You are on page 1of 2

የቡድን መሪ አስፈላጊነት፡- እንደሚታወቅ አስካሁን ባለው የውስጥ ኦዲት አወቃቀር አገልግሎቱ በሁለት

ቡድኖች ማለትም የክዋኔ ኦዲት ቡድን እና የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን በሚል ተዋቅሮ ስራውን
አቅም በፈቀደ መጠን እያከናወነ ይገኛል ፡፡ በዚህም በኤጀንሲው ታሪክ ያልነበረውን የውስጥ ኦዲት ፅንስ ሀሳብ
በአመራሩም ሆነ በሠራተኛው ዘንድ ተገቢ የሆነ ግንዛቤ እንድያዝ እና ኦዲት ከሚደረጉ አካላቶች ጋርም
መርህን መሰረት ባደረገ መልኩ ተቀራርቦ ለመስራት ጥረት ተደርጓል ብለን እናምናለን፡፡ በዚህም በኦዲት ወቅት
የሚታዩ ክፍተቶች ላይ አስፈላጊውን የማሻሻያ ሀሳብ በመስጠት ኤጀንሲው አሰራሮችን እንዲያሻሽል ብርቱ
ጥረት እየተደረገ ይገኛል ምንም እንኳን ግኝቶች ላይ ወቅቱን የጠበቀ ውሳኔ መስጠት ላይ አሁንም ያልተቀረፉ
ጉዳዮች ቢኖሩም፡፡ ሆኖም ግን አሁን አዲስ እየተጠና ባለው የኤጀንሲው አወቃቀር የሁለቱም ቡድን እንዲነሳ
መደረጉ ያልተጠበቀ እና ለኤጀንሲውም የማይጠቅም እንዲሁም ኤጀንሲው ላለፉት ረዥም ዓመታት የውስጥ
ኦዲት ያልነበረው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የነበረው አሰራር ብዙ ክፍተት የነበረበት እና በውጭ ኦዲተሮች
ከሚደረገው ውስን የናሙና ምርመራ በስተቀር ሠነዶችን በሙሉ በመዳሰስ ዝርዝር የሆነ ኦዲት ማድረግ
ያልተለመደ በመሆኑ የውስጥ ኦዲቱ ተዋቅሮ ስራ በጀመረበት ወቅት የነበረው ጫና በጣም ከፍተኛ የነበረ
ሲሆን እሱን ተቋቁሞ አሰራሮችን ወደ ህጋዊ መስመር ለማስገባት የነበረው አስቸጋሪ ሁኔታ ተቋቁሞ አሁን
የደረሰበትን ሁኔታ ግምት ውስጥ ያላስገባ መሆኑ በእኛ በኩል አሳዛኝ ነው፡፡

ለመሆኑ የውስጥ ኦዲት ቡድን አስፈላጊነቱ ምንድነው?

