኛ
1 ኛ ጥፋት 2 ኛ ጥፋት 3 ኛ ጥፋት 4 ኛ ጥፋት 5 ኛ ጥፋት
ጥፋት
1. ያለፈቃድ ወይም ያለበቂ የጽሁፍ የ 1 ቀን ደመወዝ  የ 2 ቀን የ 5 ቀን ከስራ
ምክንያት የሥራ ቦታውን ትቶ ማስጠንቀቂያ  ደመወዝ  ደመወዝ  ስንብት
የሄደ ወይም በግቢው ውስጥ
ሲዘዋወር የተገኘ
2. ያለፈቃድ ወይም ያለበቂ የጽሑፍ የ 2 ቀን ደመወዝ  የ 3 ቀን የ 5 ቀን 1/3 የወር ከሥራ
ምክንያት ከስራ 1 ቀን የቀረ  ማስጠንቀቂያ  ደመወዝ  ደመወዝ ደመወዝ  ስንብት 
3. ያለፈቃድ ወይም ያለበቂ የ 1 ቀን ደመወዝ  የ 3 ቀን ደመወዝ  የ 5 ቀን 1/3 የወር ከሥራ
ምክንያት ከስራ 2 ቀን በተከታታይ ደመወዝ  ደመወዝ  ስንብት 
የቀረ 
4. ያለፈቃድ ወይም ያለበቂ የ 2 ቀን ደመወዝ  የ 4 ቀን ደመወዝ  የ 5 ቀን 1/3 የወር ከሥራ
ምክንያት ከሠራ 3 ቀን በተከታታይ ደመወዝ  ደመወዝ  ስንብት 
የቀረ 
5. ያለፈቃድ ወይም ያለበቂ የ 3 ቀን ደመወዝ  የ 5 ቀን ደመወዝ  የ 6 ቀን 1/3 የወር ከሥራ
ምክንያት ከሥራ 4 ቀን ደመወዝ  ደመወዝ  ስንብት 
በተከታታይ የቀረ  

6. ያለፈቃድ ሰዓቱን አስሞልቶ የ 10 ቀን ደመወዝ  የ 15 ቀን የአንድ ወር ከሥራ


ሥራውን ትቶ ከእርሻው ቅጥር ደመወዝ  ዕገዳ  ስንብት 
ግቢ ውጭ የሄደ 
7. ያለፈቃድ ወይም ያለበቂ የጽሁፍ የ 1 ቀን ደመወዝ  የ 2 ቀን የ 3 ቀን የ 5 ቀን ከሥር
ምክንያት ከሥራ ሰዓት ከ 20-30 ማስጠንቀቂያ  ደመወዝ  ደመወዝ  ደመወዝ  ስንብት 
ደቂቃ ዘግይቶ የገባ ወይም ቀድሞ
የወጣ 
8. በሥራ ሰዓት እንዲጠቀምበት የጽሁፍ የ 1 ቀን ደመወዝ  የ 2 ቀን የ 5 ቀን ከሥራ
የተሰጠውን የሥራ ልብስና የአደጋ ማስጠንቀቂያ  ደመወዝ  ደመወዝ  ስንብት
መከላከያ አድርጎ የማይሰራ
ሰራተኛ 

9. በሥራ ላይ ሆኖ ለበላዮቹ ወይም የ 2 ቀን ደመወዝ  የ 3 ቀን ደመወዝ  የ 5 ቀን ከስራ


ለበታቾቹ ህገወጥ ፀባይ የሚያሳይ ደመወዝ  ስንብት 
ሰራተኛ 

10. በመጠጥ ወይም በአደንዛዥ ዕፅ የ 5 ቀን ደመወዝ  የ 10 ቀን የ 15 ቀን ከሥራ


ተመርዞ ወደ ሥራ የገባ ሠራተኛ ደመወዝ  ደመወዝ  ስንብት 
ወደ ቤት እንዲመለሰ ሆኖ 

11. በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሠረት የ 2 ቀን ደመወዝ  የ 3 ቀን ደመወዝ  የ 5 ቀን 1/3 የወር ከሥራ
ትርፍ ሰዓት እንዲሠራ ታዝዞ ደመወዝ  ደመወዝ  ስንብት 
ከተስማማ በኋላ ያለበቂ ምክንያት
የቀረ ወይም አልሰራም ያለ
ሰራተኛ 
12. ሲገባ አልፈተሸም ያለ ሠራተኛ የ 3 ቀን ደመወዝ  የ 5 ቀን ደመወዝ  1/3 የወር ከሥራ
ወደ ስራ እንዳይገባ ደመወዝ  ስንብት 
ይደረጋል፡፡ ከሥራ የሚወጣ
አልፈተሽም ያለ ሠራተኛ ለህግ
እንዲቀርብ ሆኖ 
13. በሥራ ቦታ ላይ የበላይም ሆነ 5 ቀን ደመወዝ  የ 10 ቀን የ 15 ቀን ከሥራ
የበታች ሠራተኞችን የተሳደበ ደመወዝ  ደመወዝ  ስንብት 
በማስረጃ ሲረጋገጥ 

14. በህጋዊ መንገድ መደበኛ ስራውን የ 2 ቀን ደመወዝ  የ 5 ቀን ደመወዝ  የ 15 ቀን ከሥራ


ለማከናወን እምቢተኛ ሆኖ ደመወዝ  ስንብት 
የተገኘ 

15. የተሰጠውን ትዕዛዝ አላግባብ የ 2 ቀን ደመወዝ  የ 5 ቀን ደመወዝ  የ 15 ቀን ከሥራ


የፈፀመና ሥራውን ሆነ ብሎ ደመወዝ  ስንብት 
ያበላሸ የንብረቱን ወቅታዊ ዋጋ
ከፍሎ  
16. በእርሻዉአጥር ዘልሎ ዘልሎ ወይም 1/3 የወር ደመወዝ  ከሥራ ስንብት 
ሾልኮ መግባትና መውጣት  

17. በኃላፊው እንዲሰራ የተሰጠውን የ 1 ቀን ደመወዝ  የ 2 ቀን ደመወዝ  የ 5 ቀን የ 6 ቀን 1/3 የወር ከሥራ


የሥራ ትዕዛዝ ወይም መመሪያ ደመወዝ  ደመወዝ  ደመወዝ  ስንብት 
ተቀብሎ ያለመፈፀም   

18. ጥጥን ኬሚካልን ወይም ሌሎች በጥፋት ተጠያቂ በጥፋቱ ተጠያቂ በጥፋቱ ከሥራ
ጥሬ ዕቃዎችን በግድየለሽነት ሆኖ የ 1 ቀን ሆኖ የ 3 ቀን ተጠያቂ ሆኖ ስንብት 
ያባከነ    ደመወዝ     ደመወዝ  የ 5 ቀን
ደመወዝ 
19. የእርሻውን የግቢ ጽዳት የጽሁፍ የ 1 ቀን ደመወዝ  የ 2 ቀን የ 5 ቀን ከሥራ
በመፀዳዳት ወይም በመሳሰሉት ማስጠንቀቂያ  ደመወዝ  ደመወዝ   ስንብት 
የሚያበላሽ 

20. ተረኛ ሆኖ በምድብ ሥራው ላይ የ 5 ቀን ደመወዝ  የ 6 ቀን ደመወዝ  የ 10 ከሥራ


የማይገኝ የጥበቃ፣ የጤና ባለሙያ፣ ደመወዝ  ስንብት 
የኢንሹራንስ ወይም የሰርቪስ
ሹፌር የእሳት አደጋ ሰራተኛ 
21. ለፍተሻ ሲጠየቅ መጥፎ ስነምግባር የጽሁፍ የ 2 ቀን ደመወዝ  የ 5 ቀን ከሥራ
ያሣየ ሠራተኛ እንዲሁም የፍተሻ ማስጠንቀቂያ  ደመወዝ  ስንብት 
ሰራተኛ ሆኖ ያለአግባብ
ያመናጨቀ 
22. በስራ ቦታ ላይ የሚያፌዝና እራሱ የጽሁፍ የ 2 ቀን ደመወዝ  የ 5 ቀን ከሥራ
ስራ ፈትቶ ሌላውን ሥራ ማስጠንቀቂያ  ደመወዝ  ስንብት 
የሚያስፈታ ሠራተኛ 

23. የቅጣት ወረቀት የክስ ቻርጅ እና የ 2 ቀን ደመወዝና የ 5 ቀን ደመወዝና የ 7 ቀን ከሥራ


ሌሎችንም ሰነዶች ፈርሞ እስኪፈርም እስኪፈርም ደመወዝ  ስንብት 
እንዲወስድ ሲጠየቅ ወይም (እስኪወሰድ) ተግዶ /እስኪወስድ
እንዲፈርድ ሲጠየቅ ፍቃደኛ ይቆያል  ታግዶ ይቆያል/
ያልሆነ 
24. የእርሻው ተሽከርካሪ ከተመደበለት የ 5 ቀን  1/3 የወር ከሥራ
ሥራ ውጪ ማዋል  ደመወዝ  ስንብት 

25. በበዓል ዋዜማና ማግስት ያለበቂ የ 2 ቀን ደመወዝ  የ 3 ቀን ደመወዝ  የ 5 ቀን ከሥራ


ምክንያት ከሥራ የቀረ   ደመወዝ  ስንብት 

26. በሐሰት ሠራተኛን የከለለ ወይም የ 2 ቀን ደመወዝ  የ 3 ቀን ደመወዝ  የ 4 ቀን ከሥራ


እንዲከሰሰ ያደረገ  ደመወዝ  ስንብት 

27. የስራ ቦታውን ለተተኪው የ 3 ቀን ደመወዝ  የ 5 ቀን ደመወዝ  1/3 የወር ከሥራ


ሳያስረክብ የሄደና በሥዓት ደመወዝ  ስንብት 
ያልተገኘ የጥበቃ የህክምና የእሳት
አደጋ ሠራተኛና ሹፌር 
28. በሐኪም የተሰጠውን መረጃ የጽሁፍ የ 1 ቀን ደመወዝ  የ 2 ቀን  የ 5 ቀን ከሥራ
ሕክምናውን እንደጨረሰ በወቅቱ ማስጠንቀቂያ  ደመወዝ  ስንብት 
ያላቀረበ ሠራተኛ 

29. ፈቃድ ጠይቅ የክፍል አለቃው የ 1 ቀን ደመወዝ  የ 3 ቀን ደመወዝ  የ 5 ቀን 1/3 የወር ከሥራ
ሳይፈቅድለት ሥራውን ትቶ የሔደ ደመወዝ  ደመወዝ  ስንብት 
ሠራተኛ  

