You are on page 1of 1

ፍርድና ምህረት

የእግዚብሔር ፍረድ ሆነ የእግዚአብሔር ምህረት ከሰው አስተሳሰብ የላቀ ነው የእግዚአብሔርን ምህረት ሆነ


የእግዚአብሔርን ፍረድ በሰው ወይም በአለም ዳኝነት ሊዳኝ እና ሊበየንበት አይችልም በምድር ፍረድ አሰጣጥ ህደት
ከፍተኛ እና ዝቅተኛ የፍርድ መስጫ ቦታዎች እና የህግ ብያኔ አሰጣጥ ዜደ አለ ይህም ካልተሳሳትኩ አንደኛ ደረጃና ሁለተኛ
ከዝያም ከፍተኛ መዓከላዊ እያላ የሚቀጥል ነው ማለት ነው ሁሉም ከባድ ፍርዶች ከዝህ ከከፍተኛው ወይም ከማእከላዊ
ፍርድ አያመልጡም እናም ሁሉ ብያኔያቸውን በአግባቡ ይቀበላሉ ታዲያ ይህ እግዚአብሔር ጋር ሚሰራ ይመስላቸዋል
አይሰራም ምክንያቱም እርሱ የሁሉ የባላይና ዋና ፍርድ ሰጪ እና ሰልጣን ሁሉ በሱ ፍርድ ትክክለኛነት ሳያመነቱ
ሚታሰሩበት ፍርዱ ለፍርድ ምህረቱም ለዳኝነት የማይቀርቡበት የሁሉ ባለስልጣን እና የፍረድ ሚዛን የማይዛቡበት
እውነተኛ ፈራጅ እና እውነተኛ ደግሞ ማህሪ አምላክ ነው።

ታዲያ

በሰው ፊት የእግዚአብሔር ፍረድ ሆነ ምህረት ሊዳኝ ይችላልን?

አንድ ሰው ከሰው ጋር ይጋጭና ባጣም አዝኖ ወደ ቤቱ ይገባና እንዲህ እያላ ይፀልያ አምላኬ ሆይ እኔን እንደዝ ያረገኝን
ሰው አሁን ወርደ ፍረድበት እባክ ሰለኔ የምትዋጋ አምላክ መሆንህን አውቃለው በቃ አሁን ውረድ በሞት አንሳው ካልሆነ
በሽታ ላይ ጣላው እያለ እየጮኸ እያለቀሰ በሃይል ይፀልያል የዛኔ አንድ ጎረበቱ ይህን ፀሎት ይሰማና ወደ ቤቱ ጎራ ይላል
ሰውየው አጋጣሚ ሆኖ በእምነቱና በመንፈሳዊ ህይወቱ ጠንካራና ደግሞም የበሰለ እውቀት ያለው ሰው ነው።ከዝያም
እቤቱ ከገባ በኋ ሰለምታ ሰቶ ሰለተፈጠረው ነገር ከሰውዬው ይረዳል ሁኔታው አሻሚ ሆኖ ያገኘዋል ነገር ግን በጉዳዩ
ምንም ለማለት አልፈለግም ግን ፀሎት ተገቢ አይደለም ብሎ ጀመረ ሰውየውም እንዴት ብሎ እንደማኩረፍና የባላንጣው
ደጋፊ አድርጎ ወደመሳል ደረስ የዛኔ ሰውዬው እንዲህ ይለዋል ወንድሜ የእግዚአብሔርን ፍርድ ሰው ላይ ሰትጠራ
ራስህንም ስህትት አልባ ለማድረግ ስትሞክር የሰማሁ መሰለኝ ወንድሜ እግዚአብሔር መፍረድ ሲጀምር እኮ ለማንም
አይመለስም እግዚአብሔር ሲፈርድ ዘመዱ እውነት ብቻ ነች ራሱም እውነት ሰለሆነ ስለዝህ ፍርዱን ከጠሪው ሊጀምር
እንደሚችል ለምን መረዳት እና ማስተዋል አቃተ ምናልባት አንተ የእግዚአብሔርን ፍርድ በሰው አፈራረድ ወይም በአንተ
አስተሳሰብ ሰለከው ለአንተ ከልፈረድ ፍርዱ ስተት ነው ብለ ልትደመድም ትችል ይሆናል እርሱ ግን ፍርዱ ለፍርድ
የማይቆምለት የታመነ እና እውነተኛ ዳኛ መሆኑን መዘንጋት እንዳትረሳ ስለዝህ የእግዚአብሔርን ፍረድ መቼም በሰው
አይምሮ ልትገምት እና ወይም ልትደረስበት ወይም ልታውቀው ለምን ይህን አደረገ ብለ ልትጠይቀው የማትችለው ፍርድ
ነው በነገራችን ላይ ምህረቱም ቢሆን እንደዛው ነው ግን የሚሻል በዘንክበት ሰው ላይ የእግዚአብሔርን ፍርድ ከምትጠራ
ለሱም ቢሆን ላንተም እግዚአብሔር ምህረት እንዲያደርግላቹ ምህረቱን ብትጠራ ይሻልሃል የበጅሃልም ምክንያቱም
ምህረት ከህይወት ይሻላልና ምን ማለት ነው ምህረት ሰለተሰጠ ነው በህይወት መኖር እንኳን የቻልከው እና አንተ እንኳን
በእግዚአብሔር ምህረት እየኖርክ እንዴት ሰው ላይ እግዚአብሔር ይፈረድ እያልክ ምትፀልየው ምናልባት እኮ ፍርዶ ሆነ
ቢባል እንኳን አንተ ላይ እግዚአብሔር ቢፈርድና ያሰው ነፃ ቢሆን እግዚአብሔርን አንተ በሳልከው ምስል ወይም ባንተ
መነጽር ኢፍታዊ ነው ፍርዱም ትክክል አይደለም ልትል ነው።ነገር ግን የእግዘብሔርን ማወቅ ተሰቶናል ነገር ግን ደግሞ
ከአእምሮአችን በላይ መሆኑን አንዘንጋ በሰው አስተሳሰብ ሚዛን እና በሰው የዳኝንት ጥግ እግዚአብሔርን መላካት
አንችልም ደግሞም አይቻለንም ይህን ስናውቅና ስንረዳ ከእንደዚህ አይነት ፀሎትና አስተሳሰብ ነፃ እንሆናለን
እግዚአብሔርንም በእግዚአብሔርነቱ አንጂ እኛ ወይም ሰዎች በጭንቅላታችን የሳሉልንን እግዚአብሔርን ከማወቅ
እንድናለን እግዚአብሔር በቃሉ ሰለራሱ በገለጠልን መልኩ እግዚአብሔርን እንድናውቀው እግዚአብሔር ይርዳን
ፀጋውንእናምህረቱንም ያብዛልን አሜን።

You might also like