You are on page 1of 1

ቀን 5/1/2014 ዓ.


ለዋና ዳይሬክተር
ጉዳዩ የደሞዝ ጭማሪን ይመለከታል
እኛ በብክሮቤ ብዝነስ ግሩፕ በድርጅቱ ውስጥ የምንሰራ ሰራተኞች በሙሉ፡-
እንኳን ለአዲሱ አመት ለ 2014 ዓ.ም ከነቤተሰብዎ በሰላም አደረሶት እንላለን፡፡
እንደሚታወቀዉ ከዚህ በፊት ስለደሞዝ ጭማሪ በ 17/06/2013 ዓ.ም መጠየቃችን
ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን ባለው ወቅታዊ ችግር እና በአንዳአንድ ሁኔታዎች ምክንያት
እርስዎም በደብዳቤው መልስ መጪውን ግዜ አብረን እንድንጠብቅ ብለው አባታዊ
ምክርዎን ተቀብለን እስካሁን የኑሮ ውድነቱንና የተለያዩ ችግሮችን ችለንና
ተቋቁመን እዚህ ግዜ ላይ ደርሰናል፡፡ ነገር ግን ይህን አባባል እንደቤተሰብና
እንደመልካም ሠራተኛ እያሰብን እያለን አንድ ላይ ሆነን የበይ ተመልካች ሆነናል፡፡
ምክንያቱም በአንድ እህታማቾች ድርጅት ውስጥ ሁለት አይነት አመራርና አሰራር
በማየታችን በጣም አዝነናል ምክንያቱም በአንድ ባለቤት ስር የሚተዳደሩ
ድርጅቶች ውስጥ ሆነን አንዱን ተጠቃሚ አንዱን ተጎጂ ሆኖ ለብዙ ግዜ ቦነስና
ደሞዝ ጭማሪ ሲሰጥ እኛን ግን የሚያየን አካል ባለመኖሩ እጅግ በጣም አዝነናል፡፡
እርስዎ ስራ ሲያዙን ሳንፈፅም የቀረነው የለም ከታዘዝን ደግሞ በደስታ ነው
የምንሰራው ፋብሪካው ከተጀመረ ጀምሮ አብረን በፍቅር ተጉዘናል ያጠፋነውም
ነገር ካለ በአካል መተው ጥፋታችንን ቢገልጹልን በጣም ደስተኞች ነን፡፡
በስተመጨረሻም የኑሮ ውድነትና የቤት ክራይ ውድነትን ያገናዘበ በቂ የሆነ
የደሞዝ ጭማሪ እንዲደረግልን ስንል በትህትና እንጠይቃለን፡፡ ችግራችን መፍቴ
አግኝቶ አዲሱ ዓመት በሰላም በደስታና በጤና በጥሩ የሥራ መንፈስ እንደምናሳልፍ
ተስፋ እናደርጋለን፡፡
አገራችንን ሰላም ያድርግልን፡፡

You might also like