You are on page 1of 49

በደቡብ ም/ኢት/ያ ሕ/ክ/መንግስት ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ

ልማት ቢሮ

ወደ አነስተኛ እና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ አዲስ ለሚገቡ ባለሀብቶች


በመንግስት የሚሰጡ ድጋፎችንና ምቹ ሁኔታዎችን ለማስተዋወቅ የተዘጋጀ የፕሮሞሽን ሰነድ
የሰነዱ አዘጋጆች
1.አቶ ስዩም ተፈራ ሀ/ማርቆስ ማስቴርስ ድግሪ/ከኢን/ኢንዱ/ል/ቢሮ፣
2.አቶ ሽመልስ ባቲሣ ባይከዳኝ ማስቴርስ ድግሪ/ከኢን/ኢንዱ/ል/ቢሮ፣

3.አቶ ማሞ ማስቴርስ ድግሪ ግብርና ቢሮ፣


4.አቶ ይደነቅ ማስቴርስ ድግሪ/ከንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ፣

ታህሳስ/ 2015 ዓ.ም


ቴፒ

ማውጫ
ርዕስ ገጽ

መግቢያ.............................................................................................................................................................3

0
ክፍል አንድ..........................................................................................................................................................6
1.1 አጭር ርዕስ.....................................................................................................................................6
1.2 የቃላት ትርጓሜ..............................................................................................................................6
1.5 የተፈጻሚነት ወሰን............................................................................................................................11
1.6 መርሆች...........................................................................................................................................11
2. በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ዘርፍ ያሉ ክልላዊ ምቹ ሁኔታዎች...............................12
2.1 አስተማማኝ የሆነ የግብርና ምርት.......................................................................................................12
1) ቡና..................................................................................................................................................12
2) የፍራፍሬና የአትክልት ምርት...................................................................................................................12
3) ቅመማ ቅመም.....................................................................................................................................13
2.2 .የእንስሳት ውጤት..............................................................................................................................13
1) ዶሮ..................................................................................................................................................13
2) ማር..................................................................................................................................................13
1) ወረቀትና ፐልፕ ፋብሪካ ግብዓት..............................................................................................................13
2.4 የከርሰ ምድር ማዕድናት......................................................................................................................14
2.6. የተረጋጋና ለኢንቨስትመንት የሚያመች የኢኮኖሚ ሁኔታ......................................................................14
2.7. የሰለጠነ የሰው ሃይል..........................................................................................................................14
2.8 የኢንቨስትመንት ዋስትና.....................................................................................................................14
በክልሉ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ማረጋገጥ የሚቻል ሲሆን ለአብነት፡-...........................14
2.9 የታክስ ማበረታቻ..............................................................................................................................14
2.10 ለአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ድጋፍ ሊሰጡ የሚችሉ ተቋማት መኖራቸዉ.........15
ክፍል ሦስት.......................................................................................................................................................16
3. በመንግስት ድጋፍ የሚደረግላቸው የማኑፋክቸሪንግ ንዑስ የሥራ ዘርፎች......................................................16
3.1 ጨርቃጨርቅና አልባሳትሥራ ውጤቶች ውጤቶች.........................................................................16
3.2 ቆዳና የቆዳ ሥራ ውጤቶች................................................................................................................16
3.3 የብረታ ብረት ሥራ ውጤቶች.............................................................................................................16
3.4 የእንጨት ሥራ ውጤቶች...................................................................................................................16
3.5 የግብርና ዉጤቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ (Agro-processing industries).......................................17
3.6 የዕደ ጥበብ ዉጤቶችና ጌጣጌጥ ሥራ ውጤቶች....................................................................................17
3.7 ኬምካልና የኬምካል ውጤቶች.............................................................................................................17
3.8 የግንባታ ግብዓቶች................................................................................................................................18
3.9 ብረት ያልሆኑ የማዕድን ውጤቶች ኢንዱስትሪ.....................................................................................18
3.10 የኮምፒወተር ፤የኤሌክትሮኒክስ እና የእይታ ዕቃዎች ኢንዱስትሪ..........................................................18

1
3.11 የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ኢንዱስትሪ......................................................................................................18
3.12 መሰረታዊ መድኃኒት ምርት እና የመድኃኒት ዝግጅት ኢንዱስትሪ............................................................19
ክፍል አራት......................................................................................................................................................20
4. በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የሚደረጉ መንግስታዊ ድጋፎች................................................................................20
4.1 የአዋጭነት ጥናቶች...........................................................................................................................20
4.2 የአቅም ግንባታና የቴክኖሎጂ ድጋፎች..................................................................................................20
4.3 የማምረቻ ቦታ ድጋፍ.........................................................................................................................20
4.4 የገበያ ትስስር.......................................................................................................................................21
4.5 የኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃ አቅርቦት ድጋፍ..................................................................................................21
4.6 የፋይናንስ ድጋፍ................................................................................................................................22
ሀ. የዱቤ ግዢ / Hire Purchase/..........................................................................................................22
ለ. የፋይናንስ ኪራይ /Financial Lease/................................................................................................23
4.7 በኢንቨስትመንት አዋጅ መሰረት የሚሰጡ ድጋፎች................................................................................24
4.9 የጉምሩክ ታሪፍ ደንበኛ 2 ኛ ሀ እና አጠቃቀም አዋጅ መሰረት የሚሰጥ ድጋፍ.......................................................27
4.10 በኤክስፖርት የስራ ላይ የሚሰማሩና የተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች የመንግስት ወጪ መጋራት ስርዓት.................27
ክፍል አምስት..................................................................................................................................................28
5. በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ትኩረት የሚሰጣቸዉ ህብረተሰብ ክፍሎች እና ቅድሚያ የሚሰጣቸዉ ባለሀብቶች.....28
5.1 በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ትኩረት የሚሰጣቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎች...................................................28
ክፍል ስድስት....................................................................................................................................................30
6. በመንግስት የሚሰጡ ድጋፎችን እና ምቹ ሁኔታዎችን የምናስተዋውቅበት የፕሮሞሽን ስልቶች.............................30
6.1 ማስታወቂያ (Advertsing)............................................................................................................30
6.2. የሁነት ስልቶች (Events)....................................................................................................................31
6.3. የህዝብ ግንኙነት ስልት..........................................................................................................................32
7. አባሪዎች........................................................................................................................................33

መግቢያ
ሀገራችን እስከ 2022 ዓ.ም ድረስ ከድህነት ተላቃ መካከለኛ ገቢ ካላቸዉ አገራት መቀላቀል የሚያስችል አገራዊ ራዕይ
ተቀርጾ እየተተገበረ ይገኛል፡፡ በዚህ መነሻ በሀገር ደረጃ የተያዘውን ራዕይ ለማሳካት በክልላችንም የአነስተኛና መካከለኛ
አምራች ኢንዱስትሪዎች ልማት ሊያሳካ የሚችል ሥራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ለብዙ ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር የህብረተሰቡን ገቢ በማሳደግ፣ ከዉጭ የሚገቡ
ምርቶችን በመተካት የዉጪ ምንዛሪን ማዳንና ወደ ዉጭ የሚላኩ ምርቶችን በማምረት የዉጪ ምንዛሪ ማስገኘት፣
በሀገር ውስጥ የፈጠራ ስራዎችንና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እንዲስፋፉ ያደርጋል፡፡ በዚሁ መሰረት የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ

2
አደረጃጀት ክልሉ አሁን የደረሰበትን እና ቀጣይ የሚፈጠሩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮችን በማስተናገድ ብሎም
የመንግስትን የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ በተጠናከረ፣ በቀልጣፋና በውጤታማ ሁኔታ የማስፈጸም አቅም ያለው እንዲሆን የክልሉ
መንግስት አስፈጻሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው በተሻሻለዉ አዋጅ ቁጥር 4/2014 ዓ.ም መሰረት ከተቋቋሙ
ቢሮዎች ውስጥ አንዱ የኢንተሪፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ነዉ፡፡

ስለሆነም ቢሮው በአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ልማት ዙሪያ የተለዩ ዋና ዋና ማነቆዎች ፡-
የአመለካከት፣ የማምረቻ ቦታ፣ የማምረቻ መሳሪያዎች፣ የፋይናንስ፣ የቴክኖሎጂና የክህሎት ክፍተቶችን ለመፍታት
ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ ይገኛል፡፡

የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ በኢኮኖሚዉ የሚኖረዉን ድርሻ ለማሳደግ በክልሉ ዉስጥ ለሚገኙ ባለሀብቶች መንግስት ለዘርፉ
ያስቀመጠውን ድጋፊ ለማሳወቅ የፕሮሞሽን ሰነድ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

በዚሁ መሠረት ሰነዱ በስድስት ክፍሎች የተዘጋጀ ሲሆን መግቢያ፣ በክፍል አንድ አጭር ርዕስ፣ የቃላት ትርጓሜ፣ ዓላማ፣
አስፈላጊነት፣ ወሰን፣ መርሆዎች በክፍል ሁለት በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ያሉ ክልላዊ ምቹ
ሁኔታዎች፣ በክፍል ሶስት በመንግስት ድጋፍ የሚደረግላቸዉ የማኑፋክቸሪንግ ንዑስ ዘርፎች፣ በክፍል አራት
በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የሚደረጉ መንግስታዊ ድጋፎች፣ በክፍል አምስት በማንፋክቸሪንግ ዘርፍ ትኩረት የሚሰጣቸዉ
የህብረተሰብ ክፍሎችና በክፍል ስድስት የፕሮሞሽን ስልቶችን አካቶ የያዘ ነው፡፡

የክልሉ አጠቃላይ ገጽታ


የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦችክልል በሀገራችን 11 ኛ ክልል ሆኖ በቅርቡ የተዋቀረ አዲስ ክልል ነዉ፡ ፡ ክልሉ በሰሜን
አቅጣጫ ከኦሮሚያ ክልል፣ በምዕራብ ከጋምቤላ ክልል፣ በደቡብ ከደቡብ ሱዳን እና ከደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ፣
በስተምስራቅ ከጎፋና ወላይታ ዞኖች፣ በስተሰሜን ምስራቅ ከምባታና ሀድያ ዞኖችያዋስኑታል። ክልሉ በ 5° 19' 39.69"N -
8° 9' 15.86" N 34° 53' 21.33" E - 37° 31' 36.40" አቅጣጫ ላይ የሚገኝ ሲሆን አሁን ባለዉ አደረጃጀት
በዉስጡ 6 ዞኖች ያሉት ሲሆን አጠቃላይ የቆዳው ስፋት 39,061.4 ስኩዌር ኪ/ሜ (3.91 ሚሊዮን ኼ/ር) እንደሚሆን
ይገመታል።

የ 1999 ዓ.ምየሕዝብና ቤቶችቆጠራን ውጤት መሰረት በማድረግ በተደረገው ትንበያ በ 2012 ዓ.ምየክልሉ ህዝብ ብዛት
3,397,005 እንደሚሆን ሲገመት ከዚህ ውስጥ ወንድ 1,695,529 (49.91%) እና ሴት 1,701,476 (50.09%) ድርሻ
አላቸው። ከአጠቃላይ ሕዝብ ብዛት በገጠር 86.4% እና በከተማ 13.6% የሚኖሩ ሲሆን የህዝብ ጥግግቱ በአማካይ በ 1
ካሬ ኪ/ሜትር መሬት 87 ሰዎችእንደሚኖሩ ይገመታል። ከጠቅላላው የህዝብ ቁጥር ከ 15-64 ዕድሜክልል ውስጥ የሚገኝ
ህዝብ ብዛት 52% መሆኑ ሲታይ በምርት ተግባር ላይ ሊሠማራ የሚችል የልማት ሀይል በበቂ ሁኔታ መኖሩን ያመላክታል።

የክልሉ መልከዓ-ምድራዊ አቀማመጥ ከባህር ወለል በላይ ከ 348-3346 ሜትር ወሰን ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ የአየር ፀባዩ
ለተለያዩ የግብርና ሥራዎች ምቹ ነው። አማካይ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ከ 400-2200 ሚ/ሜ ሲሆን የሙቀት መጠን
ከ 15.1o ሴ.ግ-27.5o ሴ.ግ ይደርሳል። ክልሉ ከሥነ-ምህዳራዊ ስብጥር አንፃር በረሃ 4.09%፣ ቆላ 56.50%፣ ወይናደጋ
33.51%፣ ደጋ 5.86% እና ዉርጭ 0.03% የአየር ፀባይ አለው። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ ሕዝቦች ክልል በሀገሪቱ
3
የውጭ ምንዛሪ ግኝት ከፍተኛ ድርሻ ያላቸዉ የተለያዩ ዕምቅ የተፈጥሮና ግብርና ሀብቶች ባለቤት ሲሆን ለአብነት ሊጠቀሱ
የሚችሉ የኮንስትራክሽን ማዕድናት፣ የከበሩ ማዕድናት፣ የገጸ-ምድር ውሃ፣ ቡና፣ ቅመማ ቅመም ወ.ዘ.ተ. እንዲሁም የተለያዩ
ዓይነት ዕፅዋትና እንስሳት የሚገኙበት ክልል ነዉ፡ ፡

ከኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ልማት ተቋምአንፃር በ 2014 በጀት ዓመት በክልሉ 92 አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ
ጣቢያ ፣ 16 የከተማ አስተዳደር ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት፣41 የወረዳ ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ
ልማት ጽ/ቤት ፣6 የዞን ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ መዋቅሮች ሲኖሩን፣በገጠር ስራ ዕድል ፈጠራ
ተደራጅተው በስራ ላይ የሚገኙ 4?200 ኢንተርፕራይዞች በውስጣቸው ወንድ 12?600 ሴት 8?400 ድምር 21?000
ተጠቃሚዎች፣በከተማ ስራ ዕድል ፈጠራና በከተማ ምግብ ዋስትና ዘርፍ 4?957 በስራ ላይ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች
በውስጣቸው ወንድ 10?984 ሴት 7@063 ድምር 1?8047 ተጠቃሚዎች፣በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ
602 መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች135 ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችድምር 737 በውስታቸው ወንድ-2?
054 ሴት894 ድምር 2@948 ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን በክልሉ ኢንተርፕራይዞችና
ኢንዱስትሪ ልማት ተቋም በአጠቃላይ በሦስቱም ዘርፍ 9@894 ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተው በውስጣቸው ወንድ
25@638 ሴት16@357 በድምሩ 41@995 ተጠቃሚዎችን/አባላትን/ በመያዝ የስራ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ፡ ፡

4
ካርታ፤1 የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ ህዝቦች ክልል የአስተዳደር ወሰን ካርታ

ክፍል አንድ
1.1 አጭር ርዕስ
ይህ ሰነድ በክልላችን ወደ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች አዲስ ለሚገቡ ባለሀብቶች

የተዘጋጀ (የፕሮሞሽን) የማስተዋወቅ ሰነድ ተብሎ ሊጠራ ይችላል፡፡


1.2 የቃላት ትርጓሜ
የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም እስካልተሰጠው ድረስ በዚህ የድጋፍ ማዕቀፍ ሰነድ ፡-

1) “ሚኒስቴር” ማለት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ማለት ነው፣


2) “ክልል” ማለት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ማለት ነው፣
3) “ከተማ” ማለት ማዘጋጃ ቤት የተቋቋመበት ወይም 2 ሺህ ወይም ከዚህ በላይ የሕዝብ ቁጥር ያለውና ከዚህ
ውስጥ 50 በመቶ የሚሆነው የሰው ኃይል ከግብርና ውጭ በሆነ ሥራ የተሰማራ ሆኖ የሚገኝበት አካባቢ ነው፣

5
4) “የከተማ አስተዳደር” ማለት በከተሞች ውስጥ እንደ ማዘጋጃ ቤት ያለ የከተማ አስተዳደርና አገልግሎት
እንዲሰጥ የተቋቋመና ራሱን የቻለ አስተዳደራዊ አካል ነው፣
5) “ቢሮ” ማለት የክሉሉን አስፈጽሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 4/2014 ን መሰረት የደቡብ
ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መንግሥት ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ነው፣
6) ”ኢንዱስትሪ” ማለት ማሽን፣ቴክኖሎጂ እና የሰው ኃይል በመጠቀም ምርትን የማምረት ሂደት ነው፣
7) “ማኑፋክቸሪንግ “ማለት ማሽንን፣ መሳሪያን ወይም ጉልበትን በመጠቀም ጥሬ ዕቃ ላይ የቅርጽ፣ የመጠን ወይም
የይዘት ለውጥ በማድረግ የተሻለ ዋጋ ያለዉ ምርት ማምረት ነው፣
8) “አነስተኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ” ማለት ከ 11 (አስራ አንድ) እስከ 50 (ሃምሳ) ቋሚ ሰራተኞች የያዘ እና ከብር
600,001 (ስድስት መቶ ሺህ አንድ) እስከ ብር 10,000,000 (አስር ሚሊዮን) ጠቅላላ ሐብት ያለው ኢንተርፕራይዝ ነው፤
ሆኖም ግን በሰው ኃይልና በጠቅላላ ሐብት መካከል አሻሚ ሁኔታ ሲፈጠር ጠቅላላ ሐብት ገዥ መስፈርት ይሆናል፤
9) “መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ” ማለት ከ 51 (ሃምሳ አንድ) እስከ 100 (መቶ) ቋሚ ሰራተኞች የያዘ እና ከብር
10,000,001 (አስር ሚሊዮን አንድ) እስከ 90,000,000 (ዘጠና ሚሊዮን) ጠቅላላ ሐብት ያለው ኢንተርፕራይዝ ነው፤
ሆኖም ግን በሰው ኃይልና በጠቅላላ ሐብት መካከል አሻሚ ሁኔታ ሲፈጠር ጠቅላላ ሐብት ገዥ መስፈርት ይሆናል፤
10) “ከፍተኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ” ማለት ከ 100 (መቶ) በላይ ቋሚ ሰራተኞች የያዘ እና
ከብር 90,000,000 (ዘጠና ሚሊዮን) በላይ ጠቅላላ ሐብት ያለው ኢንተርፕራይዝ ነው፤ ሆኖም ግን
በሰው ኃይልና በጠቅላላ ሐብት መካከል አሻሚ ሁኔታ ሲፈጠር ጠቅላላ ሐብት ገዥ መስፈርት
ይሆናል፤
11) ”ኢንዱስትሪ ፓርክ” ማለት ለኢንዱስትሪ ልማት በፕላን የተከለለና አስፈላጊውን መሰረተ ልማት የተሟላለት

