You are on page 1of 4

የሙንላይት አፀደ ህፃናት

በ 2015 . ዓ ም የተቋቋመ ክበባት አመታዊ ጥቅል


እቅድ

መግቢያ

እንደሚታወቀው ሁሉ ክበባት ለት/ቤት አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ይታወቃል፡፡ ስለሁነም


ክበባት በት/ቤት ማቋቋም የተማሪዎችን ፈጠራ ለማዳበር እርስ በርስ ተግባብተው መስራትን
ለማዳበር አይነተኛ ሚና ከሚጫወቱት አንዱ ክበባት ናቸው ስለሆነም ት/ቤታችን ክበባትን
ለአፀደ ህፃናት በሚመጥን መልኩ በማደራጀት እንደሚከተለው አቋቁመናል::
ጥቅል እቅድ

በ 2015 ዓ.ም ያሉት አጠቃላይ ተማሪዎች -- ሲሆኑ የዕድሜ ደረጃቸውም ከ 3፡6 - 6 ዓመት
ሲሆን እነዚህ ተማሪዎች አዲስና ነባር ተማሪዎች እንደ መሆናቸው መጠን ት/ቤቱን እና
ተማሪዎችን የመግባባት ባህል እንዲያዳብሩ የት/ቤት ምንነት ለህፃናት ለማስረዳት ይረዳን
ዘንድ እድሜያቸውን ያማከለ ክበብ ነድፈን ከመስከረም 9/2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ
አድርገን ቀጥሎ በዝርዝር የቀረቡት ክበባትን አቋቁመናል፡፡

