You are on page 1of 5

ኢንዱስትሪ መንደርና ገበያ መሰረተ ልማት ዋና የስራ ሂደት ለእያንዳንዱ የስራ መደብ የስራ ዝርዝር ከማዘጋጀት አኳያ

የተቀመረ ምርጥ ተሞክሮ

መግቢያ

ሀገሪቱ ኢኮኖሚውን ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ለማሸጋገር የኢንዱስትሪ ፖሊሲ በማውጣት ዘርፉን

በሚኒስቴር ደረጃ ራሱን አስችሎ በማዋቀር ከታች እስከ ከተማ ድረስ አደረጃጀት በመፍጠር በማኒፋክቸሪንግ

ኢንዱስትሪ የተሰማራና ወደ ፊትም ሊሰማራ የሚፈልግ ባለሀብትን መሰረተ ልማት በማሟላትና ሌሎች ድጋፍና

ክትትል የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው፡፡

በዚህም መሰረት በከተማችን የኢንዱስትሪ መንደርና ገበያ መሰረተ ልማት ዋና የስራ ሂደት 7(ሰባት) የስራ መደብ

እንዲኖረው ታስቦ አደረጃጀት የተፈጠረ በመሆኑ ከአንድ የስራ መደብ ማለትም የከተማ ፕላን ባለሙያ የሥራ መደብ

ውጭ ሌሎች የስራ መደቦች በምደባና በቅጥር በሰራተኛ እንዲሸፈን ተደርጓል፡፡

እነዚሁ ሰራተኞች ከጽህፈትና ቢሮ አስተዳደር ባለሙያ ውጭ ሌሎች በክልሉ አማካኝነት ደብረ ታቦር ከተማ ላይ

በተዘጋጀ የስራ ማስጀመሪያ ስልጠና ላይ መሳተፍ፣ሪፖርት ቢጋርና የትግበራ ማንዋል ከመላክ ባለፈ የስራ ዝርዝር ToBe

እንዲሁም የአሰራር ህግጋት ባለመውረዳቸው የስራ ሂደቱን ዕቅዶች ለማቀድና ከእያንዳንዱ ፈፃሚ ባለሙያ ጋር ዕቅድ

በማቀድ ለመዋዋል ችግር ስለፈጠረብን እጃችን ላይ በአሉ የትግበራ ማንዋልና የሪፖርት በጋር መነሻ በማድረግ

ለእያንዳንዱ የስራ መደብ የስራ ዝርዝር ማዘጋጀት አስፈላጊ በመሆኑ መነሻ ሀሳብ በስራ ሂደት አስተባባሪ እንዲዘጋጅ

በማድረግ የሂደቱ ሰራተኞች ተወያይተውበት ለጽ/ቤቱ ማኔጅመንት ኮሚቴ እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡

1. የምርጥ ተሞክሮ ቅመራው አላማ


 እያንዳንዱ ተግባር ከበላይ አካል ከመጠበቅ በራስ አቅም መስራት ተገቢ በመሆኑ በስራ ሂደታችን የተሰራው ለሌላ
አካል እንደ አርአያ ሊሆን ስለሚችል፣
2. መረጃ ማሰባሰቢያ ዘዴዎች
 የትግበራ ማንዋሉ ላይ በአጭሩ አራት ተግባራት ማለትም፡-
1. ለኢንዱስትሪ መንደር፣ሸድና ለገበያ ማዕከላት መሬት መረከብ
2. የአካባቢ ተስማሚነት ማረጋገጥ፣
3. መሰረተ ልማት ማሟላትና መገንባት፣
4. የለማ መሬት ሸድና የገበያ ማዕከላት ማስተላለፍና ማስተዳደር የሚሉ ተግባራትንና ከምስ/ጎጃም ዞን
አስ/ንግ/ኢን/ገ/መምሪያ የኢን/ መንደርና ገበያ ልማት ዋና የስራ ሂደት በቁጥር 258/ኢ/መ/ገ/01 በቀን
10/09/2008 በተላከልን የሪፖርት ቢጋር መሰረት የጽሁፍ ሰነዶችን መነሻ ተደርጓል፡፡