ቦታ ነው፣
“ባለሃብት”ማለት በክልል ውስጥ ኢንቨስት ያደረገ የአገር ውስጥ ወይም የውጭ ባለሃብት ነው፣
“የአገር ዉስጥ ባለሃብት” ማለት የኢንቨስትመንት ካፒታል በስራ ላይ ያዋለ ኢትዮዽያዊ ወይም አግባብ ባለዉ ህግ እንደ አገር
ዉስጥ ባለሀብት የተቆጠረ የዉጭ አገር ዜጋ ሲሆን መንግስትንና የመንግስት ልማት ድርጅትን እና አግባብ ባለዉ ህግ
የተቋቋሙ የሕብረት ስራ ማህበራትን ይጨምራል፣
“የውጭ ባለሃብት” ማለት የውጭ ካፒታል ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት ኢንቨስት ያደረገ የውጭ አገር ዜጋ ወይም ሙሉ በሙሉ
የውጭ አገር ዜጋ ባለቤትነት የተያዘ ድርጅት ወይም ከአገር ውስጥ ባለሃብት ጋር በቅንጅት ኢትዮጵያ ውስጥ በተቋቋመ
ድርጅት ኢንቨስት ያደረገ የውጭ አገር ዜጋ ወይም ድርጅት ሲሆን ትዉልደ ኢትዮጵያዊ የሆነ የዉጭ አገር ዜጋ
ይጨምራል፣
“የኢንዱስትሪ ባለቤት” ማለት ማሽን፣ ቴክኖሎጂ እና የሰው ኃይል በመጠቀም ምርትን የሚያመርት የኢንዱስትሪ ባለቤት
ነው፣
”ሠራተኛ” ማለት በኢንዱስትሪ ውስጥ በቋሚ ወይም በጊዜያዊነት ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች ማለት ነዉ፣
”ካፒታል” ማለት የሀገር ውስጥ ወይም የውጭ ገንዘብ የሚተላለፍ ሰነድ የማምረቻ ወይም የአገልግሎት መስጫ መሣሪያ ፣ሕንጻ
፣ የሥራ ማስኬጃ ካፒታል፣ የንብረት መብት ፣የፓተንት መብት ወይም ሌላ የንግድ ሀብት ነው፣
“የውጭ ካፒታል” ማለት ከውጭ ምንጭ የተገኘ ካፒታል ሲሆን በውጭ ባለሀብት ወደ ካፒታል የተለወጠ በአገር ውስጥ
የተገኘ ትርፍንና የትርፍ ድርሻን ይጨምራል፣

6
”ኢንቨስትመንት ቦርድ” ማለት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚቋቋም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ ነው፣
”የኢንዱስትሪ ልማት ክላስተር” ማለት የኢንዱስትሪ እድገትን የአከባቢ ብክለት ተፅኖን የመቀነስ እና የከተሞች እድገትን
በእቅድና በስርዓት የመምራት አበይት ዓለማዎችን የያዘ ሆኖ እቅድን መሰረት አድርጎ እንደመንገድ፣ የኤሌክትሪክ ሃይል
ውኃና የመሳሰሉ አስፈላጊ መሰረተ ልማቶች ፣የተለያዩ አገልግሎቶች ተሟልተውለት እና ልዩ የማበረታቻ ዕቅድ ኖሮት ፣
አንድ ዓይነት ወይም ተመሳሳይነት ወይም ተመጋጋቢነት ያላቸው ኢንዱስትሪዎችን በስብስብ ለማልማት ወይም ሁለገብ
ኢንዱስትሪዎችን ለማልማት የሚቋቋም ድንበር የተበጀለት አግባብ ባለው አካል የተሰየመ የተወሰነ ቦታ ሲሆን ልዩ
የኢኮኖሚ ቀጠናን የኢንዱስትሪ ፓርክን፣ የቴክኖሎጂ ፓርክን፣ የኤክስፖርት ማቀነባበሪያ ቀጠናን ነጻ የንግድ ቀጠናን እና
በኢንቨስትመንት ቦርድ የሚወሰኑ የመሳሰሉትን ይጨምራል፣
“ሊዝ ፋይናንሲንግ” ማለት ልማት ባንክ እና የክልሎች ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አክስዮን ማህበራት ለአነስተኛና
መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች የካፒታል እቃዎችን ገዝተው በዱቤ ግዥ ስርዓት (Hire-purchase modality) በኪራይ
የሚያቀርቡት አገልግሎት ማለት ነዉ፣
“ኢንቨስትመንት” ማለት አዲስ ድርጅት ለማቋቋም ወይም ነባር ድርጅትን ለማስፋፋት ወይም ለማሻሻል በባለሀብት ገንዘብ
ወይም በዓይነት ወይም በሁለቱ የሚደረግ የካፒታል ወጪ ነዉ፣
“ፕሮሞሽን/ ማስተዋወቅ” ማለት ለአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚሰጡ አገልግሎቶችንና የዘርፉን ተልዕኮ
እንዲታወቅ የማድረግ ሥራ ነው፣
“ድርጅት“ ማለት ለትርፍ የተቋቋመ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪ ነዉ፣
“የገበያ ትስስር” ማለት ለአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የገበያ እድል ለመፍጠር ከመንግስትና መንግስታዊ
ካልሆኑ ድርጅቶች፣ በሀገር ውስጥና ውጪ ከሚገኙ የመካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ጋር በግብዓት፣ በምርትና
አገልግሎት አቅርቦት (በግዢና ሽያጭ)፣ በጎንዮሽና በተዋረድ ግንኙነት የሚፈጠር የገበያና ግብይት ሥርዓት ነው፣
”ቴክኖሎጂ” ማለት አንድን ግብዓት በቀላሉ ገበያ ላይ ሊውል ወደ ሚችል ምርት የመለወጥ ሂደት ሲሆን
ቁሳዊ፣ዕውቀታዊ፣ሰነዳዊና ድርጊታዊ ክፍሎችን ያካተተ ነው፣
”የቴክኖሎጂ ሽግግር” ማለት ምርትን ለማምረት ወይም የአመራረት ሂደትን ተግባራዊ ለማድረግ ወይም ለማሻሻል ወይም
አገልግሎት ለመስጠት የሚረዳ ሥርዓት ያለው ዕውቀት ማስተላለፍ ሲሆን የሥራ አመራር እና የቴክኒክ ዕውቀት፣ የግብይት
እና ቴክኖሎጂንም ይጨምራል፡፡ ሆኖም ዕቃዎችን ብቻ ለመሸጥ ወይም ለማከራየት የሚደረግን ግንኙነት አይሸፍንም፣
“ክላስተር” ማለት በአንድ አካባቢ ተሰባስበው ያሉ የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ተመጋጋቢ የሆኑ
የተለያዩ ምርቶችና አገልግሎቶችን የሚያቀርቡና ተመሳሳይ ስጋትና መልካም አጋጣሚውንም የሚጋሩ ተቋማት ስብስብ ነው፣
"የተቀናጀ የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ" ማለት የግብርና ውጤቶችን በግብዓትነት የሚጠቀሙ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎችን
በክላስተር ደረጃ ተቋቁመው የጋራ የሆነ መሰረተ ልማት ተሟልቶላቸው ኢንዱስትሪዎቹ በተቀናጀ መልኩ የጅምላ የጥሬ ዕቃ
ግዥ፣የምርት ጅምላ ሽያጭ፣ የስልጠና እና ሌሎች አገልግሎቶችን የሚያገኙበት ማዕከል ነው፣
"የኢንዱስትሪ ዞን" ማለት አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ከክላስተር ማዕከላቱ የቆይታ ጊዜያቸውን
አጠናቀው ሲወጡ በዘላቂነት የራሳቸውን ግንባታ በማካሄድ የሚጠቀሙበት በመንግሥት መሰረተ ልማት ለምቶ የሚተላለፍ
ቦታ ነው፣
"የካፒታል ዕቃ" ማለት ምርት ለማምረት ወይም አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ የማምረቻ ወይም አገልግሎት መስጫ
መሳሪያች ወይም ዕቃዎች እና አክሰሰሪዎች ሲሆኑ ለእነዚህ አገልግሎት የሚውሉ የወርክሾፕ እና የላበራቶሪ መሣሪያዎችንና
ዕቃዎችን ይጨምራል፣
"የግንባታ ዕቃ" ማለት ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ግንባታ የሚያገለግሉ መሰረታዊ ግብዓቶችን ያጠቃልላል፣

7
"የጉምሩክ ቀረጥ" ማለት በገቢ ዕቃዎች ላይ የሚጣሉ ቀጥተኛ ያልሆኑ ታክሶችንም ይጨምራል፣
"የገቢ ግብር" ማለት የፌዴራሉ መንግስት ወይም የክልል መንግሥታት ወይም የሁለቱ የጋራ ገቢ የሆነ በትርፍ ላይ የሚጣል
ታክስ ነው፣
"የኢንቨስትመንት ማስፋፋት" ማለት ሊደረስበት የሚችል የነባር ድርጅትን የማምረት ወይም አገልግሎት የመስጠት አቅም
ቢያንስ 50 በመቶ በመጠን ማሳደግ ወይም የነባር ድርጅትን አዲስ የማምረቻ ወይም አገልግሎት መስጫ መስመር
በመጨመር ምርትን ወይም አገልግሎትን ቢያንስ መቶ በመቶ በዓይነት ማሳደግ ወይም በሁለቱም ማሳደግን ያጠቃልላል፣
"ተመላሽ ቀረጥ" ማለት ወደ ዉጭ ለሚላኩ ሸቀጦች ማምረቻ በሚዉሉ ጥሬ ዕቃዎች እና አላቂ የምርት መገልገያዎች ላይ
የተከፈለ እና ሸቀጡ ተመርቶ ወደ ዉጭ በሚላክበት ጊዜ ለከፋዩ ተመላሽ የሚደርግ ቀረጥ ነዉ፣
"ቀረጥ" ማለት ወደ አገር ዉስጥ በሚገቡ ወይም በአገር ዉስጥ በሚመረቱ ጥሬ ዕቃዎች፣ ሸቀጦች ወይም አላቂ የምርት
መገልገያዎች ላይ የሚከፈል ቀጥተኛ ያልሆነ ማንኛዉም ታክስ ወይም ቀረጥ ነዉ፣
"ወደ ዉጭ መላክ" ማለት ከኢትዮዽያ ዉጭ ሸቀጦችን መላክ ሲሆን ከኢትዮዽያ ዉጭ ለመሄድ ለተዘጋጁ መጓጓዣዎች ላይ
ሸቀጡን መጫንን ይጨምራል፣
"ሸቀጥ" ማለት ወደ አገር በገባበት ሁኔታ ተመልሶ የተላከ ወይም ለዉጭ ገበያ እንዲዉል የተመረተ ዕቃ ሲሆን ወደ ዉጭ
የሚላኩ ሸቀጦችን ለመያዣ፣ ለመጠቅለያ ወይም ለማሸጊያ የሚዉለዉን ይጨምራል፣
"ላኪ" ማለት በአገር ዉስጥ የተመረቱ ሸቀጦችን ለዉጭ ገበያ ለማቅረብ የንግድ ፈቃድ የተሰጠዉ ኢንዱስትሪ ነዉ፣
"አምራች" ማለት አምራች ላኪ ወይም ቀጥተኛ ያልሆነ አምራች ላኪ ነዉ፣
"አምራች ላኪ" ማለት ያመረተዉን ምርት ሙሉ በሙሉ፣ በከፍል ወይም በተወሰነ ወቅት ለዉጭ ገበያ የሚያቀርብ
ኢንዱስትሪ ነዉ፣
"ቀጥተኛ ያልሆነ አምራች ላኪ" ማለት ያመረተዉን ምርት በጥሬ ዕቃ ወይም በከፈል በተፈበረከ ወይም ባለቀለት ዕቃ መልኩ
ሙሉ በሙሉ፣ በከፈል ወይም በተወሰነ ወቅት ለሌላ ቀጥተኛ ያልሆነ አምራች ላኪ ፣ ለአምራች ላኪ ወይም ለላኪ
የሚያቀርብ ኢንዱስትሪ ነዉ፣
"ጥሬ ዕቃ አቅራቢ" ማለት ከዉጭ የመጣዉን ጥሬ ዕቃ በምርት ሂደት ዉስጥ እንዲያልፍ ሳያደርግ ባለበት ሁኔታ ሙሉ
በሙሉ፣ በከፈል ወይም በተወሰነ ወቅት ለአምራች ላኪ ወይም ቀጥተኛ ላልሆነ አምራች ላኪ የሚያቀርብ ሲሆን የቦንድድ
ግብዓት አቅርቦት ስርዓት ተጠቃሚ የሆነን አይጨምርም፣
12) “ተሽከርካሪ” የሚለው ቃል የደረቅ፣ የፍሳሽ/የዝቃጭ ማስወገጃ ወይም ማቀዝቀዣ የተገጠመለት የጭነት መኪናን
ወይም ለተለየ አገልግሎት ተብለው የሚዘጋጁ ተመሳሳይ መኪኖችን፤ ፒክ -አፕን፣ ማናቸውም ዓይነት ስቴሽን ዋገንን፣
ከሕዝብ መንገድ ውጭ አገልግሎት የሚሰጥ ልዩ መኪናን (ቶም ካርን) ፣ አውቶቡስን፣ ሚኒባስን፣ ሽፍን የዕቃ ማጓጓዣ
መኪናን (ዴሊቨሪ ቫንን) እና ሞተር ብስክሌትን የሚያካትት ነው፣
13) “አውቶቡስ” ማለት ታጣፊ ወንበሮችን ሳይጨምር ቢያንስ 30 መቀመጫ ያለው የሰው ማጓጓዣ ተሽከርካሪ
ነው፣
14) “ሚኒባስ” ማለት ታጣፊ ወንበሮችን ሳይጨምር ከ 10 ያላነሰ እና ከ 15 ያልበለጠ መቀመጫ ያለው የሰው
ማጓጓዣ ተሽከርካሪ ነው፣
15) “ፒክአፕ” ማለት 2WD ወይም 4WD የሆነ፣ የስሊንደሩ ብዛት በአዲሰ አበባና በአዲሰ አባባ ዙሪያ የኦሮሚያ
ልዩ ዞን ከሆነ ከ 4 ያለበለጠ፤በሌሎች አካባቢዎች ከሆነ ከ 6 ያልበለጠ እና የመጫን አቅሙ ከ 500 ኪ.ግ. እስከ
1500 ኪ.ግ. የሆነ ተሽከርካሪ ነው፣

8
16) “ዴሊቨሪ ቫን” ማለት የመጫን አቅሙ ከ 3000 ኪ.ግ. እስከ 5000 ኪ.ግ. የሆነ ሽፍን የጭነት ተሽከርካሪ ነው፡፡
17) “የጭነት መኪና” ማለት ተሳቢውን ጨምሮ የመጫን አቅሙ ከ 5000 ኪ.ግ. በላይ የሆነ ተሽከርካሪ ነው፡፡
18) “ለተለየ አገልግሎት የሚውል ተሽከርካሪ” ማለት የሥራ መስኩ ልዩ ባህርይ የሚጠይቃቸውና ለመደበኛ
የትራንስፖርት አገልግሎት የማይውሉ ተሽከርካሪዎች ናቸው፡፡
1.3 ዓላማ
ወደ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አዲስ ለሚገቡ ባለሀብቶች በመንግስት የሚሰጡ ድጋፎችን በማሳወቅ በክልሉ
የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ለማስፋትና ለማጠናከር እንዱም ለዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር
ነዉ፡፡
1.4 አስፈላጊነት
ለአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች የሚሰጡ መንግስታዊ ድጋፎች በተለያዩ ተቋማት የሚሰጡ
በመሆናቸው ወጥ የሆነ መረጃ እንዳይኖር አድርጓል፡፡ በዚህ ምክንያት በዘርፉ ለመሰማራትና መዋዕለነዋያቸውን
ለማፍሰስ ለሚፈልጉ ባለሀብቶች መንግስት የሚሰጣቸዉን ድጋፎች፣ያሉትን ምቹ ሁኔታዎችና የዘርፉን ተልዕኮ
ሙሉ በሙሉ ከማወቅ አንጻር ክፍተት ያለ በመሆኑ ይህንን ክፍተት ለመሙላት በአነስተኛና መካከለኛ
ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አዲስ ለሚገቡ ባለሀብቶች በክልሉ ያለውን ጸጋ እና ምቹ ሁኔታ ለማስተዋወቅ እንዲረዳ
ይህ የፕሮሞሽን ሰነድ ማዘጋጀት አስፈልጓል፡፡

