You are on page 1of 12

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 12 የስራ

ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ፅ/ቤት ሪፖርት

ሰኔ 2010 ዓ.ም

1. መግቢያ

0
ሀገራችን ኢትዮጵያ በፈጣን ዕድገት ላይ ትገኛለች፡፡ የህዝቦችዋን የድህነት መጠን ለመቀነስ በመረባረብ ላይ ትገኛለች፡፡ የድህነት መጠኑን ለመቀነስ

መንግስት ከአለም ባንክ ጋር በመተባበር የ 10 አመት የምግብ ዋስትና ፕሮግራም በመቅረፅ በመንቀሳቀስ ላይ ትገኛለች፡፡ እንደ አዲስ አበባ በ 2009 ዓ.ም

በ 35 ወረዳዎች በመጀመሪያው ዙር የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሎዋል፡፡ በሁለተኛው ዙር ማለትም በ 2010 ዓ.ም በ 55 ወረዳዎችን

ለማስጠቀም ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡ ወረዳ 12 ከተመረጡ 55 ወረዳዎች አንዱ ሲሆን የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡

የተሰሩት ስራዎች እንደሚከተለው በአጭሩ ቀርበዋል፡፡

የፕሮግራሙ አላማ

1
በከተሞች ከድህነት ወለል በታች የሚገኙትን ዜጎች በመለየት በፕሮግራሙ እራሳቸውንና ቤተሰባቸውን በምግብ እንዲችሉ ማድረግ፡፡

የሪፖርቱ አላማ

የቤተሰብ ምዝገባውና ልየታው የደረሰበትን ደረጃ በመመልከት ለቀጣይ ትምህርት መውሰድ፡፡

2. ሪፖርቱ የሚያተኩርባቸው ዋና ዋና ነጥቦች


1 አጠቃላይ የኮሚቴ አወቃቀርን በተመለከተ
የወረዳ ካውንስል ፡-የወረዳ ካውንስል በተመለከተ መካተት ያለባቸውን ፅ/ቤችና ባለድርሻ አካላትን በማካተት ኮሚቴውን በማዋቀር ወደ
ስራ መግባት ተችሎዋል፡፡ በካውንስሉ የተሰሩ ስራዎችንም ለመገምገም ተሞክሮዋል፡፡

የስራ ዕድል ፈጠራና እና የምግብ ዋስትና የስራ አመራር(ማኔጅመንት) MCC በተመለከተ፡- በኮሚቴው መካተት ያለባቸውን
ፅ/ቤቶችና ባለድርሻ አካላትን በማካተት ኮሚቴውን የማወቀር ስራ ተሰርቶዋል፡፡ኮሚቴውም ስራው የደረሰበትን ደረጃ በየወቅቱ

በመገምገመና የሚላኩ የምዝገባ መረጃዎችን የጋራ በማድረግ መረጃዎችል መላክ ተችሎዋል፡፡

የቴክኒክ አስተባባሪ ኮሚቴ(TCC) በተመከተ፡-የቀጥታና የማህበረሰብ አቀፍ ስራዎች የቴክኒክ አስተባባሪ ኮሚቴ ፅ/ቤቶችና ከባለድርሻ
አካላት የተውጣጣ ኮሚቴ ለማዋቀር ጥረት ተደርጎዋል፡፡የኑሮ ማሻሻያ የቴክኒክ ኮሚቴ የማዋቀር ስራ አልተሰራም፡፡

የቀጠና የልየታ ኮሚቴ በተመለከተ፡- ባሉን 8 ቀጠኛዎች የጤና ኤክስቴንሽኖችን ጨምሮ 9 የኮሚቴ አባላትን በማወቀር የነዋሪ
ምዝገባና የልየታ ስራዎችን መስራት ተችሎዋል፡፡ በጥቅሉ 72 የልየታ ኮሚቴዎች በስራው መሳተፍ ችለዋል፡፡

2
የቅሬታ እና አቤቱታ ሰሚ አካል በተመለከተ፡- ባሉ 8 ቀጠናዎች ከ 5-7 የሚሆኑ የኮሚቴ አባላትን ለማዋቀር ተሞክሮዋል፡፡ 6 አባላት
ያሉት የወረዳ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አባላትን ማወቀር ተችሎዋል፡፡በጥቅሉ 54 የኮሚቴ አባላትን በማዋቀር ቅሬታ አፈታት ላይ ስልጠና