 ባለፉት ሁለትና ሶስት ዓመታት እንደታየው የስራ ክፍሉ ሲዋቀር በአገልግሎት ደረጃ የተዋቀረ በመሆኑ
እና ኦዲት የሚደረጉት የስራ ክፍሎች ደግሞ በዳይሪክቶሬቶች ደረጃ በመሆኑ ማለት ኦዲት
ከሚደረጉት ክፍሎች በደረጃ ዝቅ ብሎ በመገኘቱ ስራውን በአግባቡ ለማከናወን እና የሚሰጡ
አስተያየቶችንም ተቀብሎ ለመፈፀም ያላቸው ትኩረት አናሳ መሆን ለክፍሎ እጅግ አስቸጋሪ ሆኖ
የቀጠለ ነው ይህም ስራውን ኦዲት የሚያደርጉ አካላቶች በቡድን ደረጃ ሆነው እያሉ ማለት ነው አሁን
ደግሞ ቡድኖችን በማንሳት በኦፊሰር ደረጃ ሲሆን ደግሞ የስራ ክፍሉን ስራ ምን ያህል ሊያዳክመው
እንደሚችል መገመት ይቻላል
 ለኤጀንሲው ከተለያዩ ለጋሽ ድርጅቶች የሚመደበው በጀት ወደ አንድ ቢሊየን የሚጠጋ በመሆኑ ይህን
ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ሙያው የሚጠይቀውን ተጠያቂነትና ኃላፊነት ተላብሶ በቡድን ካልተመራ
እንዴት ስራውን ለማከናወን ታስቦ ነው ቡድን እንዲነሳ የተደረገው የሚል ጥያቄን የሚያጭር በመሆኑ
አሁንም አስፈላጊነቱ ከዚህ አንፃር መታየት አለበት፡፡
 እስካሁን በነበረው የኦዲት የስራ ሂደት የኦዲት ስራው ከዋና መ/ቤቱ ጀምሮ በማስተባበሪያ ጽ/ቤቶችና
በስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች በሚደረገው ኦዲት ኦዲት ከሚደረጉ የስራ ክፍሎች ጋር የሚደረጉ
ውይይቶች እንዲሁም በኦዲት ወቅት አለመስማማቶች ሲፈጠሩ ወደ ላይ፣ወደጎንም ሆነ ወደታች
ካሉ ከሚመለከታቸው አካላቶች ጋር የሚደረጉ ውይይቶችን በማስተባበርም ሆነ የመተማመኑ ስራ
የሚሰራው በቡድን መሪው በመሆኑ የቡድኑ መኖር ለስራው መሳካትም ሆነ ውጤታማ መሆን
አስፈላጊ ስለሆነ ይህንን ማንሳት የስራ ክፍሉ የሚጠበቅበትን ውጤት እንዳያስመዝግብ እና
አወቃቀሩም መ/ቤቱን በሚጠቅምና እሴት በሚጨምር መልኩ ሳይሆን ለይስሙላ እንዲሁ ክፍሉ አለ
ለማለት ብቻ ያስመስለዋል የሚል እምነት አለን፡፡ በመሆኑም አሁንም አስፈላጊነቱ እንደገና ሊጤን
ይገባዋል እንላለን፡፡
 የኤጀንሲውን አወቃቀር ስንመለከት በጣም ሰፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በየበጀት ዓመቱ የሚመደቡ
በጀቶች ስደተኛውን በአግባቡ ተጠቃሚ ያደረጉና ለታለመላቸው ዓላማ መዋላቸውን ለማረጋገጥ
ኦዲተሮቹ በሁለት ቡድን ተከፍለው የሚሰሩ በመሆኑ ይህንን ስራ በበላይነት የሚመራ የሚያስተባብር
ችግሮች ሲኖሩም በቅርብ ሆኑ መፍትሄ ማፈላለግ ወደ ላይም ወደ ጎንም ከሚመለከታቸው የስራ
ክፍሎች ጋር ግኑኝነቶች መፍጠር እና ጤናማ የሆነ የኦዲት ስራ መኖሩን ማረጋገጥ የቡድን መሪው
የስራ ድርሻ በመሆኑ ይህንን ስራ በአግባቡ ለመምራት የቡድን መሪ መኖሩ ስራውን ውጤታማ
ለማድረግና የሚታዩ ክፍተቶች ላይ አስፈላጊውን ግብዓት ለሚመለከተው አካል አጠናክሮ ማቅረብ
አስፈላጊ ነው ፡፡
 ተለያዩ የመስክ ኦዲት ወቅት የሚታዩ ግኝቶችን ትክክለኛነት ማረጋገጥ፣መረጃዎችን በአግባቡ
አደራጅቶ መያዝ፣ ለህግ ሊቀርቡ የሚችሉ ጉዳዮችን ለይቶ የመያዝና በህግ አካላቶች ዘንድ ቀርቦ
የማስረዳት ስራ በዋናነት የሚፈፀመው በቡድኑ በመሆኑ ይህንን ማንሳት ስራውን ያለማሰሪያ ሜዳ
ላይ እንደመበተን በመሆኑ አስፈላጊነቱ አሁንም መታየት አለበት፡፡

You might also like