You are on page 1of 10

መልካምዘር፤ሲሳይና ጓደኞቻቸው

የአካባቢ ብክለት ክትትልና ቁጥጥር

ጀማሪ አማካሪ የህ/ሽ/ማህበር

በኮ/ቀ/ክ/ከተማ በወረዳ ፣ ፤
13 14 15

አስተዳደር ስር በአነስተኛና ጥቃቅን

1
የስራ ዕድል ፈጠራ

ኢንተርፕራይዝና በአዲስ አበባ

የአካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት

ኮሚሽን አማካኝነት የተቐቐመ

ማህበር የጥር ወር ዕቅድ፡፡

2
ጥር 2013 ዓ.ም
1.መግቢያ

የአካባቢ ጉዳይ ላለፉት አስርት አመታት የፕላኔታችን ቁልፍ ግን ትኩረት ያላገኘ ጉዳይ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት
የአለም አቀፉ ህብረተሰብ የሁኔታውን አሳሰቢነትና በአካባቢ ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት በመረዳት ልማትና አካባቢ
ተጠጣጥመው እንዲሄዱ በማድረግ የእድገት ቀጣይነትን ለማረጋገጥ እንዲያስችል በአገራት መካከል በርካታ አለም አቀፍ
ስምምነቶች ተደርገዋል፡፡

ኢትዮጵያም አብዛኞቹን ስምምነቶች የተቀበለች ስትሆን ይህንን መሰረት በማድረግ የአካባቢ ፖሊሲ፣ ስረትራቴጂዎች፣
የህግ ማእቅፎች እንዲወጡ የተደረገ ሲሆን ኪዚህም ጋር ተያይዞ በፌደራል ፣ ክልልና በከተማ አስተዳደሮች አስፈጻሚ
መስሪያ ቤት እንዲቋቋሙ ተደርጓል፡፡
በከተማ ደረጃ የአካባቢ ጉዳይ በይበልጥ ትኩረት የሚሻው በከተማ መስፋፋት፣ ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችና
የልማት እንቅስቃሴዎች የተነሳ በከተማ አካባቢ ላይ በተለይም በስርአተ ምህዳር፣ ብዝሃ ህይወት ላይ የሚደርሰው
ጥፋትና የአካባቢ ብክለት የከፋ ከመሆኑ ባሻገር እለት ተእለት የሚታየውን ከፍተኛ የሙቀት መጠን መጨመር የከተሞች
ልዩ መገለጫ እየሆነ መጥቷል፡፡
በታህሳስ 2013 ዓ/ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃና አረንጓዲ ልማት ኮሚሽን በወጣው መረጃ መሰረት
በስፋት እንደገለፀው የተፈጥሮ ሃብት ልማትና እንክብካቤ ጋር ተያይዞ በአረንጓዴ ቦታዎች ልማትና አጠባበቅ እንዲሁም
ከአካባቢ ብክለት በተለይም በከተማው ውስጥ ባሉ የብክለት ምንጭ የሆኑ ትላልቅ ተቐማት የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ
አያዝዝን በተመለከተ በመንግስትና በህብረተሰቡ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን ያስገነዝባል፡፡
በዚህም መሰረት መልካምዘር፤ሲሳይና ጓደኞቻቸው የአካባቢ ብክለት ቁጥጥርና ክትትል ጀማሪ አማካሪ ህ/ሽ/ማ
በኮ/ቀ/ክ/ከ ስር በሚገኙት በወረዳ 13፤14፤15 ላይ የሚደርሰውን የአካባቢ ብክለትና የተፈጥሮ ሃብት መመናመንን
ለመከላከል የሚያስችል እቅድ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

3
2. የወረዳ 13፤14፤15 ነባራዊ ሁኔታ
2.1 አካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት

የአለማችንን የአካባቢ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ አሳሳቢ እየሆነ የመጣ ሲሆን በተለይ ከዓለም ሙቀት መጨመርና ከአየር

ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ የአለማችን ቀዳሚ አጀንዳ እየሆነ ነው፡፡ የሚሊንየሙ የልማት ግቦች ላይም የአካባቢያዊ

ዘለቄታዊነትን ማረጋገጥ የሚለው አብይ ግብ በርካታ ስልቶችና የልማት አመልካቾችን አስፍሯል፡፡

በአገራችን 1984 ዓ.ም ወዲህ ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት ተሰጥቶት የአካባቢ ሥራዎች እንቅስቃሴ ከተጀመረበት ጊዜ

አንስቶ በአዲስ አበባ ከተማም በክልልና በክፍለ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ተቋቁሞ ሥራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል፡፡

ከ 2 ዐዐ 1 ዓ.ም ጀምሮ በ BPR ጥናት ሰነድ መሠረት የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ ከማዕከል እስከ ወረዳ መዋቅር ተዘርግቶለት