እንዲወስዱ ተደርጎዋል፡፡

2 የልየታና የምዝገባ ሂደቱን በተመለከተ በጥካሬና በድክመት የሚገለጽ

የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች

ጠንካራ ጎን

 የነበረው የክፍለ ከተማና የወረዳ ድጋፍና ክትትል አግባብ


 የነበረው የስራ ተነሳሽነት
 ኮሚቴው ተከፋፍሎ የመስራት ሁኔታ
 ኮሚቴው ለስራው የሰጠው ትኩረት
 ችግሮችን ቶሎ አይቶ ለማስተካከል መረባረብ
 የመረጃ አያያዝ

ደካማ ጎን

 የአንዳንድ ኮሚቴዎች የመንጠባጠብ ( በሰዓትያለመገኘት) ሁኔታ

3
 የመረጃ አያያዝ ችግር
 መረጃዎችን ከስር ከሰር ወደ አጀንዳው ያለማስፈር
 መረጃዎችን ሳያጠሩ መስጠት
 የመረጃ የጥራት ችግር

በኮ/ቀ/ከ/ከተማ ወረዳ 12 የስራ እድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ አጠቃላይ የነዋሪዎች
ምዝገባ መረጃ
 ሁሉም የኮሚቴ
የቤተሰብ ኃላፊ የቤተሰብ ብዛት መስራት የሚችሉ መስራት የማይችሉ
ቀጠና አባወራ እማወራ ድምር ወንድ ሴት ድምር 18-35 36-60 ድምር በዕድሜ በጤና ድምር አባላት

1 75 64 139 237 315 552 246 106 352 189 11 200


2 114 61 175 351 362 713 307 168 475 202 34 236
3 160 85 245 604 626 1230 511 265 776 445 9 454
4 408 287 695 1260 1394 2654 1153 505 1658 926 57 983
5 751 377 1128 2213 2211 4424 2093 823 2916 1740 2 1742
6 248 96 344 780 714 1494 697 307 1004 489 1 490
7 298 299 597 1217 1401 2618 1157 571 1728 892 5 897
8 303 204 507 1039 1224 2263 968 500 1468 779 8 787
ድምር 2357 1473 3830 7701 8247 15948 7132 3245 10377 5662 127 5789
በተገኙበት ልየታውን በተመለከተ ለኮሚቴዎች ኦረንቴሽን በመስጠት ልየታውን የሚሰሩበት ቦታ እድር ቤትና ኮሚኒቲ ፖሊስ በማዘጋጀት

መመሪያውን በመከተል የደረጃ 1 እና የደረጃ 2 ተጠቃሚሆን መለየት ተችሎዋል፡፡

 እያንዳንዱ የምዝገባ መረጃ በሶፍት ኮፒና በሀርድ ኮፒ በማዘጋጀት በተጨማሪም መረጃዎችን በፎቶ ግራፍ የመደራጀት ስራ ተሰርቶዋል፡፡

4
 የተለዩ ተጠቃሚዎችን በቀጠናው አደረጃጀቶች በማስተቸት መስተካከል አለባቸው የተባሉትን ተጠቃሚዎች ደረጃ የማስተካከል ስራ

ተሰርቶዋል፡፡

3 ከባለድርሻ አካለት ጋር የነበረ ቅንጅታዊ አሰራር በተመለከተ የነበረ ጥንካሬና ድክመት

ጥንካሬ

 ሁሉም እቅድ ለማዘጋጀት መሞከራችው


 ስራዎችን ተረድቶ ለመደገፍ ያደረጉት ጥረት
 በቀናነት ወስዶ ስራዎችን ለመስራትና ለመደገፍ ያደረጉት ጥረት

ድክመት

 ስራው ላይ በእኩል አቅም አለመንቀሳቀስ


 ቋሚ የግንኙነት ጊዜ አለማስቀመጥ
 በተለያዩ ስራዎች የመጠመድ

ከባለድርሻ አካላት የተሻለ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ሰራተኛና ማህበራዊ እና የጥቃቅንነቀ አነስተኛ ፅ/ቤት ሲሆኑ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ወጣ ገባ የሚሉ

