Professional Documents
Culture Documents
የአሰራር ስርዓት ሰነድ
የአሰራር ስርዓት ሰነድ
1 በአገልግሎት ሰጪው………………………………………………………….
1.1 በተገልጋዩ…………………………………………………………………..
7. ማጠቃለያ-------------------------------------------------------------------------------------11
መግቢያ
ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትመራበት በግብርና መር ፖሊሲ ውስጥ ኢኮኖሚ ዕድገታችን አካል የሆነው
የእንስሳት ሀብት ልማታችን ከፍተኛ አስተዋጽዖ አለው፡፡ በተደጋጋሚ እንደሚገለጸው ካለን የእንስሳት ሀብት
ልማት አኳያ እየተገኘ ያለው ጥቅም አነስተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ግልጽ ነው፡፡ ከእንስሳት ሀብታችን
ተገቢውን ጥቅም ለማግኘት መንግስት ትኩረት ሰጥቶ የዘርፉን ዕድገት ለማፋጠን የሚያስችሉ ተቋማትን
በማደራጀትና የሰው ሃይል በመመደብ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ ይህም ተግባር በአርሶ አደሩ፣ ከፊል አርብቶ
አደርና አርብቶ አደር አካባቢዎች ህብረተሰብእንዲሁም በከተሞች ውስጥ የተለያዩ ድጋፎች በማድረግ ላይ
ይገኛል፡፡
ከእንስሳት ሀብታችን አስፈላጊውን ጥቅም እንዳናገኝ ማነቆ ከሆኑ ምክንያቶች አንዱና ወሳኝ
የሆነው የእንስሳት ጤና ችግር ነው፡፡ በተለይም ምርትና ምርታማነትን ከመቀነስ፣የተዋልዶ ብቃትን
ከማውረድ ባለፈ ባልታሰበ ሁኔታ የእንስሳትን ዕልቂት የሚያስከትሉ ከእንስሳት ወደ ሰውና ከሰው ወደ
እንስሳት የሚተላለፉ ተዛማችና ድንበር ተሻጋሪ በሽታዎች በስፋት መኖር የዘርፉን ችግር እያባባሰው
ይገኛል፡፡
አዲስ አበባ የሀገራችን መዲና የሆነች ከ 3.8 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚኖርባት ናት፡፡ ነዋሪው የወተት
የስጋ በአጠቃላይ የእንስሳት ውጤቶች፣ፍላጎት በየጊዜው እያደገ የሚገኝባት ከተማ ስለሆነች፤
የነዋሪውን ፍላጎት ለማሟላት በከተማ የዘመናዊና ባህላዊ የእርባታ እንቅስቃሴዎች በግለሰቦች፣
በማህበራት ተደራጅተው በመስራት ለአቅርቦቱ አስተዋፅኦ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
እነዚህን እንቅስቃሴዎች የሚያግዙ በመንግስት ደረጃ ከከተማ ግብርና እስከ ወረዳ መዋቅር በመዘርጋት
አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በግል በእንስሳት መድሐኒት ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ አስመጪና
አከፋፋዮች፣የጅምላና የችርቻሮ ነጋዴዎች፣ የእንስሳት መድሃኒት ቤትና የግል ክሊኒክ ከፍተው የሚሰሩ
ይገኙበታል፡፡ ከዚህም ሌላ በህገ ወጥ የእንስሳት መድኃኒት ንግድና ህክምና ስራ ላይ የተሰማሩም
ይገኙበታል፡፡ ከዚህ አንፃርየሚሰጠውን አገልግሎት በመንግስታዊም ሆነ በግል ዘርፍ ተደራሽ ለማድረግ
ሰፊ ክፍተት በመኖሩ የቅሬታ ምንጭ ከመሆን ባሻገር የኪራይ ሰብሳቢነትና የመልካም አስተዳደር ችግር
ጎልቶ ስለሚታይ በመንግስትም ሆነ በግሉ ዘርፍ ያለውን ሁኔታ ስርዓት ለማስያዝ አሰራር ማዘጋጀት
ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
የላብራቶሪ ምርመራ አገልግሎት፡- በመስክ ለሚሰሩ ስራዎች ጠንካራ ድጋፍ የሚሰጥ ተቋም
ሲሆን የበሽታዎችን መንስኤና ስርጭት በአይነት በመለየት የመሳሰሉትን በሚገባ በማጥናት በሽታን
በምርመራ በማረጋገጥ መቆጣጠሪያ ስልቱን የማመላከት ሥራን አጣምሮ የያዘ ክፍል ነው፡፡
1.3. በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 35 ያህል የግል እንስሳት ጤና ክሊኒኮች ያሉ ሲሆን በአብዛኛው የግል
ተቋማቱ በኩል የሚታዩ ችግሮች፣
ከተፈቀደላቸው ስራ ውጭ መሥራት
ባለሙያ ያልሆኑትን ቤት ለቤት ሄደው በስማቸው እንዲሰሩ ቢዝነስ ካርድ ሰጥቶ
ማሰማራት
ተገቢ ያልሆን ከፍተኛ ዋጋ መጠየቅ /መንግስት ዋጋ ሊተምን አይችልም ነጻ ገበያ
መሆኑን መዘንጋት የለብንም ይህን ጉዳይ ከሰው ህክምናም የሚሰራውን ገና ህክምና
ሳያገኙ ለካርድ ብቻ ከ 150 ብር እንደሚከፍል መዘነጋት የለብንም
በህገወጥ መንገድ የሚሰሩት ለማጋለጥ አለመፈለግና አለመተባበር ግልጽ ቢሆን
የሰሩትን ሥራ ሪፖርት አለማድረግና አለመተባበር
የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸውን መድሃኒቶች ጥቅም ላይ ማዋል መገለጫው
የመንግስት ተቋማት ደጋፊ አገልግሎት ሰጪ መሆናቸውን አለመረዳትና የጥቅማቸው
ተቀናቃኝ አደርጎ በማሰብ በመንግስት ተቋማት ጥራት ያለው አገልግሎት እንደማይገኝ
አስመስሎ ማስወራትመገለጫው
4.1.3. በግል ተቋማትና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶት በግል የሚሰጡ የእንስሳት ጤና
አገልግሎቶች በተመለከተ
• ባለሙያ ያልሆኑትን ሰዎች ቤት ለቤት ሄደው በስማቸው እንዲሰሩ ቢዝነስ ካርድ ሰጥቶ
ማሰማራት
• ተገቢ ያልሆነ ከፍተኛ ዋጋ መጠየቅ (ነጻ ገበያ መሆኑ መዘንጋት የለበትም መንግስት ዋጋ
መተመን አይችልምተጠቃሚው ፈቅዶ ላሰራበት እኛ ተከራካሪ መሆን አንችልም
• የተጠናከረ የሪፖርት ሥርዓት መዘርጋት፣ በክፍለ ከተማው ውስጥ የሚሰሩ ህጋዊ የእንስሳት
ጤና ክሊኒክ ያላቸው ሪፖርት ለክፍለ ከተማው እንዲያቀርቡ ማድረግ፣ በማያደርጉት ላይ
እርምጃ መውሰድ ወሳጅ ማነው
ማጠቃለያ