You are on page 1of 6

በመተማ ወረዳ

ትም/ጽ/ቤት የዕቅድ
ዝግጅት ክትትልና ግምገማ
ቡድን
የ 2011 ዓ.ም የኪራይ
ሰብሳቢነት ማድረቂያ
እቅድ

የዕቅድ ዝግጅት የ 2011 ዓ/ም የፀረ-ኪራይ ሰብሳቢነት ማድረቂያ እቅድ Page 1


ሰኔ 2011 ዓ.ም
ገንዳ ውሃ

መግቢያ

የዕቅድ ዝግጅት ክትልና ግምገማ ቡድን የፀረ ኪራይ ሰብሳቢነት ያለበትን ደረጃ በየጊዜው በመገምገምና
በማስተካከል ቡድናችን ለዜጎች ቀልጣፋ ፣ ዉጤታማና ተጠያቂነት ያለበት አገልግሎት መስጠት
ይጠበቅብናል፡፡ ስለሆነም የቡድናችን የፀረ ኪራይ ሰብሳቢነት ማስፈጸሚያ እቅድ እውን ለማድረግ ሁሉም
ሙያተኞች ለታቀደዉ እቅድ መሳካት ከፍተኛ ርብርብ ማድረግ ተገቢ ነዉ፡፡

በአጠቃላይ ይህ የዕቅድ ዝግጅት ክትልና ግምገማ ቡድን የ 2011 በጀት ዓመት የፀረ ኪራይ ሰብሳቢነት
ማስፈጸሚያ እቅድ ውስጥ የእቅዱ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሰቶች፣ መርሆች፣ ዓላማ፣ የሚከናወኑ ዋና ዋና
ተግባራት፣ ስጋቶችና መፍትሔዎች አካቶ የታቀደ ነው፡፡

የዕቅድ ዝግጅት የ 2011 ዓ/ም የፀረ-ኪራይ ሰብሳቢነት ማድረቂያ እቅድ Page 2


የዕቅድ ዝግጅት ክትልና ግምገማ ቡድን

ተልዕኮ፡- በቡድናችን ቀልጣፋና ዉጤታማ አደረጃጀት አሰራርና የሰዉ ሀይል በመገንባት


በአቋራጭ

መበልፅግናን አድር ባይነትን የሚፀየፍ አመራር፣ ፈፃሚና ደንበኞችን መፍጠር

ራዕይ፡- በቡድናችን ኪራይ ሰብሳቢነትን በመፀየፍ በመርህ ላይ ተመስርቶ ተግባራትን


የሚያከናወን አመራርና

ባለሙያ ተፈጥሮ ማየት ፡፡

እሴቶች

 ሁሌም በመርህ ላይ ተመስርተን ተግባራትን እንፈጽማለን


 ሙስናን እና ኪራይ ሰብሳቢነትን አምርረን እንታገላለን
 የስራ ፍቅር ከበሬታና ስነ-ምግባር መለያችን ይሆናል
 ለተገልጋዮች /ለዜጋዉ/ ፍላጎት ቅድሚያ መስጠት መለያችን ባህላችን እናደርጋለን
 ግልጽነትና ተጠያቂነት እናሰፍናለን
 ቀልጣፋና ዉጤታማነትን እናረጋግጣለን
 ፍትሃዊነትን ማስፈን የመልካም አስተዳደር ገጽታችን ዋነኛ አካል መሆኑን
እንገነዘባለን
 ለዉጥ ናፋቂና አራማጅ እንሆናለን ፡፡

መርሆች

የዕቅድ ዝግጅት የ 2011 ዓ/ም የፀረ-ኪራይ ሰብሳቢነት ማድረቂያ እቅድ Page 3


 የአገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻልና ተገልጋዮች እርካታ እንዲያገኙ የሚያስችል
ስርአት መፍጠር
 ሀቀኛ፣ገለልተኛና ሚዛናዊ የሆነ አገልግሎት መስጠት
 የቅሬታ አቀራረብ ስርአቱን ዉጤታማ ማድረግ
 የተለያዩ መረጃወችን ግልፅ በሆነ መንገድና ቦታ ማስቀመጥ መቻል
 በመልካም የስራ ዲሲፒሊን የታነፀ ሃይል መፍጠር
 ከኪራይ ሰብሳቢነት ነፃ መሆን
 ታማኝና ሚስጥር ጠባቂ መሆን
 ንብረትና በጀትን በአግባቡ መጠቀም
 12 ቱን የስነ-ምግባር መርሆች ማክበርና መከተል

ዓላማ

 የፀረ-ኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና አዝማሚያ ተግባርን በመታግል በሰነ- ምግባሩ የታነፀ ሙያተኛ
፣ደንበኛና ማህበረሰብ በመፈጠር ኪራይ ሰብሳቢነትን የሚፀየፍና የሚጠላ የህብረተሰብ ክፍል
ማፈራት ነዉ፡፡

የሁኔታ ትንተና
በጥንካሬ
 የፀረ-ኪራይ ሰብሳቢነት ከውጤት ተኮር ጋር የተሳሰረ መሆኑ
 ሙያተኛዉ በየዓመቱ ራሱን በሚያሳይ ሁኔታ 2 ጊዜና ሲቀጥልም እንደ አስፈላጊነቱ ሂስና ግለ-ሂስ
ማድረጉና ችግሮችን እየለየ ማሻሻል መቻሉ

