You are on page 1of 1

የውስጥ ማስታወሻ

ቁጥር ቤ/መ/ል/ግ/009/15
ቀን 09/06/2015 ዓ.ም

ለ፡ ህግ እና ኢንሹራንስ መምሪያ

ከ፡ ቤቶችና መሰረተ ልማት ግንባታ

ጉዳዩ፡- በከሰም ስኳር ፋብሪካ የግንባታ ስራ ዉለታ ስምምነት ጥሰት በፈፀሙት ሥራ ተቋራጮች የህግ ሂደት ያለበት ደረጃ መረጃ መጠየቅን
ይመለከታል፤

የከሰም ስኳር ፋብሪካ ጥር 9 ቀን 2015 ዓ.ም ደ.ቁጥር 01/13/10.5 በተጻፈ ደብዳቤ፣ በአሊቤቴ እና ደሆ መንደሮች የዉሃ ማጣሪያ ግንባታ ስራ
ለማከናወን ዘለቀ ረዲ የዉሃ ስራ ተቋራጭ እንዲሁም በዋና ከተማ የመኖሪያ እና አገልግሎት መስጫ ግንባታ ስራ ለማከናወን የኦሮሚያ
ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ዉለታ በመዉሰድ ስራ ላይ ቢቆዩም በዉለታዉ መሠረት ባለመንቀሳቀሳቸዉ እና ግሩፑን ጉዳት ላይ በመጣላቸዉ ጉዳዩ
እልባት የሚያገኝበት እና ወደ ቀጣይ ስራ የሚገባበት ሁኔታ እዲመቻች ጠይቀዋል፡፡

ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ጥር 7 ቀን 2013 ዓ.ም ደ.ቁጥር ቤ/መ/ል/ግ/028/13 በተጻፈ ዉስጥ ማስታወሻ በአሊቤቴ እና ደሆ መንደሮች የዉሃ
ማጣሪያ ግንባታ ስራን በተመለከተ ዘለቀ ረዲ የዉሃ ስራ ተቋራጭ እና የካቲት 8 ቀን 2013 ዓ.ም ደ.ቁጥር ቤ/መ/ል/ግ/039/13 በተጻፈ ዉስጥ
ማስታወሻ በዋና ከተማ የመኖሪያ እና አገልግሎት መስጫ ግንባታ ስራን በተመለከተ የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ከዉለታ መጣስ ጋር
በተያያዘ በህግ አግባብ በክፍላችሁ በኩል ታይቶ ዉሳኔ እንዲያገኝ እና በግሩፑ በኩል ወደ ቀጣይ ስራ ለመግባት እንዲቻል ደጋፊ ሰነዶች በማያያዝ
መላካችን ይታወሳል፡፡

ስለሆነም የተቋረጡትን ግንባታዎች መፍትሄ ሰጥቶ ወደ ቀጣይ ስራ እንቅስቃሴ ለመግባት እና ለከሰም ስኳር ፋብሪካ ተገቢዉን ምላሽ መስጠት
ያመች ዘንድ በእናንተ በኩል የዘለቀ ረዲ የዉሃ ስራ ተቋራጭ እና የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የህግ አፈጻጸም ሂደቶች የደረሰበት ደረጃ
ግብረመልስ ይሰጠን ዘንድ እጠይቃለን፡፡

ከሠላምታ ጋር

አባሪ፡- ሁለት(2) ገጽ የከሰም ስኳር ፋብሪካ ደብዳቤ


አራት(4) ገጽ ከስራ ክፍላችን የተላከ የዉስጥ ማስታወሻ

ግልባጭ
 ለኦፕሬሽንና ፕሮጀክት አስተዳደር ዘርፍ (ያለ አባሪ)
 ለፕሮጀክት አስተዳደር መምሪያ (ያለ አባሪ)
 ለቤቶችና መሰረተ ልማት ግንባታ (ያለ አባሪ)
ኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ

You might also like