1.5 የተፈጻሚነት ወሰን


ይህ ሰነድ ተፈጻሚነት የሚኖረዉ በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ አዲስ መግባት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች
(በኮንስትራክሽን፣ ግብርና፣ ንግድ፣ አገልግሎት እና ማዕድን) ከጥቃቅን ማኑፋክቸሪንግ ወደ አነስተኛ ማኑፋክቸሪንግ
የተሸጋገሩ ኢንዱስትሪዎች፣ ሀብት ያፈሩ አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች፣ የኢንተርፕርነርሺፕ አመለካከትና ፍላጎት
ያላቸዉ የዩኒቨርሲቲ እና የቴክኒክና ሙያ ምሩቃን እንዲሁም በዘርፉ መሰማራት ለሚፈልጉ በውጭ ሃገር ያሉ
የክልሉ ዲያስፖራዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

1.6 መርሆች
ለአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ልማት ድጋፍ አፈጻጻም የሚከተሉት መርሆዎች ይኖሩታል
፡-
1) የግል ባለሀብቱ በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዉ ዘርፍ በሚካሄደዉ ልማት ላይ ሞተር ሆኖ ሚናዉን እንዲጫወት
ማስገንዘብ፣
2) የግብርና ምርቶችን በግብአትነት የሚጠቀምና እሴት ጨምሮ ለገበያ የሚያቀርብ እንዲሁም ለግብርና የሚሆኑ
ግብአቶችን የሚያመርት ኢንዱስትሪ እንዲስፋፋ ግንዛቤ መፍጠር፣
3) ለማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት መንግስት፣ የግል ባለሀብቶችና ህዝቡ በቅንጅት በጋራ
የሚረባረብበት መሆኑን ማስገንዘብ፣
4) ለአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች የሚሰጡ ድጋፎች ግልጽነትና ተጠያቂነት
ያላቸውና የዘርፉን ልማት የሚያረጋግጡ እንዲሆኑ ማድረግ፣

9
5) በዘርፉ የሚካሄዱ የማስፈጸም አቅም ግንባታ ሥራዎች በልማታዊ የህዝብ ግንኙነት እንዲታጀቡ
ማድረግ፣

10
ክፍል ሁለት

2. በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ዘርፍ ያሉ ክልላዊ ምቹ ሁኔታዎች


2.1 አስተማማኝ የሆነ የግብርና ምርት
ክልላችን በአግሮፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ኢንቨስት ለማድረግ በቡናና ሻይ፣በቅመማ ቅመም፣ በእንስሳት ሀብት፣
በቆዳና ቆዳ ውጤቶች፣ ሥጋና ሥጋ ዉጤቶች፣ ወተትና ወተት ተዋጽኦ ማምረት ስራዎች ላይ
ኢንቨስት ለማድረግ የጥሬ እቃ ችግር የሌለበት ክልል ነው፡፡ በተጨማሪ ክልሉ ቆላ፣ ወይናደጋ እና ደጋ
ተፈጥሮአዊና ምቹ የሆኑ የተለያዩ የሰብል ምርቶች፣ የአትክልትና ፍራፍሬ፣ የደን ዉጤቶች እንዲሁም
የተለያዩ ካሽ ክሮፕ የሚመረትበት መሆኑ ምቹና ተመራጭ ያደርጋል፡፡
2.1.1 በክልሉ የሚመረቱ ዋና ዋና ሰብሎች

1) ቡና
ቡና በክልላችን በዋናነት ከሚመረቱ የግብርና ምርቶች መካከል ቀዳሚው ነው፡፡ ይህም በሀገሪቱ
ለውጪና ሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ ከኦሮሚያ በመቀጠል ሁለተኛ ክልል ነው፡፡ በክልላችን ቡና
ከሚመረትባቸው አካባቢዎች ከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ማጂና ሌሎችም ቡና አምራች አካባቢዎች ናቸው
(BOFED 2016) ፡፡

ኢትዮጲያ በየዓመቱ ወደ ዓለም ገበያ ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና ታቀርባለች፡፡ ነገር ግን የሚቀርበው
ቡና ከ 90% በላይ የሚሆነው በጥሬው ታጥቦ የሚላክ ነው፡፡ የኢትዮጵያ 1 ኪሎ የታጠበ ቡና በዓለም
ገበያ አማካይ ዋጋው 1 ኪሎ ሁለት ዶላር ሲሸጥ ተቆልቶ የተቀነባበረና እሴት የተጨመረበት
የሀገራችን ቡና በኪሎ ከ 40 ዶላር በላይ እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ በዚሁ ስሌት ሀገራችን ብሎም
ክልላችን የዚህ ጥቅም ተቋዳሽ መሆን አልቻሉም፡፡

2) የፍራፍሬና የአትክልት ምርት


ማንጎ፣ አቮካዶ፣ አናናስ፣ ሙዝ፣ ወ.ዘ.ተ በክልላችን በርካታ xµÆb!ãC y¸mrt$ s!çN ngR GN kFí¬ Ãlf
Ælmçn# xRî xd„NM çn l@§WN yHBrtsB KFL BlÖM lhg¶t$ ÃSgßW _QM xlmñ„N ytlÆ
_ÂèCÂ mr©ãC ÃúÃl#፡፡

በክልሉ በሁሉም ዞኖች የተለያዩ አይነት አትክልቶችን ለማምረት የሚያስችል ሰፊ ስነ ምህዳርና


የአፈር አይነት መኖሩ መረጃዎች የሚጠቁሙ ሲሆን ለምሳሌ ቲማትም ድንች፣ ስኳርድንች፣
ጎመን፣ ካሮት ወ.ዘ.ተ በስፋት ይመረታል፡፡

11
3) ቅመማ ቅመም
ክልላችን ከሀገሪቱ የቅመማ ቅመም አምራች ክልሎች በአንደኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ከአጠቃላይ
የሀገሪቱ የቅመማ ቅመም ምርትም 37 በመቶውን ድርሻ ይይዛል፡፡ ለምሳሌ፡- እርድ፣ ኮረሪማ፣ ጥምዝ
እና ቆንዶ በርበሬ፣ በርበሬ ወ.ዘ.ተ ቅመማ ቅመሞች በሰፊው እንደሚገኝ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

2.2 .የእንስሳት ውጤት


ኢትዮጵያ በእንስሳት ቁጥር ከአለም 10 ኛ ከአፍሪካ አንደኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን ክልላችን
ደግሞ ከሀገር ምርት 22% ይሸፍናል፡፡ በክልላችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ወተትና የወተት
ተዋፅኦ፣ የስጋ ማቀነባበሪያ እንዱስትሪዎች እንዲሁም ከሚገኙ ተረፈ ምርቶች ማለትም ከቆዳ፤
ከአጥንት፣ ደም፣ ቀንድ እና ሸሆናን በመጠቀም የተለያዩ የኢንዱስትሪ ውጤቶችን ማምረት
ይቻላል፡፡ ለአብነትም የእንስሳት መኖ ማቀነባበርያ፤ የተፈጥሮ ማዳበሪያ፣ የውሀ ማጣርያ፣ አዝራር
እና የመሳሰሉት ሊጠቀሱ ይችላሉ /ምንጭ፡-የቀድመው ደቡብ ክልል የኢንዱስትሪ ፍኖተ ካርታ
ጥናት/፡፡

1) ዶሮ
ሀገራችን 56,866,719 የሚገመት የዶሮ ሀብት ያላት ሲሆን ከዚህ ውስጥ 10,433,733 /18%/ የሚሆነው
የዶሮ ቁጥር የሚገኘው በክልላችን ነው፡፡

2) ማር
ክልሉ ከፍተኛ ለማርና ሰም ልማት ሊውሉ የሚችሉ የተለያዩ ጸጋዎች ማለትም የተለያዩ የማር እጽዋቶችና
ተስማሚ የአየር ንብረትና አካባቢው በተፈጥሮ ደን የተሸፈነና የተለያዩ ለማር ምርት ተስማሚ ዕፅዋት
መኖራቸው፣ የማር ምርት በአግባቡ ቢመረት ከአከባቢው ፍጆታ በላይ በመሆኑ ወደ ውጭ ተልኮ የውጭ
ምንዛሪ ስለሚያስገኝ፣ ምርቱም በዓለም አቀፍ ተፈላጊ በመሆኑ የተለያዩ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
2.3 ደንና የደን ውጤቶች

1) ወረቀትና ፐልፕ ፋብሪካ ግብዓት


በአሁኑ ሰዓት ያሉ የወረቀትና ፐልፕ ማምረቻ እንዱስትሪዎች የሚያመርቱት ምርት ሀገር ውስጥ ገበያውን
ፍላጎት የሚያሟላ ባለመሆኑ አብዛኛው ፍላጎት የሚሟላው ከውጭ በማስገባት እንደሆነ ይታወቃል፡፡
በክልላችን ለወረቀት ፋብሪካ ግብዓት ሊሆን የሚችል ከፍተኛ የቀርክሀ ሀብት፤ ከፍተኛ ሽፋን ያለው የባህር ዛፍ
ተክል፤ ስፋት ያለው የሙዝ ቅጠልና የደረቀ ግንድ፤ በበቂ ሁኔታ ማግኘት ይቻላል፡፡

2.4 የከርሰ ምድር ማዕድናት


የከርሰ ምድር የማዕድን ሃብት በተመለከተ ሀገር አቀፍ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ እና የተፋሰስ የማስተር ፕላን
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ውድ ማዕድናት በስፋት ተሰራጭተው
እንደሚገኙና ለኢንዱስትሪ ክፍለ ኢኮኖሚ ሊውሉ የሚችሉ የወርቅ፣ የከበሩ ድንጋዮች፣ የድንጋይ

12
ከሰል፣ታንታለም፣ቲታንየም፣ዶሎማይት፣ቤንቶናይት፣እምነ በረድ፣ላይም ስቶን፣ የብረት፣ የጌጣ ጌጥና የግንባታ
ማዕድናት እንዳሉ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

2.5. የገበያ አመቺነትና የተለያዩ አማራጮች ፡-

ክልሉ ካላው ሰፊ የህዝብ ቁጥር ያለው ከመሆኑ በተጨማሪ የክልሉ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ከኦሮሚያ፤ከጋምቤላ እና
ከደቡ/ብሄ/ብህ/ህዝቦች ጋር እና ከደቡብ ሱዳን ጋር የሚዋሰንና ቁጥሩ ቀላል የማይባል በባህላዊ ማዕድን ማምረት
የተሰማራው የህብረተሰብ ክፍል ያለን በመሆኑ በክልሉ ውስጥ ለሚመረቱ የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ምርቶች
የገበያ መዳራሻ መሆን የሚችሉ ናቸው፡
2.6. የተረጋጋና ለኢንቨስትመንት የሚያመች የኢኮኖሚ ሁኔታ
 የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ልውውጥ ያለ መሆኑ፣
 መንግስት ለግል ባለሃብቱ ትኩረት የሚሰራ መሆኑ፣
 ለመስራትም ሆነ ለመኖር ምቹና የተጠበቀ የደህንነት ሁኔታ ያለ ስለመሆኑ በተባበሩት መንግስታትና በአለም
አቀፍ የንግድ ምክር ቤት የተመሰከረለት መሆኑ፣
2.7. የሰለጠነ የሰው ሃይል
ክልሉ ከ 6 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያለው ሲሆን ከዚህ ውስጥ ከ 53 በመቶ በላይ የሚሆነው በአምራች እድሜ ክልል
ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡ በክልሉ በአሁኑ ሰዓት በርካታ በተለያዩ ሙያ የሚያሰለጥኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች፣ በርካታ
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት እንዲሁም የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መኖራቸው
በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የሚሰማሩ ባለሃብቶች የሰለጠነ የሰው ሃይል በበቂ ሁኔታ ማግኘት
የሚችሉ መሆኑ፣

2.8 የኢንቨስትመንት ዋስትና


በክልሉ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ማረጋገጥ የሚቻል ሲሆን ለአብነት፡-
ለኢንቨስትመንት የዋለ ሀብት ለህዝብ ጥቅም ሲባልና በህግ በተደነገገው መሰረት ካልሆነ በስተቀር ሊወሰድ ወይም ሊወረስ
የማይቻልና ለኢንቨስትመንት የዋለ ሀብት ለህዝብ ጥቅም ተብሎ ሲወረስ ወይም ሲወሰድ ተመጣጣኝ የሆነ ካሳ የሚከፈል
ይሆናል፡፡

2.9 የታክስ ማበረታቻ


ከውጪ ለሚገቡ የካፒታል ዕቃዎች፣ የጥሬ ዕቃ፣ የገቢ ግብር ታክስ፣ ኤክሳይዝ ታክስ፣ ለወጪ ምርቶች የቀረጥ ቅነሳ
ማበረታቻዎች ያሉ መሆኑ፡፡

2.10 ለአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ድጋፍ ሊሰጡ የሚችሉ ተቋማት መኖራቸዉ

2.10.1 በፌደራል ደረጃ

 የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ፣

13
 የኢትዮዽያ የጨርቃ ጨርቅ፣ የቆዳ፣ የብረታ ብረት፣ የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓት፣ የሥጋና ወተት፣ የምግብ መጠጥ
እና ፋርማስዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ማዕከላት፣
 የኢንዱስትሪ ግብዓቶች አቅራቢ ልማት ድርጅት፣
 የኢትዮዽያ ካይዘን ኢንስቲቲዩት፣
 ኢንዱስትሪያል ዞን ልማት ኮርፖሬሽን፣
 የቴክንክና ሙያ ማስልጠኛ ተቋማት፣
 ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣
2.10.2 በክልል ደረጃ

 የክልሉ ኢንተሪፕራይዞችና ኢንድስትሪ ልማት ቢሮ፣


 የልማት ባንክ፣
 የደቡብ ካፒታል ዕቃ ሊዝ ፋይናንስ ንግድ ስራ አክሲዮን ማህበር፣
 የቴክንክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት፣
 ኦሞ ባንክ፣
 ሌሎች የግል ባንኮች/ ብርሀን፣ እናት…
 ከ 2 ዩንቪሪሲቲዎችና 1 ካምፓስ፣

14
ክፍል ሦስት
3. በመንግስት ድጋፍ የሚደረግላቸው የማኑፋክቸሪንግ ንዑስ የሥራ ዘርፎች
3.1 ጨርቃጨርቅና አልባሳትሥራ ውጤቶች ውጤቶች
 የጨርቃጨርቅ አልባሳትን ማምረት
 የሹራብ ሥራ
 ፎጣ ማምረት
 የጥልፍ ሥራ
 የተዘጋጁ ጨርቃጨርቆችን ማምረት
 ማቅለምና ህትመት
 ምንጣፎች ማምረት
 የሽመና ውጤቶች
3.2 ቆዳና የቆዳ ሥራ ውጤቶች
 የቆዳ ውጤቶች (ቦርሳ፣ቀበቶ፣ ዋሌት፣ ጓንት፣የቆዳ ኳስ ወዘተ.)
 የጫማ ሥራ ( የወንድ፣ የሴት፣የልጆች ወዘተ…)
 የቆዳ አልባሳት(የወንድ የሴት ጃኬት፣ ኮት፣ ጉርድ፣ ሱሪ)
 የቆዳ ውጤቶች ተጓደኛ አካለትን ማምረት (Accessories )
3.3 የብረታ ብረት ሥራ ውጤቶች
 በርና መስኮት ሥራዎች ፣
 የማዋቀሪያ ብረት ውጤቶች፣ የብረት በርሜሎችን፣ ገንዳዎችን እና ኮንቴይነሮችን ወይም
የእንፋሎት ማመንጫዎችን ማምረት፣
 የብረታ ብረት ውጤቶችን የእጅ መሳሪያ፣ ቁሳቁስ እና የመሳሰሉትን ማምረት፣
 ቀላል ማሽነሪዎችን ማምረት፣
 ለግብርና አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶች ማምረት፣
 የማሽነሪ መለዋወጫዎች፣
 የብረት ፖል ማምረት፣
3.4 የእንጨት ሥራ ውጤቶች
 በርና መስኮት ሥራዎች
 የቤትና የቢሮ ዕቃዎች
 የትምህርት መርጃ ሥራዎች
 የቀርከሃ ምርት ወጤቶች
 የእንጨት መስንጠቅ እና ጣውላ ማምረት

