You are on page 1of 24

Daniel Fikadu Law Office. https://t.

me/lawethiopiacomment

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ


FEDERAL NEGARIT GAZETTE
OF THE FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA

ሃያ ዘጠነኛ ዓመት ቁጥር ፲፱ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 29th Year No 19


አዲስ አበባ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም ADDIS ABABA, 18th April, 2023
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ

ማውጫ Content
አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፪፻፹፬/፪ሺ፲፭ Proclamation No. 1284/2023

የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ አዋጅ Ethiopian Digital Identification Proclamation


…………………………ገጽ ፲፬ሺ፯፻፲፭ …….......................................................Page 14715

አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፪፻፹፬/፪ሺ፲፭ PROCLAMATION NO. 1284 /2023


የኢትየጵያ ዲጂታል መታወቂያ አዋጅ ETHIOPIAN DIGITAL IDENTIFICATION
PROCLAMATION
በኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት WHEREAS, the establishment of a reliable
መዘርጋት ነዋሪዎች የመታወቅ መብታቸው Digital Identification System in Ethiopia
እንዲረጋገጥ፣ ሌሎች መብቶችን የመጠቀም እድሎችን ensures the Resident’s right to be identified,
ለማስፋት፣ የአገልግሎት ሰጪና ተቀባይ መካከል በሚኖር enhances the ability to exercise other rights,

ግንኙነት ላይ እምነት እንዲዳብር፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ improves trust between service providers and

የግልጽነት፣ የተጠያቂነት እና የተሳለጠ አሠራር residents, creates a nationwide enabling


environment to ensure transparency,
ሥርዓትን ለመዘርጋት የሚያስችል በመሆኑ፤
accountability and efficiency;

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment

ÃNÇ êU nU¶T Uz¤È ±.œ.q.Ü *¹þ1


Unit Price Negarit G. P.O.Box 80001
gA ፲፬ሺ፯፻፲፮ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፱ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ›.M Federal Negarit Gazette No.19, 18th April, 2023 …… page 14716

በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የበለፀገ፣ ዘርፍ ተሻጋሪ፣ WHEREAS, establishing a technologically


መሠረታዊ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት መዘርጋት፤ developed, cross sectorial foundational Digital

ሀገራዊ ልማትን በአግባቡ ለማቀድ፣ ምጣኔ ሃብታዊ Identification System, helps to plan national

ሽግግር ለመፍጠር፣ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን፣ development effectively, create economic

የሀብት ብክነትን ለመቀነስ፣ ፖሊሲዎች ሲቀረጹ እና transformation, ensure good governance,


reduce wastage of resources, eliminate
የልማት ሥራዎች ሲከናወኑ ድግግሞሽን ለመቅረፍ እና
redundancy and ensure inclusiveness when
አካታችነትን ለማጎልበት የሚረዳ በመሆኑ፤
policies are designed and development plans
are executed;

የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት በሀገር አቀፍ ደረጃ WHEREAS, establishing a nationwide


በመዘርጋት፣ አስተማማኝ፣ ተደራሽ እና ሚስጥራዊነቱ Digital Identification System is important to
የተጠበቀ ሥርዓትን ማጎልበት፣ የሀገሪቱን ማኅበራዊ፣ institute a reliable, accessible and secured

ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እና ተገማችነትን system, and to promote the country's social,

ለማሳደግ፤ የነዋሪዎችን ሁለንተናዊ ሰላምና ደህንነትን political and economic development and

ለማረጋገጥና የፍትሕ ሥርዓቱን ለማጠናከር የሚረዳ


predictability, to ensure the overall peace and
security of Residents and reinforcing the
በመሆኑ፤
justice system;

ሁሉን አቀፍ፣ ወጥና አስተማማኝ በሆነ ሁኔታ WHEREAS, it is necessary to establish a


የሀገሪቱ ነዋሪዎች የሚመዘገቡበትን ዲጂታል መታወቂያ legal basis for the use of Digital Identification

ሥርዓት በመዘርጋት እና የተመዝጋቢዎችን መረጃ in a comprehensive, consistent and reliable

በመያዝ የዲጂታል መታወቂያ አጠቃቀም ሥርዓትን method by establishing a Digital Identification

ሕጋዊ መሠረት እንዲኖረው ለማድረግ፤ በዲጂታል


System for the registration of Residents of the
country and by retaining the information of the
መታወቂያ ሥርዓቱ ውስጥ ባሉ የተለያዩ አካላት
Registrants; properly define the trust
ማለትም ተመዝጋቢ፣ መዝጋቢ፣ ተጠቃሚ አካላት፣
framework and legalize the relationship
አረጋጋጭ አካላት እና በዲጂታል መታወቂያ ተቋም
between the various stakeholders of the Digital
መካከል የሚኖረውን ግንኙነት በሕግ የሚመራበትን
Identification System, including the Registrant,
የመተማመኛ ማዕቀፍ መዘርጋት በማስፈለጉ፤
Registrar, Relying Party, Authentication
Service Provider and the Digital Identification
Institution;

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ NOW, THEREFORE, in accordance with


መንግሥት አንቀጽ ፶፭ (፩) መሠረት የሚከተለው Article 55(1) of the Constitution of the Federal
ታውጇል። Democratic Republic of Ethiopia, it is hereby
proclaimed as follows.

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment


gA ፲፬ሺ፯፻፲፯ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፱ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ›.M Federal Negarit Gazette No.19, 18th April, 2023 …… page 14717

ክፍል አንድ SECTION ONE


ጠቅላላ ድንጋጌዎች General Provisions

፩. አጭር ርዕስ 1. Short Title


ይህ አዋጅ “የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ አዋጅ This Proclamation may be cited as

ቁጥር ፩ሺ፪፻፹፬/፪ሺ፲፭” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል። “Ethiopian Digital Identification


Proclamation No. 1284/2023.”
፪. ትርጓሜ 2. Definition
የቃሉ አገባብ የተለየ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ Unless the context requires otherwise in this
በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፦ Proclamation:
፩/ “መሠረታዊ መታወቂያ” ማለት በአንድ ነዋሪ ልዩ 1/ “Foundational Identification” means a

ማንነት ላይ በመመስረት አገልግሎቶችን በቀላሉ legal identifier that enables Resident to

ለማግኘት የሚያስችል ሕጋዊ መለያ ነው፤ access sesrvices by making use of his
unique identity;
፪/ “የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት” ማለት 2/ “Digital Identification System” means
የዲሞግራፊክ እና ባዮሜትሪክ መረጃ መዝግቦ an organized and reliable Foundational
በማዕከላዊ ቋት በመያዝና ለእያንዳንዱ ነዋሪ Identification system that provides a
ልዩ ቁጥር በመሥጠት የተደራጀ እና Unique Number to each Resident by

አስተማማኝ መሠረታዊ የመታወቂያ ሥርዓት collecting Demographic and Biometric

ነው፤ Data in a central database;

፫/ “የዲጂታል መታወቂያ” ማለት በዲጂታል 3/ “Digital Identification” means a

መታወቂያ ሥርዓት ውስጥ ለተመዘገበ ነዋሪ Foundational Identification with a

የሚሰጥ ልዩ ቁጥር ያለው መለያ ነው፤ Unique Number that is issued to a


resident that is registered on the Digital
Identification System;
፬/ “የህፃናት ዲጂታል መታወቂያ” ማለት በተቋሙ 4/ “Minor Digital Identification” is a type
አሠራር መሠረት የሚወሰንና ለአካለ መጠን of temporary Digital Identification
ላልደረሰ ህፃን ያለ ባዮሜትሪክ መረጃ የሚሰጥ issued without collecting Biometric
ልዩ ቁጥር ያለው ጊዜያዊ የዲጂታል መታወቂያ Data to a minor as defined per the

ዓይነት ነው፤ guidelines of the Institution;

፭/ “ባዮሜትሪክ መረጃ” ማለት የጣት አሻራ፣ የዐይን 5/ “Biometric Data’’ means physical
ብሌንና የፊት ገፅታ ምስልን በስሌት ለመያዝ attributes that can be computed off of a

የሚቻሉ የአንድ የተፈጥሮ ሰው ልዩ የሰውነት natural person such as fingerprints, iris

አካላዊ መለያዎች ናቸው፤ and facial photo used for unique


calculation of a person’s identity;

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment


gA ፲፬ሺ፯፻፲፰ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፱ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ›.M Federal Negarit Gazette No.19, 18th April, 2023 …… page 14718

፮/ “የዲሞግራፊክ መረጃ” ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ 6/ “Demographic Data’’ means the non-
፱ የተጠቀሱት ወደ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት biometric personal attributes of a resident

