You are on page 1of 22

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ

የስሜት ልህቀት/Emotional Intelligence/

የስልጠና ሰነድ

ሕዳር/ 2016 ዓ.ም


አዲስ አበባ

ሰንጠረዥ 1.

i
ምልክቶች የምልክቱ ምንነት (What it Refers to?)

ⓘ ወሳኝ ነጥቦች

 መልመጃ


ፍቺ/ማብራሪያ(Definition)

 ምሳሌ

 ማጠቃለያ

ማውጫ
መግቢያ............................................................................................................................................................1

ዋና አላማ.........................................................................................................................................................2
ዝርዝር አላማዎች.............................................................................................................................................2

ii
ክፍል አንድ........................................................................................................................................................3
1. የስሜት ልህቀት/Emotional Intelligence...................................................................................................3
1.1 የስሜት ልህቀት (EI) ምንድን ነው?....................................................................................................3
ክፍል ሁለት.......................................................................................................................................................8

2. የስሜት ልህቀት ሞዴሎች/Models of Emotional Intelligence.......................................................................8


2.1 ብቃትን መሰረት ያደረገ (የጎልማን አፈጻጸም) ሞዴል...................................................................................9
2.2 ባህሪን መሰረት ያደረገ ሞዴል....................................................................................................................9
2.3 ቅይጥ (ብቃትንና ባህሪን መሰረት ያደረገ) ሞዴል.......................................................................................10
ክፍል ሦስት.....................................................................................................................................................11

3. የስሜት ልህቀት አካላት (Components of Emotional Intelligence)..............................................................11


3.1. ራስን ማወቅ /self awareness/..............................................................................................................11
3.1.1. ስሜትን መረዳት...........................................................................................................................12
3.1.1.1 ራስን ማወቅን ማሳደግ.................................................................................................................12
3.1.2 ራስን መገምገም.............................................................................................................................14
3.1.3 በራስ መተማመን............................................................................................................................14
3.2. ራስን ማስተዳደር ወይም ራስን መቆጣጠር (Self management or regulation)...............................15
3.3. ማህበራዊ ግንዛቤ.............................................................................................................................15
3.4. ማህበራዊ ክህሎት...........................................................................................................................16
3.5. የማህበራዊ ክህሎቶች ባህሪያት (Characteristics of social skills)...................................................17
3.6. የማህበራዊ ክህሎት ዓይነቶች (Types of social skills)...........................................................................18
3.7. የስሜት ልህቀት ያላቸው ሰዎች ባህሪያት................................................................................................19
ክፍል አራት.....................................................................................................................................................21

4. የስሜት ልህቀት ጥቅሞች/Importance of Emotional Intelligence...............................................................21

iii
መግቢያ
‘የስሜት ልህቀት’ የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ከመዋሉ በፊት ‘ማህበራዊ ልህቀት' በሚለው ጥቅም ላይ ይውል
የነበረ ቃል ሲሆን በኋላ ላይ ተቀላቅሎ ሁሉን አቀፍ ቃል - 'ስሜታዊ እና ማህበራዊ ልህቀት' ተብሎ መጠራት
ጀመረ።

'ማህበራዊ ልህቀት' የሚለው ቃል በመጀመሪያ የተጠቀሰው በ 1909 በጆን ዲቪ የትምህርት የፍልስፍና


ስራዎች ውስጥ ነው። እሱ "በትምህርት ውስጥ የሞራል መርሆዎች" ውስጥ "ማህበራዊ ሁኔታዎችን
የመመልከት እና የመረዳት ኃይል" በማለት ማህበራዊ ልህቀትን ገልጾታል። ከዚያም እ.ኤ.አ. በ 1940 ዎቹ
ተመራማሪው ዴቪድ ዌችለር ብልህነት “ዓላማ ተኮር ትግበራን፣ በምክንያታዊነት እንዲያስብ እና ከአካባቢው
ጋር ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲሠራ የሚያስችል የግለሰቡ እምቅ አቅም” በማለት ገልፆታል ።

የስሜት ልህቀት ያለው ሰው ከሰዎች ጋር በሚቀራረብበት ጊዜ ከፊቱ ላይ ከሚያየው ጋባዥ ስሜት


በተጨማሪም በንግግር ጊዜም በሰዎች መካከል የሐሳብ ልዩነቶች እንደሚኖሩ ያምናል፤ ነገሮች ነጭ ወይም
ጥቁር ብቻ ናቸው ብሎም አያምን፤ ሓሳቡ ላይ እንጂ ሰዎች ላይ አያተኩርም፤ ንግግርና ክርክር ሐሳብን
ማንሽራሽሪያ እንጂ የአሽናፊና የተሽናፊ ጦርነት ሜዳ ነው በሚልም አይወስድም፡፡ የሰዎችን ሐሳብ
የሚያደምጥ የውይይት መንፈስን የሰከነ እንዲሆን የሚያደርግ ነው፡፡

ዋና አላማ

የዚህ ማሰልጠኛ ማኑዋል ዋና አላማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች በስሜት ልህቀት
ጽንሰ ሐሳብ ላይ በቂ ግንዛቤ በመፍጠር የተሻለ የስሜት ልህቀት ክህሎት እንዲኖራቸው ማስቻል ነው፡፡

1
ዝርዝር አላማዎች
ሰልጠኞች ይህንን ስልጠና ካጠናቀቁ በኋላ፡-

 ስሜት፣ ልህቀት እና የስሜት ልህቀት ምንነት ይገልፃሉ፤


 አራቱን የልህቀት ዓይነቶች ይለያሉ፤
 የራስን ማወቅ ምንነት እና ጽንሰ ሐሳብ ይረዳሊ
 የስሜት ልህቀት አካላትን (Components of emotional intelligence) በዝርዝር ያብራራሉ
 የስሜት ልህቀት ሞዴሎችን በመረዳት የተሻለ ግንዛቤ ይፈጥራሉ
 የስሜት ልህቀት መገለጫዎችን መረዳት ይችላሉ
 የስሜት ልህቀት አስፈላጊነትን (ጠቀሜታን) ያብራራሉ

ክፍል አንድ

1. የስሜት ልህቀት/Emotional Intelligence

2
የመወያያ ነጥብ

የውይይቱ ዓላማ 
 የስሜት ልህቀት ምንነትን ያስገነዝባል

 የስሜት ልህቀት መገለጫ ባህሪያትን እንዲለዩ ያደርጋል

ለውይይት የተሰጠ ጊዜ: 10 ደቂቃ

የመወያያ ጥያቄ:

1. ስሜት ምንድን ነው?

2. ልህቀት ምንድን ነው?

3. የስሜት ልህቀት ማለት ምን ማለት ነው?