4.በምርጥ ልምድ ቅመራ የተመረጠው


4.1 ተቋም

 በደ/ማርቆስ ከተማ አስ/ንግድ/ኢን/ገበያ ልማት ጽ/ቤት ውስጥ ከኢንዱስትሪ መንደርና ገበያ መሰረተ ልማት ዋና
የስራ ሂደት፣
4.2 አካባቢ
 በደ/ማርቆስ ከተማ የተቋቋመው ኢንዱስትሪ መንደር ውስጥና ከኢንዱስትሪ መንደር ውጭ ለሚገኙ
ፕሮጀክቶችና የገበያ ማዕከላት አካባቢ ተገቢውን ስራ ለመስራት
4.3 ተባባሪዎች
የኢንዱስትሪ መንደርና ገበያ መሰረተ ልማት ዋና የስራ ሂደት ሰራተኞችና ጠበብ ባለ መድረክ በተዘጋጀው የስራ
ዝርዝር ላይ የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ዋና የስራ ሂደትና የእንስሳትና የእንስሳት ተዋፅኦ ዋና የስራ ሂደት ሰራተኞች
ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡ በመጨረሻም በተቋሙ ማኔጅመንት ኮሚቴ እንዲታይ ተደርጓል፡፡

5. የቅመራው ምንነት
 የበላይ አካልን ሳይጠብቅ ለሰራተኞች የስራ ዝርዝር በማዘጋጀት ወደ ስራ ለማስገባት በመቻሉ ጥሩ ተነሳሽነት
ነው ተብሎ በመታሰቡ፣
6. የተወሰደ የመፍትሄ እርምጃዎች
ከላይ በተ.ቁ 3 የተጠቀሱ ሰነዶችን መነሻ በማድረግና በአለን ጠቅላላ እውቅና መሰረት ለሁሉም የስራ መደቦች
የስራ ዝርዝር በማዘጋጀት፣
 በመጀመሪያ በስራ ሂደት ደረጃ ውይይት ተደርጓል፣
 ሁለተኛ የስራ መደራረብ ይኖራል ተብሎ ከታሰቡ የስራ ሂደቶች ማለትም፡- ከኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ዋና
የሥራ ሂደት እና ከእንስሳትና እንስሳት ተዋፅኦ የስራ ሂደት ጋር ጠበብ በአለ መድረክ ተወያይተን የጋራ
አድርገነዋል፡፡
 ሶስተኛ በንግድ ኢን/ገበያ/ል/ጽ/ቤት ማኔጅመንት ኮሚቴ በማቅረብ እንዲፀድቅ በማድረግ ለእያንዳንዱ ፈፃሚ(
ባለሙያ) ዕቅድ በማቀድ ወደ ስራ ለማስገባት ተችሏል፡፡

ክፍል 2
1. ምርጥ ተሞክሮ የተቀመረባቸው
ተቋማት
 የአብከመ ንግድ ኢን/ገበያ ልማት ቢሮ ኢንዱስትሪ መንደርና ገበያ መሰረተ ልማት ዋና የስራ ሂደት፣

አካባቢ

ባህርዳር
ተባባሪዎች

 የሚመለከታቸው የስራ ሂደት አስተባባሪና ባለሙያዎች፣


2. ከአሁን በፊት የነበሩ ችግሮች
ተቋማት

በኢንዱስትሪ መንደርና ገበያ መሰረተ ልማት ዋና የስራ ሂደት

 የስራ ሂደት አስተባባሪ፣


 የኢንዱስትሪ መንደር መሰረተ ልማት አስተዳደር ባለሙያ፣
 ገበያ መሰረተ ልማት አስተዳደር ባለሙያ፣
 ኢንዱስትሪ መንደር መሰረተ ልማት ግንባታ ክትትል ባለሙያ፣
 የከተማ ፕላን ባለሙያ፣
 የቅየሳ ባለሙያ፣
 የጽህፈትና ቢሮ አስተዳደር ባለሙያ የሥራ መደቦች የስራ ዝርዝር አለመዘጋጀት፣

