You are on page 1of 71

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ

የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት


ማስፈፀሚያ ማንዋል

አቅራቢ
ተፈራ ሙሉነህ
አማካሪ
አዘጋጆች
● ተፈራ ሙሉነህ
● ካህሳይ ወ/ተክሌ
● ዝናሽ ሰለሞን
● ኤርሚያስ ጌትነት
● እንግዳ ዳኜ
● ኤፍሬም ሳህሌ
● መሐመድ አብዱራህማን
● ዘበናይ ሸገና

2
የማንዋሉ ይዘት
ክፍል 1 ፦ አጠቃላይ መግቢያ

ክፍል 2፦ የዋና ዋና ጽንሰ-ሃሳቦች

ክፍል 3፦ የነባራዊ ሁኔታ ዳሰሳ

ክፍል 4፦ የአስፈጻሚ አካላት ሚና

ክፍል 5፦ የአስተግባሪ አካላት ሚና

ክፍል 6፦ የክትትል፣ ድጋፍ፣ ሪፖርት፣ ግምገማና ግብረ-መልስ

እና የአደረጃጀቶች ስርዓት

ክፍል 7፦ የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት መመዘኛ መስፈርት

3
መግቢያ
● የከተማ አስተዳደሩ ከተማዋን ሁለንተናዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ በማስገባት
ዜጎቿ የዚህ ለውጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ዘርፈ-ብዙ ተግባራትን
በማከናወን ላይ መሆኑ፣
● በዚህ ሂደት በርካታ ለውጦች መታየታቸው፣
● ይሁንና የህብረተሰቡን ፍላጎት በተገቢው ማሟላት እና የተገልጋዩን እርካታ
በሚፈለገው ልክ ማሳደግ ያለመቻሉ፣
● ሰለሆነም ለውጥ ማምጣት ያስፈልጋል፣
 አሁን ያሉ ችግሮችን በተገቢው በመረዳት፣ በዘላቂነት መፍታት እና ቀጣይነት
ያለው መሻሻል በማምጣት ውጤታማ አገልግሎት አሰጣጥን በከተማችን
ዕውን ለማድረግ ይህ ሰነድ ተዘጋጅቷል።

4
መነሻ ሁኔታ
● የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራም
 የአገልግሎት አሰጣት ማሻሻያ ንዑስ ፕሮግራም
● አስፈፃሚ አካላትን እንደገና ለማደራጀት የወጣው አዋጅ 74/14
 የወል ስልጣን
 ለቢሮው የተሰጠ ስልጣን
● የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል እየተተገበሩ ያሉ መሳሪያዎችና አሰራሮች ያመጡት
ለውጥ ከተገልጋይ ፍላጎት አኳያ ሲታይ ገና ብዙ የሚቀረው መሆኑ

5
የማኑዋሉ ዓላማ
● ዋና ዓላማ
 በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለህብረተሰቡ
የሚያቀርቡት አገልግሎት ውጤታማ በሆነ አሰራር በመምራት እና ቀልጣፋና
ውጤታማ አገልግሎት በመስጠት የዜጎችን እርካታ ማረጋገጥ እንዲችሉ
ለማድረግ ነው፡፡

6
ዓላማ …
● ዝርዝር ዓላማ
 በመንግስት ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ተደራሽ፣ ቀልጣፋ እና
ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል፤
 በአገልግሎት አሰጣጥ ድርሻ ያላቸው ሁሉም አካላት የሚኖራቸውን ሚና በተገቢው በመረዳት
ውጤታማ በሆነ መልኩ መወጣት እንዲችሉ ለማድረግ፤
 የክትትልና ድጋፍ ተግባር ችግር ፈቺ እና ውጤታማ እንዲሆን በማድረግ የአገልግሎት
አሰጣጡን ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሻሻል፤ እና
 ተቋማት አዳዲስ አሰራሮችንና የለውጥ መሳሪያዎችን በመለየትና በመተግበር ቀጣይነት ያለው
የአገልግሎት መሻሻል እንዲመጣ የተደራጀ አመራር ለመስጠት ነው።

7
ክፍል ሁለት

የአገልግሎት አሰጣጥ ጽንሰ-ሃሳብ

8
ጽንሰ-ሃሳብ …

አገልግሎት
● አገልግሎት የተገልጋዮችን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ ዓላማ ተኮር ተግባራት ሲሆኑ
○ ስኬታማና ኢኮኖሚያዊ ቅልጥፍናን በተላበሰ መልኩ የሚከናወኑ
○ በጊዜ፣ በመጠን፣ በወጭና በጥራት እንዲሁም በተገልጋይ እርካታ ሊለኩ የሚችሉ
○ በአገልግሎት ተቀባዩ ዘንድ ፋይዳ ያለው እሴት የሚጨምሩ
○ በአገልግሎት አቅራቢው የሚከናወኑ ተግባራት ናቸው።

9
አገልግሎት …

10
ጽንሰ-ሃሳብ …

11
ጽንሰ-ሃሳብ …
ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት አምስት ቁልፍ አስቻዮች

12
ጽንሰ-ሃሳብ …
የሰው ሀብት ልማት
● ለአንድ ተቋም ከሚኖሩት ሀብቶች መካከል እጅግ ወሳኝ የሆነው ሀብት ነው።
● ያለንን የቴክኖሎጂም ይሁን ሌሎች ተቋማዊ አቅሞች ወደ ሥራና ውጤት የሚቀይር
ሃይል ነው።
● ስለሆነም
 አሁናዊም ሆነ የወደፊት ፍላጎት ለማሟላት በሚያስችለን ሁኔታ መገንባቱን፤
 ያለንን አመራርና ፈፃሚ ብቃትና ክህሎት ከተቋም ተልዕኮ አኳያ የተቃኘ መሆኑን
 አቅም ለመገንባት የሚያስችሉ ቀላልና አዋጪ የሆኑ ስልቶች ተግባራዊ እየተደረጉ
መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