15
3.5 የግብርና ዉጤቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ (Agro-processing industries)
 ሥጋና የሥጋ ውጤቶችን ማቀነባበር፣
 ዓሣና የዓሣ ውጤቶችን ማቀነባበር፣
 ፍራፍሬ እና አትክልት ማቀነባበር፣
 የምግብ ዘይት መጭመቂያና ማቀነባበሪያ ፣
 የእንስሳት መኖ ማቀነባበር፣
 የሻይ ምርት ማቀነባበርና ማሸግ፣
 የኦቾሎኒ ቅቤ ማምረት፣
 የወተት ተዋጽኦ ማቀነባበር፣
 ማር እና ሰም ማቀነባበር፣
 ጥራጥሬ የቅባት እህል ማቀነባበር፣
 የቅመማ ቅመም ማቀነባበር፣
 ዱቄት ማምረት፣
 ጣፋጭ ምግቦችን ማምረት (ቸኮሌት፣ ከረሜላ፣ ብስኩት…)፣
 እስታርችና የእስታርች ውጤቶችን ማምረት፣
 የወይን ጠጅ ማምረት፣
 የአልኮል መጠጥ ማምረት፣
 ለስላሳ መጠጥ፣ የማዕድን ወይም የታሸጉ ሌሎች ውሃዎችን ማምረት፣
3.6 የዕደ ጥበብ ዉጤቶችና ጌጣጌጥ ሥራ ውጤቶች
 የከበሩ ድንጋዮች ማስጌጥ ሥራ፣
 የነሐስ ጌጣጌጥ ሥራ፣
 የአሸንጉሊት ስራ፣
 የሙካሽ ሥራ፣
3.7 ኬምካልና የኬምካል ውጤቶች
 መሰረታዊ ኬሚካሎችን/ኢታኖልን ጨምሮ ማምረት፣
 የፕላስቲክ ወይም የሰው ሰራሽ ጎማ ጥሬ ዕቃዎችን ማምረት፣
 ሰው ሰራሽ ጭረቶች ማምረት፣
 የስፖንጅ ምርት ዉጤቶች፣
 የግድግዳ ቀለም፣ ቫርኒሽ ወይም መሰል መለሰኛዎችን፣የማተሚያ፣የመጻፊያ ወይም የስዕል ቀለም ወይም
ማጣበቅያ ማምረት፣
 ጸረ ተባይ ፣ ጸረ አርም ወይም ጸረ ሸጋታ ማምረት፣
 ሳሙና ዲተርጀንት፣ ማጽጃና መወልወያ፣ሽቶ፣ የውበት መጠበቂያ/Cosmotics/ ማምረት፣

16
3.8 የግንባታ ግብዓቶች
 የሴራሚክ ምርት፣
 የቴራዞ ምርት፣
 ኮንክሪት ፖል ምርት፣
 ባዞላ ምርት፣
 ጅብሰም ምርት፣
 የግንባታ ዕቃዎች ምርት፣
 ለህንጻ ግንባታ፣ ለተሸከርካሪ ወይም ለሌሎች የኢንዱስትሪ ምርቶች ግብዓት የሚሆኑ፣ ለመስኖና
ለመጠጥ ውሃ ማስተላለፊያነት እንዲሁም ለፍሳሽ መስወገጃ የሚያገለግሉ የፕላስቲክ ቧንቧዎች
ወይም መገጣጠሚያዎችን ማምረት፣
3.9 ብረት ያልሆኑ የማዕድን ውጤቶች ኢንዱስትሪ
 የሸክላና የሰሚንቶ ውጤቶችን ማምረት፣
 የወፍጮ ድንጋይ፣ የብርጭቆ ወረቀት ወይም መገደቢያ ወይም የሙቀት መከላከያ ምርቶችን ማምረት፣
 መስታወት ወይም የመስታወት ውጤቶችን ማምረት፣
3.10 የኮምፒወተር ፤የኤሌክትሮኒክስ እና የእይታ ዕቃዎች ኢንዱስትሪ
 ኮምፒዩተር እና ተጓዳኝ ዕቃችን ማምረት፣
 የዕይታ ወይም የፎቶ ማንሻ ዕቃችን ማምረት፣
 መግኔታዊ እና የዕይታ ሚዲያዎችን ማምረት/Manufacturing of Magnetic & Optical Media/፣
3.11 የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ኢንዱስትሪ
 የኢሌክትሪክ ሞተር፣ ጀነሬተር፣ ትራንሰፎርመር፣ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያና መቆጣጠርያ ማምረት፣
 የኤሌክትሪክ ሀይል ኬብሎችን፣ ሽቦዎችን፣ ገመዶችን (የፋይበር ኦፕቲክን ጨምሮ) እና ተያያዥ ዕቃችን
ማምረት፣
 ማከፋፈያ ቦርዶች፣ ብሬከሮች፣ ኮንታክተሮች፣ ሪሌዮች፣ ታይመሮችና በአጠቃላይ ከኮንተሮል ጋር ተያያዥ ዕቃዎችን
ማምረት፣
 የኤሌክትሪክ ብርሃን መስጫ ማብሪያና ማጥፊያ፣ ሶኬትና ተያያዥ ዕቃችን ማምረት፣
 የቤት ውስጥ መገልገያ የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን ማምረት፣
 ከከፍተኛ፣ መካከለኛ እና ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ጋር ግንኑነት ኖሮአቸው ከብረትና ከሴራሚክ
ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ዕቃዎች ማምረት፣
 ሌሎች የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ማምረት፣
3.12 መሰረታዊ መድኃኒት ምርት እና የመድኃኒት ዝግጅት ኢንዱስትሪ
 ለመድኃኒት ግብዓትነት የሚውሉ መሠረታዊ የመድኃኒት ውጤቶችን ማምረትና ማዘጋጀት፣
 መድኃኒት ማምረት ወይም ማዘጋጀት፣

17
ክፍል አራት
4. በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የሚደረጉ መንግስታዊ ድጋፎች
4.1 የአዋጭነት ጥናቶች
መንግስት በኢንዱስትሪ ፖሊሲ ስትራቴጂ እቅድ የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪን ዕድገት ለማፋጠን እና
በማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ የሚሰማሩ ባለሃብቶች ትርፋማ እንዲሆኑ ለፕሮጀክታቸው አሰፈላጊ የሆኑ የካፒታል፣ የጥሬ ዕቃ፣
የቴክኖሎጂ ፍላጎት፣ የሰው ሃይል እና ሌሎች ችግሮችን የሚፈታ የአዋጪነት ጥናት ባለሀብቶች በሚያዘጋጁበት ወቅት ቴክንካል
ድጋፍ ያደርጋል፡፡

4.2 የአቅም ግንባታና የቴክኖሎጂ ድጋፎች


ሀ/ የአቅም ግንባታ ድጋፍ

18
የሥራ ተነሳሽነትና ተወዳዳሪነትን ለማስፈን ጉልህ አስተዋፅኦ ያለቸውን የኢንተርፕርነርሺፕ እና የንግድ ሥራ ተወዳዳሪነት
አመለካከት፣ ክህሎትና ሥራ አመራር ስልጠና ፍላጎተ ስልጠና ላይ በመመስረትና በማዘጋጀት እንዲሰጡ ይደረጋል፡፡
በተጨማሪም የኢንዱስትሪዎች ምርት ጥራትና ምርታማነት እንዲያድግ በገበያ ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ አዳዲስ ምርቶችን
እንዲያቀርቡ እና ለውጤታማነት የሚያበቃቸው ተከታታይነትና አግባብነት ያለው የሙያ ክህሎት ስልጠና በመስጠት
በተሰማሩበት የሥራ መስኮች የሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እንዲያገኙ የሚያበቃ ድጋፍ እና የአለም አቀፍ
ደረጃን (International Organization for Standardization) መሰረት ያደረገ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓትን ተግባራዊ
ለማድረግ የሚረዱ አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎች ይሰጣሉ፡፡

ለ/ የቴክኖሎጂ ድጋፍ

ቢሮው በክልሉ ውስጥ ተቋቁመው ከሚገኙ የትምህርት፣ የሥልጠና የምርምር ተቋማት ጋር በመቀናጀት የአነስተኛ
እና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎችን ለመደገፍ የሚያስችል የተስማሚ ቴክኖሎጂ ናሙናዎችን
በመቅዳት፣ በማባዛትና በማሸጋገር የዘርፉ እንዱስትራሊስቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡

4.3 የማምረቻ ቦታ ድጋፍ

ሀ/ የማምረቻ ክላስተር ማእከላት አቅርቦት

የአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች የክላስተር ማዕከላት አቅርቦት በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለሚሰማሩ


ባለሃብቶች ለመስሪያ ቦታ ግንባታ የሚያወጡትን ወጪዎችን ለመቀነስና እንዲሁም ዓለም አቀፍ ደረጃን
የሚያሟሉ ሼዶችን በመገንባት ለማቅረብ የሚያስችል አሰራር ተዘርግቷል፡፡ በዚህ መሰረት በሁሉም ዞኖች ለሼዶቹ
ግንባታ የሚሆን በትላልቅ ከተሞች 250 ሄ/ር በመካከለኛ ከተሞች 100 ሄ/ር በወረዳ 50 ሄ/ር መሬት በማዘጋጀተ
የከተሞችን ፕላን በጠበቀ መልኩ ሁሉንም መሰረት ልማት ያሟላ እና ዘመናዊነታቸውን የተጠበቁ የማምረቻ
ሼዶች እየተገነቡ በሚዘጋጀው የመለያ መስፈርት መሰረት ባለሃብቶች እየተለዩ በተመጣጣኝ ዋጋ በኪራይ
እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡

ለ/ ነባር ክላስተር

በክልሉ በመንግስት ካፒታል በጀት ተገንብተው እና መሰረተ ልማት ተሟልቶላቸው በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ
ተሰማርተው ላሉ ኢንዱስተራያሊስቶች በአነስተኛ ኪራይ በስራ ላይ ያሉ ሼዶችና ባለአንድ ፣ባለሁለት ወለል
ህንጻዎች የበለጠ ተጠናክረው አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል፡፡

ሐ/ የምርት ማሳያና መሸጫ ማዕከላት አቅርቦት

የምርት ማሳያና መሽጫ ማዕከላትላትን በማስገንባት በአነስተኛ የኪራይ ዋጋ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ
ኢንዱስትሪ ተቋሟት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡

4.4 የገበያ ትስስር

አነስተኛ እና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎችን የገበያ መረጃና የምክር አገልግሎት በመስጠት፣ ባዛርና

19
ኤግዝብሽን በማዘጋጀት እና ምርታቸውን እንዲያስተዋውቁ በማመቻቻት፣ እንዲሁም የፌዴራል ኢምፖርየም
አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማደረግ ኢንዱስትራሊስቶቹ የውጭና የሀገር ውስጥ ገበያ ተወዳዳሪና ተጠቃሚ
እንዲሆኑ የሚያስችል ድጋፍ ይሰጣል፡፡

4.5 የኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃ አቅርቦት ድጋፍ


የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅትን በማቋቋም የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ
ኢንዱስትሪዎች የግብዓት አቅርቦት ችግር ለመፍታት ሰፊ ሥራዎች ተጀምረዋል፡፡ ድርጅቱ የኢንዱስትሪ
ግብዓትን ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር በማቅረብ የኢንዱስትሪውን የግብዓት ችግር የመቅረፍ ሥራ ይሰራል፣
ከአገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ፍጆታ በላይ የሆኑትን የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ወደ ውጭ አገር በመላክና በመሸጥ
ለሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ድጋፍ ያደርጋል፡፡

በክላስተር ውስጥ ሆነው ተመሳሳይ ምርት የሚያመርቱ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ጥሬ ዕቃ


በተመጣጣኝ ዋጋ፣ በጥራት፣ በመጠን እና በሚፈለገው ጊዜ ማግኘት እንዲችሉ ይህንን አገልግሎት
ለሚያቀርቡ የህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየኖች እና የመንግስት ልማት ድርጅቶች የብድር ስርዓት
በማመቻቸትና ከውጪ ሀገር ለሚገቡ ጥሬ ዕቃዎች በተቀናጀና የውጪ ምንዛሪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ ወደ
ሀገር ውስጥ የሚገባበት አሰራር ላይ ድጋፍ ይደረጋል፡፡

በተጨማሪም የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎችን እርስ በእርስ፣ ከከፍተኛ እንዲስትሪዎችና


አምራች አርሶና/አርብቶ አደሮች ጋር በማስተሳስር የግበዓት አቅርቦት በማመቻቸት የዘርፉ ኢንዱስትራሊስቶች
ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡

4.6 የፋይናንስ ድጋፍ


4.6.1 የስራ ማስከጃ የገንዘብ ብድር
በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ተሰማርተው ላሉ ባለሀብቶች እስከ 1,000¸000 (አንድ
ሚሊየን) ብር በክልሉ ተቋቁመው ያሉ የአነስተኛ ቁጠባና ብድር ተቋማት የስራ ማስከጃ ብድር የሚሰጡ ሲሆን
ከ 1,000¸000 (አንድ ሚሊየን) ብር በላይ ብድር የኢትዮዽያ ንግድ ባንክ የሚያመቻች ይሆናል፡፡

4.6.2 የካፒታል ዕቃዎች (Capital goods) ሊዝ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በመንግስት የኢኮኖሚ የትኩረት መስኮች ላይ የካፒታል ዕቃዎች (Capital goods)
ለፕሮጀክቶቻቸው መጠቀም ለሚችሉ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች የካፒታል ዕቃዎችን ገዝቶ
በኪራይ መልክ በማቅረብ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለተሰማሩ ኢንዱስትሪያሊስቶች የፋይናስ ሊዝ ድጋፍ
ይሰጣል፡፡

4.6.2.1 የሚሰጡ የመሳሪያ ሊዝ ዓይነቶች

20
ሀ. የዱቤ ግዢ / Hire Purchase/

የዱቤ ግዥ በካፒታል ዕቃ ኪራይ ንግድ ስራ አዋጅ ቁጥር 103/1990 በተፈቀደው መሰረት የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ
ኪራይ ዓይነት ሆኖ በአዋጁ እንደተጠቀሰው የኪራይ ስምምነቱ የሚከተሉት ልዩ ባህሪያት ይኖሩታል፡-

ሀ/ እያንዳንዱ የኪራይ ክፍያ በተፈጸመ ቁጥር ለክፍያው ተመጣጣኝ በሆነ መቶኛ ልክ የባለቤትነት መብት እንዲሁም
የመጨረሻው የኪራይ ክፍያ እንደተፈጸመ ወዲያውኑ የካፒታል ዕቃው ሙሉ የባለቤትነት መብት ለተከራዩ
የሚተላለፍለት መሆኑ፤

ለ/ ስምምነቱ በማናቸውም ወገን ያለጊዜው በሚቋረጥበት ጊዜ ከስምምነቱ የሚመነጭ የባለቤትነት መብቶችና ጥያቄዎች እልባት
የሚያገኙበትን ሁኔታ ሁለቱ ወገኖች በስምምነታቸው ሊያካትቱ የሚገባ መሆኑ፤

ሐ/ ተከራዩ ለካፒታል ዕቃው የመድህን ዋስትና የመግባትና በየዓመቱ የማደስ ኃላፊነት ያለበት መሆኑ፤

ለ. የፋይናንስ ኪራይ /Financial Lease/

የፋይናንስ ኪራይ ስምምነቱ የሚከተሉት ልዩ ባህሪያት ይኖሩታል፡-

ሀ/ ተከራዩ የኪራይ ስምምነቱ ጸንቶ በሚቆይበት ጊዜ ሁሉ የካፒታል ዕቃውን በአግባቡ እንዲጠቀምበት የውል ስምምነት
ይገባል፤ ተከራዩ በካፒታል ዕቃው ላይ ምንም አይነት የባለቤትነት መብት የለውም፣

ለ/ ስምምነቱ ውል የተገባበት ሙሉ ዋጋ በኪራይ ተከፍሎ የሚሸፈንበትና ሊሠረዝ የማይችል ሥምምነት ነው፣

ሐ/ የሥምምነቱ ጊዜ ሲያበቃ ሁለቱ ወገኖች ከተሥማሙ ተከራዩ የካፒታል ዕቃውን የመግዛት ምርጫ ይኖረዋል፤ ካልተስማሙ
ተከራዩ የካፒታል ዕቃውን ለአከራዩ ይመልሳል፤

መ/ ተከራዩ ለካፒታል ዕቃው መድህን የመግባትና ተገቢውን ዕድሳት በየወቅቱ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡

21
4.6.2..2 የልማት ባንክ የሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎቶች
 ባንኩ የሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት የሚሰጣቸው አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ሆነው
በመንግስት የኢኮኖሚ የትኩረት መስኮች ላይ የሚሰሩና የካፒታል ዕቃዎችን (Capital goods) ለፕሮጀክቶቻቸው
መጠቀም ለሚችሉት ነው፡፡
 ባንኩ ለአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ለማምረት የሚያገለግሉ የካፒታል ዕቃዎችን
(Capital goods) ገዝቶ በኪራይ መልክ ያቀርባል፡፡
 ዋጋቸው ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የማምረቻ መሳሪያዎችን ለማግኘት የማምረቻ መሳሪያውን 20 በመቶ (10 በመቶው በጥሬ ዕቃ
ሊሆን ይችላል) ኢንዱስትሪው ማዘጋጀትና በዝግ ሂሳብ (Block Account) ማሳየት ይጠበቅበታል፡፡ ማምረቻ መሳሪያው ከተገዛና ከልማት
ባንክ ጋር ርክክብ ከተፈጸመ በኋላ ያስያዙት 20 በመቶ ገንዘብ ለስራ ማስኬጂያ ይለቀቅላቸዋል፡፡