እንዲሁም በክ/ከተሞች በጽ/ቤት ደረጃ እንዲቋቋም ተደርጐ በሥራ ላይ ይገኛል፡፡ ይህም መንግስት ለአካባቢ የሰጠው

ትኩረት ያመለክታል፡፡

የወረዳ 13፤14፤15 አስተዳደርም ለአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ተግባራዊነት የተለያዩ ዕቅዶችን ነድፎ በእንቅስቃሴ ላይ

ሲገኝ ከዘርፈ ብዙ የአካባቢ ችግሮች አኳያ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች የባለድርሻ አካላትንና የህብረተሰቡን ተሳትፎ የሚሹ

ለመሆናቸው ሊሰመርበት ይገባል ፡፡

ወረዳዎቹ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የሚኖርበት ሰፊ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ፣ የንግድ እንቅስቃሴዎች እና መኖርያ

ቤቶች የሚገኙበት እንደመሆኑ መጠን በርካታ የአካባቢ ችግሮች የሚስተዋሉበት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹን

ለመጥቀስ ያክል፡-
 ከሚመነጨው ደረቅ ቆሻሻ 20% የሚሆነው የማይሰበሰብና አግባብ ባልሆነ አያያዝና አወጋገድ በየቦታው

የሚጣል ነው፡፡
 የቆሻሻ ገንዳዎቹም ደረጃውን በጠበቀ ቦታ የማይቀመጡ፣ ከልጆችና ከእንሳሳት ንክኪ እንዳይኖራቸው

ያልተከለሉና ወቅቱን ጠብቀው የማይነሱ በመሆናቸው ለአካባቢ መበከል አስተዋፅኦ ማድረጋቸው፡፡


 የሚመነጨው የፍሳሽ ቆሻሻ ደረጃውን በጠበቀ የፍሳሽ መስመር ወደ ማጣሪያ የሚገባው በጣም አነስተኛ

መሆኑ፡፡
 መኖሪያ ቤቶች የመፀዳጃ አገልግሎት ያላቸው ውስን ከመሆናቸው በተጨማሪ በተለያዩ ወረዳዎች የህዝብ

መፀዳጃ አገልግሎት የሚሰጡ ቤቶች ስርጭታቸው አነስተኛ ነው፡፡

4
 የማምረቻና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት፣ እንዲስትሪዎች፣ ጋራዦች፣ ሆቴሎች፣ ሆስፒታሎች ወዘተ

ቆሻሻዎችን ወደ ወንዞች የጐርፍ ማስወገጃ ቱቦዎች፣ ቦዮች እና ሌሎች አካባቢዎች መልቀቃቸው ሌላው

ብክለትን ከሚያባብሱ መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡


ማህበሩ በትስስር መሥራት የሚገባቸው ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ውስጥ

ከአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት፤ ከንግድ ጽ/ቤት ፣ ከሥራ አስኪያጅ፣ ከጤና ጽ/ቤት ፣ከወጣቶችና በጎፍቃደኞች ጽ/ቤት፤ ሰላምና
ጸጥታ ጽ/ቤት ፣ ከባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ፣ ከፍትህጽ/ቤት ጋር በትስስር በመሥራት ተልዕኮውን ማሳካት ይችላል

3. የማህበሩ ራዕይ ተልእኮ እና እሴቶች


3.1 ራዕይ
አዲስ አበባ ከተማ 2017 ዓ.ም ከአካባቢ ብክለትና ከተፈጥሮ ሃብት መራቆት ተጠብቃ ከአካባቢ ጋር
የተጣጣመ ልማት የሚካሄድባትና በዓለም አቀፍ ደረጃ በተምሳሌትነት ከሚታዩ 15 ከተሞች አንዷ
ማድረግ

3.2. ተልዕኮ
አዲስ አበባ ከተማን ከብክለትና ከተፈጥሮ ሃብት መራቆት ለመከላከልና ልማትን ከአካባቢ ጋር
ለማጣጣም በጥናትና በምርምር የታገዘ ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም በህዝብ ተሳትፎ የአካባቢና
የተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ በማካሄድ የከተማዋ ነዋሪ በንፅሑና ጤናማ አካባቢ የመኖር መብቱ
እንዲጠበቅ ማድረግና ዘለቄታዊ ልማትና የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀምን ማረጋገጥ ፡፡

3.3. እሴቶች
 ተጠያቂነት
 ግልፅነት
 የላቀ አገልግሎት መስጠት
 ለለውጥ ዝግጁነት
 በዕውቀትና በዕምነት መመራት/መሥራት
 አካባቢ የሕይወት መሰረት መሆኑን ማመን
 ከአካባቢ ጋር የተጣጣመ ልማት ለዘላቂ ዕድገት መሰረት እንዲሆን መስራት
 በአካባቢ ጉዳዮች ላይ ሕብረተሰቡን ማሳተፍ ናቸው