1.1
የስሜት ልህቀት (EI) ምንድን ነው?
የስሜት ልህቀት “ስሜት” እና “ልህቀት” ከሚሉ ጥምር ቃላት የተገኘ ሲሆን፡-

“ስሜት” ማለት የአንድን ነገር ክስተት ወይም ግላዊ ሁኔታዎችን የሚያንፀባርቅ ውስብስብ የንቃተ ህሊና፣
የሰውነት ስሜት እና ባህሪ ነው። ሰሎሞን ሮበርት እንደፃፈው (2023) በአሪስቶትል አገላለጽ “ስሜት ሰዎች
በውሳኔያቸው ላይ ተጽእኖ የሚያሳድርባቸው እና ሐዘን ወይም ደስታ እንዲሰማቸው የሚያደርግ ውስጣዊ
ክስተት ሲሆን ቁጣ፣ ርህራሄ፣ ፍርሃት እና የመሳሰሉት የስነ-ልቦና ክስተቶችን የሚያጠቃልል ነው። አንዳንድ
ስሜቶች አንድን ሰው፣ ነገር ወይም ሁኔታን የሚመለከቱ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ ማለትም እንደ ጭንቀት፣ ደስታ
ወይም ድብርት ያሉ ለሁሉም የሚመለከቱ ናቸው። እንዲሁም አንዳንድ ስሜቶች እንደ ድንገተኛ ሃፍረት
ወይም ንዴት በጣም አጭር እና በቀላሉ የማይታወቁ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ እንደ ፍቅር ወይም ቂም
የመሳሰሉት ለረጅም ጊዜ ማለትም ሰዓታት፣ ወራት ወይም ዓመታት የሚቆዩ ናቸው (Solomon, 2023)።
ስሜት ከፍተኛ የጥንካሬ እና የደስታ ወይም የመከፋት ይዘት ያለው ማንኛውም የአእምሮ ልምድ ነው።
(Cabanac, 2002)

ልህቀት- በሥነ ልቦና ባለሙያዎች ትኩረት ከሚሰጣቸው ርዕሰ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው። ይሁን እንጂ እስከ

አሁን ድረስ ወጥነት ያለው መደበኛ ትርጉም የለውም። አንዳንድ ተመራማሪዎች ልህቀት ጠቅላላ የማሰብ
ችሎታ እንደሆነ ሲጠቁሙ ሌሎች ደግሞ የተለያዩ እውቀቶችን፣ ክህሎቶችን እና ተሰጥኦዎችን ያጠቃልላል
ይላሉ (Cherry, 2022)። ልሕቀት ማለት ከተሞክሮ የመማር፣ ከአዳዲስ ሁኔታዎች ጋር የመላመድ፣ ረቂቅ
ፅንሰ-ሐሳቦችን የመረዳት እና የማስተናገድ እንዲሁም እውቀትን በመጠቀም አካባቢን የመቆጣጣር
ችሎታዎችን ያቀፈ የአእምሮ ብቃት ነው። (Sternberg, 2022)

3
ተርማን የተባለው ተመራማሪ ልህቀትን ረቂቅ የማሰብ ችሎታ በማለት ሲገልፀው ቶርንዲክ የተባለው ደግሞ
መማርን እና ለጥያቄዎች ጥሩ ምላሽ የመስጠት ችሎታ ላይ አፅንዖት ሰጥቷል። (Sternberg, 2022)

እንደ የሥነ ልቦና ባለሙያዎች ገለፃ አራት የልህቀት ዓይነቶች አሉ፡-

1) የማሰብ ልህቀት (IQ)

2) የስሜት ልህቀት (EQ)

3) የማህበራዊ ልህቀት (SQ) እና

4) መሰናክልን የማለፍ ልህቀት (AQ) ናቸው፡፡

1. የማሰብ ልህቀት/Intelligence Quotient (IQ)/፡- ይህ ራስን የመረዳት ደረጃ መለኪያ ሲሆን ሒሳብን
ለማስላት፣ ነገሮችን እና ትምህርቶችን ለማስታወስ የሚያስችል የልህቀት ዓይነት ነው።

2. የስሜት ልህቀት /Emotional Quotient (EQ)/፡- ይህ የልህቀት ዓይነት ከሌሎች ጋር ሰላምን


የምንፈጥርበት፣ ጊዜን ያገናዘበ ምላሽ የምንሰጥበት፣ ኃላፊነትን የምንወጣበት፣ ሐቀኝነትን የምናረጋግጥበት፣
የሌሎችን የማንነት ወሰን የምናከብርበት፣ ትሕትናን የምንላበስበት፣ እውነተኛ እና ቅን አሳቢ የመሆን ችሎታ
ነው።

3. ማህበራዊ ልህቀት/Social Quotient (SQ)/:- ይህ በዙሪያችን ካሉ ሰዎች ጋር ለሚኖረን መስተጋብር


አውታረ መረብን (network) ለመገንባት እና ግንኙነታችንን ለረጅም ጊዜ ለማቆየት ያለንን ችሎታ
የምንለካበት የልህቀት ዓይነት ነው።

ከፍ ያለ የስሜት (EQ) እና ማህበራዊ ልህቀት (SQ) ያላቸው ሰዎች ከፍተኛ የማሰብ ልህቀት (IQ) ነገር ግን
ዝቅተኛ የስሜት (EQ) እና ማህበራዊ ልህቀት (SQ) ካላቸው የበለጠ የመሄድ አዝማሚያ ይኖራቸውል።
አብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶች የማሰብ ልህቀት (IQ) ደረጃዎችን በማሻሻል ላይ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ
ሲሆን የስሜት (EQ) እና ማሕበራዊ ልህቀት (SQ) ላይ ግን ዝቅተኛ ሚና አላቸው። ከፍተኛ የማሰብ ልህቀት
(IQ) ያለው ሰው በአማካይ የማሰብ ልህቀት (IQ) ቢኖረውም ከፍተኛ የስሜት (EQ) እና ማህበራዊ ልህቀት
(SQ) ባለው ሰው ተቀጥሮ ሊሰራ ይችላል። የአንድን ሰው የስሜት ብልህነትን (EQ) ባህሪው ሲወክል
ማህበራዊ ልህቀቱን (SQ) ደግሞ ግርማ ሞገሱ ይወክላል። እነዚህን ሶስት የልህቀት ዓይነቶች በተለይም
የስሜት (EQ) እና ማህበራዊ ልህቀት (SQ) የሚያሻሽሉ ልምምዶችን ማድረግ ያስፈልጋል።

4. መሰናክልን የማለፍ ልህቀት/Adversity Quotient (AQ)፡- በአስቸጋሪ የህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ የስነ-
ልቦና ጫናን በመቋቋም፣ ችግሮችን በመጋፈጥና ተስፋ ባለመቁረጥ የሚያጋጥሙ ተጋዳሮቶችን የማለፍ

4
ችሎታን የሚለካ የልህቀት ዓይነት ነው። መሰናክልን የማለፍ ልህቀት (AQ) ችግር ሲያጋጥም ማን ተስፋ
እንደሚቆርጥ፣ ቤተሰቡን ማን ጥሎ እንደሚሄድ እና ማን እራሱን እንደሚያጠፋ ይወስናል።

ሰዎች በትምህርት ዓለም ራሳቸውን ለማሳደግ የሚያፈሱት መዋእለ ነዋይ የማሰብ ልሕቀትን ብቻ ለማሳደግ
ያለመ ሲሆን ነገር ግን የተሟላ የልህቀት ባለቤት እዲሆኑ ካስፈለገ በሌሎች የልሕቀት ዓይነቶች ማለትም
በማሕበራዊ፣ ስሜት እና መሰናክልን የማለፍ ልህቀቶች ላይ ተመሳሳይ ሀብት ማፍሰስ ይኖርባቸዋል። በቤተሰብ
ውስጥ ልጆች ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው ዘርፈ ብዙ ስራዎችን የመስራት ልምድ እንዲያዳብሩ ወላጆች እድል
መፍጠር ይኖርባቸዋል። (Karlekar, 2022)