4.6.2..4 የደቡብ ካፒታል ዕቃ ሊዝ ፋይናንስ ንግድ ስራ አክሲዮን ማህበር


የማምረቻ መሳሪያ ጥያቄው ለካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አክሲዮን ማህበራት የሚቀርብ ከሆነ ለመሳሪያው መግዣ
ከሚያስፈልገው ገንዘብ 15 በመቶ የሚሆነውን ማዋጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህን ሲያደርጉ ቀሪው 85 በመቶ በአክሲዮን ማህበሩ
ተጨምሮ የሚፈልጉት ማምረቻ መሳሪያ ይገዛላቸዋል፡፡

4.6.2..5 የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን የሚያሰገኛቸው ጥቅሞች


1) ከውጪ ተገዝተው የሚቀርቡ የማምረቻ መሳሪያዎች ከቀረጥና ታክስ ነጻ መደረጋቸው፣
2) ተከራዩ የካፒታል ዕቃውን በኪራይ በማግኘቱ ያለውን ካፒታል ለስራ ማስኬጃ የሚያውለው ስለሆነ
ለካፒታል ቁጠባ ጠቀሜታ ያለው መሆኑ፣
3) የተከራዮችን የንግድ እንቅስቃሴ፣ የመክፈል አቅም ሁኔታና ፍላጎት መሰረት ያደረገ የክፍያ መጠንና የክፍያ
ጊዜ ስምምነት ማደረግ የሚያስችል መሆኑ፣
4) ተከራዩ የጥሬ ገንዘብ ፍሰቱ በዕቅድ እንዲመራ ማስቻሉ፣
5) አገልግሎቱ ያለ ምንም የዋስትና መያዣ መሰጠቱ፣
6) የብድር መክፈያ እፎይታ ጊዜ መሰጠቱ፣
7) ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ዕድገት አስተዋጾ ማድረጉ፣

4.7 በኢንቨስትመንት አዋጅ መሰረት የሚሰጡ ድጋፎች


1) የገቢ ግብር ነጻ ማበረታቻ
በኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችና ለአገር ውስጥ ባለሃብቶች የተፈቀዱ የስራ መስኮች የሚኒስትሮች ምክር
ቤት ደንብ ቁጥር 270/2005 ዓ.ም መሠረት አዲስ ድርጅት ለማቋቋም ኢንቨስት ለሚያደርጉ እንዲሁም ለነባር
ድርጅት ማስፋፊያ ስለሚሰጥ የገቢ ግብር ማበረታቻ እንደ ኢንቨስትመንት መስኩ /እንደየ ዘርፉ/ እና
እንደቦታው ርቀት ከ 1 ዓመት እስከ 6 ዓመት ባለሃብቱ ማምረት ወይም አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጊዜ
አንስቶ ከገቢ ግብር ነጻ ማበረታቻ የሚያገኙ መሆኑ እና ቢያንስ 60 በመቶ የሚሆነውን ምርቱን ወይም
አገልግሎቱን ወደ ውጪ ለሚልክ ባለሃብት በምርት ወይም በአገልግሎት ግብዓትነት የሚያቀርብ ከሆነ
ከተፈቀደለት የገቢ ግብር ነጻ ማበረታቻ በተጨማሪ ለሁለት ዓመት ከገቢ ግብር ነጻ ይሆናል፡፡

22
2) ከቀረጥ ነጻ ተሸከርካሪ
በማኑፋክችሪንግ ዘርፍ የሚሰማሩ ባለሀብቶች ለፕሮጀክቶቻቸው የሚያስፈልጉ ተሽከርካሪዎችን እንደ ፕሮጀክቱ ባህሪ
እና ርቀት ከጉምሩክ ቀረጥና ሌሎች ታክሶች በነጻ ከውጭ እንዲያስገቡ ይደረጋል፡፡

3) የካፒታልና የግንባታ ዕቃዎች ከቀረጥ ነጻ


ባለሃብቱ ከጉምሩክ ነጻ እንዲገቡ የሚፈልጋቸው እና ለፕሮጀክቶቻቸው የሚያስፈልጉ የካፒታልና የግንባታ
ዕቃዎችን (-----በመቶ) እና የካፒታል ዕቃ መለዋወጫዎችን (የካፒታል ዕቃውን ዋጋ 15 በመቶ) ከጉምሩክ ቀረጥና
ሌሎች ታክሶች በነጻ ከውጭ እንዲያስገቡ ይደረጋል፡፡

4.7 የወጪ ንግድ የቀረጥ ማበረታቻ ስርዓት አዋጅ መሰረት የሚሰጥ ድጋፍ

1) የተመላሽ ቀረጥ ስርዓት


የሥርዓቱ ተጠቃሚዎች ከዉጭ በሚያስመጧቸዉ ወይም በአገር ዉስጥ በሚገዟቸዉ ዕቃዎች ላይ የተከፈለዉ ቀረጥ ከብር 1000.00
(አንድ ሺህ) በላይ ከሆነ የተከፈለዉ ቀረጥ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
የድጋፉ ተጠቃሚዎች
 አምራች ላኪዎች
 ቀጥተኛ ያልሆኑ አምራች ላኪዎች፣
 ጥሬ ዕቃ አቅራቢዎች፣
2) የቫዉቸር ስርዓት
የሥርዓቱ ተጠቃሚዎች ጥሬ ዕቃ አቅራቢዎች በሚሰጡት ዱቤ ወይም በፍራንኮ ቫሉታ ወደ ሀገር በማስገባት ተፈላጊዉን ምርት በሀገር
ዉስጥ ከተመረተ በኋላ የሚርቱ ተቀባይ መኖሩን የሚያረጋግጥ ከገዥዉ የተላከ ትዕዛዝ ወይም ዉል ማቅረብ የሚችል ወይም ጥሬ ዕቃዉ
የወጭ ምርቶችን ለማምረት ዉጭ ሀገር ከሚገኝ ተባባሪ ኩባንያ የተላከለት የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ለሚችል ተጠቃሚ ተመላሽ የሚሆን
ታክስ ነዉ፡፡
የድጋፉ ተጠቃሚዎች
 አምራች ላኪዎች
 ቀጥተኛ ያልሆኑ አምራች ላኪዎች
 ጥሬ ዕቃ አቅራቢዎች
3) የቦንድድ ኤክስፖርት ፋብሪካ ስርዓት
የቦንድድ ኤክስፖርት ፋብሪካ ስርዓት ተጠቃሚዎች ወደ አገር ዉስጥ ያስገቡት ጥሬ ዕቃ ከቀረጥ ነጻ ሆኖ በጉምሩክ ቁጥጥር ስር ወደ
ፋብሪካ በማጓጓዝ የገባዉን ጥሬ ዕቃና ከፋብሪካዉ ለዉጭ ገበያ የሚላከዉን ምርት የኢትዮዽያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን
ይቆጣጠራል፡፡
የድጋፉ ተጠቃሚዎች
 ምርታቸዉን ሙሉ ለሙሉ ለዉጭ ገበያ የሚያቀርቡ፣
 በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የስርዓቱ ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስችል የምስክር ወረቀት የተሰጣቸዉ እና
 የኢትዮዽያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሚያወጣዉን መስፈርት የሚያሟላ የማምረቻ ፋብሪካ ያላቸዉ
ኢንዱስትሪዎች፣
4) የቦንድድ ኤክስፖርት ማምረቻ መጋዘን ስርዓት

23
የቦንድድ ኤክስፖርት ማምረቻ መጋዘን ስርዓት ተጠቃሚዎች ወደ አገር ዉስጥ ያስገቡት ግብዓት ከቀረጥ ነጻ ሆኖ በጉምሩክ ቁጥጥር ስር
ከጉምሩክ ጣቢያዎች ወደ መጋዘን በማጓጓዝ መጋዘን የገባዉን እና ከመጋዘኑ የሚወጣዉን ግብዓት የኢትዮዽያ ገቢዎችና ጉምሩክ
ባለስልጣን ይቆጣጠራል፡፡

የድጋፉ ተጠቃሚዎች
 የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የስርዓቱ ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስችል የምስክር ወረቀት የሰጣቸዉ እና
የኢትዮዽያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሚያወጣዉን መስፈርት የሚያሟላ መጋዘን ያላቸዉ
ኢንዱስትሪዎች ይሆናሉ፡፡
5) የቦንድድ ግብዓት አቅርቦት መጋዘን ስርዓት
የቦንድድ ግብዓት አቅርቦት መጋዘን ስርዓት ተጠቃሚዎች ወደ አገር ዉስጥ ያስገቡት ግብዓት ከቀረጥ ነጻ ሆኖ በጉምሩክ ቁጥጥር ስር
ወደ መጋዘን በማጓጓዝ መጋዘን የሚገባዉን እና ከመጋዘኑ የሚወጣዉን ግብዓት የኢትዮዽያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን
ይቆጣጠራል፡፡
የድጋፉ ተጠቃሚዎች ፡-
 የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የስርዓቱ ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስችል የምስክር ወረቀት የሰጣቸዉ እና
የኢትዮዽያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሚያወጣዉን መስፈርት የሚያሟላ መጋዘን ያላቸዉ
ኢንዱስትሪዎች ይሆናሉ፡፡
6) የኢንዱስትሪ ቀጠና ስርዓት
የኢንዱስትሪ ቀጠና ስርዓት ተጠቃሚዎች ወደ አገር ያስገቡትን ጥሬ ዕቃ ከጉምሩክ ቀረጥ ነጻ ሆኖ በጉምሩክ ቁጥጥር ስር ከጉምሩክ
ጣቢያዎች ወደ ኢንዱስትሪዉ ቀጠና በማጓጓዝ ኢንዱስትሪ ቀጠና የሚገባዉን ጥሬ ዕቃ እና በኢንዱስትሪ ቀጠና ተመርቶ ለዉጭ እና
ለሀገር ዉስጥ ገበያ የሚቀርበዉን ምርት የኢትዮዽያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ይቆጣጠራል፡፡
የድጋፉ ተቃሚዎች
 የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሚያወጣዉን መስፈርት የሚያሟሉ በኢንዱስትሪ ቀጠና ዉስጥ የሚቋቋሙ
ኢንዱስትሪዎች ይሆናሉ፡፡
4.9 የጉምሩክ ታሪፍ ደንበኛ 2 ኛ ሀ እና አጠቃቀም አዋጅ መሰረት የሚሰጥ ድጋፍ
የጉምሩክ ታሪፍ በገቢ ዕቃዎች ወይንም ባንዳንድ የወጭ ዕቃዎች ላይ የሚጣል ሲሆን በሚገቡበት ወይም በሚወጡበት በር
ላይ በዕቃዎቹ ክብደት፣ ብዛት፣ ይዘትና ዋጋ ላይ የሚከፈል የቀረጥ ዓይነት ሲሆን ዓላማዉም ፡-
የሀገር ዉስጥ ታዳጊ ኢንዱስትሪዎችን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ፣ ገበያ እንዲያገኙ ለማድረግና የዉጭ ምንዛሪ ለማዳን፣ የገቢ
ምርቶችን ለመተካት ለማበረታታትና ስትራቴጂያዊ የሆኑ አምራቾችን መደገፍ እና ለመንግስት ገቢ ማመንጨት ናቸዉ፡፡
4.10 በኤክስፖርት የስራ ላይ የሚሰማሩና የተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች የመንግስት ወጪ መጋራት ስርዓት
በኤክስፖርት ተኮር የተሰማሩ ወይንም የሚሰማሩ ባለሀብቶች ያለባቸዉን የሙያ፣ የስራ አመራርና ክህሎት ችግር ለማሻሻል
የዉጭ ባለሙያ ቀጥረዉ በሚያሰሩበት ጊዜ ከሚከፍሉት ክፍያ የስራ ግብር ነጻ በማድረግ መንግስት ወጪ የሚጋራበት
ስርዓት ነዉ፡፡
የድጋፉ ተጠቃሚዎች
 ኤክስፖርት ዘርፍ አምራች ኢንዱስትሪ ሆነዉ ምርቶቻቸዉን ወደ ዉጭ በመላክ የዉጭ ምንዛሪ
የሚያፈሩ አምራቾች፣

24
 በኤክስፖርት ዘርፍ ለተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች እንደ ማሸጊያ፣ ቁልፍ፣ ሌቤሊንግ የመሳሰሉትን
ለሚያቀርቡ፣

ክፍል አምስት
5. በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ትኩረት የሚሰጣቸዉ ህብረተሰብ ክፍሎች እና ቅድሚያ የሚሰጣቸዉ
ባለሀብቶች

5.1 በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ትኩረት የሚሰጣቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎች

1) ሀብት ያፈሩ አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች በተናጥል/ በህበረት ስራ ማህበራት

በአሁኑ ወቅት የግብርና የህብረት ሥራ ማህበራት ሃብት ያፈሩ ሞዴል አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች
ያፈሩትን ሃብት በቀጣይ እሴት በሚጨምሩ የአግሮ ኢንዱስትሪዎች ላይ በተናጥል እና በጋራ በመሆን መዋዕለ
ነዋያቸውን በማፍሰስ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ የሚደረገውን ሽግግር ሊያፋጥኑ ስለሚችሉ ትኩረት
የሚሰጣቸው ይሆናሉ፡፡

2) የኢንተርፕርነርሽፕ ፍላጎትና ክህሎት ያላቸዉ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን

በቴክኒክና ሙያ እና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች እየተመረቁ ናቸው፡፡ እነዚህም
ሃይሎች እውቀትና ክህሎት ያላቸው ሲሆን የተለየ የፋይንናስ እና የማሽነሪ ብድር አቅርቦት የሚያረጋገጥ
ስርዓት ከተዘረጋላቸው የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪውን በቀላሉ ሊያንቀሳቅሱ ይችላሉ፡፡

3) ከጥቃቅን ማኑፋክቸሪንግ ወደ አነስተኛ ማኑፋክቸሪንግ የሚሸጋገሩ ኢንዱስትሪዎች

ከጥቃቅን ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ወደ አነሰተኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የሚሸጋገሩ ኢንዱስትሪዎች


በተቀመጠው የሽግግር አሰራር መሰረት በመቀበል በኢንዱስትሪው ልማት ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡

4) በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ባለሃብቶች/ አንቀሳቃሾች

25
በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ባለሃብቶች/ አንቀሳቃሾች ወደ ኮንስትራክሽን ግብዓቶች አምራች
ኢንዱስትሪዎች (የግንባታ ዕቃዎችን ማምረት፣ የሴራሚክ፣ ቴራዞ ማምረት፣ ለህንጻ ግንባታ የኢንዱስትሪ
ምርቶች ግብዓት የሚሆኑ ቁሳቁሶችን) ዘርፍ ኢንቨስት እንዲያድረጉ ይበረታታሉ፡፡

5) በንግድና አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ባለሃብቶች/ ድርጅቶች

እንደ ቡና፣ ሰሊጥ፣ የቁም እንስሳት እና ሌሎች የግብርና ውጤቶች በቀጣይ እሴት በመጨመር ኤክስፖርት በማድረግ
የአገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ግኝት ማሳደግ አስፈላጊ በመሆኑ በእነዚህ ጥሬ ዕቃ ኤክስፖርተርነት የተሰማሩ
ባለሃብቶች/ ድርጅቶች ለስራው ቅርበት ስላላቸው በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ እንዲሰማሩ የበለጠ አስቻይ
ሁኔታ በመፍጠር ኢንዱስትሪውን እንዲቀላቀሉ ይበረታታሉ፡፡

6) በማዕድን ዘርፍ የተሰማሩ ባለሃብቶች

ባህላዊ የማዕድን ሥራዎችና የከበሩ ድንጋዮችን በማምረት ሥራ ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶች (ዕብነበረድ ማምረት፣
የወርቅና የከበሩ ማዕድናት ማምረት፣ አሸዋ ማምረት እና የመሳሰሉት) ወደ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ እንዲገቡ
በመንግስት በኩል አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል፡፡

7) በውጭ አገር ያሉ ዲያስፖራዎች

የተለያዩ አገሮች ተሞክሮ እንደሚያሳየው የዲያስፖራ ኮሙዩኒቲ አባላት የአገሮች የውጭ ምንዛሪ አንድ ምንጭ ሲሆኑ
ከዚያም ባለፈ ወደ አገር ውስጥ ይዘውት የሚመጡት እውቀትና ኢንቨስትመንት ቀላል አይደለም፡፡ በመሆኑም በውጭ
ለሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪን እምቅ አቅም በማስተዋወቅ እና ምልመላ በማድረግ
በዘርፉ እንዲሰማሩ ይበረታታሉ፡፡

8) ሌሎች የትኩረት የሥራ መስኮችን በተመለከተ


በኤክስፖርት ምርት ላይ በቀጥታ ለሚሰማሩ፣ የገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ለሚሰማሩና
በቴክኖሎጂ ፈጠራና ማምረት ስራ ላይ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች ትኩረት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

26
ክፍል ስድስት
6. በመንግስት የሚሰጡ ድጋፎችን እና ምቹ ሁኔታዎችን የምናስተዋውቅበት የፕሮሞሽን
ስልቶች
6.1 ማስታወቂያ (Advertsing)