13
የሰው ሀብት …

14
ጽንሰ-ሃሳብ …
የስራ አመራር ስልቶች ምንነት
● መሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ (BPR)
 ከተቋሙ ውስጥም ሆነ ውጭ ለሚከሰት የለውጥ ፍላጎት ፈጣን ምላሽ በመስጠት፣
 ለውጡን ከሚፈለገው አዲስ አሰራር ጋር ፈጥኖ በማላመድ፣
 አሰራሮችንና አደረጃጀቶችን በማሻሻል፣
 የመንግስት ተቋማት ያላቸውን ውስን ሀብት በአግባቡ በመጠቀም፣
 የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋና ውጤታማ /Efficient and effective/ በማድረግ
 የተገልጋዩን እርካታ ከፍ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት የለውጥ መሳሪያ

15
ስልቶች …
● ሚዛናዊ ስራ አመራር/BSC
 የተቀናጀ የስትራቴጂያዊ ዕቅድ ሥራ አመራር፤
 የተግባቦትና
 የመለኪያ ስርዓትን አጣምሮ የያዘ የለውጥ መሳሪያ ነው፡፡
● የዜጎች ስምምነት/ Citizen Charter
 ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል እና
 በተገልጋዩ ህብረተሰብና በመንግስት ተቋማት መካከል ስራን መሰረት ያደረገ
ጤናማና መተማመን ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እንዲኖር የሚያስችል የአሰራር
ስርዓት ነው፡፡

16
ጽንሰ-ሃሳብ …
ተቋም ተኮር አገልግሎት ማሻሻያ ስልት መንደፍ
● አገልግሎት አሰጣጥ በቀጣይነት ለማሻሻል የሚቻለው
 ተቋማት የተገልጋዮቻቸውን ፍላጎት በየጊዜው እያጤኑ
 አሰራራቸውን አደረጃጀታቸውንና የሰው ኃይላቸውን እያሻሻሉ
የሚሄዱበትን አሰራር ተግባራዊ ሲያደርጉ ነው፡፡
● ተቋማት እንደራሳቸው ባህሪ አገልግሎት አሰጣጡን የሚያሻሽሉ የስራ አመራር
ስልቶችን በመቅረጽ፣ በማጥናትና ተግባራዊ በማድረግ አገልግሎት አሰጣጡን
ማሻሻል ይችላሉ፡፡

17
ጽንሰ-ሃሳብ …
ቅሬታ አቀባበልና አፈታት
● ቅሬታዎች ተቀብሎ መፍታት የተቋምን የአሰራር ስርዓት ለማሻሻል ዕድሎችን
ይሰጣል

● ስለሆነም የቅሬታ አቀባልና አፈታት ስርዓት የተገልጋይን ቅሬታ ወይም ትችት


 ሳይንሳዊ በሆነ ዘዴና
 ርህራሄ በተሞላው መንገድ ማስተናገድ ይገባል።

18
ጽንሰ-ሃሳብ …
የባለድርሻ አካላትና የዜጎች ተሳትፎ
● ዜጎች የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ጥቅም ላይ ያልዋሉ ሀብቶች ናቸው
● የዜጎች ተሳትፎ፦
 በዜጋውና በመንግስት አስተዳደር መካከል ሚዛን ያለው ግንኙነትን ያዳብራል፤
 አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ይረዳል፣
 የአገልግሎት ተደራሽነትና ፍትሃዊነትን ያሻሽላል፡፡
 ዜጎች ፍላጎቶቻቸውን፣ ምርጫዎቻቸውን የሚገልጹበትንና መብቶቻቸውን
የሚያስከብሩበትን እድል ይፈጥራል፡፡
● ስለሆነም ተቋማት፦
 ማን በምን ጉዳይ ላይ እንደሚሳተፍ በመለየት
 የሚሳተፍበትን መስፈርት በማዘጋጀት
 የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ለመፍታት የጋራ መድረክ ፈጥሮ መፍትሄ መስጠት
ያስፈልጋል፡፡

19
ጽንሰ-ሃሳብ …
የመረጃ ተደራሽነት
● የህገ-መንግስት ድንጋጌዎች
 ማንኛውም ዜጋ መረጃ የማግኘት ህገ-መንግስታዊ መብት አለው
 የመንግስት አሰራር ለህዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ መከናወን አለበት
● ስለሆነም ማንኛውም የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋም
● ለዜጋው ምቹ በሆነ መንገድ
 በጽሑፍ፣
 በምስል፣
 በኦዲዮ እና ቪዲዮ
 አማራጮችን በመጠቀም
- ድረ ገጽ፣ - የኢንፎርሜሽን ዴስክ፣
- ፖስተር፣ - ብሮሸር፣
- መጽሄት፣ ወዘተ.)
በመጠቀም መረጃ መስጠት አለበት፡፡ 20
ክትትል
አንድ ዕቅድ የታለመለትን ግብ በሚፈለገው ደረጃ ማሳካቱን በሂደት ውስጥ
የሚያጋጥሙ ችግሮችን እና የችግሮቹን ምንጭ በማወቅ ወቅታዊ የመፍትሄ
እርምጃ ለመውሰድ በተከታታይነት የሚደረግ የአፈፃፀም ወይም የአሰራር
ክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ
ዳሰሳ/ፍተሻ ነው፡፡

ድጋፍ
በክትትልና ግምገማ የታዩ የተቋማት የአፈፃፀም ደረጃዎችን በመለየት
የነበሩ ጥንካሬዎች የበለጠ እንዲሻሻሉ እና መስተካከል ለሚገባቸው
ክፍተቶች የመፍትሄ ሀሳቦችን በማቅረብ እንዲታረሙ እገዛ
ግምገማ
የምንሰጥበት አግባብ ነው፡፡
የተጣሉ ግቦች የታለመላቸውን ዒላማ መምታታቸውን ሥራው
ከተጠናቀቀ በኃላ የሚመጣው አዎንታዊ/አሉታዊ ተጽዕኖ ምን
እንደሚመስል የሚያመላክት በጥልቀት የሚካሄድ የመረጃ አሰባሰብ፣
ትንተናና ሪፖርት የማቅረቢያ አሰራር ነው፡