የሚገቡ የተመዝጋቢ መረጃዎች ሲሆኑ entered into the Digital Identification

የባዮሜትሪክ መረጃን አይጨምርም፤ System, referred in Article 9 of this


Proclamation;
፯/ “ልዩ ቁጥር” ማለት በዲጂታል መታወቂያ 7/ “Unique Number” means a special, and
ሥርዓት ውስጥ አንድ ነዋሪ ስኬታማ non-repeating number issued to a
የባዮሜትሪክ እና የዲሞግራፊክ መረጃዎችን Registrant by the Digital Identification
ምዝገባን ሲያጠናቅቅ ለተመዝጋቢ የሚሰጥ System after a successful registration of
ልዩ፣ ተደጋጋሚ ያልሆነ ቁጥር ሲሆን፤ በልዩ Biometric and Demographic Data and
ሁኔታ ተቋሙ በሚሰጠው ውሳኔ ካልሆነ once issued, it is permanent unless in
በስተቀር፤ አንድ ጊዜ ለተመዝጋቢ ከተሰጠ exceptional circumstances defined by

የማይለወጥ ቋሚ ቁጥር ነው፤ the Institution;

፰/ “ተለዋጭ ቁጥር’’ ማለት ከዲጂታል መታወቂያ 8/ “Alias Number” is a Unique Number


generated one or more times from the
ጋር በሚስጥራዊ ሁኔታ የተያያዘ፤
Digital Identification System to be
የተመዝጋቢን ግላዊነት ለመጠበቅ በሚያስችል
securely and privately associated with
መልኩ ከዲጂታል መታወቂያ ሥርዓቱ አንድም
the unique Digital Identification of the
ሆነ ከዛ በላይ ሊፈጠር የሚችል ልዩ ቁጥር
Resident;
ነው፤

፱/ ‘‘ተቋም’’ ማለት የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓትን 9/ “Institution’’ means a Govenmental


የሚያስተገብርና ይህንን አዋጅ የሚያስፈጽም Digital Identification entity that will
መንግሥታዊ የዲጂታል መታወቂያ ተቋም implement the Digital Identification
ወይም እንደአስፈላጊነቱ ለሥራው አግባብነት System and execute this Proclamation

ያለው መንግሥታዊ ተቋም ውስጥ የሚደራጅ or it may be an office established within

ጽህፈት ቤት ሊሆን ይችላል፤ a relevant Government body;

፲/ “ነዋሪ” ማለት በፍትሐብሄር ሕጉ አንቀጽ ፩፻፸፬ 10/ “Resident” means a natural person

እና ፩፻፸፭ የተመለከተውን የመኖሪያ ቦታ living in Ethiopia fulfilling the


requirement of residence place provided
መስፈርት በሚያሟላ አግባብ በሀገሪቱ ውስጥ
in Article 174 and 175 of the Civil Code
የሚኖር ወይም አግባብ ባለው ሕግ መሠረት
or living in Ethiopia by obtaining
በሚመለከተው አካል ፈቃድ አግኝቶ የሚኖር
residence permit from relevant authority;
የተፈጥሮ ሰው ነው፤

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment


gA ፲፬ሺ፯፻፲፱ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፱ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ›.M Federal Negarit Gazette No.19, 18th April, 2023 …… page 14719

፲፩/ “ተመዝጋቢ” ማለት የዲሞግራፊክ እና 11/ “Registrant” means a resident person


የባዮሜትሪክ መረጃ በመስጠት፣ ምዝገባ who receives a Digital Identification

አከናውኖ የዲጂታል መታወቂያ የሚሰጠው ነዋሪ after providing his Demographic and

የሆነ ሰው ነው፤ Biometric data;

፲፪/ “መዝጋቢ አካል” ማለት የዲጂታል መታወቂያ 12/ “Registrar” means the Digital
Identification Institution or a person
ተቋም ወይም በተቋሙ በሚሠጥ ፈቃድ ወይም
entrusted by the Institution to collect
ውክልና መሠረት የተመዝጋቢን መረጃ
the individuals’ data;
የሚሰበስብ ሰው ነው፤

፲፫/ “ምዝገባ” ማለት ከመዝጋቢ አካል ወደ ዲጂታል 13/ “Registration’’ means the process of

መታወቂያ ሥርዓቱ የተላከ የተመዝጋቢ enrolling a Registrant, through a

መረጃን ልዩ በሆነ ሁኔታ በማረጋገጥ unique deduplication process of


personal data sent by the Registrar to
የመመዝገብ ሂደት ነው፤
the Digital Identification System;
፲፬/ “ተጠቃሚ አካል” ማለት ከዲጂታል መታወቂያ 14/ “Relying Party” means a person that

ተቋም እና ከግለሰቡ በተሰጠ ፈቃድ እና መረጃ authenticates an individual's identity,

ላይ ተመሥርቶ የግለሰብ ማንነትን with the knowledge and consent of the


Digital Identification Institution and
የሚያረጋገጥ ሰው ነው፤
the individual;
፲፭/ “ማረጋገጥ’’ ማለት ከዲጂታል መታወቂያ 15/ “Authentication”means the process of
ሥርዓት ማእከላዊ መረጃ ቋት ጋር ቀጥታ verifying and authenticating, whether
በኔትዎርክ ወይም ያለኔትዎርክ በማመሳከር online or offline, the identity of an
የግለሰብን ማንነት የማጣራትና ማረጋገጫ individual against the registered

የመስጠት ሂደት ነው፤ information in the Digital


Identification System central
database;

፲፮/ “አረጋጋጭ አካል’’ ማለት የዲጂታል መታወቂያ 16/ “Authentication Service Provider’’

መረጃዎች ከተጠቃሚ አካል በሚቀርብ ጥያቄ means a person that responds to a

የማረጋገጥ አገልግሎት የሚሰጥ ሰው ነው፤


request for authentication of Digital
Identification Data at the inquiry of a
Relying Party;

፲፯/ “የግል መረጃ” ማለት በዲጂታል መታወቂያ 17/ “Personal Data” means Biometric Data
collected with the Digital Identification
ሥርዓት የሚሰበሰቡ የባዮሜትሪክ እና በዚህ
System and Demographic Data indicated
አዋጅ አንቀፅ ፱ ላይ የተመለከቱት የዲሞግራፊክ
under Article 9 of this Proclamation;
መረጃዎች ናቸው፤

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment


gA ፲፬ሺ፯፻፳ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፱ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ›.M Federal Negarit Gazette No.19, 18th April, 2023 …… page 14720

፲፰/ “ጥንቃቄ የሚፈልግ የግል መረጃ” ማለት:- 18/ “Sensitive Personal Data” means data
on a natural person:
ሀ) ብሔርን፣
a) racial or ethnic origins,
ለ) የዘረመልን፣
b) genetic data,
ሐ) የአካላዊ ወይም የአዕምሯዊ ጤንነት ወይም c) physical or mental health or

ሁኔታን፣ condition,

መ) የፖለቲካ አመለካከትን፣ d) political opinion,

ሠ) ሃይማኖትን ወይም ሌላ ሃይማኖት ነክ e) religious beliefs or other beliefs of a

አስተሳሰብን፣ similar nature,


f) the commission or alleged
ረ) የተፈጸመ ወይም ተፈጸመ የተባለ ወንጀልን፤
commission of an offense,
ሰ) የተፈጸመ ወይም ተፈጸመ የተባለ ወንጀልን g) any proceedings for an offense
አስመልክቶ የተካሄዱ ሂደቶችን፣ እነዚህ committed or alleged to have been
ሂደቶች የተጠናቀቁበት መደምደሚያን ወይም committed, the disposal of such

በሂደቶቹ ዙሪያ ፍርድ ቤቶች የሰጡት የቅጣት proceedings or the sentence of any

ውሳኔን፣ court in the proceedings,

ሸ) በተቋሙ ወይም ሌሎች ሥልጣን ባላቸው h) any other personal data as the
ተቋማት የሚወሰኑ ጥንቃቄ የሚፈልጉ የግል Institution or other authorized
መረጃዎችን ሊጨምር ይችላል:: entities may determine to be
sensitive personal data.
፲፱/ “የዲጂታል መታወቂያ ማስረጃ” ማለት ልዩ 19/ “Digital Identification Credential’’
የመታወቂያ ቁጥር ወይም ተለዋጭ ቁጥርና means a physical or Digital
የተመዝጋቢ መረጃ የያዘ በቁሳዊ ወይም documentary evidence containing

በዲጂታል አማራጭ የሚዘጋጅ የሰነድ ማስረጃ Personal Data and either the Unique

ነው፤ Identification Number or Alias


Number;

፳/ “ክልል” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ


20/ “Region” means a Region established
in accordance with Article 47 of the
ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ
Constitution of the Federal Democratic
፵፯ መሠረት የተቋቋመ ክልል ሲሆን ለዚህ
Republic of Ethiopia and for the
አዋጅ ዓላማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና
purpose of this Proclamation, it
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን ይጨምራል፤
includes Addis Ababa City
Administration and Dire Dawa City
Administration;

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment


፲፬ሺ፯፻፳፩
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፱ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ›.M Federal Negarit Gazette No.19, 18th April, 2023 …… page 14721

፳፩/ “መንግሥት” ማለት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ 21/ “Government” means the Government
ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ሲሆን of the Federal Democratic Republic of

ለዚህ አዋጅ ዓላማ የክልሎች አስተዳደሮችንም Ethiopia; and for the purpose of this

ያካትታል፤ Proclamation, it includes Regional


Administrations;
፳፪/ “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ 22/ “Person” means any natural or
የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፤ Juridical person;

፳፫/ በዚህ አዋጅ ውስጥ በወንድ ፆታ የተገለፀው 23/ In this Proclamation, any phrase
የሴትንም ፆታ ይጨምራል፡፡ expressed with a masculine gender
includes the feminine gender.

