You are on page 1of 9

በመተማ ወረዳ

ትም/ጽ/ቤት የዕቅድ
ዝግጅት ክትትልና ግምገማ
ቡድን
የ 2011 ዓ.ም
የመልካም አስተዳድር ዕቅድ
ገንዳዉሃ

ሰኔ 2011 ዓ.ም

የዕቅድ ዝግጅት የ 2011 ዓ/ም የመልካም ዓስተዳድር ዕቅድ Page 1


መግቢያ

ጽፈት ቤታችን የህ/ሰቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በልማትና መልካም አስተዳደር ዙሪያ በርካታ ስራዎችን
እየሰራ ይገኛል ፡፡ እስካሁን ባለዉ ሁኔታ በየቡድኑ በርካታ አበረታች ዉጤቶች ተመዝግበዋል ፡፡
እንደቡድን ተቋሞቻችን የተመደበላቸውን አጠቃላይ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ኣና መደበኛ በጀት
በመመሪያውና በቀመሩ መሰረት በመመደብና ክትትል በማድረግ ስራ ላይ በተገቢው መንገድ ስራ ላይ
እንዲያውሉት ወጥነት ያለዉ አሰራርንና ተጠያቂነትን ለማስፈን አበረታች ጥረቶች ማስመዝገብ
ተችሏል፡፡

ኪራይ ሰብሳቢነት በማስወገድና ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ከማሳደግ አኳያ ትክክለኛ ፖሊሲና አቅጣጫ
ተቀምጦ ከየትኛዉም ጊዜ የተሻለ እንቅስቃሴ በመደረጉ ተጨባጭ የሆኑ ዉጤቶችም እየተመዘገቡ
ይገኛሉ፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና በተሰሩ ስራዎችም የማይናቁ ለዉጦች
ታይተዋል፡፡

ነገር ግን መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ አኳያ ገና ያልፈታናቸዉ ችግሮች በርካታ ሆነዉ


እናገኛቸዋለን፡፡ ስለሆነም እንደ ቡድናችን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከምንጩ ለማክሰም
የሚያስችሉ ስልቶችን በመቀየስ ይህን ዕቅድ አቅደናል ፡፡