በድክመት
 ሙያተኛዉ የሚያሳየዉ የትግል ሁኔታ ከአድርባይነት የተላቀቀ አለመሆኑ
 በሂስና ግለ-ሂስ ወቅት ከተወሰኑ ባለሙያዎች ዉጭ ሂስን ከመቀበል ይልቅ የማኩረፍ ሁኔታ መኖሩ
 በሂስና ግለ-ሂስ ወቅት ሁሉም ባለሙያ በምን አለብኝነት ዝምታን የመምረጥ ሁኔታ መኖሩ

የኪራይ መሰብሰቢያ ምንጭች


1. ከስልጠና መልስ ወደ ስራ ቦታ አለመመለስ
2. መስክ ተመድቦ በድብቅ የመስክ ስራን ትቶ መምጣት
3. ሙያተኛዉ የመንግስትን የመዉጫና የመግቢያ የስራ ስዓት በትክክል አለመጠቀም
4. በሀሰተኛ ምክንያት ፈቃድ መጠየቅ
5. ባልተሰራ ስራ ላይ አበል መጠየቅ

የዕቅድ ዝግጅት የ 2011 ዓ/ም የፀረ-ኪራይ ሰብሳቢነት ማድረቂያ እቅድ Page 4


6. በጽ/ቤቱ ዉስጥ የምንጠቀምባቸዉን እስክብሪቶ፣ወረቀትና ማቴሪያሎችን በአግባቡ
አለመጠቀም ወ.ዘ.ተ የመሳሰሉት ዋና ዋና የኪራይ መሰብሰቢያ ምንጮች ናቸዉ፡፡

ኪራይ ሰብሳቢነትን የማደረቂያ ስልቶች

 በሙያተኞች ላይ የሚታዩትን የክህሎት፣አመለካከት፣የእዉቀትና የግንዛቤ ችግሮችን በተገቢዉ መንገድ


እየገመገሙ እንዲሰተካከል ማድረግ
 የልማት ቡድና የ 1 ለ 5 ዉይይቶችን በመጠቀም በቡድናችን የሚታዩ ዋና ዋና ችግሮችን እየለየን
መፍታት
 በመረጃ አያያዝ፣በአገልግሎት አሠጣጥ የሲ/ሰርቪሱን ሪፎርሞች በመጠቀምና በማስተግበር የላቀ ሚና
እንዲኖር ማደረግ
 የስልጠና ቆይታውን በማረጋገጥ መድረሻወንና የመመለሻውን ቀን በማሳወቅ ወደ ስራ
የሚመለሱበትን ቀን ማሳወቅ
 በጠነከረ ድጋፍና ክትትል ቡድኑ የሲ/ሰርቪሱን ሪፎርሞች እንዲተገብር በማድረግና ኪራይ ሰብሳቢነትን
ባለሙያዎች እንዲታገሉ ማድረግ
ዋና ዋና ግቦች
ግብ 1፡- ከስልጠና መልስ ወደ ስራ ቦታ የሚገቡበትን አስራርን መፍጠር
ግብ 2፡- የተመደበቡትን የመስክ ተግባር በሃላፊነት የሚያከናውኑበት አመለካከት ማስረጽ
ግብ 3፡- የተለያዩ መመሪያዎችን ደንበኞች እንዲያዉቋቸዉ ማድረግና በመመሪያዉ መሰረት ጠያቂ
/ሞጋች ህብረተሰብ መፍጠር
ግብ 4፡- ሁሉም የቡድኑ አባላት በሲ/ሰርቪስ ሪፎርሞች እንዲተዳደሩ ማድረግ መቻል
ግብ 5፡- ማንኛዉንም ደንበኛ በፈገግታ መቀበል ፣በቅንነትና ፣በታማኝነት ሳይጉላሉ ወቅቱን በጠበቀ
ሁኔታ ማስተናገድ ማስቻል
ግብ 6፡ በእያንዳንዱ የትምህርት ተቋም የሚፈፀሙበት የልማትና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ
ከኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና ተግባር የፀዱ መሆኑን ማረጋገጥ፣ ህዝባችንን በለዉጡ ተሳታፊና
ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግና ማንኛዉም የህብረተሰብ ክፍል ከራሱ ጀምሮ ኪራይ ሰብሳቢነትን
ተፀያፊ እንዲሆን ማስቻል፡፡

ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች


 የአጋር አካላት ግንኙነት የላላ መሆኑና ትኩረት ያለመስጠት ችግር መኖር
 የኪራይ ሠብሳቢነት አዝማሚያ በሙተኞች ላይ ሲታይ የጠነከረ ትግል ያለማድረግ ችግር
 በሚደረገዉ ማንኛዉ ግምገማ ላይ ሙያተኛዉ ዝምታን የመምረጥና የአድረባይነት ችግር መኖር

መፍትሔ
 የድጋፍና የክትትላችን ሁኔታ ችግር ፍች እንዲሆን በማድረግ ፣የሲ/ሰርቪስን ሪፎርሞች በማስተግበር የነቃ
ሙያተኛ መፍጠር
 አጋር አካላትን መለየት ፣ማጠናከርና የስራ ድርሻዉን ማሳወቅ

የዕቅድ ዝግጅት የ 2011 ዓ/ም የፀረ-ኪራይ ሰብሳቢነት ማድረቂያ እቅድ Page 5


 ተከታታይነት ያለዉ ዉይይት በማድረግ ሙያተኛዉ በአመለካከት ፣በእዉቀትና፣ የክህሎት ችግሮች
ካሉበት ችግሮችን እንዲቀርፍ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራቸዉ ማድረግ

የዕቅድ ዝግጅት የ 2011 ዓ/ም የፀረ-ኪራይ ሰብሳቢነት ማድረቂያ እቅድ Page 6

You might also like