21
ክፍል ሶስት

አገልግሎት አሰጣጥ ያለበት ነባራዊ ሁኔታዎች

22
ነባራዊ ሁኔታ …

● በከተማ አስተዳደሩ ዜጋውን ህብረተሰብ ለማገልገል በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እና


አበረታች ውጤት እየተመዘገበ ቢሆንም

● ከተለያዩ ግምገማዎችና የጥናት ግኝቶች መረዳት እንደሚቻለው የአገልግሎት አሰጣጡ


○ በሚፈለገው ደረጃ ያላደገ፣
○ ተገልጋዩን ህብረተሰብ ለምልልስ፣
○ እንግልትና እሮሮ የዳረገ እንደሆነ ነው።

23
ነባራዊ ሁኔታ …
የአመራሩና የሰራተኛው ሁኔታ
● በአመራሩ ላይ በስፋት የሚስተዋለው ክፍተት፦
ስትራቴጂክ በሆነ መልኩ ዕቅድን በክትትልና ድጋፍ፣ በግምገማ፣ ግብረ-መልስ በመስጠት
የመምራት ችግር፤
ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ለሚኖሩ ግድፈቶች የተጠያቂነት ስርዓት ተግባራዊ ያለመደረግ፣
የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል የሚያስችሉ የተለያዩ አሰራሮችን ለይቶ ያለመተግበር፣
በተሞክሮና በስልጠና የተገኘን ዕውቅት ወደ ተግባር የመቀየር ክፍተት እና
ለተገልጋዩ አፋጣኝ እና ወቅታዊ ምላሽ ያለመስጠት የታዩ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

24
ነባራዊ ሁኔታ …
● የመንግስት ሰራተኛው ላይ በስፋት የሚስተዋለው ክፍተት
 የተነሳሽነት መቀዛቀዝና ቸልተኝነት ባህርይ ማሳየት፣
 የራሱን ጥቅምና መብት ሊያገኝ የሚችልባቸውን አማራጮች በማማተር ጊዜውን የሚያጠፋ መሆኑ፣
 የስራ ሰዓትን ለመንግስት ስራ ብቻ ያለማዋልና የአገልጋይነት ስሜት መሸርሸር፣
 ከፍተኛ የሆነ የአመለካከትና የጥገኝነት ስሜት መኖሩ፣
 በተቋሙ የሚታዩ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን መፍታት እኔንም ይመለከተኛል ብሎ ያለመውሰድ፣
 በእቅድ ያለመመራትና ከኃላፊ ብቻ የሚመጡ ተልዕኮዎችን መጠባበቅ፣
 የለውጥ መሳሪያዎችን በዕምነት ተቀብሎ ተግባራዊ አለማድረግ፣
 ራሱን ለማብቃት የሚያደርገው ጥረት ዝቅተኛ መሆኑ፣
 ስራዎችን በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት አለመተግበር በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

25
ነባራዊ ሁኔታ …
● ከሰው ሀብት ልማት አንጻር
 ከመጀመሪያ ዲግሪ በታች የሚገኘው ሰራተኛ 48% ያህል መሆኑ

 በአገልግሎት አሰጣጡ ላይም አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለው የሚያሳይ ነው፤

 ተቋማት የሰው ሀብታቸውን ከየት ተነስተው የት ማድረስ እንደሚፈልጉ ግልጽ የሆነ ዕቅድ

አውጥተው ያለመምራት፤
 በየመስሪያ ቤቶች የሚሰጡ የትምህርትና የስልጠና ፕሮግራሞች

 የተቋሙን ፍላጎትና /ክፍተቶችን መሰረት ያላደረጉና

 መርሃ-ግብርን ለማሟላት ሲባል የሚሰጡ

 ሀብት የሚባክንባቸው ናቸው።

26
ነባራዊ ሁኔታ …

የለውጥ ስራ አመራር መሳሪያዎች ትግበራ ያለበት ደረጃ


●የመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ (BPR) ትግበራ ደረጃ
 በአንዳንድ ዘርፎች ወደታችኛው መዋቅር መውረድ የሚገባቸውን አገልግሎቶችን

ያለመውረድ፣
 ስለአገልግሎት ስታንዳርድ ያለው ግንዛቤ አነስተኛ መሆን፣

 በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት አገልግሎት ያለመስጠት፣

 ስታንዳርድ በየቀኑ እየመዘገቡ አለመሄድ፣

 አገልግሎቶች በስታንዳርዱ መሰረት መሰጠትና አለመሰጠታቸውን በመገመገም የማሻሻያ

እርምጃዎችን ያለመውሰድ …

27
ነባራዊ ሁኔታ …
● የሚዛናዊ ሥራ አመራርና ምዘና ስርዓት /BSC/ ያለበት ደረጃ
 አመራሩና ፈፃሚዉ ትግበራው ውጤት ያመጣል ብሎ በእምነትና በዕውቀት ያለመቀበል፣
 የጠራ የተቋም ስትራቴጂክ ዕቅድ ዝግጅት ላይ እጥረት መኖሩ፣
 በፈፃሚው የስኮር ካርድ ዝግጅት እና ካስኬዲንግ ላይ የክህሎት ክፍተት መኖሩ፣
 በየደረጃው የሚገኘው አመራር የክትትልና ድጋፍ አግባብ ችግር ያለበት መሆኑ ፤
 ከምዘና ስርዓት አተገባበር አንፃር
 የምዘና ስርዓቱን ጥራት ያለማስጠበቅ፣
 በቴክኖሎጂ መደገፍ ያለመቻል፣
 የተቀመጡ አፈጻጸሞችን በተግባር መኖራቸውን ማረጋገጥ ያለመቻል፣
 የተቋም አፈፃፀም በትክክል ሊመዝን የሚችል መስፈርት ማዘጋጀት ያለመቻል፣