1. የእቅዱ መነሻ ሁኔታዎች


1.1 የቡድኑ ባለሙያዎች ያሉበት ሁኔታ

የዕቅድ ዝግጅት የ 2011 ዓ/ም የመልካም ዓስተዳድር ዕቅድ Page 2


የቡድኑ ባለሙያዎች በየደረጃዉ ያለዉን የት/ቤት አመራር የግንዛቤ ደረጃ በማሳደግ የት/ቤቶች የዕቅድ
አፈፃፀም ደረጃ በማሻሻል የመንግስትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ፖሊሲዎች ከማሳካት አኳያ
ቁልፍና የማይተካ ሚና አላቸዉ፡፡ በመሆኑም በ 2011 ዓ.ም የቡድኑ ባለሙያዎች ከበላይ አካላት የተሰጡት
ተልዕኮዎች ለማሳካት ርብርብ በማድረግ፤ የአገልግሎት አሰጥጥችንን ለማሻሻል የአስተያየት መስጫ
ደብተር በማዘጋጀት ከደንበኞች አስተያየት በመቀበል እንዲሁም የዜጎች ቻርተር እቅድ በማዘጋጀት
በዕቅዱ ላይ ግልጽነት በመፍጠር እቅዱን ለመፈጸም ጥረት ተደርጓል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የእስካሁኑ
የለዉጥ ሥራችን ውጤት የሚያሳየን ሌላኛው ገፅታም አለ ይሄውም የለውጥ ሥራችን የመንግስት
አደረጃጀቶችና አሠራሮችን በማስተካከል በመጣው ለውጥ ልክ አደረጃጀቱንና አሠራሩን ተጠቅሞ ውጤት
እንዲያስመዘግብ የሚጠበቀው የሰዉ ኃይላችን በአመለካከትና በክህሎት ያሉበትን ክፍተቶች ለይቶ
እነዚህን ክፍተቶች ለማጥበብ ብሎም ለመድፈን የሚያስችል አቅም የመገንባት በዋነኝነት የቡድኑ
ባለሙያዎች ነዉ፡፡ በእስካሁን የለዉጥ ስራችን ሂደት የተስተዋለዉና የት/ቤት አመራሮችን ግንዝቤ
ከማሳደግ ጋር ተያይዞ በግልጽ የታየዉን ጉድለት ከጽ/ቤቱ አመራር ሚና መጓደል ጋር በቀጥታ
የተያያዘዉ መሆኑ የሚታወቅ ነዉ ይህም ሲባል አዳዲስ የሚቀጠሩ ር/መ/ራን፣ ሱ/ዘር እና በተወካይነት
የሚመሩ የት/ቤት አመራሮች እንደመኖራቸው መጠን ለግንዛቤ ማስጨበጫና ለመስክ ድጋፍ የሚዉል
በጀት በበቂ ሁኔታ ባለመመደቡ ለቡድኑ ሙያተኞች የስራ እንቅስቃሴ እንቅፋት ሆኗል፡፡ ሌላዉ ዉስንነት
ደግሞ ቡድኑ ያለ ቡድን መሪ ብዙ ወራትን ማስቆጠሩ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም በቀጣዮ የእቅድ ዘመናችን
የቡድኑን ተገልጋዮች በአግባቡ ግንዛቤአቸዉ እንዲዳብር ለሁሉም የት/ቤት አመራሮች በመስፈርትነት
በማስገባት በቋሚነት በየወሩ በግብረመልስ እየገመገምን የሄድን ቢሆንም የዉጤት ተኮራቸዉ አንዱ አካል
እንዲሆኑ ከማድረግ አኳያና እነዚህ ጉዳዮች በሁሉም አካላት በኩል ተከብረዉ እየተፈፀሙ ስለመሆናቸዉ
በሚታዩ ጉድለቶችቸ ላይ የጋራ የእርምት እርምጃ እየወሰዱ ከማስተካከል አኳያ አሁንም
ያልተሸገርናቸዉ በመሆኑ የእቅዳችን አካል አድርገን ለመጓዝ በሚያስችል ቡድናዊ አሰራር መምራት
አስፈላጊና በልዩ ትኩረት ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ ነዉ፡፡ ስለሆነም በየደረጃዉ ያሉ ባለድርሻ አካላትን
የግንዛቤ ችግሮች በመፍታት በአመለካከት፣በክህሎትና በአቅርቦት ያለዉን ማነቆ በማስወገድ በወረዳችን
ያሉ የት/ቤት አመራሮች የአመለካከት ፣የክህሎትና የአቅም ክፍተቶች ቆጥሮ በመለየት ችግሮችን
ለመፍታት የሚያስችል ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በመስራት የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን
ለመፍታት ከምንጊዜዉም በላይ መስራት ይገባናል ፡፡

1.2 የት/ቤት አመራሩ ያለበት ሁኔታ

በ 2010 በጀት ዘመን የወረዳችን የት/ቤት አመራሮች በተፈጠረላቸዉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች
ከምንግዜዉም በተሻለ ወደ ተግባር ስራ የገቡ ቢሆንም አሁንም ድረስ ያልፈታናቸዉ በርካታ የአሰራር
ክፍተቶች እንዳሉ ማስተዋል ችለናል፡፡ ለአብነት ያህልም በአንዳንድ ተቋማት የዕቃ ግዥ

የዕቅድ ዝግጅት የ 2011 ዓ/ም የመልካም ዓስተዳድር ዕቅድ Page 3


ር/መ/ሩ ንብረት ክፍልም እራሱ፣ የተለያዩ የገቢኛ ወጪ ሞዴሎች አለመኖራቸውና
በመሸኛ የሚሄዱ ተማሪዎችን መሸናውን ለሚመለከተው ሁሉ ብሎ መፃፍ እንዲሁም
የህ/ሰብ ተሳትፎን የተጋነነ አድረጎ መላክ ወዘተ የአፈፃፀም ክፍተቶች ተስተዉለዋል፡፡
ስለሆነም ጠንካራ የመፈጸም አቅም ያለዉ ከኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር የጸዳ
የልማታዊ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ተልዕኮ በተሟላ ሁኔታ ተገንዝቦ ይህንኑ መፈጸም
የሚችል እዉቀት አመለካትና ክህሎት ያለዉ የት/ቤት አመራር በሚፈለገዉ ደረጃ
አልተፈጠረም፡፡

በመሆኑም የአሰራር ስርአቱን ግልጽነት ለማሻሻል የተጠያቂነት ስሜት ይበልጥ ለማዳበር


በተለይም የልማታዊ የት/ቤት አመራር ግልጽነት ይዞ በብቃት በመፈጸም የጸና
አመለካከት ያለዉና በክህሎቱ የዳበረ የት/ቤት አመራር ለመፍጠር ትልቅ ጥረት መደረግ
አለበት፡፡