30. ሠራተኛውንና ሥራውን የ 3 ቀን ደመወዝ  የ 4 ቀን ደመወዝ  የ 5 ቀን 1/3 የወር ከሥራ


የማይቆጣጠር የሥራ ኃላፊ  ደመወዝ  ደመወዝ  ስንብት 

31. እሁድ እና በበዓል ሥራ ታዝዞ ሥራ የ 8 ቀን ደመወዝ  የ 10 ቀን ከሥራ


ያልገባ የእሳት አደጋ፣ ሹፌር፣ ደመወዝ  ስንብት 
የኤሌክትሪክ፣ የውሃ ክፍል የጤና
አገልግሎትና የሠዓት ቁጥጥር
ሰራተኛ 
32. ተተኪ ሠራተኛ ሳይገባለት ሥራ የ 5 ቀን ደመወዝ  የ 6 ቀን ደመወዝ  የ 15 ቀን ከሥራ
ትቶ የወጣ የእሳት አደጋ፣ ሹፌር፣ ደመወዝ  ስንብት 
የኤሌክትሪክ ፣ የውሃ ክፍል፣ የጤና
አገልግሎትና የሥዓት ቁጥጥር
ሠራተኛ 
አንቀጽ 29
የቅሬታ አቀራረብ ሥነ ሥርዓት
29.1. ሠራተኛው የተወሰደበት የሥነ ሥርዓት እርምጃ ያ አግባብ ነው ብሎ ካመነ ቅሬታውን በ 3 ቀን
ውስጥ በማመልከቻ ለክፍል ኃላፊው ያቀርባል፡፡ 
29.2. የክፍል ኃላፊው በ 2 ቀን ውስጥ በጽሁፍ ውሳኔ ይሰጠዋል፡፡ ሠራተኛው በክፍል ኃላፊው ውሳኔ
ካልረካ በተዋረድ እስከ መምሪያ ኃላፊው ያመለክታል ሁሉም በ 2 በ 2 ቀን ጊዜ ውስጥ ውሳኔአቸውን
ያሳውቃል፡፡ የመምሪያ ኃላፊው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፡፡ 
29.3. ማንኛውም ቅሬታ ከአንድ በላይ በተዘረዘረው ጊዜ ጠብቆ ካልቀረበ ተቀባይነት የለውም፡፡ 
29.4. ከሥራ ያለፈቃድ የቀረ፣ ያረፈደ፣ በሥራ ገበታው ላይ ያልተገኘ ሠራተኛን በክፍሉ ኃላፊ
በሚያቀርበው የሥነ ሥርዓት እርምጃ መሠረት ድርጅቱ እርምጃ ይወስዳል፡፡ 
29.5. ያለፍቃድ ከሥራ የቀረን ሠራተኛ በማግስቱ የቀረቡትን ምክንያት ለክፍል ኃላፊው አሳውቆ ነፃ
ፍቃድ ካልተሞላበት በአንቀጽ 29.4 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 
አንቀጽ 30
ቅጣትን ስለማሻሻል
30.1.ድርጅቱ ስለተወሰደው የሥነ ሥርዓት እርምጃ አጥጋቢና በቂ ነው ብሎ ካላመነ በሠራተኛው ላይ
ተወሰደውን የሥነ ሥርዓት እርምጃ የማቅለል ወይም የመሠረዝ መብት አለው፡፡ 
ክፍል ሰባት
ስለ ሥራ ስንብት ክፍያና ካሳ
አንቀጽ 31
የሥራ ስንብት ክፍያ የሚሰጥበት ሁኔታ
31.1. የሙከራ ጊዜውን የጨረሰና በአዋጅ ቁጥር 377/96 እና በማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 494/98 መሠረት
የስራ ውሉ የተቋረጠ ሠራተኛ በአዋጁ መሠረት የሥራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት አለው፡፡ 
31.2. አንድ ሠራተኛ የሥራ ስንብት ክፍያ ከማግኘቱ በፊት ቢሞት የሥራ ስንብት ክፍያ በአዋጅ ቁጥር
377/96 አንቀጽ 110/2 ለተመለከቱት ጥገኞች ይከፈላል፡፡ 
አንቀጽ 32
የስራ ስንብት ክፍያ መጠን
ሀ/ ለመጀመሪያ የአንድ ዓመት አገልግሎት የሠራተኛው የመጨረሻው ሳምንት አማካይ የቀን ደመወዙን
በሰላሳ ተባዝቶ ይከፈለዋል፡፡ ከአንድ ዓመት በታች ያገለገለ ሠራተኛ ግን እንደ አገልግሎት ጊዜው በንጽጽር
እየተተመነ ተሠርቶ ይከፈለዋል፡፡ 
ለ/ ከአንድ ዓመት በላይ ያገለገለ ሠራተኛ በአንቀጽ 32.ሀ በተጠቀሰው ክፍያ ለእያንዳንዱ ተጨማሪ
የአገልግሎት ዓመት የደመወዙ አንድ ሦስተኛ (1/3) እየታከለ ይከፈለዋል፡፡ ሆኖም ጠቅላላ ክፍያው ከአስራ
ሁለት ወራት ደመወዙ መብለጥ የለበትም፡፡ 
ሐ/ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 24/4 እና አንቀጽ 29 መሠረት የሥራ ውል ሊቋረጥ በዚህ ህ/ስምምነት
አንቀጽ 32.ሀ እና ለ ከተመለከተው በተጨማሪ የሠራተኛው የመጨረሻ ሳምንት የቀን ደመወዙ በ 60
ተባዝቶ ይከፈለዋል፡፡ 
መ/ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 32 ንዑስ አንቀጽ 1 (አንድ) መሠረት የሥራ ውሉን የሚያቋርጥ
ሠራተኛ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 40 ከተመለከተው የሥራ ስንብት በተጨማሪ የመጨረሻ ሣምንት
አማካይ የቀን ደመወዝ በ 30 (ሰላሳ) ተባዝቶ ካሳ ይከፈለዋል፡፡ ይህም አግባብ ባለው ፍ/ቤት ሲወሰን
የሚፈጸም ይሆናል፡፡ ይህ ድንጋጌ አግባብ ባለው የጡረታ ህግ በተሸፈነ ሠራተኛ ላይ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡ 
አንቀጽ 33 
የምስክር ወረቀት አሰጣጥ 
33.1 አንድ ሰራተኛ የሥራ ውሉ ሲቋረጥ ክሊራንሱን አዙሮ ከጨረሰና መረጃው እንዲሰጠው ሲጠይቅ
ወይም በሥራ ላይ እያለ የሥራ ልምድ እንዲሰጠው በደብዳቤ ሲጠይቅ የጠየቀው መረጃ ይጻፍለታል፡፡ 
33.2. አንድ የሥራ ልምድ ከተጻፈ በኋላ ሁለተኛ የሥራ ልምድ ለማጻፍ ቢያንስ 6 ወር መቆየት አለበት፡፡ 
33.3. የምስክር ወረቀት ወይም የሥራ ልምድ የሚከተሉትን ማካተት ይኖርበታል፡፡ 
ሀ. የሠራተኛውን ሥም  ሐ. የሥ ቦታው  ሠ. የሚያገኘው ደመወዝ
ለ. የሥራው ዓይነት  መ. የአገልግሎት ዘመን  ረ. የስራ ግብር መክፈሉን የሚገልጽ 
አንቀጽ 34
በሥራ ምክንያት ስለሚመጡ ጉዳቶች ከሳ ክፍያ /ኢንሹራንስ/
34.1. በአዋጅ ቁጥር 377/96 እና በዚህ ህብረት ስምምነት መሠረት በሥራ ላይ የሚደርስ ጉዳት ማለት
በሥራ ላይ የሚደርስ አደጋ ወይም ከሥራ ምክንያት የሚመጣ በሽታ ነው፡፡ ይኸም ከዚህ የሚከተሉትነን
ይጨምራል፡፡ 
ሀ/ ሠራተኛው ከሥራ ቦታው ወይም ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጪም ቢሆን የአሰሪውን ትዕዛዝ ስራ ላይ
ያውል በነበረበት ጊዜ የደረሰ ጉዳት፡፡  
ለ/ ሠራተኛው ከቤቱ ወደ ስራ ቦታው ወይም ከሥራ ቦታው ወደ ቤቱ ሲጓጓዝ የደረሰ ጉዳት፡፡  
ሐ/ ሠራተኛው ሥራውን በማከናወን ላይ እያለ በድርጅቱ ወይም በሌላ ሶስተኛ ወገን ድርጊት ምክንያት
የደረሰበት ጉዳት፡፡ 
34.2. በሥራ ላይ ለደረሰ ጉዳት የሚሰጠው የካሳ ክፍያ /ኃላፊነት ወሰን/ እርሻው ለዚህ ጉዳት ከመድህን
ድርጅት ጋር በገባው ስምምነት ወይም የመድህን ዋስትና ውል መሠረት ብቻ ነው፡፡ 
34.3. በዚሁ መሠረት የኢንሹራንስ መብት ያለው ሠራተኛ ለደረሰበት ጉዳት በ 24 ሰዓት ውስጥ ለእርሻው
ክሊኒክ ወይም በወቅቱ ላለ የሥራ ኃላፊ በማስመዝገብ በቀጣይ ሶስት ምስክሮችን አስመስክሮ
ፈርመውበት ማቅረብ አለበት፡፡ ሠራተኛው በጉዳቱ አማካኝነት ሪፖርት ማድረግ ካልቻለ ቤተሰቡ ሪፖርት
ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በተወሰነው ጊዜ ያልተመዘገበ ጉዳት ተቀባይነት አይኖረውም፡፡  
34.4. በራሱ ላይ ሆን ብሎ ማንኛውንም ጉዳት ያደረሰ ሰራተኛ እርሻው ኃላፊነት አይኖረውም፡፡ በተለይም
በሚከተሉት ድርጊቶች የሚመጣ ጉዳት በራሱ ላይ ሆን ብሎ ያደረሰ ጉዳት ሆኖ ይቆጠራል፡፡ 
ሀ. አካሉን ወይም አእምሮውን ለመቆጣጠር በማይችልበት ሁኔታ በአደንዛዥ ዕጾች፣ በመጠጥ ደንዝዞ
በሥራ ላይ መገኘት፣ 
ለ. በአሰሪው አስቀድሞ የተሰጠውን የሥራ ልብስና የአደጋ መከላከያዎች አለመጠቀምና የአደጋ መከላከያ
ደንቦችንና መመሪያዎችን መጣስ፣ 
34.5. ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ መሰረት በስራ ላይ የሚመጣ ጉዳት
መድረሱን አግባብ ላለው አካል ድርጅቱ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡   
35.6. በድርጅቱ ሠራተኛ ላይ የደረሰው ጉዳት ሞት ወይም የአካል ጉድለት ያስከተለ ከሆነ ድርጅቱ
የኢንሹራንስ ክፍያውን ለማስፈጸም እገዛ ያደርጋል፡፡ 
ክፍል ስምንት
አንቀጽ 35
የአደጋ መከላከያ የሥራ ልብስ አሰጣጥ
35.1. እርሻው ለሠራተኛው እንደ ሥራው ባህሪ የሚያስፈልገውን የሥራ ልብስና የአደጋ መከላከያ
ይሰጣል፡፡ 
35.2. ሠራተኛው ለሥራ ተብሎ የተሰጠውን የሥ ልብስ የአደጋ መከላከያ በመደበኛ የሥራ ሰዓቱ
ምንጊዜም ለብሶ መገኘት አለበት፡፡ 
35.3. በማንኛውም ሁኔታ የሥራ ውሉ የተቋረጠ ሠራተኛ የሥራ ልብስ፣ ጫማ የአደጋ መከላከያ ቁሳቁስ
ወዘተ አይሰጠውም፡፡ 
35.4. የአደጋ መከላከያና የሥራ ልብስ የሚያስፈልጋቸው 
ሀ. የምርትና ቴክኒክ መምሪያ ሠራተኞች በሙሉ 
ለ. የጥራት ቁጥጥር አገልግሎት ሠራተኞች በሙሉ 
ሐ. ከአስተዳደር መምሪያ የትራንስፖርት፣ የጥበቃ፣ የክሊኒክ፣ የተላላኪና ጽዳት፣ የሰዓት ቁጥጥርና
የመዝገብ ቤት ፐርሶኔክ ክለርክ ሠራተኞች
መ. ከንግድ መምሪያ የንብረት ክምችት ሠራተኞች፣ ጫኝና አውራጅ ሠራተኞች ይሆናሉ፡፡ 
ሠ. ከፋይናንስ መምሪያ ፔሮል ሠራተኞች ኮስትና በጀት ሠራተኞች የጠቅላላ ሂሳብ ሰራተኞች 
35.5. እርሻው በአመት አንድ ጊዜ ለሠራተኞች በሃገር ውስጥ ባለሙያ የተሰፋ ጥራቱን የጠበቀ ከሃገር
ውስጥ ምርቶች ከኮተን ወይም ከፖሊስተር ኮተን የተሰራ የሥራ ልብስ ወር በገባ በሐምሌ ወር የመስጠት
ግዴታ ይኖርበታል፡፡   
ሀ. በዓመት፣ በሁለት ዓመት፣ በሶስት እና በአራት ዓመት ለሚታደሱ ሠራተኞች የአደጋ መከላከያ
መገልገያዎች በሐምሌ ወር የሚታደል ይሆናል፡፡ 
ለ. ለወንድ ሠራተኞች ቱታ፣ 
ሐ. ለፈረቃ መሪዎች፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ ፎርማኖች እና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ጋዋን፣ 
መ. ለጥበቃ ሠራተኞችና ለሹፌሮች ድርጅቱ በመረጠው ኮትና ሱሪ አስለክቶና አሰፍቶ እንዲሁም ሸሚዝና
ቆዳ ጫማ፣ ለጥበቃ ሠራተኞች ከዚህ በተጨማሪ አርማ ያለበት ኮፍያ እንዲሁም የዝናብ ልብስ በ 3 ዓመት
አንድ፣ ካፖርት ከብርድ መከላከል የሚያስችል በ 4 ዓመት አንድ እና የባትሪ ቀፎ በዓመት አንድ ጊዜ፣ ባትሪ
ድንጋይ በዓመት 4 ጊዜ የባትሪ ቀፎ በዓመት አንድ ጊዜ ለምርት ፈረቃ መሪ ይሰጣል፣ 
ሠ. ለቢሮና ለእርሻው ሽንት ቤት ጽዳት ሠራተኞች ቆዳ ጫማና ለወንዶች ቱታ ለሴቶች ቀሚስና
ፕላስቲክ ጓንት ይሰጣል፣ 
ረ. የቦይለር፣ የንብረት አስተዳደር ሠራተኛ፣ መካኒካል ወርክሾፕ፣ ኤልክትሪክ፣ እሣት አደጋና የጥገና ክፍል
ሠራተኞችን በተመለከተ በሠራተኛና በማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥናት መሠረት ይሰጣል፡፡ ወደፊትም
በጥናት ሚኒስቴሩ ለሚፈቅደው የሥራ መደቦች በጥናቱ መሠረት ይፈፀማል፡፡ 