ከዚህ በመነሳት የስሜት ልህቀት የሚለውን ትርጉም ስንመለከት ጭንቀትን ለማርገብ፣ ውጤታማ በሆነ
መንገድ ለመግባባት፣ ከሌሎች ጋር ለመተሳሰብ፣ ተግዳሮቶችን ለማሸነፍ እና ግጭትን ለመፍታት የራስን
ስሜቶች የመረዳት፣ የመጠቀም እና የማስተዳደር ችሎታ ነው። የስሜት ልህቀት ጠንካራ ግንኙነቶችን
ለመገንባት፤ በትምህርት፣ በስራ እና ግላዊ የሕይወት ግብን ለማሳካት የሚያግዝ ልምድ ነው። እንዲሁም
ከስሜት ጋር እንዲገናኙ፣ ሐሳብን ወደ ተግባር እንዲቀይሩ እና አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በመረጃ ላይ
የተመሰረተ ውሳኔ እንዲሰጡ የሚረዳ ነው።

የስሜት ልህቀት እንደ ሌሎች የትምህርት ዘርፎች ሁሉ በርከት ያለ ትርጉም፣ ጽንሰ-ሐሳብ ወይም ትንታኔ
ያለው ሲሆን የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

 የስሜት ልህቀት ማለት፡-


 የራስን ስሜት በወጉ የመረዳት፣ በአግባቡ የመጠቀም፣ የመቆጣጠር፣ የመግዛትና የማስተዋል ሂደት
ነው።
 የራስንና የሌሎችን ስሜት ተረድቶ መያዝ።
 የራስንና የሌሎችን ስሜት በመረዳትና በመቆጣጠር ሐሳብን የመግለጽ ችሎታ ነው።
 ከሌሎች ፍጥረታት ጋራ ያለንን ግንኙነት በአግባቡ በመያዝ የራሳችንን ስሜት የመቆጣጠር፣
የማስተዳደር፣ የመረዳትና ከሌሎችም ጋራ መልካም መስተጋብር የመፍጠር ችሎታ ነው።
 የስሜት የእድገት (ልህቀት) ደረጃ ለመድረስ ስሜታችንን የምናውቅበት፣ የምንረዳበት፣
የምንቆጣጠርበትና ራሳችንን በመግዛት ምላሻችንን፣ ምርጫችንን፣ ውሳኔያችንን የተሻለ
የምናደርግበት መንገድ፤
 አስተሳሰብን በመቆጣጠር፤ ስሜታችንን በማስተዳደር፤ ራስን ጠንቅቆ በማወቅ ከኅብረተ ሰባችን ጋራ
ያለንን ግንኙነት መልካም የማድረግ ሂደት
 ስሜትን መግራት፣ ማረቅ፣ ማሠልጠን፣ መቆጣጠር፣ መልካሙን ማዳበር፣ መጥፎውን በመቀነስ

ከሰዎችና ከፍጥረታት ጋራ ያለንን ግንኙነት በጥሩ ሁኔታ ማሳለጥ፤

5
 የራስን ስሜት የማወቅና የመረዳት ችሎታና ይህን ዐቅም (ዕውቀት) በመጠቀም ራስን መቆጣጠር፣
በኅብረተሰብ ውስጥ ሰላምን የመፍጠርና ከሌሎች ጋር ያለንን ግንኙነት በመልካም የመገንባት ችሎታ
ነው፤
 በስሜት ሕዋሶቻችን የምንቀበለውን መረጃ በማስተዋል፣ በጥበብ በመረዳት ሌላው አካል ያለበትን
ሁኔታ ተረድቶ በዕውቀት ስሜትን በመግዛት በማስተዋል ምላሽ መስጠት ነው፤
 በስሜታችን ውስጥ ያለንን ክፍተት ወይም ደካማ ጎን ለይቶ በማውጣት የስሜት ልህቀታችንን
ማዳበር የሚሉ ብያኔዎች ይቀርቡበታል፣

በአጠቃላይ የስሜት ልህቀት ማለት “አንድ ሰው ከግለሰብ፣ ከቡድን፣ ከኅብረተሰብ ጋር ባለው ግንኙነት (ሥራ፣
ትዳር፣ ቤተሰብ አመራር፣ ኀላፊነትና ሃይማኖታዊ አገልግሎቶች እንዲሁም የንግድ ግንኙነት) ማኅበራዊ
ክንውኖች፣ ተፈጥሯዊ መስተጋብሮች፣ በተጨማሪም ልዩ ልዩ ግንኙነቶች ወቅት የራስን ስሜት እንዲሁም
የሌሎችን ስሜት በመረዳት፣ ማወቅ፣ መቆጣጠር፣ ማረጋጋት እና ከመልካምነት እንዳይጎድል ማድረግና
ዓላማውን እንዳይስት፣ አጠቃላይ እንቅስቃሴውንና ሂደቱን የማሳለጥ፣ የመቆጣጠርና የመምራት ብቃት ነው።
ይህን ስናደርግ እኛ የምንጫወተው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ በመረዳት፣ የራሳችንን ባሕርይና የሌሎችን ባሕርይ
መረዳትና መቆጣጠር እጅግ ወሳኝ ነው። የሌሎችን የስሜት ልህቀት ክፍተት ወይም ድክመት ለይቶ በማወቅ
በማይጐዱበት መልኩ ለማስተካከልና ለማረቅ መርዳት፣ ማገዝ፣ ማስተማርና ማሠልጠን እጅግ ጠቃሚ ነው።
(Mekibeb, 2023)

6
ክፍል ሁለት
2. የስሜት ልህቀት ሞዴሎች/Models of Emotional Intelligence

የመወያያ ነጥብ
የውይይቱ ዓላማ
 የስሜት ልህቀት ሞዴሎችን ለይተው ይረዳሉ
 ሦስቱም የስሜት ልህቀት ሞዴሎች ይዘረዝራሉ
ለውይይት የተሰጠ ሰዓት፡ 30 ደቂቃ
የመወያያ ጥያቄ:
1. የስሜት ልህቀት ሞዴሎች የሚባሉ እነማን ናቸው? ተወያዩበት

7
እ.ኤ.አ. በ 1990 በሳልቪ እና ሜየር ገለጻ የስሜት ልህቀት የመጀመሪያ ፅንሰ-ሀሳብ የስሜት ልህቀት የማህበራዊ
እውቀት እይታ አካል መሆኑን ገልፀዋል።

ጋርድነር ካቀረቡት 'የግል' ከሚባሉት ልህቀት ጋር በሚመሳሰል መልኩ፣ የስሜት ልህቀት ስለራስ እና ስለሌሎች
ግንዛቤን ይጨምራል ብሏል (Salovey, 1990)። ጋርድነር ስለ ግል የስሜት ልህቀት ከ'ግላዊ' የማሰብ ችሎታ
የሚለየው አጠቃላይ የራስን ስሜት እና የሌሎችን ግምገማ ላይ አለማተኮር ነው ፡፡ ይልቁንም ችግሮችን
ለመፍታት እና የራስን እና የሌሎችን ስሜታዊ ሁኔታዎችን ማወቅ እና መጠቀም ላይ ያተኮረ ነው። ፋልታስ
በ 2017 እ.ኤ.አ የስሜት ልህቀትን በሶስት ዋና ዋና ሞዴሎች ከፍሎታል፡፡ እነሱም፡-

1. ብቃትን መሰረት ያደረገ ሞዴል


2. ባህሪን መሰረት ያደረገ ሞዴል
3. ቅይጥ (ብቃትንና ባህሪን መሰረት ያደረገ) ሞዴል ናቸው፡፡

እነዚህ ሦስት ሞዴሎች ከምርምር፣ ትንተና እና ሳይንሳዊ ጥናቶች አንፃር እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-