4. የማህበሩ የጥር 2013 ዓ.ም ዕቅድ


4.1 የትኩረት አቅጣጫዎች
 የጀማሪ አማካሪ ማህበሩ የጋራ ዕቅድ ማዘጋጀት
 ከወረዳ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ጋር በመነጋገር የቢሮና የጽህፈት መሳሪያዎች ምናገኝበትን ሁኔታ ማመቻቸት
 በየወረዳው የባለድርሻ አካላትን መለየት
 በተዘጋጀው የመረጃ መሰብሰቢያ ፎርማት መሰረት መረጃ መሰብሰብ መጀመር

5
 ግንዛቤ መፍጠር-ለማህበረሰብ፤የብክለት ምንጭ ለሆኑ ተቐማት፤ወዘተ
 ከፍተኛ ብክለት እያስከተሉ ያሉ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን መለየት

4.2. የማስፈፀሚያ እስትራቴጂዎች

 ህብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የአካባቢ ልማትና እንክብካቤ ስራዎችን መስራት


 ሕጎች፣ደንቦችና፣የአፈፃፀም መመሪያና ማኑዋል መተግበር
 የክትትልና ግምገማ ስራዎችን መስራት
 መጠነ ሰፊ ግንዛቤ የመፍጠርና የማስጨበጥ ስራ መስራት
 በወረዳዎች ውስጥ ያሉትን ባለድርሻ አካላትን በማጠናከር የአካባቢን ጉዳይ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ

5. ስጋቶች

 የቢሮ ስራዎችን ለመስራት ቢሮ በጊዜ አለማግኘት


 ስራ ማስኬጃ በጀት በተፈለገው ጊዜ አለመጽደቅ
 የግብአት ችግር
 ከአንዳንድ ተቋማት ተቀናጅቶ ለመሰራት አለመቻላቸው
 አመራሮች ለአካባቢ የሚሰጡት ትኩረት አነስተኛ መሆን

6. የክትትልና ድጋፍ ስርዓት


6.1. የሪፖርት ስርዓት
 በየሳምንቱ እና በወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እንዲቀርብ ክትትል ማድረግ
 በሚቀርበው ሪፖርት እና በመስክ በሚደረግ ቅኝት የመደበኛ ስራዎችን በመከታተል ጥሩ የሰሩትን
እንዲቀጥሉበት ደከም ያሉትን የሚደገፉበትን ስልት በመነደፍ ተግባራዊ ማድረግ
 በአፈፃፀም ዝቅተኛ ደረጃ ያላቸውን የማህበሩን አባላት ስልጠና በመስጠት የአፈፃፀም አቅማቸውን ማሳደግ

6.2. የሱፐርቪዥንና ግብረ መልስ አሠራር

 በየሳምንቱ፣ እና በየወሩ ሪፖርቶች ላይ በመመስረት እያንዳንዱ የስራ ክፍል ምን ያህል እንዳከናወነ ይገመገማል
 በሪፖርቶቹ ላይ በመንተራስ በአፈፃፀም የታዩ ጉድለቶች የእርምት እርምጃ እንዲወሰድባቸው ግብረመልስ
ይሰጥባቸዋል
 በተለያዩ መድረኮች ስራዎች ይገመገማሉ የማስተካከያ አቅጣጫም ይወሰዳል፡፡

6.3 የግምገማ አሠራር

6
በለውጥ ስራዎች ትግበራ ሂደት በተቀመጠው የመከታተያ ቼክ ሊስት መሠረት ከአመራር ጀምሮ እስከ ፈፃሚው ድረስ
የተግባራት አፈፃፀም ያጋጠሙ ችግሮችና ቀጣይ አቅጣጫዎች በየደረጃው እየተገመገመ ሪፖርት የመረጃ ቅብብሎሽ
ስርዓቱን ጠብቆ እንዲላክ ይደረጋል፡፡

7. ማጠቃለያ

በአካባቢ ላይ መጠነ ሰፊ ግንዛቤ የሚፈጥሩና የሚያስጨብጡ ስራዎችን በመስራት የህብረተሰቡንና የባለድርሻ አካላትን
ያሳተፈ የአካባቢ ልማትና እንክብካቤ ስራዎችን መስራት፣ የአካባቢ ሕጎች፣ ደንቦችና የአፈፃፀም መመሪያ እንዲተገበሩ
በማድረግ የክትትልና ግምገማ ስራዎችን መስራት