28
ነባራዊ ሁኔታ …
● የሚዛናዊ ሥራ አመራርና ምዘና ስርዓት /BSC/ ያለበት ደረጃ
 ተቋማት በወቅቱ ያለመመዘንና አንዳንድ ተቋማት ለመመዘን ፈቃደኛ ያለመሆን፣

 የምዘና ሂደቱን ተከትሎ ተገቢውን የማበረታቻና ተጠያቂነት ስርዓት በመዘርጋት ረገድ ሰፊ

ውስንነት ተስተውሏል
 የሚቀመጡ የአፈጻጸም ውጤቶች በተጨባጭ መሬት ላይ ከሚታየው የአገልግሎት አሰጣጥ

እና ከተገልጋይ እርካታ ጋር የተጣጣመ ያለመሆን፣ …

29
ነባራዊ ሁኔታ …

● የዜጎች የስምምነት ሰነድ/Citizen Charter/ያለበት ደረጃ


 ተቋማት ባስቀመጡት የአገልግሎቶች ስታንዳርድ መሰረት ስለመሰጠቱ ማረጋገጥ
አለመቻላቸው፣
 አንዳንድ ተቋማት ዘንድ ደግሞ የዜጎች ስምምነት ሰነድ ያለማዘጋጀት፣
 ቻርተሩን መሰረት ያደረገ የተጠያቂነት ስርዓት ያለመዘርጋት፣
 ተገልጋዩ በቻርተሩ መሰረት አገልግሎት ሳያገኝ ሲቀር መብቱን ማስከበር እንዳለበት ግንዛቤ
በመፍጠር የተሰሩ ስራዎች አናሳ መሆናቸው …

30
ነባራዊ ሁኔታ …
● የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስርዓትን በተመለከተ
 ተለማጭ/Flexible የቅሬታ አቀራረብ ስርዓት ያለመኖር፤

 የቅሬታ ሰሚ የስራ ክፍሎች እና/ወይም ኮሚቴዎች በቅሬታ አፈታት ስርዓት ላይ ያላቸው

ግንዛቤ አናሳ መሆን፣


 የውሳኔ መዘግየት፣

 ከቅሬታና አቤቱታ መመሪያ ውጪ ከፍተኛ የዲሲፕሊን ቅጣቶችን መውሰድ፣

 አመራሩ በሚሰጠው ውሳኔ ማስተካከያ ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆን …

31
ነባራዊ ሁኔታ …
● የዜጎችና የባለ ድርሻ አካላት ተሳትፎ
 ተቋማት የየራሳቸውን የባለድርሻ አካላትን
o የመለየት፣ የማወያየትና የማሳተፍ
o በሚሰጡት ግብዓት መሰረት አሰራሮችን የማሻሻል እና
o ወቅታዊ የውይይት መድረክ በመፍጠር ውስንነት መኖር
● ከመረጃ ተደራሽነት አንፃር
 ቴክኖሎጂን በመጠቀም ቀላልና ተደራሽ የሆነ የመረጃ ስርዓት ያለመዘርጋቱ
 ተገልጋዩ ወደ አገልግሎት ስፍራ ከመጣ በኋላም ትክክለኛውን መረጃ በመስጠት በአክብሮት
ከመቀበልና ከማስተናገድ ይልቅ እንዳላዩ ማየት በሰፊው ይስተዋላል፡፡

32
ነባራዊ ሁኔታ …
● የክትትልና ድጋፍ እና የሱፐርቪዥን ስራዎች አፈጻጸም
 የክትትልና ድጋፍ ስራዎች በተሟላ መልኩ አለማከናወን፣
 የሚደረጉ የድጋፍ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት በማምጣት ረገድ ውስንነት ያለው መሆኑ፣
 የተቋማት አመራር ለስራው ያላቸው ትኩረት አናሳ መሆኑ፣
 የሚሰጡ ግብረ-መልሶችን በግብዓትነት በመጠቀም ወይም መታረማቸውን በማረጋገጥ ረገድ
ክፍተት መኖሩ፣
 የተጠያቂነት ስርዓትን መዘርጋት አለመቻሉ፣
 ክፍተትን መሰረት ያደረገ የድጋፍ ስርዓት አለመኖሩ እና
 የበላይ አመራሩ ወቅትን ጠብቆ የድጋፍ፣ ግምገማና የሱፐርቪዥን ስራዎችን በማከናወን የስራ
አፈጻጸምን ከማሳደግ አኳያ ክፍተት ነበር

33
ነባራዊ ሁኔታ …

• የክትትልና ድጋፍ እና የሱፐርቪዥን ስራዎች አፈጻጸም


 የድጋፍና ክትትል ሙያተኛ
o ወቅቱ ከሚጠይቀው ዕውቀት፣ ክህሎትና ብቃት እንዲሁም የቴክኖሎጂ ደረጃ ጋር እራሱን
ማዘመን አለመቻሉ፣
o የተቋማትን መሻሻል /Progress/ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመረዳት ፍላጎትን መሰረት ያደረገ ክትትልና
ድጋፍ ያለማድረግ፣
o ተቋማት የሚፈልጉትን ድጋፍ ምን መቼ እንዴት መተግበር እንዳለበት ባለመረዳት ለሁሉም
ተቋም ተመሳሳይ ድጋፍና ክትትል ማድረግ፤
o ሙያዊ ስነ-ምግባርና የስራ ግብረ ገብነት ተላብሶ ለውጤት ከመስራት ይልቅ ለኮታ/ለሽፋን ብቻ
መንቀሳቀስ በክፍተት የሚቀመጥ ነው፡፡

34
ነባራዊ ሁኔታ …

● የጥናት ውጤታማነትን ከማሳደግ አንፃር


 በከተማ አስተዳደሩ በሁሉም ዕርከን አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል የሚደረጉ

ጥናቶች፦
 ሲጠናቀቁ ለሚመለከተው አካል ያለማቅረብ፣

 ግኝቶችንና ምክረ-ሃሳቦችን በመጠቀም አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል በግብዓትነት