ክፍል ዘጠኝ
አንቀጽ 36
ህክምና
36.1. እርሻው ሠራተኛው ከደረሰበት ህመም ወይም በሽታ እንዲፈወስ በመጀመሪያ በግቢው ውስጥ
ባለው ክሊኒክ ህክምና ይሰጣል፣ 
36.2. በሽታው ወደ ከፍተኛ ምርመራና ህክምና ሄዶ መታከም እንዳለበት በድርጅቱ ክሊኒክ ባለሙያ
ሲረጋገጥ ድርጅቱ ሥምምነት ከአደረገባቸው የመንግስት ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ሄዶ እንዲታከም
ይደረጋል፡፡ 
36.3. ማንኛውም ሠራተኛ በዓመት ዕረፍት ፍቃድ ላይ እና በሌሎች የዕረፍት ቀናት በድንገት
ቢታመም እንዲሁም ሴት ሠራተኛ ምጥ ይዟት ወደ እርሻው ለመምጣት ባትችል በመንግስት ሆስፒታል
ወይም ጤና ጣቢያዎች በአንዱ ታክመው ወይም ወልደው ደረሰኝ ሲያቀርቡ ይከፍላል፡፡ 
36.4. ሠራተኛው እንዲታከም የተላከበት ጤና ጣቢያ ወይም ሆስፒታል በሃገር ውስጥ በሚገኙ ሌሎች
የመንግስት ጤና ጣቢያዎች ወይም ሆስፒታሎች ሄዶ እንዲታከም ማስረጃ ቢሰጠው እርሻው ያሣክማል፡፡
ይህም የኤክስሬይ፣ የላብራቶሪ፣ የአልትራሣውንድ የመሳሰሉትን ያጠቃልላል፡፡ ሆኖም ያለሃኪም ፍቃድ
ሠራተኛ በመረጠው የህክምና ማዕከል ሄዶ መታከም አይችልም፡፡ 
36.5. ራቅ ወዳለ አካባቢ በዓመት ዕረፍት በመሣሰሉት ፈቃዶች ሄዶ በህክምና ላይ እያለ ቢሞት
በመንግስት ሆስፒታል ወይም ጤና ጣቢያ ለህክምና ያወጣውን ወጪ ህጋዊ ወራሾች በጠየቁ ጊዜ አሰሪው
በደረሰኙ መሠረት አረጋግጦ ይከፍላል፡፡ 
36.6. ሠራተኛው ታሞ ሆስፒታል የተኛ እንደሆነ የ 3 ኛ ማዕረግ ወጪን እርሻው ይሸፍናል ሶስተኛ ማዕረግ
ከሞላ /ከሌለ/ በሁለተኛ ማዕረግ እንዲታከም ይደረጋል፡፡ የሶስተኛ ማዕረግ እያለ ሠራተኛው ፈልጎ በሌላ
ማዕረግ የተኛ እንደሆነ የማዕረጉን ወጪ ልዩነት ሠራተኛው ይሸፈናል፡፡ ሆኖም በሽተኛው በተላከበት
ሆስፒታል የ 3 ኛ ማዕረግ ካልተገኘ የበሽታው ሁኔታ ጊዜ የማይሰጥ መሆኑ በሃኪም ከተረጋገጠ 3 ኛ ማዕረግ
እስኪገኝ በተገኘው ማዕረግ ተኝቶ ይታከማል፡፡ 
36.7. ለሕክምና ወጪ ድርጅቱ 60% ሠራተኛው 40% ይሸፍናሉ፡፡ ይህም የአደጋ ሕክምናን አያካትትም፡፡ 
36.8. የድርጅቱ ጊዜአዊ ሠራተኞች የመጀመሪያ ደረጃ የድንገተኛ ህክምና 60% ድርጅቱ 40% ሠራተኛው
ይሸፍናሉ፡፡ 
36.9. በድርጅቱ ውስጥ በሥራ ላይ እያለ ድንገተኛ አደጋ ወይም ህመም ሲደርስና በሌሊት ወደ ሌላ
ሆስፒታል ሪፈር ለሚባል ሠራተኛ በደረሰኝ የሚወራረድ በክሊኒኩ ብር 500.00 /አምስት መቶ/ የሚሆን
ገንዘብ እንዲቀመጥ ይደረጋል፡፡ 
አንቀጽ 37
የህክምና አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት
37.1. የእርሻው ክሊኒክ ለህክምና አገልግሎት 24 ሰዓት ክፍት ይሆናል፣ 
37.2. የህክምና ወይም የምርመራ አገልግሎት ሠራተኛው የሚያገኝበትን ዕለትና ሰዓት የእርሻው ክሊኒክ
ፕሮግራም ይወጣል፣ 
37.3. ክሊኒኩ ባወጣው ፕሮግራም ተራ በመያዝ ካርዳቸውን አስወጥተው በሥነ ሥርዓት ክሊኒኩ ባወጣው
ፕሮግራም መሠረት ተራ በመያዝ ካርዳቸውን አስወጥተው በሥነ ሥርዓት ወደ ሃኪም ይቀ ርባሉ፡፡ ሆኖም
በሥራ ላይ አጣዳፊ ህመምና አደጋ ለደረሰባቸው ሠራተኞች ቅድሚያ ይሰጣል፡፡ 
37.4. በድንገተኛ ህመም ለህክምና ከሥራው ላይ ወደ ክሊኒክ የመጣ ሠራተኛ ህክምናውን እንደፈጸመ
የክሊኒኩ ባለሙያ ሰዓቱን በቅጹ ላይ ሞልቶና ፈርሞ ለሠራተኛው ይሰጣል፡፡ ሠራተኛውም ወዲያውኑ ወደ
ሥራ ተመልሶ ቅጹን ለቅርብ አለቃው ያስረክባል፡፡ ለአፈጻጸም የሚያመች ቅጽ ክሊኒኩ አዘጋጅቶ ሥራ ላይ
ያውላል፡፡ 
37.5. ክሊኒኩ ለሠራተኛው የህመም ፈቃድ ሲሰጥ በዕለቱ ለክፍሉ ኃላፊና ለሰዓት ቁጥጥር ያሳውቃል፡፡ 
37.6. ሠራተኛው በሥራ ላይ እያለ ከሥራ የመነጨ አደጋ ቢደርስበት ለከፍተኛ ህክምና ወደ ሆስፒታል
ለማድረስ እና መመለስ የማይችል ከሆነ ለመመለሻ ትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣል፡፡ 
37.7. የእርሻው ክሊኒክ በክሊኒክ ደረጃ በክምችት ሊኖረው የሚገባውን መድሃኒት ገዝቶ ይይዛል፡፡
ታማሚው ሠራተኛ ሃኪም ያዘዘለትን የመድሃኒት ማዘዣ በማምጣት መድሃኒቱ በክሊኒኩ ካለ ይወስዳል፡፡
መድሃኒቱ በክሊኒክ ከሌለ ከመንግስት መድሃኒት ቤቶች መድሃኒቱን ገዝቶ እንዲጠቀም ይደረጋል፡፡
መድሃኒቱ በመንግስት መድሃኒት ቤቶች አለመኖሩ በህክምና ባለሙ ከተረጋገጠ ወይም ክሊኒኩ ከሌላ ቦታ
እንዲገዛ ሊፈቅድ ከማንኛውም መድሃኒት ቤት ሊገዛ ይችላል፡፡ 
37.8. በሥራ ላይ በደረሰ ጉዳት ሙሉ ህክምና ይሰጣል፡፡ የጉዳት ካሣ የሚያሰጥ ከሆነ በህክምና ቦርድ
ሲረጋገጥ እርሻው በኢንሹራንስ ድርጅት ጋር በገባው ውል መሠረት የጉዳት ካሳ ክፍያ ይከፍላል፡፡ 
37.9. በሥራ ላይ ወይም በሥራ ምክንያት ለደረሰ ጉዳት ሠራተኛው በህክምና ላይ ለሚያጠፋቸው
ጊዜያቶች እርሻው የሚከተለውን ክፍያ በደመወዝ ፋንታ ይከፍላል፣ 
ሀ. ለመጀመሪያው ሶስት ወራት የወር ደመወዙን 100%
ለ. ለሚቀጥለው ሶስት ወራት የወር ደመወዙን 75%
ሐ. ለሚቀጥሉት 6 ወራት የደመወዙን 50% ይከፍላል፡፡ 
37.10. በአንቀጽ 37.9 ሥር የተጠቀሰው ክፍያ ከዚህ በሚከተሉት ምክንያቶች በማንኛውም ዕለት
ያቆማል፡፡ 
ሀ. ሠራተኛው የደረሰበት ጊዜያዊ ጉዳት የተወገደለት መሆኑ በሃኪም ሲረጋገጥ 
ለ. ሰራተኛው ሥራ መሥራት ካልቻለ ጡረታ ወይም ዳረጎት ማግኘት ከጀመረበት ቀን ጀምሮ 
ሐ. ሠራተኛው ሥራ መሥራት ካቆመበት ቀን ጀምሮ 12 ወራት ሲሞላው፡፡ 
37.11. አንድ ሠራተኛ በሥራ ምክንያት በደረሰበት አደጋ ወይም ህመም ተገቢው ህክምና ተደርጎለት እስከ
መጨረሻው የማይድን መሆ ወይመ ለተቀጠረበት ሥራ ብቁ ያለመሆኑ በሐኪሞች ቦርድ ሲረገጋገጥ
የሚገባው ተከፍሎት ከሥራው ይሰናበታል፡፡ 
ክፍል አስር
አንቀጽ 38
የትራንስፖርት አገልግሎት
38.1. ድርጅቱ ለሥራ መግቢያ መውጪያ በተወሰነው ሰዓት ለሠራተኛው የትራንስፖርት አገልግሎት
ይሰጣል፡፡ 
38.2. የእርሻው ሰርቪስ መበላሸቱ በአስተዳደር መምሪያ ተረጋግጦ በማስታወቂያና በተለያየ መልኩ
ሲገለጽ ሠራተኛው ወደ ሥራ ቦታ ለመምጣትም ሆነ ከሥራ ቦታ ወደ ቤቱ ለመሄድ ለ 3 ቀን የመተባበር
ግዴታ አለበት፡፡ 
38.3. እርሻው የተበላሸውን የሰርቪስ መኪና በተቻለ መጠን አስጠግኖ አገልግሎት እንዲሰጥ የማድረግ
ግዴታ አለበት፡፡ ሆኖም በ 3 ቀን ውስጥ ትራንስፖርት የሚያቀርብ ከሆነ የትራንስፖርት ወጪውን በታክሲ