አካባቢ

 በከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ መንደር ውስጥና ኢንዱስትሪ መንደር ውጭ እንዲሁም ገበያ ማዕከላት አካባቢ
ለሚሰሩ ስራዎች፣

ተባባሪዎች

 የክልሉ ንግድ ኢን/ገበያ/ል ቢሮና ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ፣


3. ከችግሮች ለመውጣት የተደረጉ ትግሎችና የሚወሰዱ ምርጥ አፈፃፀሞች
 ከክልል የስራ ዝርዝር ተዘጋጅ እንዲላክ ስልጠና ላይ በአካልና በተደጋጋሚ በስልክ የሚመለከታቸውን
አካላት ጠይቀናል፡፡
 ከላይ እንደተጠቀሰው በተወሰኑ ሰነዶች መነሻነትና በአለ ጠቅላላ እውቀት የስራ ዝርዝር በማዘጋጀት
ከተለያዩ አካላት ጋር ስምምነት ላይ በመድረስ የ 6 ወር፣የወርና የሳምንት ዕቅድ በመዘጋጀት ስራወችን
ለመስራት ተችሏል፡፡

ለእያንዳንዱ የሥራ መደብ የተዘጋጁ የሥራ ዝርዝሮች

ሀ/ የኢንዱስትሪ መንደር መሰረተ ልማት አስተዳደር ባለሙያ


 የኢንዱስትሪ መረጃ መያዝ/መተንተን፣
 በተሰበሰበው መረጃ መሰረት የድጋፍ ማዕቀፍ ማዘጋጀትና መደገፍ፣
 የስልጠና ፍላጎት መለየትና ስልጠና እንዲሰጥ ማድረግ፣
 የፋይናንስ ችግር ያለባቸው ወደ ማምረት የገቡ ኢንዱስትሪዎች መለየትና ችግራቸው እንዲፈታ
ማድረግ፣
 የኢንዱስትሪና ሌሎች አጋር አካላት የጋራ የውይይት መድረኮች እንዲዘጋጁ ማድረግ፣
 በኢንዱስትሪ መንደር ላይ ያሉ የመሰረተ ልማት ችግሮችን በመለየት እንዲፈቱ ማድረግ፣
 መሬት የተረከቡ ባለሀብቶች ባግባቡ እያለሙ መሆኑን መከታተል በአግባቡ ያላለሙትን እንዲነጠቁ
ማድረግ፣
 ባለሀብቱ የሚያቀርበውን ጥያቄ ለማስተናገድ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል እና ፕላንት ሌይ አዉት በልማት
ቡድን በማስገምገም የመሬት ጥያቄን ማስወሰን፣
 የኢንዱስትሪ ባለሀብቶችን የገበያ ትስስር መፍጠር፣

ለ/ የገበያ ልማት አስተዳደር ባለሙያ


መጋዘን እሚገነባቸው ቦታዎችን መለየትና ከሚመለከታቸው ባለሙያዎች ጋር ግንባታውን
መከታተል፣
 ሁለገብ የገበያ ማዕከላትን እንዲቆቋሙ ማድረግ፣
 የአጠና ገበያ ማዕከላትን ማቋቋም ክትትል ማድረግ፣
 የእንስሳት ገበያ ማዕከላትን እንዲቆቋሙና የማስተዳደር ስራ መስራት፣

