Professional Documents
Culture Documents
ለመር ሰብል ፖምኘ ጨረታ ሰነድ-converted
ለመር ሰብል ፖምኘ ጨረታ ሰነድ-converted
የገቢ/ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ስራ ሂደት
ቁጥር
ገቢ/ግ/ፋይ/ንብ/ገ-3/264/2013
ቀን 19/12/2013
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 0011/2013
የደ/ብርሃን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገ/ጽ/ቤት ለ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት
የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ፣ የውሃ ጉድጓድ ሞተር እና ስዊች ቦርድ በዘርፉ ከተሰማሩ ንግድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ
አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፣ ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር ለሚፈልጉ ተጫራቾች፡
1. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቲን ነምበር ሰርተፊኬት
ያለው የግዥ መጠኑ 200,000 ብር እና ከዚያ በላይ የሚሆን ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ
አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፣
2. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ ኦርጅናሉንና ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ የአንዱን ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል በመሙላት
ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ የድምር ስህተት ካለ በአንድ መስመር በመሰረዝ ፖራፍ በማድረግ
የተስተካከለውን በምርመራ አምድ ላይ በትክክል መሙላት ይጠበቅባቸዋል፣
3. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ
የማይመለስ ብር 100/መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል በደ/ብ/ከ/ው/ፍ/አ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት የሚችሉ መሆኑን
እንገልፃለን፣
4. ተጫራቾች ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ ለየብቻው በማዘጋጀት እና እያንዳንዱን ኮፒ እና ኦርጅናል በፖስታው ላይ በማለት በአግባቡ እና
በጥንቃቄ በማሸግ ለቴክኒካል እና ለፋይናንሽያል ሰነድ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን ለየብቻ ለይቶ ማስገባት ይኖርባቸዋል
5. የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ እና በ15ኛው ቀን ድረስ በ11፡29 ሰዓት ክፍት
ሆኖ በዚሁ ቀን 11፡30 ታሽጎ የተጠቀሱት የግዢ አይነቶች ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ወይም በዓልና
እረፍት ቀን ከሆነ በማግስቱ በ3፡00 ሰዓት ቴክኒካል ሰነዱ የሚከፈት ሲሆን ፋይናንሽያል ሰነዱ የሚከፈተው ቴክኒካል ሰነዱ ታይቶ ሲያልቅ
በውስጥ ማስታወቂያ በሚገለፀው ማስታወቂያ መሰረት ይሆናል፡፡
6. የጨረታውን ማስከበሪያ ተጫራቾች የተጫረቱበትን የጠቅላላ ዋጋ 1% በማስላት በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በመ/ቤቱ ገቢ ደረሰኝ
ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል ሆኖም በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዝ ተጫራች ያስያዘበትን ኮፒ በማድረግ በጨረታ ሰነዱ አሽጎ ማቅረብ
ይጠበቅባቸዋል፣
7. አሸናፊ የሚለየው በነጠላ ዝቅተኛ ዋጋ የሞላ ድርጅት ይሆናል፣
8. አሸናፊው ድርጅት ወዲያውኑ ውል ይፈጽማል የውል ማስከበሪያ በአሸነፈበት ብር 10% ያሲዛል፣
9. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም እራሳቸውን ከጨረታው ማግለል
አይቻልም፣
10. ተወዳዳሪዎች እራሳቸውን ከጨረታው ማግለል ቢፈልጉ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማመልከቻ በመፃፍና ሳጥን ውስጥ በማስገባት
ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል ይችላሉ፣
11. አሸናፊው ተጫራቾች ያሸነፋበትን እቃ በራሱ ወጪ ደ/ብ/ው/ፍ/አገ/ጽ/ቤት ቢሮ ማድረስ ይጠበቅበታል፣
12. አሸናፊው ድርጅት መ/ቤቱ በጠየቀው እስፔስፊኬሽን መሠረት እቃውን ማስረከብ ይኖርበታል፣
13. በማስታወቂያው ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
14. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፣
15. አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፣
16. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-681-70-23 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ጠቅላላ ድምር---------------------------------
Vat 15%______________________________________
Total With vat_____________________________________