2.1 ብቃትን መሰረት ያደረገ (የጎልማን አፈጻጸም) ሞዴል


ይህ ሞዴል ችሎታ ወይም ብቃት ላይ መሰረት ያደረገ አራት ዋና ዋና ሁኔታዎችን ሲያካትት እነሱም ስሜትን
መገንዘብ፣ ስሜትን መጠቀም፣ ስሜትን መረዳትና ስሜትን ማስተዳደር ናቸው፡፡ (Faltas, 2018)

1. ስሜትን መገንዘብ፡- ፊትን፣ድምጽንና የመሳሰሉትን በማየትና በመስማት ለስሜት ዕውቅና የሚሰጥበት


እና የሚረዱበት ብቃት ነው፡፡
2. ስሜትን መጠቀም፡- ከፍተኛ የሆነ የስሜት ልህቀትን በመጠቀም ስለሁኔታዎች የሚታሰብበትና ችግሮችን
ለመፍታት የሚጠቀሙበት ሲሆን የተሰጠን ተግባራት ለመስራት የሚጠቅም ሞዴል ነው፡፡
3. ስሜትን መረዳት፡- ከሌሎች ጋር በሚደረግ መስተጋብር የሚፈጠረውን ግጭት ወይም መልካም ጎን
የምንረዳበት ክፍል ነው፡፡
4. ስሜትን ማስተዳደር፡- ከፍተኛ የስሜት ልህቀት ያለው ሰው የራሱንም ሆነ በሌሎች ሰዎች የሚመጡትን
መልካም እና መጥፎ ስሜቶች የሚቆጣጥርበትና የሚመራበት ወይም የሚያስተዳድርበት ክፍል ነው፡፡

8
2.2 ባህሪን መሰረት ያደረገ ሞዴል

በ 2009 ፐትሪዲንግና ጓደኞቹ ለህትመት ያበቁት ሞዴል ሲሆን ስሜታዊ ልህቀት በችሎታ ላይ የተመሰረተ
ነው የሚለውን ጽንሰ-ሐሳብ ውድቅ ያደረገ ሞዴል ነው። ሰዎች በርካታ የስሜት ግላዊ ግንዛቤ እና ባህሪያት
እንዳላቸው ይጠቁማል። እነዚህ ባህሪያት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚለኩ ሳይሆን ሰዎች በሚያሳዩት ስሜታዊ
ምላሽ ሲሆን ይህም ምላሽ ሰጪው የራሱን ባህሪያት በትክክል መግለጽ የሚችልና የአንድን ሰው ስብዕና
የሚገልፅ መሆኑን ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ ነው። ይህ ከሌሎቹ ሞዴሎች የተለየ የሚያደርገው የስሜት
ልህቀት በአእምሮ ላይ የተመሰረተ ችሎታ እንጂ ውጫዊ የስብዕና ገጽታ አይደለም። ይህም ስብዕናን፣ ለራስ
ያለንን ግንዛቤና ባህሪን መሰረት በማድረግ የተቀረጸ ሞዴል ነው፡ (Faltas, 2018)

2.3 ቅይጥ (ብቃትንና ባህሪን መሰረት ያደረገ) ሞዴል

ይህ ሞዴል በዳንኤል ጎልማን የተዘጋጀ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ተቀባይነትን ያገኘ እና አገልግሎት እየሰጠ ያለ ነው፡፡
የስሜት ልህቀት ክህሎትን በ 4 ዘርፎች ሊከፈሉ እንደሚችሉ ይጠቁማል፡፡ እነሱም፡-

 የራስን ስሜት መገንዘብ


 ሀሳብን ለማመቻቸት ስሜትን መጠቀም
 ስሜትን መረዳት እና
 ስሜትን መቆጣጠር ናቸው።

እያንዳንዱን ቅርንጫፍ ሞዴሎች እንደሚከተለው ማየት ይቻላል፡፡

1. ስሜትን መገንዘብ፡- የሌሎችን የፊት እና የኋላ አገላለጾችን መለየት መቻልን የሚጨምር ሲሆን ፊትን
በማየትና ድምጽን በመግባባት የቃል ያልሆነ ግንዛቤን እና ስሜታዊ አገላለጾችን የሚያንጸባርቅ ነው
(Mayer et al., 2004)።
2. ሀሳብን ለማመቻቸት ስሜትን መጠቀም፡- ይህ ክፍል አዎንታዊና አሉታዊ የሆነ አስተሳሰብን በመለየት
ሃሳቡን ለመረዳትና ለመጠቀም የሚረዳ አምድ ነው፡፡
3. ስሜትን መረዳት፡- አቅምን ማወቅ፣መተንተን፣ አዝማሚያዎችን መረዳት፣ሃሳብ የመስጠትና
የመቀበል አቅምንም እንዲሁም ከስሜት ጋር የተገናኙ ውጤቶችን ማድነቅን ያካትታል።
4. ስሜትን መቆጣጠር፡- ግለሰቦች ከሌሎች ጋር በሚያደርጉት ተግባቦት በግለሰቦች መካከል የሚታዩ
ጥሩም ሆነ መትፎ ጎኖችን በማየት ስሜትን ከሚጎዱ ነገር ረስን መቆጣጠር ወይም መጠበቅ ማለት
ነው (ሜየር እና ሌሎች፣ 2004)።

9
ክፍል ሦስት

3. የስሜት ልህቀት አካላት (Components of Emotional Intelligence)

የመወያያ ነጥብ

የውይይቱ ዓላማ 
 የስሜት ልህቀት አካላትን እንዲለዩ ለማድረግ

 አራቱን የስሜት ልህቀት ዋና ዋና ክፍሎች ጽንሰ-ሐሳብ መረዳት ያስችላል

ለውይይት የተሰጠ ጊዜ: 10 ደቂቃ

የመወያያ ጥያቄ:

1. አራቱን የስሜት ልህቀት ዋና ክፍሎችን አብራሩ?

አሜሪካዊው ሳይኮሎጂስት እና የሳይንስ ጋዜጠኛ ዳንኤል ጎልማን በመጀመሪያ የስሜት ልህቀት የሚለውን ቃል

በመፍጠር ስለ ሰው አእምሮ ውስብስብነት እና ባህሪ ሳይንስ ሪፖርት አቅርቧል። የስሜት ልህቀት (EI)

የአንድን ሰው ስሜት የመረዳት እና የማስተዳደር እንዲሁም የሌሎችን ስሜት የማወቅ ችሎታን

ያመለክታል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት የስራ ላይ የስሜት ልህቀት ህይወትን፣ ግንኙነትን፣ ትምህርትን፣

አእምሮአዊ እና አካላዊ ደህንነትን ለመከታተል ጠቃሚ መሳሪያ ነው።

የጎልማን የስሜት ልህቀት ጽንሰ-ሐሳብ አራት ዋና ዋና ክፍሎችን የያዘ ሲሆን እነሱም ራስን ማወቅ፣ ራስን

ማስተዳደር ፣ማሕበራዊ ግንዛቤ እና ማህበራዊ ክህሎት ወይም ግንኙነትን ማስተዳደር ናቸው።

3.1. ራስን ማወቅ /self awareness/

ራስን ማወቅ የሁሉም ነገር መሰረት ሲሆን የሚሰማንን ሳናውቅ ወደ ሌሎች ክህሎቶች መሸጋገር አንችልም፡፡
በጎልማን የክህሎት ክፍሎች ራስን ማወቅ ሶስት ክህሎቶችን አካቶ ይይዛል፡፡