2. የመልካም አስተዳደር ዋና ዋና ችግሮችና መግለጫዎች


2.1 ከአመለካከት አንጻር
 በመልካም አስተዳደር ዙሪያ የሚመጡ ለዉጦችን ከራሱ አቅም ጋር እያዛመዱ
መስጋት
 ከሌሎች ባለሙያዎች ልምድን በመቅሰም ራስን አለማዘጋጀት
 ተሞክሮዎችን አለመተንተን ፤አለመቀመርና ለማስፋፋት ጥረት አለማድረግ
2.2. ከክህሎት አንጻር
 የአሰራር መመሪያዎችን አውቆ አለመተግበር
 ለት/ቤቶች የሚመደብላቸውን በጀት በመመሪያው መሰረት አለመጠቀም
 የት/ቤት አመራሮች በሚላኩ ቸክሊስቶች ተረድቶና ተገንዝቦ ተግባራቶችን
የመፈጸምና የማስፈጸም ችግር
2.3 ከግብዓት አንጻር

ተቋማት ራሱን በቻለ ር/መ/ር አለመመራት



ለቡድኑ ተግባራት ማስፈጸሚያ የሚዉል በጀት ያልተመደበለት መሆኑ

የኮፒ ማሽን ወይም የሪዝዮ ግራፊ መሳሪያ በተቋሙ ባለመኖሩ ስነዶችንና

ቸክሊስቶችን ለየተቋማት አባዝቶ ለማሰራጨት አስቸጋሪ መሆኑ
3. የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ቡድን የመልካም አስተዳደር ዕቅድ

3.1 የመልካም አስተዳደር እቅዱ አስፈላጊነት

የዕቅድ ዝግጅት የ 2011 ዓ/ም የመልካም ዓስተዳድር ዕቅድ Page 4


በቡድናችን እየታየ ያለዉን የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራትን ስኬት በተሻለ
መንገድ፣በተፋጠነና ዘላቂነት ባለዉ መንገድ ለማስቀጠል በአገልግሎት ሰጭዉና አገልግሎት
ተቀባዩ በኩል እየታየ ያለዉን የአፈጻጸም ወይም የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር አንጻር
የሚፈልገዉን ለዉጥ ለማምጣት በተደራጀና በተቀናጀ መንገድ ለመንቀሳቀስ የቡድኑ
ባለሙያዎችና የት/ቤት አመራሮች በእኩልነት ቀልጣፋነቱንና ዉጤታማነቱን ያረጋገጠ
አስተማማኝ እምርታ ያለው መልካም አስተዳደር ለማስፈን ነዉ፡፡

1. 1 ሊቀረፉ የሚገባቸው የመልካም አስተዳደር ችግሮች


 ለቡድኑ የሚላኩ የአቋራጭ ተማሪ መረጃ እና የህብረተሰብ ተሳትፎ ስራዎችንና የበጀት
አጠቃቀም ሪፖርቶች በቋሚ መረጃ በትክክል መዝግቦ አለማያዝ
 ለት/ቤቶች የተመደበውን በጀት ለሚወስዱ አካላት የሚጠበቅባቸውን አስፈላጊ ነገሮች
አሟልተው እንዲመጡ አለማድረግ
 የትስመ መረጃን ለሚሞሉ ር/መ/ራን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና አለመስጠት
 የት/ቤት አመራሮች ትክክለኛ መራጃ/ሪፖርት አለማላክ
 የትስመ መረጃን ሞልተው ለሚያስረክቡ እና በጀትን ለማወራረድ ለሚመጡ ር/መ/ራን
በፕሮግራም ከፋፍሎ መድቦ አለማሳወቅ
 የት/ቤት አመራሮች በጀቱን ለማወራረድ የሚያስፈልጉ ሰነዶችን በግልጽ አለማሳወቅ
3.2 ለእቅዱ መፈጸም ምቹ ሁኔታዎች
 የቡድኑ አባላት የተሟላ የሰው ሀይል መኖሩ
 ሁሉም ተግባራትና እንቅስቃሴዎች በመርህ ላይ ተመስርቶ የሚደረግ መሆኑ
 ልማትንና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ቁርጠኛ አቋም ያለዉ መሆኑ
 ልዩ ልዩ አደረጃጀቶችና አሰራሮች እስከ ታችኛዉ አካል ድረስ የተዘረጉ መሆኑ
 የተገልጋዮች የአስተያየት መስጫ ደብትር መዘጋጀቱ
 ተገልጋዩ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚሰማዉን አስተያት መስጠት የሚችልበት
የአስተያየት መስጫ ደብተር መኖሩ
 በተገልጋዮች የአገልግሎት አሰጣጥ እርካታ ዙሪያ የዳሰሳ ጥናት የሚደረግ መሆኑ
 የዜጎች ቻርተር መዘጋጀቱ በአገልግሎት ሰጭውና በአገልግሎት ተቀባዩ የሚደረግ
ስምምነት