ናቸው፡፡ አካባቢ ጥበቃ ምንም ተሳትፎ ያላሳየ ባለድርሻ ነው፡፡

4. የመረጃ አያያዝ በተመለከተ

አጠቃላይ የነዋሪ ምዝገባው እና የተጠቃሚ ልየታ መረጃዎች በሶፍትና በሀርድ ኮፒ በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው አካላት በመስጠት ሀርድ ኮፒዎችን

በኬንት አስሮ ማስቀመጥ ተችሎዋል፡፡ አስፈላጊ ማኑዋሎችን እና መመሪያዎችን በአግባቡ በየዘርፉ በማደራጀት ለማስቀመጥ ተሞክሮዋል፡፡ አጠቃላይ

የተደረጉ የመድረኮች አቴንዳንስና ቃለ-ጉባኤዎች በአግባቡ ተይዘዋል፡፡


5
5. ግብዓት ከማሟላት አንፃር

የሰው ኃይል እንዲሟላ ለማድረግ የተለያዩ ጥረቶች የተደረጉ ቢሆንም እስካሁን ቅጥሩ አልተካሄደም፡፡ የቀጠናው የልየታ ኮሚቴዎች ለምዝገባውባ

ለልየታው አመቺ የሆነ እዛው ቀጠናው ውስጥ ያለ እድር ቤትና ኮሚኒዩቲ ፖሊስ በማዘጋጀት የልየታው ስራ በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠናቀቅ

ማድረግ ተችሎዋል፡፡ የቢሮ ግብሃት ሙሉ በሙሉ ማለት ባይቻልም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብሃቶችን ለሟሟላት ተሞክሮዋል፡፡

6. የአካባቢ ልማት የሚሰራባቸው ቦታዎች ከመለየት አንፃር

በአካባቢ ልማት የሚሰሩ ስራዎችን ለመለየት ተሞክሮዋል፡፡ለአብነት የማህበረሰብ አቀፍ ልማት፣የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ፣የክፍትና ዝግ ትቦ ጠረጋ

፣የአረንጓዴ ልማት እና የችግኝ ጉድጓድ ቁፋሮና ተከላ የመሳሰሉ የአካባቢ ልማት ስራዎችን ለመስራት ቦታዎችን የመለየት ስራ ተሰርቶዋል፡፡