ለመጠቀም የሚደረጉ ጥረቶች ብዙም አይስተዋሉም።

35
ክፍል አራት

አገልግሎትን ውጤታማ ለማድረግ የአስፈፃሚ ተቋማት ሚና

36
1. የተቋማት ሚና
● ከሰው ሀብት ልማት አንጻር
 የሰው ሀብቱን ቀጣይነት ባለው መልኩ ማብቃት
o የሰራተኞችን የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተት ዳሰሳ ማድረግ
o ቢያንስ በአመት ሁለት ጊዜ
 የአመለካከት
 የአቅም ክፍተታቸውን የሚሞላ ስልጠና መስጠት
o ይህንንም ተግባር አቅዶ መንቀሳቀስ

37
የተቋማት ሚና …
● ከሚዛናዊ ስራ አመራር (Balanced Scorecard) አንጻር
 ማቀድ፡ -
o መሻሻልን ያለመ ስትራቴጂክ እቅድ
o የዕለት ተዕለት ስራዎችን (Operational Plan)
 ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፡-
o የስትራቴጂክ እቅድ አፈጻጸም ክትትል
- የበላይ ኃላፊዎች ከዳይሬክቶሬቶች ጋር ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ
o የኦፕሬሽና አፈጻጸም ክትትልና ድጋፍ
- የስራ ክፍል መሪዎች ከባለሙያዎቻቸው ጋር ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ
 አፈጻጸምን መለካት፡-
o አፈጻጸሞችን በቀጣይነት ለማሻሻል
o ፈፃሚን ለማበረታታት እና/ወይም የተጠያቂነት ስርዓት ለማስፈን

38
የተቋማት ሚና …
● የዜጎች ስምምነት ሰነድ ትግበራ
 የሚሰጡ አገልግሎቶችን መለየትና ሰንዶ ማዘጋጀት

 የስምምነት ሰነዱን ለተገልጋዮች ግልጽ ማድረግ

 የስታንዳርድ አፈጻጸሞችን መመዝገብና መፈተሸ

 በስታንዳርድ አፈጻጸም ላይ የተጠያቂነት ስርአት ማስፈን

39
የተቋማት ሚና …
● ከመሰረታዊ ስራ ሂደት ትግበራ አንጻር/BPR/
 የተቋም ተልዕኮን በአዋጅ በተሰጠ ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት መወጣት
o በወል እና በተናጠል የተሰጡ የስልጣን እና ተግባራት በተሟላ አቅም መወጣት
መቻል
 አገልግሎቶችን በመዋቅር ተደራሽ ማድረግ
o በBPR የተጠኑ አገልግሎቶችን እስከታችኛው እርከን ተግባራዊ መደረጋቸውን
ማረጋገጥ
o መውረድ ሲገባቸው ያልወረዱና መውረድ ሳይገባቸው የወረዱ አገልግሎቶችን እና
ዋና ተግባራትን በጥናት ለይቶ ማስተካከል፡፡

40
የተቋማት ሚና …
● ከመሰረታዊ ስራ ሂደት ትግበራ አንጻር/BPR/
 ለአገልግሎት አሰጣጡ ምቹ የቢሮ አደረጃጀት መፍጠር
o ምቹ የቢሮ አቀማመጡን (Office lay out)
o የሀሁ ስራዎችን ሟሟላትና በተግባር እንዲውሉ ማድረግ
 ተቋማዊ ባህል መገንባት /organizational Culture/
o ሙያዊ ስነ-ምግባር ያለው እና የአገልጋይነት መንፈስ የተላበሰ ሰራተኛ መገንባት
o በአመራርና በፈፃሚው መካከል ጠንካራና መልካም የሥራ ግንኙነት መገንባት፤

41
የተቋማት ሚና …
● የተቋም ባህሪን መሰረት ያደረጉ አዳዲስ የስራ አመራር ስልቶችን መቀየስ
 ተቋማት ቀጣይነት ያለው ውጤታማ የአገልግሎት አሰጣጥ ለማረጋገጥ እንደየራሳቸው
ተጨባጭ ሁኔታ የስራ አመራር ስልቶችን የመቅረጽ፣ የማጥናትና በሚመለከተው አካል
ሲጸድቅም የመተግበር ሚና ይኖራቸዋል፡፡
● አገልግሎቶችን ተደራሽ ማድረግ /service accessibility/
 አገልግሎቶችን ምቹ፣ ዘመናዊና ቀላል በሆነ መንገድ ተገልጋዩ ማቅረብ
 ለምሳሌ፦
o አፕሊኬሽኖችንና ሲስተሞች መጠቀም፤
o የአገልግሎት መስጫ ሰዓትን በማራዘም /Flexible opening hours/፤
o የእይታ ካሜራ (CCTV) መጠቀም ወዘተ.

42
የተቋማት ሚና …
● ቅሬታን ከመቀበልና ከመፍታት አንጻር
 ቅሬታን ከጅምሩ አገልግሎት በሚሰጡበት ቦታና ጊዜ የመፍታት ባህልን ማዳበር
 ተገልጋዩ ቅሬታውን የሚያቀርብበትና የሚፈታበት ቀላል፣ ግልጽና ምቹ ሁኔታን መፍጠር
 ቅሬታን ከምንጩ የሚያደርቅበትን እና ችግር ፈጣሪዎች ተጠያቂ የሚሆኑበትን አሰራር
መፍጠር
● የመረጃ ግልጽነትን ማረጋገጥ /Transparency/
 ሁሉንም ተገልጋይ ያማከለ የመረጃ አሰጣጥ ዘዴዎች በመጠቀም
o የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች፣
o ከተገልገዩ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎች፣
o እቅድና የአፈጻጸም ሪፖርት፣
o የጥናት ውጤቶች፣ ወዘተ. መረጃዎችን መስጠት