10
 ስሜትን መረዳት፣
 ራስን መገምገም እና
 በራስ መተማመን

እነዚህ ሶስት ክህሎቶች እርስ በእርሳቸው የሚደጋገፉ ሲሆኑ በቅድሚያ ስለ ስሜት ሁኔታችንን ማወቅ
አለብን፤ ከዚያ በትክክለኛው መንገድ ራሳችንን በመገምገም ስሜቶቻችንን በትክክል መረዳት ስንችል በበለጠ
የራስ መተማመን ስሜት ውስጥ እንድንሆን ያደርገናል፡፡ እነዚህን ክህሎቶች በዝርዝር ስንመለከት፡-

3.1.1. ስሜትን መረዳት


ስሜትንና የስሜት መንስኤዎችን ለይቶ አለማወቅ ደሰተኛ እና ውጤታማ ሕይወት ለመምራት አስቸጋሪ እና
የማይቻል ያደርገዋል። እንደ ገንዘብ፣ ክብር ወይም የስራ ስኬት ያሉ ውጫዊ ምልክቶች ስኬትን የሚያሳዩ
ሲሆኑ ነገር ግን ውስጣዊ ደስታ እና ጥሩ ስሜት እንዲሰማን የሚያደርገን ዋና ጉዳይ ምን እንደ ሆነ ለይተን
መረዳት መቻል አለብን። መጥፎ ስሜት እንዲሰማን የሚያደርገውንም መለየት ያጠቃልላል፡፡ ስሜትን ሙሉ
በሙሉ ማወቅና ለስሜቱ እውቅና መስጠት ብቻ ሳይሆን ስሜቱን መለየት እና በመጨረሻም ሊያስተላልፍልን
የፈለገውን መልእክት መቀበል ያስፈልጋል፡፡
አብዛኛው የማሕበረሰባችን ክፍል ስሜቱን ከማድመጥ ይልቅ ችላ ማለትን ይመርጣል። አንዳንድ የዘርፉ
ተመራማሪዎች እንደሚሉት ሰዎች መብላትን፣ መጠጣትን፣ ማጨስን፣ መድኃኒት መውሰድን፣ ከመጠን በላይ
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራትን ወይም በራስ ላይ የስራ ጫና መፍጠርን ስሜትን ላለማድመጥ እንደ
ማምለጫ መንገድ ይጠቀማሉ።

ስሜትን የመረዳት ክህሎት ሲዳብር በማንኛውም ጊዜ ምን እንደሚሰማ መግለፅ እና ስሜቱ ከየት


እንደመጣ፣ እንዲሁም ያንን ስሜት እንዴት እንደሚገለፅ መለየት ይቻላል፡፡

3.1.1.1 ራስን ማወቅን ማሳደግ

ራስን ለማወቅ ልምምድ የሚፈልግ ሲሆን መጀመሪያ ላይ የሚሰማንን ልዩ ስሜት ለመለየት አስቸጋሪ ቢሆንም
ምን እንደሚሰማን የማስተዋል ችሎታችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ራስን ማወቅን ለማሳደግ
የሚረዱ መንገዶች ከዚህ በታች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡

ሀ) ራስን መፈተሸ

11
ስሜትን ለመለየት ጊዜ መመደብ፣ ለብቻ መሆን እና መረጋጋት እንድንችል በቀን ውስጥ የሚመች ጊዜ መምረጥ
ማለትም በጠዋት፣ በምሳ እና በመኝታ ሰዓት መጀመር ጥሩ ይሆናል።
•ምን ይሰማኛል?
•ለምን ያህል ጊዜ እንደዚህ አይነት ስሜት ተሰማኝ?
•ስሜቴ በሰውነቴ ውስጥ እንዴት ሊገለጥ ይችላል? ውጥረት፣ ጥርስን በመንከስ፣ እጄን እየጨበጥኩ፣ የድካም
ስሜት እየተሰማኝ የሚሉትን ጥያቄዎች በተመስጥኦ ራስን በመጠየቅ መፈተሸ፡፡
ለ) የተሰማን ስሜት መለየት
ምን እንደሚሰማን መናገር ከቻልን አሉታዊ ስሜት በምን እንደጀመረን ማወቅ እንችለን። እንግዳ የሆነ ስሜትን
በመለየት ረገድ እየተሻሻልን ስንሄድ፣ ሁሉም ስሜቶች አሉታዊ እንዳልሆኑ ማስታወስ እና አዎንታዊ የሆኑትንም
መለየትና እውቅና መስጠትን እንለማመዳለን።
እንግዳ የሆኑ ስሜት ቀስቃሾችን ለመለየት የሚረዱ ጥያቄዎች ራስን መጠየቅ ያስፈልጋል። እነዚህም፡-
• ስሜቱ መቼ ተጀመረ?
•ስሜቱ ሲጀምር ምን ተፈጠረ?
•የስሜቱ መጠን በምን ደረጃ ላይ ነው? እንዴት?
ሐ) በሁኔታው ውስጥ መሆን
አንዳንድ ስሜቶቻችን ምን እያሉን እንደሆነ ለመስማት መሞከር በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ የኛ የነርቭ ስርዓት ሊፈጠር
ስለሚችል አደጋ ንቁ እንድንሆን የሚያደርግበት መንገድ አለው። ውስጣዊ ወይም ደመ ነፍሳዊ ብለን የምጠራው ነገር ግን
ይህ ተመሳሳይ ስሜታዊ ምላሽ በሌሎች የሕይወታችን አካባቢዎችም ይከሰታል፡፡ ስሜቶች ሲሰሙ እውቅና መስጠት
ስለራስ ለማወቅ ተጨማሪ እድሎችን ይሰጣል፡፡
መ) መሰረታዊ ምክንያቱ ጋር መድረስ
በአንድ ጊዜ አንድ ስሜት ብቻ እንደማይሰማን ልብ ማለት ያስፈልጋል። አንዳንዶቹ እርስ በርስ የሚጋጩ
ይመስላሉ፤ ነገር ግን የሚሰማንን እያንዳንዱ ስሜት በምክንያት ነው፡፡ ከሚሰማን ነገር የበለጠ መረጃ
ለማግኘት እያንዳንዱን ለመለየት እና እውቅና ለመስጠት ጊዜ መውሰድ ያስፈልገናል፡፡

3.1.2 ራስን መገምገም


ራስን የማወቅ ሁለተኛው ክፍል ስሜቶቻችን በአፈጻጸማችን፣ በባህሪያችን እና በግንኙነቶቻችን ላይ እንዴት
ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ በትክክል መገምገም ነው፡፡ በተጨማሪም ስሜቶቻችን በስራ ቦታ ላይ ባሉ ሌሎች
ሰዎች ላይ እንዴት ተጽእኖ እንደሚያሳድሩ መገምገም ያስፈልጋል፡፡ ራስን መገምገም በተለይ ለመሪዎች
በጣም አስፈላጊ ሲሆን የስሜታቸውን ተፅእኖ ካላወቁ የመላው ቡድናቸውን ስኬት እንዴት እንደሚያበላሹ
መረዳት አይችሉም።