ታሪፍ ዋጋ ድረጅቱ ይከፍላል፡፡   
38.4. የትራንስፖርት ሰርቪስ ያለ ማስታወቂያ ቢቋረጥ ሠራተኛው ለ 1፡30 ሰዓት ላልበለጠ ጊዜ ቢያረፍድ
ደመወዙ ይታሰብለታል፡፡ ሆኖም ከምሽቱ 6 ሰዓት የሚገቡ ሠራተኞችን አይመለከትም፡፡ 
38.5. ከተለመደው ፊርማታ ውጪ አዲስ ፊርማታ ለመፍጠር ካልፈለገ ድርጅቱና ማህበሩ በሚስማሙት
መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ 
39.6.  የትራንስፖርት አገልግሎት መሣፈሪያና መውረጃ ቦታዎች ከዚህ የሚከተሉት ይሆናሉ፡፡ 
ዊንጌት  ሳሪስ 
ጳውሎስ  ጎተራ 
ኮልፌ  መገናኛ  ጎፋ 
አየር ጤና  ጊዮርጊስ  ገነት ሆቴል 
መካኒሣ 
38.7. የሽሮ ሜዳና የሰሜን ገበያ ፊርማታዎች በዚህ የህብረት ስምምነት እንዲታጠፍ የተደረገ ሲሆን
የዚህ መስመር ቋሚ ሠራተኞች የትራንስፖርት ክፍያ በከተማ ታክሲ ታሪፍ መሰረት ድርጅቱ ይከፍላል፡፡ 
38.8. ቁጥራቸው አነስተኛ ሲሆኑ ሠራተኞች ሲባል ሰርቪሱን ረዥም መንገድ የሚያስኬድ ሆኖ ሲገኝ
ሰራተኞቹ በታክሲ እንዲመጡ ወይም እንዲሄዱ ሆኖ የትራንስፖርት ወጪውን በከተማው ታክሲ ታሪፍ
መሠረት ድርጅቱ ይከፍላል፡፡ 
ክፍል አስራ አንድ
ደመወዝና ልዩ ልዩ ክፍያዎች
አንቀጽ 39
የደመወዝ አወሣሠን
39.1. የሠራተኛው የደመወዝ መነሻ መጠን የሚወስነው በእርሻዉ የደመወዝ ስኬል ወይም በቅጥር ውል፣
ወይም በህግ መሠረት ይሆናል፣ 
39.2. ድርጅቱ ትክክለኛና አንድ ዓይነት የደመወዝ ስሌት ለማስፈን የማንኛውም ሠራተኛ የአንድ ወር
ደመወዝ በ 26 የሥራ ቀን ላይ ተመሥርቶ የሚሰራ ይሆናል፡፡ 
39.3. በዚህ ህ/ስምምነት አፈጻጸም የሚከተሉት ክፍያዎች አንደ ደመወዝ አይቆጠሩም፡፡ የትርፍ ሰዓት፣
ልዩ ልዩ አበሎች፣ ዓመታዊ ጎርሻ፣ የተወካይ ወይም የተተኪነት አበል፣ የማበረታቻ ክፍያ እና የጉድለት
ማሟያ፡፡   
አንቀጽ 40
የደመወዝ አከፋፈል ደንብ
40.1. ድርጅቱ ደመወዝ የሚከፈለው እ.ኤ.አ ወር በገባ በ 28 ኛው ቀን ሲሆን ይህ ቀን እሁድ ቀን ወይም
በሕዝባዊ በዓል ቀን ከዋለ የመክፈያ ቀን አስቀድሞ በዋለው ቀን ይሆናል፡፡ 
40.2. በአንዳንድ ልዩ ልዩ ምክንያቶች የሠራተኛው ደመወዝ አስቀድሞ እንዲከፈል አስፈላጊ መሆኑ
ማህበሩ በጽሑፍ ሲጠይቅና ማኔጅመንቱ ሲያምንበት ከተወሰነው የመክፈያ ጊዜ በፊት የሠራተኛውን
ደመወዝ ሲከፍል ይችላል፡፡ 
40.3. ደመወዝ የሚከፈለው በቀጥታ ለሠራተኛው ሆኖ በልዩ ልዩ አስገዳጅ ምክንያቶች ቀርቦ ደመወዙን
መቀበል ካልቻለ ቤተሰቡን ወይም የሥራ ባልደረባውን በጽሁፍ ሲወክል ውክልና ለተሰጠው ሰው
ይከፈላል፡፡ 
40.4. መተላለፍ የሚገባው ደመወዝ ነክ መረጃ ወይም ሰነድ በቂ ካልሆነ ምክንያት ዘግይቶ ሲደርስ
ሠራተኛው የሠራበትን ደመወዝ የማግኘት መብቱ የተጠበቀ ሆኖ በጥፋተኛው ላይ የሥነ ሥርዓት እርምጃ
ይወስዳል፡፡ 
40.5. ደመወዝ የሚከፈለው በሥራ ቀንና በእርሻዉቅጥር ግቢ ውስጥ ነው፡፡ 
40.6. በህግ፣ በፍ/ቤት ትዕዛዝ በዚህ ህብረት ስምምነት ወይም ሠራተኛው ሲስማማ ካልሆነ በስተቀር
አሠሪው ከሠራተኛ ደመወዝ ሲቀንስ ወይም ሊያቻችል አይችልም፡፡ የሚቀነሰው የገንዘብ መጠንም
ከሠራተኛ ደመወዝ 1/3 መብለጥ የለበትም፡፡ 
40.7. ሠራተኛው ደመወዙን በሚቀበልበት ጊዜ የደመወዙን መጠን የሚገልጽና የተቀናሽ ደመወዙን
የሚያብራራ ሰነድ አሰሪው አዘጋጅቶ ይሰጣል፡፡ በአሠራሩ ቅር ያለው ሠራተኛ ሲገኝ አሰሪው ማስረዳትና
ስህተት መኖሩ ሲረጋገጥ ከሶስት ቀን ባበለጠ ጊዜ ውስጥ አስተካክሎ መክፈል አለበት፡፡  
40.8. ሠራተኛው ለመሥራቱ ዝግጁ ሆኖ ሳለ ለሥራው የሚያስፈልገው ጥሬ ዕቃና መሣሪያ ሳይቀርብለት
በመቅረቱ ወይም በሠራተኛው ችግር ባልሆነ ምክንያት ሣይሰራ ቢውል ደመወዙን የማግት መብት አለው፡፡
ሆኖም ድርጅቱ ሠራተኛውን አስፈላጊ በሆነበት ቦታ ለጊዜው አዛውሮ ማሠራት ይችላል፡፡
40.9. ሁሉም የድርጅቱ ቋሚና ጊዜአዊ ሠራተኞች ደመወዝ የሚከፈለው ወር በገባ በ 28 ኛው ቀን አንድ
ጊዜ ብቻ ይሆናል፡፡ 
አንቀጽ 41 
የውጤት ክፍያ 
41.1. የውጤት ተከፋይ የሚባሉት በውጤት በሚከፈልበት መኪና /ማሽን/ ላይ ተመድበው ባመረቱት
ምርት መጠን ተሰልቶ የሚከፈላቸው ሠራተኞች ናቸው፡፡ 
41.2. ማንኛውም የውጤት ተከፋይ ሠራተኛ በዓመት ፍቃድ በወሊድ ፍቃድ በአደጋ ፍቃድ ወዘተ..
የሚከፈለው ክፍያ በሥራ መደቡ በተሰጠው መደበኛ የወር ደመወዝ መሠረት ነው፡፡ 
41.3. በመደበኛ የውጤት ተከፋይ ሠራተኛ በሚሠራበት መኪና ላይ ተጠባባቂ ሠራተኛ ተመድቦ ቢሰራ
በሥራው ውጤት መሠራት ክፍያ ያገኛል፡፡ 
41.4. የውጤት ክፍያ ወደፊት እርሻው በሚያወጣው ዝርዝር አሠራር መሠረት የሚፈጸም ይሆናል፡፡ 
41.5. አንድ ሠራተኛ በውጤት ክፍያ ሲሰራ የውጤት ክፍያው ከደመወዙ በታች ከሆነ በውጤቱ መሠረት
ይከፈለዋል፡፡ ይህ የሚሠራው የኢንሴንቲቭ ሲስተም ሲዘረጋ ነው፡፡ 
አንቀጽ 42
ቦነስ ወይም የደመወዝ ጭማሪ
42.1. ለሠራተኛው የሚሰራው የደመወዝ ጭማሪ የእርሻው ዓመታዊ የምርት ውጤት እንቅስቃሴ ወጪና
ገቢ ተገናዝቦ ከብር 1,000,000.00 /አንድ ሚሊዮን ብር/ ያላነሰ የተጣራ ትርፍ መገኘቱ ዕውቅና ባለው
የውጭ ኦዲተር ሲረጋገጥ የትርፉን 8 የደመወዝ ጭማሪ ለሠራተኛው ይሰጣል፡፡ አፈጻጸሙም እርሻውና
ሠራተኛ ማህበሩ በደረሱበት ስምምነት መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ 
42.2. ቦነስ ወይም የደመወዝ ጭማሪ የሚሰጠው በበጀት ዓመቱ ከ 9 ወር በላይ ለሠራ ሠራተኛ ነው፡፡
4.2.3. ከአንድ ሚሊዩን በላይ ለሚገኝ የተጣራ ትርፍ ድርጅቱና ማህበሩ በሚደርሱበት ስምምነት መሠረት
ቦነስ ይሰጣል፡፡
አንቀጽ 43
ልዩ ልዩ የአበል ክፍያዎች
43.1. የውሎ አበል ክፍያ፣ ማለት ሠራተኛው ከመደበኛ ሥራ ቦታው ከአዲስ አበባ ከተማ ክልል ውጭ
ወደሆነ ሌላ የሥራ ቦታ ሥራ እንዲያከናውን በእርሻዉሲታዘዝ በሄደበት ቦታ ለሚያጋጥመው የምግብ
የመኝታና ሌሎች ጥቃቅን ወጪዎች እንዲሸፈን የሚደረግ ክፍያ ነው፡፡ 
43.2. የውሎ አበል ክፍያው የትራንስፖርት ወጪን አይሸፍንም የትራንስፖርት ወጪው በመንገድ
ትራንስፖርት ታሪፍ መሠረት በሚያቀርበው ደረሰኝ/ሪሲት መሠረት የሚወራረድ ይሆናል፡፡ 
43.3. እርሻው ለሠራተኛው የውሎ አበል የሚከፍለው ክፍያ ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
 