43
የተቋማት ሚና …
● የተገልጋይ እና ባለድርሻ አካላትን ማሳተፍ
 ተቋማት የየራሳቸውን ተገልጋይና ባለድርሻ አካል መለየት
 ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ህዝብ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች ለመፍታት
የጋራ መድረክ መፍጠር
 ተገልጋይና ባለድርሻ አካላትን
o በእቅድ ዝግጅት፣
o በሪፖርት አፈጻጸም ግምገማ፣
o አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል በሚደረጉ ጉዳዮች ወዘተ. ማሳተፍ
ይኖርባቸዋል፡፡

44
የተቋማት ሚና …
● አሰራርንና ውጤታማነትን በጥናት መፈተሸ
 አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የሰራተኛውንና የተገልጋዩን ፍላጎት እና እርካታ ቢያንስ
በዓመት አንድ ጊዜ በጥናት የመፈተሸ፣
 አሰራርን የሚያሳልጡ ምርጥ ተሞክሮዎችን የመለየት፣ የመተግበርና የማስፋት፣
 የቅሬታ መንስዔዎችን በጥናት ለይቶ ዘላቂ መፍትሄ የመስጠት፣
 ብልሹ አሰራሮችን በጥናት የመፈተሽና መፍትሄ የመስጠት ሚና ይኖራቸዋል፡፡

45
ክፍል አምስት

የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሚና

46
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሚና

የሰው ሀብቱን የማልማትና የማስተዳደር ሚና

የሰራተኞች አፈፃፀም
አጫጭር ስልጠናዎች ምዘና የማበረታቻና ተጠያቂነት
የረዥም ጊዜ ስልጠና
ስርዓት መዘርጋት
የሰዉ ሀብት ልማት ከተለመደው አሰራር በአገልግሎት አሰጣጣቸው
የከተማዋን ፍላጎት እና
በቀጣይነት የሚለማበትንና በተጨማሪ ከተገልጋዩ ምስጉን የሆኑትን
የቴክኖሎጂ እድገት
ጥቅም ላይ የሚዉልበትን በቀጥታ በቴክኖሎጂ ለማበረታታት
መሰረትያደረገ አቅም ግንባታ
ስርዓት መዘርጋት የሚሰጥበት የአሰራር ስርዓት የሚያደናቅፉትን ደግሞ
መዘርጋት ተጠያቂ ለማድረግ

47
የፐብሊክ ሰርቪስ ሚና ...

48
የፐብሊክ ሰርቪስ ሚና ...

የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነትን በጥናት መፈተሸ

የእርካታ ዳሰሳና ጥናቶችን ሀሳብ አመንጪ ቡድን


የህግ ማዕቀፎችን ማዘጋጀትና
ማካሄድ /Think Thank Group
ማስተግበር
ማዋቀር
የተገልጋዩን እና የሰራተኛውን እርካታ
የአገልግሎት አሰጣጡን ውጤታማ በጥናት መለካትና
ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣
በተሰጠው ምክረ-ሀሳብ መሰረት ከምሁራንና ከአማካሪ ድርጅቶች ጋር
የአሰራር መመሪያዎች፣ ደንቦች እና የእርምት እርምጃ መወሰድ
ማንዋሎች ይዘጋጃሉ በመቀናጀት የማዋቀርና ምክረ-
ሃሳባቸውን የመቀበያና የማስተግበሪያ
ስርዓት መዘርጋት

49
የፐብሊክ ሰርቪስ ሚና ...

የቅሬታና አቤቱታ አቀራረብ እና አፈታት ስርዓት መዘርጋት

የመንግስት ሰራተኞችን ቅሬታ


የተገልጋይ ቅሬታ አፈታት ስርዓት
ማስተናገድ
መዘርጋቱን ማረጋገጥ
ቅሬታዎች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ
በተገልጋይ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን የሚቀርቡበት ስርዓት በመዘርጋት ቀልጣፋ
ማስተናገድ የሚያስችል ስርዓት በየተቋማቱ አገልግሎት በየደረጃው እንዲኖር ማስቻል
መዘርጋቱን እና በወቅቱና እየተፈቱ እና ዉጤታማነቱን ማረጋገጥ
ስለመሆኑ የማረጋገጥ ሚና ይኖረዋል።

50
የፐብሊክ ሰርቪስ ሚና ...

የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት መመዘኛ መስፈርት ማዘጋጀት


● ተቋማት ያሉበትን ደረጃ ዳሰሳ በማድረግ በዓመቱ መጨረሻ ሊደርሱበት በሚገባ ውጤት
ላይ በመግባባት ከየተቋማቱ ጋር የስምምነት ውል ማድረግ

● በመመዘኛ መስፈርቱ መሰረት በአመት ሁለት ጊዜ ምዘናውን በማካሄድ የክትትልና ድጋፉ


ስራ በተቋሙ ውጤታማነት ላይ ያበረከተውን አስተዋጽዖ መመዘን፡፡

51
ክፍል ስድስት

የአደረጃጀቶች አወቃቀርና ግንኙነት ስርዓት እና

የክትትል፣ ድጋፍ፣ ሪፖርት፣ ግምገማና ግብረ-መልስ

52
6.1 የአደረጃጀቶች አወቃቀርና የአፈጻጸም ግምገማ ስርዓት
ራ ሮች
አ መ
ተ ሿ ሚ ቀን
ም 1
ሁሉ በሳምንት

ራ ሮ ችና
ም አመ ች
ሁሉ
ሬ ክ ተሮ
ዳይ ቀን
በ 15

ኃ ላፊና
የዘርፍ ክተሮች
ዳይሬ ቀን
በ15
ስ ር ያሉ

/ በ ቡድ ተኞች
በዳ/ት ሉም ሠራ ቀን

ም ንት1
በሳ
ራሮች

ናአ ን
ፈ ፃ ሚ ቀ
ሉ ም
ሁ በ3 ወ ር 1
53
6.2 የክፍል ከተማ እና የወረዳ የአደረጃጀቶች አወቃቀርና የአፈጻጸም ግምገማ
ስርዓት
ሉም
እናሁ
ኃላፊ ሪዎች