12
3.1.3 በራስ መተማመን
ራስን የማወቅ የመጨረሻው ክፍል በራስ መተማመን ሲሆን ስሜትን እና የስሜትን ተጽእኖ ማወቅ እና እውቅና
መስጠት ሁል ጊዜ በተለይ ስሜቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያጋጥም ምቾት የማይሰጥ እንደሆነ ቢታወቅም በጣም
የዳበረ በራስ መተማመን ያላቸው ሰዎች ስለ ጥንካሬያቸው እና ድክመታቸው የሚለዩ እና በሕይወታቸው ውስጥ
በሚደርስባቸው ነገር ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር የሚያደርጉ ናቸው፡፡ የላቀ በራስ መተማመን ያላቸው ሰዎች፡-
 ስለራሳቸው እሴት እና አቅም እርግጠኛ ናቸው
 ጥሩ የመገኘት ልምድ ይኖራቸዋል
 ከፍተኛ ደረጃ የራስ ጽናት አላቸው
 ለትክክለኛ ነገር አንገታቸውን ለመስጠት ፈቃደኞች ናቸው
 ላመኑበት ነገር ከተወዳጅነት በጸዳ መልኩ አስተያየታቸውን ይገልፃሉ
 እርግጠኛ ባልሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን ፈጣን ውሳኔዎችን መወሰን ይችላሉ
 የሕይወታቸውን አቅጣጫ መቆጣጠር እንደሚችሉ የሚያምኑ እና የሚያደርጉ ናቸው፡፡
በራስ መተማመንን ለመገንባት የሚያግዙ ነጥቦች

ሀ) ጥንካሬዎችን መለየት
የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገብንባቸው ቦታዎች(ሁኔታዎች) መመዝገብ መጀመር ይኖርብናል። ስኬታማ
የሆንባቸው ቦታዎች በእርግጠኝነት ስለምናውቅ ከአስተያየቶች ተጨማሪ ጥንካሬዎችን ለማግኝትና እና
ስኬታማ የሆንባቸውን ነገሮች ለማስታወስ ስንፈልግ መዝገቡን በየጊዜው እያሻሻልን መመልከት ያስፈልጋል።
ለ) ድክመቶቻችንን መለየት
ይህ መሻሻል በሚያስፈልገን ሁኔታ ለመከታተል የሚያስችል ሲሆን በመጨረሻ ድክመቶቻችንን ወደ ጥንካሬ
ዝርዝር ማዛወር እንችላለን፡፡ ያሰብነውን ነገር ማሳካት እንደምንችል ማየት በራስ የመተማመን ስሜትን
ለማጠናከር ይረዳል።
ሐ) ውድቀታችንን እንደ መማሪያ መውሰድ
መሰናክሎች ወይም ውድቀቶች ሲያጋጥሙን እንደ መማሪያ እድሎች ወይም ትርጉም ያላቸው ተግዳሮቶች
አድርገን ማየት እና የምንችለውን ነገር መማር ለቀጣዩ የህይወት አቅጣጫችን እውቀት እንዲኖረን ይረዳናል፡፡
3.2. ራስን ማስተዳደር ወይም ራስን መቆጣጠር (Self management or regulation)
በስሜታችን መካከል ለሚፈጠሩ ሁኔታዎች ማለትም እንደ ቁጣ፣ ሃዘን፣ ደስታ፣ ብስጭት፣ ንዴት ወዘተ…
ሲከሰቱ መጥፎ ነገሮችን ከማድረግ ራስን በመግዛት፣ ታማኝነትን በመላበስ፣ ህሊናን ከሚጎዱ ሁኔታዎች
በመታቀብ፣ ለውጥን በመለማመድ፣ በፈጠራ በመታገዝ ራስን ማስተዳደር ወይም መቆጣጠር መቻል ማለት
ነው፡፡ ራስን ማወቅና ራስን መቆጣጠር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው፡፡

13
3.3. ማህበራዊ ግንዛቤ
ማህበራዊ ግንዛቤ የስሜት ልህቀትን ለማዳበር የሚረዳ ሶስተኛው እርምጃ እንደመሆኑ መጠን በራሳችን
ውስጥ ለመገንባት ሁላችንም መስራት ያለብን ችሎታ ነው (Eli Straw, 2023)። ይህ አካባቢን፣ ባህልን፣
ማህበረሰብን፣ የማህበረሰብ ደንብን፣ በሕይወት ውስጥ የሚገጥሙትን መሰናክሎች እና የምንኖርበትን
ማህበራዊ ድባብ መረዳትን ያጠቃልላል ። የማህበራዊ ግንዛቤ የሌሎችን ስሜት በትክክል የመረዳት፣ ለእነሱ
ትኩረት የመስጠት እና ለተወሰነ ጊዜ ከግል ስሜት በመውጣት በዙሪያችን ስላሉ ሰዎች ማሰብ መጀመር ነው።
በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ምን እንደሚያስቡ እና እንደሚሰማቸው በትክክል ለመለየት እና ለመረዳት የራስ
ወዳድነት አስተሳሰብን ማስወገድ ይጠይቃል። እኛ ማህበራዊ ፍጥረታት እንደመሆናችን መጠን ማህበራዊ
ተግባቦትን ለስኬታማ ህይወት ወሳኝ ሚና የሚጫወት ሲሆን ይህም የሌሎችን ስሜት የመረዳት ችሎታን
ማሳደግ አስፈላጊ ያደርገዋል። ማህበረሰባዊ ግንዛቤን ማሳደግ ጠንካራ ተግባቦትን ለመፍጠር፣ ግጭትን
ለማስተዳደር ፣አዎንታዊነትን ለመጨመር እና አድሏዊነትን ለመቀነስ ይጠቅማል (Eli Straw, 2023)።
ማህበራዊ ግንዛቤን ለመገንባት ልንከተላቸው የሚገቡን አንዳንድ መመሪያዎች/መንገዶች ሲኖሩ እነሱም
የተሻለ አድማጭ መሆን እና እራስን በሌሎች ጫማ ውስጥ አድርጎ ማሳብ ጥቂቶቹ ናቸው።

3.4. ማህበራዊ ክህሎት


ማህበራዊ ክህሎቶች በንግግር፣ በምልክት፣ በአካላዊ ቋንቋ እና በአለባበስ ተግባቦትና ግንኙነት ለመፍጠር
የምንጠቀምባቸው ክህሎቶች ናቸው። ማህበራዊ ልህቀት ከስሜት ልህቀት አምዶች ውስጥ አንዱ ሲሆን
ግለሰቦች ከሌሎች ጋር ለመግባባት የሚጠቀሙት ችሎታ ወይም ክህሎት፤ የተፈጠረውን ወይም የተገነባውን
ተግባቦት ጠንካራና ትርጉም ያለው እንዲሆን ስለሚያስችል፤ በዚህም የሌሎችን ስሜት እንዴት መረዳት
እንደሚቻልና ለሌሎች ያለን ድርጊት፣ባህሪ፣ ርህራሄን ያካትታል፡፡

አንድ ሰው ብቻውን መኖር የማይችል፤ ልኑርም ቢል ይሄን አሁን የምንመለከተውን ማህበረሰብ እንደምናየው
ሆኖ ባላገኘነው ነበር፡፡ አንድ ሕፃን ተወልዶ ከማንም ሰው ጋር ሳይገናኝ ቢያድግ ምን ዓይነት ሰው ሊሆን
እንደሚችል መገመት ነው፡፡ በሕይወት መቆየት ቢችል እንኳ ሌላው ቀርቶ እንደ ሰው ማሰብ መቻሉ
አጠራጣሪ ይሆናል፡፡ ማሕበራዊ ተግባቦት ባይኖር ቋንቋና መግባባት፣ ባሕል፣ ትምህርት፣ መረዳዳት፣ ስልጣኔ
ወዘተ… ሁሉ ባልኖሩ ነበር፡፡