፫. የተፈጻሚነት ወሰን 3. Scope of Application


ይህ አዋጅ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኝ በማንኛውም ሰው This Proclamation shall be applicable on any
ላይ ተፈጻሚ ይሆናል። person in Ethiopia.

፬. ዓላማዎች 4. Objectives

የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የሚከተሉት The Digital Identification System shall have
the following Objectives: -
ዓላማዎች ይኖሩታል፡-

፩/ ነዋሪዎች በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ሲንቀሳቀሱ 1/ To contribute to the protection of human


በቀላሉ የመታወቅ መብታቸው እንዲረጋገጥ rights and the improvement of good
በማድረግ ለሰብአዊ መብቶች አከባበር እና ለመልካም governance by ensuring that residents’
አስተዳደር መሻሻል አስተዋፅኦ ማድረግ፤ right to be easily identified when they
move from place to place in the country;
፪/ አገልግሎት ማግኘት የሚፈልጉ ግለሠቦችን በቀላሉ 2/ To establish a Digital Identification
ለመለየት የሚያስችል የዲጂታል መታወቂያ System that allows easy identification of
ሥርአት በመዘርጋት በአገልግሎት ሰጪ እና individuals who want to receive services,
አገልግሎት ተቀባይ መካከል እምነት አንዲጎለብት to build trust between service providers
ማድረግ፣ ሕገ-ወጥ ተግባራትን መከላከል፤ and service recipients, and prevent illegal
activities;

፫/ ሀገር አቀፍ የዲጂታል መታወቂያ ሥርአት ሀገራዊ 3/ To address duplication of efforts in the

ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች እና ዕቅዶች ሲቀረፁ እና preparation of national policies,

የልማት ሥራዎች ሲከናወኑ ድግግሞሽን መቅረፍ፤


strategies, plans and in undertaking
development activities; thereby reducing
በዚህም የሃብት ብክነትን መቀነስ እና አካታችነትን
resource wastage and enhancing
ማጎልበት፤
inclusiveness;

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment


gA ፲፬ሺ፯፻፳፪ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፱ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ›.M Federal Negarit Gazette No.19, 18th April, 2023 …… page 14722

፬/ የዜጎችን የዲሞግራፊክ እና ባዮሜትሪክ መረጃ 4/ To collect demographic and biometric


ለመሰብሰብ የሚያስችል አንዲሁም፤ በዘርፉም ሆነ data of residents by establishing a system

በክልል አደረጃጀት ያልተገደበ በብሔራዊ ደረጃ that is consistent at the national level,

ተናባቢ የሆነ ሥርአት በመዘርጋት፤ ለሌሎች which is not limited by sector or regional

መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ላልሆኑ አካላት states and to serve as a source of


identification system for other
የመታወቂያ ሥርአት የመረጃ ምንጭ ሆኖ
governmental and non-governmental
ማገልገል፤ አገልግሎት ተኮር የሆኑ የመታወቂያ
entities; to ensure the transition of
ሥርአቶች ወደ ዲጂታል መታወቂያ ሥርአት
service-oriented identifications to a
እንዲሸጋገሩ ማጠናከር፡፡
Digital Identification System.
፭. ተቋም ስለማቋቋም 5. Establishing Instituion
በዚህ አዋጅ መሠረት የዲጂታል መታወቂያን ሥርዓት The Council of Ministers may establish by

በተመለከተ የተደነገጉ ተግባርና ኃላፊነቶችን Regulation an Institution to implement the


powers and responsibilities of the Digital
የሚያስፈፅም ተቋም የሚኒስትሮች ምክር ቤት
Identification System stipulated in this
በሚያወጣው ደንብ መሠረት ይቋቋማል ወይም
Proclamation or it may be established within
እንደአስፈላጊነቱ ለሥራው አግባብነት ያለው
a relevant Government body as the case may
መንግሥታዊ ተቋም ውስጥ ሊደራጅ ይችላል፡፡
be.
ክፍል ሁለት SECTION TWO
ስለ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት መርሆዎች ፣ ምዝገባ Digital Identification System Principles,
እና አገልግሎት አሰጣጥ Enrollment and Service Provision

፮. መርሆዎች 6. Principles
የዲጂታል መታወቂያ ሥርአት በሚከተሉት መርሆች Digital Identification System shall abide by
ይመራል፡- the following principles:

፩/ አካታችነት፤ 1/ Inclusiveness;

2/ Infallibly;
፪/ አስተማማኝነት፤

፫/ የተመጠነ መረጃ፤ 3/ Data minimization;

4/ Interoperability;
፬/ የተናባቢነት፤

፭/ ግልፀኝነት እና ተጠያቂነት፤ 5/ Transparency and accountability;

፮/ ቴክኖሎጂ መር፡፡ 6/ Technology lead.

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment


gA ፲፬ሺ፯፻፳፫ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፱ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ›.M Federal Negarit Gazette No.19, 18th April, 2023 …… page 14723

፯. የዲጂታል መታወቂያ የማግኘት መብት 7. The Right to get Digital Identification


Any resident who registered for Digital
ማንኛውም ዲጂታል መታወቂያ ለማግኘት
Identification by giving his biometric and
የባዮሜትሪክና ዲሞግራፊክ መረጃ በመስጠት demographic data shall have the right to get
የተመዘገበ ነዋሪ ዲጂታል መታወቂያ የማግኘት Digital Identification.
መብት አለው፡፡
፰. የምዝገባ ስርዓት 8. Registration System
፩/ ተቋሙ ወይም መዝጋቢው አካል ማንኛውም ነዋሪ 1/ When any Resident applies for
ለምዝገባ በሚያመለክትበት ጊዜ ቀደም ሲል registration, the Institution shall ensure
አመልካቹ ዲጂታል መታወቂያ ያልተሰጠው that the applicant has not given Digital
መሆኑን የማረጋገጥ ሃላፊነት አለበት፤ Identification before;

፪/ ተቋሙ ወይም መዝጋቢው አካል የተመዝጋቢው 2/ The Institution or Registrar entity shall
የግል መረጃን ለማረጋገጥ የሚያገለግሉ verify and register the personal data of the
የመታወቂያ ሰነዶች እና ሌሎች በተቋሙ Registrant using identification documents

ተቀባይነት ባላቸው ሰነዶች ወይም የሰው ምስክር and other documents acceptable by the

ማስረጃዎችን በመጠቀም በማረጋገጥ መመዝገብ Institution or witnesses. The details shall be


decided by Directive to be issued by the
ይኖርበታል፡፡ ዝርዝሩ ተቋሙ በሚያወጣው
Institution.
መመሪያ ይወሰናል፡፡

፱. የግል መረጃ ምዝገባ ሥርዓት 9. Registration System of Personal Data

1/ Personal Data pushed to the Digital


፩/ ወደ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የሚገባ የግል
Identification System shall consist of
መረጃ የእያንዳንዱን ተመዝጋቢ የዲሞግራፊክ
Demographic and Biometric Data of each
መረጃ እና ባዮሜትሪክ መረጃን ያካተተ መሆን
Registrant;
አለበት፤

፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ላይ የተደነገገው 2/ Without prejudice to Sub Article (1) of this
ጠቅላላ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ የዲጂታል Article, Digital Identification System shall

መታወቂያ ሥርዓት የሚከተሉትን consist of the following Demographic Data:

የዲሞግራፊክ መረጃዎች ማካተት አለበት፦


ሀ) ስም፣ የአባት ስም፣ የአያት ስም ወይም a) First Name, Father’s Name,
በዚህ መልክ የተደራጀ ሕጋዊ ስም ለሌለው Grandfather’s Name or when the

ተመዝጋቢ ተቋሙ ተመዝጋቢው በአካባቢው Registrant does not have such legal name,

ማህበረሰብ በሚጠራበት ስም the Institution may collect the name of the


Registrant which is known by the local
ይመዘግበዋል፤
community;

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment


gA ፲፬ሺ፯፻፳፬ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፱ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ›.M Federal Negarit Gazette No.19, 18th April, 2023 …… page 14724

ለ) ዜግነት፤ b) Nationality;

ሐ) የትውልድ ቀን፣ ወር እና ዓመት፤ c) Date of birth, month and year;

መ) ፆታ፤ d) Gender;

ሠ) መኖሪያ አድራሻ፡፡ e) Domicile Address.