ጽ ቡድን መ ቀን
/ ቤ
በ 15

ድ ኑ
ና በቡ ኞች
ሪ እ ራ ተ
ድን መ ሉም ሠ ቀን
ቡ ሁ 1
ያ ሉ ን ት
ስር በሳም

ሁሉም
እና
ኃ ላፊ ዎች
/ ቤት ፃሚ ቀን
ጽ ፈ ር1

በ3
54
የአደረጃጀቶች አወቃቀር …

ከባለድርሻና ከተገልጋይ አደረጃጀቶች ጋር የሚደረግ ውይይት


●እንደየተቋማት ባህርይ ከተደራጁና ከተለዩት አካላት ጋር
○ በተቋሙ ዕቅድ፣
○ የዕቅድ አፈፃፀም፣
○ በአገልግሎት አሰጣጥ
○ በተቋሙ አሰራሮች
○ በየሩብ ዓመቱ መድረክ በመፍጠር እንዲሳተፉ እና የድርሻቸውን እንዲወጡ በማድረግ

55
የአደረጃጀቶች አወቃቀር …
ከተማ አቀፍ የለውጥ አመራር ፎረም አደረጃጀትና አሰራር
ሀ/ የፎረሙ አደረጃጀት
○ በማዕከል
- የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ሰብሳቢ
- የማስፈጸም አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ም/ሰብሳቢ
- የአገልግሎት አሰጣጥ ክ/ድጋፍና ምዘና ዳይሬክተር ፀሐፊ
- የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አመራሮች፣
- የሪፎርሙን እንዲመሩ የተሰየሙ የተቋም ኃላፊዎች፣
- የክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና
- የተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ክ/ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት

56
ከተማ አቀፍ የለውጥ አመራር ፎረም …

ሀ/ የፎረሙ አደረጃጀት
○ በክፍለ ከተማ
- ዋና ስራ አስፈጻሚ ሰብሳቢ
- የፐብሊክ ሰርቪስ ጽ/ቤት ኃላፊ ም/ሰብሳቢ
- ሁሉንም የጽ/ቤት ኃላፊዎች፣
- የወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣
- የአገልግሎት አሰጣጥ ክ/ድጋፍና ምዘና ቡድን መሪ ፀሐፊ
○ በወረዳ
- ዋና ስራ አስፈጻሚ ሰብሳቢ
- የፐብሊክ ሰርቪስ ጽ/ቤት ኃላፊ ም/ሰብሳቢ
- የአገልግሎት አሰጣጥ ክ/ድጋፍና ምዘና ቡድን መሪ ፀሐፊ
- ሁሉም የጽ/ቤት ኃላፊዎች ያካተተ ይሆናል፡፡
57
ከተማ አቀፍ የለውጥ አመራር ፎረም …
ለ/ የግንኙነቱ ዓላማ

●ፎረሙ በተመረጡ ተቋማት


○ በአገልግሎት አሰጣጥ፣
○ በአደረጃጀት እና በአሰራር ዙሪያ በክትትልና ድጋፍ የታዩ ግኝቶችን መሰረት በማድረግ
○ ከጠንካራ አፈፃፀሞች ትምህርት ለመውሰድ፤
○ ደካማ አፈፃፀሞችን ለይቶ ለማረም እና የቀጣይ አፈፃፀም አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ
ነው፡፡

58
ከተማ አቀፍ የለውጥ አመራር ፎረም …
ሐ/ የውይይቱ አጀንዳና የግንኙነት ጊዜ
○ በወር አንድ ጊዜ በወሩ የመጨረሻው ዓርብ ከ8፡00 ሰዓት ጀምሮ
○ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ የለውጥ አመራር ፎረም ከከተማ የግንኙነት ጊዜ ቀድመው
በመገምገም በውይይቱ የተደረሰበትን ድምዳሜ ይዞ መገኘት ይኖርባቸዋል።
መ/ ከውይይቱ የሚጠበቅ ውጤት
○ በክትትልና ድጋፍ የተለዩ የአፈጻጸም ክፍተቶች ላይ ማስተካከያ መስጠት፤
○ በከተማ፣ በክፍለ ከተማ እና በወረዳ ደረጃ መፍትሔ የሚሹ ጉዳዮችን ለይቶ ድጋፍ ማድረግ
○ በአፈጻጸማቸው የተሻሉ ተቋማትን/ ጽ/ቤቶችን ዕውቅና መስጠት እና
○ ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ይሆናል፡፡

59
ከተማ አቀፍ የአመራር ካውንስል አደረጃጀትና አሰራር
ሀ/ የካውንስሉ አደረጃጀት
●ከተማ አቀፍ የአመራር ካውንስሉ
 የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ የካውንስሉ ሰብሳቢ፣
 ም/ከንቲባ የካውንስሉ ም/ሰብሳቢ
 የፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ የካውንስሉ ፀሐፊ
 የማዕከል አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣
 የሁሉም ተቋማት የበላይ ኃላፊዎች፣
 የተቋም ምክትል ኃላፊዎች፣
 የክፍለ ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣
 የክፍለ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ ጽ/ቤት፣
 የወረዳ ዋና ሥራ አስፈፃሚ
 የወረዳ የፐብሊክ ሰርቪስ ጽ/ቤት ኃላፊ ይሆናሉ፡፡
60
ከተማ አቀፍ የአመራር ካውንስል …
ሀ/ የካውንስሉ አደረጃጀት
●ክፍለ ከተማ
 ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰብሳቢ፣
 ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ ም/ሰብሳቢ
 የፐብሊክ ሰርቪስ ጽ/ቤት ኃላፊ ፀሐፊ
 በክፍለ ከተማ ደረጃ አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣
 ሁሉም የጽ/ቤት ኃላፊዎች፣
 የወረዳ አስተባባሪ ኮሚቴዎች እና
 የወረዳ የፐብሊክ ሰርቪስ ጽ/ቤት ኃላፊዎችን የያዘ ይሆናል