ተ.ቁ  የደመወዙ እስኬል  የቀን አበል 
1. እስከ 500.00 ብር ለሆነ  ብር 90 
2. ከብር 501-1000 ብር ለሆነ  ብር 100 
3. ከብር 1001-1500 ብር ለሆነ  ብር 115 
4. ከብር 1501-2000 ብር ለሆነ  ብር 130
5. ከብር 2001-3000 ብር ለሆነ ብር 150
7. ከብር 3000 ብር በላይ ለሆነ  ብር 175
43.4. የውሎ አበሉ ለቤትም ከዚህ በሚከተለው መሠረት ተተንትኖ ይከፈላል 
 ለቁርስ  15%  እስከ ጥዋቱ 2 ሰዓት ድረስ ባለጊዜ ለሥራ ከተላኩ 
 ለምሳ  25%  እስከ 6 ሰዓት ድረስ ባለጊዜ ለሠራ ከተላኩ 
 ለዕራት  25%  ከምሽቱ 2 ሰዓት በኃላ ወደ አ.አ. ለሚገቡ 
 ለአልጋ  35% ከቤተት /ከአ.አ/ ውጪ ሄደው ካደሩ 
43.5. ሠራተኛው በአዲስ አበባ ክልል ውስጥ ለስልጠናም ይሁን ለሴሚናር ሲላክ ለትራንስፖርት በታሪፍ
መሠረት እና የምሳ አበል ብቻ በስሌቱ መሠረት ይከፈላል፡፡ የምሳ ወጪው በአሰልጣኙ ድርጅት የሚከፈል
ከሆነ ለትራንስፖርት ብቻ ይሰጠዋል፡፡  
43.6. ከአዋሽ መገንጠያ ጀምሮ መካከለኛው አዋሽና ተንዳሆ ላይኛው አዋጅ ጅቡቲ ጋምቤላ ኦሞ እርሻ
ልማት ጊቤ እርሻ ልማት ለሥራ ሲሔድ የአበሉ 50% የበረሃ አበል ከአበሉ በተጨማሪ ይከፈለዋል፡፡ 
43.7. ከኢትዮጵያ ውጪ ለሥራ መላኩ በመንግስት ታሪፍ መሠረት የሚከፈል ይሆናል፡፡ 
አንቀጽ 44
ለገንዘብ ያዥ የሚሰጥ የመጠባበቂያ ገንዘብ
44.1. ለዋና ገንዘብ ያዥ ለገንዘብ ጉድለት ማካካሻ ብር 150 በወር ይከፈላል 
44.2. በደመወዝ መክፈል ወቅት የሠራተኞች የደመወዝ መክፈያ ቢል በማደል ለሚያስከፍሉ ሁለት
ሠራተኞች ለእያንዳንዳቸው ብር 75.00 በወር ይከፈላል፡፡ 
44.3. እርሻው ለገንዘብ ያዥ እንዲከፈል የወሰነው ወርሃዊ ክፍያ የመጀመሪያው 12 ወራት በሠራተኛው
ሥም በመጠባበቂያ ገንዘብ መልክ ያጠራቅማል ከዚህ በኋላ ግን የመጠባበቂያ ገንዘብ ከፍያውን በየወሩ
ለገንዘብ ያዥ ይከፍላል፡፡ 
44.4. ከገንዘብ ያዥ ላይ በኦዲተር ወይም በሂሳብ ኃላፊው የተረጋገጠ የገንዘብ ጉድለት ሲገኝበት እርሻው
በገንዘብ ያዥ ስም ካጠራቀመው መጠባበቂያ ገንዘብ ተቀናሽ በማድረግ ጉድለቱን ወዲያውኑ ያሟላል፡፡
ጉድለቱ ከመጠባበቂያው ገንዘብ በላይ ከሆነ ገንዘብ ያዡ/ዣ/ በአስቸኳይ ልዩነቱን ወዲያውኑ እንዲያስገባ
/እንድታስገባ/ ይደረጋል፡፡ 
44.5. ገንዘቡን በተራ ቁጥር 44.4 መሠረት ማሟላት ካልቻለ /ካልቻለች/ ከከፋይነት የሥራ መደብ ታግዶ
/ታግዳ/ በህግ ይጠየቃል /ትጠየቃለች/ ወይም ተገቢው የሥነ ሥርዓት እርምጃ ይወሰድበታል
/ይወሰድባታል/፡፡ 
44.6. ገንዘብ ያዥ ከእርሻው በተለያየ ምክንያት ከሥራ ሲሰናበት /ስትለሰናበት/ ወይም ወደሌላ የሥራ ቦታ
ሲዛወር /ስትዘዋወር/ በስሙ /በስሟ/ የተጠራቀመው ገንዘብ በአንድ ጊዜ ይከፈለዋል /ይከፈላታል/፡፡ 
አንቀጽ 45
የፈጠራ ሥራ ማሻሻያ ሃሳብ አቀራረብና የማትጊያ ክፍያ ሥርዓትን በተመለከተ
45.1. የሥራ ውድድርና የሥራ ፈጠራ ማሻሻያ ሃሳብ አቀራረብና የማትጊያ ክፍያ ስርዓት (Incentive
Scheme) በተመለከተ በየደረጃው በሠራተኛውና በሥራ ኃላፊው መካከል የሥራ ውድድር መኖር
ለእርሻው የምርት ዕቅድ አፈጻጸም ውጤታማነት ከፍተኛ ሚና ያለው መሆኑን እርሻው ያምናል፡፡ 
45.2. ይህም የፈጠራ ሥራ ማሻሻያ ሃሳብ አቀራረብና የማትጊያ ክፍያ ሥርዓት እርሻው አጥንቶ ወይም
አስጠንቶ በሚያቀርበው የአሰራርና የአፈጻጸም መመሪያ መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ 
ክፍል አስራ ሁለት
የሥራ ሰዓት፣ የትርፍ ሰዓት፣ የሳምንት የዕረፍት ቀንና የህዝብ በዓላት
አንቀጽ 46
የእርሻው መደበኛ የሥራ ቀን ወይም የሣምንቱ የሥራ ሰዓት
46.1. የማንኛውም ሠራተኛ መደበኛ የሥራ ሰዓት በቀን ከ 8 ሰዓት ወይም በሣምንት ከ 48 ሰዓት መብለጥ
የለበትም፡፡ 
46.2. እርሻው እንደ ሥራው ፀባይ ሥራውን በቀን ፈረቃ፣ በምሺ ፈረቃና በሌሊት ፈረቃ /ሶስት/ ፈረቃ
ከፍሎ ያሠራል፡፡ 
46.3. በቀን ፈረቃ ወይም በመደበኛ የሥራ ሰዓት ለሚሠሩ ሠራተኞች የሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ባሉ
የሥራ ቀኖች ጧት ከ 2 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ 7 ሰዓት እስከ 10 ሰዓት ቅዳሜ ከ 2 ሰዓት እስከ
6 ሰዓት ይሆናል፡፡ 
46.4. በፈረቃ/በሽፍት/ ለሚሠሩ ሠራተኞች የሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ፡-
ሀ. ለጠዋት ገቢ ከጥዋቱ 2፡00 /ሁለት ሰዓት/ እስከ ምሽቱ 6፡00 /ስድስት ሰዓት/
ለ. ለ 10 ሰዓት ገቢ ከቀኑ 10፡00 /አስር ሰዓት/ እስከ ምሽቱ 6፡00 /ስድስት ሰዓት/
ሐ. ለሌሊት ገቢ ከምሽቱ 6፡00 /ስድስት ሰዓት/ እስከ ጥዋቱ 2፡00 /ሁለት ሰዓት/ ይሆናል፡፡ 
46.5. በፈረቃ ለሚሠሩ ሠራተኞች ለምግብ መመገቢያ በስራ ሰዓት መካከል 30 ደቂቃ ይኖራቸዋል፡፡ ይህም
የምሣ ሰዓት ምርትን ለማያደናቅፍ መልኩ በእርሻዉየክፍል ኃላፊዎች ይደለደላል፡፡ 
46.6. የእርሻው የሥራ ፀባይ ሲያስገድድ ወይም ከእርሻው አቅም በላይ የሆነ ችግር ሲያጋጥም የሣምንቱን
የሥራ ሰዓት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 62፣63፣64 መሠረት ማደላደል ይቻላል፡፡ 
አንቀጽ 47
የሣምንቱ የዕረፍት ቀን
47.1. ማንኛውም ሠራተኛ በሰባት ቀናት /በሣምንት/ ጊዜ ውስጥ ያልተቆራረጠ ከ 24 ሰዓት የማያንስ
የዕረፍት ቀን ያገኛል፡፡ 
47.2. በተቻለ መጠን የማንኛውም ሠራተኛ የሣምንት የዕረፍት ቀን እሁድ ቀን ይሆናል፡፡ ሆኖም ከሥራ
ፀበይና የአገልግሎት አሰጣጥ የተነሳ የጥበቃ ሠራተኞችን አይመለከትም፡፡
47.3. በአንቀጽ 47.2. ለተጠቀሱ ሠራተኞች በሣምንቱ የሥራ ቀኖች በአንዱ በማደላደል በተከታታይ ከ 24
ሰዓት የማያንስ የዕረፍት ቀን ያገኛሉ፡፡ 
47.4. በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 71 መሠረት የተገለጹት ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ በሣምንቱ የዕረፍት
ጊዜ ማሠራት ይቻላል፡፡ ሆኖም ክፍያው በትርፍ ሰዓት አከፋፈል ሥርዓት መሠረት ይፈጸማል፡፡
የትራንስፖርት አገልግሎት እንደ አስፈላጊነቱ ይሰጣል ወይም የትራንስፖት ክፍያ በታክሲ ሂሳብ
ይከፈላል፡፡ 
አንቀጽ 48
የትርፍ ሰዓት ክፍያ
48.1. በዚህ ህብረት ስምምነት መሠረት ከተወሰነው መደበኛ የሥራ ሰዓት በላይ የሚሠራ ሥራ የትርፍ
ሰዓት እንደሆነ ይቆጠራል፡፡ 
48.2. የትርፍ ሰዓት ሥራ እንዲሠራ የሚደረገው በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 67
መሰረት ነው፡፡ 
48.3. ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጪ ለሚሠራ የትርፍ ሰዓት ስር ለሰራተኛ የሚከፈለው በሚከተለው
መሰረት ይሆናል፡፡ 
ሀ. ከንጋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ለሚሠራ የትርፍ ሰዓት ስራ ለመደበኛ የስራ ሰዓት የሚከፈለው
ደመወዝ በአንድ ሩብ (1¼) ተባዝቶ 
ለ. ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት የሚሰራ የትርፍ ሰዓት ሥራ ለመደበኛ ሥራው በሰዓት
የሚከፈለው ደመወዝ በአንድ ተኩል (1½) ተባዝቶ
ሐ. በሣምንት የዕረፍት ቀን የሚሠራ የትርፍ ሰዓት ሥራ ለመደበኛው ሥራው በሰዓት የሚከፈለው
ደመወዝ በሁለት /2/ተባዝቶ
መ. በሕዝብ በዓላት ቀን ለሚሠራ የትርፍ ሰዓት ስራ ለመደበኛ ሥራው በሰዓት የሚከፈለው ደመወዝ
በሁለት ተኩል /2½/ ተባዝቶ ይከፈላል፡፡ 
48.4. የትርፍ ሰዓት ክፍያ ለደመወዝ መክፈያ በተወሰነው ቀን ከደመወዝ ጋር ይከፈላል፡፡ 
48.5. የትርፍ ሰዓት ክፍያ የሚከፈላቸው የፈረቃ ኃላፊ /ሽፍት ሊደርና/ ከዚያ በታች ላሉ የሥራ መደቦች
ይሆናል፡፡ 
48.6. ከደረጃ አስራ አንድ በላይ ከመምሪያ ኃላፊ በታች ላሉ የሥራ መደቦች ከመደበኛ የሥራ ሰዓታቸው
ውጪ የሠሩበት ሰዓት በማካካሻ ተይዞላቸው በሌላ ጊዜ እንዲያርፉበት ይደረጋል፡፡ የሠሩት ሰዓትም በበላይ
ኃላፊያቸው ፊርማ ተረጋግጦ በሰዓት ቁጥጥር እንዲቀመጥ ይደረጋል፡፡ የሰዓት ቁጥጥርም ያረፈበትን ሰዓት
እየተከታተለ ተቀናሽ ያደርጋል፡፡ 