፫/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) ድንጋጌ 3/ Without prejudice Sub-Article (2) of this
እንደተጠበቀ ሆኖ ጥንቃቄ የሚፈልግ የግል Article, with the exception of sensitive
መረጃን ሳይጨምር የዲጂታል መታወቂያ Personal Data, additional personal data may
ሥርዓት የሚከተሉትን መረጃዎች እና ሌሎችም be collected including, but not limited to:

በአማራጭነት ሊይዝ ይችላል፡-


ሀ) የእናት ሥም፤ a) Mother's name;

ለ) ስልክ ቁጥር፤
b) Phone number;
c) Email address;
ሐ) የኢሜይል አድራሻ፤
d) Postal Address.
መ) ፖስታ አድራሻ፡፡

፬/ አንድ ተመዝጋቢ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፰ 4) Pursuant to Article 8 of this Proclamation;

መሠረት የተዘረዘሩ የመታወቂያ ሰነድ if the Registrant fails to submit the required

ማስረጃዎች ማቅረብ በማይችልበት እና


proof of identity, he may present an
individual witness who:
በምስክር በሚመዘገብበት ጊዜ ምስክሩ:-

ሀ) ልዩ ቁጥር ያለው፣ ወይም a) has a Unique Number, or


ለ) በዲጂታል መታወቂያ ሥርአት የተመዘገበ b) is Registerd in the Digital Identification

መሆን አለበት፡፡ System.

፭/ ስለ ባዮሜትሪክ መረጃ ምዝገባ 5) Registration of Biometric Data


a) without prejudice to Sub Article (1) of
ሀ) በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (፩) የተደነገገው
this Article, if it is confirmed by the
እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በአካል ጉዳት ወይም
Registrar that the Registrant can not
በሌላ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት
give Biometric Data because of
ተመዝጋቢው ሌሎች ባዮሜትሪክ መረጃ
physical injury or due to a reason
መስጠት አለመቻሉ በመዝጋቢው አካል
beyond capacity, Digital Identification
ከተረጋገጠ፣ የፊት ገፅታ ፎቶግራፍ ብቻ
may be provided by registering facial
በመመዝገብ ዲጂታል መታወቂያ ሊሰጥ
photograph;
ይችላል፤

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment


gA ፲፬ሺ፯፻፳፭ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፱ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ›.M Federal Negarit Gazette No.19, 18th April, 2023 …… page 14725

ለ) በዚህ ንዑስ አንቀፅ ፊደል ተራ (ሀ) b) Without prejudice to Pharagraph (a) of


የተጠቀሰው አንደተጠበቀ ሆኖ፤ በአካል ጉዳት this Sub Article, if it is attested by the

ምክንያት ተመዝጋቢው ሌሎች ባዮሜትሪክ Institution that the Registrant can not

መረጃ መስጠት አለመቻሉ በተቋሙ give other Biometric Data due to

ከተረጋገጠ፤ ከፊት ገፅታ ፎቶግራፍ ውጪ physical injury, other Biometric data


except facial photo shall not be
ሌላ የባዮሜትሪክ መረጃ አስገዳጅ መሆን
mandatory;
አይኖርበትም፤

ሐ) በጤና፣ በዕድሜ ወይም በሌላ ከአቅም በላይ c) The Registrar may register Registrants

በሆነ ምክንያት መዝጋቢው አካል ምዝገባ


who can not appear at the registration
place due to health, age or due to other
በሚያደርግበት ቦታ መምጣት የማይችሉ
reason beyond capacity at their place or
ተመዝጋቢዎችን ባሉበት ቦታ ወይም አመቺ
any other convenient place;
በሆነ ቦታ በመገኘት መዝጋቢው አካል ምዝገባ
ሊያደርግ ይችላል፤

መ) የግል መረጃ ተቋሙ በሚያወጣው መመሪያ d) Personal Data shall be renewed with in time
በሚወሰነው የጊዜ ገደብ መሠረት መታደስ interval decided by Directive to be issued by

ይኖርበታል፤ the Institution;

ሠ) የዚህ ንዑስ አንቀፅ ዝርዝር አፈፃፀም ተቋሙ e) The detail implementation of this Sub

በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል፡፡ Article shall be decided by Directive to be


issued by the Institution.

፲. ህፃናት የዲጂታል መታወቂያ ስለሚያገኙበት ሁኔታ 10. Circumstances of Issuance of Digital


Identification for Minors

በዚህ አዋጅ አንቀፅ ፯ እንዲሁም አንቀፅ ፱ ንኡስ Notwithstanding to Article 7 and Article 9
አንቀፅ (፩) ላይ የተደነገገው ቢኖርም፤ ለህፃናት Sub Article (1) of this Proclamation,
የዲጂታል መታወቂያ ሥርአት ላይ ለመመዝገብ፤ minors can be registered upon giving the
በሥርአቱ ላይ የተመዘገበ ወላጅ፤ አሳዳጊ፤ ሕጋዊ Demographic Data by a registered parent,

ሞግዚት ወይም ሌላ ማንኛውም ሕጋዊ አካል በኩል caretaker, legal guardian or any legal body

የህፃኑን ዲሞግራፊክ መረጃ ብቻ በመመዝገብ ህፃኑ who can take responsibility to the minor

መታወቂያውን መውሰድ ይችላል፡፡


and such person may take Digital
Identification.

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment


gA ፲፬ሺ፯፻፳፮ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፱ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ›.M Federal Negarit Gazette No.19, 18th April, 2023 …… page 14726

፲፩. ስለ ልዩ ቁጥር 11. Unique Number Issuance


፩/ መዝጋቢው አካል በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፱ 1/ Upon collection and pushing of Personal
የተዘረዘሩትን የተመዝጋቢ መረጃዎች መዝግቦ Data to the system as described under
ወደ ሥርዓቱ ካስገባ በኋላ፣ ተቋሙ አንድ ነዋሪ Article 9 of this Proclamation, the
ከሌላ ነዋሪ በልዩነት እና በአስተማማኝነት Institution shall issue to each Registrant a
ለመለየት የሚያስችል ልዩ ቁጥር ለእያንዳንዱ Unique Number that uniquely
ተመዝጋቢ መስጠት ይኖርበታል፤ differentiates that person from others;

፪/ ልዩ ቁጥሩ ኤሌክትሮኒክ በሆነ ሥርዓትና 2/ The Unique Number shall be generated


በሚስጥራዊ መንገድ የሚመነጭ ሲሆን ከቁጥሩ by electronic means in a confidential
ጀርባ ያለውን ዝርዝር መረጃ እና ግላዊነት manner, and shall preserve the security

የሚጠብቅ ይሆናል፤ and privacy of the Personal Data behind


the number;

፫/ አንድ ልዩ ቁጥር ለአንድ ተመዝጋቢ ብቻ 3/ One Unique Number shall be given only
የሚሰጥ ሲሆን፤ ይህ ልዩ ቁጥርም በቋሚነት to one Registrant and shall remain
ሳይቀየር ከተመዝጋቢው ጋር ይተሳሰራል፤ immutable, irrevocable and permanent;

፬/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) የተጠቀሰው ልዩ 4/ Without prejudice to the Unique Number

ቁጥር እንደተጠበቀ ሆኖ በተቋሙ አሠራር referred to in Sub-Article (2) of this


Article, Alias Numbers for different
ለተለያዩ የሥራ ዘርፎች፣ በተለየ መልኩ ወይም
work sectors, distinctively or based on
በተመዝጋቢው ፍላጎት፣ ከልዩ ቁጥር ጋር
the need of the Registrant, with a set
በሚስጥራዊ ሁኔታ የተያያዙ፣ የተመዝጋቢን
validity period meant to shield the
ግላዊነት ለመጠበቅ የሚያስችሉ፣ የራሳቸው ጊዜ
privacy of the Unique Numbers, allowing
ገደብ ያላቸው፣ ልዩ ቁጥሩን ተክተው መሥራት
the Registrant to receive authentication
የሚችሉ ተለዋጭ ቁጥሮች ማመንጨት
service similar to what the Unique
ይቻላል፤
Number enables may be generated based
on the working procedure of the
Institution;
፭/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) የተጠቀሰው ልዩ 5/ The Unique Number described in Sub
ቁጥር የማይለወጥ ሲሆን፣ የተመዝጋቢውን Article (2) of this Article is immutable,
የመረጃ ደኅንነት ለመጠበቅ ሲባል በማስረጃ ላይ hence for the purpose of protecting the
የሚታተመውና በሌሎች ሁኔታዎች ጥቅም ላይ privacy of the Registrant it can be
የሚውለው ቁጥር በተለዋጭ ቁጥር ሊተካ replaced by an Alias Number that may be