7
ሂደት ዝርዝር መርሀ-ግብር

1.የትግበራ ምዕራፍ

ዓላማዎች ግቦችና ዝርዘዝር ተግባራት የክንውን ጊዜ


አስፈጻሚ አካላት

ዓለማ 1፡ 1.የጀማሪ አማካሪ ማህበሩ የጋራ ዕቅድ ማዘጋጀት ከጥር 7-10 2013 ዓ.ም የወረዳው አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤትና
በክ/ከተማው
የማህበሩ አባላት
የሚደርሰውን
2.ከወረዳ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ጋር በመነጋገር የቢሮና ከጥር 12-14 2013 ዓ.ም ››
የአካባቢ የጽህፈት መሳሪያዎች ምናገኝበትን ሁኔታ ማመቻቸት
ብክለትን
በመከላከልና
3.በየወረዳው የባለድርሻ አካላትን መለየት ከጥር 13-15 2013 ዓ.ም ››
በመቆጣጠር
ለነዋሪዎቿ
4.በተዘጋጀው የመረጃ መሰብሰቢያ ፎርማት መሰረት ከ 10 ከጥር 17-24 2013 ዓ.ም ››
ንጹህና ጤናማ አግልግሎት ሰጪ ተቐማት መረጃ መሰብሰብ መጀመር
አካባቢ
መፍጠር፡፡
5.ግንዛቤ መፍጠር-ለ 10፤የብክለት ምንጭ ለሆኑ ከጥር 26-27 2013 ዓ.ም ››
ተቐማት፤ወዘተ

6.ከፍተኛ ብክለት እያስከተሉ ያሉ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ከጥር 28-30 2013 ዓ.ም ››


ድርጅቶችን መለየት

8
2.የክትትልና ግምገማ ሥርዓት ማስቀመጥ

ዋና ዋና ዓላማዎች

ዓላማ፡- 1- በኮ/ቀ/ክ/ከ ስር በሚገኙ ወረዳዎች(13፤14፤15) የአካባቢ ብክለት መከላከልና መቀነስ፣

ቁልፍ ተግባር

 የማህበሩን አባላት አቅሞች በመጠቀም እቅድን በጊዜና በጥራት መፈፀም

 የክትትል ድጋፍና ግምገማ ሥርዓት መዘርጋት(ዕለታዊ፤ሳምንታዊ፤ወርሀዊ)

ማህበሩ በቀጠይነት ሚሰራቸው ዓበይት ተግባራት

በኮ/ቀ/ክ/ከ ስር በሚገኙ ወረዳዎች (13፤14፤15) እየተከሰተ ያለውን የአካባቢ ብክለትና የሕግ ማዕቀፎችን ለመተግበር እንዲያስችል የሕብረተሰቡ ግንዛቤ በማሳደግና
የተቀናጀ የቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት የአካባቢ ብክለት መከላከል፡፡

ዓለማ 1፡ በኮ/ቀክ/ከ ስር በሚገኙ ወረዳዎች (13፤14፤15) የሚደርሰውን የአካባቢ ብክለትን በመከላከልና በመቆጣጠር ለነዋሪዎቿ ንጹህና ጤናማ አካባቢ መፍጠር፡፡

ግብ 1፡ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል አሰራርን በመዘርጋት አገልግሎት ሰጭና ማምረቻ ተቋማት ላይ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ

ግብ 2፡ የግንዛቢ መፍጠሪያ ሰነድ ማዘጋጀት

ግብ 3፡ግንዛቤ መፍጠር-ለማህበረሰብ፤የብክለት ምንጭ ለሆኑ ተቐማት፤ወዘተ

9
ግብ 4፡ በተዘጋጀው የመረጃ መሰብሰቢያ ፎርማት መሰረት መረጃ መሰብሰብ መጀመር

ግብ 5፡ ከፍተኛ ብክለት እያስከተሉ ያሉ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን መለየት

ግብ 6፡ በሂደቱ ከብክለት ምንጭነት ያልታቀቡ ተቐማትን ለኮሚሽኑ ማሳወቅ

ግብ 7፡ መድረኮች በአካባቢ ብክለት ችግሮችና መፍትሄዎች ላይ ለተለያዩ የወረዳው አገልግሎት ሰጪ ተቐማት የግንዛቤ ማስጨበቻ ስራ መስራት

ግብ 8፡ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ የሚያስፈልጋቸውን ፕሮጀክቶችን አተገባበር መከታተልና መቆጣጠር

ግብ 9፡ በወረዳው ልማትና አካባቢ ተጣጥመው እንዲሄዱ የተለያየ ደረጃ ያላቸው አዳዲስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት/ፕሮጀክቶች ከአካባቢ አንጻር እንዲገመገሙ
ማድረግ

ግብ 10፡ የአካባቢ ብክለት ላይ ለሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ስልጠና የሚያገኙበት መንገድ ማመቻቸት

ግብ 11፡ ምርጥ ተሞክሮዎችን የመቀመርና የማስፋት ስራ መስራት

10

You might also like