1) የቴሌቪዥን ማስታወቂያዎች
በዚህ የፕሮሞሽን ስልት ለዘርፉ የተቀመጡ የመንግስት ድጋፎችን ግልጽና ሳቢ በሆኑ የቴሌቪዥን ማስታወቂያዎች እና የተለያዩ
ዘዴዎችን በመጠቀም ማስተዋወቅ ተገቢ ነው፡፡ ስለሆነም የቴሌቪዥን ማስታወቂያዎች ለመስራት በመሳሪያ እና በባለሙያ በኩል
ምርጥ የሆኑትን ድርጅቶችን በመጠቀምና ለስራው ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ዘርፉ እንዲጠናከር የፕሮሞሽን ስራ መስራት ይገባል፡፡

የቴሌቪዥን ማስታወቂያዎች ሊሰሩባቸው የሚችሉባቸው መንገዶች፡-

 ድራማቲክ
መንግስት ለዘርፉ የሚሰጠውን ድጋፍ ለማስተዋወቅ በጭውውት ወይም በድርጊት መልክ የሚሰራ የማስታወቂያ ስራ ሲሆን የፅሁፍ እና
የትወናው ጥራትና ብቃት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በዚህ የፕሮሞሽን ስልት ዘርፉን ማስተዋወቅ ይገባል፡፡

 ኤንዶርስመንት ወይም ታዋቂ ሰዎችን መጠቀም


ይህ አሁን በሀገራችን እየተለመደ የመጣ እና በተለይ በፕሮሞሽን ስራ ላይ ከፍተኛ ውጤት አምጪ የሆነ ዘዴ ነው፡፡ በመሆኑም ታዋቂ
ስፖርተኞች፣ ፖለቲከኞችን፣ ስነጥበብ ባለሞያዎችንና ስኬታማ ሰዎችን በመጠቀም በዘርፉ ያሉትን ድጋፎችና ምቹ ሁኔታ
ማስተዋወቅ ያስፈልጋል፡፡

 መረጃ አስተላላፊ ማስታወቂያዎች


ለፕሮሞሽን ስራው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖራቸው ዘንድ ጥራት ያለው ጽሁፍና (ስክሪኘት) እንዲሁም ቅንብር (አርትኦት) ያላቸውን
ማስታወቂያዎች በመጠቀም በዘርፉ ያሉትን ምቹ ሁኔታና ድጋፎች ማስተዋወቅ ይገባል፡፡

2) የሬዲዮ ማስታወቂያዎች
የቴሌቪዥን ማስታወቂያዎች በምስል የሚደገፍ በመሆኑ ለቴሌቪዥን የተዘጋጁ ማስታወቂያዎች ትንሽ በመቀየር ወደ ሬድዮ
ማስታወቂያነት በመቀየር ወይም አዲስ በማዘጋጀት ማስተዋወቅ የሚገባ ሲሆን እዚህ ጋር ግን ሊተኮርበት የሚገባው አንድ ነጥብ ሬድዮ
ከቲቪ የሚለይበት ማለትም ምስልን ማካተት አለመቻሉ ሲሆን በድምፅ ብቻ በመጠቀም የሰሚው አዕምሮ ባልተገደበ ሁኔታ የራሱን
ስዕል እንዲስል የሚፈቅድ በመሆኑ እና ብዛት ያላቸው ተከታዮች ስለሚኖሩት ጥሩ ስክሪፕት በመጠቀም ለፕሮሞሽን የአየር ሰዓት
በመያዝ /በመግዛት/ ለዘርፉ የተቀመጡ ድጋፎችንና ማበረታቻዎችን ማስተዋወቅ ይገባል፡፡

27
3) ግራፊክስ ዲዛይን እና የህትመት ማስታወቂያዎች
ለህትመት ማስታወቂያዎች ስኬታማነት የሚያስፈልጉትን ምርጥ የሆኑ ፎቶግራፎች፣ ግልፅ እና አጭር የሆነ የጽሁፍ መልዕክት
በመጠቀም በዘርፉ ያሉትን ምቹ ሁኔታዎች የህትመት ውጤት የሆኑትን (ብሮሸር፣ በራሪ ወረቀት፣ ቢል ቦርድ እና ጋይድ ቡክ)
በመጠቀም ማስተዋወቅ ይገባል፡፡

4) ድረገፅ (Website)
በዘርፉ የተቀመጡትን ድጋፎችንና ምቹ ሁኔታዎችን በተለይም ለዲያስፖራ ባለሀብቶች ለማስተዋወቅ አስተዋጽኦ የሚኖረው ሲሆን
የተለያዩ ምስሎችን፣ ፎቶግራፎችንና ጽሁፎችን በመጠቀም በድረገጽ ማስተዋወቅ ይገባል፡፡

5) የስጦታ ዕቃዎች
የተለያዩ ምስሎች የተቀረፁባቸው ቲሸርቶች፣ ቁልፍ መያዥዎች፣ ሠዓቶች፣ ዣንጥላዎች፣ እስክሪኘቶዎች፣ ዋንጫዎች፣ አጀንዳዎች፣
ካሌንደሮች እና ወዘተ በመጠቀም እና በማሰራጨት ዘርፉን ማስተዋወቅ ይገባል፡፡

6) /ዘጋቢ/ ዶክመንተሪ ፊልም


በዘርፉ ያሉ ምቹ ሁኔታዎችን ማለትም የኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ፣ የክላስተር ማዕከላት ግንባታ፣ የጥሬ ዕቃ አቅርቦት፣ በዘርፉ
ተሰማርተው ውጤት ያመጡ ኢንዳስትሪዎችን፣ የክልሉ የተፈጥሮ ሀብት፣ መሰረት ልማት ግንባታና አገልግሎት ያካተተ በጥናት እና
መረጃ ላይ የተመሰረተ ዶክመንተሪ/ ዘጋቢ ፊልም በመስራት ማስተዋወቅ ይገባል፡፡ እነዚህ የተሰሩ ዘጋቢ ፊልሞች በተመረጡ
የቴሌቪዥን ቻናሎች እንዲሁም በ CD እና DVD እንዲሰራና እንዲተላለፍ መደረግ አለበት፡፡

6.2. የሁነት ስልቶች (Events)

እንደሚታወቀው ሁነቶች ወይም ኢቨንቶች ለተመረጡ ቡድኖች አስፈላጊ የሆነውን መረጃ ለማስተላለፍ ወሣኝ የፕሮሞሽን መንገድ
ሲሆን የተለያዩ አዝናኝ፣ ቀስቃሽ፣ አበረታች፣ አስተማሪ ሁነቶች በማዘጋጀት መልዕክት ማስተላለፍ ያስፈልጋል፡፡ ከነዚህ መካከል
በዋናነት ከታች በዝርዝር የተቀመጡትን የሁነት ስልቶች መጠቀም ይገባል፡፡

1) ፎረሞችን ማጠናከር
እስካሁን እየተሠሩ ያሉ በተለይ ባለሀብቱን እና መንግስትን አብረው የሚያገናኙ መድረኮች የበለጠ በማጠናከር ማከናወን ሌላው ወሣኝ
የፕሮሞሽን ስልት ሲሆን በዚሁ መስክ ተጨማሪ ሚና ሊጫወቱ የሚችሉ ባለሀብቶችን በማሣተፍና የአጠቃላይ ተሣታፊዎችን ቁጥር
በማሣደግ ዘርፉን ማስተዋወቅ ያስፈልጋል፡፡

2) ጥያቄና መልስ ውድድር


በአነስተኛ መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ያለውን ዝቅተኛ አመለካከት የሚቀይርና በዘርፉ ያለውን ምቹ ሁኔታ የሚያሳውቅ
ጥያቄና መልስ ውድድር ከላይ በዝርዝር በቀረቡ የማስታወቂያ ስልቶች በመጠቀም ከፍተኛ ግንዛቤ በመፍጠር በማዝናናት
በተመሳሳይ ጊዜም በማስተማር ማስተዋወቅ ይገባል፡፡

3) የጎዳና ላይ ትርኢት

28
የጎዳና ላይ ትርኢቶች አንድ ሀሳብን ለአንድ ከተማ ወይም አካባቢ ነዋሪዎች ፊት ለፊት ለማስተዋወቅ የሚያስችል ዘዴ ነው፡፡ ይህ የጎዳና
ላይ ትርኢት የፕሮሞሽን ስራ ወደ ገጠራማ አካባቢዎች ለሚደረገው የማስተዋወቅ ስራ ውጤታማነቱ የተረጋገጠ ነው፡፡ ስለሆነም
የተለያዩ መልዕክቶች እና ትርኢቶችን የአስተሳሰብና የስሜት ለውጥ ለማነሣሣት፣ ሠዎችን ለድርጊት ለማነሣሣት፣ ከህዝቡ ጋር የቀረበ
ግንኙነት ለመፍጠር (ፊት ለፊት ከህዝቡ ጋር በመነጋገር ሀሳብ ለመለዋወጥ) ይህንን የፕሮሞሽን ስልት በመጠቀም ማስተዋወቅ
ያስፈልጋል፡፡

4) ስፖንሰር ማድረግ
የተለያዩ በመደበኛነት እና በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፉ ፕሮግራሞችን ስፖንሰር በማድረግ ዘርፉን ማስተዋወቅ ያስፈልጋል፡፡

6.3. የህዝብ ግንኙነት ስልት


የህዝብ ግንኙነት ሥራ በተለይ የሚያተኩረው ሚዲያውን ሞቢላይዝ በማድረግ ስለ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ
ድጋፍና ማበረታቻ በቂ የሆነ የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኝ የአየር ሰአት በመግዛት፣ ፕሮግራም በማሰራትና ለዜና የሚሆኑ መረጀዎችን
በማዘጋጀት ቴሌቭዥን ጣቢያዎች፣ ሬዲዮች፣ ጋዜጦችና ሚዲያዎች እንዲደርሣቸው በማድረግ ማስተዋወቅ ይገባል፡፡ ይገባል፡፡

7. አባሪዎች
 የኢቨስትመንት ማበረታቻዎችና ለአገር ውስጥ ባለሃብቶች የተከለሉ የሥራ መስኮች የሚኒስትሮች ምክር
ቤት ደንብ 270/2005 መሰረት የኢንቨስትመንት መስኮች እና የገቢ ግብር ማበረታቻዎች፣
 ለማምረቻ ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንቶች ተሽከርካሪዎችን ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ እንዲገቡ የሚፈቀድላቸው
መመሪያ ቁጥር 4/2005 መሰረት የኢንቨስትመንት መስኮችና የተሽከርካሪዎች ዓይነትና ብዛት፣

ዋቢዎች
 የፌደራል አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የፕሮሞሽን ማኑዋል 2010 ዓ.ም
 ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ የኢንቨስመንት ማበረታቻዎችና ለሀገር ውስጥ የተከለሉ የሥራ መስኮች የሚኒስትሮች ምክር ቤት
ደንብ ቁጥር 270/2005
 ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ የፌደራል አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ልማት ኤጀንሲ ለማቋቋም የወጣ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 373/2008 ዓ.ም
 በኢትዮጲያ ኢንቨስትመንት ቦርድ የወጣ መመሪያ ቁጥር 02-01/2008 ዓ.ም

29
 የኢትዮጲያ ልማት ባንክ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ዕቃዎች ኪራይ /የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት መመሪያ
ጥቅምት/2016 እ.ኤ.አ
 በኢትዮጰያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ የከተማ ልማት ፖሊስ ግንቦት/2005 ዓ.ም
 በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተረፕራይዞች ልማት ስትራቴጂ ሚያዝያ/2005
 ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የወረዳ ኢንዱስትሪያላይዜሺን ለማስተባበር የተዘጋጀ ሰነድ (ረቂቅ) ጥቅምት 2009
 በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የፌደራል አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪ ልማት ኤጀንሲ የአምስት አመት /2008-2012)
የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ
 የኢትዮጲያ የማዕከላዊ እስተስቲካል ኤጀንሲ ድረ ገጽ ( Central Statistical Agency of Ethiopia web site)
WWW.CSA .gov.et/index.php/
 የኢትዮጲያ ፌደራላዊ ዲሞክራሳዊ የኢንዱስትሪ ልማት እስትራቴጂ
 የካፒታል ዕቃ ኪራይ ንግድ ሥራ አዋጅ ቁጥር 807/2005
 በአዲስ የካፒታል ዕቃ የፋይናንስ ንግድ ሥራ አ.ማ የተዘጋጀ ብሮሸር
 Intergrated Agro-Industral Parks(IAIPs) In Ethiopia brochure
 https://en.wikipedia.org/wiki/Industrial_park
 የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ቁጠባና የቁጠባ ሂሳብ አገልግሎት ብሮሸር
 www.Industrial Parks Development Corporation
 የኢትዮጲያ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዌብ ሳይት /Ministry of Science and Technology web site /
 የኢትጲያ ንግድ ሚኒስቴር ዌብ ሳይት /Ministry of Trade web site /
 በኢትዮዽያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የወጪ ንግድ የቀረጥ
ማበረታጫ ስርዓት አዋጅ ቁጥር 768/2004

30
31
በኢንቨስትመንት ደንብ ቁጥር 796/2005 መሰረት የኢንቨስትመንት መስኮች እና የገቢ ግብር ማበረታቻዎች የማምረቻ ዘርፍ ቢቻ የተወሰደ

በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ


የኢንቨስትመንት መስክ በሌሎች አካባቢዎች
ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን
1. የማምረቻ ኢንዱስትሪ
1.1. የምግብ ኢንዱስትሪ
1.2. ሥጋና የሥጋ ውጤቶችን ማቀነባበር
1.3. ዓሣና የዓሣ ውጤቶችን ማቀነባበር
1.4. ፍራፍሬ እና/ወይም አትክልት ማቀነባበር ለ 3 ዓመት ከገቢ ለ 5 ዓመት ከገቢ
1.5. የምግብ ዘይት ማምረት ግብር ነፃ የመሆን ግብር ነፃ የመሆን
1.6. ወተት ማቀነባበር እና/ወይም የወተት ውጤቶችን ማምረት
1.7. ስታርች እና የስታርች ውጤቶችን ማምረት
1.8. ዱቄት ማምረትን ሳይጨምር ጥራጥሬ፣ የቅባት እህል ወይም ሌላ
ማቀነባበር
1.9. ሌሎች ምግቦችን ማምረት
ለ 6 ዓመት ከገቢ
ግብር ነፃ የመሆን

ለ 5 ዓመት ከገቢ
1.10. ስኳር ማምረት
ግብር ነፃ የመሆን

0
በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ
የኢንቨስትመንት መስክ በሌሎች አካባቢዎች
ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን

1.10.1. ቸኮሌት፣ ከረሜላ፣ ብስኩት ወይም ሌሎች ጣፋጭ


ምግቦችን (አይስክሬም እና ኬክን ስራሽ ማር፣አዮዲን ለ 2 ዓመት ከገቢ
የተጨመረበት ጨው ወይም መሰል ምግቦችን ማምረት ለ 1 ዓመት ከገቢ ግብር ነፃ የመሆን
1.10.2. የእንሰሳት መኖ ማቀነባበር ግብር ነፃ የመሆን

1.11. የመጠጥ ኢንዱስትሪ


1.11.1. የአልኮል መጠጥ ማምረት ለ 1 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 2 ዓመት ከገቢ ግብር ነፃ የመሆን
ነፃ የመሆን
1.11.2. የወይን ጠጅ ማምረት ለ 3 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 4 ዓመት ከገቢ ግብር
ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን
1.11.3. ቢራ እና/ወይም የቢራ ብቅል ማምረት ለ 2 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 3 ዓመት ከገቢ ግብር ነፃ የመሆን
ነፃ የመሆን
1.11.4. ለስላሳ መጠጥ፣ የማዕድን ወይም የታሸጉ ሌሎች ለ 1 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 2 ዓመት ከገቢ ግብር ነፃ
ውኃዎችን ማምረት ነፃ የመሆን የመሆን

1.12. የጨርቃጨርቅና የስፌት ውጤቶች ኢንዱስትሪ

በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ


የኢንቨስትመንት መስክ በሌሎች አካባቢዎች
ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን

1
1.12.1. የጥጥ፣የሱፍ፣ የሐር እና የመሳሰሉ የጨርቃጨርቅ ጭረቶችን ለ 4 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 5 ዓመት ከገቢ ግብር ነፃ የመሆን
ማዘጋጀትና መፍተል ነፃ የመሆን

ለ 5 ዓመት ከገቢ ግብር 6 ዓመት ከገቢ ግብር


1.12.2. ጨርቃ ጨርቅ መሸመን፣ ማጠናቀቅና ማተም ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን

1.12.3. ጣቃ ጨርቅ፣ ክር፣ ድርና ማግ፣ አልባሳትና ሌሎች


የጨርቃጨርቅ ውጤቶችን በማንጣት፣ በማቅለም፣ ለ 3 ዓመት ከገቢ ግብር
ለ 4 ዓመት ከገቢ ግብር ነፃ የመሆን
በማኮማተር፣ በማፍካት፣ በማጠንከር፣ ወርድንና ቁመትን ነፃ የመሆን
በመጠበቅ ወይም በማስዋብ ማጠናቀቅ