ይችላል፤ printed on Digital Identification


Credentials or can be used for other
purposes;

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment


gA ፲፬ሺ፯፻፳፯ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፱ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ›.M Federal Negarit Gazette No.19, 18th April, 2023 …… page 14727

፮/ የዲጂታል መታወቂያ ልዩ ቁጥር የጠፋበት 6/ Any Registrant who has lost his Unique
ማንኛውም ሰው ልዩ ቁጥሩ ስለመጥፋቱ Number may recover from the Institution

ለዲጂታል መታወቂያ ተቋም ወይም ተቋሙ or from another entity authorized by the

ከወከለው አካል ተገቢውን ክፍያ በመፈፀም Institution up on effecting the necessary

በተቋሙ አሠራር መሠረት ቁጥሩን መልሶ payment based on procedures put in


place by the Institution;
ማግኘት ይችላል፤
፯/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፬) የተመለከተው 7) Without prejudice to Sub-Article (4) of
እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በተቋሙ አሠራር መሰረት this Article, if the death of the Registrant

የተመዝጋቢው ሞት ከተረጋገጠ፤ ተቋሙ ልዩ is confirmed by the procedures of the

ቁጥሩ ሳይቀየር እንደፀና እንዲቆይ እና Institution, the Institution shall has the

ለማረጋገጥ አገልግሎት ሥራ ላይ እንዳይውል obligation to make the Unique Number


remains immutable and ensure that the
የማድረግ ሃላፊነት ይኖርበታል፤
Unique Number is not used for
authentication service;

፰/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፫) ላይ ያለው 8) Without prejudice to Sub Article (3) of
ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በተመዝጋቢው this Article an individual’s Digital
ፍላጎት ወይም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ የዲጂታል Identification Uniqe number may be
መታወቂያ ልዩ ቁጥር ሊቆለፍ ወይም ከሥራ locked or disabled as per his request or

ውጪ እንዲሆን ሊደረግ ይቻላል፤ ዝርዝር by a court order. The detailed procedure

አፈፃፀሙ ተቋሙ በሚያወጣው መመሪያ shall be determined by a Directive to be

የሚወሰን ይሆናል።
issued by the Instituion.

12. Digital Identification Credential


፲፪. ስለ ዲጂታል መታወቂያ ማስረጃ
፩/ ተቋሙ እና ውክልና በተሰጣቸው አካላት 1/The Digital Identification Credential

የሚሰጥ ማንኛውም ዓይነት የዲጂታል issued by the Institution and by other


authorized entities shall contain the
መታወቂያ ማስረጃ የሚከተሉትን መረጃዎች
following personal data:
መያዝ አለበት፦

ሀ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፱ ንዑስ አንቀጽ (፪) a) All the Data listed under Article
9 Sub Article (2) of this
የተዘረዘሩት መረጃዎች በሙሉ፤
Proclamation;

ለ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፱ ንዑስ አንቀጽ (፭) b) facial Photograph referred to in

ፊደል ተራ (ለ) ላይ የተጠቀሰውን የፊት Article 9 Sub Article (5)

ገፅታ ፎቶግራፍ፤ Paragraph (b) of this


Proclamation;

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment


gA ፲፬ሺ፯፻፳፰ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፱ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ›.M Federal Negarit Gazette No.19, 18th April, 2023 …… page 14728

ሐ) ልዩ ወይም ተለዋጭ ቁጥር፤ c) Unique or Alias Number;

መ) መታወቂያው የተሰጠበት እና የሚያበቃበት d) Date of issuance and date of

ቀን፤እና expiry of the Digital


Identification Credential; and

ሠ) ሌሎች በአንቀጽ ፱ ውስጥ ከተጠቀሱ e) Other Data provided under

መረጃዎች ውስጥ በተቋሙ የሚወሰኑ Article 9 of this Proclamation

መረጃዎች፡፡ subject to the decision of the


Institution;

፪/ የዲጂታል መታወቂያ ማስረጃ ዕድሳት 2/ The Digital Identification Credential must be


ከባዮሜትሪክ መረጃ የእድሳት ዘመን ጋር አብሮ renewed upon the recapture of biometric
መሆን ይኖርበታል፤ ሆኖም የዲጂታል data; however, if the Digital Identification

መታወቂያ ማስረጃ እስከሚታደስ ድረስ Credential has expired, it shall not be used

የዲጂታል መታወቂያ ማረጋገጫ አገልግሎት for authentication services;

መስጠት አይቻልም፤

፫/ የዲጂታል መታወቂያ ማስረጃ በተቋሙ ወይም 3/ Digital Identification Credentials may be


ተቋሙ በወከላቸው አካላት ሊሰጥ ይችላል፤ issued by the Institution or by other bodies
mandated by the Institution;

፬/ ተቋሙ የዲጂታል መታወቂያ ማስረጃ 4/ The Institution shall has the obligation to
በሚያድስበት ጊዜ ቀድሞ የተሰበሰቡ መረጃዎች renew the Digital Identification Credential
ትክክለኛነታቸውን እና የተመዝጋቢውን after verifying the Registrant’s Personal

ማንነት ትክክለኛነት አረጋግጦ የማደስ ግዴታ Data collected before;

አለበት፤

፭/ ዲጂታል መታወቂያ ማስረጃ የጠፋበት ወይም 5/ A Registrant whose Digital Identification


የተበላሸበት ማንኛውም ነዋሪ፤ መታወቂያው Credential is lost or damaged can apply for
ስለመጥፋቱ የሚገልጽ ማስረጃ ወይም a replacement and obtain a new credential

የተበላሸውን መታወቂያ በማያያዝ፤ በምትኩ upon presenting proof of loss or attaching

ዲጂታል መታወቂያ እንዲሰጠው ለተቋሙ the damaged credentials as per the


procedures put in place by the Institution;
በማመልከት የተቋሙን አሠራር ተከትሎ
መውሰድ ይችላል፤

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment


gA ፲፬ሺ፯፻፳፱ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፱ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ›.M Federal Negarit Gazette No.19, 18th April, 2023 …… page 14729

፮/ የዲጂታል መታወቂያ ማስረጃ ወድቆ ያገኘ 6/ Any person who finds a lost physical Digital
ማንኛውም ሰው መታወቂያውን ወዲያውኑ Identification Credential shall return it to the

ለተቋሙ ወይም በአቅራቢያው ለሚገኝ ፖሊስ Institution or to a nearby police station.

ጣቢያ ማስረከብ አለበት።

፲፫. ስለ ቋንቋ 13. Language


፩/ በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የሚመዘገቡ እና 1/ Personal Data collected into the Digital
በዲጂታል መታወቂያ ማስረጃ ላይ የሚገለፁ የግል Identification System and displayed on
መረጃዎች በፌደራል መንግሥት የሥራ ቋንቋ፣ Digital Identification Credentials shall be

ምዝገባ በሚካሄድበት ክልል የሥራ ቋንቋ እና in the working languages of the Federal

በእንግሊዘኛ ይሆናል፤
Government, in the working language of
the Regional Government where
registration is took place and in English;

፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ላይ የተመለከተው 2/ Without prejudice Sub Article (1) of this
እንደተጠበቀ ሆኖ በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት Article, Personal Data may be recorded
የሚመዘገብም ሆነ በዲጂታል መታወቂያ ማስረጃ and Digital Identification Credential
ላይ የሚወጣ መረጃ ተቋሙ በሚያወጣው መመሪያ printed in additional local language as per

በሚወሰነው መሰረት በተጨማሪ የሀገር ውስጥ a Directive to be issued by the Institution.

ቋንቋ ሊመዘገብ ይችላል። [

14. Change of Information of Digital


፲፬. ስለ ዲጂታል መታወቂያ የመረጃ ለውጥ
Identification

፩/ ማንኛውም ተመዝጋቢ ወደ ዲጂታል መታወቂያ 1/ Any Registrant shall notify to the

ሥርዓት በገቡ የግል መረጃዎች ላይ ለውጥ Institution of the changes to his Personal

ሲኖር የዲጂታል መታወቂያ ለሚሰጠው አካል Data collected to the Digital

ማሳወቅ አለበት።
Identification System after Registration.