ማኀበራዊ ተግባቦት ለሰው ልጆች በመሰረታዊነት የሚያስፈልግ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ መልካም ወይም
ጤናማ ማሕበራዊ ክህሎት ለሁለንተናዊ ስብዕና፣ ከሰዎች ጋር በሰላም ለመኖር እና ለስኬታማ ሕይወት እጅግ
አስፈላጊ ነው፡፡ ስሜት ደግሞ በሰዎች መካከል ለሚኖር ተግባቦት ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡ እንደ ሃፍረት፣ ደጋፊ
ማጣት፣ የብቸኝነት ስሜት፣ የበደለኝነት ስሜት ፍቅርና ርህራሄ የመሳሰሉት ስሜቶች ማህበራዊ ነገርን
ማዕከል የሚያደርጉ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሰዎች ከሌሎች ጋር ያላቸው

14
የማኀበራዊ ተግባቦት ሁኔታ ደስተኛ ሰው ከመሆናቸው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው (MTD Training,
2023)

የሰዎችን ስሜት መረዳት በማኀበራዊ ሕይወት ጠቃሚ እንደሆነው ሁሉ የራስን ስሜት ለሌሎች መግለፅ
ሌላው በጣም ጠቃሚውና አስፈላጊው ጉዳይ ነው፡፡ ስሜት ከፍ ካለበት ዝቅ ወደ አለበት የመተላለፍ ወይም
ሌላውን የማስከተል ፀባይ አለው፡፡ በደስታ እየተፍለቀለቀ የሚስቅ ሰው ለሌላውም ሳቅንና ደስተኝነትን
ያስተላልፋል፡፡ በሐዘንና ቁዘማ ውስጥ ያለ ሰው ለሌላውም ይህንኑ ያካፍላል፡፡ የማህበራዊ ክህሎት በቃል
ሊገለጽ የማይችል ቋንቋ ነውና ሰዎች በስሜቶቻቸው ብቻ መግባባት ይችላሉ፡፡

በጤናማ ስሜት ውስጥ ያለ ሰው የተሰማውን መልካም ስሜት ቃላት ሳያወጣ በሚያሳየው ስሜት ይገልፃል፤
በዚህም ይግባባል፡፡ በመልካም ስሜት ውስጥ ያለ ሰው ሌሎች ከእርሱ ጋር መሆን ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው
ስለሚያደርግ አብረውት መሆንን ይፈልጋሉ፤ ቀለል ያለና ነፃ የሆነ መንፈስ እ ንዲሰማቸው ያስችላል፡፡ የጥሩ
ስሜት ገፅታ የሚታይበት ሰው የሌሎችን ትኩረት ለመሳብ፣ ለማነሳሳትና የልብ ጓደኛ ለማፍራት እና በሰዎች
ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት የቀረበ ነው፡፡ በአጠቃላይ ማሕበራዊ ክህሎት ያለው ሰው ተፅዕኖን ለመፍጠር
አቅም የሚፈጥርለት ሲሆን በአንጻሩ ደግሞ አሉታዊ ስሜት ምልክቶች አብዝቶ የሚነበቡበት ሰው ግን ምንም
እውቀት፣ ክህሎትና ጠቃሚ ነገሮች ቢኖሩትም እንኳን ከሰዎች ሊሸሽ የሚችል ወይም ሰዎች የሚሸሹት
በመሆኑ እና እምነት የሚጥሉበት ባለመሆኑ በማሕበራዊ ሕይወቱ ስኬታማ የመሆን ዕድሉ አናሳ ነው፡፡

የማሕበራዊ ክህሎት በውስጡ የራስን ስሜት በአግባቡ መምራትንና የሰዎችን ስሜት በመረዳት ስሜታቸውን
ጠብቆ መግባባት መቻልን ሲሆን የሌሎችን ስሜት በተገቢው ለመረዳትና ለመግባባት ከአሉታዊ ስሜት ውጭ
መሆንንና የተረጋጋ አዕምሮአዊ ሁኔታን ይፈልጋል፡፡ የስሜቱ ተገዢ የሆነ ሰው (ለምሳሌ በፍርሃት ወይም
በንዴት ስሜት ላይ ያለ ሰው) የሌላውን ሰው ስሜት በሚገባ ሊረዳም ሆነ ሌሎችን ሊያረጋጋ አይችልም፡፡
(MTD Training, 2023)

3.5. የማህበራዊ ክህሎቶች ባህሪያት (Characteristics of social skills)


ማህበራዊ ክህሎት ሰዎች እንዲማሩ፣ ጤናማ ግንኙነት እንዲፈጥሩ፣ ፍላጎቶቻቸውን በተገቢው መንገድ
እንዲያሟሉ፣ ጓደኛ እንዲያፈሩ፣ ራሳቸውን እንዲጠብቁ ያስችላል፡፡ ማህበራዊ ክህሎት እንደ ኃላፊነት፣
ታማኝነት፣ መከባበር፣ ፍትሃዊነት፣ መተሳሰብ ያሉ አስፈላጊ ባህሪያትን ይገነባል። እነዚህ ባህሪያት የሰዎችን
ውስጣዊ ሥነ-ምግባር በመገንባት ጥሩ ውሳኔ እንዲሰጡ ያስችላሉ፡፡ የማህበራዊ ክህሎቶች ባህሪያት
እንደሚከተሉት ቀርበዋል፡፡
 ማህበራዊ ክህሎቶች ግብ ተኮር ናቸው፡፡
 ማህበራዊ ክህሎት ያላቸው ሰዎች በአንድ ጊዜ ከአንድ በላይ የሆኑ ባህሪያትን ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡
 ማህበራዊ ክህሎቶች ለግል እና ለስራ ግንኙነት ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡

15
 ማህበራዊ ክህሎቶችን መማር፣ መለማመድ እና ማስተማር ይቻላል፡፡ መማር ስንል ምን አይነት
ባህሪያትን መቼ እና እንዴት መጠቀም እንዳለብን ያካትታል፡፡

3.6. የማህበራዊ ክህሎት ዓይነቶች (Types of social skills)

1. መሰረታዊ ማህበራዊ ክህሎቶች (Basic social skills)

መሰረታዊ ማህበራዊ ክህሎቶች ሰዎች መጀመሪያ የሚያገኟቸው ክህሎቶች ሲሆኑ እነሱም ግንኙነቶችን
ለመጀመርና ለማዝለቅ መነሻ የሆኑ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ክህሎቶች መካከል ጥቂቶቹ፡- ውይይትን እንዴት
መጀመር፣ ማዝለቅ እና ማቆም እንዳለብን ማወቅ፣ ጥያቄዎችን እንዴት መጠየቅ እንዳለብን ማወቅ ወዘተ…
ናቸው።
2. የላቀ ማህበራዊ ክህሎት (Advanced social skills)