3.3 ስጋቶች
 ተግባሩን በክትትልና ግምገማ አለመምራት
 በወቅታዊ ተግባራት መጠመድ ምክንያት ማድረግ
 የኮፒ ማሽን አገልግሎት ያለማግኘት ችግር
 የመልካም አስተዳደር መስፈን ሚናን አሳንሶ ማየትና ከልማቱ ሰራ ጋር አስተሳስሮ
አለማየት

የዕቅድ ዝግጅት የ 2011 ዓ/ም የመልካም ዓስተዳድር ዕቅድ Page 5


3.4 ዓላማ
 የቀልጣፋና ዉጤታማ አገልግሎት በመስጠትና በመቀበል ሂደት ላይ የሚያጋጥሙ
የሰራ ችግሮችን ለማቃለልና ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገትን ለማፋጠን አመች
ሁኔታ መፍጠር
 በተገልጋይ ህ/ሰብ የነቃ ተሳትፎ መልካም አስተዳደርን በላቀ ደረጃ ማረጋጥ
 ፍትሃዊ ቀልጣፋ አገልግሎትን መስጠቱን ማረጋገጥ
 ከቡድናች አስከ ት/ቤት ተቋማት የሚገኙ 3 ቱን ኃይሎች /መንግስት፣ድርጅትና
ህዝብ/ ተቀናጅተዉ የ 5 ዓመቱን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በማሳካት
መልካም አስተዳደር ማስፈን

3.5 ግብ

 ዉጤታማና ቀልጣፋ እንዲሁም ወጭ ቆጣቢ አገልግሎት በመስጠት መልካም


አስተዳደር እንዲሰፍን ማድረግ
 ለተገልጋዮች ፍትሃዊ ግልጽና ዉጤታማ አገልግሎት ለማበርከትና ለፍላጎታቸዉ
አፋጣኝ መልስ መስጠት
 የልማት የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ግቦችን በተሟላ
መንገድ ለማሳካት
 ተነሳሽነቱ ከፍተኛ የሆነ በሙያተኛውና በመርሱዎች ተቀባይነት በተለይም ኪራይ
ሰብሳቢነት አመለካትን ለመናድ በጽናት የሚታገል ሙያተኛ መፍጠር
 በአሰራር አደረጃጀትና በአመለካከት የሚታዩ ክፍተቶች ለይቶ በማዉጣት
መርሱዎች የሚፈልጓቸዉን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መመለስ
 የህዝብ አገልጋይነት አመለካከት ማዳበር
 ተደራሽ ያልሆነ አገልግሎቶችን ተደራሽ በማድረግ የመርሱዎች እንግልት መቀነስ
ከመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ ፈጻሚዎችንና መርሱዎችን በማነቃነቅ
የተጀመረዉን የልማት ሰራ ግንባታ ተግባር ማጠናቀር
 በተለያየ ምክንያት ምላሽ ያልተሰጠዉን ለይቶ በመፍታት የመርሱዎች እርካታ
ማሳደግ
 ከቡድናችን እስከ ት/ቤት ተቋማት ድረስ ባለዉ እርከን የሚስተዋሉ /የሚታዩ/
የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት

4 በቡድኑ ዉስጥ የተለያዩ የመልካም አስተዳር ችግሮችን ለመፍታት የተቀመጡ


የመፍትሄ ሃሳቦች

 በተለያዩ የመልካም አስተዳር ችግሮችና መፍትሄዎች ዙሪያ ለቡድኑ ሙያተኞች እና ለት/ቤት


አመራሮች ግንዛቤ መፍጠር
 ለአገልግሎት አሰጣጥ አጋዥ የሆኑ የፈጣን አገልግሎት አምጭ /quick wines/ በቋሚነት ማሟላትና
ሰነዶችን የተሟሉ ማድረግ