አንቀጽ 49
የህዝብ በዓላት
አግባብ ባለው ህግ መሠረት የሚከበሩ የሕዝብ በዓላት ከዚህ የሚከተሉት ይሆናሉ፡፡
49.1. በወር ደመወዝ የሚከፈለው ሠራተኛ በህዝብ በዓላት ባለመሥራቱ ምክንያት ከደመወዙ
አይቀነስበትም፡፡ 
49.2. አንድ የህዝብ በዓል ከሌላ የህዝብ በዓል ጋር ተደርቦ ወይም በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሠረት ወይም
በማንኛውም ልዩ ህግ በተወሰነ የዕረፍት ቀን ላይ ወይም በዚህ ህ/ስምምነት በተወሰነው የዕረፍት ቀን ላይ
ቢውል ለዚህ ቀን የሠራ ሠራተኛ ክፍያ የሚያደርግበት በአንዱ የህዝብ በዓል ብቻ ይሆናል፡፡ 
49.3. የእርሻውን የምርት ሂደት ለመጠበቅ ሲባል በህዝብ በዓል ቀን ማሠራት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝና
በእርሻዉሲታዘዝ ሠራተኛው የመሥራት ግዴታ አለበት፡፡ ይህንንም የእርሻው አስተዳደር አስቀድሞ
በማስታወቂያ ይገልጻል፡፡ ክፍያውም በህዝብ በዓል ክፍያ ስሌት መሠረት ይፈፀማል፡፡ 
አንቀጽ 50
የትርፍ ሰዓት ክፍያ የማይከፈልበት ሥራ
ሀ. የውሎ አበል የሚከፈለው ሠራተኛ በውሎ አበል ክፍያ ላይ እያለ፣ 
ለ. ለሥልጠና የሚላክ ሠራተኛ በሥልጠና ላይ እያለ፣ 
ሐ. በተተኪነት ወይም በውክልና ላይ ያለ ሠራተኛ፣  
ክፍል አስራ ሦስት
ልዩ ልዩ ፈቃዶችን በተመለከተ
አንቀጽ 51
የዓመት እረፍት /ፍቃድ/ መጠን
51.1. የዓመት እርፍት ፍቃድ የሚታሰበው ሰራተኛው የተቀጠረበትን ጊዜ መሠረት በማድረግ ነው፡፡ 
51.2. ለመጀመሪያ አንድ ዓመት ያገለገለ ሠራተኛ 14 የሥራ ቀን የዓመት ፍቃድ ይሰጠዋል፡፡ 
51.3. ከአንድ ዓመት በላይ ለሆነ አገልግሎት በ 14 ቀን ላይ ለእያንዳንዱ ተጨማሪ ዓመት አንድ ተጨማሪ
ቀን እየታከለ ይሰጣል፡፡ 
51.4. በዓመት ፍቃድ ላይ የሚገኝ ሰራተኛ የሚከፈለው ደመወዝ ሥራ ላይ ኖሮ ከሚከፈለው ጋር እኩል
ይሆናል፡፡ 
51.5. ለዓመት ፍቃድ ብቁ የሚያደርገው ቀን ለመወሰን ሲባል በድርጅቱ ለ 26 የሥራ ቀናት የሠራ ሠራተኛ
ለአንድ ወር እንደሰራ ይቆጠራል፡፡ 
51.6. በዚህ ህ/ስምምነትና በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሠረት የሥራ ውሉ የተቋረጠ ሠራተኛ
ያልተጠቀመበት የዓመት ፍቃድ ታስቦ በገንዘብ ይከፈለዋል፡፡ 
51.7. አንድ ሠራተኛ ያገለገለበት ጊዜ ከአንድ ዓመት በታች ከሆነ በአገልግሎት ዘመኑ ልክ ተመጣጣኝ የሆነ
የዓመት ፍቃድ በዚያው በአገከለገለበት ዓመት ይሰጠዋል፡፡ 
አንቀጽ 52 
የዓመት ፍቃድ አሰጣጥ 
52.1. አሠሪው የሠራተኛው የዓመት እረፍት የሚወጣበትን ቀን ፕሮግራም በማውጣት ይወሰናል፡፡ ይህም
አሰሪው ሥራውን በተለመደው ሁኔታ ለመሥራት በሚያስችለው እና በተቻለ መጠን በሠራተኛው ፍላጎት
ላይ የተመሠረቱ እንዲሆን ጥረት ያደርጋል፡፡ 
52.2. እርሻው በሚያወጣው የዓመት እረፍት ፕሮግራም መሠረት በእያንዳንዱ ዓመት ለሠራተኛው
የሚገባውን የዓመት ፍቃድ ይሰጣል፡፡ ሆኖም ሠራተኛው ያልታሰበና አጣዳፊ ችግር ሲያጋጥመውና
ማኔጅመንቱ ሲፈቅድ ካለው እረፍት ላይ ቀንሶ ሊሰጠው ይችላል፡፡ 
አንቀጽ 53
የዓመት ፍቃድ ስለመከፋፈልና ስለማስተላለፍ
53.1. አንድ ሰራተኛ ሳይከፋፈል የሚሰጥ የዓመት ፍቃድ ከክፍያ ጋር ያገኛል ሆኖም ሠራተኛው ተከፋፍሎ
እንዲሰጠው ሲጠይቅና አሰሪው ሲስማማ ለሁለት ተከፍሎ ወይም አጣዳፊ ችግር ሲያጋጥም ከ 5 ቀን
የማያንስ የዓመት ዕረፍት ሲሰጠው ይችላል፡፡   
53.2. አሠሪው የሥራ ሁኔታ ሲያስገድደው የሰራተኛውን የፈቃድ ጊዜ ሲያስተላልፍ ይችላል፡፡ 
53.3. አንድ ሠራተኛ በዓመት እረፍት ላይ እያለ የጋብቻ፣ የወሊድ፣ የሃዘን እንዲሁም የህመም ፍቃድ
ቢያገኝ የዓመት እረፍቱ ጊዜ ባገኘው ፍቃድ መጠን ይራዘማል፡፡ 
53.4. ሠራተኛው የያዘው የሥራ መደብ ተተኪ የሚይገኝለት ከሆነና ጥያቄው በሥራ ክፍሉ ቀርቦ በሥራ
አስኪያጅ ሲፈቀድ የዓመት እረፍቱ ሊራዘም ይችላል፡፡ ሆኖም የዓመት እረፍት ፍቃድ ከ 2 ዓመት በላይ
ሊራዘም አይችልም፡፡ 
53.4. ሠራተኛው የያዘው የስራ መደብ ተተኪ የማይገኝለት ከሆነና ጥያቄው በሥራ ክፍሉ ቀርቦ በሥራ
አስኪያጅ ሲፈቀድ የዓመት እረፍቱ ሊራዘም ይችላል፡፡ ሆኖም የዓመት እረፍት ፍቃድ ከ 2 ዓመት በላይ
ሊራዘም አይችልም፡፡ 
53.5. የዓመት ፍቃድን በመከልከል ወደ ገንዘብ ለውጦ መክፈል የተከለከለ ነው፡፡ ሆኖም ሠራተኛው
ሊስማማና አሠሪው ለመክፈል ሲፈቅድ የዓመት ዕረፍቱን በገንዘብ ለውጦ መስጠት ይቻላል ይህም
የሚሆነው የዓመት ዕረፍቱን ወደ ገንዘብ ለመለወጥ የሚያስችል የሥራ ችግር ሲያጋጥመው፡፡  
አንቀጽ 54
በፍቃድ ላይ ያለ ሠራተኛ ስለመጥራት 
54.1. በዓመት ፍቃድ ላይ ያለ ሠራተኛ ተጠርቶ እንዲሰራ ሊደረግ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 80
መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል፣ 
አንቀጽ 55 
የጋብቻ ፍቃድ 
55.1. አንድ ሠራተኛ ለመጀመሪያ ጊዜ ህጋዊ ጋብቻ ሲፈጽም 3 ቀን ደመወዝ የሚከፈልበት 5 ቀን
ደመወዝ የማይከፈልበት ነጻ ፍቃድ ያገኛል፡፡  
አንቀጽ 56 
የሃዘን ፍቃድ 
56.1. የሠራተኛው አባት፣ እና፣ ባል፣ ሚስት፣ ልጅ፣ ወንድም፣ እህት፣ የትዳር ጓደኛ እናት፣ አባት፣ ልጅ፣
ወንድም፣ እህት ሲሞት 3 የሥራ ቀን ደመወዝ የሚከፈልበት ፍቃድ 5 ቀን የማይከፈልበት ነጻ ፍቃድ
ያገኛል፡፡ ስለ እርግጠኝነቱ ሠራተኛው ማስረጃ ከዕድር ወይም ከቀበሌ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም
ዕድር የሌለውና በቀበሌ ያልተመዘገበ ሠራተኛ ከላይ ከተጠቀሱት ዘመዶች ሲሞትበት ስለመሞቱ በሶስት
ምስክሮች ሲረጋገጥ የሃዘን ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ ይህም በቤተሰቡ ዝርዝር ውስጥ ሲቀጠር ካለመዘገበው
ውስጥ ሆነው ከተገኙ ነው፡፡ 
56.2. ከሠራተኛው ቤት ከተጠቀሰው ዝምድና ውቺ አስክሬን ቢወጣ 2 ቀን ከክፍያ ጋር ፈቃድ ያገኛል፡፡ 
56.3. የእርሻው ቋሚ ሠራተኛ በሞት በሚለይበት ጊዜ ለቀብር ማስፈጸሚያ የሚሆን ብር 3.000 /ሶስት
ሺህ/ ለሠራተኛው ቤተሰብ አሰሪው ይከፍላል፡፡ አፈጻጸሙን ማህበር ተከታትሎ ያስፈጽማል፡፡ 
56.4. አንድ የእርሻው ቋሚ ሠራተኛ በሞት በሚለይበት ጊዜ በቀብር ስነሥርዓቱ ላይ የሚገኙ ከ 10
ለማይበልጡ የእርሻው ሠራተኞች የ 2 ሰዓት ደመወዝ የሚከፈልበት ፍቃድ ሥራ በማይበደልበት ሁኔታ
ይሰጣል፡፡ አንድ የማጓጓዣ ሰርቢስም ይመደባል፡፡ 
አንቀጽ 57
ለማህበር ሥራ የሚሰጥ ፍቃድ
57.1. የሠራተኛ ማህበር መሪዎች የሥራ ክርክር ለማቅረብ፣ የሕብረት ስምምነት ለመደራደር፣ በማህበር
ስብሰባ ለመገኘት፣ ለሴሚናሮችና በስልጠና ለመካፈል እንዲችሉ፣ የማህበሩን ሥራ ለማከናወን ማህበሩ
በጽሁፍ ሲጠይቅና ማስረጃ ሲያቀርብ ፍቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጣል፡፡ 
57.2. የማህበር የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ስብሰባ ሥራን በማይበድል ሁኔታ በየ 15 ቀን ከ 3-6 ሰዓት
ስብሰባ ያደርጋሉ የስብሰባ ቀኑንም በጽሁፍ ያሳውቃሉ፡፡ 
57.3. የማህበሩ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴና የምክር ቤት አባሎች በገቢ ውስጥ ለመሰብሰብ ሲፈልጉ
ከ 24 ሰዓት በፊት እርሻው በጽሁፍ ሲጠየቁ በ 6 ወር አንድ ጊዜ ደመወዝ የሚከፈልበት ፍቃድ
ይሰጣቸዋል፡፡ 
አንቀጽ 58
ልዩ ልዩ ተግባሮችን ለማከናወን ለሠራተኛ የሚሰጥ ፍቃድ
58.1. አንድ ሠራተኛ የሥራ ክርክር ለማሰማት፣ ወይም የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ህጎችን ለማስፈጸም
ስልጣን ያላቸው አካሎች ዘንድ ጉዳዩን ለማስማት ሲቀርብ በሚያቀርበው ህጋዊ ማስረጃ መሠረት ለዚሁ
አላማ ላጠፋው ጊዜ ብቻ ከክፍያ ጋር ፍቃድ ይሰጣል፡፡ 
58.2 አንድ ሠራተኛ የሲቪል መብቱን ሲያስጠብቅ ወይም የሲቪል ግዴታውን ሊፈጽም በሚያቀርበው
ህጋዊ ማስረጃ መሠረት ለዚሁ ዓላማ ላጠፋው ጊዜ ብቻ ከክፍያ ጋር ፍቃድ ይሰጠዋል፡፡ 
58.3. ማንኛውም ሠራተኛ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ሲደርስበትና ይኸውም በአሰሪው ሲታመንበት
የቅርብ አለቃውን ፍቃድ በመጠየቅ ከክፍያ ነፃ የሆነ ፍቃድ ይሰጠዋል፡፡ ሆኖም ሠራተኛው የዓመት ዕረፍት
ካለውና ከዓመት እረፍቱ እንዲታሰብለት አስቀድሞ ከጠየቀና ይህም በአሰሪው ከታመነበት ወደ ዓመት
እረፍት ሊቀየርለት ይችላል፡፡ ይህ የዓመት ዕረፍት ከአንድ ቀን በታች የሆነ ሰዓታን አይመለከትም፡፡ 
58.4. የክፍል አለቃው ከ 5 ተከታታይ ቀን በላይ ከክፍያ ነፃ የሆነ ፍቃድ በአንድ ጊዜ መስጠት አይችልም፡፡
ከዚህ ጊዜ በላይ ነፃ ፍቃድ የሚያሰጥ ችግር ሊያጋጥም ማመልከቻው በክፍሉ ኃላፊ አስተያየት ተሰጥቶበት
ይኸው በአስተዳደር መምሪያ ተቀባይነት ሲያገኝ ነፃ ፍቃድ ሊፈቀድለት ይችላል፡፡ 
አንቀጽ 59
የህመም ፈቃድ
59.1. ማንኛውም የእርሻው ቋሚ ሠራተኛ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በተከታታይ ወይም በተለያየ ጊዜ
ከዚህ የሚከተለውን የህመም ፍቃድ ያገኛል፡፡ 