ሐ/ የቅየሳ ባለሙያ
 ኢንዱስትሪ መንደር ላይ ያለ የመሰረተ ልማት ችግር መለየት ችግሩን እንዲፈታ ማድረግ፣
 የሰርቨይንግ ዳታ ለቀማ ስራ መስራትና ለዲዛይን ባለሙያው ማስረከብ፣
 ወደ ኢንዱስትሪ መንደር የሚካተትን መሬት ከሶስተኛ ወገን ነፃ ማድረግ፣
 ከሶስተኛ ወገን ነፃ የሆነ መሬትን እንዲሁም በኢንዱስትሪ መንደር የተከለለ መሬትን መለየትና ሳይት
ማዘጋጀት፣
 መሰረተ ልማት ግንባታ የሚካሂድበትን ቦታ ለስራ ተቋራጭ ርክክብ ማድረግ፣

መ/ የግንባታ ክትትል ባለሙያ


 ኢንዱስትሪ መንደር ላይ የገበያ መሰረተ ልማት ዲዛይንና የስራ ዝርዝር ማዘጋጀት፣
 ለመሰረተ ልማት የስራ የጫራታ ሰነድ ማዘጋጀትና ውል መያዝ፣
 የሸድ፣ መጋዝን እና ገበያ ማዕከላት ዲዛይንና ስራ ዝርዝር ማዘጋጀት
 የሚገነባውን ግንባታ መከታተልና የክፍያ ሰርተፊኬት በመመርመርና ክፍያ ለማስፈጸም ርክክብ
መፈጸም፣
ሠ/ የከተማ ፕላን ባለሙያ
 የኢንዱስትሪ መንደር ክላስተር ፕላን ማዘጋጀት፣
 ኢንዱስትሪ መንደር ላይ ለሚገነቡ ሸዶች ከመሬት አጠቃቀም አኳያ ቦታዎችን መለየት፣
 የገበያ ማዕከላት የሚገነቡበት ቦታዎች ከመዋቅራዊ ፕላኑ አኳያ መለየት ለሚመለከተው ባለሙያ
ማስረከብ፣
 ኢንዱስትሪ መንደርና ገበያ አካባቢ ለሚገነቡ ግንባታዎች አርክቲካልቸራል ፕላን ማዘጋጀት፣

ረ/ ጽህፈትና ቢሮ አስተዳደር ባለሙያ

1. የሚቀርቡ ደብዳቤዎችን መፃፍ፣


2. የተለያዩ ደብዳቤዎችን ፋይል ላይ ማስርና ፋይል ላልተከፈተላቸው ፋይል መክፈት፣
3. ሪፖርት መፃፍ፣
4. ከቅርብ ሃላፊ የሚሰጥ ስራ መስራት፣
5. ደብዳቤ ወጭና ገቢ ማድረግ፣
6. ባለጉዳዮችን በአግባቡ ማስተናገድ፣
7. ቁልፍ ተግባራትን በአግባቡ መስራት፣
4. የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች
 ከክልል/ከዞን ሁሉን ነገር አለመጠበቅ
5. ማጠቃለያ
ሌላው ከምርጥ ተሞክሮ ምን ይሰራል፣
1. ግብዓት
2. ይዘት
3. ውጤት አኳያ ስናየው ከላይ በተ.ቁ 3 የተጠቀሱ ሰነዶችን መነሻ በማድረግና በአለን ጠቅላላ እውቅና
መሰረት ለሁሉም የስራ መደቦች የስራ ዝርዝር በማዘጋጀት
 በመጀመሪያ በስራ ሂደት ደረጃ ውይይት ተደርጓል፣
 ሁለተኛ የስራ መደራረብ ይኖራል ተብሎ ከታሰቡ የስራ ሂደቶች ማለትም ከኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ዋና
የሥራ ሂደት በእንስሳትና እንስሳት ተዋፅኦ የስራ ሂደት ጋር ጠበብ በአለ መድረክ ተወያይተን የጋራ አድርገነዋል፡፡
 ሶስተኛ በንግድ ኢን/ገበያ/ል/ጽ/ቤት ማኔጅመንት ኮሚቴ በማቅረብ እንዲፀድቅ በማድረግ ለእያንዳንዱ ፈፃሚ
ባለሙያ ዕቅድ በማቀድ ወደ ስራ ለማስገባት ተችሏል፡፡

You might also like