የዕቅድ ዝግጅት የ 2011 ዓ/ም የመልካም ዓስተዳድር ዕቅድ Page 6


 ለተገልጋዮች በራሪ ወረቀቶችን በማዘጋጀት መብቶቻቸዉና በግዴታቸዉ ዙሪያ ግንዛቤ የማስጨበጥ
ስራ መስራት

5 የሚከናወኑ ተግባራት
 በየሩብ ዓመቱ በቡድናችን ደረጃ በመልካም አስተዳር የመጡ ለዉጦችን ያጋጠሙ
ችግሮች የተሰጡ መፍትሄዎችንና ያልተፈቱ ችግሮችን ከነምክንያታቸዉ
በመገምገም አቅጣጫ ያስቀምጣል፡፡
 በቼክሊስቶች የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችና ግብረ በማዘጋጀት ለጉድኝትና
ለተቋማት መላክ
 አሰራርና አደረጃጀቶችን ማጠናከር
 የመልካም አስተዳደር ማሻሻያ ተግባሮችን መፈጸምና የአፈጻጸም አቅጣጫዎችን
ማጠናከር
 የቡድናችን የተገልጋይ እርካታ ማረጋገጥ
 በተቋማት ደረጃ የሚገኙ ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች በእቅዳቸዉ መሰረት
ተግባራቸዉን እንዲፈጽሙ ማስቻል፡፡
 በቡድኑ ደረጃ የተዘጋጀዉ የመልካም አስተዳደር እቅድ ላይ ለጉድኝት ማዕከል
ሱ/ዘሮች እውቅና መፍጠር
 የተገኙ ዉጤቶችን የመመዝገብና የማረጋገጥ ስራ መስራት

6 .የክትትልና ግምገማ ስርዓት


 የልማት እና የመልካም አስተዳደር እቅዶች በአግባቡ መፈጸማቸዉን መከተልና ማረም
 በአፈጻጸም ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮች ካሉ በየደረጃዉ በማስተካከል የእርምት እርምጃ
መዉሰድ
 በሩብ አመት አንድ ጊዜ የቡድኑ ባለሙያዎችና የት/ቤት አመራሮች በተገኙበት አፈጻጸሙን
በመገምገም የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥ
 በአመቱ ማጠቃለያ የጽ/ቤቱ ኃላፊ፤ የቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት አፈጻጸሙን
እንዲገመግም በማድረግ ስራዎችን በደረጃ መለየትና ችግሮችን ለይቶ የመፍትሄ አቅጣጫ
ማስቀመጥ ዋና ዋናወቹ ናቸዉ ፡፡

የዕቅድ ዝግጅት የ 2011 ዓ/ም የመልካም ዓስተዳድር ዕቅድ Page 7


7. የድርጊት መርሃ ግብር


.
በተቋሙ የተለያዩ የመ/አስ/ችግሮች ለመፍታት
ቁ የተቀመጡ የመፍትሄ ሀሳቦች የሚፈቱበት ፈጻሚ አካላት
ጊዜ
በአጭር
ጊዜ በመካከለኛ
በረጅም
ጊዜ ጊዜ
1 ለቡድኑ የሚላኩ የአቋራጭ ተማሪ መረጃ እና 
የህብረተሰብ ተሳትፎ ስራዎችንና የበጀት
* የቡድኑ ሙያተኞች
አጠቃቀም ሪፖርቶች በቋሚ መረጃ በትክክል
መዝግቦ መያዝ

2 ለት/ቤቶች የተመደበውን በጀት ለሚወስዱ 


አካላት የሚጠበቅባቸውን አስፈላጊ ነገሮች
* የቡድኑ
አሟልተው እንዲመጡ ማድረግ ሙያተኞች

3 የትስመ መረጃን ለሚሞሉ ር/መ/ራን የግንዛቤ 


ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት * የቡድኑ
ሙያተኞች
* የጽ/ቤት ሀላፊ
4 የት/ቤት አመራሮች ትክክለኛ መራጃ/ሪፖርት 
እንዲልኩ ማድረግ * የቡድኑ
ሙያተኞች
5 የትስመ መረጃን ሞልተው ለሚያስረክቡ እና 
በጀትን ለማወራረድ ለሚመጡ ር/መ/ራን
* የቡድኑ ሙያተኞች
በፕሮግራም ከፋፍሎ መድቦ ማሳወቅ * ፋይናንስ

6 የት/ቤት አመራሮች በጀቱን ለማወራረድ 

የሚያስፈልጉ ሰነዶችን በግልጽ ማሳወቅ * የቡድኑ


ሙያተኞች

ማሳሰቢያ ፡- በአጭር ጊዜ የሚፈታ ማለት እስከ ጥቅምት 30/2011 ዓ.ም የመካከለኛ ጊዜ ማለት እስከ
ጥር 30 ሲሆን የረጅም ጊዜ ማለት ደግሞ እስከ ዓመት መጨረሻ ድረስ የሚፈቱ ማለት ነዉ ፡፡

የዕቅድ ዝግጅት የ 2011 ዓ/ም የመልካም ዓስተዳድር ዕቅድ Page 8


የዕቅድ ዝግጅት የ 2011 ዓ/ም የመልካም ዓስተዳድር ዕቅድ Page 9

You might also like