የላቀ ማህበራዊ ክህሎት መሰረታዊ ማህበራዊ ክህሎትን ካገኘን በኋላ የምንማራቸው ክህሎቶች ናቸው።
ውስብስብ ከሆኑት ማህበራዊ ክህሎቶች መካከል፤ ሐሳብን እንዴት እንደሚያካፍሉ ማወቅ፣ እርዳታን እንዴት
እንደሚጠይቁ ማወቅ፣ ይቅርታ እንዴት እንደሚጠየቅ ማወቅ፣ መመሪያ መስጠትና መከተል የሚሉት ጥቂቶቹ
ናቸው፡፡
3. የስሜት ማህበራዊ ክህሎት (Emotional social skills)
እነዚህ ክህሎቶች ቅጽበታዊ እና ዘላቂ ስሜቶችን ከመለየት እና ማስተዳደር ጋር በቅርበት የተሳሰሩ ናቸው፡፡
ለምሳሌ፡- ስሜትን፣ ርህራሄን፣ አክብሮትን መለየት እና መግለጽ የሚሉትን ያካትታል፡፡
4. የማህበራዊ ድርድር ክህሎት (Social negotiation skills)

የማህበራዊ ድርድር ክህሎት ግጭትን በተገቢው መንገድ ማስተዳደርን የሚያበረታታ ማህበራዊ ክህሎት ነው።
ለምሳሌ እንደ ድርድር፣ ግጭት አፈታት፣ ለሌሎች ጥቅም ቅድሚያ መስጠት፣ ከሌሎች ጋር መጋራት እና
ወዘተ… የሚሉትን ክህሎቶች ማግኘት እንችላለን፡፡
5. ተቋማዊ ማህበራዊ ክህሎት (Organizational social skills)
እነዚህ ክህሎቶች ሰዎች የዕለት ተዕለት ኑሮዋቸውን በትክክል እንዲመሩ ያስችላል፤ ለጭንቀት፣ ስጋትና ሌሎች
አሉታዊ ሁነቶች ምክንያት የሚሆኑ ነገሮችን ያስወግዳል። በዚህ ዓይነት የማህበራዊ ክህሎት ውስጥ የውሳኔ
አሰጣጥ አቅምንና ድርጅታዊ አቅምን መለየት የሚሉት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ማህበራዊ ክህሎትን ለማሻሻል የሚያግዙ ነጥቦች፡-

 ያልተገደቡ ጥያቄዎችን መጠየቅ


 የሌሎች ሰዎችን ማህበራዊ ክህሎት መረዳት

16
 የአይን ለአይን ግንኙነትን ማዳበር
 በንቃት የማዳመጥ ባህልን ማዳበር እና
 ለሌሎች ማሰብ ናቸው (ኬንድራ ቼሪ፣ 2023)፡፡

3.7. የስሜት ልህቀት ያላቸው ሰዎች ባህሪያት

ዳንኤል ጎልማን እንደሚለው የስሜት ልህቀት ያለው ሰው የሚከተሉት ባሕርያት አሉት፡፡

ሀ) ራስን ማወቅ
 ራስን ማወቅ ማለት ስለራስ ጥንካሬ እና ድክመት ማወቅ ማለት ሲሆን አንድ ሰው ተጨባጭ ግቦችን
በማውጣት ግቡን የማሳካት ዕድሉ ከፍ ያለ እንዲሆን የሚያደርግ ነው።
ለ) በራስ ተነሳሽነት
 እንደዚህ ያሉት ሰዎች ከፍተኛ ጭንቀትን የመቆጣጠር እና ከውድቀት በፍጥነት የማገገም ችሎታ
ያላቸው ሲሆን በራስ ተነሳሽነት ምክንያት ቀጣይነት ያለው ተግባር መከወን ይችላሉ።
ሐ) ራስን መቆጣጠር
 በስሜታዊነት ለሚከሰቱ ክስተቶች የተመጣጠነ ምላሽ መስጠት የሚያስችል ሲሆን ይህ ሊሆን
የቻለው የስሜታቸው እስረኛ እንዲሆኑ ስለማይፈቅዱ ነው።
መ) ርህራሄን መላበስ
 የሌሎችን እይታ እንዲረዱ በሌሎች ጫማ ውስጥ ሆነው ሁኔታዎችን ለመገንዘብ ጥረት ያደርጋሉ።
 ርህራሄ በሦስት ዓይነቶች ሊከፈል ይችላል።
1. የእውቀት (ኮግኒቲቭ) ርህራሄ፡- የሌላውን ሰው አመለካከት የመረዳት ችሎታ
2. የስሜት ርህራሄ፡- ሌላ ሰው የሚሰማውን የመሰማት ችሎታ
3. የይመለከተኛል ስሜት፡- ሌላ ሰው ከአንተ/ከአንቺ ምን እንደሚፈልግ የማወቅ ችሎታ
ሠ) ግንኙነቶችን ወይም ማህበራዊ ክህሎቶችን በተሻለ ሁኔታ መያዝ
 ግለሰቡ ግንኙነቱን በብቃት ለማስተዳደር/ለመምራት/ የሚያስችሉ ማህበራዊ ክህሎቶች ማለትም
መቻቻልን፣ ትዕግስትን፣ ብልኃተኛነትን፣ ጥሩ ማህበራዊ ትውስታን፣ ቀልድ እና ራስን የመቻል
ስሜትን ያጠቃልላል።
 ከፍተኛ የስሜት ልህቀት ያለው ሰው ሰዎችን በራዕዩ የማሳተፍ፣ ተግዳሮቶችን ወደ መልካም ዕድል
የመቀየር እና ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ተጠቃሚ የሚያደርግ ሁኔታ የመፍጠር ችሎታ አለው።
ረ) ፈጠራ
 አወንታዊ ስሜት ፈጠራን የሚያበረታታ ሲሆን የስሜት ልህቀት አንድ ሰው የጭንቀት መጠኑን
እንዲቆጣጠር እና ችግር ሲያጋጥመው በጎ አመለካከት እንዲያመነጭ ያስችለዋል።

17
ክፍል አራት

4. የስሜት ልህቀት ጥቅሞች/Importance of Emotional Intelligence

የመወያያ ነጥብ
የውይይቱ ዓላማ
ሰልጣኞች በራሳቸው አቅም የስሜት ልህቀት በስራ ቦታ እና በህይወታቸው ላይ
ከሚያመጣው ጥቅም ጋር በማያያዝ ሃሳባቸውን እንዲያነሱ ለማድረግ
ለውይይት የተሰጠ ሰዓት፡ 30 ደቂቃ
የመወያያ ጥያቄ:
1.የስሜት ልህቀት በጤናና በስራ ቦታ ላይ የሚያመጣው ጥቅም ምንድነው? ከስራ
አካባቢያችሁና ከጤና ሁኔታችሁ ጋር በማያያዝ ተወያዩበት

18
የስሜት

ከስሜት ልህቀት ጥቅሞች መካከል ጥቂቶቹን እንደሚከተለው ለመዘርዘር ተሞክሯል፡፡ እነሱም፡-


o ግንኙነትን ያሻሽላል
o ከሌሎች ጋር የሚኖረንን ተግባቦት ያጠነክራል
o ርህራሄን ያላብሳል
o ቅንጅታዊ አሰራርን ያጠነክራል
o ለሌሎች አክብሮት መስጠትን ያበረታታል
o በራስ መተማመንና አዎንታዊ አስተሳሰብን ለማዳበር ያግዛል
o ሙያዊ ዕድገትን ለማምጣት ያስችላል
o ጭንቀትን ይቀንሳል
o ፈጠራን ያበረታታል
o ከስህተት ለመማር ይጠቅማል

19

You might also like