፪/ ተቋሙ ወይም መዝጋቢው አካል በዲጂታል 2/ The Institution or Registrar shall notify to
መታወቂያ ሥርዓት የተሰበሰቡ መረጃዎች the Registrant and let the Registrar

በተለያዩ ተፈጥሯዊም ሆነ ሰው ሰራሽ አደጋ updtated Data collected by Digital


Identification System if the Data collected
ምክንያት ከጠፉ ወይም ከተበላሹ
are misplaced or destroyed by any natural
ለተመዝጋቢው ማሳወቅ እና መረጃዎቹ እንደገና
or man made disasters.
እንዲሟሉ ማድረግ አለበት፡፡

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment


gA ፲፬ሺ፯፻፴ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፱ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ›.M Federal Negarit Gazette No.19, 18th April, 2023 …… page 14730

ክፍል ሶስት SECTION THREE


ስለ ዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ አካላት እና Relying Parties and Authentication Service
የማረጋገጥ አገልግሎት

፲፭. ስለ ተጠቃሚ አካላት 15. Relying Parties


፩/ ማንኛውም ተጠቃሚ አካል ለነዋሪው ለሚሰጠው 1/Any Relying Party that wants to put Digital

አገልግሎት የዲጂታል መታወቂያ እንደ Identification as a mandatory requirement

አስገዳጅ ቅድመ ሁኔታ የሚያደርግ አሠራር to provide service shall get approval from

ለመዘርጋት ከሚመለከተው ተቆጣጣሪ አካል the concerned regulator.

ፈቃድ ማግኘት አለበት::


፪/ ተጠቃሚ አካላት በተመዝጋቢው ፈቃድ ላይ 2/ Relying Parties may receive a Registrant's
ተመስርተው የግለሰብ ማንነትን ለማረጋገጥ Personal Data from the Institution or other
የሚያስፈልጋቸውን መረጃ ከተቋሙ ወይም Authentication Service Providers

ተቋሙ ከወከለው አረጋጋጭ አካል ማግኘት authorized by the Institution, to

ይችላሉ:: authenticat the individual’s identity based


on the consent of the Registrant.

፫/ ማንኛውም ተመዝጋቢ፣ በዲጂታል መታወቂያ 3/ Any Registrant that needs to access


ላይ የተመሰረቱ አገልግሎቶችን ማግኘት Digital Identification based services, can
ሲፈልግ፣ በተጠቃሚ አካላት በኩል የማረጋገጥ get Authentication Services from the

አገልግሎት ማግኘት ይችላል:: Relying Parties.

፬/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (፪) የተደነገገው 4/ Notwithstanding to Sub Article (2) of this

እንደተጠበቀ ሆኖ ተጠቃሚ አካላት አገልግሎት Article Relying Parties shall obtain

መሥጠት ከመጀመራቸው በፊት ከተቋሙ authorization from the Institution before


they start providing service.
ፈቃድ ማግኘት አለባቸው::
፭/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀጽ (፪) እና ንዑስ 5/ Notwithstanding to Sub Article (2) and
አንቀጽ (፬) የተጠቀሰው ቢኖርም ተጠቃሚ Sub Article (4) of this Article, if the
አካላት የተመዝጋቢ መረጃን ትክክለኛነት Relying Parties can not obtain Data of
ከአረጋጋጭ አካል ማግኘት በማይችሉበት the Registrant from the Institution, they
ወቅት፤ የራሳቸውን ሌላ አማራጭ ተጠቅመው have the right to give service using their
አገልግሎት የመሥጠት መብታቸው የተጠበቀ own other method.
ነው::

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment


gA ፲፬ሺ፯፻፴፩ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፱ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ›.M Federal Negarit Gazette No.19, 18th April, 2023 …… page 14731

፮/ ተጠቃሚ አካላት ከዲጂታል መታወቂያ 6/ The duration of the retention period for
የማረጋገጥ ሥርዓት ያገኙትን መረጃ ይዘው Personal Data by a Relying Party shall be

ማቆየት የሚችሉበትን የጊዜ ገደብን በተመለከተ specified by a Directive of the Digital

ተቋሙ በመመሪያ ይወስናል፡፡ Identification Institution.

፲፮. ስለ ማረጋገጥ አገልግሎት አሰጣጥና አጠቃቀም 16. Authentication Service Provision and
Usage

፩/ የዲጂታል መታወቂያ የአንድን ነዋሪ ማንነትን 1/ Digital Identification may be taken as a


ለማስረዳት ወይም ለማረጋገጥ እንደ ህጋዊ እና legal and sufficient evidence to proof or
በቂ ማስረጃ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ authenticate a Resident’s identity.

፪/ የዲጂታል መታወቂያ ተቋሙ አንዱ አረጋጋጭ 2/ Though the Institution is one of the
አካል ቢሆንም፤ ተቋሙ በሚሰጠው ውክልና authentication service providers, It may

ተጨማሪ አረጋጋጭ አካላትን መሰየም authorize an additional authentication

ይችላል፡፡ service providers.

፫/ ማንኛውም ተመዝጋቢ የዲጂታል መታወቂያ ላይ 3/ Any Registrant that wants to receive

የተመሠረተ የማረጋገጥ አገልግሎት ለማግኘት Digital Identification based

ልዩ ቁጥር ወይም ልዩ ቁጥሩን የያዘ የዲጂታል


Authentication Service shall present
Unique Number or a Digital
መታወቂያ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
Identification Credential with its Unique
Number.

፬/ አረጋጋጭ አካላት የግል መረጃን ለተጠቃሚ 4/ When the Authentication Service


አካላት በሚያረጋግጡበት ወቅት የአገልግሎት Providers authenticat personal data, they

ፍላጎትን መነሻ በማድረግ፣ ተቋሙ በሚሰጠው shall provide only minimal necessary

ፈቃድ መሠረት፣ ዝቅተኛ ተፈላጊ የግል level of personal data based on the needs
of the Relying party as authorized by the
መረጃዎችን ብቻ መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡
Institution;

፭/ አረጋጋጭ አካላትም ሆኑ ተጠቃሚ አካላት 5/ Authentication Service Providers as well

ከዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት ላገኙት የግል as Relying Parties shall ensure the safety

መረጃ ተገቢ ጥበቃና ደኅንነት የማድረግ and security of the Personal Data they

ኃላፊነት አለባቸው፡፡ received from the Digital Identification


System.

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment


gA ፲፬ሺ፯፻፴፪ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፱ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ›.M Federal Negarit Gazette No.19, 18th April, 2023 …… page 14732

ክፍል አራት SECTION FOUR


የግል መረጃ ጥበቃና ደኅንነት፣ አስተዳደር እና የቅሬታ Personal Data Protection, Security,
አፈታት ሥርዓት Management and Grievance Redressal
፲፯. የግል መረጃ ጥበቃ እና ደኅንነት 17. Protection and Security of Personal Data
፩/ በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የተሰበሰበ 1/ The owner of any Personal Data

ማንኛውም የተመዝጋቢ ግላዊ መረጃ ባለቤት collected for the Digital Identification

ተመዝጋቢው በመሆኑ፤ በማንኛውም የዲጂታል System is the Registrant; Hence any


authentication processes under the
መታወቂያ አሠራር ሥርዓት ውስጥ
Digital Identification System shall be
አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚደረጉ የማረጋገጥ
done with the consent of the Registrant.
ተግባራት በተመዝጋቢው ፈቃድ መደረግ
አለባቸው::
፪/ ወደ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የሚገቡ 2/ The Institution shall ensure that, the

መረጃዎችን በመሰብስብ፣ በመመዝገብ፣ confidentiality of Personal Data is

በማረጋገጥ እና ይዞ በማቆየት ሂደት ባሉ maintained in the course of collecting,


registering, authenticating, storing, and
ተግባራት ውስጥ የተመዝጋቢ መረጃዎች
processing of the same.
ሚስጢራዊነት የተጠበቀ እንዲሆን ተቋሙ
ማረጋገጥ አለበት::
፫/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ ንዑስ አንቀፅ (፫) 3/ Data collected in accordance with the
በተቀመጠው መርህ መሠረት ለዲጂታል principles set out in Article 6 Sub
መታወቂያ ሥርዓት የሚሰበሰቡ መረጃዎች፤ Article (3) of this Proclamation; no
ነዋሪዎችን በልዩ ሁኔታ ለመለየት የግዴታ information shall be collected for the
የሚያስፈልጉና ሥርዓቱን በቀጥታ ከሚደግፉ Digital Identification System other than
በስተቀር ሌሎች መረጃዎች ሊሰበሰቡ those necessary to identify Residents

አይችሉም:: and have direct support to the system.

፬/ ማንኛውም ሰው ተመዝጋቢ ፈቃዱን በግልጽ 4/ Any person may not collect, distribute,
ሳይሰጥ በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት print, use, provide data or transfer a copy

የተመዘገቡ የግል መረጃዎችን መውሰድ፣ to a third party or body or disclose data

ማሰራጨት፣ ማተም፣ መጠቀም፣ መረጃውን collected with Digital Identification

መስጠት ወይም ቅጂውን ለሶስተኛ ወገኖች


System without the Registrant’s consent.