ሀ. ለመጀመሪያው ወር ከሙሉ ደመወዝ ክፍያ ጋር (100%)


ለ. ለሚቀጥሉት ሁለት ወራት ከደመወዙ ሃምሳ በመቶ ክፍያ ጋር (50%)
ሐ. ለሚቀጥሉት 3 ወራት የህመም ፍቃድ ክፍያ የማይፈጽምበት   

59.2. ከዚህ በላይ በአንቀጽ 59.1 ከፊደል ሀ-ሐ የተመለከውን የሕመም ቃድ መብቱን ጨርሶ ድኖ ወደ ሥራ
ለመመለስ ያልቻለ ሠራተኛ ተገቢ መብቱን ጠብቆ አሠሪው የማሰናበት መብት አለው፡፡ 
59.3. የህመም ፍቃድ የጊዜ ገደብ የሚያገለግለው ለአንድ ዓመት ጊዜ ብቻ ሲሆን ዓመቱ ሲያልቅ የሕመም
ፍቃድ ስሌት በአዲስ ከመሉ ደመወዝ ጋር ይጀምራል፡፡ 
59.4 የእርሻው ቋሚ ሠራተኛ ከሥራ ጋር በተያያዘ የመጣ ህመም መሆኑ በሃኪም ሲታመንበት በዓይኑ ላይ
ጉዳት ቢደርስበት በሀኪም መነጽር ከታዘዘለት ድርጅቱ የመነጽርና የሕክምና ወጪውን ይሸፍናል፡፡ 
59.5. ማንኛውም የሐኪም ፍቃድ በእርሻዉክሊኒክ ኃላፊ ወይም ሪፈር በተደረገበት ተቋም ይሰጣል፡፡
የክሊኒኩ ኃላፊ ወይም በክሊኒክ ኃላፊ ተወካይ ሠራተኛ በሌለበት በማታ ሽፍት ጤና ረዳቶች ለ 1 ቀን
ፍቃድ መስጠት ይችላሉ፡፡ ሆኖም በተከታዩ ቀን ህመምተኛው ካልተሻለው ለሐኪም መቅረብ አለበት፡፡ 
59.6. በሕክምና ላይ እያለ በሌላ ምክንያት የሥራ ውሉ የሚቋረጠበት ቀን ጀምሮ ያለው የህመም ፍቃድ
ክፍያ አይከፈለውም፡፡ 
59.7. የአንድ ሠራተኛ የህመም ፍቃድ ከጀመረበት ቀን አንስቶ በ 12 ወራት ውስጥ በተከታታይ ወይም
በተለያዩ ጊዜያት ቢወሰድም በማንኛውም ሁኔታ ከ 6 ወር አይበልጥም፡፡ 
አንቀጽ 60
የወሊድ ፍቃድ
60.1. ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ ከዕርግዝናዋ ጋር የተያያዘ ምርመራ ለማድረግ አሠሪው ከደመወዝ ጋር
ፍቃድ ይሰጣታል፡፡ ሆኖም ሠራተኛዋ ከምርመራ ኃላፊ የሐኪም ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡ 
60.2. ነፍስ ጡር የሆነች ሴት ከመውለዷ በፊት ሐኪም እንድታርፍ ካዘዘ ከክፍያ ጋር እረፍት ይሰጣታል፡፡ 
60.3. ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ እወልዳለሁ ብላ ከገመተችው ቀን በፊት መውለጃዋ ሲደርስ የ 30
ተከታታይ ቀን የወሊድ ፍቃድ እንዲሁም ስትወልድ ከወለደችበት ቀን ጀምሮ 60 ተከታታይ ቀናት የወሊድ
ፍቃድ ከክፍያ ጋር ይሰጣታል፡፡ 
60.4. ሠራተኛዋ ከመውለዷ በፊት የወሰደችው የ 30 ቀን ፍቃድ ሲያልቅ ካልወለደች እስከ ምትወልድበት
ቀን ድረስ በአንቀጽ 60.2 መሠረት ዕረፍት ልታገኝ ትችላላች፡፡ የ 30 ቀን ፍቃዷ ሣያልቅ የወለደች በዚህ
አንቀጽ ንዑስ ቁጥር 3 መሠረት የምትወስደው ፍቃድ ይጀምራል፡፡ 
60.5. አንዲት ነፍሰጡር ሠራተኛ የ 5 ወር ነፍሰጡር መሆኗ በህክምና ባለሙያ ሲረጋገጥ ወይም
ሲታመንበት፣ 