●በወረዳ
 ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰብሳቢ፣
 ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ ም/ሰብሳቢ
 የፐብሊክ ሰርቪስ ጽ/ቤት ኃላፊ ፀሐፊ
 የወረዳ አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣
 ሁሉንም የወረዳ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ያካተተ ይሆናሉ፡፡ 61
ከተማ አቀፍ የአመራር ካውንስል …

ለ/ የግንኙነቱ ዓላማ
○ በቢሮ ክትትልና ድጋፍ ግኝቶች፣
○ በከንቲባ ጽ/ቤት የሱፐርቪዥን ግኝቶችና
○ በፕላን ኮሚሽን በሚጠመር የተቋማት እቅድ አፈጻጸም የተቀናጀ ሪፖርትና ምልከታ ላይ
ተመስርቶ በአፈፃጸም ረገድ ያሉ ጠንካራና ደካማ አፈፃፀሞችን ለይቶ ማሻሻያዎችን
ለመውሰድ ይሆናል፡፡

62
ከተማ አቀፍ የአመራር ካውንስል …

ሐ/ የውይይቱ አጀንዳና የግንኙነት ጊዜ

●በየሩብ ዓመቱ የመጨረሻ ሳምንት የሚወያይ ይሆናል፡፡


●የውይይቱ አጀንዳም
○ የሶስት ወር የተቋማት አፈጻጸምን፣
○ የአገልግሎት አሰጣጡን መሰረት ያደረገ የክትትልና ድጋፍ እና
○ የሱፐርቪዥን ግኝቶችን በመተንተን/Triangulate/ የተዘጋጀውን ሪፖርት መገምገም
ይሆናል፡፡

63
ከተማ አቀፍ የአመራር ካውንስል …

መ/ ከውይይቱ የሚጠበቅ ውጤት

●የአፈጻጸም ክፍተቶችን በመለየት ማስተካከያ መስጠት፣


●በየደረጃው ባሉ እርከኖች ምላሽ የሚሹ ጉዳዮችን ለይቶ ድጋፍ ለማድረግ
●በአፈጻጸማቸው የተሻሉ ተቋማትን ወይም ጽ/ቤቶችን ዕውቅና ለመስጠት፣
●ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸውን ለመደገፍ እና መሻሻል ማሳየት ያልቻሉትን ተቋማት ተጠያቂ ለማድረግ
●እንዲሁም ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ የሚጠበቅ ውጤት ነው፡፡

64
6.2 የክትትል፣ ድጋፍ፣ ሪፖርት ግምገማና ግብረ-መልስ ስርዓት
የእቅድ ዝግጅት /ስትራቴጂክ እና ኦፕሬሽናል እቅድ/
• በፕላንና ልማት ኮሚሽን የእቅድ ቢጋር
• በሥራ ክፍል፣ በፕሮሰስ ካውንስል፣ በአጠቃላይ ካውንስል፣ በስትራቴጂክ ካውንስል፣ አጠቃላይ
ሠራተኛው እና ከባለድርሻ አካላትና ከህዝብ አደረጃጀቶች የተወያያበት
• እንደአስፈላጊነቱ መከለስ፣

የሪፖርት አቀራረብ የአፈጻጸም ግምገማ


• ቡድኖች ለዳይሬክቶሬቶች በየወሩ ከ25-26
• ዳይሬክቶሬቶች ለዘርፎች ከ26-27 ከላይ በክፍል 6.1
• ከ28-29 ባሉ ቀናት የተጠቃለለ ሪፖርት ለተቋሙ የበላይ በተቀመጠው መሰረት
አመራር መቅረብ ይኖርበታል ይሆናል

የመስክ ምልከታ
• በማዕከል በተቋሙ የበላይ አመራር የሚዋቀሩ ከስራ ክፍል መሪዎችና አማካሪዎች
የተውጣጡ ቡድኖች
• በክፍለ ከተማ እና በወረዳ ደረጃ በስራ አስፈጻሚው የሚዋቀሩ የጽ/ቤት ኃላፊዎች ቡድን
• በ3 ወር አንድ ጊዜ በታቀደ መልኩ የተመረጡ የስራ አፈፃፀሞች የመስክ ምልከታ
65
የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
ክፍል ሰባት

የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት መመዘኛ ማዕቀፍ

66
የመመዘኛ ማዕቀፎቹ መነሻዎችና ምንነት
● ማዕቀፉ European Institute of Public Administration በ2013 ያዘጋጀውን
‘Common Assessment Framework of Public Institution’ መነሻ
በማድረግ እና ከከተማችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም የተዘጋጀ ነው፡፡

● ዋና ዓላማ
ይህ የመመዘኛ ማዕቀፍ በሁሉም የመንግስት ተቋማት ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ
ውጤታማነትን በመመዘን የሥራ አፈፃፀምን ለማሻሻል እና ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር
ያለመ ነው፡፡

67
የመመዘኛ ማዕቀፍ …

ዝርዝር ዓላማዎች
○ ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ልህቀትን ባህል እንዲያደርጉ ለማስቻል፤
○ ቀጣይና የማያቋርጥ የማቀድ፣ የመተግበር፣ የመከታተልና የማሻሻል ሂደት እንዲከተሉ ለማድረግ፤
(PLAN, DO, CHECK, ACT)
○ ተቋማት የራሳቸውን ክፍተት በራሳቸው እንዲፈቱ እና ወደ ተሻለ አሰራር እንዲገቡ የራስ መመዘኛ
(self assessment) እንዲተገብሩ ለማስቻል፤
○ የክትትልና ድጋፍ ትግበራን ውጤታማነት ከተቋም ውጤታማነት ጋር በማስተሳሰር መገምገም፣
መፈተሸና ማሻሻል የሚያስችል አሰራር ለመቀየስ፤
○ የመማር ተሞክሮ (bench learning) በመንግስት ተቋማት መካከል እንዲኖር ለማስቻል፤

68
የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት መመዘኛ ማዕቀፍ

69
የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት

መመዘኛ ማዕቀፍ

ቅጽ1 እና 2

70
71

You might also like