ወይም አካላት መስጠት ወይም ይፋ ማድረግ


የተከለከለ ነው::

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment


gA ፲፬ሺ፯፻፴፫ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፱ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ›.M Federal Negarit Gazette No.19, 18th April, 2023 …… page 14733

፭/ አሠራርና ሕግን ጠብቆ በዲጂታል መታወቂያ 5/ It is prohibited to disclose, transfer or


ሥርዓት ለተሰበሰበ የማንኛውም ተመዝጋቢ modify the Personal Data of any

ግላዊ መረጃ ያለ ተመዝጋቢው ፈቃድ ለሌላ Registrant, collected under the Digital

ሰው መግለጽ፣ ማስተላለፍም ሆነ እንዲለወጥ Identification System in accordance with

መፍቀድ የተከለከለ ነው:: the Rules and Regulations without the


Registrant’s consent.

፮/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፭) ላይ የተደነገገው 6/ Notwithstanding the Provisions of Sub
ቢኖርም፣ በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው ወይም Article (5) of this Article, the data may be
በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሠረት የግል መረጃው disclosed or transferred to the relevant
ለሚመለከተው ሕጋዊ አካል ሊገለጽ ወይም legal entity authorized by law or by court

ሊተላለፍ ይችላል:: order.

፯/ በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የተሰበሰቡ ግላዊ 7/ Summarized demographic reports and

መረጃን የማያጋልጡ የተጨመቁ ዲሞግራፊክ statistical data which will not disclose

ሪፖርቶች እና የስታትስቲክስ መረጃዎችን በሕግ Personal Data collected with in digital

ለተፈቀደላቸው አካላት በተቋሙ አሠራር


identification system may be shared to
legally authorized parties in accordance
መሠረት ሊሰጡ ይችላሉ::
with the procedures of the Institution.

፰/ ከዲጂታል መታወቂያ ቋት አሠራሩን ጠብቆ 8/ Personal Data transmitted to a Relying


ለተጠቃሚ አካላት የተላለፈ የተመዝጋቢ መረጃ Party from a Digital Identification System
የሚያገለግለው ወይም ጥቅም ላይ የሚውለው database following the working
ለተፈለገው አገልግሎት ብቻ ሲሆን፤ መጀመሪያ procedure, can be used only for that
ከተላለፈበት ዓላማ ባልወጣ መልኩ ተጠቃሚው particular service for which it was

አካል ይህንን መረጃ በራሱ ቋት ውስጥ requested; Relying Parties may store this

ማስቀመጥና ለራሱ አገልግሎት ብቻ መጠቀም information in their own database and use

ይችላል::
it only for their own use, without violating
its original purpose.

፱/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፯) የተጠቀሰው 9/ Without prejudice to Sub Article (7) of
እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ተጠቃሚ አካላት this Article, using of Personal Data
በተመዝጋቢው ፈቃድ ያገኙትን መረጃ፣ obtained upon the concent of the

መረጃውን ከወሰዱበት ዓላማ ውጪ ለራሳቸው Registrant for personal purpose other

መጠቀምም ሆነ ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ than they were designed for or sharing to
the third parties is prohibited.
መስጠት የተከለከለ ተግባር ነው::

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment


፲፬ሺ፯፻፴፬
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፱ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ›.M Federal Negarit Gazette No.19, 18th April, 2023 …… page 14734

፲/ በምዝገባ ወቅት በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት 10/ During registration, a standard consent
የሚዘጋጅ የተመዝጋቢውን ሙሉ ፈቃድ፣ form prepared by Digital Identification

መብት እና ግዴታዎች የሚገልፅ የፈቃደኝነት System, which describe the Registrant’s

ቅፅ በተመዝጋቢው መሞላትና መፈረም rights and obligations shall be completed

አለበት፡፡ and signed by the Registrant as proof of


consent.

፲፩/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፲) ላይ የተጠቀሰው 11/ Without prejudice to Sub Article (10) of
እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በምዝገባ ወቅት ለተመዝጋቢ this Article, in case when a witness testifies
ምስክር ሆኖ ለሚቀርብ ሰው፤ በተቋሙ for the Registrant, such witness shall fill in

የሚዘጋጅ የምስክሩን ሙሉ ፈቃድ፣ መብት እና a standard consent form prepared by the

ግዴታዎች የሚገልፅ የፈቃደኝነት ቅፅ በምስክር Institution stating his voluntary consent,

መሞላትና መፈረም አለበት፤ የምስክሩ ልዩ


rights and obligations, the witness’s
Unique Number or proof of Digital
ቁጥር ወይም የምዝገባና የማንነት ማረጋገጫ
Identification registration and proof of
ሰነዶች በቅጹ ላይ መሞላት እና በዲጂታል
identity, must be provided, signed and
መታወቂያ ሥርዓቱ ተመዝግቦ መያዝ አለበት፡፡
completed on the form.

፲፪/ በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የተሰበሰቡ 12/ The Institution shall employ strong
መረጃዎች ከተለያዩ የተፈጥሯዊም ሆነ ሰው administrative, legal, procedural and
ሰራሽ አደጋ፣ የኤሌክትሮኒክ መንገዶችን technical safeguards to ensure the
በመጠቀም ከሚደርሱ ጥቃቶች፣ ከስርቆት፣ protection of Personal Data from either
ከመጭበርበር እና መሰል የወንጀል ጥፋቶች natural or man-made disasters, electronic

የሚከላከል ደኅንነቱ የተጠበቀ የሕግና attacks, theft, destruction and other similar

አስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት እንዲሁም losses.

ጠንካራ የቴክኒክና የደኅንነት ሥርዓት


መተግበር አለበት፡፡
፲፫/ ለዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የተሰበሰቡ የግል 13/ Personal Data collected for the Digital
መረጃዎች፣ ለአጠቃቀም አመቺ በሆነ አኳኋን Identification System must be organized

በሥርዓት ተደራጅተው ተቋሙ in a convenient manner and stored

በሚያስተዳድረው የመረጃ ቋት ውስጥ መቀመጥ securely in a database managed by the

አለባቸው።
Institution.

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment


፲፬ሺ፯፻፴፭
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፱ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ›.M Federal Negarit Gazette No.19, 18th April, 2023 …… page 14735

፲፰. ስለ መረጃ መጭበርበር ወይም መሳሳት 18. Data Fraud or Error


፩/ የአንድ ነዋሪ ዲጂታል መታወቂያ የተጭበረበረ 1/ When the Digital Identification of a

መሆኑ ከተረጋገጠ፤ ተቋሙ ዲጂታል Resident is confirmed to be fraudulent,

መታወቂያውን ሊቆልፍ፣ መረጃውን the Institution may lock the Digital

ሊያስተካክል፣ ወይም የተጭበረበረው መረጃ Identification, update the data or take


other legal precautionary measures to to
ለሌላ አገልግሎት እንዳይውል ለማድረግ
block the fraudulent data from further
የሚያስችሉ ሕጋዊ የጥንቃቄ እርምጃዎችን
use or may initiate suit or charge.
ሊወስድ ወይም ክስ ሊመሰርት ይችላል።
፪/ ተቋሙ የተሳሳተ መረጃ መኖሩን ሲያረጋግጥ ልዩ 2/ Whenever the Institution verifies that
ቁጥሩ ሳይቀየር መረጃውን የማስተካከል there is erroneous Personal Data it has
ኃላፊነት አለበት። the responsibility to rectify the error,
with out changing the Unique Number.
፲፱. የግል መረጃ አስተዳደር 19. Personal Data Management

፩/ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የተመዝጋቢ 1/ The Digital Identification System shall be


መረጃን በአስተማማኝነት የሚይዝ ጠንካራ መረጃ a reliable and robust system to securely
አስተዳደር ሥርዓት መሆን አለበት፡፡ and safely administer Personal Data.
፪/ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት በጊዜ ሂደት 2/ The Digital Identification System is
የሚለዋወጡ የዲጂታል መታወቂያ መረጃዎችን tasked with maintaining Personal Data
የማዘመን፣ እንደገና የማረጋገጥ፣ የማደስ፣ quality over time, including the
በጊዜያዊነት የመቆለፍ ወይም የመሻር ሥራዎችን responsibility of updating, re-verifying,
ይሠራል፡፡ renewing, temporarily locking or
revoking Digital Identification
Information.

፳. የቅሬታና አቤቱታ አቀራረብና አፈታት ሥርዓት 20. Grievance and Complaint Redressal
፩/ ተቋሙ የቅሬታ ማስተናገጃ ክፍል ማቋቋም እና 1/ The Institution shall establish a

ይህንኑ ለተገልጋዮች ይፋ ማድረግ አለበት:: complaint handling department and


notify such establishments to its
customers.

፪/ ማንኛውም ሰዉ በተቀበለው የዲጂታል መታወቂያ 2/ Any person against whom Digital

አገልግሎትና በተላለፈበት ውሳኔ ላይ ካልተስማማ Identification service is provided and a

ለተቋሙ ቅሬታ የማቅረብ መብት አለው:: decision is made has the right to lodge a
complaint to the Institution.