ሀ. በጠዋት ፈረቃ ብቻ እንድትሠራ ይደረጋል፣


ለ. ሁልጊዜ ከመውጫ ሰዓት በፊት 10 ደቂቃ ቀድማ እንድትወጣ ይፈቀዳል፣ 
ሐ. የትርፍ ሰዓት ሥራ እንድትሰራ አትገደድም፣
መ. ነፍሰጡር ሴት ከምሽቱ 4 ሰዓት 
60.6. አንዲት ነፍሰጡር ሠራተኛ ገንዘቧን ቀርባ መውሰድ ካልቻለች በጽሁፍ በምትወክለው ሠራተኛ
አማካኝነት ገንዘቧን መውሰድ ትችላለች፡፡ 
60.7. ነፍሰጡር የነበረች ሠራተኛ የወለደችው ልጅ ታ ሆስፒታል ቢተኛ ሠራተኛዋ ለማስታመም ፍቃድ
ከጠየቀች ድርጅቱ በሚፈቅድላት መሠረት የማይከፈልበት ነጻ ፍቃድ ታገኛለች፡፡ ሆኖም ህክምናው
ሲጠናቀቅ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ 
60.8. አንዲት ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ በሥራ ውል ከተመለከተው ሥራ ውጪ ማሠራተ አይቻልም፡፡
ሆኖም ነፍሰጡሯ የምትሠራው ሥራ ለጤንነቷም ሆነ ለጽንሷ አደገኛ መሆኑ በሐኪም ሲረጋገጥ ለጤናዋ
አስፈላጊ ባልሆነ ቦታ ተመድባ እንድትሰራ ይደረጋል፡፡ 
ክፍል አስራ አራት
ማህበራዊ አገልግሎትን በተመለከተ
አንቀጽ 61
61.1. ድርጅቱ ማንኛውም ሠራተኛ መደበኛ የጡረታ ጊዜው ከመድረሱ ከአንድ ዓመት በፊት ቅድመ
ዝግጅት እንዲያደርግ ለሠራተኛው ጡረታ የሚወጣበትን ጊዜ በጽሁፍ ያሳውቀዋል፡፡ 
61.2. አንድ መደበኛ የጡረታ መውጪያው የደረሰ ሠራተኛ አሠሪው በጽሁፍ ሲያሳውቀው አልቀበልም
ማለት አይችልም፡፡ 
61.3. በዚህ የህብረት ስምምነት ስለ ዓመት ፍቃድ የተጠቀሰው ቢኖርም በጡረታ የሚገለል ሠራተኛ
የመጨረሻ አንድ ዓመት እረፍት ፍቃዱን አጠራቅሞ በገንዘብ ተለውጦ ይሰጠዋል፡፡ ሆኖም ሠራተኛው
የተለየ ችግር ገጥሞት የዓመት ፍቃዱን ሊጠቀምበት ቢፈልግ ሊጠቀምበት ይችላል፡፡ 
61.4. አንድ ሠራተኛ ጡረታ ከመውጣቱ በፊት የአበል መቀበያ ደብተሩ እንዲደርሰው እርሻው በወቅቱ
አስፈላጊውን ፎርማሊቲ አሟልቶ ለማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ያስተላልፋል፡፡ 
61.5. በማንኛውም ሁኔታ የሥራ ውሉ የተቋረጠ ሠራተኛ እርሻውን ሲለቅ የጡረታ መዋጮ ያወጣውን
እንዲመለስለት ሲጠይቅ እርሻው የጡረታ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ተገቢውን መረጃ በማስተላለፍ
ያስፈጽማል፡፡ 
61.6. የጡረታ ወራሾች የወራሽነት መብታቸውን በፍርድ ቤት አስወስነው ሲያቀርቡ ህጉ በሚፈቅደው
መሠረት ይፈጸማል፡፡ 
አንቀጽ 62 
ማህበራዊ አገልግሎት 
62.1. የሠራተኛ ችግሮችን ለመቅረፍ ታስቦ ለሚቋቋም እንደ ዕድርና የገንዘብ ቁጠባ የመሳሰሉ
አገልግሎቶች በእርሻውና በማህበሩ ስምምነት ሲደርስበት ተቀባይነት ይኖራቸዋል፡፡ 
62.2. የአስተዳደር መምሪያ የእርሻውንና የሠራተኛውን ደህንነት ለመጠበቅ የሚረዳ የማህበሩን
የሚያሳትፍ አንድ የሴፍቲ ኮሚቴ ከሚመለከታቸው ክፍሎ በመሰየም ያቋቁማል፡፡ የተቋቋመው ኮሚቴ
የተስማማበትንና መውሰድ የሚገባውን የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃ በእርሻዉበሪፖርት መልክ ያቀርባል፡፡
እርሻውም ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፡፡ 
62.3. ለሠራተኛው የቁጠባና የብድር አገልግሎት ማህበር በእርሻዉውስጥ ለጽህፈት ሥራ የሚገለገልበት
ጽ/ቤት ይፈቀድለታል፡፡ 
ሀ. ከሠራተኞች ላይ የተሰበሰበው ገንዘብ በቀጣዩ 10 ቀን ውስጥ ማህበሩ ለወከለው አካል በህጋዊ ደረሰኝ
ገቢ ያደርጋል፡፡ 
ለ. የቁጠባ ማህበሩ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ለመሰብሰብ ሲፈልጉ ድርጅቱን ሲጠይቁ ከ 2 ሰዓት
ያልበለጠ ጊዜ ድርጅቱ ሲፈቅድ ይችላል፡፡ 
ሐ. የቁጠባ ብድር ኮሚቴ አባላት ከሥራው ጋር ተያያዥነት ባለው መንገድ ከእርሻው ውጭ ለስብሰባ
ሲጠሩ ማስረጃ ሲቀርብ የሚከፈልበት ፍቃድ ይሰጣል፡፡ 
62.4. ለእርሻው ሠራተኞች በእርሻዉአድራሻ የሚመጡ ደብዳቤዎች በእርሻዉመዝገብ ቤት ተመዝግበው
ለሠራተኛ እንዲደርሱ እርሻው ያደርጋል፡፡ 
62.5. ድርጅቱ ለማህበሩ መገልገያ የሚሆን ጽ/ቤት እንዲኖረው ያደርጋል፡፡ 
62.6. ድርጅቱና ማህበሩ የበዓል ዋዜማና ማግስት የእርሻው ሥራ ተቋርጦ ከዋዜማው በፊት ወይም በኋላ
በማካካሻ እንዲሰራ በማስማማት በሚያሳልፉት ውሳኔ መሠረት የእርሻው ሥራ ስምምነት ላይ
በተደረሰበት ቀን እንዲካካስ ማድረግ ይቻላል፡፡ 
አንቀጽ 63 
ፕሮቪደንት ፈንድ 
63.1. የፕሮቪደንት ፈንድ ማጠራቀሚያ ለእያንዳንዱ ሠራተኛ በስሙ የተለየ አካውንት ድርጅቱ ውል
ከመሠረተበት ባንክ ውስጥ ይከፍታል፡፡ 
63.2. የፕሮቪደንት ፈንድ ከሠራተኛው ደመወዙን 7 በየወሩ በመቁረጥ ከድርጅቱ 11 የሚያክል በመቁረጥ
በድምሩ 18 በየወሩ በተከፈተው የየአንዳንዱ ሠራተኛ አካውንት እንዲጠራቀም ያደርጋል፡፡ ሆኖም
የመንግስት የጡረታ ህግ ክፍያ በአዋጅ ሲሻሻል ከሠራተኛውና ከአሰሪው ለጡረታ በሚሰበሰበው መጠን
የፕሮቪደንት ተከፋዮችመም በዚያው መጠን የሚሰበሰብ ይሆናል፡፡ 
63.3. ሠራተኛው በማንኛውም ምክንያት የሥራ ውሉ ከተቋረጠ በየወሩ ከአሠሪውና ከሠራተኛ
የተጠራቀመለትን ከነባንክ ወለዱ ተሰልቶ ይከፈለዋል፡፡ 
ክፍል አስራ አምስት
ጠቅላላ ስምምነቶችንና ድንጋጌዎችን በተመለከተ 
አንቀጽ 64 
የይርጋ ጊዜ 
64.1. በዚህ ህ/ስምምነት ከተጠቀሱት በስተቀር ማናቸውም የይርጋ ጥያቄ በአዋጅ ቁጥር 377/96
መሠረት ይፈጸማል፡፡ 
አንቀጽ 65
የህብረት ስምምነት ስለማሻሻል
65.1. ይህን የህብረት ስምምነት እርሻውና ሠራተኛ ማህበሩ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96
መሠረት ለማሻሻል ይችላሉ፡፡ 
65.2. በዚህ ህ/ስምምነት የተጠቀሱትን አንቀጾች አግባብ ያላቸው በእርሻዉውስጥ ያሉ ደንቦች
መመሪያዎች፣ ሰነዶች፣ ትዕዛዞች የዚህ ህ/ስምምነት አካል ይሆናሉ፡፡ 
65.3. አዲስ ሁኔታዎችና አዲስ አሠራር ሲያጋጥም እርሻውና ማህበር በጋራ በመነጋገር የዚህ ህብረት
ስምምነት አካል እና የሆኑ በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት እንዲመዘገብ 
አንቀጽ 66
የህብረት ስምምነት ኮፒ ለሠራተኛ ማህበር ስለመስጠት 
66.1. ድርጅቱና ሠራተኛ ማህበሩ ተደራድረው ስምምነት የደረሱበትንና በማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር
ጽ/ቤት ጸድቆ የተመዘገበውን ሰነድ ድርጅቱ ለማህበሩ ሥራ አስፈጻሚ በኮፒ እንዲደርስ ያደረጋል፡፡ 
66.2. ድርጅቱና ሠራተኛ ማህበሩም ለእያንዳንዱ ሠራተኛ የህ/ስምምነቱ ቅጂ እንዲደርስ ጥረት
ያደርጋሉ፡፡ 
አንቀጽ 67 
የህብረት ስምምነቱ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ 
67.1. ይህ የህብረት ስምምነት በዕድገት ድርና ማግ የስፌት አክስዮን ማህበር ሥራ አመራርና በእድገት
ድርና ማግ የስፌት ክር አክስዮን ማህበር መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር መካከል ተፈርሞ በሰራተኛና
ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት ጸድቆ ከተመዘገበበት ወር የመጀመሪያው ቀን አንስቶ ለሶስት ዓመት
የሚያገለግል ይሆናል፡፡ 
የህብረት ስምምነት ተደራዳሪ ወገኖች 
ሀ. የድርጅቱ ተወካዮች  ኃላፊነት  ፊርማ 
1. አቶ ተስፋዩ ያይንሸት  አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ  _______________
2. አቶ ተስፋዩ መዋህዶ  የባለሀብት አማካሪ   _______________
3. አቶ አዲ አናጋው  የፈትል ምርትና ጥገና ክ/ኃ  _______________

ለ. የመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ተወካዮች  ኃላፊነት  ፊርማ 


1. አቶ ለማ በላይነህ  የማህበሩ ሊቀመንበር 
2. አቶ እሸቱ ማሞ  የማህበሩ ም/ሊቀመንበር
3. ወ/ሮ ሰናይት የሚ  የማህበሩ የሂሳብ ሹም 

You might also like