1.12.4. ሌሎች የጨርቃጨርቅ ማጠናቀቅ ሥራዎች ለ 2 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 3 ዓመት ከገቢ ግብር
ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን
1.12.5. ሹራብ ወይም ፎጣ ማምረት
1.12.6. ከአልባሳት በስተቀር የተዘጋጁ ጨርቃ ጨርቆችን 4 ዓመት ከገቢ ግብር 5 ዓመት ከገቢ ግብር
ማምረት ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን
1.12.7. ምንጣፍ ማምረት
1.12.8. የጨርቃ ጨርቅ አልባሳትን (የስፓርት አልባሳትን ጨምሮ) ማምረት
1.12.9. የጨርቃ ጨርቅ ውጤቶችን ተጓዳኝ አካላትን አክሰስሪስ ማምረት ለ 5 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 6 ዓመት ከገቢ ግብር
ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን

1.13. የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪ


1.13.1. ባለቀለት ደረጃ ቆዳና ሌጦ ማልፋት ለ 5 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 6 ዓመት ከገቢ ግብር
ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን
የገቢ ግብር ማበረታቻ የገቢ ግብር ማበረታቻ
1.13.2. ካለቀለት ደረጃ በታች ቆዳና ሌጦ ማልፋት አያገኝም አያገኝም

በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ


በሌሎች አካባቢዎች
የኢንቨስትመንት መስክ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን

2
1.13.3. የቆዳ ውጤቶችን ሻንጣ፣ ቦርሳ፣ የቆዳ ኳስ እና
የመሳሰሉትን) ማምረት
1.13.4. የቆዳ ጫማ ማምረት ለ 5 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 6 ዓመት ከገቢ ግብር
1.13.5. የቆዳ ውጤቶች ተጓዳኝ አካላትን (አክሰስሪስ) ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን
ማምረት

1.14. የእንጨት ውጤቶች ኢንዱስትሪ

የእንጨት ውጤቶችን እንጨት መሰንጠቅን፣ ጣውላ ማምረትን እና


ቀድመው የተዘጋጁ የእንጨት ውጤቶችን መገጣጠምን ሳይጨምር
ለ 2 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 3 ዓመት ከገቢ ግብር
ማምረት
ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን

1.15. የወረቀት እና የወረቀት ውጤቶች ኢንዱስትሪ


1.15.1. ሌሎች የወረቀት ውጤቶችን ማምረት ለ 1 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 2 ዓመት ከገቢ ግብር
ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን
የገቢ ግብር ማበረታቻ የገቢ ግብር ማበረታቻ
1.16. የማተሚያ ኢንዱስትሪ
አያገኝም አያገኝም
1.16.1. የኬሚካልና የኬሚካል ውጤቶች ኢንዱስትሪ
1.16.2. መሠረታዊ ኬሚካሎችን (ኢታኖልን ጨምሮ) ማምረት
1.16.3. ማዳበሪያ እና/ወይም የናይትሮጅን ውህዶችን ማምረት
ለ 5 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 6 ዓመት ከገቢ ግብር
ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን

በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ


የኢንቨስትመንት መስክ በሌሎች አካባቢዎች
ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን
1.16.4. የኘላስቲክ እና/ወይም የሰው ሠራሽ ጎማ ጥሬ ዕቃዎችን
ለ 3 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 5 ዓመት ከገቢ ግብር
ማምረት
ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን
1.16.5. ፀረ-ተባይ፣ ፀረ-አረም ወይም ፀረ-ሻጋታ ማምረት

3
1.16.6. የግድግዳ ቀለም፣ ቫርኒሽ ወይም መሰል መለስተኛዎችን፣
የማተሚያ፣ የመጻፊያ ወይም የሥዕል ቀለም ወይም ማጣበቂያ
ማምረት ለ 2 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 4 ዓመት ከገቢ ግብር
1.16.7. ሳሙናና ዲተርጀንት፣ ማፅጃና መወልወያ፣ ሽቶ እና መሰል ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን
መዋቢያዎችን ማምረት

1.16.8. ሰው ሰራሽ ጭረቶችን ማምረት ለ 5 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 6 ዓመት ከገቢ ግብር
ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን
1.16.9. ሌሎች የኬሚካል ውጤቶችን ባሩድ ፈንጂ፣ የፎቶግራፍ ፊልም ለ 2 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 3 መት ከገቢ ግብር
እና የመሳሰሉትን) ማምረት ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን
1.16.10. የመሠረታዊ መድኃኒት ምርት እና የመድኃኒት ዝግጅት
ኢንዱስትሪ
1.16.11. የጎማና ውጤቶችን ማምረት ለ 3 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 5 ዓመት ከገቢ ግብር
ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን
1.17. ለሕንጻ ግንባታ፣ ለተሽከርካሪ ወይም ለሌሎች የኢንዱስትሪ ምርቶች
ግብዓት የሚሆኑ፣ ለመስኖና ለመጠጥ ውሃ ማስተላለፊያነት
እንዲሁም ለፍሳሽ ማስወገጃ የሚያገለግሉ የኘላስቴክ ቧንቧንዎችን
ወይም ቱቦዎችን እና መገጣጠሚያዎችን ማምረት
ለ 4 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 5 ዓመት ከገቢ ግብር
ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን

በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ


የኢንቨስትመንት መስክ በሌሎች አካባቢዎች
ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን
1.17.1. ፌስታልን ሳይጨምር ሌሎች የፕላስቲክ ውጤቶችን ማምረት ለ 1 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 2 ዓመት ከገቢ ግብር
ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን
1.17.2. ብረት ያልሆኑ የማዕድን ውጤቶች ኢንዱስትሪ

1.17.3. መስተዋት እና/ወይም የመስታወት ውጤቶችን ማምረት ለ 4 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 5 ዓመት ከገቢ ግብር
1.17.4.የሴራሚክ ውጤቶችን ማምረት ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን

4
1.17.5. ሲሚንቶ ማምረት ለ 4 ዓመት ከገቢ ግብር
የገቢ ግብር ማበረታቻ አያገኝም
ነፃ መሆን
1.17.6. የሸክላና የሲሚንቶ ውጤቶችን ማምረት
የገቢ ግብር ማበረታቻ አያገኝም የገቢ ግብር ማበረታቻ አያገኝም
1.17.7.ዕብነ በረድ እና የኖራ ድንጋይ መቁረጥ፣ ቅርፅ ማውጣት እና
ለ 1 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 2 ዓመት ከገቢ ግብር
ማጠናቀቅ ከካባድ የወፍጮ ድንጋይ፣ የብርጭቆ ወረቀት ወይም
ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን
የሙቀት መከላከያ ምርቶችን ማምረት
1.17.8. የመሠረታዊ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪ (ማዕድኑን ማውጣትን
ሳይጨምር)
1.17.9. መሠረታዊ ብረታ ብርትና የአረብ ብረት ማምረት ለ 5 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 6 ዓመት ከገቢ ግብር
ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን
1.17.10. ከብረት እና ከአረብ ብረት ፈሳሽ የተለያዩ ቅርፆችን ማውጣት
ለ 4 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 5 ዓመት ከገቢ ግብር
ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን

1.17.11.የማምረቻ ማሳሪያዎችንና ዕቃዎችን ማምረትን የማይጨምር


የብረታ ብርት ዕቃዎች ኢንዱስትሪ

በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ


የኢንቨስትመንት መስክ በሌሎች አካባቢዎች
ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን

1.17.12. የማዋቀሪያ ብረት ውጤቶችን፣ የብረት በርሜሎችን፣ ገንዳዎችን ለ 3 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 4 ዓመት ከገቢ ግብር
እና ኮንቴይሮችን ወይም የእንፋሎት ማመንጫዎችን ማምረት ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን

1.17.13. የቤት ክዳን ቆርቆሮንና ምስማርን ሳይጨመር ሌሎች የብረታ ለ 1 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 2 ዓመት ከገቢ ግብር
ብረት ውጤቶችን ይእጅ መሳሪያ፣ ቁሳቁስ እና የመሳሰሉትን) ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን
ማምረት

5
1.18.የኮምፒውተር፣ የኤሌክትሮኒክስ እና የዕይታ ዕቃዎች ኢንዱስትሪ

1.18.1. የኤሌክትሮኒክስ አካሎችንና ሰሌዳዎችን ማምረት ለ 4 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 5 ዓመት ከገቢ ግብር
ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን

1.18.2.ኮምፒውተር እና ተጓዳኝ ዕቃዎችን ማምረት

1.18.3.የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ኢንዱስትሪ


1.18.4. የኤሌክትሪክ ሞተር፣ ጀነሬተር፣ ትራንፎርመር ወይም ለ 4 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 5 ዓመት ከገቢ ግብር
የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ወይም መቆጣጠሪያ ዕቃዎችን ማምረት ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን

በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ


የኢንቨስትመንት መስክ በሌሎች አካባቢዎች
ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን
1.18.5. የኤሌክትሪክ ኃይል ማከማቻ ወይም ባትሪ ማምረት
1.18.6. የኤሌክትሪክ ኃይል ሽቦዎችን ወይም ገመዶችን (የፋይበር
ኦፕቲክስን ጨምሮ) እና ተያያዥ ዕቃዎችን ማምረት ለ 2 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 4 ዓመት ከገቢ ግብር
1.18.7.የኤሌክትሪክ ብርሃን መስጫ ዕቃዎችን ማምረት ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን
1.18.8.የቤት ውስጥ መገልገያ የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን ማምረት
1.18.9.ሌሎች የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን ማምረት
1.18.10. ሁለገብ መሳሪያዎችን ሞተር፣ ዕቃ ማንሻ፣ ፓምፕ እና
የመሳሰሉትን ማምረት)
1.18.11.ለተለያዩ ዓላማዎች ለግብርና ሥራ፣ ለምግብ ማቀነባበሪያ፣
ለመጠጥ፣ ለጨርቃ ጨርቅና ማዕድን ለማምረት የሚሆኑና ለ 5 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 6 ዓመት ከገቢ ግብር
ለመሳሰሉት ሥራዎች የሚውሉ መሳሪያዎችን ማምረት ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን
1.18.12. መኪና ማምረት ለ 2 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 3 ዓመት ከገቢ ግብር
ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን
1.18.13. የመኪና አካላትን፣ ተጎታችን እና/ወይም ከፊል ተጎታችን ለ 3 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 4 ዓመት ከገቢ ግብር
ማምረት ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን

6
1.18.14. የመኪና መለዋወጫዎችን እና ተጓዳኝ አካላትን ማምረት
1.18.15. የባቡር ሞተሮችን እና ጋሪዎችን ማምረት ለ 5 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 6 ዓመት ከገቢ ግብር
ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን
1.18.16. ሌሎች የትራንስፓርት ዕቃዎችን ጀልባ፣ ብስክሌት፣ ሞተር ለ 2 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 3 ዓመት ከገቢ ግብር
ብስክሌት እና የመሳሰሉትን ማምረት ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን

በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ


የኢንቨስትመንት መስክ በሌሎች አካባቢዎች
ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን

1.18.17. የቢሮና የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎችን (ከሴራሚክ የሚሠሩትን


ሳይጨምር) ማምረት
ለ 1 ዓመት ከገቢ ግብር ለ 2 ዓመት ከገቢ ግብር
1.18.18. ሌሎች ዕቃዎችን (የጌጣጌጥና ተዛማጅ ዕቃዎች፣ የሙዚቃ
ነፃ የመሆን ነፃ የመሆን
ማሳሪያዎች፣ የስፓርት ዕቃዎች፣ መጫወቻዎችና አሻንጉሊቶች
እና የመሳሰሉትን) ማምረት
ለ 5 ዓመት ከገቢ ግብር
ለ 4 ዓመት ከገቢ ግብር ነፃ የመሆን
1.18.19. ከግብርና ጋር የተቀናጀ የማምረቻ ኢንዱስትሪ ነፃ የመሆን

7
ለማምረቻ ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንቶች ተሽከርካሪ ከጉምሩክ ነፃ እንዲገቡ የወጣ መመሪያ ቁጥር 4/2005
ለማምረቻ ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንቶች ተሽከርካሪ ከጉምሩክ ነፃ እንዲገቡ በወጣዉ መመሪያ ቁጥር 4/2005 መሰረት ቀጥሎ በተቀመጠዉ ሠንጠረዥ ከተመለከቱት
የሥራ መስኮች በአንዱ ቢያንስ 10 ሚሊዮን ብር ካፒታል ለፕሮጀክቱ የሚያውል ማንኛውም ባለሀብት ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ከውጭ እንዲያስገባ የሚፈቀዱለት
የተሽከርካሪዎች ዓይነትና ብዛት በሥራ መስክ እና በሚቋቋምበት የልማት አካባቢ ይሆናል፡፡

ለማምረቻ ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንቶች የሚፈቀድ ተሽከርካሪዎች በኢንቨስትመንት ሥራ መስክና በአስተዳደር አካባቢዎች


የአስተዳደር አካባቢዎች
በሌሎች አካባቢዎች
በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን
የኢንሸስትመንት ሥራ መስክ
ሽፍን የጭነት ሽፍን የጭነት
ፒክ አፕ መኪና መኪና የጭነት መኪና ፒክ አፕ መኪና መኪና የጭነት መኪና
(ዴሊቨሪቫን) (ዴሊቨሪቫን)

1. የምግብ ኢንዱስትሪ
1.1. ሥጋናየሥጋውጤቶችን ማቀነባበር
1.2. ዓሣና የዓሣ ውጤቶችን ማቀነባበር
1.3. ፍራፍሬ እና/ወይም አትክልት
ማቀነባበር
1.4. የምግብ ዘይት ማምረት
1.5. ወተት ማቀነባበር እና/ወይም የወተት አንድ አንድ ሁለት አንድ ሁለት ሁለት
ውጤቶችን ማምረት
1.6. ስታርች እና የስታርች ውጤቶችን
ማምረት
1.7. ዱቄትን ማምረት ሳይጨምር
ጥራጥሬ፣ የቅባት እህል ወይም ሌላ
እህል ማቀነባበር
1.8. ሌሎችምግቦችንማምረት
1.9. ስኳር ማምረት - - - ሁለት ሁለት ሁለት
1.10. ቸኮሌት፣ ከረሜላ፣ብስኩት ወይም
ሌሎች ጣፋጭ ምግቦችን
አይፈቀድም አይፈቀድም አንድ አንድ አይፈቀድም
(አይስክሬም፣ጄላቲን እና ኬክን አንድ
ሳይጨምር) ማምረት
1.11. ማካሮኒ፣ ፓስታ እና/ወይም
የመሳሰሉ ምግቦችን ማምረት አንድ አንድ አይፈቀድም አንድ አንድ አንድ

1.12. የሕጻናት ምግብና ወተት፣ ተቆልቶ አንድ አንድ አይፈቀድም አንድ አንድ አንድ

0
የአስተዳደር አካባቢዎች
በሌሎች አካባቢዎች
በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን
የኢንሸስትመንት ሥራ መስክ
ሽፍን የጭነት ሽፍን የጭነት
ፒክ አፕ መኪና መኪና የጭነት መኪና ፒክ አፕ መኪና መኪና የጭነት መኪና
(ዴሊቨሪቫን) (ዴሊቨሪቫን)
የተፈጨ ቡና፣ የሚሟሟ ቡና፣
ሻይ፣ እርሾ፣
ሆምጣጤ፣ማዮኔዝ፣ሰው ሰራሽ
ማር፣አዮዲን የተጨመረበት ጨው፣
ወይም መሰል ምግቦችን ማምረት
1.13. የእንሰሳት መኖ ማቀነባበር አንድ አይፈቀድም አንድ አንድ አይፈቀድም ሁለት
2. የመጠጥ ኢንዱስትሪ
አንድ አንድ አንድ አንድ አንድ አንድ
2.1. የአልኮል መጠጥ ማምረት

2.2. የወይን ጠጅ ማምረት አንድ አንድ አንድ አንድ አንድ አንድ

2.3. ቢራ እና/ወይም የቢራ ብቅል ማምረት አንድ አንድ አንድ አንድ አንድ ሁለት
አንድ አንድ አንድ አንድ አንድ አንድ
2.4. ለስላሳ መጠጥ፣ የማዕድን ወይም
የታሸጉ ሌሎች ውኃዎችን ማምረት

3. የጨርቃጨርቅና የስፌት ውጤቶች


ኢንዱስትሪ

3.1. የጥጥ፣የሱፍ፣ የሐር እና አንድ አንድ አንድ ሁለት ሁለት ሁለት


የመሳሰሉየጨርቃጨርቅ ጭረቶ ችን
ማዘጋጀትና መፍተል

3.2. ጨርቃጨርቅመሸመን (ጨርቃጨርቅ


መፍተልንና ማጠናቀቅን ሊጨምር አንድ አንድ አንድ ሁለት ሁለት ሁለት
ይችላል)
3.3. ጨርቃጨርቅ ማጠናቀቅ
3.3.1. ጣቃ ጨርቅ፣ ክር፣ ድርና ማግ፣
አልባሳትና ሌሎች
የጨርቃጨርቅ ውጤቶችን አንድ አንድ አንድ አንድ ሁለት ሁለት
ማንጣትንወይም ማቅለምን
ሳይጨምር ጨርቃጨርቅ
ማጠናቀቅ