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment


gA ፲፬ሺ፯፻፴፮ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፱ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ›.M Federal Negarit Gazette No.19, 18th April, 2023 …… page 14736

፫/ በተቋሙ የአሠራር ሥርዓት ሂደት የሚያጋጥሙ 3/ Any complaints and grievances that may be
ቅሬታዎችና አቤቱታዎች አቀራረብና አፈታት encountered in the course of service

ሂደት፤ ተቋሙ በሚዘረጋው የቅሬታ አቀራረብና provision of the Institution shall be solved in

አፈታት መመሪያ መሠረት ይፈታል:: accordance with the grievance filing and
redressal Directive of the Institution.

፬/ በተቋሙ ውሳኔዎች ቅር የተሰኘ አካል ቅሬታውን 4/ A party who is dissatisfied with the
ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል:: decisions of the Institution may file a
complaint to the pertinent court.

ክፍል አምስት SECTION FIVE


ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች Miscellaneous Provisions
21. Duty to Cooperate
፳፩. የመተባበር ግዴታ
ማንኛውም ሰው በዚህ አዋጅ ላይ የተመለከቱት Any person when requested by concerned

ዓላማዎች እና ተግባራት ዉጤታማ እንዲሆኑ organ to render the necessary cooperation

አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ በሚመለከተው


for the effective implementaion of
objectives and activities indicated in this
አካል በተጠየቀ ጊዜ የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡
Proclamation shall has the obligation to
cooperate.

፳፪. የወንጀል ተጠያቂነት 22. Criminal liablity

፩/ በዚህ አዋጅ እና ይህን አዋጅ ተከትለው በሚወጡ


1/ Any person who refuses to receive
digital identification as a legal
ደንቦች እና መመሪያዎች መሠረት ሥልጣን
identification or refuse to provide
ባለው አካል የተሠጠን ዲጂታል መታወቂያን
services with Digital Identification
እንደ ሕጋዊ መታወቂያ ለመቀበል ፈቃደኛ
issued upon verification of identity by
ያልሆነ ወይም ማንነትን ብቻ በማረጋገጥ
the relevant authority based on this
የሚሰጡ አገልግሎቶችን በዲጂታል መታወቂያ
Proclamation, Regulation and
ለመስጠት ፍቃደኛ ያልሆነ ወይም በዚህ አዋጅ
Directives to be issued following this
አንቀፅ ፳፩ ላይ የተመለከተውን የመተባበር
Proclamation or violates duty to
ግዴታ የተላለፈ ማንኛውም ሰው ከ፲ሺ (አስር
cooprate under Article 21 of this
ሺህ) ብር እስከ ፩፻ሺ (አንድ መቶ ሺህ) ብር Proclamation shall be punished with a
በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል:: fine from Birr Ten Thousand (10,000)
to Birr One Hundred Thousand
(100,000).

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment


gA ፲፬ሺ፯፻፴፯ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፱ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ›.M Federal Negarit Gazette No.19, 18th April, 2023 …… page 14737

፪/ በዚህ አዋጅ አንቀፅ ፲፯ ንዑስ አንቀጽ ፫፣ ፬ ወይም 2/Any Registrar who collected more data
፭ ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ መታወቂያ than needed to get digital Identification

ለማግኘት አስፈላጊ ከሆኑት መረጃዎች ውጪ in violation of Article 17 Sub Article

ሌሎች መረጃዎችን የሰበሰበ ማንኛውም መዝጋቢ (3), (4) or (5) of this Proclamation shall

አካል ከ፲ሺ (አስር ሺህ) ብር እስከ ፩፻ሺ (አንድ be punished with fine from Birr Ten

መቶ ሺህ) ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ Thousand (10,000) to Birr One hundred

ይቀጣል:: Thousand (100,000).

3/ Any person who intentionaly transfer


፫/ በዚህ አዋጅ አንቀፅ ፲፯ ንዑስ አንቀጽ (፱) ሥር
data collected to receive Digital
የተደነገገውን በመተላለፍ ዲጂታል መታወቂያ
Identification to a third party in
ለማግኘት የተሰበሰቡ መረጃዎችን ሆነ ብሎ
violation of Article 17 Sub Article (9) of
ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ የሰጠ ማንኛውም ሰው
this Proclamation shall be punished
ከ፩(አንድ) ዓመት እስከ ፭(አምስት) ዓመት ወይም
from 1(One) year to 5(Five) years or in
እንደነገሩ ክብደት እስከ ፰(ስምንት) ዓመት
accordance with the circumstance of the
በሚደርስ ፅኑ እስራት ይቀጣል::
case up to 8(Eight) years rigorous
imprisonment.
፬/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (፩) እና (፪) ላይ 4/ If the crime provided under Sub Article
የተመለከተው ጥፋት የተፈፀመው የሕግ የሰውነት (1) and (2) of this Article is committed
መብት በተሰጠው አካል ከሆነ ከ ፫፻ሺ (ሶስት መቶ by juridical person, it shall be
ሺህ) ብር እስከ ፰፻ሺ (ስምንት መቶ ሺህ) ብር punishable with fine from Birr Three
በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል:: Hundred Thousand (300,000) to Birr
Eight Hundred Thousand (800,000).

፭/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (፫) ስር የተመለከተው 5/ If the crime provided under Sub Article
ድርጊት የተፈፀመው በቸልተኝነት ከሆነ ቅጣቱ ከ (3) of this Article is committed

፮ (ስድስት) ወር እስከ ፩ (አንድ) ዓመት በሚደርስ negligently the punishment shall be

ቀላል እስራት ወይም ከ ፲ሺ (አስር ሺህ) ብር punishable from 6(Six) month to 1(One)
year simple imprisonment or with fine
እስከ ፸ሺ (ሰባ ሺህ) ብር በሚደርስ የገንዘብ
from Birr Ten Thousand (10,000) to
መቀጮ ይሆናል::
Birr Seventy Thousand (70,000).
፮/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (፫) ላይ የተመለከቱት 6/ If the crime provided under Sub Article
ጥፋቶች የተፈፀሙት የሕግ የሰውነት መብት (3) of this Article is committed by a

በተሰጠው አካል ከሆነ ከ ፩፻ሺ (አንድ መቶ ሺህ) juridical person, it shall be punishable

ብር እስከ ፭፻ሺ (አምስት መቶ ሺህ) ብር with fine from Birr One Hundred

በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል፡፡


Thousand (100,000) to Birr Five
Hundred Thousand (500,000).

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment


gA ፲፬ሺ፯፻፴፰ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፱ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ›.M Federal Negarit Gazette No.19, 18th April, 2023 …… page 14738

23. Repealed Laws


፳፫. የተሻሩ ሕጎች
No law or customary practice, inconsistent
የዚህን አዋጅ ድንጋጌዎች የሚቃረን ማንኛውም
with the provisions of this Proclamation
ሕግ ወይም የአሠራር ልማድ በዚህ አዋጅ በተሸፈኑ
shall be applicable with respect to matters
ጉዳዮች ተፈፃሚነት አይኖረውም።
provided for by this Proclamation.
፳፬. የመሸጋገሪያ ድንጋጌ 24. Transitory rovisions
የዚህ አዋጅ አንቀፅ ፳፫ ድንጋጌ ቢኖርም ይህ አዋጅ Notwithstanding Article 23 of this
ከመውጣቱ በፊት በተቋሙ የተሰጠ የዲጂታል Proclamation, Digital Identification issued

መታወቂያ በዚህ አዋጅ መሠረት እንደተሰጠ before the adoption of this Proclamation,
shall be considered as issued based on this
መታወቂያ ተቆጥሮ ሕጋዊነት ይኖረዋል፡፡
Proclamation and remain legal.
፳፭. ደንብና መመሪያ የማውጣት ሥልጣን 25. Power to Issue Regulation and Directive
፩/ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህንን አዋጅ 1/ The Council of Ministers may issue
ለማስፈጸም የሚያስፈልግ ደንብ ሊያወጣ Regulation necessary to enforce this

ይችላል:: Proclamation.

፪/ ተቋሙ ይህን አዋጅ እና ይህን አዋጅ ተከትሎ 2/ The Institution may issue necessary
የሚወጡ ደንቦችን ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ Directives to implement this

መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል፡፡ Proclamation and Regulations issued


following this Proclamation.

፳፮. አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ 26. Effective Date


ይህ አዋጅ በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ This Proclamation shall enter into force on
ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል። the date of its publication in the Federal
Negarit Gazeta.

አዲስ አበባ ሚያዚያ ፱ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም Done at Addis Ababa, On this 18th Day of
April, 2023.

ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ‹


SAHLEWORK ZEWDIE
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ

PRESIDENT OF THE FEDERAL


ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት DEMOCRATIC REPUBLIC
OF ETHIOPIA

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment


Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment

You might also like