Professional Documents
Culture Documents
HR Ad Hoc 82
HR Ad Hoc 82
የሙያ መሰላል/አቅጣጫ (Career Path ) ከሚተገበርባቸው መንገዶች አንዱ የሙያ ዕድገት (Career progression) ስርዓት ሲሆን፣
የሙያ ዕድገት (Career progression)ማለት ከአንድ ዝቅተኛ ንዑስ የስራ መደብ(Sub band) ወደሚቀጥለው ከፍተኛ
ንዑስ የስራ መደብ ሰራተኛው በሚቀመጡ መስፈርቶችና የመምረጫ ስርዓቶች እንዲሸጋገር የሚደረግበት ስርዓት ነው፡፡ ይህ በተለመደ
መልኩ በማስታወቂያ ከሚተገበረው የዕድገት አሰራር የተለየ ሲሆን፣ በዚህ ስርዓት የሚደረገው ምደባ ያለማስታወቂያ በየስራ ክፍሉ
ውስጥ ያሉትን ሰራተኞች እርስ በርስ በማወዳደርና ለምርጫ የተቀመጡትን የመምረጫ መስፈርቶች በተሻለ ውጤት የሚያልፉትን
ወደሚቀጥለው ሰብባንድ እንዲሸጋገሩ የሚያደርግ ስርዓት ነው፡፡ ይህ ስርዓት ቀደም ሲል ያልነበረ ሲሆን፣ የኬርየር ፓዝ ስርዓትን
መጀመር ተከትሎ የሚተገበር አዲስ አሰራር ይሆናል ማለት ነው፡፡
ይህ ስርዓት መጠነኛ የዕድገትና የደመወዝ ጭማሪ የሚያስገኝ ስለሆነ አንድ ሰራተኛ በኬርየር ፕሮግሬሽን የሰብ ባንድ ለውጥ ካገኘ የ5
ፐርሰንት የደመወዝ ጭማሪ ይደረግለታል፡፡ በዚህ መልክ የኬርየር ፕሮግሬሽን ዕድል ተጠቃሚ የሆነ ሰራተኛ ወደሚቀጥለው የኬርየር
ፕሮግሬሽን ለመወዳደርና ለማደግ ቢያንስ ሁለት ዓመት መስራት ያለበት ሲሆን በመደበኛው ምደባ በማስታወቂያ ለሚደረግ የዕድገት
ውድድር ለመሳተፍ ግን ቢያንስ አንድ ዓመት ማገልገል ይኖርበታል፡፡ ስለሆነም አንድ ሰራተኛ አዲስ በሚጀመረው የኬርየር ፕሮግሬሽን
ተጠቃሚ ከሆነ ቢያንስ እስከ አንድ ዓመት ለዕድገት መወዳደር አይችልም ማለት ነው፡፡
ሰራተኛውንም ኩባንያውን በሚጠቅም መልኩ ምላሽ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ይህ አዲስ ስርዓት በኩባንያው የቆየውን የረዥም ጥያቄ
ከመመለስና በፍጥነት ከመተግበር አንፃር የተጠራቀመውን ጥያቄ ለመፍታት ሲባል በየዓመቱ አንድ ጊዜ ብቻ የሚደረገው የኬርየር
ፕሮግሬሽን ስርዓት ትግበራ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ብቻ በየስድስት ወራት የሚደረግ ይሆናል፡፡ ይህ ማለት በመጀመሪያው
ዙር ያላገኙ ሰራተኞች በሁለተኛው ወይም በሶስተኛ ዙር ተጠቃሚ የሚሆኑበት ዕድል ይኖራል፡፡ ለዚህ ሰራተኞች ከአንደኛ ወይም
ከሚቀጥለው ዙር የሚማሩትን ትምህርት በመውሰድና ማሻሻል የሚገባቸውን ነገር የሚቀጥለው የውድድር ጊዜ ከመምጣቱ በፊት
በማሻሻል ለቀጣዩ ውድድር መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በዚህ መሰረት የመጀመሪያው ዙር የኬርየር ፕሮግሬሽን ምደባ በየካቲትና
በመጋቢት 2019 ወራት በኮርፖሬት፣ በዞንና ሪጅን በሚደረጉ የቃለ መጠይቅ ፈተናዎች የሚጀመር ሲሆን ሁለተኛው ዙር ከስድስት
ወራት በኋላ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
በኩባንያው የቆየውን የኬርየር ፓዝ ጥያቄ በፍጥነት ከመመለስ አንፃር የተቀየሰው አሰራር ከሁለት ዓመት በኋላ ግን በየዓመቱ
አንድ ጊዜ ብቻ የሚሆን ሲሆን የመምረጫ መንገዱም ከቃለ መጠይቅ ፈተና በተጨማሪ የፅሁፍ ፈተና እና የ360 ዲግሪ ምዘና
ስርዓትን በማካተት የሚተገበር ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ከሁለት ዓመት በኋላ የሚተገበረው የኬርየር ፕሮግሬሽን ስርዓት በደፈናው
በኮታ የሚተገበር ሳይሆን እያንዳንዱ የስራ ክፍል ባስመዘገበው የቀደመው በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም እና ኩባንያው ለዚህ ስርዓት
መተግበር በሚመድበው በጀት ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
በመሆኑም ሰራተኞች በአንድ በኩል ለኬርየር ፕሮግሬሽን የሚያስፈልጉትን ቅድመ ሁኔታዎች እና የኬርየር ፕሮግሬሽን ተጠቃሚ
መሆን ያለውን ጥቅምና ውጤት እንዲሁም በማስታወቂያ ከሚደረግ መደበኛ የእድገት ውድድር ጋር ያለውን መስተጋብር በአግባቡ
በመረዳት ለተግባራዊነቱና ለውጤታማነቱ የራሳቸውን አስተዋፅዖ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
የኬርየር ፕሮግሬሽን ስርዓትን ዝርዝር አተገባበር አስመልክቶ በተከታታይ ለሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክቶች የሚተላለፉ
ሲሆን ሁሉም የኩባንያችን ማህበረሰብ ይህ አዲስ ስርዓት የታሰበለትን ዓላማ በማሳካት ሰራተኛውን ደስተኛ ኩባንያውም ውጤታማ
እንዲሆን በሚያስችል መልኩ እንዲተገበር የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ከአደራ ጭምር እናሳስባለን፡፡