1
የአስተዳደር አካባቢዎች
በሌሎች አካባቢዎች
በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን
የኢንሸስትመንት ሥራ መስክ
ሽፍን የጭነት ሽፍን የጭነት
ፒክ አፕ መኪና መኪና የጭነት መኪና ፒክ አፕ መኪና መኪና የጭነት መኪና
(ዴሊቨሪቫን) (ዴሊቨሪቫን)
አንድ አንድ አንድ አንድ ሁለት ሁለት
3.3.2. ሌሎች የጨርቃጨርቅ
ማጠናቀቅ ሥራዎች

3.4. ሌሎች ጨርቃጨርቆችን ማምረት

3.4.1. ሹራብወይም ፎጣ ማምረት


3.4.2. ከአልባሳትበስተቀር
አንድ አንድ አንድ ሁለት ሁለት ሁለት
የተዘጋጁጨርቃጨርቆችን
ማምረት ምንጣፍ ማምረት

3.5. የጨርቃ ጨርቅ አልባሳትን (የስፖርት


አንድ አንድ አንድ ሁለት ሁለት ሁለት
አልባሳትነ ጨምሮ) ማምረት
3.6. የጨርቃጨርቅ ውጤቶች ተጓዳኝ ሁለት ሁለት
አንድ አንድ አንድ ሁለት
አካላትን (አክሰሰሪስ) ማምረት
4. የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪ
አንድ አንድ አንድ ሁለት ሁለት ሁለት
4.1. ባለቀለት ደረጃ ቆዳና ሌጦ ማልፋት
4.2. ካለቀለት ደረጃ በታች ቆዳና ሌጦ
አንድ አንድ አንድ ሁለት ሁለት ሁለት
ማልፋት
4.3. የቆዳ ውጤቶችን (ሻንጣ፣ቦርሳ፣የቆዳ ሁለት አንድ አንድ ሁለት ሁለት አንድ
ኳስ እና የመሳሰሉትን) ማምረት
4.4. የቆዳ ጫማ ማምረት
4.5. የቆዳ ውጤቶች ተጓዳኝ አካላትን
አንድ አንድ አንድ ሁለት አንድ ሁለት
(አክሰሰሪስ) ማምረት
አንድ አይፈቀድም አንድ አንድ አይፈቀድም አንድ

5. የእንጨት ውጤቶችን (እንጨት


መሰንጠቅን፣ጣውላ ማምረትን እና

2
የአስተዳደር አካባቢዎች
በሌሎች አካባቢዎች
በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን
የኢንሸስትመንት ሥራ መስክ
ሽፍን የጭነት ሽፍን የጭነት
ፒክ አፕ መኪና መኪና የጭነት መኪና ፒክ አፕ መኪና መኪና የጭነት መኪና
(ዴሊቨሪቫን) (ዴሊቨሪቫን)
ቀድመው የተዘጋጁ የእንጨት ውጤቶችን
መገጣጠምን ሳይጨምር) ማምረት

6. የወረቀት እና የወረቀት ውጤቶች


ኢንዱስትሪ - - - ሁለት _ ሁለት
6.1. ፐልኘ ማምረት
6.2. ወረቀት ማምረት - - - ሁለት አንድ አንድ
6.3. የወረቀት ማሸጊያዎችን ማምረት አንድ አንድ አይፈቀድም አንድ አንድ አንድ
6.4. ሌሎች የወረቀት ውጤቶችን
አይፈቀድም አንድ አይፈቀድም አንድ አንድ አይፈቀድም
ማምረት
7. የማተሚያ ኢንዱስትሪ አንድ አንድ አንድ አንድ አንድ ሁለት

8. የኬሚካልና የኬሚካል ውጤቶች ኢንዱስትሪ


አንድ አንድ አይፈቀድም ሁለት አንድ አንድ
8.1. መሠረታዊ ኬሚካሎችን ማምረት
8.2. ማዳበሪያ እና/ወይም የናይትሮጅን
አንድ አይፈቀድም አንድ ሁለት አይፈቀድም ሁለት
ውህዶችን ማምረት
8.3. የኘላስቲክ እና/ወይም የሰው ሠራሽ
ጎማ ጥሬ ዕቃዎችን ማምረት አንድ አይፈቀድም አንድ አንድ አይፈቀድም አንድ

8.4. ፀረ-ተባይ፣ ፀረ-አረም ወይም ፀረ-


አንድ አንድ አይፈቀድም አንድ አንድ አይፈቀድም
ሻጋታ ማምረት
8.5. የግድግዳ ቀለም፣ ቫርኒሽ ወይም መሰል
መለሰኛዎችን፤ የማተሚያ፣ የመጻፊያ
አንድ አይፈቀድም አንድ አንድ አይፈቀድም አንድ
ወይም የሥዕል ቀለም ወይም
ማጣበቂያ ማምረት
8.6. ሳሙናና ዲተርጀንት፣ ማፅጃና
መወልወያ፣ ሽቶ እና መሰል አንድ አንድ አይፈቀድም አንድ አንድ አንድ
መዋቢያዎችን ማምረት
8.7. ሰው ሠራሽ ጭረቶችን ማምረት አንድ አይፈቀድም አንድ አንድ አይፈቀድም አንድ

3
የአስተዳደር አካባቢዎች
በሌሎች አካባቢዎች
በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን
የኢንሸስትመንት ሥራ መስክ
ሽፍን የጭነት ሽፍን የጭነት
ፒክ አፕ መኪና መኪና የጭነት መኪና ፒክ አፕ መኪና መኪና የጭነት መኪና
(ዴሊቨሪቫን) (ዴሊቨሪቫን)
8.8. ሌሎች የኬሚካል ውጤቶችን
( ባሩድ፣ ፈንጂ፣ የፎቶግራፍ ፊልም
እና የመሳሰሉትን) ማምረት አይፈቀድም አንድ አይፈቀድም አይፈቀድም አንድ አይፈቀድም

9. የመሠረታዊ መድኃኒት ምርት እና


የመድኃኒት ዝግጅት ኢንዱስትሪ

9.1. ለመድኃኒት ግብዓትነት የሚውሉ


አንድ አንድ አይፈቀድም ሁለት አንድ አይፈቀድም
መሠረታዊ የመድኃኒት ውጤቶችን
ማምረትና ማዘጋጀት

9.2. መድኃኒት ማምረት ወይም ማዘጋጀት አንድ አንድ አይፈቀድም ሁለት አንድ አይፈቀድም

10. የጎማና የፕላስቲክ ውጤቶች ኢንዱስትሪ

10.1. የጎማ ውጤቶችን ማምረት አንድ አይፈቀድም አንድ ሁለት አይፈቀድም አንድ
10.2. ለሕንጻ ግንባታ፣ ለተሽከሪካሪ ወይም
ለሌሎች የኢንዱስትሪ ምርቶች
ግብዓት የሚሆኑ፤ ለመስኖና ለመጠጥ
ውሃ ማስተላለፊያነት እንዲሁም
አንድ አይፈቀድም አንድ ሁለት አይፈቀድም አንድ
ለፍሳሽ ማስወገጃ የሚያገለግሉ
የፕላስቲክ ቧንቧዎችን ወይም
ቱቦዎችን እና መገጣጠሚያዎችን
ማምረት
አንድ አይፈቀድም አይፈቀድም አንድ አይፈቀድም አይፈቀድም
10.3. ፌስታልን ሳይጨምር ሌሎች
የፕላስቲክ ውጤቶችን ማምረት
11. ብረት ያልሆኑ የማዕድን ውጤቶች አይፈቀድም አንድ አይፈቀድም ሁለት
ኢንዱስትሪ አንድ አንድ

4
የአስተዳደር አካባቢዎች
በሌሎች አካባቢዎች
በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን
የኢንሸስትመንት ሥራ መስክ
ሽፍን የጭነት ሽፍን የጭነት
ፒክ አፕ መኪና መኪና የጭነት መኪና ፒክ አፕ መኪና መኪና የጭነት መኪና
(ዴሊቨሪቫን) (ዴሊቨሪቫን)
11.1. መስተዋት እና/ ወይም የመስ ታወት
ውጤቶችን ማምረት
11.2. የሴራሚክ ውጤቶችን ማምረት አንድ አይፈቀድም አንድ አንድ አይፈቀድም ሁለት
11.3. ሲሚንቶ ማምረት _ _ _ ሁለት አይፈቀድም ሁለት

11.4. የሸክላና የሲሚንቶ ውጤቶችን _ አይፈቀድም አንድ አንድ አይፈቀድም ሁለት


ማምረት
11.5. ዕብነ በረድ እና የኖራ ድንጋይ አንድ አይፈቀድም አንድ አንድ አይፈቀድም ሁለት
መቁረጥ፣ ቅርፅ ማውጣት እና
ማጠናቀቅ (የማዕድኑን ሥራ
ሳይጨምር)
11.6. ኖራ፣ ጀሶ እና/ወይም የመሳሰሉ _ _ _ አንድ አይፈቀድም አንድ
መለሰኛዎችን ማምረት
11.7. የወፍጮ ድንጋይ፣ የብርጭቆ ወረቀት አንድ አይፈቀድም አንድ አንድ አይፈቀድም አንድ
ወይም የድምጽ መገደብያ ወይም
የሙቀት መከላከያ ምርቶችን
ማምረት
12. የመሠረታዊ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪ
(የማዕድኑን ሥራ ሳይጨምር)
አንድ አይፈቀድም አንድ ሁለት አይፈቀድም ሁለት
12.1. መሠረታዊ ብረትና የአረብ ብረት
ማምረት
12.2. መሠረታዊ የከበሩና የብረት ይዘት
አንድ አይፈቀድም አንድ ሁለት አይፈቀድም ሁለት
የሌላቸው ብረታ ብረቶችን ማምረት
12.3. ከብረት እና ከአረብ ብረት ፈሳሽ አንድ አይፈቀድም አንድ ሁለት አይፈቀድም አንድ
የተለያዩ ቅርፆችን ማውጣት
13. የማምረቻ መሣሪያዎችንና ዕቃዎችን አይፈቀድም አንድ አይፈቀድም ሁለት
ማምረትን የማይጨምር የብረታብረት አንድ ሁለት
ዕቃዎች ኢንዱስትሪ
13.1. የማዋቀሪያ ብረት ውጤቶችን፣
የብረት በርሜሎችን፣ ገንዳዎችን እና
ኮንቴይነሮችን ወይም የእንፋሎት

5
የአስተዳደር አካባቢዎች
በሌሎች አካባቢዎች
በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን
የኢንሸስትመንት ሥራ መስክ
ሽፍን የጭነት ሽፍን የጭነት
ፒክ አፕ መኪና መኪና የጭነት መኪና ፒክ አፕ መኪና መኪና የጭነት መኪና
(ዴሊቨሪቫን) (ዴሊቨሪቫን)
ማመንጫዎችን ማምረት

13.2. የቤት ክዳን ቆርቆሮ እና ምስማርን


ሳይጨምር ሌሎች የብረታ ብረት
አንድ አይፈቀድም አንድ ሁለት አይፈቀድም ሁለት
ውጤቶችን (የእጅ መሣሪያ፣ ቁሳቁስ
እና የመሳሰሉትን) ማምረት
14. የኮምፒዩተር፣ የኤሌክትሮኒክስ እና የዕይታ
ዕቃዎች ኢንዱስትሪ
አንድ አንድ አይፈቀድም አንድ አንድ አይፈቀድም
14.1. የኤሌክትሮኒክስ አካሎችንና
ሰሌዳዎችን ማምረት
14.2. ኮምፒዩተር እና ተጓዳኝ ዕቃዎችን
ማምረት
14.3. የመገናኛ መሣሪያዎችን ማምረት
14.4. የፍጆታ ኤሌክትሮኒክስ
(ቴሌቪዥን፣ዲ.ቪ.ዲ፣ ሬድዮ እና አንድ አይፈቀድም አንድ አንድ አይፈቀድም አንድ
የመሳሰሉ) ዕቃዎችን ማምረት
14.5. የመለኪያ፣ የመፈተሻ፣ የመቃኛ፣
የመቆጣጠሪያ ዕቃዎችን ወይም ሰዓት
ማምረት
14.6. የሕክምና መሣሪያዎችን
(ኢራዲዬሽን፣ ኤሌክትሮ-ሜዲካል
አንድ አንድ አንድ አንድ አንድ ሁለት
ወይም ኤሌክትሮ - ቴራፔቲክ)
ማምረት
14.7. የዕይታ ወይም የፎቶ ማንሻ ዕቃዎችን
ማምረት
14.8. መግነጢሳዊ እና የዕይታ ሜዲያዎችን አንድ አንድ አይፈቀድም አንድ አንድ አይፈቀድም
ማምረት

15. የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ኢንዱስትሪ


15.1. የኤሌክትሪክ ሞተር፣ ጀነሬተር፣
ትራንስፎርመር ወይም የኤሌክትሪክ አንድ አይፈቀድም አንድ አንድ አይፈቀድም አንድ
ማከፋፈያ ወይም መቆጣጠሪያ
ዕቃዎችን ማምረት

6
የአስተዳደር አካባቢዎች
በሌሎች አካባቢዎች
በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን
የኢንሸስትመንት ሥራ መስክ
ሽፍን የጭነት ሽፍን የጭነት
ፒክ አፕ መኪና መኪና የጭነት መኪና ፒክ አፕ መኪና መኪና የጭነት መኪና
(ዴሊቨሪቫን) (ዴሊቨሪቫን)
15.2. የኤሌክትሪክ ኃይል ማከማቻ ወይም
ባትሪ ማምረት
15.3. የኤሌክትሪክ ኃይል ሽቦዎችን ወይም
ገመዶችን (የፋይበር ኦፕቲክስን
ጨምሮ) እና ተያያዥ ዕቃዎችን
ማምረት
አንድ አይፈቀድም አንድ አንድ አይፈቀድም አንድ
15.4. የኤሌክትሪክ ብርሃን መስጫ
ዕቃዎችን ማምረት
15.5. የቤት ውስጥ መገልገያ የኤሌክትሪክ
ዕቃዎችን ማምረት፣
15.6. ሌሎች የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን
ማምረት
16. የማምረቻ /አገልግሎት መስጫ
መሣሪያዎችና ዕቃዎች ኢንዱስትሪ

16.1. ሁለገብ መሣሪያዎችን (ሞተር፣ ዕቃ


ማንሻ፣ ፓምፕ እና የመሳሰሉትን)
ማምረት
16.2. ለተለያዩ ዓላማዎች (ለግብርና ሥራ፣ አንድ አይፈቀድም አንድ ሁለት አይፈቀድም ሁለት
ለምግብ ማቀነባበሪያ፣ ለመጠጥ፣
ለጨርቃ ጨርቅና ማዕድን ለማምረት
የሚሆኑና ለመሳሰሉት ሥራዎች)
የሚውሉ መሣሪያዎችን ማምረት

17. የመኪና፣ የተጎታች እና ከፊል ተጎታች


ኢንዱስትሪ አንድ አይፈቀድም አንድ ሁለት አይፈቀድም ሁለት
17.1. መኪና ማምረት
17.2. የመኪና አካላትን፣ ተጎታችን
እና/ወይም ከፊል ተጎታችን
ማምረት፣
17.3. የመኪና መለዋወጫዎችን እና
ተጓዳኝ አካላትን (አክሰሰሪስ) አንድ አይፈቀድም አንድ ሁለት አይፈቀድም ሁለት
ማምረት

7
የአስተዳደር አካባቢዎች
በሌሎች አካባቢዎች
በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን
የኢንሸስትመንት ሥራ መስክ
ሽፍን የጭነት ሽፍን የጭነት
ፒክ አፕ መኪና መኪና የጭነት መኪና ፒክ አፕ መኪና መኪና የጭነት መኪና
(ዴሊቨሪቫን) (ዴሊቨሪቫን)
17.4. የባቡር ሞተሮችን (locomotives)
እና ጋሪዎችን ማምረት አንድ አይፈቀድም አንድ ሁለት አይፈቀድም ሁለት

17.5. ሌሎች የትራንስፖርት ዕቃዎችን


(ጀልባ፣ ብስክሌት፣ ሞተር ብስክሌት አንድ አይፈቀድም አንድ ሁለት አይፈቀድም ሁለት
እና የመሳሰሉትን) ማምረት
18. የቢሮና የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎችን
(ከሴራሚክ የሚሠሩትን ሳይጨምር) አይፈቀድም አይፈቀድም አንድ አንድ አይፈቀድም አንድ
ማምረት
19. ሌሎች ዕቃዎችን (የጌጣጌጥና ተዛማጅ
ዕቃዎች፣ የሙዚቃ መሣሪያዎች፣ የስፖርት
ዕቃዎች፣ መጫወቻዎችና አሻንጉሊቶች እና አንድ አይፈቀድም አይፈቀድም አንድ አይፈቀድም አይፈቀድም
የመሳሰሉትን) ማምረት
20. ኢንዱስትሪ ከግብርና ጋር የተቀናጀ
የማምረቻ አንድ አንድ አንድ አንድ አይፈቀድም ሁለት
21. ከግብርና ጋር የተቀናጀ የማምረቻ አንድ አይፈቀድም አንድ አንድ አይፈቀድም አንድ
ኢንዱስትሪ

You might also like