7. የድጋፍና ክትትል አግባብ በጥንካሬ እና በድክመት

በጥንካሬ

6
 የክፍለ ከተማው ድጋፍ የተሻለ
 የወረዳ ዋና አመራር ድጋፍ
 የሰራተኛና ማህበራዊ እና የጥቃቅን ፅ/ቤት ድጋፍ የተሻለ መሆን

በድክመት

 ክ/ከተማው ወጥ የሆነ ድጋፍ አለማድረግ


 ወረዳ ላይ ውስን ፅ/ቤትና አመራር ድጋፍ
 የአጠቃላይ አመራር ድጋፍ ውስን መሆን

8. በአጠቃላይ በእያንዳንዱ ሂደት

ያጋጠሙ ችግሮች

 የግብሃት ችግር
 የቢሮ ችግር
 የሰው ኃይል ችግር

ችግሮቹ የተፈቱበት አግባብ

 ከተለያዩ ፅ/ቤቶች ግብሃት በማሰባሰብ


 ከሌላ ቢሮ ጋር በጋራ በመስራት እና ክፍት ቢሮ ፈልጎ በመጠቀም
 ከሌሎች ፅ/ቤቶች የሰው ኃይል መዋስ

አጠቃላይ ስራው ሲመራ የነበረበት አግባብ በጥንካሬ እና በድክመት

በጥንካሬ

7
 ቀጠና ድረስ ወርዶ ለመደገፍ የተደረገው ጥረት

 ከኮሚቴዎች ጋር ተዋህዶ ለመስራት የተደረገው ጥረት

 ለኮሚቴዎች ውሃና ቆሎ ለማዘጋጀት ጥረት መደረጉ

 መረጃዎችን በየቀኑ ለማደራጀት መሞከሩ

በድክመት

 ለሁሉም ቀጠናዎች እኩል ድጋፍና ክትትል አለማድረግ

 ለሁሉም ቀጠናዎች አመቺ የሆነ ቦታ አለማዘጋጀት

 ከክፍለ ከተማና ከወረዳ ወጥ ሆነ ድጋፍ አለማድረግ

 ደከም ያሉ ኮሚቴዎችን ለይቶ ድጋፍ ያለማድረግ

የዳግም ምዝገባና የባንክ አካውንት የማውጣት ስራውን በተመለከተ

8
አጠቃላይ የተመዘገቡ አባወራና እማወራ በስራቸው የሚገኙ የቤተሰብ አባላቸውን ለፕሮግራሙ የመምረጥና የተመረጡትን
የማስመዝገብ ስራ ለ አንድ ወር ያክል ሲሰራ ቆይቶዋል፡፡ የተመዝጋቢዎችን ድካምና እንግልት ለመቀነስ በማስብ ጎን ለጎን
ተመዝጋቢዎች በአንድ ማዕከል የባንክ አካውንት እንዲያወጡ ለማድረግ ተሞክሮዋል፡፡

የታዩ ደካማና ጠንካራ ጎኖች

በጠንካራ ጎን

 ምዝገባውን በጥራት ለመስራት የተደረገው ጥረት


 የተመዝጋቢዎችን መረጃ ለሟሟላት የተደረገው ጥረት
 የፈፃሚዎች የስራ ተነሳሽነት

በደካማ ጎን

 ምዝገባው በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ አለመጠናቀቁ


 ባንኮን በሰዓት ተገኝተው አለማስተናገድ
 የባንክ አካውንት ለከፈቱት ተመዝጋቢዎች ቶሎ የባንክ ቡክ ያለማዘጋጀት

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወራዳ 12 አስተዳደር የ 2 ተኛ ዙር የምግብ ዋስትና ተጠቃሚዎች ምዝገባ አፈፃፀም መረጃ
የተመዘገበ የባንክ ሂሳብ የከፈተ
  ቀጥታ ድጋፍ አካባቢ ልማት ቀጥታ ድጋፍ አካባቢ ልማት አጠቃላይ
9
የምዝ   የተጠቃሚ ብዛት       የተጠቃሚ ብዛት      
ገባ
እቅድ
በተጠ አባ እማ አባ እማ ድም እማ አባ ድም አባ እማ ድም አባ እማ ድም
ቃሚ ወራ ወራ ድ ወ ሴ ድ ወራ ወራ ር ወ ሴ ድ ወራ ወራ ር ወራ ወራ ር ወራ ወራ ር
2625 30 107 137 77 167 244 206 351 557 773 1028 1801 30 107 137 206 351 557 236 458 694
12/10/2010 ዓ.ም 0 3 3 2 3 5 7 11 18 25 30 55 0 3 3 7 11 18 7 14 21
13/10/2010/ዓ.ም 0 0 0 0 0 0 4 12 16 21 29 50 0 0 0 4 12 16 4 12 16
14/10/10 ዓ.ም
 
  0 4 4 1 4 5 3 12 15 4 12 0 0 4 4 3 12 15 3 16 19
      1 2 3 3 7 10 0 3 3 4 5 9 1 2 3 0 3 3 1 5 6
    0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0
    0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0
    0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0
ድምር   31 116 147 83 181 264 220 389 609 827 1104 1931 31 116 147 220 389 609 251 505 756

በአጠቃላይ እንደ ወረዳ የተጠቃሚ ኮታችን 2625 ሲሆን አሁን በምዝገባና አካውንት በማውጣት የደረስነው 2195 ተጠቃሚዎች
ሲሆን 430 የሚሆኑ ተጠቃሚዎች በቀጣይ የሚመዘገቡና አካውንት የሚያወጡ ይሆናል፡፡ የተቀሩት በፍላጎትና በተለያዩ
ምክንያቶች መመዝገብ አልቻሉም፡፡

የ 1 ለ 5 እና የ 1 ለ 30 አደረጃጀት በተመለከተ

ዳግም ምዝገባ እና አካውንት የከፈቱ አባወራና እማወራ በ 1 ለ 5 እና በ 1 ለ 30 የማደራጀት ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡የማደራጀት


ስራው በሚቀርባቸው ቦታ ይሆን ዘንድ አደረጃጀቱ በየቀጠናው ለማድረግ ተሞክሮዋል፡፡ነገር ግን በርካታ መጠናቀቅ የሚገባቸው
ስራዎች ይቀራሉ፡፡
10
11

You might also like