1. የግል ንጽህናን የመጠበቂያ ቀን:- ሲሆን ተግባራዊ የመደረገውም ዘወትር ሰኞ


ጠዋት በሰልፍ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከ 2፡45-2፡55 ድረስ ይታያል ያሉባቸው ችግሮች
ለራሳቸውና ለቤተሰብ በማሳወቅ ችግሮቹ እንዲቀረፉ እናደርጋለን፡፡
2. ስለ ትራፊክ አደጋ ግንዛቤ መስጫ ቀን፡- ዘወትር ማግሰኞ በሰልፍ ሥነ-ሥርዓት
ወቅት ለተማሪዎች በሚገባቸው ቋንቋ የተለያዩ የምክሮችን አገልግሎት ይሰጣል፡፡
3. ስለተላላፊ በሽታዎች የግንዛቤ መስጫ ቀን፡- ይህ ክበብ ዋና አላማው
ተማሪዎችን ከተላላፊ በሽታ ለመከላከል ሲሆን አቅማቸው የሚችለውን የምክር
አገልግሎት በሚገባቸው መልኩ የሰጣቸዋል፡፡
4. የአከባቢ ጽዳት ቀን፡- የሚከናወንበት ግዜ ዘወትር ሰኞ ከሰዓት በኋላ ከ 8፡30-9፡55
ባለው ግዜ ውስጥ ነው፡፡
5. አትክልትን የመንከባከቢያ ቀን፡- ዘወትር ዓርብ ከ 8፡30-8፡55 ድረስ አትክልቶችን
ውሃ ያጠጣሉ የኮተኩታሉ በጋራ የተሰጣቸውን አትክልት ይንከባከባሉ
6. የሥነ-ምግባርና ሥነ-ዜጋ ቀን፡- ዘወትር ሰኞ እና ዓርብ ጠዋት በሰልፍ ሥነ-ሥርዓት
ላይ ከ 2፡45-2፡50 ድረስ ይሆናል በዚህ ግዜ መምህራን ተማሪዎች ከሚያውቋቸውና
ከሚያከናውኗቸው ነገሮች በመነሳት መከተል (መተግበር) ያለባቸውን እና የሌለባቸውን
ነገሮች ለይተው እንዲያውቁና ወደትግበራ እንዲገቡ የሚበረታቱበት ጊዜ ነው፡፡
7. እርስ በርሳቸው የሚመካከሩበት ግዜ፡- ዘወትር ዓርብ በሥነ-ምግባር ክበብ ላይ
በተማሪዎች ተራ ላይ የተሸለ ተማሪ በማስወጣት በተማሪዎች ላይ የሚታዩ ችግሮችን
እያነሳ እንዲመክር ማድረግና እርስ በእርስ የመተራረም ባህላቸውን እንዲያዳብሩ
በማድረግና መምህሯ በተናገሩት ላይ ማስተካከያ በመስጠት ሁሉም ተማሪ በእርስ
በርስ ምክክሩ ላይ እንዲሳተፍ ማድረግ በየሳምንቱ እንዲሳተፉ ማድረግ
8. አደጋ ከሚያደርሱ ነገሮች የመከላከያ ቀን፡- በት/ቤታችን የግንዛቤ መፍጠር
የሚደረገው በየወሩ የመጀመሪያ ቀን ሰኞ ሲሆን ይህ ክበብ የተቋቋመበት አይነተኛ
አስተዋፅኦ ልጆች እራሳቸውን ከአደጋ እንዲከላከሉ አደጋ የሚያደርሱ ነገሮችን
እራሳቸው ለይተው እንዲያውቁ እና እራሳቸውን ከአደጋ እንዲከላከሉ ግንዛቤ
ለማስጨበጥ እንድንችል ይጠቅማል፡፡
9. የውሃ ቀን፡- የውሃ ቀን በተመለከተ ተማሪዎች ውሃን በአግባቡ መያዝ የሚጠጡትን
ውሃ ንጽህና እንዲጠብቁ ማድረግ ውሃን አለማፍሰስ በአግባቡ ተጠቅሞ መዝጋት
እንዳለባቸው ማስረዳትና ተረኛ ተማሪዎችን ማዘጋጀት ውሃን በአግባቡ እንዲጠቀሙ
ምክር እንዲሰጡና እንዲቆጣጠሩ ሀላፊነት መስጠት፡፡ የውሃ ቀን ተግባራዊ
የሚሆንበትን ዕለት መጋቢት 12 ሚያዝያ 10 ግንቦት 15 ሲሆን እነዚህን ቀናቶች
በመከተል ክንውኑ ተግባራዊ ይሆናል፡፡
10. የስፖርት ቀን፡- በት/ቤታችን የስፖርት ቀን የሚባለው ዘወትር ዕሮብ ከጠዋቱ 2፡45-2፡
55 ባለው ሰዓት ሲሆን ትግበራውም መምህራን የተወሰነ ጊዚያት በማሰራት
ተማሪዎችን ማለማመድ እና እነሱም ያዩትን የሚተገብሩበት ጊዜ ማዘጋጀት እና ወደ
ሥራ ማዋል፡፡
11. የንባብ (መጽሀፍ የሚያገላብጡበት)ቀን፡- ከሰኞ - ዕሮብ ከ 5፡30-2፡55 ባለው ሰዓት
ሲሆን ተማሪዎች በዚህ ክፍለ ግዜ መጽሀፍቶች በማገላበፅ ይደሰታሉ የቤተመጽሃፍትን
ህግና ደንብ የለያሉ እንዲሁም የየክፍል ደረጃቸውን የተዘጋጁ መጽሀፍትን
እንዲያነብ ይበረታታሉ፡፡

እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸው ክንውኖች በ 2015 ዓ.ም ላሉት ለኬጂ ተማሪዎች የተዘጋጀ አቅማቸውን
ያገናዘበ የክበብ ምስረታ ሲሆን ለወደፊቱ ጥቅል እቅዱ እንደአስፈላጊው እንደግዜው እንደተማሪው
የእድገት ደረጃ እንደ ቁጥር መጠኑ ሊሻሻል የችላል፡፡

You might also like